Friday, 8 November 2013

ከመሬት፣ እንዱ ስትሪና ከተማ ፤ልማት ጋር በተያያዘ ከ990 ሺ በላይ አቤቱታዎች መፍትሄ ማጣታቸው ተመለከተ።

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመሬት፣  ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች  መንግስት መልስ ለመስጠት እንደተሳነው መረጃዎች አመልክተዋል።
የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ፅ/ቤት የ2005 የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያሳየው ከመሬት፣  ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች መንግስት መልስ ለመስጠት ተስኖታል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ መንግስት የአጭር፤ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ  ዕቅድ ማዘጋጀቱ ይታወቃል። ከዚህ መነሻ ዕቅድ በመነሳት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ፤የክልል ተቋማትና የዞን አስተዳደሮችም  የየራሳቸዉን ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ገብተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተከፈተው ሃገር አቀፍ የመልካም አሰተዳደር ንቅናቄ መድረክ የመግቢያ ማስታወሻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ህዝብን ማእከል ያደረጉት የመልካም አሰተዳደር ስራዎች ገና አልተንቀሳቀሱም ፡፡ ህዝብን ያማረሩ ፤ የሚያሰለቅሱ አሰራሮች ግን  አሁንም አንደተሸከምናቸው ናቸው ሲሉ  የችግሩን ግዙፍነት አስታውሰዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የስምንት መስሪያ ቤቶች የሱፐርቪዝን ጥናት ሪፖርት ተጠናክሮ ቀርቧል፡፡ በቀረበው ሪፖርት እንደተጠቀሰው  ሰራተኛዉን በወር አንድ ጊዜ ስለመልካም አስተዳደር እንዲሰበሰብ የሚያዘው ህግ ተግባራዊ አልሆነም።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ዘርፍ አሰተባባሪ አቶ ሙክታር ከድር አንዳሉት በመሬት አሰተዳደር ችግር ብቻ በመላ ሃገሪቱ 670 ሺ 857 አቤቱታዎች ቀርበዉ  ምላሽ አልተሰጠም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም  የ9 ሺ 964 መሬት ነክ አቤቱታዎች በሽምግልና መፍታቱን ጠቁመዋል ።
የራስ አገዝ ማህበራት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሠጣጥ  ፤የስመ-ንብረት ዝውውር አፈፃፀም እንዲሁም የቦታ ስታንዳርድ መመሪያ ፡ ጥራት የሌላቸው መሆኑ በሚኒስትሩ ተገልጿል።
በአቶ ሙክታር  መሰረታዊ ችግሮች ናቸው ተብለው ከተዘረዘሩት መካከል ህጋዊ የመሬት ይዞታ ሠነድ ጥያቄ ፤ለተንጠለጠሉ ጉዳዮች በፍጥነት ምላሽ አለመስጠት፤መሬት አሠጣጡ ያለአግባብ ነው ተብሎ በከፍተኛ አመራሩ ውሳኔ ያረፈባቸው ጉዳዮችና ችግሮች እንዲስተካከሉ አለማድረግ፣ይገኙበታል ፡፡ እንዲሁም መሬት መስጠት ከመታገዱ በፊት በህጋዊ አግባብ መሬት እንዲያገኙ የተወሠነላቸውና ህጋዊ ሠነድ ያላቸው ግን ደግሞ መሬት ያላገኙ ግለሰቦች መሬት እንዲያገኙ አለማድረግ፤ተጠያቂነትን አለማረጋገጥ፤ዉሳኔ የተላለፈባቸዉን ጉዳዮች ያልፈፀሙ አመራሮችና ባለሙያዎች በህግ እንዲጠየቁ አለማድረግ፣የዲዛይን ምርመራና ፈቃድ አገልግሎት መዘግየትና የጥራት መጓደልን ማስተካከል አለመቻል፣ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የወጣውን የተሻሻለ አዋጅ አለማስተግበር የዘርፉችግሮች ናቸው ተብሏል፡፡

በቁጫ ወረዳ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ የሚማሩ ተማሪዎች ከማንነት እና መብት መከበር ጋር በተያያዘ ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የአንደኛ እና መለስተኛ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ በቋንቋችን እንማር፣ በአካባቢያችን የሚታየው የመብት ረገጣ ይቁም የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ ቁጥራቸው ከ25 እስከ 40 የሚደርሱ ተማሪዎችን ይዞ አስሯል።
ውጥረቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ፣ ቀደም ብሎ ያለበቂ ምክንያት ታስረው የተፈቱት 40 ሰዎች በዛሬው እለት ተመልሰው እንዲታሰሩ ተደርጓል።
መምህራን ትናንትና ዛሬ ስብሰባ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ለተፈጠረው ችግር መምህራንን ተጠያቄ አድርገዋል። ባለስልጣናቱ ” ለኢሳት፣ ለጀርመን ወይም ለአሜሪካ ሬዲዮ ከመናገር ውጭ ምንም የምታመጡት ነገር የለም መባላቸውን ያነጋጋርናቸው አንድ መምህር ገልጸዋል ።  የአካባቢውን የፖሊስ ሀላፊዎች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Thursday, 7 November 2013

“በሳዑዲ ኢትዮጵያዊ ህገ ወጥ ስደተኞች ሳንጃና ቆንጨራ መታጠቃቸውን አረጋግጠናል” አምባሳደሩ

(አምባሳደሩ በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ስም በሚያንቀሳቅሱት የአሰሪ እና ስራተኛ ኤጄንሲ ለሞቱት 3 ሴቶች ተጠያቂ ናቸው)
eth saudi


ኖቬበር 4 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የምህረት አዋጅ የግዜ ገደብ መጠናቀቅ አስመልክቶ ለተለያዩ የልማት ማህበር አባላት ኤምባሲው አርብ ኖቬምበር 1 2013 በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር የሚገልጹ ምንጮች ስብሰባው በኢትዮጵያውያን ቆጨራ እና ሳንጃ መታጠቅ ዙሪያ ኤምባሲው ማህብረሰቡን ለመነጋጋር አጀንዳ ይዞ መቅረቡ ስብሰባው በጣም አሳፋሪ እና ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ለመወንጀል ሆን ተብሎ የታቀደ ከስም ማጥፋት ዘመቻ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ገልጸዋል።
በተለይ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በወቅቱ ለተሰባስቢው ስለአጀንዳው ሲገልጹ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ አያሌ በባህር የመጡ ኢትዮጵያውያን በተለምዶ «ባህር ሃይል እየተባሉ የሚታወቁ» መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጠቀሰው እነዚህ ህገወጦች የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን ህግ ተከትሎ የሚወሰድባቸውን እርምጃ ለመከላከል ሳንጃ መታጠቃቸውን ኤምባሲው በመረጃ አረጋገጦል ብለው መናገራቸው በአብዛኛው ተሰብሳቢ ዘንድ ተቃውሞን ቀስቅሷባቸዋል። አምባሳደሩ በዚህ ዙሪያ ሰላማዊ ወገኖቻችንን በመወንጀል የሃገራችንን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት በኤምባሲ ደረጃ አጀንዳ ተይዞ ስብሰባ መጠራቱ ያበሳጫቸው ተሰብሳቢዎች የአምባሳደሩን ጤናማነት እስከ መጠራጠር መድረሳቸውን ምንጮቻን አክለው ገልጸዋል። ድጋፍ እናገኛለን ብለው የጠሯቸው ታማኝ የልማት ማህበራቱ ስራ አመራር የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ያቀረቡት ክስ ከምን ጭብጥ ተነስተው እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጦቸው ስብሰባው ላይ ወጥረው ይዘዋቸው እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች ስብሰባው ገና ከመነሻው በተሳታፊው ከፍተኛ ተቃውሞ አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡
mohammed hassenአንዳንድ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን አባባል ያንገበገባቸው አስተያየት ሰጪ የቀረበው አንጀዳ ስህተት መሆኑንን ገልጸው ሴት እህቶቻችን ጉልበታቸውን ያፈሰሱበትን የወር ደሞዛቸውን ተነጥቀው ተደብድበው እና ተደፍረው በየጎዳናው ወድቀው የፍትህ ያለህ እያልን ጣረሞት እያሰማን ባለንበት የስደት አለም እኛው አጥፊ እኛው ገዳይ አረመኔ እና ጨካኝ ተብለን በተለያዩ ሚዲያዎች ስማችን ሲጠፋ እና የሃገራችን በጎ ገጽታ በማጉደፍ በባእዳን ጥላቻ የተቃጣብንን የስም ማጥፋት ዘመቻ አምባሳደሩ እንደ አንድ ሃገር መሪ ተወካይ መጋፈጥ ሲገባቸው የዝሆን ጆሮ ይስጥኝ ብለው ከርመው ዛሬ በድፍረት እኛ ፊት ቆመው እኛኑ ለመወንጀል መቃጣታቸው በጣም ያሳዝናል ብለዋል።
በሌላ በኩል አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ሲናገሩ አምባሳደር መሃመድ ሃሰንን ከእንግዲህ እንደማያውቋቸው ገልጸው ስለኢትዮጵያውያን ለመናገር የሞራል ብቃት የሌላቸው ከሳቸው ይልቅ በዲፕሎማት ደረጃ አንቱ የሚባሉ እንደነ አቶ መስፍን እና መሰል ዲሲፒሊን ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የመንግስት ተወካዮች ስለኮሚኒቲው ችግር ህዝቡን ማወያየት እንደሚገባቸው በአጽኖት ጥቀስ በኤምባሲው ዝርክርክ አሰራር የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የተሳናቸው ወገኖቻችን ላይ ለሚደረሰው ማንኛውም አደጋ አምባሳደሩ ሃላፊነትን መውሰድ እንደሚገባቸው በሰጡት አስተያየት ከተሰብሳቢው በተደረገላቸው የድጋፍ ጭብጨባ በወቅቱ የስብሰባ አዳራሹን ድባባ ለውጦታል።
አምባሳደር መሃመድ ሃሰን በአምባሳደርነት ማዕረግ ተሹመው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከተላኩ ጀምረው በተለያዩ የግል ንግድ ላይ በእጅ አዙር ተሰማርተው ያለአግባብ የበለጽጉ ከበርቴ አምባሳደር መሆናቸውን የሪያድ ነዋሪዎች ያናገራሉ። አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ኢትዮጵያ ውስጥ በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ስም በከፈቱት 2 የአሰሪ እና ስራተኛ ኤጄንሲ አማኝነት ወደ ሳውዲ አረቢያ መጥተው እስካሁን ድረስ ህልፈተ ህይወታቸውን ቤተሰቦቻቸው ላልተረዱ 3 ሴት እህቶቻችን ሞት ተጠያቂ ከመሆናቸውም በላይ በቅርቡ 2 ሚሊዮን ሪያል «5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር» ወደ ሌላ ሃገር ለማሸሽ ሲሞክሩ በሳውዲ ደህንነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ከዋሉት ከቀድሞው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፋ ሁሴን አልዬ ጋር አምባሳደሩ እጃቸው እንዳለበት ይጠረጠራል።
በአጠቃላይ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን መንፍሃ ውስጥ ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቆ መሽጓል ብለው ለመወንጀል የፈለጉት የየተኛውን ብሄር አባል እንደሆነ ስብሰባው ላይ በይፋ ባይናገሩም በዚህ አካባቢ ቀደም ብሎ ጥቂት ስርዓት አልበኛ ኢትዮጵያውያን መሃከል አልፎ አልፎ በሚቀሰቀስ የጉሩፕ ግጭት በሳንጃ እርስ በእርሳቸው ይተራረዱ እንደነበርና በአካባቢው ማህበረሰብ የዕለት ተዕለት እንቅስቅሴ ላይ ቀላል የማይባል ተጸኖ ያሳድሩ የነበሩ ወጣቶችን ለማስታረቅ ኤምባሲው ቢጠይቀም ፈቅደኛ ሳይሆን መቅረቱ ይታወሳል። ይህ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ብዛት ያላቸው በባህር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የከተሙባት እና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በንግድ ዘርፍ የተሰማራባት በመሆኑ በመርካቶነት የሚሰይሙት ወገኖች ለአያሌ ኢትዮጵያውያን የእድገት ማዕከል በመሆኗ በማውሳት የአምባሳደሩን ንግግር ቀደም ሲል በተለያዩ ሚዲያዎች በኢትዮጵያውያን ላይ ከተቃጣ ውንጀላ ለይተው እንደማያዩት ይገልጻሉ።
የጎልጉል ደንበኛ በፌስቡክ የላኩት
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

እስክንድር ነጋን ለማስፈታት አንድ እርምጃ !

በቀደም ጋዜጠኛ ሰርካለም እስርቤት ለሚገኘዉ ባለበቷ ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በድምጽ የላከችዉን መልእክት አዳምጠን ቁጭታችንን ሀዘናችንን አሰምተን ነበር፤ አሁንAmnesty International UK HELP GET ESKINDER HOME በሚል ርእስ የፊርማ ማሰባሰብ ጀምሯ Amnesty International UK ቀደም ብሎ የታሰሩ እስረኞች ለማስፈታት  በናንተ የፊርማ ትብብርና በAmnesty ደጋፊ መንግስታት ጫና ነበር እያለን ፤ አሁንም የኢትዮጲያን መንግስት/ገዢ/ ጫና ፈጥረን እስክንድርን ለማስፈታት የያንዳችንን ትብብር ይጠይቃል እስካሁን 4951 ፊርማዉን ሰጥቷል የሚፈለገዉ 10,000 ብቻ ነዉ ይህን ሊንክ በመጫን አሁኑኑ ፊርማዎትን ያኑሩ
https://www.amnesty.org.uk/ የታሰሩት ሁሉ ይፈቱ! ሞት ለወያኔ!
Prisoners freed. Torture stopped. Executions prevented. We know that actions like yours have a real impact.
Now please share Eskinder’s story so as many people as possible take action like you.
When the Ethiopian government used anti-terror laws to silence its critics, Eskinder spoke out in protest. And when the people of nearby Egypt and Libya rose up in the ‘Arab Spring’, he speculated that the same could happen in Ethiopia. That scared the Ethiopian authorities.
So Eskinder was arrested, for the eighth time and charged with ‘incitement to commit terrorist acts’ and ‘treason’.
Yet despite the lies and the pain of separation from his family, Eskinder sleeps in peace, his conscience clear. The same, he wrote in an open letter recently:
‘cannot be said of my incarcerators though they sleep in warm beds, next to their wives, in their homes.’
Eskinder Nega
Now is our chance
The Ethiopian government has bowed to pressure from people like you before. Opposition politician Birtukan Midekssa was imprisoned alongside Eskinder and Serkalem from 2005 to 2007. She says pressure on the government from Amnesty supporters was instrumental in securing her release.
We believe we can do the same for Eskinder if we can show that tens of thousands of people around the world know and care about his plight. Please help us get him home to his wife, his child – and his work as a journalist, exposing repression.
‘Individuals can be penalised, made to suffer (oh, how I miss my child) and even killed. But… I will live to see the light at the end of the tunnel. It may or may not be a long wait. Whichever way events go, I shall persevere.’
Eskinder Nega
Because whatever the Ethiopian authorities may do, they will never silence Eskinder Nega.

Saturday, 2 November 2013

የአስተሳሰብን ህግ ካልጠበቅን ለመግባባት ያቅተናል!!! ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ለብዙ ዓመታት የማውቀው ወዳጄ ገብሩ ታረቀኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ፣ የማላውቀው አቶ ዓሥራት በአድማስ ጋዜጣ ላይ በትግሬነታቸው ተቆርቁረውና እኔን ባዕድ አድርገው የጻፉትን አንብቤ ሁላችንንም የሚያውቁ ሌሎች ሰዎች አስተያየት እንዲሰጡበት በማለት መልስ ከመስጠት ተቆጥቤ ቆየሁ፤ ሆኖም እስካሁን ከአንድ ሰው በቀር የደረሰልኝ የለም፤ ስለዚህ እኔው ልጋፈጠው፡፡ ገብሩ ወዳጄ ነው የምለው ሰው ስለሆነ የጋለ ስሜቱን ይዞ አደባባይ ከመውጣቱ በፊት ከእኔ ጋር ጉዳዩን አንስቶ አለመወያየቱ ከሚችለው በላይ የሆነ ግፊት ቢያጋጥመው መስሎ ታየኝ፤ እንዲያውም ሌላ ሰው እሱ ያለውን ሲናገር ቢሰማ ለእኔ ቆሞ ይከራከራል ብዬ የምገምተው ሰው ነበር፤ አንድ ሳይካያትሪስት (የአእምሮ ሐኪም) ሲናገር እንደሰማሁት የጎሳ አስተሳሰብ የጎሳን ድንበር ጥሶ ወዳጅነት የሚባል ነገር አያውቅም ያለውን አስታወሰኝ፤ ይህ እንደማይሆን ተስፋ አለኝ፡፡
በምን ላይ እንደጻፍሁት ሳልናገር ለሁለቱም የትግራይ ተቆርቋሪዎች የሚከተሉትን አጫጭር ነጥቦች ላመልክታቸው፡-
1. ወያኔ ..ከሚኒልክ በፊት ኢትዮጵያ አገር አልነበረችም ሲል የአፄ ዮሐንስንና የራስ አሉላን ትግሬነትና ኢትዮጵያዊነት በመካድ.. ጀመረ፤
2… የጎንደርን በሬ፣ የጎጃምን በሬ፣ የሸዋንም በሬ፣
ባንድ አርጎ ጠመደው የትግሬው ገበሬ..
(የትግራይን የኢትዮጵያዊነት መሰረት ለማስረዳት የጠቀስሁት)
3. ..የትግሬ ዘር (ኤርትራውያንን ጨምሮ) የኢትዮጵያ መሰረት ነው፤ የትግሬ ዘር የኢትዮጵያን ታሪክ ተሸካሚ ነው፤ እንኳን በኢትዮጵያዊነታቸው ያሉትን ትግሬዎች የተገነጠሉትንም ለማጥፋት ማሰብ በምድርም በሰማይም ይቅርታ የማያስገኝ ወንጀል ነው፡፡ ከኤርትራውያን ጋር የተደረገውንም የወንድማማቾች ጦርነት አጥብቄ የተቃወምሁት በዚህ ምክንያት ነበር፤ በሰሜን ያሉትን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ከመቅጽበት ወደባዕድነት ለውጠን አሁን ደግሞ የተረፍነውን አጥፊና ጠፊ አድርጎ መፈረጁ ለማንም የሚበጅ አይሆንም፡፡..
ብዙ ሌሎችንም መጥቀስ እችላለሁ፤ ልብ ላለው ይበቃል፡፡
በደርግ ዘመን በዩኒቨርስቲ ውስጥ ስናወራ ስለ የአእምሮ ወዝ-አደር ስናገር አንዱ ካድሬ የአእምሮ ወዘ-አደር የሚባል ነገር የለም ብሎ ተቆጣ፤ አብረውን የነበሩት ሁሉ በስምንት ተኩል እኔ ቢሮ እንዲመጡ ጋበዝሁና መጽሐፉን ይዤ መጣሁና ለካድሬው አሳየሁት፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌኒን ተናዶ በደርዘን የሚቆጠሩ ካድሬዎችን በአንድ ትጉህና ታታሪ ባለሙያ የሚለውጠኝ ባገኘሁ ብሏል ስል ያው የማይማር ካድሬ ተቆጣና ..አይወጣውም…. አለ፤ መቶ ብር ከኪሴ አወጣሁና አንድ ጊዜ በነፃ አስተምሬሃለሁ፤ አሁን ግን መክፈል አለብህ፤ የሌኒንን ጽሑፍ ካላመጣሁልህ መቶ ብር ታገኛለህ፤ ካመጣሁ ግን መቶ ብር ትከፍላለህ ብለው አሻፈረኝ ብሎ በስሀተቱ ጸና፤ አቶ ዓሥራት ብዙውን ጽሑፎቾን አንብቤአለሁ ሲል እውነት እንዳልሆነ ስለማውቅ ውርርድ ላቀርብለት ፈልጌ ነበር፤ ስለአማራ የተናገረው እኔ የጻፍሁትን እንዳላነበበ ጥሩ ማስረጃ ነው፤ ሳያውቁ በእርግጠኛነት አዋቂ መስለው ለሚቀርቡ ቀላሉ መንገድ በአደባባይ ውርርድ ነው፤ ገብሩ ታረቀ እንኳን በአሜሪካ የፈረንጅ ልጆች ሲያስተምር ስለኖረ በአገር ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ ማንበቡ አጠራጣሪ ነው፡፡
ለነገብሩና ለነዓሥራት ትልቁ ፍሬ ነገርና ቁም-ነገር ትግሬነታቸውን ለብቻቸው የያዙት መስሎአቸው ነው፤ በትግሬነታቸው ውስጥ አነሱንና እኔን የሚያያይዙ ብዙ ከባድ ሰንሰለቶች መኖራቸውን አያውቁም፤ ለነሱ ትግሬ ከትግሬነት ሌላ ፋይዳ ወይም ትርጉም የለውም፤ እንደዚህ ያለ ክርክር መነሳቱ ኢትዮጵያዊነት ምን ያህል እንደላላ የሚያመለክት ነው፡፡
..ማወቅ ወደ እርግጠኛነት የሚያመራው በመጠራጠርና በመጠየቅ ነው፤ አለማወቅ ግን ምንጊዜም ወደጠን ካራ የጨለማ እርግጠኛነት የሚመራ ነው፤ አለማወቅ ከኃይል ጋር ሲጋባ የአምላክን ቦታ ይይዝና እስመ አልቦ ዘይሰአኖ ይሆናል፡፡..
ሁለቱም ሰዎች፣ ፕሮፌሰር ገብሩም አቶ ዓሥራትም ባሳዩዋቸው ሁለት የእውቀት ጉድለቶች ልጀምር፤ ይህንን ማድረጉ አያስደስተኝም፤ ነገር ግን አለማወቅን ወደ እውቀት እየለወጡ ሰዎችን ማሳሳቱ፣ ከዚያም አልፎ በትግራይ ማህበረሰብ ላይ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ የጥላቻ መርዝን ለመንዛት የሚደረገውን ሙከራ አገርን የሚጎዳ ነውና ሊታለፍ አይገባም፤ ፕ/ር ገብሩም አቶ ዓሥራትም በሂሳብ ትምህርታቸው ስለ Set theory ትንሽ ቢያውቁ ..የኤርትራና የትግራይ ዜጎች..ያልሁት ደማቸውን አያፈላውም ነበር.. ትግራይ በኢትዮጵያ ውስጥ፣ ኢትዮጵያ በትግራይ ውስጥ ይገኛሉ፤ የኔ ስህተት የአንባቢዎችን ደረጃ ከፍ አድርጌ መመደቤ ነው፡፡
ሌላው የእውቀት ልዩነት ሰው የመሆን ግንዛቤያችን ነው፤ ለእኔ ሰው በቁና የሚሰፈር፣ ወይም በከረጢት የሚታሰር አይደለም፤ እያንዳንዱ ሰው በነጠላ ለራሱ ስራ ኃላፊነቱን ይወስዳል፤ እንኳን በ2004ዓ.ም ጥንትም ቢሆን ጽድቅም ሆነ ኩነኔ የግል ነው፤ በጎሳ ወይም በጅምላ አይመጣም፤ የሰው ልጅ እንደ አይጥና እንደድመት አይደለም፤ እንኳን አብሮ የኖረና የተዛመደ፣ አንዱ ለሌላው የመጨረሻ መስዋዕትነት የከፈለ ቀርቶ እንግዳም ቢሆን አንዱ ለሌላው መሰረታዊ ጠላትነት የለውም፤ ፕ/ር ገብሩና አቶ ዓሥራት እንጀራቸውን ለማብሰል ለትግሬዎች ዘብ የቆሙ መስለው ባልገባቸው ነገር ሁሉ ደማቸውን ያገነፈሉት እኔን ባዕድ በማድረግ ለመጠቀም ነው፤ ለእነሱ አዝናለሁ፤ የትግራይ ህዝብ እኔን በነሱ ዓይን እንደማያየኝ አምናለሁ፡፡
ፕ/ር ገብሩ ..እኔም እንደአስገዶም ገ/ስላሴ የወዲያ ማዶ ልጅ ነኝ.. ይላል፤ ወዲያ ማዶ ስል ትግራይ ማለቴን ማን ነገረው? ስብሐት ነጋን ወዲህ ማዶ ሳደርገው በገብሩ ግንዛቤ ትግሬ አይደለም ማለቴ ነው መሰለኝ.. ገብሩን ወዴት ከፍ ከፍ እለዋለሁ.. ገብሩ የወዲያም የወዲህም ልጅ አይደለም፤ የባህር ማዶ ልጅ ነው..
ሁለተኛ ስለኤርትራውያን የተናገረው መልካም ስሜቱን ከመግለጽ በቀር መጽሐፉን ቢያነብበው ኤርትራውያን በስሜት ሳይሆን በተግባር እሱ ..እስረኞች.. ያላቸው ሰዎች የገለጹትን እውነት ያስተባብለዋል፤ በተጨማሪም ለታሪክ ባለሙያው መንገር ካልሆነብኝ የሠርጸ ድንግልን ዜና መዋዕል ቢያነበው ከወራሪ መከላከል እንደሚችሉ ሊገነዘብ ይችላል፡፡
ሶስተኛ፣ ..የሞራል ሉዓላዊነት.. በአማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ አልገባኝም፤ አላግባብ ተሰካክቶ የተደነቀረ ነገር ነው፡፡
አራተኛ፣ ለኢጣልያ ገብረው የጠላት ወታደር በመሆን ወገናቸውን የወጉት ኤርትራውያን እጅና እግር መቆረጡ በአሁኑ ጊዜ ላለነው የሚዘገንን ነው፤ ነገር ግን ፕ/ር ገብሩ በዓድዋ ጦርነት በምኒሊክ አገዛዝ የተደረገውን ሲናገር በቅርቡ በማይጨው የደጃዝማች ኃ/ስላሴ ጉግሳን ሆነ በሌላ የተፈፀመን ቅጣት አለማንሳቱ፤ በአገራችንም ቢሆን የአፄ ቴዎድሮስን አልሰማም ይሆን? የአጼ ዮሐንስንስ አልሰማም ይሆን? ወይስ እኔ እንዳነሳለት ፈልጎ ይሆን? አንዳንድ ነገሮችን እየነቀሱ በማውጣት ታሪክ እንደማይጻፍ ለፕ/ር ገብሩ መንገር አያስፈልግም፤ የምኒልክን ሀጢአት ለማበራከት ከሆነ ከሸዋ ሳይወጣ በጧፍ ያነደዱትን ሊጨምርበት ይችላል፡፡
አሁን ከባድ ወደሚመስሉኝ ነጥቦች ልምጣ፤ ለእኔ እንደሚገባኝ ታሪክ ሁነትን በመግለጽ ይጀምራል፤ በትክክል ለተመዘገበው ሁነት ፍቺ መስጠት፣ ወይም ጥሩና መጥፎነቱን በመግለጽ ፍርድ መስጠት በኋላ የሚመጣ ነው፤ በሌላ አነጋገር ፍርድ ሁነትን ተከትሎ ይመጣል እንጂ የሁነቱ ፍቺ ወይም በሁነቱ ላይ የሚሰጠው ፍርድ አይቀድምም፤ ይህ ከሆነ ፈረንጆች እንደሚሉት ፈረሱን በጋሪው ለመጎተት እንደመሞከር ይሆናል፤ አጉል ድካም ነው፤ አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም፤ ለሁለት ጊዜ ገብሩ ለማድረግ የሚፈልገው ይህንን ነው፤ ምን እንደተናገርሁ ለአንባቢው ሳይነግር፣ በራሱ ግምት የተናገርሁ ለመሰለው ነገር ፍቺና ፍርዱን መስጠት ይጀምራል፤ ይህ የእውቀትና የእውነት ፈላጊ ምሁር የአጻጻፍ ስርዓት አይደለም፤ በዚህ ጉዳይ አቶ ዓሥራት እኔ ያልሁትን በትክክል ጠቅሶ ወደራሱ አስተያየት ይሻገራል፤ ይህ ተገቢ ነው፡፡
ገብሩ ግን ..ኢትዮጵያዊ ዜግነትን በትግራይ ዜግነት መተካትዎ ምን ቢያስቡ ነው?.. ይለኛል፤ መጀመሪያ በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ ምን እንደተናገርሁ አይገልጽም፤ የተገነጠለውን ኤርትራን ይገድፍና ዘልሎ ትግራይን ለማስገንጠል የፈለግሁ ለማስመሰል ..ምን ቢያስቡ ነው?.. ይለኛል.. ኤርትራን የጨመረ እንደሆነ ተንኮሉ ይበላሻል.. ለኢትዮጵያውያን ነግሮ ሊያስወነጅለኝ ፈልጎ ነው? ወይስ ለአስገንጣዮቹ ነግሮ ሊያስሸልመኝ.. ለተገንጣዮቹና ለአስገንጣዮቹ በስሜት ማንኛችን እንቀርባለን?
ከላይ እንደጠቀስሁት በሂሳብ ወይም በፍልስፍና ንባብ ቢደገፍ እዚህ ስህተት ላይ አይወድቅም ነበር፤ ..ምን አስበህ ነው?.. የሚለው ለመወንጀልና ለማስወንጀል የተቃጣ ለማንም ግልጽ የሆነ ንጹህ ተንኮል ነው፤ ከኢትዮጵያ ዜግነት የተለየ የትግራይ ዜግነት መኖሩን ሊነግረኝ ያሰበ ይመስላል፤ እንዲህ ያለ መያዣና መጨበጫ የሌለው ነገር እኔ አልተናገርሁም፤ በ1998 ጓደኞቼና እኔ ከተከሰስንበት አንዱ የትግሬን ዘር ለማጥፋት መሞከር የሚል ለጆሮም የሚቀፍ ነገር ነበር፤ በ1998 ፍርድ ቤት በቀረብንበት ጊዜ የዛሬው የገብሩ ጽሑፍ ቢገኝ ትልቅ ማስረጃ ሆኖ ይቀርብ ነበር፤ እግዚአብሔር ሲያወጣን ገብሩ በዚያን ጊዜ ከእኛ ጣጣ ተከልሎ በአሜሪካው ነበር፤ ዛሬም 1998 እየሸተተ ነውና ገብሩ ስራ አያጣም፡፡
አንድ የታሪክ ባለሙያ ፕ/ር ትናንት በጋዜጣ የተጻፈውን በትክክል መድገም ሲሳነው ከአስር፣ ከሃምሳ፣ ከመቶ ወይም ከዚያ በላይ የቆዩ ጉዳዮችን እንዴት አስታውሶ እውነቱን ሊናገር ነው? እኔ የጻፍሁትን እሱ በመሰለው ተርጉሞ ከአገርና ከዘመድ ጋር የሚያጣላ ከባድ ነገር ሲለጥፍብኝ በጣም ያሳዝናል፤ መቼም ኢትዮጵያ ሆነና ነው እንጂ በሌላ አገር ቢሆን የጋዜጣው አዘጋጅ ያልተባለ ነገር ተቀብሎ አያሳትመውም ነበር፤ ከዚያም በላይ ገብሩና እኔ ስለምንተዋወቅ እሱ የጻፈውን ሌላ ሰው ቢጽፈው ገብሩ ይቃወማል ብዬ ሙሉ እምነት ነበረኝ፤ እንዲህ ዓይነት ጭራሽ ትርጉም የሌለው ነገር እኔ አልወጣኝም፤ ከኢትዮጵያ የተለየ የትግራይ ዜግነት የሚባል ነገር መኖሩንም አላውቅም፤ ዜግነት ምን እንደሆነና ከጎሳዊነት የተለየ መሆኑን አውቃለሁ፤ ዜግነትን በጎሰኛነት የሚተኩት እነማን እንደሆኑ ገብሩ አላወቀም ማለት ነው፤ ወይም አምስት መቶ ዶላር ኪራይ የሚከፈልበት ጊዜያዊ ዜግነት ከሌለው በቀር ወደ ቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት ሲሄድ ያስረዱታል፤ እኔ ግን ዜግነትንና ጎሰኛነትን አላነካካቸውም፤ ዜግነቴንም እንዲያው በዋዛ አላየውም፡፡
* ..የኤርትራና የትግራይ ዜጎች.. ያልኋቸው ኢትዮጵያውያን ካልሆኑና የዜግነት ግዴታ ከሌለባቸው ኃላፊነቱን ከየት አምጥቼ ጫንሁባቸው?
* ገብሩስ የኢትዮጵያ ዜግነታቸውን ተገፈፉ ብሎ ወደቁጣና ወደመከፋት ያመራው ዜግነታቸውን ከዜግነታቸው ግዴታ እንዴት ለይቶ ነው?
የዜግነት መብትና ግዴታ በእያንዳንዱ ግለሰብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ዘርን ወይም ጎሳን ከዜግነት ጋር ማገናኘት ግልጽ ስህተት ነው፤ በ1969 ሶማልያ ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ አንድ የትግራይ ዜጋ በራሱ ፈቃድና ወጪ አዲስ አበባ መጥቶ ለመዝመት መወሰኑን በቴሌቪዥን አይተናል፤ የኢትዮጵያ ዜጋ ስላላልሁት በተግባር የገለጠውን የዜግነት ግዴታ ይፍቀዋል የሚል የጎሳ ህመም የያዘው ብቻ ነው፡፡
እጅግ የሚያስደንቀውና ከገብሩ በጭራሽ የማልጠብቀው የቼኮዝላቫኪያውን ጸሐፊ የሀበሻ ጀብዱ የሚለውን መጽሐፍ ገና ሳያነብበው መጥላቱ ነው፤ እኔ ሰውዬውን ጎበዝ በማለቴም የተበሳጨ ይመስላል፡፡
..የትግሬ ሽፍቶች.. በሚለውም ጥቅስ ተበሳጭቷል፤ የእሱ መበሳጨት አንሶ ሌሎችን ለመቆስቆስ ..በዚህ አባባልዎ ብዙዎች ዜጎችን ሳያስከፉ እንዳልቀሩ ሳልጠቅስ ለማለፍ አልፈልግም.. ይላል፤ ብዙ ሰዎችን የሚያስከፋው አባባሌ ምን እንደሆነ የታሪክ ፕ/ሩ አልተናገረም፤ የእኔን ጽሑፍ ያላነበበ ሰው አንድ መጥፎ ነገር የተናገርሁ ይመስለዋል፤ እኔ ያልሁት ስላልተጠቀሰ አንባቢው የራሱን ፍርድ ለመስጠት እንዳይችልና የገብሩን ፍርድ ብቻ ተቀብሎ መስመር እንዲይዝ ይጋብዘዋል፤ ከገብሩ እኔ የምጠብቀው አንደኛ ምንም ያህል ቢያስከፋ እውነትን ለመቀበል ዝግጁ መሆንን ነበር፤ ሁለተኛ ፀሐፊው የጠቀሳቸውን የትግሬ ሽፍቶች ለትግራይ ህዝብ በሙሉ ማልበስ አጉል ጎሰኛ አስተሳሰብ ነው፤ ትዕግስትና ፍላጐት አድሮበት መጽሐፉን ቢያነብበው የራስ ስዩምም ጦር ከራስ ካሣ ጦር ጋር ተሰልፎ ሲዋጋ እንደነበረ መረዳት ይችል ነበር፤ በህገ ኀልዮት (ሎጂክ) ለጥቂቶች የተነገረውን ለጠቅላላው ማልበስ ልዩ ስም ያለው የአስተሳሰብ ጉድለት ነው፤ ነገር ግን ፕ/ር ገብሩ በዚህ በህገ ኀልዮት ስሀተቱ እኔን ለማቄል ..በሽፍቶች አሳበው መላውን ትግሬ ለመፈረጅ ነው የሚል እሳቤ የለኝም ይላል፤.. እንኳን ይቺንና የዝንብ ጠንጋራ እናውቃለን ሲባል አልሰማም መሰለኝ..
በፍትህ ጋዜጣ ከአቶ ስብሓት ነጋ ጋር የተጀመረው ክርክር በአንድ ጉዳይ ላይ ነበር፤ ከዚያ ክርክሩ እየወረደ የጎሳ ሽታ ይዞ መጣ፤ የኔ የመጨረሻ ጥረት ይህንን የጎሳ ሽታ ለማስወጣት ነበር፤ ሐጎስ እርገጤ ሌባ ነው ሲል በላቸው የሚናደድ ከሆነ፣ እርገጤ ሐጎስ ሌባ ነው ሲል ጥዑም የሚናደድ ከሆነ እንደሰዎች ለመነጋገር የምንችልበት ጊዜ አልደረሰም ማለት ነው፤ በግላችንም ሆነ በህዝብነታችን የሚያዳክመን አጉል መሸፋፈንና ድብብቆሽ ነው፤ እውነቱን ለማወቅና እውነቱን ለመናገር ድፍረቱን ከአገኘን ሳንጎዳዳ እንደልብ ለመነጋገር እንችላለን፤ ለጋዜጦቹም ሆነ ለአንባቢዎች አንድ ለመግባቢያ የሚረዳን ሀሳብ ላቅርብ፤ INTERNET ውስጥ ገብተን LOGICAL FALLACY ብለን ብንጠይቀው በምንነጋገርበትም ጊዜ ሆነ በምንጽፍበት ጊዜ ሊረዳን የሚችል ትምህርት የምናገኝ ይመስለኛል፤ በገለባ እየለወጥን የምናውቀውንም የማናውቀውንም እያደባለቅን ብንነታረክ ዋጋ የለውም፤ ከዚያም በላይ እያንዳንዳችን ተምረናል፤ አውቀናል፤ ብለን በውስጣችን ያለውን መርዝ ከምንነዛው በውስጣችን ይዘነው እኛኑ እንዳደረገ ያድርገን፡፡

Friday, 1 November 2013

ኢትዮቴሌኮም የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሰ መንጸባረቂያ መሆኑን የግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ አጋለጠ

2665272d78511e341383257989
 Oct 31,2013 የመረጃቴክኖሎጂ  መሠረት የሆነዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ አፍሪካ፤ ላቲን አሜሪካና ኢሲያ ዉስጥ የሚገኙ በእደገት ወደ ኋላ የቀሩ አገሮችን ለዘመናት ከተዘፈቁበት የኋለ ቀርነት ማጥ ዉስጥ ጎትቶ አዉጥቶ ወደ ፈጣን የእድገት ጎዳና ይወስዳቸዋል ተበሎ የታመነበትና በአንዳንድ አገሮች ዉስጥ ይህ ለእድገት አመቺነቱ በተግባር የተመሰከረለት ዘርፍ ነዉ። ይህ ዘርፍ ገበሬዉ፤ ሰራተኛዉ፤ ተማሪዉ፤ ወታደሩና ለሌላም በማንኛዉም የስራ ዘርፍ ለተሰማራ የህብረተሰብ ክፍል የእዉቀት ምንጭ በመሆን የስራ ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የሚረደና በህብረተሰብ መካከል ፈጣን የሆነ የመረጃ ልዉዉጥ አንዲኖር የሚያደርግ ዘርፍ ነዉ። በእድገት ወደ ኋላ ለቀረችዉ አገራችን ኢትዮጵያም ይሀ ዘርፍ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ዘርፍ ነዉ። ነገር ግን በአፍሪካ ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ወደኋላ ከቀርችባቸዉና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ሆን ብሎ እድገታቸዉ እንዲገታ ካደረጋቸዉ ኋላ ቀር ዘርፎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ይሄዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ ነዉ።
እራሱን “ልማታዊ መንግስት” ብሎ የሚጠራዉ የወያኔ አገዛዝ ስልጣን ከያዘባቸዉ የመጀመሪያዎቹ አመታት ጀምሮ አስከ ቅርብ ግዜ ድረስ እንደ ቤት ዉስጥ ዕቃዉ ከተቆጣጠራቸዉና የኢትዮጵያን ህዝብ በሚጠቅም መልኩ እንዳያድጉ ካደረጋቸዉ ቁልፍ መስሪያ ቤቶች ዉስጥ አንዱ ኢትዮቴሌኮም ነዉ። ወያኔ ኢትዮቴሌኮምን ያላደረገዉ ነገር የለም። ዘረኝነትን በሚጠቅም መልኩ አደራጅቶታል፤ የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆበታል፤ ቻይናዎችን አምጥቶ የስለላ ተቋም አድርጎታል፤ የሚገርመዉ ዛሬ ኢትዮቴሌኮም የተራቀቀዉ በስልክ፤ በኢንተርኔትና በሌሎችም የመገናና አገልግሎቶች ሳይሆን ዜጎችን በመሰለልና የመረጃ ጨለማ በመፍጠር ርካሽና ጎታች ስራዎች ነዉ። ይህንን ርካሽ ስራ ደግሞ በቅርቡ የአገዛዙ የኢንፎርሜሺን ደህንነት ኤጀንሲ ሹም ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን” የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን የመቆጣጠርና የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን የማገድ አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁም ይህ ነዉ በማለት በአዳባባይ አረጋግጧል።
የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ በላፉት አስራ ሁለት ወራት ይህንኑ ኢትዮቴሌኮም በሚል መጠሪያ የሚተወቀዉንና በስለላ ስራ ላይ የተሰማራዉን የሲቪል መስሪያ ቤት አደረጃጀት፤ አወቃቀርና የሰዉ ኃይል አመዳደብ በቅርብ ተከታትሎ ከዚህ ቀትሎ የሚታየዉን መረጃ አጠናቅሯል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚገባ እንደሚያዉቀዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያን ቴሌኮሚኒኬሺን ተቋም ከኋላ ቅርነት ለማላቀቅ በሚል ሰበብ የኮርፖሬሺኑን የማኔጅመንት ዘርፍ ለፈረንሳይ ኩባኒያ መስጠቱ የሚታወስ ነዉ። ወያኔ እንደሚለዉ የኢትዮቴሌኮም ማነጅመንት ለፈረንሳዩ ኩባኒያ የተሰጠዉ የኮርፖሬ ኑን አቅም ለማሳደግ ቢሆን ኖሮ መልካም ነበር፤ ነገር ግን ወያኔ የሚናገረዉና የሚሰራዉ ስራ የተለያየ በመሆኑ ዛሬ ወያኔ ኢትዮቴሌኮም በየዘርፉ የረጂም ግዜ ልምድ ያላቸዉን ባለሙያዎች አባርሮ ታማኝ የህወሀት ታጋዮችን በመተካት ኮርፖሬሺኑን የለየለት የስለላ ተቋም አድርጎታል። ስለሆነም ዛሬ ብዙ የአፍርካ አገሮች ትልቅ ግስጋሴ ያደረጉበትና የዜጎቻቸዉን ህይወት የለወጡበት ዘርፍ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎችን እየሰለለ አገረን የመረጃ ጨለማ ዉስጥ የከተተ ተቋም ሆኗል።
ባላፉት ሁለት አመታት የኢትዮቴሌኮም ማነጅመንት ኤን አንድና ኤን ሁለት በሚባሉ ሁለት ከፍተኛ የአስተዳደር እርከኖች ተከፍሎ በሁለቱም ከፍተኛ የአመራር እርከኖች ዉስጥ የሰዉ ኃይል ተመድቧል። ይህ በከፍተኛ ማነጅመንት ደረጃ የተመደበዉ የሰዉ ኃይል ኢትዮጵያዉያንንና የፈረንሳይ ዜጎችን የሚያጠቃልል ነዉ። በኤን አንድና በኤን ሁለት የማነጅመንት ደረጃ የስራ ድርሻ የተሰጣቸዉ ኢትዮኦጵያዉያን በቁጥር 54 ሲሆኑ ከዚህ ዉስጥ 46.3 በመቶ ወይም ሃያ አምስቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በዚህ ከፍተኛ የማነጅመንት እርከን ዉስጥ የኦሮሞ፤ የአማራና የተቀሩት ስድሰት ክልሎች ድርሻ በቅደም ተከተል 18. 5 በመቶ፤ 29.6 በመቶና 5.6 በመቶ ብቻ ነዉ። ከሁለቱ የማነጅመንት እርከኖች ዉስጥ ኤን አንድ የሚባለዉ ከፍተኛዉ ሲሆን በዚህ እርክን ዉስጥ ሰምንት የትግራይ ተወላጆች ሲኖሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች እያንዳንዳቸዉ ሁለት ቦታ የያዙ ሲሆን በዚህ ከፍተኛ የአመራር እርከን ዉስጥ ከተቀሩት ስድስት ክልሎች የተመደበ አንድም ሰዉ የለም።
ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 194 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያለቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም። ሌላም መራራ ሀቅ አለ። 66 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ ዜጎች ብዛት አራት ብቻ ነዉ (ሁለት ከኦሮሚያ ሁለት ከአማራ)። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5.4 በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል ግን ስምንት ሰዎች ኤን አንድ በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ተቀምጠዋል።
በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ከተቀሩት ስድስት የአገሪቱ ክልሎች የመጡትን ሰዎቸ ስንመለከት የሚታየዉ ስዕል እጅግ በጣም የሚያሳዝንና ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት እያለ ከሚሰብከዉ ስብከት ጋረ የሚጋጭ ነዉ። በ2012 ከኦሮሚያ፤ ከአማራና ከትግራይ ክልል ዉጭ በተቀሩት ስድስት ክልሎች ዉስጥ የሚኖረዉ ህዝብ 25,627,349 እንደሚሆን ይገመታል። ከዚህ ህዝብ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ እድል ያገኙት 0.000012 በመቶ ብቻ ወይም ከእያንዳንዱ 8.5 ሚሊዮን ህዝብ አንዱ ብቻ ነዉ። እንግዲህ ይህንን ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነታቸዉን ተጎናጽፈዋል እያለ የሚናገረዉ።
የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህ ቀደም ወያኔ “የኢትዮጵያ መከላከያ” ጦር እያለ የሚጠራዉን ሠራዊት ምን ያክል የኔ በሚላቸዉ የህወሀት ሰዎች ብቻ እንደሚቀጣጠር የሚያሳይ መግለጫ በመረጃ አስደግፎ ለህዝብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። አሁንም ወያኔ ኢትዮቴሌኮምን ምን ያክል የራሱ የቤት ዉስጥ እቃዉ እንዳደረገዉ የሚያሳየዉን በጽሁፍና በአኀዝ የተፈገፈ መረጃ በዛሬዉ እለት ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን እየገለጸ ከአሁን በኋላም የወያኔን ዘረኝነትና ህግወጥነት የሚያጋልጡ ስራዎችን በተከታታይ እየሰራ ለህዝብ የሚያቀርብ መሆኑን ይገልጻል።

የጥናቱ እጠቃላይ ውጤት

ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication1
ማስታወሻ: ከላይ በስዕሉ የሚታየው እንደተጠበቀ ሆኖ በኢትዮ-ቴሌኮም ቁልፍ የሃላፊነት ቦታወች ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ ወደ 50% የሚሆነው ቦታ የተያዘው በትግራይ ተወላጆች ነው።
ይንንም ለማብራራት ያህል በአሁኑ ሰአት ካለው ጠቅላላ የሃፊነት ቀልፍ ቦታወች 14ቱ በፈረንሳውያን የተያዙ ቢሆንም ከ14 የፈረንሳይ ባለሙያወች ከያዟቸው ቀልፍ ቦታወች ውስጥ 7ቱ በትግራ ተወላጆች እንደሚያዙ ይጠበቃል። ይህም ማለት በትግራይ ተወላጆች የተያዙትን እና የሚያዙትን ቁልፍ የኢትዮ-ቴሌኮም ቦታወች ከተጠቅላለው 64ቱ የሃላፊነት ቦታቸው ውስጥ 32ቱ በትግራይ ተወላጆች የተያዙ ይሆናሉ። ይህም ማለት ከጠቅላላወ የኢትዮ-ቴሌኮም ቁልፍ የሃልፊነት ቦታቸው ውስጥ ግማሹ ማለትም 47% የሚሆኑትን በትግራይ ተወላጆች የተያዙ መሆናቸው ያሳያል።

የጥናቱ ዝርዘር ማብራያ

በዚህ ሰነድ ላይ የተጠቃለሉት ስሞች በኢትዮ ቴሌኮም ዋና መስሪያ ቤት ዉስጥ በሁለት ከፍተኛ (N1 & N2) የአመራር እርከኖች ዉሰጥ የተመደቡ ሰዎች ስምና የመጡበት ብሔር ስብጥር ነዉ። ባጠቃላይ በሁለቱ የአመራር እርከኖች ዉስጥ 68 ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ አስራ ሰባቱ (N1 ዉስጥ 8 N2 ዉስጥ 9) የፈረንሳይ ተወላጆች ነበሩ። ሆኖም ቀስ በቀስ በተደረገዉ መሸጋሸግ የፈረንሳይ ዜጎች የለቀቁት ቦታ እየተመረጠ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ በመሰጠቱ አሁን በN1 ዉስጥ 5 N2 ዉስጥ 9 ባጠቃላይ 14 የፈረንሳይ ዜጎች አሉ ፤ በቅርቡ አንድ ሌላ የፈረንሳይ ዜጋ በኢትዮጵያዊ የተተካ ቢሆንም ይህ ሠኢድ አራጋዉ የተባለ ግልሰብ አማራ ይሁን ትግሬ ለግዜዉ በዉል ለይቶ ማወቅ አልተቻለም። በእርከን አንድ ዉስጥ ስምንት የትግራይ፤ ሁለት የአማራና ሁለት የኦሮሞ ተወላጆች ሲኖሩበት ከሌሎቹ ሰባት ክልሎች የመጣ አንድም ሰዉ በዚህ N1 በሚባለዉ የአመራር አርከን ላይ አልተመደበም። በአጠቃላይ በ N1 የአመራር አርከን ዉስጥ 17 ሰዎች ሲኖሩ አስራ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን አምስቱ ደግሞ የፈረንሳይ ተወላጆች ናቸዉ። ከአስራ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን ዉስጥ ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። N2 በሚባለዉ የአመራር አርከን ዉስጥ ደግሞ 51 ግለሰባኦች በአመራር ቦታ ላይ የተመደቡ ሲሆን 42 ኢትዮጵያዉያን 9ኙ ፈረንሳዉያን ናቸዉ። ከአርባ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን ዉስጥ አስራ ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ።
ይህ በከዚህ ቀጠሎ የተቀመጠዉ ግራፍ እና ሰነተረዥ የሚያሳየዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የተቀመጡትን ሰዎች የብሔር ስብጥር ነዉ። ግራፉ የሚያሳየዉ ሦስቱን ማለትም ከኦሮሚያ፤ ከአማራና ከትግራይ ክልል የተመረጡ ሰዎችን ለየብቻቸዉ ሲሆን ከተቀሩት ሰባቱ ክልሎች የመጡት ሰዎች ግን ተጨፍለቀዉ አንድ ላይ ነዉ የቀረቡት።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication2ማስታወሻ: ከላይ በሰንጠረዡ የጠቀሰው የህዝብ ብዛት እኤአ በ2007 CSO ያወጣዉን የህዝብ ብዛት መግለጫ ተንተርስሶ በ2012 የኢትዪጵያ ህዝብ ብዛት 90,076, 661 ይሆናል በሚል ግምት የተቀመረ ነዉ።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication3
በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የተቀመጡት ሰዎች የብሔር ስብጥር
ከላይ በተቀመጠዉ የህዝብ ብዛት መሠረት በ N-1 እና በ N-2 የአመራር እርከን ኢትዮ ቴኦኮም ከተመደቡ ሰራተኞች ዉስጥ የሚከተለዉን ገሀድ እዉነት መመልከት ይቻላል። ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 193.9 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያለቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም። ሌላም መራራ ሀቅ አለ። 66.2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ ዜጎች ብዛት 4 ብቻ ነዉ (2 ከኦሮሚያ 2 ከአማራ)። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5.4 በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል ግን 7 ሰዎች N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ተቀምጠዋል።
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ የሚያሳየዉ ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-1 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር ነዉ፤ በዚህ ስብጥር ዉስጥ የፈረንሳይ ዜጎችም አሉበት። በ N-1 አመራር እርከን ዉስጥ ከትግራይ፤ ከኦሮሚያና ከአማራ ብሔረሰቦች ዉጭ ከሌሎቹ የተካተተ ማንም የለም።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication4
ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-1 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር
ከላይ ካለው ሰንጠረዥ ላይ እንደምንመለከተዉ በ N-1 የአመራር እርከን ደረጃ ላይ የተቀመጡ ኢትዮጵያዉያን ብዛት አስራ አንድ ሲሆን ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። የእነዚህን 7 ሰዎች የስልጣን ቦታ ስንመለከት ደግሞ ሁሉም የያዙት ቦታ ቁልፍ ቁልፋዩን ቦታ ነዉ። ለምሳሌ የፕሮግራም ማነጀር፤ ፕሮግራም ዳይረክተርና የቺፍ ፋይናንሻል ኦፊሰርነቱን ቦታ የያዙት የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ የኦሮሞዉና የአማራዉ ተወላጆች በቅደም ተከተል የህግ አማካሪነቱንና የኢዲተርነቱን ቦታ ነዉ የያዙት።
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ የሚያሳየዉ ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-2 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር ነዉ። በ N-2 ከፍተኛ የአመራር እርክን ዉስጥ ዘጠኝ የፈረንሳይ ዜጎች የሚገኙ ቢሆንም በሰንጠረዡ ዉስጥ የፈረንሳይ ዜጎች ቁጥር አልተካተተም (N-2 ከ N-1 ያነሰ ደረጃ ነዉ)።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication5
ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-2 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር
ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ብዛትም ሆነ በተማረ ሰዉ ሀይል ብዛት ከፍተኛዉን ቦታ የያዘዉ የኦሮሚያ ክልል ነዉ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ከፍተኛዉን የመቀመጫ ቁጥር የያዙት የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ናቸዉ። ሆኖም በሰንጠረዡ ላይ እንደምንመለከተዉ ኢትዮቴሌኮም ዉስጥ በN-1ም ሆነ በN-2 ደረጃ በአመራር ላይ ከተቀመጡት መሪዎች ዉስጥ የኦሮሚያ ድርሻ ከክልሉ ትልቅነት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነዉ ወይም ከትንሿ ትግራይ ጋር ሲወዳደር ቁጥሩ እጅግ በጣም አነስተኛ ነዉ። በፖለቲካ ሀይል መስክም ቢሆን እንደዚሁ ነዉ። ህወሀት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ ብዛት 8 ብቻ ነዉ። ሆኖም የፖለቲካዉ ጡንቻዉ 178 መቀመጫ ካለዉ ኦህዴድ ጋር ሲወዳደር ሰማይና ምድር ነዉ። ህወሀት የአገሪቱን ጦር ሀይል፤ ፖሊሰ ሰራዊት፤ የደህንነት ተቋምና የኤኮኖሚ መዋቅሮች ይቆጣጠራል። ኦህዴድ ግን ከሰሞኑ እንደማስተዛዘኛ ከተወረወረለት የይስሙላ ምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ዉጭ ይህ ነዉ የሚባል የፖለቲካ ጡንቻ የለዉም።
ከሦስቱ ክልሎች ማለትም ከአማራ፤ ከኦረሚያና ከትግራይ ክልሎች ዉጭ በሌሎቹ ስድስት ክልሎች ዉስጥ 25,627,349 ያክል ህዝብ እንደሚኖር ይታመናል። ኢትዮቴሌኮም ዉስጥ በ N- 1 ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የእነዚህ ሰባት ክልሎች ድርሻ ሦስት ብቻ ነዉ። እንግዲህ ዜጎች በሞያቸዉ በሚሰሩት ስራ፤ በፖለቲካ ህይል አሰላለፍና በኤኮኖሚዉ ዘርፍ ዉስጥ በሚጫወቱት ሚና እንዲዚህ አይነት አይን ያወጣ አድሎ የሚደረግባቸዉ ከሆነ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፈጠርኩት የሚለዉ እኩልነት ምኑ ላይ ነዉ? የባህል ዘፈን መዝፈን ከሆነ እንደዛሬዉ በቴሉቪዥን አይታይም እንጂ ድሮም እንዘፍናለን።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication6
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication8

ህወሓት አይድንም፤ እያቃሰተ ነው (አስገደ ገብረስላሴ ከመቀሌ)

272d8-599201_480729571949477_370096823_n
‹‹የህ.ወ.ሓ.ት  ትንሳኤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ድላችን የማይቀር ነው ›› ስብሓት ነጋ

በጌታቸዉ  አረጋዊ  የህ.ወ.ሓ.ት ኣባልና የድምፅ ወያነ ጋዜጠኛ  «ውራይና » የሚል በትግርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ለአራተኛ ጊዜ በነሃሴ ወር 2005 ዓ/ም የታተመ መፅሄት ስብሓት ነጋ  የህ.ወ.ሓ.ት   ፈላስፋ ቃለ መጠይቅ ያደረገበት መፅሄት በፅሞና  ኣነበብኩት። የመፅሄቱ ዋና ይዘት   ‹‹ህ.ወ.ሓ.ት እናድናት›› ነዉ የሚለዉ ስብሓት ነጋ በመፅሄቱ የተካተቱ ብዙ ስንክሳራዊ  ሃተታ ተናግሯል ።
  • አሁን ማለት የፈለግኩት በመፅሄቱ የተካተቱ በሙሉ መልስ ለመስጠት አይደለም፡፡ ምክንያቱም የስብሓትን ስንክሳር መልስ ለመስጠት  ከፈለኩ ግዜ አይገኝም  መፅሃፍም  ሊሆን የሚችል ነዉ። በመሆኑም አለፍ አለፍ በማለት  የስብሓትን አንኳር አንኳር ነጥቦች መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ።
ሌላ ይህ ፅሁፍ መልስ ለመስጠት የተገደድኩት የ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ለትግርኛ ቋንቋ  ማዳበርን  በትግርኛ ስነ-ፅሁፍ ለማስፋት ብለዉ በፅሁፍ ቢናገሩ እጅጉን የሚደገፍና የትግራይ ህዝብ መስዋእት ነበር። ይህ ደግሞ ማንም ኢትዮጵያዊ  ይድግፈዋል፤፤
የ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ግን ከረጅም ጊዜ ጀምረዉ ለትግራይ ህዝብ በጠባብነት ለመነሳሳት ሲፈልጉ ወይ መምቻ ሃይል ሊጠቀሙበት ሲፈልጉ የሚናገሩት  የሚፅፉበት ኢትዮጵያዊ አጀንዳ እያለና  ያለ ትግራይ ህዝብ የሚነገር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ አድርገዉ እንደመናገር ፈንታ በድብቅ ይናገራሉ።
ስብሓት ነጋም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሃገራችን ብዙ ደንቃራ ሁኔታዎች ተደቅነውባትና ህዝቡ በብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖለቲካዊ  ችግሮች አጋጥመውት እያሉ ለትግራይ  ለአንድ ክልል ከ4-5 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ለብቻዋ የሚወከል ህ.ወ.ሓ.ት ትንሳኤ መተንበይ ሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ክልሎች … በሂወት ካሉት በታች ከሞቱት  በላይ የሆኑ ህዝቦችና ክልሎች እንደማሰብ ትግራይን ጨምሮ ማለት ነዉ። ለትግራይ ብቻ  ማሰብ ለስብሓት ነጋ ጠባብ ሊያስብላቸዉ የሚችል ይመስለኛል።
በሌላ በኩል የስብሓት ነጋ ትንሳኤ ሙዉታን ሲለን የህ.ወ.ሃ.ት ትንሳኤ ሙታን ለመመለስና የህ.ወ.ሃ.ት  መሪዎች  ከመሰነጣጠቅና ከመክሰም እንዴት እናድነዉ ጭንቀቱ እንጂ የትግራይ ህዝብ ባጠቃላይ የሃገራችን ህዝቦች ብሄር ብሄረሰቦች ከዲሞክራሲና  ሰብኣዊ መብቶች ነፃነትና አፈና አስተዳደር እንዴት እናድናት አይደለም ጭንቀቱ፤፤ ይህ ካልኩ በኃላ ወደ መፅሄቱ ላይ የሰፈረዉ አንዳንድ መልስ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ።
ስብሓት ነጋ በአሁኑ ጊዜ ያለዉ  የህ.ወ.ሓ.ት አመራር ለነዚህ ለአመታት እያጠራቀማቸዉ የቆየ ችግርን በፍፁም ነፃነት በፍፁም አባታዊነት በትክክል ከተረዳቸዉ  መረዳትም ያለበት ነዉ።‹‹የ ህ.ወ.ሓ.ት ትንሳኤ ጊዜ ይወስዳል እንጂ ድላችን የማይቀር ነዉ።›› ይላል ውራይና መፅሄት ነሃሴ 2005 ገፅ 4 ሶስተኛ  አምድ አዲስ መስመር ሁለት
ስብሃት ነጋ ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀዉ  ህ.ወ.ሓ.ት ከነበሩበት ብዙ ችግሮች ሲያሳየዉ የነበረ መገላበጥ የተሳሳቱ ሃገራዊና አህጉራዊ አቋሞች በተለይ ደግሞ በሃገር ሉኣላዊነት የሚመለከት ሃገራዊ ሃላፊነት የጎደለዉ ብዙ ስህተትና ጥቁር ነጥብ  ቢሰራ በፀረ-ደርግ የነበረዉ አቋም የኃላ ኃላ ለስልጣኑና የግዛቱን ማስፋፋት ሲል ያመጣዉ አገር አቀፍ አመለካከት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለጊዜዉ ከፋሽስታዊ   ደርግ አፈና አድኖታል። ተነፃፃሪ ሰላም ያመጣ ይመሰል ነበር ሆኖም ግን   የህ.ወ.ሓ.ት  አመራርና እሱን እሚመስሉ እሱ የፈጠራቸዉ የህ.ዋ.ሓ.ት ስሪት ፓርቲዎች ልክ ደርግ መጀመሪያ ወደ ስልጣን ሲመጣ  ኢትዮጵያ ትቅደም ያለ ምንም ደም እንዳለና  ቀስ በቀስ ወታደራዊ ባህሪዉ አገርሽቶበት ፍፁም ለኢትዮጵያ ህዝብ  ፋሽስትና ፀረ ህዝብ የሆነዉ የህ.ዋ ሕ.ት መሪዎች የትግራይ ህዝብና ልጆቹ በሃገር ደረጃ ደርግ ከተደመሰሰ ብቻ ነዉ ሰላም፣ ፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ ነፃነት፣ የህግ የበላይነት ይመጣል እያለ በመቶ ሺዎች ዜጎች የሰጡትን ደርግን አስወግዶ ወንበሩን ከተቆናጠጠ በኃላ ትላንትና ሽሮ  አለ መረቅ አለ እያለ ወደ እሳት እየማገደዉ የመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከዳ የትግራይ ህዝብ ነበር። ውጤቱ ደግሞ የትግራይ  ህዝብ ሳይሆን መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በአሁኑ ጊዜ አግኝቶት ያለ ምንድነዉ ?
ስደት በየአህጉሩ ተበታትኖ ሞት መታረድ በባህር የአሳ ቀለብ መሆን ሁሉም አይነት መብቶች ማጣት አንድነት መላላት ሉአላዊነቱን መደፈር ነዉ። በተለይ ደግሞ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች አመራር ትንሳኤ መውታን ካልተረጋገጠ የትግራይ ህዝብ አይኖርም  የምትሉት 22 አመት ሙሉ ለውጥ ያላመጣ ችሎታ አሁን በሁሉም ነገር ከፈረጃችሁ በኃላ ‹‹ከገባንበት አዘቅት  አውጡን››  ብትሉን  አቶ ስብሃት ማን ያምንሃል የትግራይ ህዝብ ለናንተ ተንከባክቦ  አምጥቶ ምን ጥቅም አገኘ ። የትግራይ ህዝብ ልጆች ተምረዉ ስራ አጥተዉ የሚላስ የሚቀመስ አጥተዉ የስብሓትና  የጓደኞቹ ልጆች ግን ዘር መንዘራቸዉ በቻይና  በእንግሊዝ፣ ኣሜሪካ  በሌሎች ምእራብ አገሮች ተምረዉ በተቀማጠለ ኑሮ  ነዉ የሚኖሩት፤፤ ይህ እኮ የኢትዮጵያ ህዝብ አበጥሮ ያውቀዋል። ስለዚህ በኔ እምነት በአሁኑ ጊዜ  ስብሓት እንደ ምትለዉ የ.ህ.ወ.ሓ.ት  መሪዎች ትንሳኤ ሙታን    በአሁኑ ጊዜ አያስፈልግም፡፡ አዲስ ትውልድ የአዲሱ ትውልድ የህ.ወ.ሓ.ት አመራር ንኪኪ ያልተበላሸ  ኢትዮጵያዊ አመራር ያስፈልጋል። ይህ ነዉ ሃቁ።
« ስብሃት ነጋ የህ.ወ.ሓ.ት አመራር እዚህ ግባ የማይባለዉ አቅም ተነስቶ ለትግራይ ህዝብ አሳልፎ እጅጉን ጥልቀት ካለዉ አድሃሪ አሰላለፍ አሸንፎ  ለማመን የማይቻል ሃገራዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመፍጠር ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። አሁንም አሁን ያለዉ የህ.ወ.ሓ.ት አመራር  የትግራይ ህዝብ  በመያዝ ህ.ወ.ሓ.ት አይፈጠርም አንልም። ‹‹በመሆኑ ቅድምና በቅርቡ ከህ.ወ.ሓ.ት ማ/ኮሚቴ የወጡ የህ.ወ.ሓ.ት አመራር ነበር እንደ አዲስ በመደራጀት አሁን ላለዉ ማ/ኮሞቴ የሚያግዝበት መንገድ መፈለግ አለበት ይላል»
‹‹ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ›› ይባላል አይደለ አቶ ስብሃት የህ.ወ.ሓ.ት አመራር 40 አመት ሙሉ ቆይቷል፤፤ ስብሃት ነጋም 39 አመት በአመራር ቆይተሃል በህ.ወ.ሓ.ት   ከ1967፣ 1969፣1970 ዓ/ም  የነበሩ የህ.ወ.ሓ.ት  የሃሳብ ልዩነት በፀረ ዲሞክራሲ የግጭት አፈታት   ስብሃትም ነበርክ  በ 1982 ዓ/ም አባይ ፀሃዬ ከስልጣን በማውረድ መለስን ወደ ስልጣን  ካስወጡ አንዱ አንተ ነበርክ ።በ1993 ዓ/ም ከህ.ወ.ሓ.ት መሰናጠቅ  ጋር ተያይዞ  ህ.ወ.ሓ.ት በሁለት አንጃ  ሲሰናጠቅ አንተም ስልጣን ከያዘዉ አንጃ  ጋር ሆነህ ለወጣዉ አንጃ በማውገዝ በዋናነት አንተ ነበርክ። አሁንም በቅርቡ የነበረዉ የህ.ወ.ሓ.ት መተካካት የሚባልም የተኩ ይሁኑ የተተኩ በሁሉም ነገር እዚህ ግቡ የማይባሉ ናቸዉ፤፤ መሪ የነበረ ሲወርድ አንጃ የነበረዉ ነዉ ወንበሩን የያዘዉ፤፤ ስለዚህ  ህ.ወ.ሓ.ት ከሲቪል ብቁ መሪ አላፈራም ብቁ ምሁር የማስጠጋት ባህል አልነበረውምና፤፤ በቅርቡ  ከህ.ወ.ሓ.ት የወጡ አመራሮች በመሰረቱ የሚበቃቸው ነገሮች ስለያዙ ነዉ እንጂ ስልጣን ጠልተዉ አይደለም፤፤ እነሱ ቢመለሱም እያቃሰተ ያለዉ ህ.ወ.ሓ.ት ሊያድኑት አይችሉም። አቶ ስብሃት ወንበር ብትይዝም አንደኛ ተቀባይነት የለህም፡ ሁለተኛ እድሜዉም ገፍቷል እነርሱም  በቅን ይሁን በተንኮል እየሰሩ አቅማቸው ተጨርሷል። ስለዚህ በቅርቡ ከ ህ.ወ.ሓ.ት የተቀነሳችሁ ህ.ወ.ሓ.ት ልታገግም ለማድረግ አትችሉም፤፤ ህ.ወ.ሓ.ት እኮ በስም እንጂ በአካል የለችም ይህ ትክክልኛ ነዉ።
በ 1993 ዓ/ም የተገነጠሉ አንጃዎች በስብሀት አይን እነሱ ከተመለሱ ህ.ወ.ሓ.ት ትነሳለች ነዉ እያለ  ያለዉ?
በኔ እምነት የወጡ አንጃዎች አብዛኞቹና የቀረዉ አንጃ የስልጣንና የሃብት ማካበት ልዩነት እንጂ መሰረታዊ የሆነ የህዝብ ጥያቄ አልነበራቸዉም እነዛ የህዝብ ጥያቄ የሃገር ሉአላዊነት አልተከበረም ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች አልተከበሩም በኢኮኖሚ ፖሊሲ፣በፖለቲካዊ አስተሳሰብ(አይዶሎጂ) ልዩነት የነበራቸውና አሁንም ለህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ እየታገሉ ያሉ  ከ3 ሰዎች አይበልጡም።
ሌሎች ግን ትላንትና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣት ግቡ እያሉ ወደ ጦርነት እያስገቡ አዲስ አበባ እንደገቡት እንደጥርስ መፋቂያ ተጠቅመዉ የጣሉት አሁን  በወጣቱ መስዋእት ስማቸዉ ገኖ በአለም አቀፍ ታዋቂነት አግኝተዉ በንግድ አለም ተሰማርተዉ ከነቤተሰቦቻቸዉ በመላዉ አለም እየናጠጡ  ይገኛሉ። በሃገር ውስጥ ያላቸዉ ሃብትም ለዘር መንዘራቸዉ የሚበቃቸዉ ነዉ። ስለዚህ  ስብሃት እያልከን ያለሀዉ እነዚህ አንጃዎች ተመልሰዉ ወደ ህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ  ከመጡ ህ.ወ.ሓ.ትን አድነዉ በሃገራችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ያመጣሉ ነዉ እያልከን ያለሀዉ ? ይህም የዋህነት ይመስለኛል አሁንም 1ኛ የመንግስትን ያህል ሃብት የሰበሰቡ ናቸዉ ፤
ሁለተኛ እድሜም ገፍቷል፤ ሶስተኛ ተቀባይነት የለም፤፤ ስለሆነም እዚህ ላይም የስብሃት አባባል ውድቅ ነዉ።
እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲ ልማት ፍትህ አጥቶ ከላይ እንደገለፅኩት ህዝቡ ተቸግሮ በአለም ተበታትኖ የከፋ ኑሮ ሲገፋ ስለህዝብ ችግር አጀንዳ አንስተዉ ሊነጋገሩስ ይቅርና ጭራሹም በዚህች  አገር ምን ችግር እንዳለ ግምት ላይ አያስገቡም እንዳውም ከዚህ ድሃ ህዝብ የተወለዱ አይመስሉም፤፤ ከልዩ ፍጥረት የተፈጠሩ  ነዉ የሚመስሉት ። እነዚህ  በኔ እምነት በተለያዩ ጊዜ ከህ.ወ.ሓ.ት ተገንጥለውና በመተካካት የተቀነሱ በስልጣን ያሉ  የህ.ወ.ሓ.ት  መሪዎች ቢሰባሰቡ ህ.ወ.ሓ.ትን አክመዉ ለሞት ከመቃሰት አያድኑትም። ስብሃት ነጋ ያልተረዳዉ ነገር ቢኖር ህ.ወ.ሓ.ት የምትባል ፓርቲ አቶ ስብሃት ያለበት ፈራጅ ቡድን በ 1985 ዓ/ም የዲሞክራሲ ጥያቄ የሉአላዊነት  ጥያቄ በማስነሳቱ በግፍ የታሰሩ የተባረሩ በዛ እንደወጡ የቀሩ እለት ነዉ ህ.ወ.ሓ.ት የሞተች  መለስም አንተም በ1993 ዓ/ም ለነበረ  የህ.ወ.ሓ.ት የሁለተኛ አንጃ መሰንጠቅ ለመምቻ ተብሎ ያመናችሁበት ነበር እሱም የ1985 ዓ/ም ታጋዩ ያስነሳዉ ጥያቄ ትክክል ነበረ  ግን ምን ይሁን ኮለፍነዉብላችሃል።
« ስብሃት ነጋ አሁን ደግሞ የ ህ ወ.ዋ.ሓ.ት አባልና የትግራይ ህዝብ ታግሎ  ያመጣውን ስርአት ማክበር ብቻ ሳይሆን ታግሎ ለመጣዉ ስርአት ቀዳሚ ግንባር በመሰለፍ ሊከብርና ሊያስከብር  ሊያገኝ ሌሎችም እንዲያገኙ ማክበር አለበት» በገፅ 4 ሶስተኛ አምድ አንቀፅ ሁለት መስመር 25፤፤                       አቶ ስብሃት የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወገኖች ጋር ታግሎያመጣዉ ስርአት ነበር ግን በናንተ ተቀምቷል፤፤ አይቶ አጥቷል የትግራይ ህዝብ የደርግን ሁሉም አይነት ግፍ ያልፈራ በእናንተ ግን የመግስት ሰራተኛ ነጋዴዉ ፣ አርሶ ሰደሩ ፣ ወዛደሩ፣ ተማሪዉ ፈርቶ ተሸማቅቆ እንዲኖር ተርቦ እያለ አልራበኝም ታሞ እያለ አልታመምኩም ውሃ ጠምቶት አልጠማኝም እንዲል አድርጋችሁታል፤፤ ለባለስልጣን መውቀስ ሂስ  ካደረገ ወደ ላይ አትንጠራራ ብሎ  ጭንቅላቱን ደፍቶ እንዲሄድ  ተደርጓል። ሌላዉ አቶ ስብሃት የትግራይ ህዝብ ታግሎ ያመጣውን ስርአት ፊት ተሰልፎ መጠበቅ አለበት ተብሏል፤፤ የማንና የማን ሃብት ህንፃ ሊጠበቅ ነዉ ይህ ማታለል ነዉ። የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ጊዜ በወንዝ ተከልሎ ማሰብ ትቶ ተሻግሮ በሩቅ አይቶ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉኣላዊነት ነዉ ሚታየዉ ያለዉ እምቢ ለጠባብነት እያለ ያለዉ።
የአቶ ስብሃት ጠባብ አመለካከት  አልፏል ድሮም የህ.ወ.ሓ.ት አፈና ደርግን ለመጣል ሲባል ተሸፍኖበታል እንጂ ስለ አንድነት ጉዳይ ስለ ባህር በር ስለ ኤርትራ ጉዳይ ብዙ ጥያቄ አንስቶ እነ ስብሃት ምን አይነት መልስ ትሰጡት እንደነበራችሁ ራስህም ታውቀዋለህ። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ሃሳብህን አይቀበልህም።
ሌላዉ የትግራይ ህዝብ ይሁን መላዉ የኢትዮጵያ ህዝባችን  የህ.ወ.ሓ.ት በ1983 ዓ/ም ደርግን አስወግዶ ወንበሩን ሲቆነጠጥ የህ.ወ.ሓ.ት  መሪዎች ህዝቡ ታግሎ ባመጣዉ ድል ተጠቅማችሁ ከደርግ ተለይታችሁ ለመታየት ብዙ ዲሞክራሲ የሚመስሉ መግለጫዎች ትሰጡ ነበር።በመሬት ላይ የነበራችሁ ፖሊሲም ለምእራብ ሃገሮች ፖለቲካ ፍጆታ ብላችሁ ነፃ ኢኮኖሚነት መብት የምትጠብቁ ትመስሉ ነበር ቀስ በቀስ ግን የፀረ ዲሞክራሲ ባህሪያችሁ አገርሽቶበት እንደ ወትሮ ሆናችሁ የቻይና ታማኝነታችሁ አረጋግጣችሁ መሬት ለምን የህዝብ አላችሁ።
በአሁኑ ጊዜ የህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መሪዎች የከተማም ሆነ የገጠር መሬት የኔ ነዉ 90 ሚሊዮን ህዝብ የመሬት ጢሰኛ ነህ ብላችሁ ፍፁም ዜግነቱ ቀምታችሁታል፤፤ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኑ እንዲጠራጠር አድርጋችሁታል፤፤ ታዲያ ስብሃት ነጋ የትግራይ ህዝብ የታገሉለት  አላማ እንዳይቀማ ፊት ተሰልፎ ለህ.ወ.ሓ.ት ይጠብቃት ስትለን በ 17 አመቱ የትጥቅ ትግል የከፈለዉ ሂወትና ቁሳቁስ ያልጠቀመዉ አሁን እንደገና የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ልጆቻቸዉ እንዲሁም ምንጩ የማይታወቅ የሰበሰቡት ሃብት ሊጠብቅ ነዉ የምትፈልገዉ? አይታሰብም ዋና ችግራችሁ ለሁሉም ስራችን መስተዋታችን ህዝብ ነዉ ስትሉ የነበረ በመክዳት በአሁኑ ጊዜ ህዝብ ምን ይላል የሚል መረጃ አለመኖራችሁ ነዉ እንጂ ህዝቡ ለውጥ ፈልጓል የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ልክ ከባህር እንደወጣ አሳ ከልብ አውጥቶ ጥሏቹሃል። አሁን ግን ትልቁ ችግር ሆኖበት ያለዉ የመንግስት የፍትህ አካላት በደህንነት በፖሊስና ፌዴራል ፖሊስ በአቃቤ-ህግ ታፍኗል፤፤ በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን ያለዉ አስተዳደር በአዋጅ ወታደራዊ አስተዳደር ስላልተባለ ነዉ እንጂ በተግባር ወታደራዊ አንባገነናዊ ስርአት ነዉ ያለዉ። ታዲያ ስብሃት ነጋ ለትግራይ ህዝብ ለዚህ ስርአት ጠብቀዉ  ነዉ እያለ ያለዉ  ደግሞ በባዶ ሆዱ እንዴት ብሎ ይታሰባል;
« የትግራይ ህዝብ ታግሎ የሚያታግለዉ  የሚጠቅመዉ አብዮታዊ መሪ ድርጅት ያስፈልጋል›› ስብሃት ነጋ ገፅ 4 በአርእስት የተፃፈ» (በትግርኛ ህዝቢ ትግራይ ተቓሊሱ ዘቃልስ ዝጠቕሞ ወያናይ ውድብ ክረክብ ይግበኦ)
ስብሓት ነጋ  እያልከን ያለሀዉ የትግራይ ህዝብ ታግሎ የሚያታግለዉ አብዮታዊ  ፓርቲ ያስፈልገዋል ነዉ። በዚህ አባባል እኔም እስማማለሁ አዎን አብዮታዊ ፖለቲከዊ ድርጅት ያስፈልገዋል ።ግን የትኛዉ አብዮታዊ ፓርቲ; ህ.ወ.ሓ.ት ከማቃሰት እናድነዉ ከሆነ በትግራይ ክልል ህዝብ ይሁን ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ. ኣ.ዴ.ግን አይፈልግም፤፤ በወታደራዊ አስተዳደር ስለታፈነ በምርጫ ጊዜ ለፈለገዉ ቦታ የመረጠዉ ካርድ ስለተቀማ ከክልል እስከ ጎጥ  በአንድ ለአምስት የደህንነት መዋቅር ስለታፈነ ብቻ ነዉ። ስለዚህ ከእንግዲህ  የትግራይ ህዝብ ለስብሃትና ጓዶቹ ሎሌ ሆኖ አይኖርም፤፤ በሰላማዊ መንገድ ትግሉን በማስቀጠል የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ሉአላዊነቱ ሊያረጋግጥ ነዉ።
ግን አቶ ስብሀት ነጋ ሁሉ ግዘ ለትግራይ ህዝብ እየተቆረቆርክ መስለህ የጠባብንት አመለካከት ታሰራጫለህ፤፤
ይህንን ያልኩበት ምክንያት 90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ በአስከፊው የህ.ወ.ሀ.ት ኢ.ህ.አ.ደ.ግ መሪዎቹና ካድረዎቹ አፈና መዳፍ ገብቶ እያለ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ማሰብ ፋንታ የትግራይ ህዝብ ለብቻው ነጥለህ ለበሰበሰ ስርአታችሁ ዘበኛ ማድረግ አያዋጣም፤፤ የትግራይ ህዝብም አይቀበለውም፤፤ ለአንድነቱ የቆመ ነውና፤፤
‹‹ «ስብሃት ነጋ ሙስና ዋነኛዉ የስርአታችን አደጋ ነዉ›› ብሎ የተነሳ ፓርቲና መንግስት ለምን ወደዚህ የተበላሸ  ሙስና አደጋ ደረሰ የሚል ጥያቄ በብቃትና በቆራጥነት  ካለተፈታ  በዚህች አገር ምን ሊፈጠር ነዉ? ሙስናና ብልሹነት ከቁጥጥር እየወጣ ነዉ የሚል ጥቆማ ከአገር ውስጥም ከውጭ አገር ለሚመለከተዉ ጥቆማዉ እንደ ጎርፍ ይፈስ ነበር በጊዜዉ ግን ሰሚ ጆሮ አላገኘም » ›› ውራይና መፅሄት ገፅ 3  አንቀፅ አንድ መስመር ሰባት፤፤
አቶ ስብሃት እንደምትለዉ    ህ.ወ.ሃ.ት ከ1984 ዓ/ም ጀምሮ በስብሰባ በብዙሃን መገናኛ ስለሙስና ብዙ ይናገር ነበር፤፤ በተለይ ደግሞ የህ.ወ.ሃ.ት አመራሮች ሙስና በናንተ ነበር የተጀመረዉ፤፤ ምርጥ ቤት ለራስህ ለዘር መንዘርህ ለአንድ መሪ ከሁለት እስከ 3( 4 መኪና) መያዝ ነዳጅ ያለገደብ መጠቀም የራስህና የቤተሰብ ህን ኑሮ ማሻሻል ከውርሃዊ ገቢህ ጋር የማይመጣጠን በየቀኑና በየሳምንቱ በሂልተን በሶደሬ መዝናናት የቤት እቃዎች በሚሊዮን  የሚቆጠር ገንዘብ ወጭ ማድረግ ከባለሃብቶች ገፀ በረከት ስጦታ መቀበል፣ በየጊዜዉ ብዙ ወጭ  በማውጣት ግብዣ ማድረግ ልዩ ፍጡር ሆነህ መታየት ረጅም ሳይጓዙ  ወደ ይኩራሩበት የነበሩ  የንጉሳዊ ቤተሰብ ቅምጥል ኑሮ እነሱን አልፈዉ ሄደዉ በየምሽቱ  በአስር ሺህ ብር የሚቆጠር  ገንዘብ ማባከን በልጅ ጥምቀት ፣ የልደት ቀን ሰንጋዎች ማረድ በዊስኪ መራጨት  ጊዜ እየገፋ ሲሄድ በግልፅ የማይታወቅ  ሃብት  ማካበት በተለያየ መንገድ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች መገንባትና ስም ቀይሮ ብዙ የደረቅና የፍሳሽ የጭነት መኪና መግዛት ሌላ ቀርቶ የመሪዎች ሚስቶች ውጭ አገር ሄደዉ እንዲወልዱና  ለወደፊት በዛው የውጭ አገር ዜግነት ይዘዉ ቆይተዉ መሸሻ ቦታ  ማዘጋጀት ብሎም ቤት መስራት ስልጣንህ ተጠቅመህ ዘርመንዘርህ ውጭ መላክ ነበር። ለዚሁ ማረጋገጫ በቻይና በ10 ሺህ  የሚቆጠሩ የመሪዎች ልጆች የሚማሩ ኣሉ። ሌላ ዋነኛዉ በመንግስት ስራ አመዳደብ በሞያ እንደመሆን በዘመድ አዝማድ በጋብቻ በጓደኝነት አድርገህ ስራው በሞኖፖል መያዝ ሌላ ስራተኛ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ማየት ነበር።
ኣቶ ስብሃት ይመሩት የነበረ የኢፈርት ድርጅቶች በአስር ቢሊዮን የሚቆጠር ካፒታል ያላቸውም ለስሙ በህዝብ ስም እየተነገደባቸው ለሙሰና ብልሹነት የተጋለጡ ሆነው የሄዱት ስፍር ቁጥር የላቸውም፤፤ ሁሉም   ለስሙ በህዝብ ስም እየተነገደባቸዉ ለሙስናና ብልሹነት የተጋለጡ ሆነዉ የኦዲት ቁጥጥር የለባቸዉም፤፤ ሁሉም ገንዘቡን የሚያውቀዉ ስብሃት ነጋ ነበር፤፤ ቁልፉም እሱ ነበር ኃላም ስብሃት ሲለቅ ስዬ አብርሃ ቀጥሎ ኣባዲ ዘሞ በመጨረሻም አዜብ መስፍን የበላይ ጠባቂ ጠ/ሚኒስቴር መለስ ነበሩ።ስብሃት ነጋም እስከአሁን የግዙፍ ካምፓኒ የወጋገን ባንክ ቦርድ ዳይሬክተር ነህ፤፤ ይህ ባንክ ከፍተኛ  አክሲዮን የህ.ወ.ሃ.ት ሃብት ነዉ ስንት ካፒታል አለዉ ማን ይቆጠቀጠረዉ የሚለዉ መልሱ ለስብሃት ነጋ ነዉ።
እንግዲህ የሙስና ጉዳይ ከተነሳ በዘመነ ህ.ወ.ሃ.ት ስርአት ሙስና በኢትዮጵያ አደጋዉ እንዲስተካከል አስተያየት የሚሰጡ ቅን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የውጭ አንባሳደሮች መንግስታት የአለም ባንክም ምክር ይሰጡ ነበር፤፤ ለዚህ አስተያየት ከአቶ ስብሃት ጀምሮ ሁሉም የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሰሚ ጆሮ አይሰጡትም ነበር። ምክንያቱም ሁሉም የተነካኩ  ናቸዉና።  ስለዚህ ስብሃት ነጋ ‹‹የሙስና መረጃ እንደጎርፍ ይፈሱ ነበር ግን ሰሚ ጆሮ አልነበረም፤፤›› ስትለን አንተስ ሙስና ኣለ ብሎ መረጃ የሰጠህ ቅን ኢትዮጵያዊ እንደ ጠላት አይተህ ከስራ አላባረርክም ? በጥላቻ እንዲታይ አላደረክም ይህ አባባል ማታለያ ነዉ ። አንድ ነገር በዚሁ እድሜ በገፋበት በምፅተአለም ዋዜማ አገራችን በሰዉ ሃብት የሃገር ሃላፊነት የማይሰማቸዉ ጅቦችና ከወደመችና የአገራችን አንጡራ ሃብት ውጭ አገር ከሰፈረ በኃላ ሆነ ራሱ ግን የስብሃት ልግም እንጂ አብዮታዊ ነት አያሳይም።
ስብሃት ነጋ ‹‹የተበላሸ ሙሰኛ ሁሉ በየደረጃዉ መታረም አለበት ስርአቱን  በመጣስ ቤት ከፍቶ የሰረቀ መሆኑ እያወቀና እየሰማ  እርምጃ ያልወሰደ በከፍተኛ ደረጃ ጥፋት መጠበቅ አለበት። ያ ቤት ከፍቶ አግኝቶ ትንሽ የቀመሰ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ የሚስተካከል መሆኑ ህዝቡን ለማረጋጋት ያስችለዋል» ውራይና መፅሄት ገፅ 5 3ኛ አምድ አንቀፅ 3 መስመር አንድ
አቶ ስብሃት ነጋ አንደኛ ነገር አንተን ከሙስና ነፃ እንደሆንክ  በሁለተኛ ደግሞ ቢሊየን የሰረቀና ሚሊዮን የሰረቀ እኩል መታየት  የለባቸዉም፤፤ ምክንያቱም ትንሽ ለሰረቀ ቀላል ቅጣት ከሰጠኸዉ ህዝብ ሊረጋጋ ይችላል ብለሀናል። የትኛዉ ህዝን ነዉ? ግልፅ አይደለም፤፤ አሁን እኮ ዋና ሌባ የሚባለዉ ከቀበሌ እስከ ፌዴራል ያለዉ ባለስልጣን በሙስና ተራክሷል፤፤ ይህ መዋቅር ከህዝቡ ከ3 እስከ 5%  ነዉ የሚሆነዉ ቅጣቱ ይቀላል  ምትለዉ ያለህ ለማነዉ? ለምስ ነዉ የሚቀልበት? በኔ እምነት አቶ ስብሃት የምትለን ያለ ታች  ሆኖ ህዝብ ያሰቃዩ ሎሌዎች ከተመቱ ለወደፊቱ በየመድረኩ እጅ እያወጣ የስ እያለ የሚውል ሰዉ አናገኝም፤፤ በምርጫ ጊዜ ኮረጆ የሚሰርቅ የለንም፤፤   ከሚል የመነጨ ነዉ ትንሽ  የሰረቀ ይማር የምትለን ያለህ በሌላ በኩል ትልቁ ብልሹ ሙሰኛም ይመታ ስትለን ቁርጠኝነትህን አይደለም የሚያመለክት፤፤  አቶ ስብሃት ነጋ ትልቁ የሙስና ግንድ  ከተመታ አንተም ልትመታ መሆንህ በመረዳትህ ነዉ የተድበሰበሰ ትንታኔ የተናገርከዉ። በኔ እምነት ግን በኢትዮጵያ ትልቁ ጠላት ሙስናና ብልሹ አስተዳደር ከግንዱ ብቻ ሳይሆን ከስሩ ከቀበሌ ጀምሮ መቆረጥ አለበት እላለሁ። እዚህ ላይ ግን የስብሃት አሰራር እማውቀዉ ነገር አለ፤፤ ስብሃት በስሙ ገንዘብ ይሁን ንብረት የለዉም። ብዙውን ጊዜም የሆነ ወጭ አይፈርምም ነበር፤፤  ሁሉም ነገር በውክልና ነበር የሚያሰራዉ ። ስለዚህ ትንሽ የሰረቀ ይማር ሲለንም  እነዛ ወኪሎቹ እንዳይቆረጡ ካለዉ ስጋት ነዉ። የገንዘቡ ጎተራም ከነሱ ነዉ በስብሃት ወንድሞች ዘርመንዘሩ ስም የተሰሩ ህንፃዎች ምንጫቸዉ የማይታወቅ ሃብትም አላቸዉ።
ሌላዉ ስብሃት ነጋ ስለ ሙስና መረጃ ሲሰጥ ሰሚ ጆሮ አልነበርንም ብለህናል፤፤ ማነዉ የማይሰማ በግልፅነት ልትነግረን አትችልም ማነዉ ለሙስና ጨካኝ ያልሆነ ጠ/ሚኒስቴር? ውጭ ጉዳይ? መከላከያ ሚኒስቴር? የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ? ደረጃ መዳቢዎች? ያገር ውስጥ ገቢ ደህንነት? የከተማ ልማት? የአዲስ አበባ ከንቲባ ዳይሬክተር? እመቤትዋ የጥረት ዳይሬክተር? የወጋገን ዳይሬክተር? የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ሚኒስትሮች? የክልል ውሃ ሃብት ኢንተርፕራይዝ ሃላፊዎች ? የስኳር ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር? የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፓርቲዎች ናቸዉ ታዲያ አቶ ስብሃት ከፍተኛዉ ሙሰኛ ( ትልቁ) ቦታ ነዉ የሚገኘዉ  ብለሃል፤፤ ከነዚህ የተኞቹ ናቸዉ ሙሰኞች፤፤ የአቶ ስብሃት አሽሙር አነጋገር 40 አመት ጊዜ ስለፈጀብህ በአንድ አረፍተ ነገር ይቅርና የማያውቅህ እኔም  በአስር የሚቆጠሩ አመታት  አብረን  ተቀምጠን አሽሙርህ ሊረዳኝ አልቻለምና ለዚህ ትውልድ አሽሙር ከምናወርሰዉ ግልፅነትን እናውርሰዉ።
አቶ ስብሃት አንድ ጥያቄ ግን ልጠይቅህ  በዚህ ፅሁፍ ላይ ያሰፈርከዉ ለትግራይ ህዝብ ብቻ ታግሎ የሚያታግለዉ መሪ ድርጅት ያስፈልገዋል ብለሃል በሌላ በኩል ደግሞ ህ.ወ.ሓ.ት እናድን ትላለህ እዚህ ላይ ሁለት ነገር እንድመለከት አድርጎኛል።
1ኛ ለትግራይ ህዝብ ብቻ ለምን አዲስ መሪ ድርጅት ያስፈልገዋል ? ተበላሽቶ ያለዉ የኢትዮያ ህዝብ መሪ ነኝ የሚለዉ ህ.ወ.ሓ.ት  ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ክህመሙ ካላጋገመ  ህ.ወ.ሓ.ት ብቻውን አክመህ ይድናል ወይ ? በሙሉ ተሟል ነውና ወይስ አዲስ የትግራይ መሪ ፓርቲ በመመስረት ወደ ዱሮ የነበርክበት አስተሳሰብ ነፃ  ( ትግራይ ትግርኚ) የሰሜን ኢትዮጵያ መንግስት ለመመስረት አስበህ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል፤፤ አባባልህ ለብዙ ዜጎች  የተብራራ እይደለም፤፤ ደግሞ በቅርብ ጊዜ አሜሪካ ሄደህ ኤርትራዊ ነኝ ከማለትህ እጅጉን ተጠራጠርኩህ፤፤
2ኛ ለምን ህ.ወ.ሓ.ት  ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግና አጋሮቹ እናድን ተበላሽተዋልና ብለህ በሃገር ደረጃ ላሉ ጓዶች ችግር ማየት ለምን ተሳነህ ? ወይ  የህ.ወ.ሓ.ት  መሪዎች ብቻ ነዉ የታመማችሁት ? አሁን ያለዉ ችግር እኮ  የህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ መሪዎች በሙስና መበላሸትና የመበስበስ አደጋ ነዉ አጋጥሟችሁ ያለዉ፤፤         አቶ ስብሃት በጥልቀትና በስፋት ብታስብበት፤፤ በአሁኑ ጊዜ  ህ.ወ.ሓ.ት   ብዙ ነገር ተበላሽቶባቸዋል፤፤ አንድ እርምጃ ለመራመድ ተስናችሁ በመቃሰት ላይ ናችሁ፤፤ በሰለጠኑ አገሮች እንደምናየው ከሆነ ይቅር እና እናንተ በስብሰባችሁ እንዳላችሁት ስብሰባዉ አንድ ቃል በውሸት ተናግረዉ ህዝብ ካወቃቸዉ ወይ ባገራቸዉ ከባድ ወንጀል ከተፈፀመ ከስልጣን ይወርዳሉ፤፤ እናንተ ግን አገር ያህል የባህር በር የሌላት አስቀርታችሁ የዘሂግ  ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸንፋችሁ እያላችሁ አሸንፈናል ውሳኔዉ የኛ ነዉ ብላችሁ በመድረክ ዋሽታችሁ ይሀው ቁማችሁ ትሄዳላችሁ። በተጨማሪ የመላው ህዝብ ተቃውሞ እልባት ለማድረግ አልቻላችሁም፤፤ ይህም ከስልጣን ያወርዳል፤፤ እንደ ጃንሆይ ተጎትታችሁ ከወንበሩ ከምትወርዱ ለምን ይቅርብን ብትሉና ህዝብ የፈለገዉን መሪ ቢመርጥስ ?
ስብሃት ነጋ  ከአሁን በኃላ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ከህመማችሁ አገግማችሁ ህ.ወ.ሓ.ት እናድናት ማለትህ የዋህነት ነዉ። ዋና ችግርህ የህዝብን ፍጎትና ልብ ትርታ ኣለመረዳትህና የትግራይ ክልል ህዝብ ከህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች የተፋታ መሆኑን አልደረስክበትም፤፤ በሸራተን ሆነህ ስለ የትግራይ ህዝብ ከመናገር እስቲ ወደ ገጠር ህ/ሰብ ስሜቱን አጥና ።  እናንተ  ህዝቡን ለማደናገር ብላችሁ የምትናገሩትና የምትሰሩት  አበጥሮ ያውቃልና።