Sunday, 15 September 2013

የዓመቱ አወዛጋቢ፣ አነጋጋሪና ትኩረት ሳቢ አጀንዳዎች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)
የዓመቱ አወዛጋቢ፣  አነጋጋሪና ትኩረት ሳቢ አጀንዳዎች
የአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አዲሱ አስተዳደር
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ2004 ዓ.ም መገባደጃ ላይ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የአገሪቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ ብዙዎችን ማሳሰቡ አልቀረም፡፡ የዳያስፖራ ፖለቲከኞችና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢህአዴግ ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ እንደሚፈጠር ስጋታቸውን ገልፀው ነበር፡፡ በአገር ውስጥም ተመሳሳይ ስጋት የነበሯቸው ወገኖች አልነበሩም ማለት አይቻልም፡፡ ይሄ ስጋት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠ/ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ በመስከረም 2005 ዓ.ም በጠ/ሚኒስትርነት ከተሾሙም በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የቀጠለ ይመስላል፡፡ አንዳንድ የተቃዋሚ መሪዎችና የፖለቲካ ተንታኞች አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሥልጣን ክፍተቱን ለመሙላት ለጊዜው ተቀመጡ እንጂ የጠ/ሚኒስትርነቱ ቦታ ከህወሐት እጅ እንደማይወጣ ተንብየው ነበር፡፡ ቢያንስ እስካሁን ግን ትንበያቸው የሰራ አይመስልም፡፡ በአዲሱ ህግ መሰረት ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ለአስር ዓመት (ሁለት ተርም) በሥልጣናቸው ላይ እንደሚቆዩ ይጠበቃል።
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ ተፎካካሪያቸውን (ብአዴን ያቀረባቸውን) አቶ ደመቀ መኮንንን በማሸነፍ ነው የጠ/ሚኒስትርነት ሥልጣኑን የያዙት፡፡ በድምፅ ብልጫ የተሸነፉት አቶ ደመቀ መኮንንም ከትምህርት ሚኒስትርነታቸው በተጨማሪ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ለማግኘት ችለዋል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን የምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ሃላፊነታቸውን በቅጡ እንዲወጡ በሚል ከትምህርት ሚኒስትርነታቸው ተነስተዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም በአንድ ዓመት የሥልጣን ዘመናቸው በርካታ ሹም ሽሮችን አድርገዋል፡፡ ከሁሉም የሚቀድመው ግን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሚጠሩ ሁለት ተጨማሪ ባለስልጣናትን መሾማቸው ነው፡፡ ከኦህዴድ አቶ ሙክታር ከድር፣ ከህወኃት ደግሞ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚኒስትርነት ከሚመሯቸው መስሪያ ቤቶች በተጨማሪ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ሹመት አግኝተዋል፡፡ ይሄ ያልተለመደ አሿሿም ህገመንግስቱን የጣሰ ነው በሚል ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተቃወሙት ሲሆን ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም በበኩላቸው፤ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር በህይወት ሳሉ የታሰበበት ጉዳይ እንደነበርና ሥራን በጥራትና በብቃት ለማከናወን ታልሞ የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአቶ ኃይለማርያም አስተዳደር ትልቁ “ራስ ምታት”
ለአዲሱ የአቶ ኃይለማርያም መንግስት ከምንም በላይ ትልቅ ራስ ምታት የሆነበት “የሃይማኖት አክራሪነት” ጉዳይ ነው፡፡ ከእስልምና ምክር ቤት ምርጫ እና ከአወሊያ ት/ቤት ጋር ተያይዞ የተነሳው ውዝግብ “የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ” አባላት መታሰርን ተከትሎ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን “ድምፃችን ይሰማ” እና “የታሰሩት ይፈቱ” የሚሉ ተቃውሞዎች በየጊዜው ሲሰሙ ቆይተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ አጀንዳቸው መሆኑ ደግሞ መንግስትን ክፉኛ አስቆጥቶታል፡፡ በአመቱ መገባደጃ ግድም በደሴ ከተማ ግድያ የተፈፀመባቸው የሼክ ኑሩ ይማም ጉዳይም ነገሩን የበለጠ አባብሶታል፡፡ መንግስት ሼኩን አክራሪዎች ስለመግደላቸው በቂ ማስረጃ አለኝ ሲል፤ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ ጉዳዩን “የመንግስት ድራማ ነው” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ የአክራሪነት አጀንዳ በዚህ መልኩ አሁንም ድረስ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል፡፡ በ2006 መቋጫ ይበጅለት ይሆን?
ከ8 ዓመት በኋላ የተነሳው የሰላማዊ ሰልፍ እገዳ
ከ97 ምርጫ በኋላ ላለፉት 8 አመታት ታግዶ የቆየው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት የተፈቀደው ባሳለፍነው አመት ነበር፡፡ በግንቦት ወር በሠማያዊ ፓርቲ የተጀመረው የተቃውሞ ሠልፍ፤ በአንድነት ፓርቲ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ሠማያዊ ፓርቲም የጠየቃቸው አራት ጉዳዮች ምላሽ ባለማግኘታቸው በድጋሚ ሠላማዊ ሠልፍ መጥራቱ ይታወሳል፡፡ አንድነት ፓርቲ የ3 ወር የህዝባዊ ንቅናቄ መርሃ ግብር ዘርግቶ በ16 ያህል ከተሞች ሠላማዊ ሠልፎችና ህዝባዊ ስብሠባዎችን አድርጓል፡፡ “የሚሊየኖችን ድምፅ” በሚል ስያሜም አወዛጋቢ የሆነውን የፀረ ሽብር ህግ ለማሠረዝ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ይሄንን ተከትሎም አዋጁ ከወጣ ከአራት አመት ገደማ በኋላ በኢቴቪ አዘጋጅነት ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች በፀረ ሽብር ህጉ ላይ ትኩረትን የሳበ ጠንካራ ክርክር አድርገዋል – በዓመቱ መገባደጃ ላይ፡፡
“ፓርላማው ጥርስ አወጣ?” ወይስ ድሮም ነበረው?
ሌላው ዘንድሮ የታየ ጉልህ ለውጥ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከፍተኛ መነቃቃት ማሳየቱ ነው፡፡ ባለፉት 21 አመታት ባልታየ መልኩ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካላትን የስራ ውጤት አጥብቆ ሲሞግትና ሲገመግም ተስተውሏል፡፡ ይሄን ያስተዋሉ አንዳንድ ፖለቲከኞች “ፓርላማው ዘንድሮ ጥርስ አወጣ” ሲሉ አፈጉባኤውን ጨምሮ አብዛኞቹ የምክር ቤቱ አባላት በዚህ አይስማሙም፡፡ “ፓርላማው ድሮም ጥርስ ነበረው” የሚሉት አባላቱ እስካሁን ያልታየው ሚዲያው ትኩረት ሰጥቶ ስለማይዘግብ ነው በማለት ይከራከራሉ፡፡ ከህወሐት የመጀመርያ መስራቾች አንዱ የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ ለአዲስ አድማስ በሰጡት አስተያየት፤ የምክር ቤቱን መነቃቃት ማጤናቸውን ጠቁመው “የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራውን በመጀመሩ የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ ያለው” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ አሁን ብዙዎችን የሚያሳስባቸው ጥርስ አወጣ አላወጣም የሚለው ክርክር ሳይሆን የተጀመረው መነቃቃት ተጠናክሮ ይቀጥላል ወይስ እንደ ወረት ታይቶ ይጠፋል የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ለጊዜው ይሄን የሚያውቀው ደግሞ መንግስት ብቻ ነው ይላሉ – አስተያየት ሰጪዎች፡፡
“መንግስት ይከሰሳል” የተባለበት ዓመት
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአማራ ተወላጆች መፈናቀልም በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ክስተቶች ተጠቃሽ ነው፡፡ በወቅቱ የተፈናቀሉት ቁጥራቸው ከ3ሺህ የሚልቅ ሠዎች፤ በአማራ ክልል ፍኖተ ሠላም ከተማ በጊዜያዊነት እንዲጠለሉ ከተደረገ በኋላ፣ የክልሉ መንግስት አመራሮች “እኛ ሣናውቅ ነው የተፈናቀሉት” በማለት ወደነበሩበት እንዲመለሡ ተደርጓል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም በይፋ ድርጊቱን በማውገዝ በድርጊቱ የተሣተፉ ወንጀለኞች ለፍርድ እንደሚቀርቡ በፓርላማ ገልፀዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ መኢአድና ሠማያዊ ፓርቲ መንግስትን ለመክሠስ የሚያስችለንን ዝግጅት እያደረግን ነው ሲሉ በይፋ ያስታወቁ ሲሆን መንግስት በበኩሉ ተቃዋሚዎች ጉዳዩን ለፖለቲካዊ ጥቅማቸው እያዋሉት ነው ሲል ተችቷል፡፡ መንግስት ጥፋት ሲፈፅም ይከሰሳል ወይ የሚለውን በተመለከተ ግን ቁርጥ ያለ መልስ የምናገኘው ምናልባት ወደፊት ሊሆን ይችላል፡፡
ሶስቱ አነጋጋሪ የዓመቱ ምርጫዎች
በ2005 ዓ.ም ከተከናወኑ አበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች መካከል የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤት ምርጫ ይጠቀሳል፡፡ በሚያዚያ ወር በተካሄደው ምርጫ ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች “ምርጫ ቦርድ ለጥያቄያችን ምላሽ አልሰጠንም” በሚል ራሣቸውን ያገለሉ ሲሆን በዚህም አጋጣሚ “33 ፓርቲዎች” በሚል የጋራ መሠባሠቢያ መድረክ ለመፍጠር ችለዋል፡፡ ኢህአዴግ በምርጫው በተወዳደረባቸው አካባቢዎች ሁሉ ማሸነፉን ምርጫ ቦርድ የገለፀ ቢሆንም ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ኢህአዴግ ለብቻው ተወዳድሮ ለብቻው አሸንፏል በማለት ምርጫው “ፍትሃዊ” አልነበረም ሲሉ ተቃውመዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ለአምስት አመት ያስተዳደሯትን ከንቲባ ኩማ ደመቅሳን አሰናብታ አዲሱን አቶ ድሪባ ከማልን የተቀበለችውም ባሳለፍነው ዓመት ነበር፡፡
የተጠናቀቀው አመት ከፖለቲካዊ ምርጫ ባሻገርም የሃገሪቱ ዋና ዋና ሃይማኖቶች መሪዎች ምርጫም አስተናግዷል፡፡ በጥቅምት ወር ላይ በውዝግብ የታጀበው የኢትዮጵያ እስልምና ምክር ቤት አመራሮች ምርጫ የተካሄደ ሲሆን በየካቲት ወር ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ተካሂዷል፡፡ በእስልምና ምክር ቤት ምርጫ ሼህ ኪያር መሃመድ አማን በፕሬዚዳንትነት ሲመረጡ በፓትርያርክ ምርጫው አቡነ ማትያስ ተመርጠዋል፡፡
መንግስት ሙስና ላይ ያመረረበት ዓመት
ኢህአዴግ በሥልጣን ላይ በቆየባቸው 21 ዓመታት እንደ ዘንድሮ በሙስና ላይ አምርሮ አያውቅም ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች፡፡ ነገሩ እውነት ይመስላል፡፡ በግንቦት ወር መጀመርያ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ከፍተኛ ሃላፊዎች፣ ሠራተኞች፣ ደላላዎችና ባለሃብቶች በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታስረዋል፡፡ በሚኒስትር ማዕረግ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፋንታ፣ የህግ ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እንዲሁም የአቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ እሸቱ ወልደሠማያትን ጨምሮ ሌሎች የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም ትላልቅ ባለሃብቶች በአጠቃላይ ከ60 በላይ ተጠርጣሪዎች ታስረው ጉዳያቸውን በፍ/ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ከታዋቂ ባለሃብቶች መካከልም የኬኬ ኃ.የተ.የግ.ማህ. ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ፣ የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባለቤት አቶ ስማቸው ከበደ፣ የነፃ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር እና ሌሎችም ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ ይገኙበታል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ዘጠኝ የስራ አመራሮችም በሙስና ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው በዚሁ ዓመት ነው፡፡ ከሙስና ጋር በተያያዘ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትም ከሃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃነ ሃይሉ እንዲሁም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዳሬክተርና ሁለት ምክትሎቻቸው ይገኙባቸዋል፡፡
መንግስት ከአቅሙ በላይ አቅዶ ይሆን? (የቤቶች ፕሮግራም)
ባለፈው ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ ትኩረት ሠጥቶ ከተንቀሳቀሰባቸው ጉዳዮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው አዲሱ የቤት ፕሮግራም ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ሠዎች ይመዘገባሉ በተባለለት የቤት ፕሮግራም፣ 10/90፣ 20/80፣ 40/60 እና የማህበራት በሚል አራት ቦታ ተከፋፍሎ የቀረበ ነው፡፡ የቤት ፕሮግራሙ ውጤታማ ይሆናል አይሆንም የሚለው ጉዳይ ሲያወዛግብ የከረመ ሲሆን መንግስት በቁርጠኝነት አሣካዋለሁ ሲል ተቃዋሚዎች ደግሞ ስኬቱ ያጠራጥረናል ብለዋል፡፡ ከዚሁ የቤት ፕሮግራም ጋር በተያያዘ ተመዝጋቢዎች የቁጠባ ሂሳብ በመንግስት ባንክ ብቻ እንዲከፈቱ መደረጉ ለግል ባንኮች ስጋት እንደሆነ መነገሩ የሚታወስ ሲሆን የግል ባንኮች ብዙ ደንበኞቻቸውን እንዳጡም መግለፃቸው አይዘነጋም፡፡
2005 ዓ.ም እነዚህን ዋና ዋና አነጋጋሪና አወዛጋቢ ጉዳዮችን አስተናግዶ አልፏል፡፡ አዲሱ ዓመትስ? አብረን የምናየው ይሆናል፡:

ኢትዮዽያዊያን ስደተኞች በሱዳን ፖሊሶች መጠነ ሠፊ በሆነ የአፈሳ ፕሮግራም እየተያዙ ወደ እስር ቤት እየታጐሩ ነው

ኢትዮዽያዊያን ስደተኞች በሱዳን ካርቱም ከተማ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 07/2013ዓ/ም ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በሱዳን ፖሊሶች መጠነ ሠፊ በሆነ የአፈሳ ፕሮግራም እየተያዙ ወደ እስር ቤት እየታጐሩ ነው ፖሊሶች የሚይዙበት መታወቂያ ያልያዘና ያላደሰ በሚል ምክንያት ኢትዮዽያዊያን በብዛት በሚኖሩበት ሠፈርና በሚሰሩበት አካባቢ ነው ለአብነት ለመጥቀስ ያህል :
1.saዉራ ዘጎሎና ኸምስታአሸር
2.እምበዳ ጀሚአብ ጃሚ ማካዊ
3.እምበዳ wa ሂዱ እሽሪን
4. ኦምዱሩማን ሱቀ ሻቢ በሌሎችም ሠፈሮች ናቸው
ፖሊሶች በሺህ የሚቆጠሩ ethiopian ዜጐጎቻችንን ሠብአዊነት በጐጎደለው ጭካኔ በተሞላበት ምንም ሳያጠፉ እየተሰደቡና እየተደበደቡ ሞባይላቸውንና ገንዘባቸውን አየተቃሙ ወደ እስር ቤት እየገቡ ነው ጉዳዩን ለUNHCR እና ለኢትዮዽያ ኢምባሲ betedegagami ብናሳውቅም minim aynet መፍቴሄ የለውም አብሶ አፈሳው ከእለት እለት ተጠናክሮ ketlual እርስዎ ይህን ጉዳይ ለኢትዩዽያ ህዝብ እንዲያውቀው bemadregina ችግሩን ለሚመለከተው አካል እንዲያቀርቡልን እጠይቃለሁ ከትህትና ጋር !! ከድር ሙሀመድ

አርከበ ‘ለቀቀ’ ወይስ ‘ከዳ’??

አርከበ ዑቅባይ ከህወሓት ጉባኤ በኋላ ስራው በአግባቡ እንደማይሰራ እንዲሁም በቅርቡ ከነቤተሰቡና ከወንድሙ አቶ ጌታቸው ጋር ፓርቲውና ሐላፊነቱ ትቶ አሜሪካን ሀገር መግባቱ ፅፌ ነበር። ‘ፓርቲውና ሐላፊነቱ ትቶ አሜሪካ ገባ’ ማለትና ‘ፓርቲውና ሀገሩ ከዳ’ ማለት ፍፁም የተለያዩ ናቸው። እኔ አርከበ ‘ከዳ’ ብዬ አልፃፍኩም። አርከበ አልከዳም፣ ለቀቀ እንጂ።
ፓርቲ ወይ ሀገር መክዳት (defect ማድረግ) ሌላ ከባድ ነገር ነው። አርከበ ፓርቲውና ሀገሩ እስካልከዳ ድረስ እንደማንኛውም ዜጋ ወደ ሀገሩ መመለስ ወይ ከሀገሩ መውጣት ይችላል። መክዳት ወይ defect ማድረግ የራስን ፓርቲ በመተው የሌላው ተቃራኒ ፓርቲ እስከመቀላቀል ይደርሳል። ስለዚህ ዳንኤል ብርሃነ Daniel Berhane) መልቀቅና መክዳት አትቀላቅል። ያልተፃፈውን አታንብብ።
ሌላው የተክለወይኒ አሰፋ ጉዳይ ነው። አንድ ግዜ ተክለወይኒ ወደ አሜሪካ ሂዶ እዛው መቅረቱና ይህን መረጃ የሰማሁትና ራሴ ያላረጋገጥኩት መሆኔ በመጥቀስ ፅፌ ነበር። አሜሪካ መቅረቱ ትክክል ነበር። እርግጠኛ ያልሆንኩበት መረጃ በምን ጉዳይ እንደቀረ ነበር።
በኋላ እንዳረጋገጥኩት ግን ተክለወይኒ አሜሪካ የቀረው ለሕክምና እንጂ ለፖለቲካ ጥገኝነት አልነበረም። እናም ከጤና ምርመራ በኋላ ተመልሶ መጣ። ወድያው ትግራይ ከገባ በኋላ ወደ ሀገሩ መግባቱ ፅፌያለሁ። ተክለወይኒ ከአሜሪካ መመለስ ከነበረት ግዜ በሃያ (20) ቀናት ግዜ ዘግይቶ ነበር የገባው። ከጓደኞቹ ጋር አልነበረም የተመለሰው፤ ግን የዘገየው ለጤና ምርመራ ነበር።
አሁን ደግሞ የህወሓት የትግራይ ቁልፍ ሰው አቶ ቴድሮስ ሓጎስ በጠና ታሞ በአሜሪካን ሀገር ሕክምና እየተደረገለት ነው።
It is so!!!
Abraha Desta

Saturday, 14 September 2013

የፖለቲካ ካሊፕሶ (ከተስፋዬ ገብረአብ)

(ከተስፋዬ ገብረአብ)
ለኢትዮጵያ የ2006 አዲስ አመት እንኳን አደረሰን!
በተጨማሪ ለኤርትራ የቅዱስ ዮሃንስ በአል እንኳን አደረሰን!
በኢትዮጵያና በኤርትራ የምትገኙ የበአሉ ባለቤቶች ሁሉ እንኳን አደረሳችሁ!!
እንዲህ ለኢትዮጵያና ለኤርትራውያን በዘዴ ሰላምታ ማቅረቡን ከቴዲ አፍሮ ነው የተማርኩት።
ቴዲ ገና በወጣትነቱ የፖለቲካ ካሊፕሶ ገብቶታል። ቴዲ አፍሮ ባለፈው ሃምሌ ወር አምስተርዳም ላይ
ኮንሰርት አቅርቦ እንደነበር ሰማሁ። እኔ እንኳ ለእረፍት ወጣ ብዬ ስለነበር አመለጠኝ። እንደሰማሁት
ከ40% በላይ ታዳሚዎቹ ኤርትራውያን ነበሩ። የኤርትራን ባንዴራ ይዘው ቀወጡት አሉ። እሱም
“ፊዮሪና ጓል አስመራን” ደጋግሞ ዘፈነላቸው። ዘፍኖ ሲጨርስ የኤርትራን ባንዴራ ሸለሙት (አለበሱት?)
ብለው ነገሩኝ። ድንቅ ነው። ቴዲ ወደ አስመራ ብቅ ብሎ ኮንሰርት ቢያቀርብ ርግጠኛ ነኝ አስመራ
ስታድየም አይበቃውም። እንዲህ ያለውን የፖለቲካ ካሊፕሶ ሄለን መለስም ብትሞክረው አይከፋም።
ከጋሽ ግርማ ይልቅ ሄለን እና ቴዲ አዲሳባ – መቀሌ – አስመራ አንድ ዙር ጉዞ ቢያደርጉ ተአምር
መፍጠር የሚችሉ ይመስለኛል። መቼም የድንበር ውዝግቡን ባይፈቱትም፣ ያንዣበበውን የጥላቻና
የጦርነት ደመና መግፈፍ አይሳናቸውም።
ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከትናንት በስትያ አንድ ነጣላ ቀልድ መልቀቃቸውን
የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ላይ ሰማሁ። አስመራ ለመሄድ ማሰባቸውን ተናገሩ። ጋሽ ግርማ እንድችው
እንደቀለዱ የስልጣን ዘመናቸውን ጨረሱ። ከዚህ ቀደም ቢያንስ ሶስት ጊዜ እንደተኮረኮረ ሰው
አስቀውኛል።
አንድ ጊዜ 12 ሙሉ ሱፍ ልብሳቸውን ለተቸገሩ ሰዎች ማበርከታቸው ተሰማ። በመሰረቱ
የተቸገረ ሰው የእሳቸው ልብስ ሊበቃው አይችልም። አስጠብበው ይለብሱታል ቢባል እንኳ፣ በጣም
ሞራል ይነካል።
ሌላ ጊዜ ደግሞ ፓርላማ ላይ ቀርበው፣
“ቆሜ የማልናገረው በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ነው” ብለው ይቅርታ ጠየቁ።
እንቅልፋሙ የወያኔ ፓርላማ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልቡ ሳቀ። ደግ አደረጉ! ቁጭ ከማለት መሳቅ
ይሻላል። ለነገሩ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቤቴ ስለሌለኝ ይህን ትርኢት በቀጥታ አልሰማሁትም ነበር።
ኤልያስ ክፍሌ መቼም ክፉ ነው። “ፕሬዚዳንት ግርማ ይቅርታ ጠየቁ!” ብሎ ዜና ሰራ። “ምን ይሆን?”
ብዬ ሰፍ ብዬ ብገባ ነገሩ ሌላ ነበር።
ሌላ ጊዜ ደግሞ ጋሽ ግርማ፣
“ፕሬዚዳንት እንደምሆን ወላጅ እናቴ ህልም አይታ ነበር” ማለታቸውን ሰማሁ።
ይኸው እንግዲህ በመጨረሻ የኢትዮጵያና የኤርትራን የድንበር ውዝግብ ለመሸምገል ወደ
አስመራ መጓዝ እንደሚፈልጉ ሰማን። የሚገርመው የያዙት የመፍትሄ ሃሳብ፣ “በአከራካሪው መሬት
ላይ የሚገኘው ህዝብ የሚመርጠውን መፈፀም ይገባል” የሚል ነው። ይህን ለሻእቢያ ለመንገር አስመራ
ድረስ መጓዝ አያስፈልጋቸውም። ሰው ቢያማክሩ ይሻላቸዋል። በርግጥ አስመራ የሚገኙ የቀድሞ ወዳጆቻቸውን ለመጠየቅ፣ የባለቤታቸውን ዘመዶች ለማየት፣ እግረመንገድ ደግሞ ምፅዋ ብቅ ብለው
አሸዋ ላይ ለመቀበር ቢጓዙ አይከፋም።
ባሳለፍነው አሮጌ አመት በርካታ የፖለቲካ ካሊፕሶ ተመልክተናል።
የመለስ ራእይ መለስን ሲደበድብ ታዝቤ ከልቤ ተገርሜያለሁ። “የመለስን ራእይ እናስፈፅማለን!”
እያሉ ከፍ ባለ ድምፅ ቢናገሩም መለስ ቁልፍ ቦታ ያስቀመጣቸውን ቁልፍ ሰዎቹን ይመነጥሯቸው
ይዘዋል። መለስ የመቃብር ሳጥኑን በርግዶ ቢነሳ መጀመሪያ የሚፈፅመው ነገር ቢኖር፣ አዜብን ወደ
ኤፈርት ይመልሳታል። ገብረዋህድን ከእስር በመፍታት ስልጣን ጨምሮ ይሰጠዋል። ወልደስላሴን
በጌታቸው አሰፋ ቦታ ያስቀምጠዋል። በመጨረሻ አባይ ፀሃዬን ወደ እስርቤት ይልከው ነበር።
ህወሃት የእርስበርስ ጦርነት በማድረግ ላይ መሆኑን እየሰማን ሰንብተናል። ጦርነቱ በመቀሌ
እና በአዲሳባዎች መካከል መሆኑ ተሰምቶአል። የአዲሳባዎቹ መቀሌ ላይ እጅ አላቸው፡፤ የመቀሌዎቹም
በአንፃሩ አዲሳባ ላይ መረባቸውን ዘርግተዋል። ብአዴን ቋሚ የምክትልነት ወንበሩን ለደመቀ መኮንን
መሰጠቱን ካረጋገጠ በሁዋላ “ድርሻዬን አጊኝቻለሁ” ብሎ የህወሃትን የርስበርስ ጦርነት ዳር ላይ ቆሞ
ይመለከታል። ኦህዴድ አለ ይባላል እንጂ በህይወት የለም። እነርሱም “አልሞትንም!” ብለው
አልዋሹም። ሌንጮ እና ዲማ ሸገር ገብተው በወደቀ ዋጋ እስኪገዟቸው እየጠበቁ ይመስላሉ። ህወሃት
ከሚያንገላታቸው ይሻላቸዋል።
የፖለቲካው ካሊፕሶ በዚህ አላበቃም። እመለስበታለሁ…
የሰላም አዲስ አመት ያድርግልን።
(በነገራችን ላይ “የስደተኛው ማስታወሻ” የተባለ መፅሃፍ ፅፌያለሁ። 418 ገፆችና 39
ምእራፋት ይዞአል። ለመግዛት ወይም ለማከፋፈል የምትፈልጉ ነፃነት አሳታሚን ጎብኙ። በትክክል
ለገበያ የሚቀርብበትን ቀን፣ የሚሸጡባቸውን ከተሞች ዝርዝር በድረገፃቸው ላይ እንደሚገልፁ
ነግረውኛል። http://www.npabooks.com)

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሕዝብ ጋር ሊወያዩ ነው



(ዘ-ሐበሻ) የግንቦት 7 ንቅናቄ አመራር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እሁድ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2013 በዋሽንግተን ዲሲ/ ቨርጂኒያ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሕብረተሰቡ ገለጻ ለማድረግ ሕዝባዊ ስብሰባ መጥራታቸውን የመርሃ ግብሩ አዘጋጆች ለዘ-ሐበሻ በላኩት በራሪ ወረቀት አስታወቁ። “የወቅቱ የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታና ለነፃነትና ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል ላት ገለጻ ይደረጋል” በሚል በአርሊንግተን ቨርጂኒያ ከቀኑ 2 ሰዓት ጀምሮ የተጠራው ይኸው ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ሰፊ የጥያቄና መልስ ክፍል ስለሚኖረው ማንኛውም ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያን ወዳጅ በመገኘት እንዲሳተፍ አዘጋጆቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ለዚህ ሕዝባዊ ውይይት መድረክ የመጥሪያ በራሪ ወረቀት የሚከተለው ነው::

Monday, 9 September 2013

“በስልጣን ምክንያት ህወሓት ለሁለት የተከፈለ ይመስለኛል” – አቶ ገብሩ አስራት (ቃለ ምልልስ)

246522dcb1a158f71378732826
sep 9,2013
ሐገር ቤት የሚታተመው ሎሚ መጽሔት አቶ ገብሩ አስራትን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አነጋግሯቸዋል። ዘ-ሐበሻ ለአንባቢዎቿ ይጠቅማል በሚል እንደወረደ አቅርባዋለች።
ሎሚ፡- ባለፈው መቀሌ ላይ “አረና” ሕዝባዊ ስብሰባ አከናውኖ ነበር፡፡ የነበረው ሁኔታ በአጠቃላይ ምን ይመስል ነበር;
አቶ ገብሩ፡- እንግዲህ የመቀሌውን ስብሰባ ከሁለት ጉዳዮች አንፃር ልንመለከተው እንችላለን፡፡ አንዱ ሕዝቡ እንዴት እንደተቀበለው ስብሰባውን … ሁለተኛው መንግስት ወይም በክልሉ ያለው ፓርቲ ስብሰባው እንዳይካሄድ ያደረጉትን ጫና በተመለከተ መመልከት ይቻላል፡፡ እንግዲህ አስቀድሜም መንግስት ስብሰባው እንዳይካሄድ የፈጠረውን ጫና ነው የማየው፡፡ እንግዲህ ትግራይ ውስጥ ገዢው ፓርቲ ህወሓት ነው፡፡ ህወሓት ከእሱ ውጭ ሌላ ፓርቲ እዛ ቦታ ላይ እንዲንቀሳቀስ ፍላጐት የለውም፡፡ ይህም ባፈለው 2002 ዓ.ም. በተካሄው ምርጫ ጠ/ሚ መለስ ትግራይ ውስጥ ምንም አይነት ክፍተት መኖር የለበትም፣ ምንም አይነት የሀሣብ ልዩነት መኖር የለበትም ብለው የተናገሩበትና በርካታ ስድቦች የተሰነዘረበት በተለይም በ”አረና” ላይ በርካታ ስድቦችን ያወረዱበት ጊዜ ነበር፡፡ እንግዲህ አሁን ያለው አመራርም የእሣቸውን “ሌጋሲ” ፈለግ እከተላለሁ የሚል ስለሆነ አካሄዱ ተመሳሳይ ነው፡፡ በትግራይ ውስጥ ምንም አይነት የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዲኖር አይፈልግም፡፡ በህገ መንግስትም ፣ በቃልም ተቃዋሚ ቢኖር አንጠላም ሊሉ ይችላሉ፡፡ ዋናው ስጋታቸው በአካባቢው የተለየ ሀሣብ ፣የተለየ አመለካከት ፣ የተለየ አደረጃጀት እንዳይኖር ስጋትና ጭንቀት ያለባቸው ስለሆነ አጠቃላይ ድርጅቱን በእነሱ ስር የተደራጀ ሲቪክ ማህበረሰብ፣ የመንግስት ድርጅቶችን አደራጅተው ነው አንድ ፓርቲ በዛ አካባቢ ስብሰባ እንዳያካሂድ የሚያደርጉት፡፡ ባለፈው ጊዜም ስብሰባ ስናካሂድ እንደውም እነሱ በሚመሯቸው ድርጅቶች ፣ ኩባንያዎች /ኢፈርት/ ሠራተኞችን ሰብስበው በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት ከጠላት ጋር እንደማበር ይታሰባል ብለዋቸዋል፡፡ እና ስለዚህ ስራ ለማግኘት አትችሉም፣ ስጋት ላይ ትወድቃላችሁ ፣ ከጠላት ጋር የመተባበር ያህል አድርገን ነው የምናየው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡
ይህንን ካሉ በኋላም በዚህም አላበቃም በኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ መሠረት እንደተፈቀደው ማንም ፓርቲ ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ መቀስቀስ የማይችለው በትምህርት ቤትና በቤተ እምነት ቦታ ውስጥ እንጂ በሌላ ቦታ ድምፅ ማጉያ ተጠቅሞ መቀስቀስ ይችላል የሚል ነገር አለ፡፡ መቀሌ ላይ ግን ሌላ ህግ አውጥተዋል ወይም አውጥተናል ነው የሚሉት፡፡ እኛ ግን አላየነውም፣ ህጉ ምንድነው የሚለው ማንኛውም እንቅስቃሴን ማጉያ ተጠቅሞ መቀስቀስ አይቻልም ነው የሚሉት፡፡ ይሄ እንግዲህ ከሀገሪቱ ህግ ፣ ከፌዴራል ህግ ጋር የሚጣረዝ ህግ ነው፡፡ ህግም ቢሆን …read more,,http://www.zehabesha.com/amharic/archives/7183

Saturday, 7 September 2013

እጃቸው የኋሊት ከተጠፈረ በኋላም አቶ ነጋ እንዲህ አሉ። “በቃ! ህወሃት አበቃለት!”

ክንፉ አሰፋ
በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች “ጸዳ” ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና
አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ
ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ።
በዚህ ያልተለመደ ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። ይልቁንም የፌዴራል ፖሊሶቹ ለተጨማሪ ጥበቃ የመጡ ነበር
የመሰላቸው። አንድ ብርጌድ ያህል ጦር አስከትለው የመጡት ፖሊሶች ግን አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄርን አስጠሯቸው። አቶ ነጋም ለጥሪው
እንደወትሮው በመወጣጠርና ፍጹም ትእቢት በተሞላበት አነጋገር ምላሽ ሰጡ። በፖሊስ አባላቱ እና በአቶ ነጋ መካከል የሃይለ-ቃል
ልውውጥ ተጀመረ። እሰጥ እገባው አንድ፣ ሁለት እያለ ሄደና በመጨረሻ ተካረረ። በዚህ ሰዓት አቶ ነጋ ስልክ መደዋወል ያዙ። ከፍተኛ
የሚባሉ ባለስልጣናትና ምኒስትሮች ጋ ደወሉ። ከዚያም በመቀጠል፣ ጀነራሎች ጋ ደወሉ… የጦር መኮንኖች፣ የፓርቲ ባለስልጣናት…
ሁሉም ጋ ተደወለ። የባለስልጣናቱ ምላሽ ግን ጥሩ እንዳልነበር ከአቶ ነጋ ፊት ላይ ይነበብ ነበር። ወዳጆቻቸው ሁሉ እንደ ቱኒዚያው ቤን
አሊ በአንድ ጊዜ ከዷቸው።
“በል – ና – ውጣ!” አለ አንደኛው የፖሊስ አባል፣ የስልኩን ሽርጉድ በጥሞና ከተከታተለ በኋላ።
“ምን ማለትህ ነው? እኔኮ ነጋ ነኝ። ነጋ ታሪኩ!” አሉ። አነጋገራቸው የጀምስ ቦንድን ይመስል ነበር። በዚህ ጊዜ ታዲያ እጃቸውም
አላረፈም። ከጎን ያሸጎጡትን መሳርያ ለማውጣትም ዳዳቸው።
በቅጽበት ግን ፌዴራል ፖሊሱ ቀደማቸው። በድንገት “ጯ!” የሚል ድምጽ አዳራሹን አናጋው። የፖሊሱ አይበሉባ የግራ
መንጋጭላቸው ላይ ሲያርፍባቸው ጊዜ፤ አይቴ ነጋ ነገር አለሙ ተደበላለቀባቸውና እጅ መስጠትን መረጡ። ግብር ሊያበሉ በጠሯቸው
የክብር እንግዶቻቸው ፊት፣ ከዚህ በላይ መዋረድ አልፈቀዱም። ሁለት እጃቸውንም ወደ ፖሊሱ በመዘርጋት ለብረት ማሰርያው
ራሳቸውን አመቻቹ። እጃቸው የኋሊት ከተጠፈረ በኋላም አቶ ነጋ እንዲህ አሉ። “በቃ! ህወሃት አበቃለት!”
“ባለሃብቱ” በዚህ ሁኔታ በፖሊስ መኪና ተጭነው ወደ እስር ቤት ሲሄዱ፣ ተጋባዥ እንግዶቹም እግሬ-አውጭኝ እያሉ
ከስፍራው አፈተለኩ። ይህ ታሪክ ድራማ ሊመስል ይችላል። ግን በእውን የተፈጸመ ሃቅ ነው። ታሪኩን ያጫወተኝ ሰውም እዚያ ግብዣ
ላይ ግብር ሊበላ ተገኝቶ ነበር። እንደ አግራሞቱም “ይህ መቼም የፈጣሪ ስራ ነው።” ከማለት ውጪ ስለ ጉዳዩ እንድምታ የሰጠው
ማብራሪያ የለም።
ነጋ ገብረእግዚአብሄር የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ (ሰዎች ያልተወሰነ ይሉታል) የግል ማህበር ባለቤት ነበሩ። ድርጅታቸውም
እንደስሙ ከሁሉም ነገር ነጻ ነበር። ከግብር ነጻ፤ ከቁጥጥጥር ነጻ፤ ከፍተሻም ነጻ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጭነት መኪናዎች እቃ ጭነው
በየኬላው ሳይፈተሹ እንዲያልፉ የተሰጠ ልዩ መብት ሁሉ እንደነበራቸው ይነገራል። ዛሬ ፈጣሪ ሲፈርድባቸው በኢፍትሃዊ መንገድ
ቢልየነር ያደረጋቸው ስርዓት፤ ያው ስርዓት ሰለባ አደረጋቸው… ነጋ ገብረእግዚአብሄር ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው ለወ/ሮ አዜብ
መስፍን ቅርብ – በጣም ቅርብ ነበሩ። ለጉምቱ ባለስልጣናት ይሰጡት የነበረው እጅ መንሻ ከዚህ አይነት ውርደት እና እስራት ሊያድናቸው
አልቻለም። በትግራይ ውስጥ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አውጥተው በስማቸው ያሰሩት የቴክኒክ ኮሌጅም እንደ ውለታ
አልተቆጠረላቸውም።…
ይህችን አጭር መጣጥፍ ለመጫር እንደተቀመጥኩ አንድ ዜና በኢሜይል ደረሰኝ። የዜናው ርእስ “ጀነራል ባጫ ደበሌ
የአዋሽ ባንክ ሰራተኞችን ከሥራ እንዲባረሩ አደረጉ!” ይላል። ባጫ ደበሌ የባንክ ሰራተኞቹን ያባረሩዋቸው ‘’እኔ ጀነራል ባጫ ደበሌን
እንዴት አታውቁኝም?’’ በሚል በሰራተኞቹ አለመታወቃቸው አበሳጭቷቸው ነበር። ወደ ፌስ ቡክ ጎራ ስልም አንዳንዶች በዜናው ላይ
ሲወያዩ አስተዋልኩ። ይህ እኮ አዲስ ክስተት አይደለም። ለብዙ ጊዜ የሚደጋገም እና የተለመድ ነገር ዜና ሊሆን አይችልም። ውሻ ሰውን
ሲነክስ ዜና አይሆንም። በተቃራኒው ግን ሰው ውሻን ከነከሰ ዜና ይሆናል። እንዲህ አይነቱ ክስተት ስር የሰደደ የስርዓቱ ባህርይ ነው። ባጫ
ደበሌ እነዚያን ሰዎች ማስገደል የሚያስችልም ስልጣን እና መብት ያላቸው የአዜብ ሰው መሆናቸውን አንዘንጋ። ጀነራል ባጫ በተልእኮ
ትምህርት ከአንድም ሁለተኛ ዲግሪ እንዲገዛላቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለምርቃታቸው ስነ-ስርዓት፣ ሰንጋዎች ጥለው፣ የሙዚቃ ባንድም
አስመጥተው፣ መንገድ ሁሉ እንዲዘጋ አድርገው ሲያበቁ፤ በተለመደው ብሬክ ዳንሳቸው መንደሩን የቀወጡ ሰው ናቸው። በብርሃን
ፍጥነት ከኪነት ጓድነት ወደ ጀነራል የተሸጋገሩት ባጫ ደበሌ በመደበኛ የስራ ጊዜያቸው ጫት ይነግዳሉ። በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞየሙስናው ጉዳይ ገጽ 2
በዜጋው ላይ እንዲሁ እንደዋዛ እየቀለዱ እስካሁን አሉ። የነገውን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው። የፍትህ ሳይሆን የግለሰቦች የበላይነት
የሰፈነበት ሃገር ስልጣንን ያላግባብ መጠቀም ሙስና ሊደንቀን አይገባም። የፍትሃዊ ስርዓት መጥፋት ነው ሙስና።
ፕሮፌሰር አል ማርያም ባለፈው መጣጥፉ ስለሙስና ሲጽፍ ከሙስና ሁሉ በላይ ሙስና የሚሆነው የፍትህ መጓደል እንደሆነ
አስነብቦናል። የፍትህ መጥፋት ስብእናን፣ ነጻነትንና ንብረት ማጣትን ያስከትላልና። In my view, denial of due process (fair
trial) is the highest form of corruption imaginable in the “justice sector” because it results in the
arbitrary deprivation of a person’s life, liberty and property. (Al Mariam)
ከሰሞኑ ደግሞ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አፍርተሃል በመባል ተወንጅሎ ወህኒ የወረደው
የወልደስላሴ ወልደሚካኤልም ዜና በስፋት እየተሰራጨ ነው። ወልደስላሴ ሌላኛው የአዜብ መስፍን የቅርብ ሰው ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ
ዳዊት ከበደ በስፋት ትንታኔ ስለሰጠበት እዚህ ላይ አልደግመውም። ወልደስላሴ ግን ከህወሃት የጫካ ትግል ጀምሮ ቀልፍ ቦታዎች ላይ
ተመድቦ የሰራና – የመለስ ቀኝ እጅ የነበረ ሰው ነው። ታማኝ አገልጋይም ስለነበረ በህወሃት ውስጥ ወሳኝ ቦታ ነበረው።
ከወልደስላሴ እስር በኋላ ብዙዎች በህወሃት ውስጥ ውጥረት እንዳለ መናገር ጀምረዋል። ውስጥ ለውስ እየተንከባለለ ያለው
ውጥረትማ ከከረረ ትንሽ ዘግየት ያለ ይመስላል። በውጥረቱ የተነሳም በባለስልጣናቱ መካከል እርስ በርስ መተማመን ከጠፋ ቆየ። አንድ
ውስጥ አዋቂ ስለዚህ ሁኔታ ሲያጫውተኝ አባላቱ በምሽት ሲወጡ እንደ ጅብ ጎን ለጎን ነው የሚሄዱት። ጅብ ስለሚፈራ ብቻውን
አይሄድም። ሁሌም ተጠራርቶ በቡድን ይሄዳል። ከባልንጀራው ጋር አብሮ ሲሄድ ደግሞ ጎን ለጎን መሆን አለበት። ፊትና ኋላ ከሆኑ
እርስበርስ ይበላላሉ።
በአሁኑ የህወሃት አሰላለፍ ግን አንደኛው ወገን ከኋሊት መጥቶ የቀደመ ይመስላል። ከፊት ያለው የኋላውን መብላት
ጀምሯል። ተገላቢጦሽ የሆነው ይህ አስገራሚ ክስተት ነው ውጥረቱን ይበልጥ ያከረረው። የአዜብን ቡድን የማጥፋቱ ሂደት ላይ ግን
ከፍተኛ ጥናት ሳይደረግ አልቀረም። የፖለቲካ ሃይል አሰላለፉ ላይ ሚዛን የደፋው አንደኛው ቡድን ከደሙ ንጹ ባይሆንም የሙስናውን
ወንጀል ለብቀላ መጠቀምያ ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው።
አንዳንድ የዋሆች ታዲያ ይህ የጸረ-ሙስና ዘመቻ አቶ መለስን ለማሳጣት እየተደረገ ያለ ድራማ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ
ሃይለማርያም ደሳለኝንም የሚያመሰግኑም አልጠፉም። አቶ ሃይለማርያም ብዙውን ክስተት እንደ ተራው ሰው በዜና እንደሚሰሙ
የሚያውቁት በቅርብ ያሉት ሰዎች ብቻ ናቸው። ለነገሩ እሳቸውም አስቀድመው “የእኔ ስራ ከፊትም ሆነ ከኋላ የሚሰጠኝን ትእዛዝ
እየተቀበሉ ማስፈጸም ብቻ ነው።” ብለዋል። ከፊትና ከኋላ ብቻ ሳይሆን ከላይና ከታችም መመርያ እየተቀበሉ ያስፈጽማሉ። በሙስናው
ስም የሚካሄደው ጨዋታ ከሳቸው ራዳር ውጭ ያለ መሆኑን ለመረዳት የፖለቲካ ጥበብን አይጠይቅም።
አቦይ ስብሃት በአንድ ቃለ-መጠይቅ ላይ ስለዚህ ጨዋታ ሲናገሩ የ10 ሚሊዮኑ ዘራፊ ቁጭ ብሎ የ10 ሺው መታሰር የለበትም
ብለው ነበር። አቦይ ስብሃት እውነት ብለዋል። ከሌላው ጋር ሲነጻጸር ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ቤት ተገኘች ተብላ በኢቲቪ
ጭምር ስትታይ የነበረችው 26 ሺ ኢሮ ኢምንት ናት። Global Financial Integrity (GFI) በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ የገንዘብ
ግልጸኝነት ተቋም ከ 2001 እስከ 2010 ብቻ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደውጭ የወጣው ገንዘብ 16.5 (አስራ ስድስት ነጥብ አምስት) ቢሊየን
ዶላር ነው ሲል መረጃውን ከነማስረጃው ይፋ አድርጓል። ይህ ድርጊት ደግሞ በሙስና ከዘቀጡ ሃገራት ኢትዮጵያን በመጀመሪያው ደረጃ
ላይ አስቀምጧታል። ልብ በሉ! 16.5 ቢሊየን ዶላር ከአራት በላይ የ”ህዳሴ” ግድቦችን ያሰራል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ መላው
አውሮፓን ከውድቀት ያስነሳው የማርሻል ፕላን በጀት 20 ቢሊየን ዶላር ነበር። ከኢትዮጵያ በስምንት አመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ የወጣው
16 ቢሊየን ዶላር ደግሞ አፍሪካ ካለችበት ውድቀት ሊያስነሳት የሚችል ገንዘብ እንደሆነ የኢኮኖሚ ጠበብት ይናገራሉ።
ኤ.ቢ.ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን ግብይት ብቻ ለልብሷ 1.5 ሚሊዮን
ዶላር እንዳወጣች ዘግቧል። አዜብ መስፍን ባለፈው የህወሃት ስብሰባ ላይ ተገኝታ ስትናገር ግን የአቶ መለስ የወር ደሞዝ 250 ዶላር
እንደሆነ ነበር የተናገረችው። አዜብ የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ልብስ በአንዲት ምሽት ስትሸምት መንግስት ድጎማ አድርጎላት ከሆነ ይኸው
በይፋ ይነገር። በ250 ዶላር የወር ገቢ በሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረግ የሚቻልበት ሚስጥር የአባባ ታምራት ገለቴ ምትሃት ካልሆነ
ታዲያ ምን ሊሆን ይችላል? ይህንን መራራ ሃቅ የጸረ-ሙስናው ኮሚሽንን የሚነዳው ቡድን እንዴት ችላ ሊለው ቻለ? በዚህ ጉዳይ ላይ
በርካታ ታዛቢዎች የሚሰጡት አስተያየት የሚያስኬድ ይመስላል። ቡድኑ በቅድሚያ ወደ እነ አዜብ ሰፈር የሚወስደው መንገድ ላይ
ያሉ ከእንቅፋቶችን ሁሉ ማጥራት አለበት።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደ ቀልድ የሚነገሩ አንዳንድ እውነታዎች ለማመን የሚከብዱ ናቸው። አንዱ ‘ልማታዊ ባለሃብት’
በሪል ስቴት ስም የተመራው ቦታ ሲሰላ ከጅቡቲ የቆዳ ስፋት በልጦ ተገኘ። ይህ ሰው ትንሽ ቆይቶ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በመጠቀም
የመገንጠል ጥያቄም ሊያነሳ ይችላል እያሉ ያወሩ ነበር – በዚያ የቀኑት ባልንጀራዎቹ። በመጨረሻ ግን “ባለሃብቱ” በሙስና ታሰረና ይዞት
የነበረው መሬት ለነ ቱሬ ዘመዶች በሄክታር ሁለት ብር ሂሳብ ተቸበቸበ። ለነገሩ 3.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከዜጋው እየተቀማ
ለውጭ ዜጎች በተቸበቸባት ሃገር ይህ ምንም ላይደንቀን ይችላል።የሙስናው ጉዳይ ገጽ 3
የሙስና ሰለባ የሆነው የሌላኛው ባለስልጣን ቤት ሲበረበር ደግሞ ብሄራዊ ባንክ ይመስል ነበር። እዚያ ቤት ውስጥም የአለም
መገበያያ ገንዘብ ተገኘ። ዶላር፣ ኢሮ፣ ድራም፣ የን፣ ፓውንድ፤ ክሮን፤ ፍራንክ፣ ዲናር፣ ረንቢኒ … እንዲያውም የኤርትራ ናቅፋ በገፍ
ነበር። ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ 26 ሺ ዶላር ተጋንና በቲቪ ስትቀርብ የዚህኛው ንግድ ፈቃድ የሌለው ባንክ በግል እጅ ሲገኝ
ሜዲያም ዝም ማለትን መረጠ። በዚህ ጊዜ ነበር የአሳሪው ቡደን ሃላፊ የኮሎኔል መንግስቱን ንግግር የተጠቀመው። “ደፍረውናል፣
ንቀውናል።.. ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል።”
አነጋገሩ ለምን ሃገር ተዘረፈ ሳይሆን እኛ ታግለን ለዚህ የደረስን የቁርጥ ቀን ታጋዮች ቁጭ ብለን እንዴት ከኋላ የመጣው
ሊበልጠን ቻለ ለማለት ነበር። የሙስናው ዘመቻ ድራማ ቁልፍ እዚህ ላይ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በሰፊው እሄድበታለሁ።
ለአሁን ግን በአቶ ኤርምያስ አመልጋ የሚደነቅ ታሪክ ጽሁፌን ልቋጭ።
በዚያ ሰሞን የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ኤርምያስ ጠቅል አመልጋ፣ በተለይ በውጪ
ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣ ከሃገር መጥፋታቸው ተዘግቦ ነበር። ታዲያ
አቶ ኤርምያስን የሚረግሙ ጌጃ ዲያስፖራዎች እንዳሉ ሁሉ እሳቸውን የሚያደንቁም አልጠፉም። ስለአቶ ኤርምያስ በቀልድ እየተመሰለ
ብዙ ነገር ይወራል። የተከበሩ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን እና አቶ ኤርምያስን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁለቱም የተዋጣላቸው
ሰአሊያን መሆናቸው ነው ተብሏል። ለላሜ ቦራው ዲያስፖራ እንዲሰሩ ገንዘብ የተከፈለባቸው ቤቶች ሁሉ ባማሩ ስዕሎች በወረቀት ላይ
ዱቅ ብለዋል። በንዴት ገንዘቡን ሊያስመልስ የሚሄደው ሁሉ በስእሎቹ እና በአቶ ኤርምያስ ምትሃታዊ ንግግር እየተማረከ እንዲያውም
ለሁለተኛና ሶስተኛ ቤት የከፈለው ዲያስፖራ ቁጥር ትንሽ አይደለም። አቶ ኤርምያስ በአንድ በኩል በሙስና ክስ እየተፈለጉ፤ በሌላ
በኩል ደግሞ ከሃገር በቦሌ አድርገው እንዲወጡ የተደረጉ “ጀግና” ባለሃብት ናቸው።
ለፖለቲካው እንግዳ ለሆኑ ሰዎች፤ እነዚህ ሁሉ ፈጠራ ሊመስሉ ይችላሉ። ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የእለት ተለት ገጠመኞች
ውስጥ አንድ እጅ እንኳን የማይሞሉ እውነታዎች ናቸው።
ethio media
posted by Aseged Tamene