Wednesday, 12 June 2013

አዲስ አበባ ረክሳለች! ለጋ ህጻናትን ለባለስልጣናትና ባለሃብቶች ማቅረብ “ትርፋማ” ሆኗል



kids for sale


ትውልድ አምካኝ ቤቶችን፣ ትውልድ አምካኝ ደላሎችን፣ በህጻናት የወሲብ ንግድ ገንዘብ የሚሰበስቡትን፣ ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪዎቹ፣ ህግ አወጪዎቹና ዋናዎቹ “የአገሪቱ ህዳሴ ባለቤቶች” የሚባሉት በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶች በሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንና ሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደሙባቸዋል።
ሃኪሞች፣ የህግ ባለሙያዎች፣ አገር የሚመሩት፣ ህግ የሚያስከብሩት፣ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ አውራ ባለስልጣናት፣ ህዝብ ፊት ቀርበው በልማት ስም የሚምሉት ሃብታም ተብዬዎች፣ የፖሊስ የበላይ አመራሮች፣ የስለላ አውራ ሰዎች፣ አጫፋሪዎች፣ የአቻ ፓርቲ አመራሮችና መካከል ጥቂት የማይባሉ ከዳር እስከዳር መመሸጊያቸው ዝግ ቤቶች ናቸው። አንዳንዴም ከዝግ ቤቶች ፍራሽ ላይ ሆነው የፖለቲካ መመሪያ የሚሰጥበት አጋጣሚ አለ። ይህን አስደንጋጭ እውነት “መርከስ” ነው። አዲስ አበባ ይፋ አደረገችው እንጂ በየክልሉ ከተሞች የሚደረገው ተመሳሳይ ነው።
የሺሻና የጫት በጀት የሚመድቡ ባለስልጣናት አሉ። አስቤዛ ሲደረግ “ሙአሰል” ከህጻናት ዳይፐርና የዱቄት ወተት እኩል የሚመድቡ አሉ። ህጻናትን በመመልመል ሳውና በማስገባት፣ በማሰልጠን፣ ዘመናዊ ልብስ በማልበስ ለገበያ የሚያቀርቡ ብዙ ናቸው። እገሌ ለሚባል አየር መንገድ አስተናጋጅ እንቀጥራለን በሚል ታዳጊዎችን እያንጋጉ በወሲብ የሚነዱና የሚያነዱ ይህን ተግባራቸውን የሚፈጽሙት ማስታወቂያ እያስነገሩ ነው።

ግብረሰዶም የሚያስፋፉ በየሆቴሉ ድሆችን በማደን ማበላሸት ከጀመሩ ቆይተዋል። አሁን አሁን በየጎዳናው ታዳጊዎችን በማታለል ህሊና የሚያስት ኬሚካልና እጽ በመጠቀም ህሊናቸውንና አካላቸውን መስበር ተለምዷል። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው በዚህ የግብረሰዶም ወረራ ውስጥ ተጠቃሚ በመሆን ወንድሞቻቸውን የሚደልሉ መበራከታቸው ነው።
ህጻናትን ለወሲብ የሚያቀርቡ ነፍሰ በላዎች ኢኮኖሚያቸው አድጎ ባለ ዘመናዊ መኪናና ህንጻ መሆናቸው ነው። አዲስ አበባ ባሉ ዝግ ቤቶች ወሲብንና ግብረ ሰዶምን የሚያሻቅጡ ህሊና ቢሶች ጉዳይ ያሳሰበው ቀጭኑ ዘ-ቄራ የሚባለው የአዲስ አበባው አምደኛችን ከወራት በፊት “የሚዘጋባቸው ህጻናት” በሚል ርዕስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ጠቁሞ ነበር። (ዕድሜ ለኢንሳና አፈናው ብዕሩ ማዕቀብ ተደርጎበት በተከታታይ ጽሁፎችን ሳያስነብብ ቢቆይም እንዲሁ እንደጠፋ ግን አይቀርም፡፡)
የከበረውን ትዳራቸውንና ያብራካቸውን ፍሬዎች ቤት ጥለው፤ ባይወልዷቸውም ልጆቻቸው ከሚሆኑት ጋር የሚዳሩትና፣ የውሽሞች ቀን እያከበሩ አረቄ የሚራጩት ሃብታሞች ጠለቅ ያለ ምርመራ ቢደረግባቸው እስከ ዱባይ የዘለቀው የግፍ ገመናቸው ይገለጥ ነበር። ዳሩ የወንጀሉ ዋና ተባባሪዎች ተቆጣጣሪዎቹና ህግ አስከባሪዎቹ በመሆናቸው አስቀድሞ እንደተባለው አይታሰብም።
አዲስ አበባ መርከሷን ጥር 11 ቀን 2013 በአዲስ አበባ አስተዳደር ይፋ የተደረገው ጥናት፤ የቀንና የማታ ጭፈራ ቤቶችን፣ የእርቃን ዳንስ ቤቶችን፣ የማሳጅ፣ የቪዲዮ፣ የአደንዛዥ ዕጽ መጠቀሚያ፣ የግብረሰዶማውያን ማዘውተሪያ ቤቶችንና የመኪና ላይ ወሲብ መፈፀሚያና ጫት መቃሚያ ቦታዎችን በሚገባ በመቃኘት ተሰብስቦ በተሰራው ጥናት መረጋገጡን መረጃውን ይፋ ባደረገው አዲስ አድማስ ጋዜጣ በኩል ሰምተናል። ዘገባው ትኩረት የሚያሻውና በሚሊዮን በሚቆጠሩት ታዳጊዎች ህይወት ላይ ያነጣጠረ ስለሆነ እንዳለ አትመነዋል።

ግብረሰዶም ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋ ነው፣ አብዛኞቹ የከተማዋ ማሳጅ ቤቶች የወሲብ ንግድ እንደሚያጧጡፉ ታውቋል፣ ከ3600 በላይ ህገወጥ ልማዶችና የወሲብ ድርጊቶች የሚፈፀምባቸው ቤቶች አሉ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ፖሊሶችና ነጋዴዎች የአነቃቂ እፆች ተጠቃሚ ናቸው፣ በእርቃን ጭፈራ ቤቶች ደጃፍ ከሚቆሙ መኪኖች አብዛኛዎቹ የመንግስትና የንግድ ታርጋ የለጠፉ ናቸው፡፡
በአዲስ አበባ ህገወጥ ተግባራት የሚከናወኑባቸው ቤቶች በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ መምጣታቸውንና ከተማዋ አደጋ ላይ እንደሆነች ሰሞኑን ይፋ የተደረገ ጥናት አረጋገጠ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት ይፋ የተደረገው ጥናት “መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም በወጣቶችና ሴቶች ላይ እያስከተሉት ያለው አሉታዊ ተጽእኖ” በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን ከ3600 በላይ ህገወጥ የወሲብ ድርጊት የሚፈፀምባቸው ቤቶች እንዳሉ ጠቁሟል፡፡
ወደ 3 ሚሊዮን ከሚጠጋው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ውስጥ 52.4 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ወጣቶች እንደሆኑ ያመለከተው ጥናቱ፣ አብዛኞቹ ሴቶችና ወጣቶች ላልተገቡ መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች እየተጋለጡ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡ የከተማዋ ሴቶችና ወጣቶች ለሱስ አስያዥ እፆችና ለአልኮል መጠጦች እንዲሁም ለመጤ ባህል ወረርሽኞች ተጋላጭ ሆነዋልም ብሏል፡፡
ለዚህ እንደዋና ምክንያትነት የቀረበው በከተማዋ የቀንና የሌሊት ጭፈራ ቤቶች፣ የራቁት ዳንስ ቤቶች፣ የግብረሰዶም ወሲብ መፈፀሚያ ቦታዎች፣ የሺሻና የጫት ቤቶች፣ የቁማር ቤትና ህገወጥ የቪዲዮ ቤቶች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እያደገ መምጣቱ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
(ምስል: አዲስ አድማስ)
በአሥሩም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የፖሊስ መምሪያዎች የተሰበሰበ መረጃ እንዳመለከተው፣ 3691 ቤቶች ለእነዚሁ ተግባራት ተከፍተው በከተማዋ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
በእነዚህ ቤቶች መበራከትና በስፋት መሰራጨት ሳቢያም በርካታ ወጣቶች ለወንጀል ተግባራት፣ ለአደገኛ እፆች ሱሰኝነት፣ ለዝርፊያ፣ ለስደት ለጐዳና ተዳዳሪነት፣ ለኤችአይቪና ተያያዥ በሽታዎች እንዲሁም ላልተፈለገ እርግዝና ተዳርገዋል፡፡
ትናንት ይፋ የተደረገው ጥናት፤ የቀንና የማታ ጭፈራ ቤቶችን፣ የእርቃን ዳንስ ቤቶችን፣ የማሳጅ፣ የቪዲዮ፣ የአደንዛዥ ዕጽ መጠቀሚያ፣ የግብረሰዶማውያን ማዘውተሪያ ቤቶችንና የመኪና ላይ ወሲብ መፈፀሚያና ጫት መቃሚያ ቦታዎችን በሚገባ በመቃኘት በተሰበሰበ መረጃ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የጥናቱ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የተመሳሳይ ፆታ የወሲብ ግንኙነት ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ ከሚገምተውና ከሚያስበው እጅግ በበለጠ መልኩ ተስፋፍቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ድርጊቱ እየተስፋፋ በማህበረሰቡ ላይ የስነልቡና፣ የማህበራዊ ግንኙነት፣ የትምህርት ማቋረጥና፣ የጤና ችግር እያስከተለ ነው ተብሏል፡፡
ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት፣ የ2ኛ ደረጃና የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች፣ በወሲብ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች፣ እንዲሁም በማረሚያ ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች የችግሩ ከፍተኛ ተጠቂዎች እንደሆኑ ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ከተመሳሳይ ፆታ ጋር በመሄድ በወሲብ ንግድ ሥራ የሚተዳደሩ ሰዎች ቁጥርም እየተበራከተ መሆኑንና ድርጊቱ በሚያስደነግጥ ፍጥነት እየተስፋፋ እንደሆነ ታውቋል፡፡
አዲስ አበባ የጭፈራ ቤቶችና የራቁት ዳንስ ቤቶች ከቀን ወደቀን እየጨመረ የሚሄድባት ከተማ መሆኗን የጠቆመው ጥናቱ፤ በተለይ ከማህበረሰቡ ወግና የአኗኗር ዘይቤ የወጡ፣ ግለሰባዊ ክብርን የሚፈታተኑ፤ የኢትዮጵያዊነት እሴቶችን የሚያጠፉ የእርቃን ጭፈራ ቤቶች እየተስፋፉ መምጣታቸውን አመልክቷል፡፡
በእነዚህ የእርቃን ዳንስ ቤቶች በራፍ ላይ ከሚቆሙ መኪናዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ የመንግስት ታርጋ የለጠፉ መሆናቸውን ይፋ ያደረገው ጥናቱ፤ የግልና የንግድ ታርጋዎችን የለጠፉ መኪኖች በብዛት እንደሚታዩና የተወሰኑ የዲፕሎማትና የእርዳታ ድርጅቶች መኪኖችም እንደሚገኙበት ጠቁሟል፡፡
ከእርቃን ዳንስ ቤቶች ጠባቂዎችና ከእርቃን ደናሾቹ ጋር በተደረገ ኢ-መደባዊ ውይይት በቦታው መጥተው የሚገለገሉም ሆነ በየቤታቸው በግል በማስጠራት አገልግሎት ከሚያገኙት ደንበኞች መካከል የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የመንግስት ሠራተኞች፣ የውጭ ዲፕሎማቶችና በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች እንደሚገኙበት የጥናቱ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡
የእርቃን ደናሾቹ ወርሃዊ ገቢ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ሳይጨምር ከ3ሺ-14ሺ ብር እንደሚደርስ የሚጠቁመው ጥናቱ፤ ለዚህ ሥራ የሚመለመሉት ወጣት ሴቶች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅ ያለ፤ መልካም የሰውነት አቋም ያላቸው፤ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ከሞዴሊንግ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚመረቁ ወጣቶች እንደሆኑም ያመለክታል፡፡
በአሁኑ ወቅት ወሲብና ወሲብ ነክ ጉዳዮች የሚፈፀሙባቸው ማሳጅ (መታሻ) ቤቶችን መጠቀም እየተለመደ መምጣቱን ይፋ ያደረገው መረጃው፤ ከመታሻ ቤቶቹ አብዛኛዎቹ ደረጃቸውን በጠበቁ ትላልቅ የመኖሪያ ቤቶችና በትላልቅ የንግድ ህንፃዎች ላይ እንደሚገኙና የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ እንደሆኑ ጠቁሟል፡፡ በእነዚህ ቤቶች በሚሰጠው የመታሸት አገልግሎት ሥር በተለየ ሁኔታ ለምርጫ የሚቀርቡት ድርጊቶች ህብረተሰቡን ከባህልና ሥነምግባር ውጪ ለሆነ ባህርያት እየዳረጉት እንደሆነና የማሳጅ አገልግሎት መስጫ ቤቶቹም ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ መሄዱ በጥናቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡
የጥናቱ አዲስ ግኝት ሆኖ የተገለፀው ሌላው ጉዳይ በመኪና ውስጥ የሚፈፀሙ ጫት የመቃምና የወሲብ ድርጊቶች መስፋፋት ነው፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በቦሌ በሚገኙ ትላልቅ ህንፃዎች፣ ባሮችና ሬስቶራንቶች ሥር፣ በመንገዶች ግራና ቀኝ እንዲሁም በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ላይ በመኪና ውስጥ በተናጥል እና በጥንድ በመሆን ጫት መቃም፣ ወሲብ መፈፀምና ሌሎች ያልተገቡ ተግባራትን መከወን በስፋት እየታየ መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡
ይሄም ተግባር ከተማዋን እጅግ አደገኛ ወደሆነ አደጋ ውስጥ እየከተታት እንደሆነ የጠቆመው ጥናቱ፤ በአገሪቱ የሬዲዮ ፕሮግራሞች በቀጥታ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ለእንዲህ ያሉት ድርጊቶች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ገልጿል፡፡
በሬዲዮ የሚቀርቡና በወሲብ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የቀጥታ ውይይት ስርጭቶች ከአስተማሪነታቸው ይልቅ ወጣቶችንና ህፃናትን ለወሲብ ተግባር የሚገፋፉና ያዳመጡትን በተግባር ላይ ለማዋል ከቤት ወይም ከጐረቤት ጀምረው ወደሴተኛ አዳሪዎች እስከመሄድ እያደረሳቸው እንደሆነ የጥናቱ ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡
ሱስ አስያዥ እፆችን መጠቀም፣ ሀሺሽ፣ ሺሻ፣ ሄሮይን እና የአልኮል መጠጦች ለዚህ ተግባር ሰፊ ድርሻ እንዳላቸው የጠቆመው መረጃው፤ ዕድሜያቸው ከ25-30 አልፎ አልፎም በአስራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህፃናት የማሪዋና ወይንም የካናቢስ ተጠቃሚዎች እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጿል፡፡
በመረጃው መሠረት፤ በተለያየ የመንግስት ኃላፊነት ላይ የሚገኙ ግለሰቦች፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ማህበራዊ ደረጃ የሚሰጣቸው ግለሰቦችና በኢኮኖሚው ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ ባለሙያዎችና የንግድ ሰዎች በዚህ መጤና ያልተገባ ልማድ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቂ ሆነዋል፡፡
የእነዚህ ግለሰቦች በዚህ ያልተገባ ተግባር መጠመድ አርአያ ሊሆኑለት ለሚገባው ህብረተሰብ የሚያስተላልፈው አፍራሽ መልዕክት ከፍተኛ ነው ያለው ጥናቱ፤ በአገሪቱ እድገትና የልማት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ የዝቅጠት አደጋ እያደረሰ መሆኑን አመልክቷል፡፡
ለህገወጥ ተግባራቱ መስፋፋት በአገሪቱ ያለው ህግ እርስ በርሱ የሚጣረስ መሆኑን ጥናቱ እንደምክንያት አቅርቧል፡፡ “መንግስት በአንድ በኩል ለቪዲዮ ቤቶች ፍቃድ ይሰጣል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጐጂነቱን ያወራል፤ በየጊዜው ሺሻ ቤቶችን የማጥፋት ዘመቻ ያካሂዳል፣ ሺሻ ማጨሻውን እየሰበሰበ ያቃጥላል፤ ነገር ግን ይህንን ሥራ የሚከለክልና የሚቀጣ ህግ ስለሌለ ዕቃውን መልሰው በመግዛት ሥራውን ይጀምራሉ፡፡” ያለው የጥናቱ ሪፖርት፤ ከዚህ በተጨማሪም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ባገኙበት የሥራ ዘርፍ ስለመሰማራታቸው የሚከታተልና ከመስመር ሲወጡም የሚቀጣ የህግ አግባብ አለመኖሩ ለህገወጥ ተግባራቱ መስፋፋት ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡

Sunday, 9 June 2013

ግብፅ በቅድመ ሁኔታ የታጠረ የድርድር ጥያቄ አቀረበች -ኢትዮጵያ ቅድመ ሁኔታውን አልተቀበለችም


ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለመጀመር የዓባይን ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ በጊዜያዊነት ከቀየረች በኋላ፣ ግብፅ የፈጠረችው ፖለቲካዊ ውጥረት ባለፈው ሳምንት የተለየ መልክ ይዟል፡፡
ሱዳን በግድቡ ላይ ተቃውሞ እንደሌላት በመግለጽ ግብፅን ብቸኛዋ ተቃዋሚ አገር እንድትሆን አድርጋታለች፡፡ በሌላ በኩል ግብፅ በጉዳዩ ላይ የተለሳለሰ የሚመስል አቋም በማሳየት በቅድመ ሁኔታ የታጠረ የድርድር ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቅርባለች፡፡ መንግሥት በበኩሉ የግብፅ ጥያቄ በሳይንስ ላይ ያልተመረኮዘና ግልጽነት የሚጎድለው ነው ብሏል፡፡ የግድቡ ግንባታ እንዲቋረጥ የቀረበው ሐሳብም ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ሲል ቁርጥ ያለ አቋሙን ገልጾ፣ በእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥም ድርድር እንደማይኖር አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓባይን የፍሰት አቅጣጫ ከቀየረች በኋላ የግብፅ መንግሥት ከፍተኛ ተቃውሞውን እያሰማ ሰንብቷል፡፡ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በጋራ ያቋቋሙት የባለሙያዎች ቡድን በግድቡ ተፅዕኖ ላይ ያቀረበውንም ሪፖርት እንደማትቀበል ግብፅ አሳውቃለች፡፡ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የጀመረችው የኃይል ማመንጫ ግድብ ግብፅና ሱዳን በቅኝ ግዛት ዘመን ውል መሠረት የሚያገኙትን የውኃ ኮታ የሚቀንስ በመሆኑ፣ የግብፅን ህልውና አደጋ ላይ ይጥላል የሚለው የግብፅ ዋነኛ መከራከሪያ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የግብፅ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ከአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት ማድረጋቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ከተወያዮቹ ዕውቅና ውጭ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት በተላለፈው በዚህ ውይይት ላይ፣ አክራሪ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት መክፈት እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱን ሲመክሩ ታይተዋል፡፡ በዚሁ ውይይት ላይ የተሳተፉትና የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎችን በመደገፍ አገሪቱን ማተራመስ ወይም በግብፅ የደኅንነት ኃይል ግድቡ እንዲወድም መደረግ አለበት የሚል ምክራቸውን ሲሰጡ የነበሩት አይማን ኑር የተባሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር፣ በሱዳን ላይም ትችታቸውን ሰንዝረው ነበር፡፡
በዓባይ ውኃ ፖለቲካ ዙሪያ ከግብፅ በተለየ ሁኔታ ዝምታን እየመረጠች ያለችው የሱዳን አቋም የሚያበሳጭ ነው ነበር ያሉት አይማን ኑር፡፡
የግለሰቡ ንግግር ያበሳጫት ሱዳን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የመንግሥት ቃል አቀባይ በሆኑት ሚስተር አህመድ ቢላል ኦስማን በኩል ምላሽ ሰጥታለች፡፡ በሱዳን ቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ያደረጉት ሚኒስትሩ የግብፅ ባለሥልጣናት ሱዳንን ከመዝለፍ እንዲቆጠቡ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ ‹‹በዓባይ ወንዝ ጉዳይ ሱዳን የያዘችው አቋም ግብፅን የሚያስደስት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡
የግብፅ ፖለቲከኞች በሱዳን ላይ የሰነዘሩት ዘለፋ ለግብፅ ፖለቲካዊ ፍላጐት ጥቅም የለውም ሲሉ አክለዋል፡፡
በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው ወቅት ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ግድብ ላይ የመንግሥታቸው አቋም ኢትዮጵያን የሚደግፍ መሆኑን፣ ምክንያቱ ደግሞ ሱዳንም በውጤቱ ተጠቃሚ ስለምትሆን ነው ብለዋል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ግድቡን መገንባት የዓባይን የውኃ ፍሰት የሚያሻሽል በመሆኑ ሱዳን በዝናብ ላይ ብቻ የነበራትን ጥገኝነት የሚቀንስ ነው፤›› ብለዋል፡፡
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዓባይ ፖለቲካ ተወጥረው የሰነበቱት የግብፅ ባለሥልጣናት፣ በሳምንቱ መጨረሻ ላይም አለ የሚሉትን ችግር ከኢትዮጵያ ጋር ውይይት በማድረግ ለመፍታት የመምረጥ ፍላጐት አሳይተዋል፡፡
የግብፅን የውኃ ፍላጐት ለማስከበር የተሻለ ነው ባሉት ፖለቲካዊ ውይይት መሠረት ለኢትዮጵያ መንግሥት የውይይት ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ በማቆም ውይይቱ መጀመር እንዳለባት ጠይቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ የድርድር ጥያቄ ተስማምታ በጉዳዩ ላይ እልባት ካልተገኘ ግን፣ ግብፅ ማንኛውንም አማራጭ በመጠቀም ብሔራዊ ደኅንነቷን ለማስከበር እንደምትገደድ፣ የፕሬዚዳንት ሙርሲ የፖለቲካ አማካሪ የሆኑት አይማን አሊ መናገራቸውን የግብፅ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል፡፡
‹‹ግብፅ የራሷን ፍላጐት የማስከበር ፍላጐት እንዳላት ሁሉ የሌላው አገር መንግሥትና ሕዝብ የራሳቸውን ፍላጐት መከተል ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ በግብፅ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያስከትል ልታረጋግጥ ይገባል፡፡ በተጨባጭ ዋስትና መስጠት ይኖርባታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ግብፅ ያሏትን አማራጮች በሙሉ ተጠቅማ ጥቅሟ እንዲከበር ታደርጋለች፤›› ሲሉ በማስጠንቀቂያ የታጀበ ዛቻ ሰንዝረዋል፡፡
ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የተፈጠረውን የፖለቲካ ውጥረት በማርገብ ረገድ እየሄደችበት ያለው መንገድ የተደበላለቀ የሚመስል ሲሆን፣ በውይይት ለመፍታት ያሳየችው ፍላጐት በቅድመ ሁኔታ ታጥሯል፡፡ በሌላ በኩል ወታደራዊ ጉልበት የመጠቀም ፍላጐት እንዳላትም ለማሳየት እየሞከረች ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት መጀመርያ ላይ በቀጥታ ሥርጭት የተላለፈው የባለሥልጣናቱ ውይይት ሆን ተብሎ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ዕለት የግብፅ የደኅንነት ኃላፊ በሆኑት መሐመድ ራፋት ሸሃታ የተመራ ልዑካን ቡድን ሱዳንን መጐብኘቱን የግብፅ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ነገር ግን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዘገባውን አስተባብለዋል፡፡
ግብፅ ወታደራዊ ጥቃት የመጠቀም አማራጭ እንዳላትና ልትጠቀም እንደምትችልም በተደጋጋሚ መዘገቡን አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የግብፅን ወታደራዊ አማራጭ ‹‹የቀን ቅዠት ነው›› ሲሉ ገልጸውታል፡፡ አቶ ጌታቸው ግድቡን ለማውደም ወይም ኢትዮጵያን ለማተራመስ በግብፅ ፖለቲከኞች ስለተሰነዘረው አስተያየት በሰጡት ምላሽ፣ ኢትዮጵያን ደካማ በነበረችበት ጊዜ እንኳ ለማተራመስ የተደረገው ሙከራ አለመሥራቱን፣ አሁን ደግሞ እጅግ በጣም በተሻለ ደረጃ ላይ ስለምትገኝ ከግብፅም ሆነ ከሌላ አገር የሚቃጣን ጥቃት ታከሽፋለች ብለዋል፡፡ የግብፅ ፕሬዚዳንት ምክንያታዊ ሆነው ወደ ግጭት የማይገባበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ በሆስኒ ሙባረክ ዘመን ኢትዮጵያን በአማፂያን አማካይነት ለማተራመስ የተደረገው ሙከራ መክሸፉንም አስረድተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው፣ የግብፅ የውይይት ጥያቄ ተቀባይነት ያለው መሆኑን፣ ነገር ግን የግድቡ ግንባታ መቆም አለበት በማለት ግብፅ ያስቀመጠችውን ቅድመ ሁኔታ ‹‹የማይታሰብ›› ሲሉ በትዊተር ድረ ገጽ ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ከግብፅ ጋር ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስታውቆ፣ አንዳንድ የግብፅ ፖለቲከኞችና ባለሥልጣናት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን የሚጎዳ ፕሮፓጋንዳ መንዛታቸው እንዳሳዘነው ገልጿል፡፡ በትዕግስት አንዳንድ ጉዳዮችን ለማለፍ ቢፈልግም ገንቢ ያልሆኑ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች በመነዛታቸው፣ በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደርን በመጥራት የመንግሥታቸውን አቋም ጠይቀው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቁንና ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የግብፅ መንግሥት እስካሁን ለተጠየቀው ማብራሪያም ሆነ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡
ethiopian reporter

                       ESAT Weekly -. News June 9 2013 Ethiopia


Saturday, 8 June 2013

Interview with Egypt president Morsi on Ethiopian Renaissance Dam


  • Ahram.org [Egypt government media]
In an interview with state daily Al-Ahram published late Thursday evening, Egyptian President Mohamed Morsi said that, while Egypt had a “keen interest” in maintaining friendly relations with African states – especially Sudan and Ethiopia – it was also keen not to risk losing a “single drop of Nile water.”
The president’s statements came following last week’s move by the Ethiopian government to divert the waters of the Blue Nile in advance of building its planned Renaissance Dam, the prospect of which has worried Egyptian officials and politicians regarding the dam’s possible effect on Egypt’s share of Nile water.
“The operational strategy is to communicate with Ethiopia, its government and its people, to prevent any harm from befalling Egypt’s share of Nile water or that of our Sudanese brothers,” Morsi stated in the interview.
When the president was asked if current negotiations only aimed to reduce possible harm to Egypt, Morsi asserted (“angrily,” according to Al-Ahram) that Egypt’s position on the subject emanated from the desire to ensure that Egypt’s allotment of Nile water wasn’t affected and that no harm whatsoever occurs.
Morsi hinted at the complicated nature of the issue, saying that “a lot of details are involved” and that information regarding the dam from the Ethiopian government remained “insufficient.”
A trilateral technical committee – consisting of experts from Egypt, Sudan and Ethiopia – announced this week that its long-awaited report was “inconclusive” as to the planned dam’s effects on Egypt and Sudan.
The Ethiopian government nevertheless issued a statement saying the dam would not impact Egypt’s traditional share of Nile water, which – according to a colonial-era agreement and another 1959 treaty – currently stands at an annual 55 million cubic metres.
The Ethiopians are “Egypt’s friends,” who should look after its interests, said Morsi, stressing that Egypt in turn “will not allow itself to harm a friend, and therefore we don’t speak of thwarting the development of a friendly state.”
He concluded with the assertion: “The Nile is the lifeline and the axis of development for coming generations.”
On Thursday, an Egyptian presidential aide told state news agency MENA that Egypt was planning to officially demand a halt to the Ethiopian dam project.
However, an Ethiopian government spokesman told AFP Thursday that construction of the dam would go on, adding that Ethiopia had invited Morsi for talks, which would not include the option of halting the project.
Downstream Egypt enjoys the lion’s share of Nile water compared to upstream countries. Nile water treaties signed by Egypt allow it to veto any upstream projects planned by Nile Basin states.
Egypt’s traditional allotment of Nile water was challenged in 2010 when a new water-sharing agreement was signed between six upstream states, including Ethiopia.

ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው? “በሩ ይከፈት፣ በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ”

Image
በግብጽ ረዳትነት፣ በሱዳን መሪነት መንግስት ለመሆን የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ግዙፉን የጣና በለስ ፕሮጀክትና ንብረቱ እንዲዘረፍ ያደረገበትን ምክንያት በማንሳት መከራከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ እንዳደረጉት በአገር ጉዳይ ሁሉንም ያሳተፈ ግልጽ አቋም እንዲያዝና አጋጣሚውን በመጠቀም ብሔራዊ ህብረት እንዲፈጠር ኢህአዴግ በሩን ሊከፍት እንደሚገባ ተገለጸ።
በተለያዩ ጉዳዮች ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ በማሳሰብ ለጎልጉል አስተያየት የሚሰጡት የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት በርካታ ጉዶች ያሉበትን የአባይን ግድብ ተከትሎ ከግብጽ ጋር የተነሳው ውዝግብ አስቀድሞ የሚታወቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ስልትና ውጤት ነው።
አሁን ድረስ አገር እየመራ በነጻ አውጪ ስም የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ “ዲሞክራሲ አመጣሁ” በማለት ኢትዮጵያን መምራት እንደጀመረ የሚያወሱት የኢህአዴግ ሰው፤ አቶ መለስ ብቻቸውን ይነዱት የነበረው ኢህአዴግ እንደፈለገ ቆዳውን እየቀያየረ የተጠቀመበትንና በእስስት በመመሰል “ከሽፏል የሚሉትን” ስልት ያብራራሉ።
በዲሞክራሲ ስም የተጀመረው የኢህአዴግ አገዛዝ ቆየት ብሎ “ልማታዊ ነኝ፣ ልማት ግቡን የሚመታው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቀመር ነው” በማለት ፕሮፓጋንዳውን አሰፋ። የልማት ህልመኛነቱ ሲነቃበት “የትራንስፎርሜሽን ዘመቻ” በማለት አዲስ የፕሮፓጋንዳ እቅድ ነድፎ ህዝብና አገር ሲያታልል ቆየ። ይህም አላራምድና በህዝብ የመታመን ድል ሊያስገኝለት እንደማይችል ሲታመን “የህዳሴያችን ግድብ” ተብሎ አባይ አጀንዳ እንደተደረገ ያመለከቱት ዲፕሎማት፤ “ኢህአዴግ አገር ውስጥ የሚያምታታባቸው መንገዶች ሲጠናቀቁበት የፕሮፓጋንዳውን ዘመቻ አንድ ደረጃ ከፍ አደርገው” በማለት አሁን ከግብጽ ጋር ስለተጀመረው ውዝግብ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
አባይን በመገደብ ኢትዮጵያን በልማት ለማሳደግ እየተጋ እንደሆነ የሚናገረው ኢህአዴግ፤ አስቀድሞ በመላው የብአዴን የበታች አመራሮችና በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታና ቂም ስላስቋጠረው የጣና በለስ ሰፊ ፕሮጀክት ዝርፊያና ውድመት የጠራ መልስ ሊሰጥ እንደሚገባ ዲፕሎማቱ ይናገራሉ።
በጣሊያን መንግስት ሙሉ ድጋፍ አባይ ወንዝን መሰረት አድርጎ የተገነባውን የጣና በለስ ፕሮጀክት ህዝብ እያየ አፈራርሰው እንደወሰዱት፣ የተዘረፈው ንብረት ወደ ኤርትራ እንዲጓጓዝ መደረጉን ያመለከቱት እኚሁ ሰው፣ “ጣና በለስን አፈራርሶ ያስዘረፈ ፓርቲና አመራሮቹ አሁን አባይን ለመገደብ የተነሱበት መነሻ ለአብዛኛው የኢህአዴግ አባላት እንቆቅልሽ ነው” ባይ ናቸው። በማያያዝም በወቅቱ ዝርፊያው ሲካሄድ ህዝብ አካፋና ዶማ በመያዝ “ንብረቱ አይዘረፍም” በማለት መንገድ በመዝጋቱ ዝርፊያው በሌሊት እንዲካሄድ ያደረገ ድርጅት እንዴትስ ይታመናል የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።
“ኢህአዴግ የህይወት ዘመኑ የሚጠናቀቅበት ጠርዝ ላይ ስለሚገኝ፣ በአባይ ጉዳይ አመካኝቶ ህዝባዊ ማዕበል ለማቀጣጠል አቅዷል። የአባይ ጉዳይ ከዚህ የተለየ ተግባርና ዓላማ የለውም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ፣ የጣና በለስ ፕሮጀክት እንዲወድም መመሪያ የተሰጠው ከግብጽ እንደነበር መረጃ እንዳላቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ቀንደኛ ታሪካዊ ጠላት የሆነችው ግብጽ አባይ ላይ የሞትና የህይወት አቋም ቢኖራትም አሁን የተጀመረው ውዝግብ ከወሬ የዘለለ ግጭት እንደማያስነሳም ተናግረዋል።
በግብጽ አሁን ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት ለማስቀየር እየሰሩ ያሉት ፕሬዚዳንት ሙርሲ፣ የአባይን ጉዳይ ልቡን ከነፈጋቸው የአገራቸው ህዝብ ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ እንደሚጠቀሙበት ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ፣ የአገራችን ተቃዋሚዎች እንደ ግብጽ ተቃዋሚዎች መጫወቻ እንዳይሆኑ ይመክራሉ። “ኢህአዴግ የሚቃወሙትን ፓርቲዎች አባይን ተንተርሶ በአገር ክህደትና የአገርን ብሔራዊ ጥቅምን በመጻረር ፈርጆ ከህዝብ ጋር ሊያጋጫቸው ተዘጋጅቷልና ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ” ሲሉ ይመክራሉ።
በሌላ በኩል ሙርሲ እንዳደረጉት ኢህአዴግ በወቅቱ ጉዳይ ላይ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ሊያነጋግር እንደሚገባ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረዋል።
አቶ ኦባንግ እንደሚሉት “አገር የህዝብ ነው። ህዝብ በተለያየ መልኩ ይወከላል። ከሚወከልበት መንገድ አንዱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው። አገርን አስመልክቶ በየደረጃው ያሉ የህዝብ ወኪሎችን ማግለል ህዝብን የማግለል ያህል ነው። ይህን ማድረግ ይቅር የማይባል ወንጀል ይሆናል”
አገር ቤት ያሉትን ብቻ ሳይሆን በውጪ አገር ያሉትንም ፓርቲና ድርጅቶች በዚህ ጉዳይ ማነጋገር ግድ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ለዚህ አገራዊ ውይይት ማንኛውም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥ አይገባም” ብለዋል።
አጋጣሚው ለምንናፍቀውና ሁሉንም የአገሪቱን ህዝብ በእኩል ደረጃ ለማስተናገድ የሚያስችል ስርዓት ለመፍጠር እንደሚረዳ አቶ ኦባንግ ጠቁመዋል። የተለየ አመለካከት በማራመዳቸው ብቻ ዜጎችን እስር ቤት በማጎር እስከ ወዲያኛው መዝለቅ እንደማይቻል ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የውይይት በር በመክፈት የማያልፍ ታሪክ ሊሰሩ እንደሚገባ መክረዋል።
“ሙስሊም ወንድሞች ፍትህ የጠማቸው ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ የሚያረጋግጡበትን መድረክ አቶ ሃይለማርያም በማመቻቸት የማይረሳ ታሪክ ሊሰሩ ይገባል” በማለት ጥሪ ያስተላለፉት አቶ ኦባንግ “አገር የህወሃት አይደለችም፤ አገር የኢህአዴግ አይደለችም፣ አገር የግለሰቦች አይደለችም። አገር የሁሉም ነው። ባገር ጉዳይ ባይተዋር ሊደረጉ የሚገባቸው ዜጎች ሊኖሩ አይገባም። ኢህአዴግ ይህን ጉዳይ ሊያስብበትና በሩን ለእርቅና ለውይይት በመክፈት ህዝብንና ራሱን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይገባል” ብለዋል።
“ባድመ በተወረረች ጊዜ የተፈጠረው ህብረት በስተመጨረሻ በክህደት መጠናቀቁ፣ በዜጎች አጥንትና ደም ላይ የአገር ብሔራዊ ጥቅም ተላልፎ እንዲሰጥ መደረጉና በበርካታ ቁልፍ አገራዊ ጉዳዮች ኢህአዴግ በህዝብና በአባላቱ ጭምር እምነት ያጣ ፓርቲ ነው” በማለት ኢትዮጵያ የከፋ ችግር ቢያጋጥማት እንዴት ልትቋቋም ትችላለች የሚል ስጋት እንዳላቸው አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።
ስርዓቱ በየደረጃው በችግር የተተበተበና በህዝብ የማይታመን፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን እስር ቤት ያጎረ፣ በሰብአዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ ቂም የተቋጠረበት፣ ፍትህና ርትዕ የተጓደለባቸው ያዘኑበት፣ በየአቅጣጫው ጠላት ያከማቸ፣ አገርን የሚፈትን አደጋ ቢፈጠር ህዝብን አስተባብሮ አደጋውን ለመመከት የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን የገለጹት አቶ ኦባንግ “ኢህአዴግ አጋጣሚውን አሁንም ሊጠቀምበት ይገባል” ሲሉ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ኦባንግ የሰማያዊ ፓርቲ ያስተባበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ ኢህአዴግ ክስ ለመመስረትና ዜጎችን ለማሰር እያደረገ ያለውን ዝግጅት በመቃወም ሰሞኑን ለአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ መጻፋቸው ይታወሳል። ከደብዳቤያቸው በተጨማሪ ከተለያዩ አካላት ጋር በመነጋገር ኢህአዴግ ዜጎችን ከማሰሩ በፊት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች መግባባት ላይ መደረሱን ጨምረው ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ የአባይ ግድብን አስመልክቶ በከፍተኛ ደረጃ ውዝግብ ውስጥ የገቡት ኢትዮጵያና ግብጽ መጨረሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ በርካታ አስተያየትና ትንተና እየቀረበበት ነው። ሁለቱ አገሮች ወደ ጦርነት አያመሩም፤ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከመጠቀም ውጪ ሌላ አጀንዳ የላቸውም የሚሉ ያሉትን ያህል ግብጽ በጦር አቅሟ ያላትን የበላይነት በማመልክት ባልታሰበ ሰዓት ጥቃት ለመፈጸም መዘጋጀቷን የሚያትቱም በርካታ ናቸው።
የግብጽ ፕሬዚዳንት ከተቃዋሚዎች ጋር ያደረጉትና ይፋ የተለቀቀው ቪዲዮ ላይ “ተቃዋሚዎችን በመርዳት ኢትዮጵያን ማተራመስ፣ ኢትዮጵያን መደብደብ ነው … ” በማለት ሲዝቱ የነበሩት ጽንፈኛ ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት የከረረ ቃላት ሲወረውሩ ሰንብተዋል። ኢትዮጵያም በበኩሏ የግብጽን አምባሳደር በማስጠራት ማብራሪያ እንዲሰጣትና በይፋ ይቅርታ እንድትጠይቅ ማዘዟን ይፋ አድርጋለች።
ግብጽ በችግር መተብተቧን፣ የሶማሌ መበታተንና፣ የሱዳን ሁለት አገር መሆን፣ የኤርትራ መሽመድመድ ኢትዮጵያን በቀጠናው ጉልበት ያላት አገር አድርጓታል የሚሉ ተንታኞች በበኩላቸው ግብጽ ወደ ጦርነት እንደማታመራ ሰፊ መከራከሪያ በማቅረብ ይናገራሉ። ከግድቡ ግንባታ ጀርባ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ አገሮች እጅ እንዳለበትም የሚጠቁሙ ዘገባዎች በየፊናው ተሰራጭተዋል።
“ኤርትራ ተነፈሰች” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች፣ አሁን በተፈጠረው ሁኔታ ግብጽ ተቃዋሚዎችን ለመርዳት ከተንቀሳቀሰች ኤርትራ ርዳታውን በማከፋፈልና ቀድሞውንም ቢሆን ኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነቷን የጠበቀች ጠንካራ አገር እንድትሆን ስለማትፈልግ በችግሩ ዙሪያ ቤንዚን ለማርከፍከፍ አጋጣሚው እንደሚመቻችላት ያስረዳሉ። የአረብ ሊግ የክብር አባል የሆነችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ጋር በተያያዘ በበርካታ ጉዳዮች የምትታማ አገር እንደሆነች የሚታወስ ነው።
ዘግይታ “እኔ ከግብጽ የተለየ አቋም ነው ያለኝ” በማለት የገለልተኛነት ስሜት እንዳላት ይፋ በማድረግ ለግብጽ የድጋፍ ጥሪ መልስ የሰጠችው ሱዳን እንደማትታመን የሚግለጹ ደግሞ “አቶ መለስ ደቡበን ሱዳን ላይ ሲከተሉ በነበረው አቋምና ደቡብ ሱዳን እንድትገነጠል በመናደረጓ ሱዳን አቂማለች” ይላሉ፡፡ እንደነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች ምንም ይሁን ምን በአገር ውስጥ ያለውን ችግር በውይይት በመፍታት ብሔራዊ አንድነትና ህብረትን ማጠናከሩ ለኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊዋ ነው። ስለዚህ “በር ይከፈት በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ” የሚለው የአቶ ኦባንግ ብቻ ጥያቄ አይደለም።

ተቃዋሚዎች የግብፅን ዛቻ አጣጣሉት

  • “የጦርነት መንገድ ለኢትዮጵያም ለግብፅም አይጠቅምም” – አቶ ሙሼ ሰሙ
  • “ከገዢው ፓርቲ ያነሰ የአገር ፍቅር ያለን አይመስለኝም” – ዶ/ር መረራ ጉዲና
ተቃዋሚዎች የግብፅን ዛቻ አጣጣሉት ኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ መቀየሯንና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በግብጽና በሱዳን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተጽእኖ እንዲያጠና የተቋቋመው የኤክስፐርቶች ቡድን ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ፤ የግብጽ ተቃዋሚዎች የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማስተጓጐል ያቀረቡትን ሃሳብ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ተቃወሙት፡፡ የግብፁ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ከአገሪቱ ባለስልጣናት፣ ከተቃዋሚዎችና ከሃይማኖት ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ፤ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማወጅና፣ የአገሪቱን ተቃዋሚዎች በመደገፍ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ እንድታስተጓጉል ማስገደድ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በስብሰባው ላይ የተንፀባረቀውን ሃሳብ በተመለከተ አስተያየት የሰጡት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ “በርግጥም ግብፃውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቀዳዳ አይጠቀሙም ብሎ መከራከር ያስቸግራል፡፡ የአገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ለውጭ ሃይል መጠቀሚያ ለመሆን ይዘጋጃሉ የሚል ግምት የለኝም” ብለዋል፡፡ “በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ቢያንስ ቢያንስ ከኢህአዴግ ያነሰ የአገር ስሜት አላቸው ብዬ አልገምትም” ያሉት ዶ/ር መረራ “ይሄም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ፈርጀ ብዙ ችግሮች ካልተፈቱ የውጭ ሃይሎች ባገኙት ክፍተት ተቅመው የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር አይሞክሩም ማለት አይቻልም” ብለዋል፡፡ “ከሰባት ዓመት በፊት በፓርላማ የሶማሌን ጉዳይ በሚመለከት ስንወያይ ዳር ድንበራችንን አገራችን ውስጥ ሆነን መከላከል ይሻላል፣ የሰው አገር መግባት አስቸጋሪ ነው፣ እና አሜሪካ እንኳን ያን ያህል ሃብትና ቴክኖሎጂ ይዘው በድል መውጣት አልቻሉም” ብለን ለቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሃሳብ አቅርበን ነበር፡፡ እሳቸው ግን “በእኔ ይሁንባችሁ ጥቂት ሳምንት ብቻ ነው በዚያ የምንቆየው” ሲሉን ነበር፡፡
ኢትዮጵያ አሁንም እዚያው ነች፤ ያ ቀዳዳ አለ፤ የኦጋዴን፣ የኤርትራ፣ የሱዳን ቀዳዳዎች አሉ፡፡ የውጪ ሃይሎች እነዚህን ክፍተቶች ለመጠቀም አይሞከሩም ማለት አይቻልም፡፡ የአባይ ወንዝን በሚመለከት ከገዥው ፓርቲ ያነሰ የአገር ፍቅር አለን የሚል ግምት የለኝም ብለዋል ዶ/ር መረራ፡፡ አቶ ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው፤ “የግብፅ መንግስት በአገር ውስጥ ያሉና በሰላማዊ ትግል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎችን የፈለጋቸው፣ የራሱን አጀንዳ ለመሸጥ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የመልካም አስተዳደር የፍትህ እጦት አሳስቦት አይደለም፣ የአባይ ግድብ እንዳይገደብ ተቃዋሚዎችን መሳሪያ አደርጋለሁ ብሎ መነሳቱ አግባብ አይመስለኝም፣ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም አጀንዳ ስላልሆነ ትርጉም የለውም” ብለዋል፡፡
“መሐመድ ሙርሲ፤ የኢትዮጵያ መንግስትንና ህዝቡን አከብራለሁ የሚል አስተያየት ሲሰጡ በቅርብ ሰዎቻቸው ተሰምተዋል፡፡ በደጋፊዎቻቸውም ይሁን በህዝቡ ወይም በማንም ተባባሪ ሃይል ቢታገዝም፣ የጦርነት መንገዱ ብዙ ርቀት አያስኬድም፡፡ የጋራ ጥቅማችንን ለማስከበር በሩ ክፍት እስከ ሆነ ድረስ ተቀራርቦ መነጋገር እንጂ፣ በጦርነት መልኩ ማሰብ ዘመኑ የሚፈቅደው አይደለም፡፡ በጉዳዩ ላይ ጥናት እንዲያደርጉ በስምምነት ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ያወጡትን ዝርዝር ሰነድ መመልከትና በምስራቅ አፍሪካ አገሮች የሚገኙ ህዝቦችን መጥቀም የሚችልበትን አቅጣጫ መከተል ነው የሚበጀው፡፡ የጦርነት መንገድ ለኢትዮጵያም ለግብፅም አይጠቅምም” ብለዋል፡፡
addisadmas

ድንቁርና የሚድንም የማይድንም ሕመም ሊሆን ይችላል !መስፍን ወልደ ማርያም

መስፍን ወልደ ማርያም
ሰኔ 2005
ከጥቂት ቀናት በፊት አንዳንድ ሰዎች በዓባይ ጉዳይ ቀረርቶና ሽለላ ማሰማት ሲጀምሩ ከባድ የሆነ የመረጃ እጥረት መኖሩን ስለተገነዘብሁ ስለግብጽ የኃይል ሚዛን ደረቅ መረጃ የጦርነትን መጥፎ መልክ ከሚገልጽ አስተያየት ጋር አቀረብሁ፤ የወያኔ ሎሌዎች ወዲያው በእኔ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ከፈቱ፤  ድንቁርናው ከዚህ ይጀምራል፤ ማሪዮ ፊልሞና ብሩኖ ‹‹በአፍራሽአስተሳሰባቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ዛሬም የግብጽን ጦር ገና ከሩቁ እንድንገብርለትጉትጎታ ይዘዋል፡፡›› በማለት ውርጅብኙን ይጀምራል፤ አንድም ቦታ እኔ ያቀረብሁትን መረጃም ሆነ አስተያየት አንሥቶ ጉድለትን አላሳየም፤ ዓላማው መረጃው ወይም አስተያየቱ አይደለም፤ ለረጅም ጽሑፉ ዓላማው እኔ ነኝ፤ የአሉላ ሰሎሞን ጆቫኒ የግጥም ዓይነት መልክ ከመያዙ በቀር ያው ነው፡፡
ለእነዚህ ሰዎች መልስ የሚያስፈልጋቸው በእኔ ላይ የሰነዘሩትን ለማረም አይደለም፤ አንዳንድ ሰዎች መልስ አይገባቸውም ይሉኛል፤ እውነት ነው፤ እኔ በሥራዬ እቆማለሁ፤ ወይም በሥራዬ እወድቃለሁ፤ ነገር ግን ንጹሐን ወጣቶችን አዋቂዎች መስለው እንዳይበክሉ መከላከል ግዴታ ነው ብዬ አምናለሁ፤ ድንቁርና እንደተላላፊ በሽታ ነው፤ ይጋባል፡፡
ድንቁርና መጥፎነቱና አደገኛነቱ ከኋላውም ሆነ ከፊቱ የሚያይበት ዘዴ አለመኖሩ ነው፤ ለዛሬ፣ ለሆድ ብቻ መኖርን ዕለታዊ ዓላማው የሚያደርግ ነው፤ አንጎሉ በድንቁርና የተሞላ ለምንም ሌላ ነገር ቦታ የለውም፤ ይህ ድፍን ወይም ፍጹም ድንቁርና ነው፤ ተስፋ-ቢስ ነው፤ አንጎሉ ውስጥ ድንቁርና ያልደረሰበት ትንሽ ቦታም ቢሆን ከአለ የእውቀትን ዘር ለመዝራትና ብርሃን ለመፈንጠቅ ዕድል ይኖራል፤ አለዚያ ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡
ፊልሞን በሚል ስም ራሱን የሚጠራው ከሽፍንፍን መውጣት ያልቻለው ፈሪ ፊደልን ብቻ የተማረ መሀይም ነው፤ ይህንን አንብበህ መልስ ስጥበት ብሎ ያዘዘው ሰው የእኔን ጽሑፍ ካልሰጠው በቀር የእኔ ስም ባለበት ሰሌዳ ደርሶ ከሆነ ሰውዬው የማየት ችግርም አለበት ማለት ነው፤ በሰሌዳው  መጀመሪያ ገጽ ላይ የእኔ መጽሐፎች ሽፋኖች ይታያሉ የሎሌነቱን ተግባር ለመፈጸም የቀባጠረውን በዝምታ ማለፍ እሱን ራሱንም ሆነ በተለይም የአነበቡትን ሰዎች መጉዳት ሰለመሰለኝ ከእውነቱ ጋር እንዲጋፈጥ ማስገደድ ይገባኛል፤ ባንዳውን ምሁር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስን ማወቁን ሳደንቅለት ኃይለ ሥላሴ ጉግሳንና ጭፍሮቹን እንዳልረሳቸው ተስፋ አለኝ፡፡
 እኔ እስከማውቀው ድረስ አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከእርሳቸው በበለጠ የጦርነትን ምንነት ጠንቅቆ የሚረዳ እናየጦርነትን አስከፊነት እንደክቡርነታቸው በቴሌቪዥን ሳይሆን በተግባር የሚረዳ ይመስለኛል:: እናም የሃገራችን ጥቅምለማስከበር በሚደረገው ሰላማዊ እና ፍትሃዊ ስራ ከጎን ከመቆም ይልቅ በተንኮላቸው የማይወዱትን አካል ጠልፎ ለመጣልእስከጠቀመ ድረስ የሃገርን ጥቅም ለመሸጥ ጉጉነታቸውን አይቸበታለሁ፡፡
ይህንን ለመጻፍ የሚያስችል ድንቁርና ፍጹም ነው፤ ይህንን ፍጹምነት ሲያጠናክረው፤ –
ሰውየው እኮ ሃገራችን በደም አንባ ስትታጠብ በርሃብ አለንጋ ስትገረፍና ህዝቦቿ በአለም አደባባይ ስንዋረድ የኬንያዊውንየመሃመድ አሚንን ያክል ለሃገራችን ያላበረከቱ ግለሰብ ናቸው:: ዜጎች ያለፍርድ ሲረሸኑ ሲዋረዱ ሃገራችን የጨለማ ዘመንአገዛዘን እያማከሩ ሲሰሩ የነበሩ ሰው ስለሃገር ክብርና ስለሃገር እድገት ብዙም ይገዳችዋል ብሎ መጠበቅ ከሰማይ ደመናንእንደመዝገን ይሆናል::ተማሪወቻቸው እና ከሳቸው በእጅጉ በትምህርት እና በእድሜ የሚያንሱ ወጣቶች ለሃገራቸው እናለህዝባቸው ነጻነት ሲዋደቁ ክቡርነታቸው ግን ለንደን እና ዋሽንግተን እየተንሸራሸሩ በነበረበት ወቅት በርሃብ እና በጦርነትእየነደደ ስለነበረው ህዝባቸው አንዲትም ቃል እንደተነፈሱ ታሪክ የላቸውም ::
የተማሪ ቤት ግቢን የረገጠ ይህንን አይጽፍም፤ አንደአለቆቹ መሸጦ አስተማሪ ቤቱ ድረስ እየሄደ ፊደል ያስቆጠረው ሳይሆን አይቀርም፤ ፊደሉን ማወቁን እንደመጨረሻ ትምህርት ወስዶታል፤ በአንድ በኩል የሚያሳዝን ሰው ነው፤ በሌላ በኩል ግን ድፍረቱ ድንቁርናን የሚያበረታና ለጥቃት የሚዳርግ ነው፤ ለኮሎኔል መንግሥቱ ጂቡቲ ጦርነት ብትከፍት ኢትዮጵያ እንደማታሸንፍ ነግሬው ነበር፤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የክምችት ክፍል ሄዶ በጓደኞቹ እርዳታ ትንሽ ቢቆፍር በደርግ ዘመን ‹‹ሕዝብና መንግሥት ሆድና ጀርባ ሆነዋል፤›› በማለት የተናገርሁትን ያገኘውና ዓይኑን ይከፍትለት ነበር፤ ምስክሮቹ ሁሉ በሕይወት ባሉበት ጊዜ እንዲህ ያለ ውንጀላ አያዋጣም፤ ወይም እኔን በባንዳነት ከራሱ ጋር ሊያዛምደኝ ፈልጎ ከሆነ ያማ መንገድ አያስሄድም፤ እግዚአብሔር ይመስገንና በዚህም በዚያም ከባንዳ ጋር ንክኪ የለኝም፡፡
እኔ ስለጦርነት የጻፍሁት ለሚያውቁና ማሰብ ለሚችሉ ሰዎች ነበር፤ የሚያውቁ ሰዎች የምላቸው የአሥራ ዘጠነኛውን የመጀመሪያ አጋማሽና የሃያ አንደኛውን ምዕተ-ዓመታት ሁኔታዎች ተገንዝቦ ማመዛዘን የሚችለውን፣ በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ በአድዋ ላይ የተቀዳጀችውን ድል በኩራት እያስታወሰ በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ደግሞ በማይጨው ላይ በኢጣልያ ጦር የተሸነፈችበትን ውርደት የሚያውቅና የሚሰማው፣ በዚያው ላይ ኢጣልያ በአድዋ መሸነፍ የተማረች ስትሆን ኢትዮጵያ በአድዋ ድልም ሆነ በማይጨው መሸነፍ ሳትማር መቆየቷን የሚያውቅና የሚቆረቆር፣ ካላወቀም ለማወቅ የሚጓጓ ሰው ነው፤ ከዚያ በኋላ የኢትዮጵያ ጦር ከወያኔ ጀሌ ጋር፣ ከሻቢያ ጀሌ ጋር፣ ከሶማልያ ጋር፣ በቅርቡም ከኤርትራ ጋር፣ በኋላም ከሶማልያ አክራሪዎች ጋር በተደረጉ ጦርነቶች ሁሉ የሚያኮራ ነገር አልታየም፤ ይህንን ሁሉ እውነት አውቆና አመዛዝኖ ለማየት የማሰብ ችሎታን ይጠይቃል፤  ማሪዮ ፊልሞና ለዚህ አልታደለም፤ በቅዠት ዓለም ውስጥ ሆኖ ራሱን አሉላ የሚለው ብሩኖም እንዲሁ ያልታደለ ሎሌ ነው፤ ለሁለቱም ከጉራዕና ከጉንደት በኋላ ታሪክ የለም፤ እዚያ ላይ ቆሟል፤ የደበዘዙ ዓይኖችና የደነዘዙ አንጎሎች በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የሆነውን ይዘው 2005ን ለመደልደል የሚፈልጉ እንደፊልሞንና እንደአሉላ ሶሎሞን ያሉ ምስኪኖች እንዳይታዘንላቸው ትዕቢታቸው አያስቀርብም፤ እንዳይተዋቸው መርዛቸው ብዙ ሰዎችን ሊጎዳ ይችላል፤ ያለው አማራጭ ድንቁርናቸውን ማጋለጥ ብቻ ነው፡፡
የታሪክ ዋናው ዓላማ ጥቅም ዓይኖችን በአለፈው ነገር ላይ ተክሎ ወደኋላ ለማየት ሳይሆን ከፊታችን የተደቀነውን የዛሬውን ችግር ለመወጣት ከአለፈው ስሕተት መማር ነው፤ አንድ ጥያቄ፡– የኢትዮጵያ ድንበር ከዓባይ ጀምሮ ወደሰሜን እየሰለለ የሄደው ለምንድን ነው? እነፊልሞንና እነአሉላ ሶሎሞን ይህንን የማስተዋል ብቃት የላቸውም፤ ቢያስተውሉትም ስለማያስቡ አያሳስባቸውም፤ ማሰብ ቢችሉ የሚደነፉበትንና ግጥም የሚጽፉበትን ወደእፍረት ይለውጥባቸው ነበር፤ በቅርቡም በባድመ ጦርነት ፉከራውና ሽለላው ወደእፍረት ሲለወጥ አይተናል፤ ድንቁርና የሚደነድነው እውነትን፣ ከእውነት ጋርም እውቀትን እያፈነ ነው፡፡
በ1864 ዓ.ም. አካባቢ በጦርና በጋሻ አሸንፈናል፤ ዛሬም በ2005 ዓ.ም. በዚያው ዘዴ እናሸንፋለን ማለት የድንቁርና ዘውድ ነው፤ እኛ እንዳልተለወጥን ሌሎችም አልተለወጡምና በ1988 ዓ.ም. በአድዋ ኢጣልያን ድባቅ መተናል፤ እያልን ስንፎክር በ1928 ተመልሶ ሲመጣ በማይጨው ድባቅ መታን፤ ያን ጊዜ የሆነውን ማን ነው ከታሪክ የተማረው? ዛሬ ኢጣልያ ቢመጣ ፊልሞንና አሉላ ከነጓደኞቻቸው መንገድ መሪዎች መሆናቸው እጅግም አያጠራጥርም፤ ምክንያቱም እኔ የግብጽን ኃይል ለማሳወቅ የፈለግሁት እንዳንዘናጋ ሲሆን የእነማሪ ፊልሞንና አሉላ ጆቫኒ ፍላጎት ደግሞ ለማዘናጋት መሆኑ ነው፤ ዋናው ጥያቄ ግን ለምን እንድንዘናጋ ይፈልጋሉ? የኢትዮጵያ መዘናጋትና ለአደጋ መጋለጥ ምን ይጠቅማቸዋል? የሚለው ነው፤ መልሱ ውስጥ አልገባም፤ ፡፡
ዘመኑ እውቀት የረከሰበት ነው፤ ዛሬ አንድ ሰው የፈለገውን እውቀት ለማግኘት ከስንፍናና ከእኩይ ትዕቢት በቀር የሚያግደው የለም፤ በድንቁርና ከመኩራራት ፈርጠም ብሎ በእውቀት መስተካከልና ለወደፊቱ ማሰብ ቀና ይሆናል፤ ድንቁርናን የሚድን ሕመም እናድርገው፡፡