Sunday, 8 March 2015

ሚኒስቴሩ መልስ ሰጡ! የቴድሮስ አድሃኖም የ20 ሚሊዮን ዶላር ፕሮፓጋንዳ

ኤርትራ ተወልዶ ያደገውና በአሁኑ ወቅት በችሎታው ሳይሆን በዘሩ እና በወያኔነቱ ተመርጦ “የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር” ለመሆን የበቃው ቴድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን የተለመደ ወያኔዊ ፕሮፓጋንዳ ሰርቶ ሲያራግብ ከርሟል። ይሁንና የዚህኛው ፕሮፓጋንዳ ታሪክ የሚጀምረው ወያኔዎች ከማይቆጣጠሩት ሩቅ ሃገር (አውስትራሊያ) በመሆኑ የፕሮፓጋንዳው ታሪክ ሃሰት እንደሆነ ለማወቅ ጊዜ አልፈጀም።
Tedros Adhanom's propaganda የታሪኩ ምንጭ የሆነችው ታዳጊ በሪቱ ጃለታ አሕመድ በሃገረ አውስትራሊያ በምትማርበት ትምህርት ቤት በተካሄደ ውድድር በማሸነፏ የተሸለመችውን 20 ሚሊዮን ዶላር ይዛ ኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን ልትገነባ (ኢንቬስት) ልታደርግ ገስግሳ መጥታለች በማለት ነበር አይተ ቴድሮስ አድሃኖም በፌስቡካቸውና በቴሌቪዥናቸው የፕሮፓጋንዳ ዜናቸውን ያሰራጩት።
ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ ኢሳት እና ነዋሪነታቸው በአውስትራሊያ የሆነ ኢትዮጵያውያን ጉዳዩን ለማጣራት ባደረጉት ሙከራ እንደተረዱት ከሆነ ያን ያህል ገንዘብ ለአንዲት ታዳጊ ወጣት በሽልማት መልክ የሰጠ የአውስትራሊያ ተቋም አልተገኘም። በቴድሮስ አድሃኖም ዜና ስሙ የተጠቀሰው “የአውስትራሊያ ሮታሪ ክለብ” ከነጭራሹ የለም። ጉዳዩን ለማጣራት የሞከረው ጋዜጠኛ አበበ ገላው እንደተረዳው… በአውስትራሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮታሪ (የበጎ አድራቶት፟) ድርጅቶች ያሉ ሲሆን አንዳቸው የተባለውን ያህል ገንዘብ በሽልማት ለመስጠት አቅም የላቸውም። የአውስትራሊያ መንግስት በበኩሉ በአንድ ዓመት በአጠቃላይ በአፍሪካ ለበጎ አድራጎት ያወጣው ገንዘብ መጠን ወደ 14 ሚሊዮን ገደማ እንደሆነ አመልክቷል። በቴድሮስ አድሃኖም ከሚነገረው 20 ሚሊዮን ዶላር ግማሽ ያህሉን ማለት ነው።
ቴድሮስ አድሃኖም ውሸታቸው ከተጋለጠ በኋላ እንደሰለጠነ ሰው ማስተባበያ ይሰጣሉ ወይንም ይቅርታ ይጠይቃሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ ከዚህ በታች የሰፈረውን እጅ እግር የሌለው መልዕክት አስተላልፈዋል…
“… እንደምታውቁት በሪቱ የ 14 ዓመት ታዳጊ ናት፡፡ ህፃናትና ታደጊዎች የዋሆች እንደሆኑ ክፋት እንደሌላቸው ከኔ ጋር የምትስማሙ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ምክንያትም ህፃናትና ታዳጊዎች የሚነግሩኝን ማመን እመርጣለሁ፡፡ ስህተትም ቢኖራቸው ከየዋህነት ካልሆነ ከክፋት አይመነጭም፡፡ ህፃናትን ማመን ስህተት ከሆነ መሳሳትን እመርጣለሁ፡፡…”
በቴድሮስ አድሃኖም ደረቅ መልስ የተበሳጩ ኢትዮጵያውያን ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ ብለዋቸዋል…
“ህፃናት ብፁአን ናቸዉ አሉ ዶፍተሩ የሳቸዉን ጥፋት ወደ ልጂቱ ጠጋ ጠጋ?ዛሬ መዋሸት አይቻልም እድሜ ለኢሳት እንዲህ ራቁታችሁን ያስቆማችኋል ። ይብላኝ እናተን ተከትለዉ ገደል ለገቡት!” Hirut Hailu
“…ይህን የዶ/ር ቴውድሮስን ሃሳብ ስመለከት … መንግስታችን የሚያምናቸው ያሉትን የሚሰማቸው ዜጎች ህፃናት ከሆኑ …ውሃ መብራት ዲሞክራሲና የመሳሰሉት መሰረታዊ ጥያቄወች በህፃናት ልጆቻችን በኩል ብናቀርብ አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጠን ይችላል ስል አሰብኩ ! ጥያቄው ልጆቻችን የሚታመኑት ሃያ ሚሊየን ዶላር ይዘው ሲናገሩ ነው ወይስ ባዷቸውን ቢያወሩም ይሰማሉ… የሚለው ነው ፡) ለማንኛውም ዶ/ር ይችን አንድ ፍሬ ልጅ ሃሳብሽ ጥሩ ነው የተቀደሰ ነው ግን ውሸት ‹ለህፃናት› ጥሩ አይደለም ብለው መምከር አባታዊ ግዴታዎት ይመስላኛል!!…” Alex Abraham
“…ተሸዉጃለሁ ማለቱን ስሰማ ሀገሬ አሳዘነችኝ! አንዲት ፍሬ የ14 አመት ህፃን እንዲህ ከሸወደችዉ ምላሳቸዉ ወፍ ከሰማይ የሚያወርደዉ ዲፕሎሞቶችማ ሊሸጡትም ይችላሉ!! ደግሞ ሸጠዉት ቦንድ ግዙ ከሚሉን በጊዜ ከስልጣኑ ቢያባርሩት ነዉ የሚሻለዉ! እሱም አርፎ ፎቶዎቹን ይለጥፍ ነበር!” Gashaw Mersha
“…ይህ ሰውዬ በ90 ሚሊዬን የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲቀልድ ተመልከቱት ውሸቱ የተፈጠረው ልጅቷ ትንሽ ስለሆነች በሷ የተፈጠረ ችግር ነው እና ራዕይዋ እንዲሳካ ከጎና እንሁን እያለ በሷ እየአማህኝ ነው ፤ እንግዲህ ይታያችሁ ኢትዮጵያን የምታህል ትልቅ አገር የውጭ ጉዷ ሚንስቴር ነኝ ብሎ ተቀምጦ የበሬው ላሞለደ የውሸት መረጃ እሱና ጓደኞቹ በሞኖቦል በያዙት ኢቢሲ ለህዝብ እያቀረቡ ያሉት ማፊሪያዎች።” Netsanet Beqalu
 http://ecadforum.com/Amharic/archives/14575/

No comments:

Post a Comment