Wednesday, 5 June 2013
የፍርሃቱ ኢያሪኮ ተደረመሰ
ይኸነው አንተሁነኝ
ሰኔ 5 2013
ሰኔ 5 2013
የሚሆን የማይመስለው ሆነ፤ ልቦች በአንድነት ዘመሩ፤ የደስታ እንባ ፈሰሰ፤ አእዋፍ በደስታ አብረው እስኪቀዝፉ ድረስ የነጻነት ድምጽ የነጻነት ጩኸት አየሩን ሞላው፤ የሕዝብ አሸናፊነት በግልጽ ገኖ ታየ፤ የታፈነው የድምጽ ማእበል ግድቡን ትሶ ወጣ፤ የምን እንደረግ ይሆን ጭንቀት እትትም ተደረመሰ፤ ምድር የጠበበች እስኪመስል ሽዎች በነጻነት ፈሰሱባት፤ በእውነት 1997ን በ2005 አየነው። ገዥዎቻችን የሕዝባችን የአልገዛም ባይነት ወኔ ባልተቋረጠው አፈናቸው ተዳፈነ እንጅ ፈጽሞ እንዳልሞተ በእርግጥ ባይኖቻቸው አዩ። ልዩነትን የሰበኩት ሲሳቀቁ ፀንቶ የነበረው የፍርሃት ግንብ ኢያሪኮ በሰላም በፍቅር በአንድነት መዝሙር ተደረመሰ እሁድ ግንቦት 25 2005 ዓ/ም።
በ1997 ዓ/ም ቅንጅት ካዘጋጀውና እስካሁንም ድረስ ትዝታው ከሕዝብ ህሊና ካልጠፋው ሰላማዊ ሰልፍ ወዲህ የመጀመሪያ የሆነው የግንቦት 25ቱ ሰልፍ መፈቀድን በተመለከተ አንዳንዶች ወያኔ ህዝብን ለመያዝ፣ ከሕዝብ ለመታረቅ ያደረገው ዘዴ ነው ይላሉ። ሲያስረዱም በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሶ የነበረውን የአማሮችን ከቤኒሻንጉል መፈናቀል ቀልብሶ ተፈናቃይ አርሶ አደሮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ መሞከሩ፣ ጥቂት ቢሆኑም በሙስና ተዘፍቀዋል በሚል የራሱን የወያኔን ባለስልጣናት ዘብጥያ ማውረዱን ይጠቅሱና አሁን ደግሞ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እናድርግ ጥያቄ መፍቀዱ ወያኔ አንድም በአባይ ግድብ ምክንያት በተለይ ከግብጽ ጋር የገባበት እሰጥ አገባ ስላሳሰበው ሕዝባችንን ባንድነት ለማቆም ከማሰብ የተደረገ ነው ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ በሰባዊ መብት ረገጣ አይሆኑ እየሆነ ያለው ወያኔ የእርዳታ ሰጭ ሀገሮችንና ድርጅቶችን ቀልብ ለመግዛትና የውጭውን ማሕበረሰብ አይን ለመሳብ ያደረገው ነው በማለት የተቻሉ። ተችዎች ይህን ይበሉ እንጅ ከሰልፉ ትቂት ቀናት ቀደም ብሎና ከሰልፉም በሗላ በወያኔ መንደር እየሆነ የነበረውና ያለው ግን ይህን አያረጋግጥም ነበር።
ጠቅለል ባለ መልኩ የሰሞኑን ሰልፍ በተመለከተ ወያኔ ውጥረት ውስጥ ገብቶ በዚህ የተነሳም ፈቅዶ ሊሆን ይችላል፤ ካለፉት ዓመታት ልምዳችን ስንነሳ ግን ወያኔ ሕዝብ የወደደውን አያደርግም። ሕዝብ የፈለገውንም አይሰጥም። እራሱ የመረጠውን በራሱ ጊዜና እቅድ መከወን ነው የሚያስደስተው። ከዚህ በፊት ብዙዎች ስለሕዝባችን ብዙ ነገር ብለው ጽፈውም ነበር የወያኔ ፍላጎትና ምርጫ ስላልነበረ ግን መጨረሻቸው ቃሊቲ ነው የሆነው። ከሰልፉ በሗላ ከወያኔ የተሰጠው መግለጫ አይሉት ማስጠንቀቂያም የሚያመለክተው እኛ ባልፈለግነው መልኩ የሚደረግ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ ”የሕዝብ ጥያቄም እንኳ ቢሆን” ዋጋ ያስከፍላል አይነት ነበር።
ወያኔ ሕወሃት የሚፈልገው በራሱ አፈ ቀላጤዎች አማካኝነት ሁሌ እንደሚነግረንም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሁና እንድትቀጥል፣ ሕዝባችንም በሀይማኖት፣ በቋንቋና በብሔረስብ ሳይከፋፈል እንዲኖር የኔ መኖርና መግዛት ጥያቄ ውስጥ መግባት የለበትም፣ ያልኩትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈጸም አለበት ነው። አለበለዚያ ግን ኢትዮጵያ አትኖርም ሕዝቡም ይበጣበጣል ነው።
ይሁን እንጅ ወያኔ እንደሚያወራው ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለይም ባሳለፍናቸው ሶስትና አራት ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ ያሳዩት ነገር ቢኖር ልክ እንደከዚህ ቀደሙ የተጠናከረ አንድነታቸውን ነበር። በሃይማኖት መቻቻልን መዋደድንና መፋቀርን የተለያዩ እምነት ተከታዮች ባንድ ጣራ ስር ከመኖር አንስቶ ባንድ ላይ በራሳቸው መንገድ መጸለይን፣ ላንደኛው ችግርና ዓላማ ተረዳድቶ አብሮ መቆምን በማሳየት መለያየትን መጠፋፋትን ሳይሆን አንድነትንና ወገንተኛነትን በጉልህ ለዓለም አሳይተዋል። ለወያኔ እኔ አውቅላችሗለሁ ደካማ ፖለቲካ አይበገሬነታቸውን በማሳየት የወያኔ አካሄድ ያንድነትና የጥንካሬ መንገድ ሳይሆን የመለያየትና የውድቀት መሆኑን በተግባር በደማቁ አስምረው አስመስክረዋል።
አንዳንዴ ታዲያ ከእንደዚህ ያለው አብሮ የመቆም፣ የመደጋገፍና የመረዳዳት ጠንካራ ባሕላችን በተጻራሪ የቆመው ወያኔ ከኔ መኖርና ይሁንታ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አገር ያጠፋሉ ለማለት ሲዳዳው ምን ማለቱ ነው? የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት እየተጠናከረ ከመጣ ለአገዛዜ ስለሚያሰጋኝና ከኔ ውጭም ሌላ እንዲገዛ ስለማልፈቅድ በራሴ መንገድ ሀገሪቱን እበታትናታለሁ ነው? ወይስ ጦርነትን መስራት እንችላለን ብለው እንደሚፎከሩት ሀገር ለመገጣጠምም ሆነ ለማፈራረስ አቅሙ አለን ለማለት ነው? የስነ አእምሮ ጠበብት ስቶክሆልም ሲንድረም ብለው እንደሚጠሩት ሕዝባችን በሙሉ ወያኔ ከሌለ እኛም ሀገራችንም አትኖርም ብሎ እንዲያስብ የሚደረግ ጫና ነው? ወይስ ሕወሃት ከምስረታው ጀምሮ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝለትን ሀገራችንን የመበታተን ተግባሩን በገደምዳሜ እየነገረን ነው?
ወያኔ ያሻውን ቢልም የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን አጠናክሮ ሕወሃትን ማርበድበዱን ቀጥሏል። ወያኔ የአንድነትን አስፈሪነትና ሃያልነት ከ1997 ዓ/ም ወዲህ እሁድ ግንቦት 25 ባደባባይ ባይኑ በብረቱ ተመልክቷል። እስከዛሬ ላሳለፋቸው የአገዛዝ ዘመኑም ከኔ ሙሉ ይሁንታ ውጭ የሚደረጉ መተባበሮች፣ ስብሰባዎች፣ ሰልፎች ሁሉ ለሀገር አንድነት አደገኞች ናቸው ፐሮፓጋንዳ በእርግጥም ፕሮፓጋንዳ ብቻ መሆኑን ሁላችንም በተግባር አይተናል።
ወያኔ እንዲያስታውሰው የሚያስፈልገው የቀድሞውን የወያኔ ቁንጮ ጨምሮ በዓለማችን የታወቁ ብዙ አምባገነን አገዛዞችና መሪዎች የተናገሩትንና ለማድረግ ያሰቡትን እኩይ ዓላማ ሳያደርጉና ሳያዩ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ወዲያኛው ማለፋቸውን ሲሆን፤ ሕዝቡ ግን ከፍርሃት ቆፈን ወጥቶ በበለጠ ተጠናክሮ ተፋቅሮና ተቻችሎ በአንድነት ጎዳና የነጻነት መዝሙር እየዘመረ መቀጠሉን አሰረግጦ እያሳየ መሆኑን ጭምር ነው።
ሰበር ዜና – ኢትዮጵያ ለግብፅ ምላሽ ሰጠች- ”ግብፅ የቀን ሕልም ላይ ነች” አቶ ጌታቸው ረዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ
ሰበር ዜና
ኢትዮጵያ ለግብፅ ምላሽ ሰጠች- ”ግብፅ የቀን ሕልም ላይ ነች” አቶ ጌታቸው ረዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ
”አህራም ኦን ላይን” የተሰኘው የግብፅ ድህረ ገፅ ጋዜጣ በዛሬው ግንቦት 28፣2005 ዓም ባወጣው ዘገባ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ብዙ ያልተሳካ ሙከራ ማድረጓን መግለፃቸውን እና አሁን ”በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ማድረግ እና ሴራ ማድረግ” የሚሉ አስተያየቶች ጊዜ ያለፈባቸው የከሸፉ ሃሳቦች ”old failed concept.” እና የቀን ሕልም ”day dreaming.” ከመሆን ያልዘለለ መሆኑን አክለው መናገራቸውን ዘግ ቧል።
የጋዜጣውን አጭር ዜና ከእዚህ በታች በጉዳያችን ጡመራ ላይ ያንብቡ።
A spokesman for Ethiopia’s prime minister is downplaying suggestions by Egyptian politicians that Egypt should sabotage Ethiopia’s new Nile River dam.
Political leaders in Egypt on Monday proposed carrying out hostile acts against Ethiopia. Egypt, which is dependent on the Nile, fears a diminished flow.
Getachew Reda, a spokesman for Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, said late Tuesday that Egyptian leaders in the past have unsuccessfully tried to destabilize Ethiopia. He called the suggestions of attack or sabotage an “old failed concept.” He also labeled it “day dreaming.”
Ethiopia last week ago began diverting the flow of the Nile toward its $4.2 billionhydroelectric plant that has been dubbed the Grand Ethiopian Renaissance Dam. The project, currently about 20 percent complete, has raised concerns in Nile-dependent Egypt
Tuesday, 4 June 2013
ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሉግዲና በበረከት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።
በግንቦት 25-2005 ዓ.ም በቀጠለው ውጊያ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት በተሰኘ ስፍራ ከአምባገነኑ አገዛዝ 35ኛ ክፍለጦር እና ከሚሊሻ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ በተከታታይ በስምንት/8/ ዙር ፋታ የለሽና እልህ አስጨራሽ ውጊያ 148 ሙት፣ 374 ቁስለኛ፣ 31 ክላሽንኮፍ፣ጠመንጃ 47 የእጅ ቦንብ ፣2 ስናይፐር፣ 3 መትረየስና የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች ማርኳል።
በእለቱ በተካሄደው ውጊያ የአካባቢው ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ባሳየው ከፍተኛ ወታደራዊ ጀብድ መደነቃቸውንና ድርጅቱ ያለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ብቃት ያሳየ መሆኑን ገልፀው ፣ ወጣቶችም በዚህ ሃይል ጠላት ማሽመድመድ የሚችል ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል ሲሉ ተናግረዋል።
ለስምንት ዙር ያህል በተካሄደው ውጊያ የአገዛዙ ቅጥረኛ ጦር ቁስለኞች ወደ ዳንሻ፣ ማይካድራ፣ ሁመራ የመሳሰሉት ቦታዎች በሚገኙ የጠላት የሕክምና ተቋማት ቁስለኞችን እየጫኑ ማጓጓዝ ላይ ተጠምደው እንደዋሉና ገሚሶቹ ከፉኛ በመቁሰላቸው ሕክምና እርዳታ ሳይጀመርላቸው መሞታቸው ታውቋል።
ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በደረሰበት ድንገተኛ ጥቃት አከርካሪው የተሰበረው 35ኛ ክፍለ ጦር በድንጋጤና ፍርሃት ውስጥ ተሸብቦ በመጨነቅ ላይ በመሆናቸው የአካባቢውን ማህበረሰብ ያለስራው እየተንገላታ እንደሚገኝ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አሁንም ቢሆን ወያኔው ለሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ ባለመስጠት አቋሙ የሚቀጥል ከሆነና ስለ አባይ ግድብ እያወሩ ሕዝብን ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ መግዛቴን እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት እንዲሁም በሉግዲ በ35ኛ ክፍለ ጦርና በሚሊሻ ላይ የተወሰደው አኩሪ ወታደራዊ እርምጃ አይነቱን ቀይሮና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል።
በግንቦት 24 እና 25-2005 ዓ.ም በተካሄደው ውጊያ በድምሩ 192 ሙት 440 ቁስለኛ ቁጥራቸው የበዛ ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነትጥቃቸው በመማረክ የታሪኩ አካል የሆኑ ተዋጊ አርበኞች እንዳሉት እኛ ለሀገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ፊት ለፊት በጠመንጃ አረር እየተፋለሙ እንደሚገኙና ትግሉ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚደረግ እንደመሆኑ መጠን የሁሉም ርብርብና ተሳትፎ አስፈላጊና የውዴታ ግዴታ በመሆኑ የአገራችን ችግር መፍትሔ ለመስጠት በአምባገነኑ የወንበዴ ቡድን በሆነው ወያኔ ላይ እንዝመት ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።http://www.arbegnochginbar.org/
የግብጽ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ላይ ሲመክሩ የሚያሳይ ቪዲዮ የፋ ወጣ
ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የግብጹ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን በመሰብሰብ በመሰራት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ወይይቱ ለተቃዋሚዎች ሳይነገር በቀጥታ በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ በመደረጉ ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን ሲገልጹ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ደግሞ ይቅርታ ጠይቋል።
አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበው በውይይቱ ላይ የተለያዩ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች አስገራሚ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንት ሙርሲ በቅርቡ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የተቋቋመው የሶስትዮሽ የጥናት ቡድን ያወጣውን ሪፖርት መደምደሚያ ለፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ካቀረቡ በሁዋላ ፣ መሪዎቹ የፖለቲካ ልዩነታቸውን ትተው በአንድነት እንዲሰለፉ ጠይቀዋል።
ፖለቲከኞችም ውይይቱ በቀጥታ በቴሌቪዥን እንደሚቀረጽ ሳያውቁ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
አይማር ኑር የተባሉት የሊበራል ጋሀድ ፓርቲ መሪ ” ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የጦር ጄቶችን ገዝታለች የሚል ወሬ መንዛት” እንዲሁም ” ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የስለላ እና የወታደራዊ ቡድን በማዋቀር እና ወደ አዲስ አበባ በመላክ በውስጥ ፖለቲካቸው ውስጥ ጣልቃ መግባት” ያስፈልጋል የሚል ሀሳብ ሰንዝረዋል።
የእስላሚክ ኮንሰርቫቲቭ ኑር ፓርቲ መሪ የሆኑት ዩኒስ ማክዩን በበኩላቸው ” ግድቡ ለግብጽ ስትራቴጂክ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ፣ ካይሮ የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች መደገፍ አለባት ብለዋል። ” ኢትዮጵያ የተዳከመች አገር ናት፣ ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መደራደሪያ እናደርገዋለን ያሉ ሲሆን፣ ይህ ሁሉ ካልተሳካ ግን የደህንነት ሰዎቻችንን በማሰማራት ግድቡን ማውደም አለብን” በማለት አክለዋል።
አይማን ሩር የተባሉት ፖሊቲከኛ ደግሞ ” ግብጽ በአይር ላይ ነዳጅ የሚቀዱ ተዋጊ ጀቶች እንደገዛች የሚያሳይ ወሬ በመንዛት የዲፕሎማሲ ድል ልታገኝ ትችላለች ” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
የግብጽ የመገናኛ ብዙሀን በቀጥታ የተላላፈው ስርጭት በእጅጉ አበሳጭቷቸዋል። አንዲት ጋዜጠኛ “በአባይ ጉዳይ ግልጽነት ይኑር ብለን ስንጠይቅ የአለም መሳቂያ እስክንሆን ድረስ ገመናችን ይውጣ ማለታችን አልነበረም” ብላለች።
የሙርሲ መንግስት የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ይቅርታ ጠይቀዋል። ውይይቱ በቀጥታ በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ የተወሰነው በመጨረሻ ሰአት ላይ በመሆኑ ለተወያዮቹ አልነገርናቸውም ነበር ብለዋል።
Sunday, 2 June 2013
ሰላማዊ ሰልፉን በርካቶች እየተቀላቀሉት ጉዞው ቀጥሏል፡፡
መንግስታችን ይህንን ሰልፍ ዕውቅና የሰጠው ሰማያዊዎቹ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ እንደዛቱት ያደርጉትና አልተኩስ ነገር እንግዳ አለ አላስር ነገር ስንቱን አስሬ ብሎ ሰግቶ መሆኑ ይጠረጠራል፡፡
የሆነ ሆኖ ዛሬ በመንግስት ዕውቅና ያገኘ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡ ከቀበና አራትኪሎ ከአራት ኪሎ ደግሞ ፒያሳ የተሰላፊው ቁጥር እየጨመረ ወደ ኩባ አደባባይ እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡
አንድ ወዳጄ እንዳወጋኝ መንግስት እስከዛሬ ድረስ በሚያደርጋቸው ሰልፎች ላይ ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት አስወጥቶ ወደ ሰልፉ ያሰማራቸው ነበር፡፡ እንዳይቀሩም የስም ጥሪ እና ቁጥጥር ይደረጋል የቀረ ተማሪም ማርክ ይቀነስበታል፡፡
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ
ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በተለምዶ “ሜካፕ ክላስ” እንደሚባለው በሰንበቱ ለትምህርት ጠርተዋቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ እንዳይቀሩም ሃምሳ ማርክ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸዋል፡፡
አንድ ጊዜ መንግስት የሆነ ሰልፍ ጠርቶ እኔም ስታድየም ተገኝቼ ነበር፡፡ በሰልፉ ላይ አንዲት ሴትዮን እናቴ የዚህ ሰልፍ አላማ ምንድነው ስላቸው… እንጃ ልጄ አበሏ ትጠቅመኛለች ብዬ ነው የወጣሁት ስምጥሪው አንዴ ቢየኝ ወደቤቴ እመለስ ነበር ብለውኛል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ አበልም የለም ማርክም የለም፡፡ ሰዉ ግን አሁንም እየጎረፈ ነው፡፡
በዚህ ሰልፍ ላይ ጎልቶ ከወጣው ዜማ መካከል ሙስሊሙ ህብረተሰብ እና ሌላው በአንድ ድምፅ “አንለያይም አንለያይም… መቼም አንለያይም አንለያይም!” እያሉ ያዜሙበት ይገኛል፡፡
እደግመዋለሁ፤ “በሰላም ወጥታችሁ በደህና እንድትገቡ ይመኝላችኋል መላ ህብረተሰቡ”
Subscribe to:
Posts (Atom)