Tuesday, 3 December 2013

የኢህአዴግ የድርድር ጥያቄና የግል እይታዬ – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ) | Zehabesha Amharic

የኢህአዴግ የድርድር ጥያቄና የግል እይታዬ – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ) | Zehabesha Amharic

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

አውሮፕላኑ ቅዳሜ ጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ደርሶ ከተርሚናሉ ስወጣ፣ ተጠራጥሬ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ የድሬ የጠዋት ፀሐይ ከተለመደው ንዳዷ ጋር የአዲስ አበባን የቀትር መራራ ፀሀይን ታስከነዳለች፤ እናም አጥበርባሪ ጨረሯን ያለምህረት ስትለቅብኝ፣ ጓደኛዬ መኪና ይዞ እቦታው እስኪደርስ መጠበቁ በገዛ ፍቃድ መለብለብ ስለመሰለኝ፣ በቀጥታ ከተደረደሩት ታክሲዎች አንዱን ይዤ ወደ ከዚራ አመራሁ፤ ድሬ የሄድኩት በዋናነት ከማህበራዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት በመሆኑ ሊቀበለኝ የተዘጋጀውን ጓደኛዬን ደውዬ ከማውቃቸው የአንዱን ሆቴል ስም ጠቅሼ እዚያ እንድንገናኝ ነገርኩት፡፡

Journalist Temasegan Dasaleg
የሆቴሉ ፍተሻ ከወትሮው ጠንከር፣ ጠጠር ያለ በመሆኑ ትዕግስትን ይፈትናል፡፡ እንዲህም ሆኖ ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ማረፊያ ክፍሎች በሙሉ መያዛቸው ተነግሮን ቀኝ ኋላ ለመዞር ተገደድን፤ ይሄኔም ነው የጓደኛዬ ፊት ልውጥውጥ ሲል ያስተዋልኩት፤ ጭንቅላቴን በማነቃነቅ በምልክት ምን እንደተፈጠረ ጠየኩት፤ ለአፍታ አመንትቶ ከፊት ለፊታችን በግምት አስር ሜትር ርቀት ላይ ወደቆሙ ሁለት ሰዎች ጠቆመኝ፤ ልብ ብዬ አየኋቸው፤ ሁለቱንም ከዚህ ቀደም አይቻቸው አላውቅም፤ ደግሞም በዙሪያችን ከሚርመሰመሱ ሰዎች የተለየ ምንም አይነት ሁኔታ ላስተውልባቸው አልቻልኩም፤ እናም ወደ ጓደኛዬ ዞሬ በግርታ ግንባሬን ቋጥሬ ጥያቄ በተሞላ ዓይን አተኮርኩበት፤ ጓደኛዬም ከሁኔታዬ እንዳልገባኝ ተረድቶ ከሹክሹክታም ዝቅ ባለ ድምፅ ‹‹ደህንነቶች ናቸው፣ እየተከታተሉህ ነው›› አለኝ፤ ቢሆኑስ ታዲያ!? በግዴለሽነት ትከሻዬን እየሰበቅሁ ‹‹ለራሳቸው ጉዳይ መጥተው ሊሆን ይችላል›› ብዬው ወደ ሌላ ሆቴል አቀናን፤ እዛም የተለቀቀ ክፍል አለመኖሩ ተነግሮን ፊታችንን ከእንግዳ መቀበያው ‹‹ዴስክ›› ዘወር ስናደርግ እነዛ ‹ደህንንቶች› ቆመው ተመለከትኳቸው፡፡ አሁን ከልምዴ በመነሳት ክትትል ሊሆን እንደሚችል ለማመን በተቃረበ ጥርጣሬ ተውጬ ሌላ ሆቴል ደርሰን ክፍል ጠየቅን፤ በለስ ቀናንና የሆቴሉን መስፈርት አሟልቼ ሳበቃ ጓደኛዬን ቡና ቤቱ ውስጥ እንዲጠብቀኝ አድርጌ፣ ክፍሉን ከተረከብኩ በኋላ ሻንጣዬን አስቀምጬ፣ ገላዬን ተለቃልቄ፣ ልብስ ቀይሬ ደረጃውን መውረድ እንደጀመርኩ ከሰዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገጣጠምኩ፡፡
የጭንቅላት ሰላምታ ሰጥቼ አለፍኳቸው፤ ምላሽ የለም፤ ፈገግ አልኩ፡፡ ከወዲሁ የሰሞኑ ምስራቅ ኢትዮጵያ አክራሞቴ ምን ሊመስል እንደሚችል አሰብኩና፣ በልጅነቴ ከሰፈር ማቲዎች ጋር የምንጫወተውን የአኩኩሉ ድብብቆሽ አስታውሼ፣ በድጋሚ ለራሴ ፈገግኩ፡፡
ገና ከአዲስ አበባ ስነሳ ማህበራዊ ጉዳዬን ስጨርስ የድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሶማሌ ክልልን ወቅታዊ የፖለቲካ ትኩሳት ለማዳመጥ ለተጨማሪ ስድስት ቀናት የሚያቆይ ፕሮግራም አስቀድሜ ይዤ ነበር፤ ከአራት ቀን ቆይታ በኋላም ቀጥታ ወደዚሁ ስራዬ ነበር የገባሁት፡፡ ለጉዳዩ ትኩረት እንድሰጥ ያደረገኝ በቅርቡ ሐረር ከተማ ውስጥ በተከበረው ‹‹የዓለም የመቻቻል ቀን›› ላይ በክልሉ የተንሰራፋው መድልዎና የሐብሊ ተፅዕኖ ተደብቆ፣ ፍትሐዊ አስተዳደር የሰፈነ ለማስመሰል መሞከሩ፤ እንዲሁም ህዳር 29 ቀን በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ (ጅግጅጋ) የሚከበረውን ‹ስምንተኛው የብሔር ብሔረሰብ ቀን›ን አስመልክቶ አካባቢውን ከዋጠው ስጋት በተቃራኒው መንግስት እየነዛ ያለው የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ከተጨባጩ እውነታ ጋር ለመፈተሽ ፍላጎት አድሮብኝ ነው፡፡
ፊታችሁን ወደ ምስራቅ…
ምስራቅ ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ የ3ሺ ዓመት ታሪክ ዕኩሌታውን ሰላምና መረጋጋት የተሳነው ከመሆኑም በላይ፣ ለማዕከላዊ መንግስት የስጋት ምንጭ ሆኖ ነው ዛሬ ድረስ የቀጠለው፡፡ ከአቶማን ተርኪሽ ወታደሮች እስከ አል-ሸባብ ሰርጎ ገቦች ድረስ መተላለፊያ ‹‹ኮሪደር›› ሆኖ አገልግሏል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ ሶማሊያውያን የዘር ግንድ ከጐረቤት ሀገራት ሶማሊያና ጅቡቲ ጋር የሚተሳሰር መሆኑና የሃይማኖትና የኢኮኖሚ ምንጭም ተመሳሳይነት አካባቢውን በበቂ ደረጃ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንዳደረገው የፖለቲካ ተንታኞች ያምናሉ፤ ነዋሪዎቹ በቀላሉ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው እየተዘዋወሩ የሚኖሩ መሆናቸውም ሌላው ችግር እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡
ቅኝ ገዥዎቹ የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው አካባቢውን ‹ፍሬንች ሶማሌ ላንድ›፣ ‹ብሪታኒያ ሶማሌ ላንድ› እና ‹ኢታሊያ ሶማሌ ላንድ› በሚል ከፋፍለው ማስተዳደራቸው፣ ከሶማሊያ ነፃነትም በኋላ የሞቃዲሾን ቤተ-መንግስት የተቆጣጠሩ ገዢዎች ‹ታላቋን ሶማሊያ እንመሰርታለን› በሚል ቀቢፀ ተስፋ ከአንድም ሶስቴ የኢትዮጵያን ወሰን ተሻግረው የኃይል ወረራ መፈፀማቸው የአካባቢውን ውጥረት ይበልጥ አባብሶት ነበር፤ ከዚያም ባሻገር የዚያድባሬ ሶማሊያ መፈራረስም የቀጠናውን ሠላምና ፀጥታ ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታል፡፡
በዚህ ሁሉ ከባቢያዊ ውጥረት እየታመሰ እስከ 1983 ዓ.ም. ድረስ በአንድነት በሐረርጌ ክፍለ ሀገር ስር ሲተዳደር የቆየው የምስራቁ የሀገራችን ክፍል፣ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ ባነበረው ‹‹ፌደራሊዝም›› በሶስት ሊከፈል ችሏል፤ ‹‹የሶማሌ እና ሐረር ክልል›› እንዲሁም ‹‹የድሬዳዋ አስተዳደር›› በሚል፡፡ ይህ ሁኔታም ከዚህ ቀደም በውጭ ተፅዕኖ ይተራመስ የነበረውን ‹ጂኦ-ፖለቲክስ› ብሔር ተኮር ለሆነ ተጨማሪ አዲስ ቁርቁስ አጋለጠው፡፡ በአናቱም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ኦጋዴን፣ ጎዴ፣ ደጋሀቡር፣ ቀለፎን የመሳሰሉ ከተሞች ክልሉን ‹እንገነጥላለን› የሚሉት የኦጋዴን ብሔራዊ ግንባር ታጣቂዎች መርመስመሻ መሆናቸው አካባቢውን የስጋት ቀጠና አድርጎታል፤ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ድሬዳዋ ላይ ያነጋገርኳቸውና በሽግግር መንግስቱ ወቅት የአስተዳደሩ አባል የነበሩ አቶ ኡስማን (ለዚህ ፅሁፍ ስማቸው የተቀየረ) ‹‹የዚህ ሁሉ ተጠያቂ ለጣልቃ ገብነቱ ያልተመቹትን የአካባቢው ልሂቃን ‹ለወረራ የመጡ የዚያድባሬ መኮንኖች› እያለ አሸማቅቆ ከፖለቲካው ገፍቶ በማስወጣት ክልሉን ዛሬ ላለው ደካማ አስተዳደር የዳረገው ኢህአዴግ ነው›› ይላሉ፡፡ በግልባጩ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ካሳ ተክለብርሃን የተገፉት ሰዎች ኢትዮጵያዊ አለመሆናቸውን ለ‹‹ዘመን›› መፅሄት የገለፀው እንዲህ በማለት ነበር፡-
‹‹ሶማሊያ የፈራረሰበት ወቅት ስለነበር በጣም ትላልቅ የሶማሊያ ተፈናቃዮች የሰፈሩባቸው ካምፖች ነበሩ፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ አንዱ የስደተኞች ካምፕ የነበረባት አገር ነበረች፡፡ በተለይ አርትሼክ አካባቢና ሌሎች አካባቢዎችም ትልልቅ ካምፖች ነበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የመጡ የዚያኛው ሶማሊያ መኮንኖች፣ ሲቪል ሰራተኞች ኢንጂነሮችና ፓይለቶች ነበሩ፤ በአካል ያገኘናቸው የምናውቃቸው እነዚህ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ጋር የሚለያቸው ነገር ስላልነበረ በአብዛኛው በስደተኛነት ከመጡ በኋላ የአካባቢውን የፖለቲካ ስልጣኑንም ያደራጁት እነሱ ነበሩ፡፡ አንዱ ትዝ የሚለኝ ይሄ ነው፡፡ ይሄንን የኢህአዴግ ሰራዊትና ከላይ የሄደው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሊለየው አይችልም ብቻ ሳይሆን ያ የመጣውን እንዳለ የሚያቅፍ ሁኔታ ነው የነበረው በአካባቢው፡፡ ስለዚህ ለረጅም ጊዜ ያ ኃይል ነው እንግዲህ አዲስ በተፈጠረው አጋጣሚ የታላቋ ሶማሊያን አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሶማሊያ ላይ ለመዝራት ትልቅ ጥረት ያደረገው››
ይህ ክርክር በራሱ ኢህአዴግ ‹‹ፊታችሁን ወደተረጋጋችው ምስራቅ ኢትዮጵያ (ሶማሊ ክልል) መልሱ›› ያለበት አውድ የተለመደው የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ እንጂ አካባቢው የጦርነት ወረዳን ያህል የሚያሰጋ መሆኑን ያመላክታል ፡፡ እናም ከአርቲስቶች እና ጋዜጠኞች እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፊት-አውራሪነት የተካሄደው የጉብኝት ፕሮግራም፣ መንግስት ምንም እንኳ የህዝቦችን አንድነት ‹የማጥበቅ ዕቅድ› የሚል የዳቦ ስም ቢሰጠውም፣ ‹ሶማሌ ክልል ፍፁም ሰላም ነው› የሚል የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ለመንዛት መሆኑን ለመረዳት በአካባቢው ያለውን የፀጥታ አጠባበቅ ብቻ መመልከቱ በቂ ይመስለኛል፡፡
የቦምባስ ዕገታ
ዘንድሮ ለስምንተኛ ጊዜ ‹‹ሕገ-መንግስታችን ለህዳሴያችን›› በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች ቀን›› በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ በመሆኑ በአካባቢው ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት ለመለካት ረቡዕ ህዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ወፍ ጭጭ ሳይል ነበር ድሬዳዋን ለቅቄ ወደ ሐረር ጉዞዬን የተያያዝኩት፡፡ ይህንን ሰዓት የመረጥኩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አበባ ላይ እንኳ ጋብ እየለ የመጣውን የደህንነት ሰራተኞች ክትትል ድሬዳዋ ላይ በየደረስኩበት ሲያንዣብብብኝ፣ በማስተዋሌ፣ ምናልባት ከዕይታ ውጪ መንቀሳቀስ ብችል በሚል እሳቤ ነበር፡፡ መኪናው ከአንድ ቀን በፊት የተከራየሁትና ድሬ ውስጥ ያልተጠቀምኩበት በመሆኑ፣ በስጋት የሚንጠውን የደንገጎ አቀበትም ሆነ ጥንታዊቷን ሐረር ከተማ አቋርጠን እስክናልፍ አንዳች ችግር አላጋጠመንም፡፡
ይሁንና ከሐረር በግምት 80 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በሶማሊያ ክልል የምትገኘው ቦምባስ ከተማ ደርሰን ጥቂት እንደተጓዝን፣ መኪናውን ዳር አስይዞ እንዲያቆም አንድ የትራፊክ ፖሊስ ለሹፌሩ የእጅ ምልክት አሳየው፤ ይሄኔም ነው ድሬ ላይ እንደ ተሰወርኩባቸው እርግጠኛ ሆኜ በልቤ ከሳቅኩባቸው ሁለቱ ሰላዮቼ ጋር ፊት ለፊት የተፋጠጥነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሜን ጠርተው አነጋገሩኝ፤ እኔም ከምንም ነገር በፊት መታወቂያቸውን እንዲያሳዩኝ ጠየቅኩ፤ ሳያቅማሙ አሳዩኝ፤ ወዲያውኑም የአፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ እንዳልሆነ የአነጋገር ዘዬው በግልፅ የሚያስታውቀው አንደኛው የደህንነት አባል፣ ከዚህ በላይ ጉዞውን መቀጠል እንደማልችልና በቀጥታ ወደ ድሬዳዋ መመለሱ እንደሚጠቅመኝ ሊነግረኝ ሞከረ፡፡ ከመገረሜ ብዛት ንግግሩን ለመረዳት ጥቂት ሰከንዶች ፈጅተውብኝ ነበር፡፡
መቼም ይህ ሰው ቀልደኛ መሆን አለበት! አለዛ በገዛ ሀገሬ የት ድረስ መሄድ ወይንም የት ቦታ ጉዞዬን መግታት እንዳለብኝ ሊወስንልኝ ባልደፈረ ነበር፤ ሆኖም ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ምን ማለት እንደፈለገ እንዲያስረዳኝ በትህትና ጠየኩት… ይኼኔ ጓደኛው ጣልቃ ገባና ወደ ጅግጅጋ ለመሄድ ማሰቤን እንደደረሱበትና ወደ ከተማው እንድገባ እንደማይፈቅዱልኝ ቆጣና ኮስተር ብሎ አሳወቀኝ፡፡ እኔም ፈርጠም ብዬ እዚህ ድረስ መጥቼ ጅጅጋ ሳልደርስ እንደማልመለስ ቁርጡን ነገርኳቸው፡፡ ቃለ-ምልልሱ እየከረረ ሲሄድ ማስፈራራቱን ወደ ሹፌሩ አዞሩትና በብርቱ ያዋክቡት ያዙ፤ ይህ ድርጊታቸው ያልጠበቅኩት በመሆኑና የሹፌሩንም ምላሽ አለማወቄ መጠነኛ ድንጋጤ አጫረብኝ፡፡ እንደገመትኩትም ሁኔታውን በፍርሃት ተውጦ ይከታተል የነበረው ሹፌር ትንሽ እንኳ ሳያንገራግር መኪናውን ቆስቁሶ ወደ ሐረር አዞረው፡፡
‹‹ምን ሆነሃል?›› አልኩት በንዴት ጮኽ ብዬ፡፡
‹‹ወንድሜ እኔ ቤተሰብ የማስተዳድር ሰው ነኝ፡፡››

ከ“ፎርጅድ” ፖለቲከኞች፣ባለሥልጣናት፣ ፓርቲዎች፣ … ይጠብቀን!

ሰሞኑን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ጉድ ሰምታችሁልኛል? የመቶ ምናምን መስሪያ ቤቶችን ማህተም፣ ቲተር፣ ወዘተ… በመቅረፅ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ (ሳይማሩ ድግሪ እኮ ነው!)፣ መንጃ ፈቃድ፣ የጋብቻ ሰርተፊኬት፤ ውክልና፣ ሊብሬና ሌሎች ሰነዶችን “ሲያመርት” መክረሙን የሰማሁት ከኢቴቪ የፖሊስ ፕሮግራም ነው፡፡ (ፎርጅድ በፎርጅድ ሆነናላ!) ይሄኛውን የፎርጅድ “ስፔሻሊስት” ከቀድሞዎቹ ልዩ የሚያደርገው ምን መሰላችሁ? ያልደፈረው የመንግስት መስሪያ ቤትና የግል ተቋማት የለም፡፡ (አይዞህ ያለው ማነው?) የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የግል ክሊኒኮች፣ የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች፣ ወዘተ (የማን ቀረ ታዲያ!) ማህተሞችን … ፎርጅድ እየሰራ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያቀርባል ወይም ይቸበችባል፡፡ (ፎርጅድ ፈላጊው “በሽ” ነው ማለት እኮ ነው!)
የሚገርማችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማህተምና ቲተር እንኳን አልቀረም እኮ፡፡ የእነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ቲተርና የኦነግን (አደጋ አለው!) ማህተምም ሲያዘጋጅ እንደነበር ተገልጿል – የፎርጅዱ ስፔሻሊስት፡፡ እኔ የምለው ግን … በ“ፎርጅድ” ሙያ የሚያሰለጥን “ስውር ተቋም” አለ እንዴ? (ከሽብርተኝነት አይለይም እኮ!?) እዚህ አገር ታሪካዊቷን ጦቢያ “ፎርጅድ” የማድረግ አሻጥር (Sabotage) ተጠንስሷል ማለት ነው?
የፎርጅዱ ስፔሻሊስት ሲገርመኝ ሰሞኑን ደግሞ በዚያው የፖሊስ ፕሮግራም ላይ የመኪና ስርቆት የፈፀመች የአዲስ አበባ ኮረዳ ተመለከትኩና በግርምት ተሞላሁ፡፡ እንዴ… ማንን እንመን ታዲያ? (በፎርጅድ ኮረዶችም ተከበናል ማለት እኮ ነው!)
እኔ የምላችሁ … ይሄ የሌብነት ጉዳይ “ፕሮፌሽናል ቢዝነስ” መሰለ እኮ! (የሌቦች ማሰልጠኛ ተቋም ተከፈተ እንዴ?) በዚሁ ሰሞን 20 የሚደርሱ ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ ግለሰቦች በፎርጅድ ሰነዶች እየተጠቀሙ፣ የአፍሪካን መዲና ሲያጭበረብሩ እንደከረሙ ፖሊስ ተናግሯል፡፡ ይታያችሁ … ከመኪና አከራዮች ውሃ የመሰለች መኪና ይከራዩና ፎርጅድ ውክልና አሰርተው
ጆሮዋን ይሏታል፡፡ የድግስ ወንበሮችና ድስቶች እንዲሁም የግንባታ ማሽኖች እየተከራዩም  ቸብችበዋል፡፡ (8ኛው ሺ ገባ እንዴ?) የእነዚህ “ቁጭ በሉዎች” ሰለባ የሆነች አንዲት እመቤት ለፖሊስ ስትናገር፤ ሌቦቹ “ያሪስ” መኪና ይዘው ወደ ቢሮዋ እንደመጡ ገልፃለች፡፡ (ያሪሷም እኮ ፎርጅድ ናት!)
ለነገሩ የዚህ የፎርጂድ ነገር በሌቦች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በመንግስትም በተቃዋሚዎችም በምሁሩም በባለሙያውም … በሁሉም ዘንድ እየታየ ነው፡፡ ሰሞኑን አንዲት የስራ ባልደረባዬ መታወቂያዋን ለማሳደስ ወደ ቀበሌ ጐራ ብሎ የገጠማትን አጫወተችኝ፡፡ የቀበሌው ሠራተኞች ወደው ይሁን ተገደው (እነሱም አያውቁት!) የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ምስልና “የመለስን ራዕይ እናስፈፅማለን” የሚል መፈክር የተፃፈበት ቲ-ሸርት ለብሰው ተደርድረዋል-ቢሮአቸው ውስጥ፡፡ ችግሩ ግን ምን መሰላችሁ? ቲ-ሸርቱ ለስራ ሊነሽጣቸው (Inspire ሊያደርጋቸው) አልቻለም፡፡ እንደውም መልበሳቸውንም ሳይዘነጉት አልቀሩም፡፡ ለነገሩ የራሱ ራዕይ የሌለው ሰው “የታላቁን መሪ” ራዕይ ላስፈፅም ቢል እንዴት ይሆናል? (“የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር” አሉ!) እናም ባልደረባዬን በቅጡ ሊያስተናግዷት አልቻሉም፡፡ (መታወቂያ ማደስ እኮ ነው!) እሷ ተገትራ እነሱ ወሬያቸውን እያደሱ ነበር፡፡ የማታ ማታ ዱላ ቀረሽ ሙግት ገጥማ ነው መታወቂያዋን ያደሱላት፡፡ (የፎርጅዱ “ስፔሻሊስት” በቀን ስንት የቀበሌ መታወቂያ ያመርት ይሆን?)
በነገራችሁ ላይ አንድ ፖሊስ ኦሪጂናሉንና ፎርጅዱን የቀበሌ መታወቂያ አነፃፅረው ሲናገሩ “ፎርጅድ የሚመስለው የቀበሌው ነው” ብለዋል፡፡ (የፎርጅዱን ስፔሻሊስት ወደ ህጋዊ መስመር ማምጣት አይቻልም እንዴ?) በእርግጥ መጀመሪያ ቅጣቱን መቀበል አለበት፡፡ እናላችሁ … “የመለስን ራዕይ እናስፈፅማለን” የሚል ቲሸርት ለብሰው ወሬና ሃሜት ሲያነክቱ የሚውሉ የቀበሌና የወረዳ ሰራተኞች ሁሉ “ፎርጅድ ኢህአዴጐች” ናቸው፡፡ (ኢህአዴግም ፎርጂድ አለው እንዴ?)
ይሄውላችሁ … በቲቪ መስኮት “ኪራይ ሰብሳቢ… ፀረ ሰላም ሃይላት፣ የኒዮሊበራሊዝም አቀንቃኝ” እያሉ የሚያደነቁሩን ስንቶቹ ካድሬዎችና ባለስልጣናት ሙሰኞች ሆነው እንደተያዙ በዓይናችን በብሌኑ ዓይተናል፤ሰምተናልም፡፡ አሁን እነዚህ ምን ይባላሉ? “ፎርጂድ ባለሥልጣናት!”  (“made in” የት ይሆኑ?) አንዳንዴ ሳስበው የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ፎርጅድ ሰነዶች ብቻ ሳይሆን ፎርጅድ ተቃዋሚዎችን የሚሰሩም ሳይኖሩ አይቀሩም፡፡ ጊዜ ፊቱን ያዞረባቸው ቀን ግን ቅሌት ቀለባቸው ይሆናል፡፡ (“የህዝብ ነኝ” እያሉ ህዝብን ማታለል አደጋ አለው!)
በየጊዜው የአገሪቱ የትምህርት ጥራት “ወድቋል” ሲባል እንሰማለን አይደል?! አንድም ቀን ግን ተጠያቂው “እገሌ ነው” ብለን ደፍረን አናውቅም (እኛም ራሳችን ፎርጅድ ሳንሆን አንቀርም!) እርግጥ ነው ኢህአዴግ መራሹን መንግስት የሚወነጅሉ ወገኖች አሉ፡፡ ይሄ ግን “ክሊሼ” ነው – የተሰለቸ፤ የታከተ ሰበብ! ነገርዬውን ጠልቃችሁ ስትመረምሩ ግን ዋንኞቹ ተጠያቂዎች “ፎርጅድ መምህራን” እንደሆኑ ትገነዘባላችሁ፡፡ እንዴ … ሴት ተማሪዎችን “እራት ልጋብዝሽና ስለ ግሬድሽ እንመካከር”፣ “250 ብር አምጣና ማርክ ልጨምርልህ” የሚሉ መምህራኖች እኮ በርክተዋል፡፡ እናም የትምህርት ጥራት እንጦሮጦስ የወረደው በእነዚህም “ፎርጅድ የቀለም ሰዎች” ምክንያት ነው፡፡ (መንግስትም ግን ከተጠያቂነት አያመልጥም-ጠያቂ ካለ!) የሰው ፈጠራ ወይም የጥበብ ሥራ አሊያም ሃሳብ፣ ወዘተ … መንትፈው የራሳቸው በማስመሰል እነሆ በረከት የሚሉን “ከያኒያን”ም እኮ “ፎርጂድ አርቲስቶች” ናቸው-የጦቢያ የጥበብ ቆሌ የተጣላቻቸው!
እንግዲህ ፎርጅድ ያልገባበት የህይወት ዘርፍ የለም፡፡ ለምሳሌ እዚህቹ መዲናችን ላይ የፍቅር ፎርጅድ የሚሰሩ እኮ በሽበሽ ናቸው – ከወንዱም ከሴቱም፡፡ መጀመርያ ላይ “እመቤቴ፣ ንግስቴ፤ ማሬ ወለላዬ …” እያለ የፍቅረኛውን እግር ለማጠብ የሚዳዳው የጦቢያ ወንድ፤ አግብቶ “ንብረቱ” ካደረጋት በኋላ ግን ውጭ ውጭውን ያያል፤ ኮረዳ ያማርጣል፡፡ ይሄንን እኔ “ፎርጅድ ባል” ብየዋለሁ፡፡ “ፎርጅድ ሚስቶችም” “በሽ” ናቸው!! (ዘመኑ እኮ ነው!)
ቁጥራቸው ባይበዛም መታወቂያቸው ወይም ፓስፖርታቸው ላይ “ፎርጅድ ኢትዮጵያዊ” በሚል መገለፅ ያለባቸው አንዳንድ በ “ሃሰት” የተሰሩ ዜጐችም አሉ – እዚህችው ጦቢያችን ምድር ላይ፡፡ ባለፈው ጊዜ የአገልግሎት ቀኑ (expiration date) ያለፈበት የታሸገ ምግብ ከውጭ አስመጥተው በሱፐርማርኬት ስለሚሸጡ ስግብግቦች አልሰማችሁም? እስቲ አስቡት … የተበላሹ የህፃናት ምግብና ወተት ለወገን እየሸጡ ትርፍ ማጋበስ … ምን ይባላል? እውነቴን ነው … እነዚህ ከሽብርተኞች በምንም አይለዩም፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹን ህሊናቸውን ለገንዘብ የሸጡ ግለሰቦች “ሆዳም” ወይም “ስግብግብ”፤ በሚል ለመግለፅ መሞከር ዝም ብሎ ቃላት ማባከን ነው፡፡ ትክክለኛው መጠሪያቸው “ፎርጅድ ኢትዮጵያውያን” ነው-ተመሳስለው የተሰሩ! (“ሃሰተኛ” ኢትዮጵያውያን እንደማለት!) በዜጐቻቸው ሰቆቃ የከበሩ ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችም እንዲሁ ከዚህ የተሻለ ስም ሊሰጣቸው አይችልም፡፡ እነሱም “ፎርጅድ ኢትዮጵያውያን” ናቸው (እንደ ፎርጅድ ብር ቁጠሯቸው!) ጥፋት እንጂ ልማት የላቸውም፡፡
እንዴ … ሰሞኑን በመከራና በችግር ተጠብሰው ከሳኡዲ እየተመለሱ ያሉት ዜጐች ለዚህ ጦስ የተዳረጉት እኮ በእነሱ ነው፡፡ እህቶቹን ሲኦል እየወረወረ በሚያጋብሰው ገንዘብ እንቅልፉን ለጥጦ የሚያድር ሰው ኢትዮጵያዊ ሊባል አይችልም … “ፎርጅድ ኢትዮጵያዊ” እንጂ!

መቀሌ በእሳት ቃጠሎ አደጋ ተናጠች

አብረሃ ደስታ ከመቀሌ እንደዘገበው፦ ዛሬ ሌሊት (ማክሰኞ አጥብያ) ህዳር 23/24, 2006 ዓም በመቐለ ከተማ ሰሜን ወረዳ 06 ቀበሌ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሶ 70 የFurniture and Metal works Workshops ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። በዎርክሾፖቹ የሚተዳደሩት ከ250-300 የሚሆኑ ሰራተኞች የነበሩ ሲሆን በጠቅላላ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድመዋል።
ማዘጋጃቤት መርዳት ባለመቻሉ ኗሪዎቹ ወደ አየርመንገድና ሲሚንቶ ፋብሪካ በመሄድ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪኖች እንዲረዱ የጠየቁ ሲሆን የአየር መንገዱ በመጨረሻ አከባቢ ደርሷል፤ የሲሚንቶ ፋብሪካው ግን በቂ ዉኃ ሳይዝ በመምጣቱ ብዙ ንብረት ማዳን አልቻለም።የአደጋው መንስኤ ባከባቢው የሚገኘው የመንግስት የመብራት ትራንስፎርመር በመቃጠሉ ነው። ትራንስፎርመሩ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የመቃጠል ምልክቶች እንደነበሩትና ያከባቢው ኗሪዎችም በተደጋጋሚ ለመንግስት አካላት ትራንስፎርመሩ እንዲጠግኑት ጥያቄ ቢያቀርቡም መልስ ባለመግኘታቸው ችግሩ መፈጠሩ ተጠቅሷል። ስለዚህ አደጋው ያጋጠመው በመንግስት አካላት ቸልተኝነት መሆኑ ነው።የእሳት አደጋው በቀላሉ መቆጣጠር ይቻል የነበረ ቢሆንም ሁለቱም የመቐለ ከተማ ማዛጋጃቤት የእሳት አደጋ ማጥፍያ ተሽከርካሪዎች ‘ተበላሸተው ጋራጅ ገብተዋል’ በሚል ምክንያት አደጋው የመቆጣጠሩ ጥረት አዳጋች አድርጎታል።
የመቐለ ማዛጋጃቤት የእሳት አደጋ ማጥፍያ ተሽከርካሪዎች ተበላሽተዋል ሲባል ገረመኝ። BTW, የተቃጠሉ ድርጅቶች ፎቶ ለማስነሳት ያደረግነው ጥረት በፖሊስ ሃይል ተከልክለናል። የመቐለው 06 ቀበሌ ‘የኢንዱስትሪ ዞን’ ነው።
በመንግስት ቸልተኝነት ምክንያት ንብረት ሲወድም ያሳዝናል።

አለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት የሳውድ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ምርመራ እንዲያደርግና እርምጃ እንዲወስድ አሳሰበ

ህዳር ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው መግለጫ የሳውዲ የጸጥታ ሀይሎችና የሳውዲ ዜጎች በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሀይል እርምጃ በመውስድ ጉዳት አድርሰዋል። በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የሳውድ አረቢያ መንግስት አስፈላጊውን  ምርመራ በማድረግ በአጥፊዎቹ ላይ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል ያለው ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቶሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እስከዚያው በቂ ምግብ፣ መጠለያና የህክምና አገልግሎት እንዲሰጣቸው ጠይቋል።
የሳውዲ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ዜጎች በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ፣ ኢትዮጵያውያንን የሚያጥላሉ ቅስቀሳዎች ይደረጉ እንደነበር ድርጅቱ አያይዞ ጠቅሷል።

የወያኔ አገዛዝ በመልዕክተኞቹ በኩል ላቀረበው የ“እንደራደር” ጥያቄ ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ምላሽ

DEC 2,2013
ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የገነባዉ ሥርዓት በከፍተኛ ችግሮች የተወጠረ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመሪው ሞት በወያኔ መሀል ያስከተለው ቀውስ፤ የሕዝብ ሁለገብ ትግል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበት መሄድ የፈጠረበት ስጋት እና ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚደርስበት ጭንቀት መጨመር ተደማምረው ውጥረቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እያደረሱት መሆኑን የሚያሳዩ በቂ ምልክቶች አሉ። የእስካሁኑ ተሞክሮዓችን እንደሚያሳየው ወያኔ ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ የሚገዛ መሆኑን ነው። ሰሞኑን በወያኔ አገዛዝ መልዕክተኞች በኩል የደረሰንን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄያችን በዋናነት ያየው ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘው ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ትግልና በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረጉ ዉይይቶች ቢመጣ የግንቦት 7 ምርጫ መሆኑን ንቅናቄያችን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። ግንቦት 7ን ሁለገብ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገደደው የወያኔ እምቢተኝነትና እብሪት ብቻ ነው።
የግንቦት 7 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰሞኑ የወያኔ የእንደራደር መልዕክት እንደደረሰው በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ እንጂ ግንቦት 7ን ብቻ የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከሚያደርገው ትግልና እየከፈለ ካለው መስዕዋትነት ጋር በቀጥታ ግንኙነት አለው። በመሆኑም፤ ለቀረበልን ጥያቄ ግልጽ መልስና፤ ድርድር ስለሚባለው ጉዳይም ያለንን አቋም ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችል ተጨማሪ አጋጣሚ አድርገን ወስደነዋል። በዚህም መሠረት ለቀረበልን ጥያቄ የሰጠነዉን መልስና አቋማችንን በድርጅታችን ድረ ገጽ ላይና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን በኩል በይፋ ለመግለጽ ወስነናል።
በድርድር ስለሚመጣ ለውጥ ያለን የመርህ አመለካከት:
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዳደረግነው ድርጅታችን ከምሥረታው ጀምሮ የትግል ስልቱን ሲወስን እምነቱ አድርጎ የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በሀገራችን በሰላማዊ መንገድና በድርድር ቢመጣ በእጅጉ የሚፈልገውና የሚመኘው መሆኑን ነው:: ድርጅታችንን ወደ ሁለንተናዊ ትግል የገፋው በመግቢያው ላይ እንደገለጽነው የወያኔ እብሪት ብቻ ነው:: የቀረበልን ምርጫ በባርነትና በውርደት መኖር ወይም ለነፃነት እየታገልን መሞት ቢሆን ኖሮ ንቅናቄያችን የሚመረጠው ምን ግዜም ለነፃነትና ለአገር አንድነት ታግሎ በክብር መሞት መሆኑን በተደጋጋሚ ለሕዝብ ግልጽ አድርገናል። ይህ የማይናወጥ አቋማችን ደግሞ ለይምሰል የተቀመጠ አቋም ሳይሆን ከልባችን የምናምንበትና ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አባላቶቻችንን ያሰባሰብንበት አቋም ነው። ዛሬ በትግሉ ግንባር የምንንቀሳቀሰውና ወደ ግባችን የሚወስደንን ተጨባጭ እርምጃዎች እየወሰድን ያለነውም በዚሁ አቋማችን ዙሪያ ነዉ።
ይህ አቋማችንና እምነታችን በአንድ ላይ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሁለት መርሆችን አጣምሮ የያዘ ነዉ። አንደኛው፣ ሂደትን በሚመለከት ሁሌም ለድርድር ክፍት መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ፣ ይህ የድርድር ሂደት እንዲያው ለለበጣ የሚደረግ ሳይሆን ወደሚፈለገው ነጻነት በአነስተኛ መስዕዋትነት ሊያደርስ ይችል ከሆነ በሩን ላለመዝጋት እንጂ፣ በምንም አይነት ዋና ውጤቱን፤ ማለትም ኢትዮጵያን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ማድረግን፤ የሚቀይር ወይንም ከዚያ ያነሰ ውጤትን ለመቀበል መፍቀድን ፈጽሞ የማያመለክት መሆኑን ነው::
በእኛ በኩል ድርድሩን አስፈላጊና ጠቃሚ የሚያደርጉት መነሻ የፖለቲካ እሳቤዎችም ከእነኝሁ ሁለት መንታ ገጽታዎች የሚመነጩ ናቸው:: በድርድር ለሚገኝ ፍትሀዊና እውነተኛ ውጤት ክፍት መሆናችንን ሁሌም እናሳያለን፤ ነገር ግን ይህን የምናደርገው የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት መከፈል አለበት የሚለውን መሠረታዊ የአካሄድ መርህ በመመርኮዝ እንጂ መርሀችንን ለድርድር ለማቅረብ እንዳልሆነ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል::
ስለዚህም:
ሀ)    የድርድሩ ውጤት የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ያረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን በአስቸኳይ እውን ማድረግ መሆን ይኖርበታል:: ይህ ዋናው ግብ ሆኖ ከዚህ በመለስ የሚኖሩ በሂደት የሚገኙ አነስተኛ ግቦች ሊኖሩ ይችላሉ (ለምሳሌ የፖለቲካ እስረኞች ማስፈታት…ወዘተ):: ሆኖም በምንም አይነት ለእነኝህ መለስተኛ ግቦች ተብሎ ዋናውን ግብ የሚያሳጣ ወይንም ጊዜውን ያላግባብ የሚያስረዝም ድርድር፣ ድርድር ነው ብሎ ድርጅታችን አይቀበልም። ስለዚህም ዋናው የድርጅታችን ዓላማና ግብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ፣ በፍጹም ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም:: በሥልጣን ላይ ባለው ኃይል በኩል ወደዚህ ግብ ለመድረስ ቁርጠኝነቱ በሌለበት ሁኔታ በሚደረግ ማንኛውም አይነት ድርድር ውስጥ ግንቦት 7 አይሳተፍም::
ለ)  በግንቦት 7 እምነት ማንኛውም ድርድር ወያኔ ከግንቦት 7 ጋር በተናጠል የሚያደረገው ሳይሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ያካተተ መሆን ይኖርበታል:: ድርጅቶችን በተናጠል እየለያዩ “እንደራደር” ማለት በራሱ ጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ስሌትን የያዘ እሳቤ እንጂ፣ በዘላቂነት አገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ለማድረግ መፈለግን አያመለክትም:: ለአንድ ድርጅት ለብቻው የሚመጣ ወይም የሚጠቅም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የለም:: ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ፍላጎት ያለው ድርድር በአገሪቱ ያሉትን የተለያዩ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ኃይሎችን ያካተተና ያመኑበት መሆን ይኖርበታል:: የሚደረገው ድርድርም ማን በስልጣን ላይ ይውጣ ወይንም የፖለቲካ ስልጣንን ባሉት ኃይሎች መሀከል እንዴት እናከፋፍለው የሚል የስልጣን ቅርምት ድርድር ሳይሆን፤ ሕጋዊና የሕዝቡን የሥልጣን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ ሁኔታ የፖለቲካ ስልጣን እንዴት እንደሚያዝ ፍትሀዊ የሆነ ሂደትን ለማስጀመር የሚደረግ ድርድር መሆን አለበት::
ሐ) ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ይህ ጉዳይ የሚመለከተው አንድን ድርጅት ወይንም የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው:: ይህ እስከሆነ ድረስ እንዲህ አይነት ድርድር ከሕዝቡ በተደበቀ ሁኔታ በሚስጥር የሚካሄድበት ምንም ምክንያት የለም::
2)   ከዚህ በፊት ከወያኔ ጋር ከተደረጉ ድርድሮች ያገኘናቸው ተመክሮዎችና ከዚህ በመነሳት ወደፊት በሚደረጉ ምንም አይነት ድርድሮች እንዳይደገሙ ለመጠበቂያ የሚሆኑ ከአሁኑ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
ከማንኛውም ወገን ጋር የሚደረግ ድርድር የተደራዳሪዎቹ ምንነት፤ ውስጣዊ ባህርያቸውን፤ ከተለምዶ ተግባራቸው ያላቸውን ተአማኒነትና ወደዚህኛው ድርድር ያመጣቸውን ምክንያቶች በበቂ ከመገንዘብ ጋር ተያይዞ የሚታይ ጉዳይ ነው:: ቃሉን አክባሪና ተዓማኒ ከሆነ ሰው ጋር የሚደረግ ድርድርና ያለፈው ታሪኩ ምንም አይነት የተዓማኒነት ባህርይ ከማያሳይ ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርም ሆነ ለድርድሩ የሚደረግ ዝግጅት ለየቅል ናቸው:: ይህ ማለት ግን ተዓማኒነት ካለው ኃይል ጋር ብቻ ነው ድርድር የሚካሄደው ማለት አይደለም:: በፍጹም ተዓማኒ ካልሆነ ኃይል ጋር የሚደረግ ማንኛውም ድርድር ግን ድርድሩ በእርግጥም ተግባራዊ ሊሆን የሚችል መሆኑን የሚያሳዩ ጠንካራ መጠበቂያዎች (System of Verification) እንዲሁም ግልጽ የመተግበሪያ ሥርዓቶች (Implementation Mechanism) ሲደረጉለት ብቻ ነው ከምር ሊወሰድ የሚችለው:: ከዚህም ባሻገር ግን መጀመሪያውኑ ወደ ድርድር የሚመጣው ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሳይሆን በእዉነተኛ መንፈስ ከድርድር የሚመጣውን ውጤት በመፈለግ መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” ምልክቶች ሲያሳይ ነው በእርግጥም ወደ ድርድር የመጣው ከልቡ ድርድሩንና ከድርድሩ የሚመጣዉን ዉጤት ፈልጎ መሆኑን ለማመን የሚያስችለው::
ወያኔ ከተቀናቃኝ ወገኖች ጋር “ድርድር” ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜዉ አይደለም:: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ምናልባት በኃይል ይበልጡኛል ብሎ ከሚያምናቸው ወገኖች ጋር ካልሆነ በስተቀር፣ በረሃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ጊዜ ለቃሉ ታማኝ፤ ለመርሁ እውነተኛ፤ ለደረሰበት ስምምነት ተገዢ ሆኖ አያውቅም:: ይልቁንም ሶስተኛ አደራዳሪ ወገኖችን በሚያሸማቅቅና በሚያሳፍር መልኩ ውሸትን እንደ አዋቂነት፤ ማጭበርበርን እንደ ብልጠት፤ የተስማማበትን በገሀድ ማፍረስን እንደ የአመራር ብልሀት አድርጎ የሚያይ፤ ምንም እፍረትና ጨዋነት የሚባል ነገር ያልፈጠረበት እኩይ ኃይል ነው:: ከራሱ የድርጅት ጥቅምና በስልጣን ከሚገኝ የዝርፊያ ሀብት ማካበት ባሻገር፤ ለአገር ዘላቂ ጥቅም ብሎ የራሱን ጥቅም አሳልፎ የሚወስደው ምንም እርምጃ እንደሌለ በተግባር በተደጋጋሚ ያረጋገጠልን ኃይል ነው:: በግንቦት 7 ውስጥ ያለን ወገኖች ይህንን የወያኔ ባህርይ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ሌሎች ጽፈውት ያነበብነው ሳይሆን፣ እራሳችን በተግባር በተሳትፈንበት ሂደት ያገኘነው ጥልቅ ግንዛቤ ነው:: ይህንን ደግሞ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ከድርጅቱ ታሪክ ጋር የተጣበቀ፤ በአመራር አባላቱ ላይ እንደ ግል ባህርይ የሰረጸ መሆኑን እስክንገነዘብ ድረስ በተደጋጋሚ የተመለከትነው ነው:: ስለዚህም ከዚህ ኃይል በኩል የሚመጣን የ “እንደራደር” ጥያቄ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ለገባበት የፖለቲካ ውጥረት ማስተንፈሻ፣ ለውሸት ፕሮፓጋንዳው መጠቀሚያ፤ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ መሰብሰቢያ፤ የዴሞክራሲ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈቺያና ወኔ መስለቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት በፍጹም አንፈቅድለትም:: ስለዚህም ከላይ በመርህ ደረጃ ከጠቀስናቸው ሶስት ጉዳዮች በተጨማሪ ምንም ዓይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት ወያኔ ጉዳዩን ከምር የወሰደው መሆኑን የሚያሳዩ “የመተማመኛ” እርምጃዎች መውሰድ አለበት ብለን እናምናለን::
እነኝህም፣
ሀ)  ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት:: ይህ ደግሞ በግልጽ     የሚታወቁ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን በድብቅ የተቋቋሙ ማጎሪያና ማሰቃያ ቤቶች ያሉትን ሁሉ ማጠቃለል አለበት።
ለ)  በሕዝብ በተለይ በተቃዎሚ ኃይሎች ላይ ወያኔ በየቀኑ እያካሄደ ያለውን ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር አለበት።
ሐ)   በፖለቲካ ምክንያት ከዚህ በፊት የተወሰዱ ሁሉም ዓይነት ፍርድ ተብዮ ውሳኔዎች እንዲሻሩ ማድረግ፤ በሂደት ላይ ያሉ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ አለበት።
መ)   ሕዝብን በፍርሃትና በስጋት ለማቆየት ሆነ ተብለው የወጡ አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት አለበት።
ሠ)   ማንኛውም ድርድር ገለልተኛ የሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ባሉበት፤ የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣ የድርድሩ ቦታም የተደራዳሪ ወገኖች በጋራ በሚስማሙበት ቦታ መሆኑን መቀበልና ይህንንም በግልጽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ አለበት።
እነኝህ ከላይ ያስቀመጥናቸው በወያኔ በኩል የሚወሰዱ “የመተማመኛ” እርምጃዎች ለተቃዋሚዎች ተብሎ የሚወሰዱ እርምጃዎች አይደሉም:: ወያኔ እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ቁርጠኝነት ሳይኖረው ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት የሚደረግ ድርድር ላይ ከምር ይሳተፋል ብለን ማመን በፍጹም ስለማንችል ነው ::
እስከዚያው ድረስ ግን ግንቦት 7ም ሆነ ሌሎች ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት በቁርጠኝነት የምንታገል ኃይሎች፣ ወያኔ እነኝህን የመተማመኛ እርምጃዎች እስኪወስድና ቀደም ብለው በተቀመጡት መርሆች መሠረት በሚደረግ ድርድር በተግባር ሊመነዘር የሚችል ስምምነት፣ አልፎም ለምንም አይነት ማጭበርበርና መንሸራተት እድል የማይሰጥ ጠንካራ መጠበቂያዎች መኖራቸው እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የጀመርነውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን የምንገፋበት እንጂ በምንም አይነት ለአንድ አፍታም ቢሆን በድርድር ስም የማንዘናጋ መሆኑን አበክረን እናስታውቃለን::
የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣
ኅዳር 23፣ 2006 ዓ:ም

Sunday, 1 December 2013

የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ከሰራዊቱ ሊቀነሱ መሆኑ ታወቀ በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን ነግሷል፤ የሕወሃት ጄኔራሎች ፈርተዋል


ምንሊክሳልሳዊ-

በሰራዊቱ ውስጥ የተነሳውን ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ተከትሎ የቀድሞ የኢሕዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥእንደሚቀነሱ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል:: በየቀኑ ለስብሰባ የሚቀመጠው ሕወሓት መራሹ የጄኔራል መኮንኖች የአንድ ብሄር ቡድንተጠንቷል ባለው እና የተወያየበት ሰነድ እንደሚያመለክተው በሰራዊቱ ውስጥ የሚነሱ ማንኛቸውም ጥያቄዎች የሚፈጠሩት ከአማራው እናከኦሮሞው ወገን ከሆኑት መኮንኖች ሲሆን ይህንንም የሚመሩት የውስጥ መዥገር የሆኑት የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ስለሆኑ ከሰራዊትውስጥ በመቀነስ በተለያዩ መንገዶች በወንጀል ለማጥመድ እና ከነማን ጋር እንደሚገናኙ አስፈላጊውን የደህንነት ክትትል ማድረግ ይገባል ሲልተነጋግሮበታል::
እነዚሁ የለውጥ ጥያቄ ያነሱት የሰራዊቱ መኮንኖች ከተለያዩ የታጠቁ የጠላት ሃይሎች እና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋርበመገናኘት የመንግስትን ህልውና እየተፈታተኑት ከመሆኑም ባሻገር የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ከቀድሞ ስርኣት የተወረሱ እና ለዲሞክራሲውእና ለልማቱ እንቅፋት ስለሆነ አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ተብሏል::ከግንቦት ሰባት እና ከተቃዋሚ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘትበሰራዊቱ ውስጥ ያለነበሩ እና ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በመፍጠር ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ሰዎችንበማስኮብለል መረጃ በማቀበል እንዲሁም አለመተማመን እንዲኖር በመስራት ከፍተኛ ደንቃራ ሆነዋል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮቹ እንደገለጹት የቀረበው ሰነድ ለጄኔራል መኮንኖቹ ያልተበተነ ሲሆን የስብሰባው መሪ የሆኑት ኢታማጆር ሹሙ እጅበመሆን ሰነዱ እየተነበበ የተወያዩበት እና ይህም የሚያመለክተ በሕወሓት ጀኔራሎች መካከልም መተማመን አለመኖሩን ያሳያልብለዋል::በሙስና ከአስተዳደርዊ ባለስልጣናት በበለጠ የተዘፈቁት የሕወሓት ጄኔራሎች በስብሰባ እና አብዛኛው ንብረቶቻቸን በተዘዋዋሪበመሸጥ ስራ ላይ እየተንቀሳቀሱ ሲገኝ በሱዳን በኢምሬት እና በአውሮፓ አገሮች እንዲሁም በአሜሪካ በቤተሰቦቻቸው ስም የተለያዩንብረቶችን በመግዛት ላይ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮሽ ጨምረው ገልጼዋል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10271