Tuesday, 22 April 2014

ኦሕዴድ እና ኦነግ በጋራ የፈጸሙትን ወንጀል የሚያጋልጥ ታሪካዊ ማስረጃ...



በበደኖ አርባጉጉ አሰቦት አበምሳ እና በቀሪው የኦሮሚያ ክልል የተጨፈጨፉ ዜጎች የማን ትእዛዝ ነበር?
"ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው::" ሀጅ ቃሲም (ኣርባጉጉ)
ምንሊክ ሳልሳዊ
የፕ/ር ዓስራት ወልደየስ የመአሕድ ፕሬዝደንት ሰኔ 1ቀን 1984ዓ.ም ቁጥር መአሕድ /48/84 ለኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ተወካዮች ም/ቤት በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰዉን ጭፍጨፋ እንዲያቆሙ የጻፉት ደብዳቤ ኦሕዴድ እን ኦነግ በጋራ የፈጸሙትን ወንጀል የሚያጋልጥ ታሪካዊ ማስረጃ ነው::
አንድ መቶ አመት ወደኋላ ተመልሰን ዛሬም አእምሮኣችንን እርቃኑን ከማስቀረት ከ100 አመት በፊት ከነበሩ ያልተማሩ መሪዎች ያነሰ የሚያስቡ ባዶዎች በዚህ በሰለጠነ ዘመን የፈጸሙት ወንጀል በትውልዳችን መጠየቅ ሊኖርበት ነው ብንል ባያስኬድም ለሁሉ የሚበጀው ግን መልካሙን ይዞ ማደግ ተመራጭ ነው::

በኣርባጉጉ የአውራጃ የኦህዴድ ተወካይ አቶ ዲማ ጉርሜሳ ግንቦት 26/1984 በአበምሳ ከተማና በኣካባቢው የሚኖሩትን የኦሮሞ ተወላጆችን ስብሰባ ከጠሩ በሆላ "ኣሼ :ኦዴ:ዒመና :ኣቡሌ በሚባሉ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ " በማለት ትዕዛዝ ይሰጣሉ ከተሰበሰቡት የኦሮሞ ተወላጅ መካከል ሀጅ ቃሲም የተባሉ እጃቼውን ኣውጥተው
"ለረጅም ግዜ ኣብረን የኖርን እና የተዋለድን ስለሆን አንፈርምም :የአማራ ህዝብ አይመታም መመታት ያለበት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው " የሚል አስተያየት በማቅረባቼው
የኦህዴዱ ተወካይ በመናደዱ ሽጉጡን ኣውጥቶ "የነፍጠኛ እረዳት ነህ በማለት ማስፈራራት ሲጀምሩ ስብሰባው የሀጅ ቃሲምን ሀሳብ በመከተል ተበተነ ::
ይህንን ባለ 6 ገጽ የፕሮፌሰር አስራትን ፊርማ የያዘ ደብዳቤ ይመልከቱ::
Image

Image

Image

Image

Image

Image

MinilikSalsawi

ወያኔዎች የፋሺስት ሙሶሎኒ ደቀ መዝሙሮች ናቸው- በዶክተር ጌታቸው ረዳ


ገብረኪዳን ደስታ “እምቢ አንጻር ወረርቲ” (በወራሪዎች ላይ እምቢታ) ብሎ በጻፈው ምጽሐፍ ፈላጭ ቆራጭ በነበሩት ግፈኞቹ “የትግራይ መሳፍንት እና የጉልተኞች ዲሞክራሲ” ድንቅነት እና በጐነት ለማሳየት እና ለማስተዋወቅ በተጻፈው የውሸት ክምር ተመርኩዞ “ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም” አስተያየቱን አንዲሰጥ ተጠይቆ፤ ስለ አፄ ዮሐንስ እና ስለ ምኒሊክ፤ ስለ ‘አማራ’ ጻሀፊዎች ብዙ ዘላብዷል።አስቀድሜ አንደተናገርኩት ሙሉወርቅ ጎሰኛ እና አማራ የሚጠላ መሆኑን እኔን ለመቀበል የሚያዳግታቸው ሰዎች ስላሉ በሌላ ሰው አንደበት መረጃየን ላቅርብ። አብርሃ ደስታ ይባላል። አብዛኞዎቻችሁ ይህ ወጣት በመጥፎም በደግም ጽሑፉ የምታውቁት ነው። የጻፈ ሁሉ ደራሲ ነው? በሚል ርዕስ መጣጥፉ ስለ ሙሉወረቅ ኪዳነ መርያም እንዲህ ይላል። አዲስ አበባዎች ሰለማዊ ሰልፉ ሲቀውጡት እኔ ደግሞ ከጓደኞቼ ጋር … የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በመቐለ ከተማ ቅርንጫፍ ስለመክፈቱ ተጋብዘን እየተነጋገርን ነበር። የአዲስ አበባ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁ ደስ ብሎኛል። 
እኔ ግን ስለ ማህበሩ ዉሎ ትንሽ ላካፍላቹ። ምክንያቱም ካደረግነው ዉይይት አንድ ‘ደስ የሚል’ ነገር ስላገኘሁ ነው። የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር በመቐለ ቅርንጫፍ የሚከፍትበት ዝግጅት ጥሩ ነበር። ብዙ ሙሁራን ደራሲያን ታድመው ንግግር አድርገዋል።
ግን በደራሲያኑና በሙሁራኑ ንግግር ቅር ያሰኘኝ ነገር ነበረ። ከክብር እንግዶቹ ሁሌ ‘ሊቃውንት’ ተብለው የሚቀርቡ ዶ/ር ሰለሞን ዕንቋይ፣ መምህር ገብረኪዳን ደስታና መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ነበሩ። ከኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር የተላኩ አራት ደራሲያንም ነበሩ።ንግግርአድርገዋል።
ከኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር የተወከሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው ግን ትግርኛም ይሰማሉ። የአብዛኞቹ ንግግር አልተመቸኝም። ሲበዛ ግብዝ ነበሩ። የሚናገሩት የልባቸው እንዳልሆነ በቀላሉ መገመት ይቻላል። ጥረታቸው ለግዜው እኛ የትግራይ ተወላጆችን ማስደሰት ነበር። በትክክል ግን ማስደሰት ሳይሆን መመፃደቅ ነበር። ትግራይ ሰማይ ሰቀሏት። ከነሱ አንድ ግን ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጠና አስደሰተኝ። ሌሎቹ ግን ‘የእውነት ደራሲያን ናቸው?’ ብዬ ራሴ እንድጠይቅ አድርገውኛል። ግብዝ ደራሲ አልወድም። “የኛዎቹም ተናገሩ። ዶ/ር ሰለሞን ብዙ አላባላሹም። አጠር ያለ ግሩም አስተያየት ሰጡ። መምህር ሙሉወርቅ ለመጀመርያ ግዜ (እኔ እስከሰማሁት ድረስ) ‘አማርኛ ማወቅ ጥሩ ነው’ ብሎ ተናገረ። ገረመኝ፤ አናደደኝም። ግብዝ መሆኑ ነው። ‘አማርኛ ተናጋሪዎች ከመሃከላችን ስላሉና እነሱ ለማስደሰት ስለፈለገ ነው?’ ብዬ ታዘብኩት፤ ምክንያቱም አቋሙ ከዚህ በፊት አውቀዋለሁ። ትንሽ ቆይቶ ግን ወደ ተለመደው የፖለቲካ መዘባረቁ ገባ። ተረጋጋሁ። ምክንያቱም ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተመልሷል። እንደወትሮው ለሸዋ ታሪክ ፀሃፊዎች መውቀስ ጀመረ። » እኔ ደግሞ ግራ ሲገባኝ ‘ሁሉም ፀሓፊ ደራሲ ነው እንዴ? ለምንድነው የታሪክ ተመራማሪዎች እንደ ደራሲያን አድርገን የምንቆጥራቸው? ድርሰት እኮ ጥበብ ነው፣ መፃፍ መቻል ግን ክህሎት ነው።’ ብዬ ጠየቅኩ። (የጻፈ ሁሉ ደራሲ ነው? አብርሃ ደስታ) ከላይ በአበርሃ ደስታ አንደተገለጸው ሙሉ ወርቅ ኪዳነማርያም ማለት ይህ ነው።
ሙሉወርቅ የዚህ ትምክህተኛ ቡድን አገልጋይ ሆኖ ሳዳምጥ በጣም ነው የገረመኝ። ዮሐንስ አዳራሽ መኝታ ክፍላቸው ውስጥ በተደረገው የገብረኪዳን ደስታ መጽሐፍ ድጋፍ አንደለፈፈው ትግሬዎች በብዙ የታሪክ ሰነዶች ድሮም ይሁን አሁን እንኳ በቅርቡ በባድሜ ጦርነትም ይሁን በዓድዋ፤በማይጨው ጦረነቶች ሁሉ ትግሬዎች ባካባቢያቸው የተከሰቱ ጦርነቶች ብቻቸውን አልገጠሙዋቸውም። እንኳን እና ድሮ በርሃብ፤በተላላፊ በሽታ፤በወባ፤ እና ባስቸጋሪ ክረምት የሰው ሃይል እና የስንቅ ምንጭ በሚያስፈልግበት ወቅት ብቻቸውን ሊዋጉ ቀርቶ፤ አሁን ሁሉም በእጃቸው ባደረጉበት ጦሩም ፤ሃብቱም፤ስልጣኑም፤ አይሮፕላኑም፤ መድሃኒቱም፤ፋብሪካው እና ማጓጓዣው በቁጥጥራቸው ባደረጉበት ወቅት አንኳ ‘ሻዕቢያን’ ከባድመ፤ከዓሊተና፤ከዛላምበሳ.፤ከባዳ…. መግፋት አቅቷቸው ለሁለት ዓመት የትግራይ ድንበር ተወርሮ፤ ያካባቢው ድምበር ኗሪዎቹ ተፈናቅለው፤ መኖርያ ቤቶቻቸው እየተቃጠሉ ፤ኗሪዎች እየተገረፉ እና እየተጠለፉ፤ ጫካው እየተመነጠረ፤ ድንጋዩ እየተፈነቀለ “የሻዕቢያ” ምሽግ ማጠናከሪያ ሆኖ ሁለት አመት ሲቆይ “እርዱን” ተብሎ ነው የድሮ ሰራዊት ሳይቀር እየተለመነ ተመልሶ በመታጠቅ ‘ሻዕቢያን” ድባቅ የመታው እና እስከ ባረንቱ፤ ተሰነይ እና ሰንዓፈ ገብቶ ያራወጠው። ይህ የዓምና ታሪክ ነው፡ አንዴት ልንረሳው አንችላለን? ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ፡እነ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም “በሰሜን የተደረጉ ጦርነቶች በሙሉ በትግሬዎች የተካሄደ የትግሬዎች ጀግንነት ነው እያለ ሕዝቡን በጀብደኝነት ሲያሰክሩ ማድመጥ እህግ አስገራሚ ክሰተት ነው። አለማፈር! አታኽለቲ ሓጎስ በትግርኛ እንዲህ ይላል። “ተጋሩ ንኢትዮጵያ መስዋእቲ ዝኾ ኑንን ዘድሓንዋን እየ ገይረ ዝ ወ ስዳ። (ትግሬዎች ኢትዮጵያን ለማዳን ቤዛ የሆኑ ናቸው)።(ቃለ መጠይቅ – ውራይ መጽሄት)
አታኽልቲ ሐጎስ ማለት ‘ሃቅ ሃቁን ለህጻናት’ እና “ደቂቀ ምኒሊክ፤ አይንታሓማመ” እና የመሳሰሉ ጎሰኛ እና ዘረኛ መጽሐፍ የጻፈ የወያኔ ደራሲና ገጣሚ እንዲሁም ሰዓሊ ነው።” እሱም አብሮ አደጌ ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ትግሬዎች (ወያኔን አይጨምርም) በማንኛወም ውግያ ሲሳተፉ በኢትዮጵያዊነታቸው እንጂ “ኢትዮጵያ የተባለች አገራቸው ከጠላት ለመከላከል ቤዛ የሆኑ አንጂ ‘ኢትዮጵያ የተባለች ባዕድ አገር’ ለማዳን የተሰው አይደሉም። የወያኔ ደራሲያን ችግር፤ “ትግራይ እና ኢትዮጵያ” ለያይተው የማየት በሸታቸው የጠነከረ ስለሆነ ማንኛውም ጦርነት ሲካሄድ “ኢትዮጵያ የምትባሉ ፍጡሮች ፈጣሪዎቻችሁም አዳኞቻችሁም እኛ ነን።” የሚል የትምክሕት አበዜ ሲያስተጋቡ ፣የስካራቸው ውሸት መጠን የለውም። ለዚህም ነው መላ ኢትዮጵያ እና መላው የኢትዮጵያ አካባቢሕዝብ የተካፈለበት የአክሱም ስልጣኔ የትግሬዎች ብቻ አድርገው በማጽፍ እና በመሳል በውሸት የሚስሉት፤፡ ይህንን የወያኔ ትግሬ ንብረትና ታሪክ አድርገው የሚያቀርቡት የሌሎችን አስተዋጽኦ እና ክብር የሚጋፋ አስጸያፊ ምሰል አንደናሙና ተመለክቱት። መምህር ገብረኪዳን ደስታ
“ሚኒልክ ወደ ትግራይ የመጣው “ትግሬ ከጠገበ እና አንድ ከሆነ አይገዛም፡ ወይም አይቻልም” የሚል እምነት ነበረዉ። በተጨማሪም የትግራይ ህዝብ “ብዙ ብር” አለው፤ተብሎ ስለሚታመን ገበሬውን “እየዘረፉ” ሃብት ማካበትና ሕዝቡን “ማደሕየትም” “እንደ ስልት” የተያዘ በመሆኑ አስፈላጊ ነበር። አጼ ምኒልክ ወደ ትግራይ ያደረጉት ዘመቻም እነዚህን “ሁለት ነጥቦች” ለማሳካትና ተግባራዊ ለማድረግ ነዉ” ምመህር ገብረኪዳን ደስታ (የትግራይ ሕዝብ እና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንት አስከ ዛሬ ገጽ 103) ምንጭ “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” ከሚል መጽሐፍ፤- ደራሲ ጌታቸው ረዳ። ይህ ፎቶግራፍ ወደ ግራ በኩል የሚታየው ሽማግሌው መምህር ገብረኪዳን ደስታ ነው። ወደ ቀኝ በኩል ያለው ወጣት “ዮሃንስ” (ጆን እያሉ ወያኔዎች የሚጠሩት) የተባለው የትግራይ ሰው ለወያኔ የቆመ ጋዜጠኛ ነው።
መቸም ሕሊና ላለው ሰው ምኒሊክ ወደ ትግራይ መጥተው የትግራይን ሕዝብ ከጠላት ወረራ እንዲያድኑት የተማጸነው ማን አንደሆነ የታሪክ ሰነዶች ያነበባችሁ የምትስቱት አይደለም። ሚኒሊክ ወደ ትግራይ ዓድዋ የዘመቱት ገብረኪዳን ደስታ እና የገብረኪዳን አስተማሪዎች የነበሩ በሚኒለክ ዘመን የኖሩ እነ ደብተራ ፍስሃ አብየ እዝጊ አንደሚሉት “ምኒልክ ወደ ትግራይ ያደረጉት ዘመቻ እነዚህን “ሁለት ነጥቦች” ለማሳካትና ተግባራዊ ለማድረግ ነዉ” የሚለው ውንጀላ ምንኛ እውነትን የሚረግጥ ክህደት መሆኑን ብዙ ትንተና የሚያስፈልገው ስላልሆነ ለናንተ ፍረድ እተወዋለሁ። ምኒልክ ጥሪውን ተቀብለው ጣልያን ባይመቱት፤ እናቶቻችን ብዙ የጣሊያን ዲቃላ ባፈሩልን ነበር።እናት አያቶቻችን በሰላቶ ጎረምሶች በተደፈሩ ነበር። ወንድ አያቶቻችንም የጣሊያን ጀርዲን (ጋርደን) ውሃ አጠጪ እና ዘበኛ፤ ወይንም እንቁላል ጠባሽ በሆኑ ነበር። በኤርትራ የደረሰ ውርደት ሁሉ በትግራይ ማሕበረሰብ በደረሰ ነበር። እድሜ ለምኒሊክ አንዳንል፤ ወያኔዎች ያ ሁሉ ውለታ እረስተው ‘ምኒሊክ ለብር ዘረፋ እና ትግራይን አደህይቶ ለመግዛት” አንዲያመቸው ነው ወደ ትግራይ ዓድዋ የመጣው ማለት ከባድ ወንጀል ነው። የሚኒልክ ደግነት እና በጎ ስራ ሰሪነት አንዲሁም የትግሬ መኳንንት ጎርበጣ ባሕሪ እና አርስ በርስ መጠላለፍ እና መገዳደል ባሕሪ የዘመኑ ምሁር የነበሩት የትግሬው ተወላጅ “ነጋድራስ ገ/ሕይውት ባይከዳኝ ” ስለ ምኒሊክ የጻፉትን በጎነት እና መልካም ስራ ማንበብ ነው። አሳዛኙ ግን ነጋድራስ ስለ ምኒሊክ ደካማ ጎን የጻፉትን እያጐሉ ፤ስለ በጎ ምግባራቸው እና ለትግራይ እና ስለ ኢትዮጵያ ያደረጉት አስተዋፅኦ የጻፉላቸውን እየደበቁ ወያኔዎች የገብረህይወት ባይከዳኝን ብዕር ሲያበላሹ ማየት በጣም ያሳዝናል። በዚህ ላይ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። እንደርታዊዉ ተወላጅ የወያኔው ዘፋኝ ኪዳነማርያም ረዳ
“ንአብነት ማይ ጨዉ ዓድዋ እንተዘከርና፤ ተምቤን ዓቢይ ዓዲ ሽረ እንዳባጉና፤ ኩይናት ምስ ገበሩ እቶም ወለድና፤ ጸላኢ ደምሲሶም ታሪኽ ሓደጉልና። ጨቆንትና አምሓሩ ምስ ታሪኽ ፀሓፍቶም ንዓና ዓብሊሎም ታሪኽና ጎቢጦም አለዉ ይምክሑ ብደም ወለድና፤ ንቃለስ ተጋሩ ክንመልስ ቅያና “
ትርጉም፦ ሓቀኛ ታሪክ ተደብቆ አይቀርም ለምሳሌ የማይጨዉን፤ የዓድዋን፤የሽረ የእንዳባጉናን ታሪክ ስንመረምር ወራሪዎችን ድባቅ በምመታት ትግሬ ወላጆቻችን አኩሪ ታሪክ ትተዉልን አልፈዋል። ይሁን እንጂ፤አባቶቻችን ብብዙ ዓዉደ ዉግያዎች ደማቸዉን አፍስሰዉ ያስመዘገቡትን ታሪክ “(ጨቆንትና አምሓሩ ምስታሪኽ ፀሓፍቶም”) “ጨቋኞቻችን አማሮች እና ታሪክ ጸሃፊዎቻቸዉ” በአሁኑ ወቅት እየተኮፈሱበት ነዉ። ታሪካችንን ቀብረዉ በአባቶቻችን ደም/ታሪክ እየተመኩበት ናቸዉ እና የትግራይ ተወላጆች የሆንን በሙላ ታሪካችነን ለማሳደስ በፅናት መታገል አለብን!” ይል ነበር፤ ተደርሶ የተሰጠው በረሃ ላይ እያለ የወያኔ ሙዚቀኛ የነበረው ዘፋኝ ኪዳነ ማርያም ረዳ። ምንጭ (ይድረስ ለጎጠኛው መምህር፤- ደራሲ ጌታቸው ረዳ።)
ይህ እጅግ ወደ ታች የዘቀጠ ዘረኛነት እና ውሸት ሰፊ ትንተና የሚያስፈልገው አይመስለኝም። እያንዳንዱ አንባቢ በቀላሉ የሚፈርደው ነው። ሆኖም ወላጆቻችን በጦርነት የመሸሽ ታሪክ፤ ምንም ወንጀል፤ ምንም የባንዳ ስራ እንዳልተሳተፉ አድርጎ የሚያቀርብ ጀብደኝነት የአማራ አዋቂዎች አንደሚሉት “አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል…” ነው እና ይህንን ታሪክ አስኪ አብረን አንመልከት እና ፍርዱን ሰጥተን አንሰናበት።አቡነ ጴጥሮስ አገሬን እና ሃይማኖቴን ለፋሺስት ሕዝብ አጎንብሶ አንዲሰግድ አልፈቅድም ብለው፤የድለላ ገንዘብ እና ማዕረግ ይሰጠዎታል ቢባሉም “ግንባሬ ለጥየት” ብለው በአምላካቸው ጽናት ተሞርኩዘው መስዋዕት ሲሆኑ ወላጆቻችን ቀሳውስተ አክሱም እና ዓዲግራት እንዲሁም ዓድዋ… ዘምባባ እያውለበለቡ እንደክርስቶስ “ንሴብሖ” የሚለው ውደሳ እያስተጋቡ ለፋሺስቶች ሲሰግዱ ተመዝገቧል።
ይህ የወላጆቻችን ታሪክስ ለማን ልንሰጠው ነው? አማራዎች በኛ ታሪክ እየኮሩ በባዶ ታሪካቸው እየፎረከሩ ነው እየተባለ በአማራ ላይ የተዘፈነው ዘፈን ነውር አይደለም ወይ? ታሪክ እንፍራ አንጂ! አማራዎች እና ትግሬዎች እኮ ያንድ እናት እና ልጅ ወንድማማቾች ናቸው። ከሁለቱም አብራኮች የወጣን ትግሬዎች እኮ ነን። አስኪ ይህንን ቪዲዮ/ፊልም ተመልከቱት እና ራሳችንን እንፈትሽ። ሁሉም ጎሳ የራሱ መጥፎ ታሪክ እና ደካመ ጎን አስመዝግቧል። አንዴት እኛ ትግሬዎች ብቻ ጀግንነት ብቻ የሰራን እንጂ ደካመ ጎን የለንም ብለን ሌላውነ ከዳተኛ እያልን በድርቅና አንከሳለን። ገብረኪዳን ደስታ በትግርኛው ቃለ ጠይቁ “ትግራዋይ እማ ነፀላኢኡ አይነብርከኽን/አይሰግድን፤ንጥልያን፤ ንድረቡሽ ተምበርኪኺ አይፈልጥን” ሲለን (ትርጉሙ “ትግሬ በታሪኩ ለጠላት ተምበርክኮ ፤ተጎንብሶ ሰግዶ አያውቅም። ለማንኛውም ጣሊያን ይሁን ድርቡሽ ሰግዶ እጁን ሰጥቶ በታሪካችን የታየበት የተመዘገበበት ወቅት ከቶ የለም!” የተንበረከኩ የሰገዱ ሌሎች ናቸው። ሲለን ይህ ከዚህ በታች ያለው ፊልም እሰኪ ተመልከቱ እና የገብረኪዳን ውሸትና እውነት እናመሳክረው።
Tigray ([deleted]) Ethiopians WORSHIPING Italian Colonialist inhttp://youtu.be/_20tOa8C6VU
Le bellezze di Axum, antica capitale etiopica. http://youtu.be/v3oBb0SAfqkLa popolazione indigena offre i propri servigi alle truppe colonialihttp://youtu.be/YEK5LexH1aE Il Vicerè Graziani in visita a Adigrat e Decamerè http://youtu.be/5Vn_ZLzhy_0
በሚቀጥለው ክፍል 2 ጽሑፌ ገብረ ኪዳን ደስታ አጼ ዮሐንስ ትግራይ ውስጥ ከዓፋር ማሕበረሰብ የነበራቸው ግንኙነት በሰላም በመከባበር አንደነበረ በውሸት የገለጸው፤የተዛባ ታሪክ በሰፊው እንተነትነዋለሁ። ሚኒልክ እና ቴዎድሮስ አንጂ ዮሐንስ በሃይል አላስገበሩም የሚለው ቅዠት፤ ከስሑል ሚካል ጀምሮ እስከ አጼ ዮሐንሰ ድረስ ከዓፋሮች ጋር የተደረገው ጦርነት፤ዝርፍያ የሴት ጥልፊያ (ዓፋሮች አንደሚከስሱት ከሆነ ንጉሱ ልጃቸው አርአያስላሴ የተወለደው ከሔርቶው የዓፋር ጎሳ መሪው ከ ‘ያኩሚ ሲረ ዓሊ’ ልጅ ከዴቶ ሲረ ዓሊ የተወለደው ልጅ አርአያስላሴ እናቱ ዴቶ አባቱ ደጃዝማች ካሳ (ዮሐንስ) በሽፍተነት ጊዜያቸው አንዴት በጉልበት አንደጠለፏት እና አርአያን አንዴት እንደወለዱት በዓፋሮች የተጻፈ ሙግት አቀርባለሁ። እንዲሁም በትግሬ ገዢዎች እና ዓፋር ባላባቶች የተደረገ ረዢም የደም መፋሰስ ውጊያ እስካሁን ድረስ መብረድ ለምን አንዳልቻለ እንመለከታለን። ወያኔዎች የራሳቸውን ነገሥታት ጛዳ እየደበቁ የሌሎቹን ጎሳዎች ነገሥታት እና መሳፍንቶች ወንጀል ሲቦረቡሩ “አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል…….” ነውና ሳንወድ የራሳችንን ጉድ ቦርቡሬ ማሳየት ሃላፊነት ስላለብኝ፤ በሚቀጥለው ክፍል ሁለት አንመለከታለን።
ወያኔዎች የፋሺስት ሃዋርያዎች ናቸው!
በመጨረሻም ወያኔ የፋሺስት ሐዋርያዎች/ደቀመዝሙሮች ናቸው ለምን ትላቸዋለህ;፡የወያኔ ስራ እና የሙሶሎኒ ስራ ይለያያል እያሉ ሲሞጉትኝ ለነበሩ ሰዎች በአንድ የማከብረው ውድ ወዳጄ የተላከልኝን ካነበበው መጽሐፍ አጭር መረጃ ላስነብባችሁ እና ልሰናበት። ከታች የምታዩት ሰነድ፤ንግግር፤ተግባር፤ፖሊሲ፤ትዕዛዝ እና ንገግር፤ መለስ ዜናዊ እና ግበረ አበሮቹ በኑሮ ምክንያት ከአማራ ቀዬአቸው ለቀው ወደ ደቡቡ አገራቸው በመጓዝ በሚኖሩ አማራዎች የወሰዱት እርምጃ ድሮ ሙሶሎኑ እና ረዳቶቹ የቀየሱት ፖሊሲ አንደነበረ እና ያ ስራ ወያኔዎች አንዴት ተግባራዊ አንዳደረጉት ለማነጻጸር ይረዳችሁ ዘንድ ይኼው አንብቡት።
ወያኔዎች የፋሺስት ሙሶሎኒ ደቀ መዝሙሮች ናቸው የምንለውም ለዚህ ነው።
በዶክተር ጌታቸው ረዳ

የኢሕአዴግ የደህንነት ሚ/ር አቶ ጌታቸው አሰፋ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ሆነዋል * ዘረፋው ቀጥሏል


ከምኒልክ ሳልሳዊ

በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ስልጣን እርከን ላይ የተቀመጠ እና በሙስና አልተዘፈቀም የተባለ ቢኖር ደፍሮ ይህ ነው የሚል የለም። ከራሳቸው ስም ጀምሮ እስከ ዘመድ አዝማዶቻቸው ወዳጅ ጓደኞቻቸውን ሳይቀር በዘረፋ ውስጥ በማመሳጠር ያሰማሩት የወያኔ ባለስልጣናት ተቆጥረው አያልቁም። ከትንሽ የቀበሌ ካድሬ ጀምሮ ልከክልህ እከክልኝ ብላ እንብላ መውደቂያህን አሳምር ወዘተ እየተባለ የህዝብ ሃብቶች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ባንኮችን አጨናንቀዋል።
የወያኔ ባለስልጣናት የሆኑና ከቤተሰቦቻቸው ከዘመድ ወዳጆቻቸው ጀርባ ሆነው ከፍተኛ የዘረፋ ስራ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሚተገብሩ በአደባባይ ግን እንደ ንጹሃን ምንም እንዳሌለባቸው መታየት የሚፈልጉ ያሻቸውን ነገር በስልክ ቲዛዝ አሊያም በተላላኪ ደህነንቶች የሚያስፈጽሙ እንደ ደብረጺሆን ገ/ሚ ሳሞራ የኑስ አባይ ወልዱ በረከት ስምኦን ሃይለማርያም ደሳለኝ እና የተወሰኑ 3 % የሚሆኑ የሕወሓት አመራሮች ሃገሪቷን እየዘረፉ ይገኛሉ።

ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሕወሓት አመራሮች በዘረፋ ስራ ላይ መሰማራታቸው ሳያንስ ከተለያዩ የዘረፋ ቡድኖች ጋር የተሳሰረ ግንኙነት /ኔትወርክ/ በምስራቅ አፍሪካ ዘርግተዋል ። ከአውሮፓ እና ከኢሽያ የሚነሱ የማፊያ ቡድኖች እና እጽ አዘዋዋሪዎች እና ህገወጥ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ሃገሪቷን የህገወጦች መተላለፊያ ከማድረጋቸውም በላይ ኮንትሮባንድን በህግ ሽፋን እየተገበሩ ሃገሪቷ ማግኘት ያለባትን እንዳታገኝ ለግል ጥቅማቸው በመሯሯጥ ዘረፋውን አጧጡፈውታል።

የደህኝነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ ከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖች እንዲሁም በመሃል አገር የከተሙ የሕወሓት ሹሞች በአጭር ጊዜ ውስጥ በዘረፋ ብቻ ቢሊየነር ለመሆን የበቁ እና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በተለያዩ የፈጠራ ስሞች እና ሰነዶች የትልልቅ ፋብሪካዎች እና የከባድ ኮንስትራክሽን ካምፓኒዎች ባለቤቶች ከመሆናቸውም በላይ ካለምንም ግብር እና ቀረጥ እንዲሁም ጨረታን አሸናፊ በመምሰል ለራስ ጥቅም በማዋል የውጭ ምንዛሬ በስልክ ትእዛዝ ብቻ በውጪ አገር አካውንታቸው እንዲገባ ባንኮችን በማዘዝ (ባንክ ኦፍ ማሌዥያ ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ነው) ሃገሪቷን እየበዘበዟት ነው።

በተለያዩ የቤተሰቦቻቸው ስም ዘረፋውን ከሚፈጽሙ ቢሊየነር ባለስልጣናት ውስጥ አባዱላ ገመዳ ፤ አርገበ እቁባይ ፡ግርማ ብሩ እና ካሱ ኢላላ ይገኙበታል። በቅርቡም ይህንን የቢሊየነሮች ቡድን የተቀላቀለው የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ በቤተሰቦቹ አክሲዮን ስም አዲስ የከፈተውን የኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሊያስመርቅ በዝግጅት ላይ ሲሆን አገር ውስጥ ከሚሰሩት የከባድ ኮንስትራክሽን ካምፓኒዎች 77% የወያኔ ባለስልጣናት መሆናቸው ይታወቃል።

አቶ ጌታቸው እና የጦር መኮንኖቹ አዲስ በአዋጅ በተሰጣቸው ስልታን መከታ በማድረግ የተለያዩ ባለሃብቶችን በቡድን ባደራጁት ዘራፊዎች በማዘረፍ በማስፈራራት እና የመንግስትን በጀት ያለ አግባብ በመጠቀም በሙስና እና በዘረፋ ተዘፍቀዋል። ይህንን የደህነንቶች የዘረፋ ተግባር በተመለከተ አዲስ አበባ ያሉ እና በሚሊዮን ብሮች በግዳጅ የተነጠቁ ባለሃብቶች ታሪክ ለምስክርነት ያቆያቸዋል።

Wednesday, 9 April 2014

ሙክታር ከድርና የኦሮሞ አክራሪዎች – ናዮሚ በጋሻዉ !


እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው አገልግሏል። አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ትልቅ ክልል የምትባለው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳነት ሆኗል። ሙክታር ከድር ይባላል። የኢህአዴግ አንዱ የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክርሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ነው።
ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 150 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኝ ሄቶሳ በምትባል የአሩሲ መንደር አንድ ትልቅ ግንባታ ለማስመረቅ በክብር እንግድነት ይገኛል። አንድ ወንዝ ተገድቦ፣ ወይንም የጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት ተሰርቶ ለመመረቅ አይደለም የመጡት። እልም ባለ ገጠር መሃከል፣ አካባቢዉ ሁሉ ሜዳና እርሻ በሆነበት ቦታ፣ አንድ ትልቅ በአይነቱም፣ በይዘቱም የተለየ፣ ፈረንጆች እንደሚሉት ‘ዊርድ’ የሆነ ሃዉልት ቆሟል። የአኖሌ ሃዉልት ይሉታል።
በቀድሞ ጊዜ በገዳ ስራአት ጀግና የነበሩ የኦሮሞ መኮንኖችን ገድል የሚዘክር፣ ወይም በቅርብ ታሪካችን እንደ አብዲሳ አጋ፣ ባልቻ አባ ነፍሶ የተሰኙ የኦሮሞ ጀግኖችን የሚያሳይ ሃዉልት ቢሆን ሸጋ ነበር። ነገር ግን ሃዉልቱ ጡት የያዘ አንድ እጅን ያሳያል። ከመቶ አመት በፊት የሚኒሊክ ወታደሮች የአርሲ ኦሮሞዎችን ጡት ቆርጠዋል የሚሉትን የሌለ የፈጠራ ታሪክ ለማስታወስ ነዉ ብለው ሀውልቱን ያቆሙት። ያዉ በሚሊዮኖች በሚቆጠር ከሕዝብ ካዝና በተወሰደ ብር የተሰራ ሃዉልት። “አማራዎች እንደዚህ ጡት ቆራጮች ናቸው!” የሚለው የጥላቻ መልእክት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ ከልጅነታቸው ጀምሮ ለማስረጽ ሆን ተብሎ የቆመ ሃዉልት። ኦሮሞው አማራዉን እንዲጠላ፣ እንድ ፍልስጤምና እስራኤል በመሃከላቸው ግድግዳ ተፈጥሮ እንዳይተማመኑ እንዲተላለቁ ለማድረግ የቆመ ሃዉልት። የሰይጣን የዲያብሎስ ሃዉልት!!!
በአኖሌ በአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች ተደረገ የተባለው ጡት ቆረጣ መደረጉን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት የጽሁፍ መረጃ የለም። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በፓልቶክ ሲጠየቁ “ምንም አይነት የጽሁፍ ማስረጃ የለም፤ ግን በአፈ ታሪክ ነው የተላለፈው” ነበር ያሉት። የአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች አያታቸውን አስረዉ ወፍጮ እንዲፈጩ ማስገደዳቸዉን የተናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ፣ በወለጋ የሚኒሊክ ወታደሮች ጡት ቆርጠው እንደሆነ ሲጠየቁ “ወለጋ እንደዝያ አልሆነም” ነበር መልሳቸው። አጼ ሚኒሊክ በጎጃም በሃርረ፣ በወላይታ በበርካታ ቦታዎች ወታደሮቻቸው ልከው አስገብረዋል። በአርሲ ተደረገ ከሚባለው ማረጋገጫ ካልቀረበበት አፈ ታሪክ ዉጭ በሌሎች ቦታዎች የጡት ቆረጣ ተደረገ የሚል በአፈ ታሪክም አልተሰማም።
እንግዲህ እንደዚህ ዉሸት የሆነን አፈታሪክ በማራገብ ፣ ት/ቤቶችና ክሊኒኮች በመሳሰሉ ቁም ነገሮች ላይ ገንዘብ ከማጥፋት ይልቅ፣ ዘረኛዉና ጠባቡ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ይህ አይነቱን፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቃቅር፣ ዜጎችን ወደ እልህና ወደ ጦርነት እንዲሄዱ የሚገፋፋ፣ ጥላቻን በሰዎች ልብ ዉስጥ የሚዘራ፣ አሳዛኝና አስቀያሚ ሃዉልት ማቆሙ፣ ምን ያህል ለአገር ጥቅም ሳይሆን ለአገር መጥፋት እየሰራ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
እስቲ ወደ ሙክታር ከድር መልሼ ልዉሰዳችሁ። በቅርቡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያንን በተመለከተ በኦህደድ ወንጀሎች ስለተሰሩ ግፎች ሲናገሩ፡
«I do know that there are Oromo individuals who do say “ non-Oromos or those who do not speak Afan Oromo, have no rights. They are second citizens.” I have expressed already that I am against such people. This brings me back to the OPDO “Gimgama” of 1989. OPDO was then confronted with serious problems of human rights violation, corruption and anti-democratic Oromo nationalism. We evaluated the leadership, the cadres and members of OPDO under the motto “Clean OPDO from OLF attitude (anti-democratic/narrow) and Naftagna (please note that Naftagna is not equal to Amhara) practices (violation of democratic and human rights including corruption). The result of the “Gimgama” was that thousands were found out to have anti-democratic attitudes and carried out Naftagna practices. 189 cadres were imprisoned so that they are brought to justice because of high corruption and serious human rights violationስ. Thousands were expelled because of their bad attitudes and bad practices. Only about 300 were kept after receiving warnings” በማለት ነበር በኦህድድ አክራሪዎች የተፈጸሙትን ወንጀሎች የዘረዘሩት።
ማስጠንቀቂያ ተሰጧቸው ከነበሩ አክራሪ ዘረኞች መካከል ማን የሚገኝ ይመስላቹሃል? የአኖሌ የጥላቻ ሃዉልት መራቂ የሆነው ኦሮሚያን ኦሮሞ ካልሆኑት የማጽዳት አላማ በዉስጡ ያለው፣ የኢትዮጵያዉ ጀነራል ምላዲቹ ፣ ሙክታር ከድር አንዱ ነበር።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢህአዴግ ምን ይጠብቃል የጥላቻ ሀውልት እንጂ!
«Among these were Alemayehu Atomsa and Muktar Kadir. Anyway, what was going on then was really very sad. Non-Oromo Ethiopian investors and traders were not welcome. Documents for bids for land were leaked out to Oromos so that they could win against non Oromo (for example against the 7 rich Gurage in Jimma). Shops were closed down. Boards to guide people were written only [in] Qube (no Amharic and English translation). Appeal documents written in Amharic were rejected. Schools refused to give lessons in Amharic. (With silly arguments “we were formally forced to learn in Amharic, now it is their turn to be forced to learn in Afan Oromo.) We will not pay money for Amharic teachers and books”). Unfortunately, I hear that the attitude and practice still lingers.» ይላሉ ዶር ነጋሶ በጽሁፋቸው።
ታዲያ የሙከታር ከድር ዘረኛና የጥላቻ ታሪክ እየታወቀ፣ የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት ማድረጉ፣ የአኖሌን የጥላቻ ሃዉልት ማቆሙ፣ ኦሮሞዉን ለመጥቀም ነው ወይንስ ኦሮሞውን ከሌላ ህዝብ ጋር ለማጋጨት? ኦሮሞው ከሌላው ሕዝብ ጋር የተዛመደ፣ የተዋለደ፣ የተሳሰረ አይደለምን? ለዲሞክራሲ ቆመናል የሚሉት፣ የኦሮሞ ድርጅት መሪዎችስ ይሄን የነሙክታር ከድር መርዝ ማዉገዝ የለባቸውምን? ለኦሮሞው ከአማራዉ፣ ከጉራጌዉ፣ ከጉሙዙ፣ ከቡርጂዉ፣ ከሲዳማው፣ ከጌዴዎው፣ ከሶማሌው ጋር አብሮ ተከባብሮ፣ ተስማማቶ መኖር አይሻለዉምን ? ለምንስ እነዚህ አካራሪ ኦሮሞዎች ጠብ ይፈልጋሉ? ለምን ተነጥለው ለመታየት ይሞክራሉ? የሚያስተሳሰር፣ የሚያቀራራብ፣ አንድ የሚያደርገን ማብዛትና ማስፋፋት እንጂ የሚያጣላና የሚያቃቅር ነገር ለምን እንጭራለን ?
አክራሪዎች በአኖሌ እንዳየነው አይነት ካከረሩ፣ ኦሮሞ ለኦሮሞዎች በሚል፣ ባለፈበትና በማይሰራ ባዶ ፉከራ ከተነሱ፣ በዚያኛዉ ወገን ያሉት ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ዘነጉትን? ወይስ “በዙሪያችን ካሉ ሌሎች ሕዝቦች እዚያ ማዶ ያለው የትግሬ ጦር ይጠብቀናል” የሚል ግምት አላቸው? እነዚህ አክራሪ ኦሮሞዎች ሰው ዝም ሲላቸው ትንሽ ልባቸው ያበጠ መሰለኝ። አላወቁትም እንጂ፣ እንዲሁ በባዶ ባበዱ ቁጥር እራሳቸዉን ነው የሚያስገምቱት። አለም በግሎባላይዜሽን በተሳሰረችበት ዘመን፣ ምን ያህል ኋላ ቀሮች መሆናቸዉን ነው የሚያሳዩት።
እንግዲህ ልብ ይገዙ ዘንድ እመክራቸዋለሁ። ጥላቻ ለማንም አይጠቅም። እልህ ለማንም አይጠቅምም። ዘረኝነት ለማንም አይጠቅምም።
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
April 8, 2014

አስደንጋጭ ዜና! ተጠንቀቁ! (ሹክሹክታ)


ወሬውን በዜና መልክ ለማቅረብ ተጨማሪ መረጃ ባለማግኘታችን፤ “ሹክሹክታ” ብለነዋል – ርዕሱ ላይ። አንዳንዴ በሹክሹክታ መልክ የምንሰማቸው ወሬዎች እውነት ሆነው ይገኛሉ፤ አንዳንዴም ሹክሹክታው ህዝብ ጆሮ ከመድረሱ በፊት ቶሎ እርምት ይደረግለታል። ዛሬም  በሹክሹክታ መልክ የተሰራጨውን ወሬ ወደናንታ እንደወረደ ከዚህ ቀጥሎ አቅርበነዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በኤች. አይ.ቪ በሽታ ህዝብን በመጨረስ እርዳታ ለማሰባሰብ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ኤች. አይ.ቪን ለመከላከል ተብሎ ለኢትዮጵያ መንግስት ከምእራባውያን የሚሰጠውን እርዳት በመቆሙ አዲስ አበባ የሚገኙ ከጤና ጣቢያ እስከ ሆስፒታል በተለይም ዘውዲቱ ሆስፒታል ኤች አይቪ መመርመሪያ ኪት በማጣታቸው ኤች. አይ.ቪ ያለባቸው እናቶች ፖዘቲቭ የሆነ ህጻን እየወለዱ ይገኛሉ፡፡ እርዳታው የሚቆምበት ምክንያት ኢትዮጵያ ኤች. አይ.ቪን በመከላከሉ ረገድ የተሳካላት በመሆኑ እና ምንም ታማሚ ስለሌለ እርዳታ ሰጪ ሀገራት ፊታቸውን ወደ ሌላ ሀገር በማዞራቸው እና በተለያዩ ጊዜ ለኢትዮጵያ የተሰጠው ገንዘብ በባለስልጣናት በመዘረፉ እንዲሁም ሂሳባቸውን በወቅቱ ማወራረድ ባለመቻላቸው እንደሆን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው እርዳታ ለጸረ ኤች. አይ.ቪ መድሃኒት መግዣ ብቻ ሲሆን ይህንንም በአግባቡ ገንዘቡን ባለመጠቀማቸው ምእራባውያን ርዳታውን ለማቆም ቢፈልጉም ከሰብዓዊነት አንጻር ብለው እንደሆነ የሚረዱት ተብላል፡፡ ባለፉት ዓመታት በርካታ ረጂ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የአፈጻጸም ስምምነት ለመፈራረም ቢመጡም አንዳንድ ባለስልጣናት ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ አቃቂር እያወጡ ተቋማቱን በማጉላላት አንፈራረምም በማለታቸው ምክንያት ረጂ ተቋማቱ ፊታቸውን ወደ ሌላ ሀገር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የሆኖ ሆኖ በኤች አይቪ ምክንያት የሚሞትና ስርጭቱ ቀንሷል በሚል ርዳታ ያጣው መንግስት የኤች አይቪ መመርመሪያ ኪቶችን በመደበቅ ለጤና ተቋማቱ ባለመስጠት ኤች. አይ.ቪ ሆን ተብሎ እንዲሰራጭ እና ትኩረት በማግኘት የኤች. አይ.ቪ ብር ለመብላት በሚል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት የኤች .አይ.ቪ መሳሪያዎች በጤና ተቋማቱ አይገኝም፡፡

Friday, 4 April 2014



During his speech before the Royal Institute for International Relations, Foreign Minister Nabil Fahmy said that Egypt offered to finance the construction of the Ethiopian Renaissance dam and suggested that the dam would be run by a joint committee from the two countries.
He also emphasized the importance of serious negotiations to find out solutions that serve the interests of the Nile Basin countries without harming any country.
He also asserted that Egypt would resort to all legal measures to protect its historical rights in Nile water and national security.
source - http://www.diretube.com/articles/read-fm-egypt-offers-to-finance-ethiopia%E2%80%99s-renaissance-dam_4834.html#.Uz2pb_mSxUA

በዲያስፖራ የሚኖሩ የወያኔ አገልጋዮች ስም ዝርዝር


5b591-tegadalayhegearawite

በወያኔ የከተማ ልማት፣ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተዘጋጀ “በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ዲያፖራዎች የፕሮፋይል ሰነድ” የሚል 170 ገጾች ያለው ዝርዝር መረጃ እጃችን ገብቷል። በዚህ ሰነድ ውስጥ ስማቸው ከተዘረዘረው መካከል ለወያኔ በስለላና መረጃ በማቀበል ተግባር ላይ የተሰማሩ እንዳሉ አይጠረጠርም። ሰነዱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። በዲያስፖራ የሚኖሩ የወያኔ አገልጋዮች ስም ዝርዝር
EthiopianReview.com

ረዳት አብራሪ ሃይለመድን አበራ ዛሬም በምረመራ ላይ መሆኑን የስዊዘርላንድ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ነገረኝ

593x322xco-pilot_hijacking.jpg.pagespeed.ic.X8fktOpOJt

ረዳት አብራሪ ሃይለመድን አበራ ዛሬም በምረመራ ላይ መሆኑን የስዊዘርላንድ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ነገረኝ
ዛሬ ለምን እነደሁ እንጃ፤ ረዳት አብራሪ ሃይለመድን አበራ በማለዳው በአዕምሮዬ ተመላለሰ። ምን ደርሶ ይሆን… ምን ተብሎ ይሆን… ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስራት የሰው ሃገር እስራትን ያስመረጠውን በደል የሚነግርን መቼ ይሆን… ወይስ ያቺ እህቱ እና እኒያ ወንድሙ እነዳሉት የስዊዝ ሃኪሞችም ህመምተኛ ነው ብለው ወደ ህክምና ልከውት ይሆን… (ከሆነም ካለሆነም ኢትዮጵያችን ውስጥ ጤነኛው ማነው… መቼስ ነው የምንድነው…) እያልኩ የባጥ የቆጡን ሳንሰላስል ቆየሁና፤ ድንገት የስዊዘረላንድ ወጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን ድረ ገጽ ጎግልን ጠየኩት።
የተባረክ ጎግል “ካንተማ አልድብቅህም ደንበኝ!” ብሎ ሰጠኝ። ከድረ ገጹ ላይ የኢሜል አድራሻቸውን ለቅም አደርኩና “Dear Sir Madam…”  ብዬ ሳበቃ (እኔ ከእናነት ሃሳብ እና ናፍቆት በስተቀር ደህና ነኝ) የሚለውለውን ሳላካትት የወንድማችን ሃይለመድን አበራን ነገር ከምን አደረሳችሁት… አሁን በምን ሁኔታ ላይ እነዳለ ለማወቅ ፈለጌ ነው ይህንን የኢሜል መልዕክት ወደ እናንተ መስደዴ ስል በትህትና ጠየኳቸው።
የስዊዘርላንድ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትም እግዜር ያክብረው እና በቃል አቀባዩ ጄኒት ባለመር በኩል ባደረሰኝ ኢሜል፤ ጉዳዩን  የያዘው (እኛ “ጠቅላይ ፍርድ ቤት” እንደምንለው አይነት) እነደነርሱ ደግሞ Attorney General of Switzerland (OAG) በሚሉት የህግ መስሪያ ቤት ቢሆንም ለመረጃ ያክል ግን ሰለሁኔታው በጀረመንኛ እና በፈረሳይኛ የተሰጠ መገለጫ እንካ… ብሎ ልኮልኛል።  hayelemeden abera
እኔም ጀርመንኛዬን እና ፈረሳይኛዪን ይዤ ጎግልን የቅድሙ ሰውዬ ነኝ ድጋሚ መጣሁ እባክህ ይሄንን ተርጉምልኝ… አልኩት፤ ጎግልም “ጣጣ የለውም” ብሎ ወደ እንግሊዘኛ መለሰለኝ፤
እና እንግሊዘኛው እንደሚለው፤ “ረዳት አብራሪው ሃይለመድን አበራ  አሁን በህግ ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት ነው። ያለበትን ቦታ ለመጥቀስ ወይም ሌሎች መረጃዎችን ለማቀበል፤ አሁን ምርመራው የደርሰበት እና ያልደረሰበት ደረጃ አይፈቅድም፤ ምርመራው ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችንም መስጠት ለቀጣይ ሂደት እንቅፋት ሊሆን ይችላለ ተብሎ ይገመታልና መናገር ያስቸግረናል። በጥቅሉ የኢትዮጵያዊው ረዳት አበራሪ ጉዳይ ዛሬም በምርመራ ላይ ነው።” ሲል ያትትና “የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ግን ሰኞ ባረፈ በሶስተኛ ቀኑ ረቡዕ በፈረነጆቹ አቆጣጠር በ19/02/14 ሊሄድ ወዳሰበበት ቦታ (እርሱም ጣሊያን ነው) ተሸኝቷል።” ይላል።
የስዊዘርላንድን ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሀገራቸው የስራ ቋንቋዎች በፈረንሳይኛ Merci beaucoup እንዲሁም በጀርመንኛ Vielen Dank በማለት አመሰግናለቸዋለሁ!!!
ለወንድማችን ሃይለመድን አበራም መለካሙን መመኘቴ አይቀርም።
http://www.abetokichaw.com/2014/04/04/ረዳት-አብራሪ-ሃይለመድን-አበራ-ዛሬም-በም/