Saturday, 8 June 2013

በሞልዴ የኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ ተደረገ ።

በሞልዴ ኖርዌይ ለ ኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ

በኖርዌይ ሞልዴና በቪስትነስ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደርጎ በመልካም ተጠናቀቀ።በሞልዴና በቪስትነስ የሚኖሩ ስደተኞች የኢሳት ገቢ  ማሰባሰቢያ በማዘጋጀት ያደረጉት ዝግጅት ላይ ከኦታ ፣ ከስቴንሻዬር  እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ ዜግነት ያላቸው ሰዎች የተገኙበት ሲሆን ከቀኑ 1ሰዓት30 ላይ ፕሮግራሙ የተጀመረ ሲሆን የተለያዩ ፕሮግራሞች የተደረጉ ሲሆን ከብሮግራሙ መካከል በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሚዲያ አፈና በተምነለከተ የተለያየ በመረጃ የተደገፈ ጹፎችን በማቅረብ ለታዳሚዎቹ አቅርበዋል። ከዛ በመቀጠልም የሃገራችንን ባህላዊ ምግቦች ለታዳሚዎች በማቅረብ እና የተለያዩ የሎተሪ ሺያጮችን በማድረግ የሳካ የኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀ ሁኔታ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አድርገዋል ። በፕሮግራሙ ላይ  ጋዜጠኛ አፍወርቅ አግደው በስካይፒ በቀጥታ ለታዳሚዎች በሃገራችንን ስላለው የሚዲያ አፈና ብሎ የነጻ ሚዲያ አስፈላጊነትን በማራኪ ሁኔታ አስተላልፈዋ። ከስፍራው የተገኙ ግለሰቦች ለኢሳት ያላቸውን አሌንታነት ደስ በሚል  ስሜት ገልጸዋል ። ከዚህ በተጨማሪ ብዙም የኢትዮጵያ ዜጎች በለሉበት የአለማችን ክፍሎች የገቢ ማሰባሰቢያ ማድረግ እንደሚችሉ አሳይተዋል ። ሙሉ ዘገባውን እንደደረሰን በሰፊው እናቀርባለን ።



                          ESAT Special program on Sene 1 Victims - June 8 2013

Thursday, 6 June 2013

ኢትዮጵያ ለግብፅ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

F 16 ተዋጊ ጄቶችን በመጠቀም ግብፅ በአለም 4ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከነበራት 240 ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች በተጨማሪ ነው - 20 ጄቶችን የገዛችው። እንዲህ አይነት ጄቶች ደግሞ በፍጥነትም ሆነ ረዥም ርቀት በመሄድ እና በማናቸውም አቅጣጫና ማዕዘን መገለባበጥ የሚችሉ ናቸው።
EMF: በአባይ ግድብ የተነሳ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ፍጥጫ ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ በተለየ መልኩ ውጥረት የነገሰ ይመስላል። በተለይም የግብፁ ፕሬዘዳንት “ቅንጣት ውሃ አናስነካም!” ከማለት አልፈው ካቢኔያቸውውን ሰብስበው ሲነጋገሩ በቀጥታ በቴሌቪዥን ሲተላለፍ፤ ኢትዮጵያን ለመምታት የተለያዩ ሃሳቦች ሲያቀርቡ ከታየ በኋላ፤ የግብፅ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። በተለይም ሰሜን ሱዳን እና ግብፅ የናይል ወንዝን አስመልክቶ የሁለትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት ስላላቸው፤ ሱዳን ለግብፅ በመወገን… መንደርደሪያ ከሰጠቻት ግብፅ ከሳምንት በፊት የገዛቻቸውን ኤፍ 16 ጄቶች ልትጠቀም ትችላለች የሚል ስጋት አለ።
F 16 ተዋጊ ጄቶችን በመጠቀም ግብፅ በአለም 4ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከነበራት 240 ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች በተጨማሪ ነው – 20 ጄቶችን የገዛችው። እንዲህ አይነት ጄቶች ደግሞ በፍጥነትም ሆነ ረዥም ርቀት በመሄድ እና በማናቸውም አቅጣጫና ማዕዘን መገለባበጥ የሚችሉ ናቸው።
F 16 ተዋጊ ጄቶችን በመጠቀም ግብፅ በአለም 4ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከነበራት 240 ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች በተጨማሪ ነው – 20 ጄቶችን የገዛችው። እንዲህ አይነት ጄቶች ደግሞ በፍጥነትም ሆነ ረዥም ርቀት በመሄድ እና በማናቸውም አቅጣጫና ማዕዘን መገለባበጥ የሚችሉ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ ለግብፅ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከመላክ አልፋ፤ በኢትዮጵያ የሚገኘው የግብፅ አምባሳደር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ተገኝቶ የአገሩን የግብፅን አቋም እንዲያስረዳ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተልኮለታል። እንግዲህ አምባሳደሩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የሰጣቸውን ማሳሰቢያ ተቀብለው ቃላቸውን ይሰጣሉ ወይስ ጥሪውን ንቀው ይተዉታል?  የአምባሳደሩ ምላሽ ብዙ ነገር ሊለውጥ ይችላልና መጨረሻውን  አብረን እንከታተላለን።

SEMAYAWI PARTY HAS BROKEN THE SPELL

Semayawi (Blue) Party at last a light has appeared at the end of tunnelImru Zelleke (Ambassador)
Thanks to the Semayawi (Blue) Party at last a light has appeared at the end of tunnel that leads to freedom. Those that have to be congratulated the most are the Ethiopian People at large who responded to the appeal in massive numbers with enthusiasm and dignity. They expressed clearly and without ambiguity their demands and aspirations.
A new phenomenon that gave impetus and dynamism to the movement is the overwhelming participation of the youth including the leadership. The highest accolades and compliments should be given to Engineer Yelikal Getinet and his colleagues for their courageous and exemplary leadership. They have overcome the negative paradigm of divisions and contentions that has so far infected the opposition factions, and appealed directly to the people. In fact it is time for the younger generation to take over the helm of the opposition; it is their future that is at stake. The elderly generation can give advice and share their experience, because the past is an essential element to understand the pre-existing conditions and to build the future on solid foundations.
This new advent on the political scene opens new challenges and pitfalls presaging critical events and conditions that must be met with clarity and absolute determination. I humbly suggest the following:
a. We should give up the notion of a “united” action. For the past forty years we have heard the word “unity, union, united etc.” that it has lost its meaning, and has become to mean to do nothing in unison, as the popular dictum “a committee is a gathering of people who cannot do anything by themselves, who together decide to do nothing”. A plethora of parties with hardly constituencies worth mentioning are more of a hindrance than a positive element. What is needed is a determined and genuinely patriotic group to leads the struggle for freedom. Semayawi Party has taken the lead with undeniable action let’s support them.
b. If the regime had a modicum desire to reform its governance, the current development would have been a good opportunity, unfortunately its reaction are negative and as usual consisting of intimidations and false accusations. As mass arrests and killings are likely to ferment further public anger, we have to look at what they could create to divert popular opinion and secure their survival. One way would be to use sacrificial lamb some the old honchos like Sebhat Nega, Azeb Mesfin and a few others for corruption, open some business space for loyal fellow travelers, and release some prisoners; a second way is to ignite some conflict with Eritrea or another neighbor in order to inflame the patriotism of the masses; a third way is to cause internecine conflicts and implement more coercive measures to impose their rule by share force.
c. Don’t expect any help from foreign sources; they have what they perceive as their national interest to maintain as long as things remain stable as they are momentarily. It is up to us to change conditions in our own country, and not by foreign forces.
d. The Semayawi Party and the parties who join them must be prepared to face these challenges with appropriately designed strategies and tactics, giving serious consideration to the strength and weakness of the regime, the foreign support and effective political and economic role, the present social and economic conditions, the dysfunctional federal structure imposed on the country, human rights, the rule of law and many other important matters.
e. The Diaspora could play an important role in providing professional and financial support to the movement inside the country.
I recommend that such support group be formed by all concerned, according to our capabilities and means at our disposal, without delving into partisanship and the like. Let’s do it !!!
June 3, 2013

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ (መንግስት ለሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም እንጠይቃለን!)

ሰማያዊ ፓርቲ
Blue Party Ethiopia ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ደማቅ ሆኖ ተካሂዷል፡፡ ለዚህ ሰልፍ መሳካት ከፍተኛ ድጋፍና አስተዋፅኦ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙኃንና በሰልፉ ለተሳተፉ ዜጎች እንዲሁም ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለረዱ የፀጥታ ኃይሎች ፓርቲያችን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
ከዚህ በተቃራኒ ግን ይህንን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የገዥው ፓርቲ ባለስልጣናትና የመንግስት ተወካዮች የተለመደውን ተልካሻ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡ የገዥው ፓርቲ ተወካይ ሰልፉን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት “የሐይማኖት አክራሪነት አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድብቅ አጀንዳው ገሃድ ወጣ” በማለት በሰጡት አስተያየት ፓርቲውን ለማንቋሸሽና ለማራከስ ሞክረዋል፡፡ ይህም ፓርቲውን በእጅጉ ያስቆጣ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ መሰረተ ቢስ ፍረጃ የገዥው ቡድን አባላት ለንግግራቸውና ለሚሰጡት አስተያየት ሚዛን የሌላቸው ከመሆኑ ውጭ በፓርቲው ፕሮግራምም ሆነ እንቅስቃሴ ከአሸባሪነት ጋር የሚያገናኘውን አንዳችም ነገር አልጠቀሱም፡፡ ፓርቲው በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ እና በሕገ መንግስቱ በተሰጠው መብት ተጠቅሞ በሕጋዊ ሥነስርዓት ያደራጀውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በእንዲህ አይነት መንገድ መፈረጅ ሰልፉ ከተጠራበት ዓላማና መንፈስ በእጅጉ የራቀ አስተያየት ሆኖ አግኝቶታል፡፡
ፓርቲው ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ በሰጣቸው መግለጫዎች በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት መቃወሙ ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ጥያቄ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ወደ አደባባይ ይዞ መውጣቱ ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ከባለሥልጣኑ የተሰጠው አስተያየት ግን የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገዥው ፓርቲ በበጎ ጎን አለማየቱንና የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ሁሉ ወደ ሽብርተኝነት ፍረጃ ለመክተት የሚያደርገውን ጥረት የሚያመላክት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በተጨማሪም ገዥው ፓርቲ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንደሆኑ አድርጎ እንደማያያቸውም ሰማያዊ ፓርቲ ተገንዝቧል፡፡
የመንግስት ተወካይ የሆኑት ባለስልጣን በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በሰላማዊ መንገድ ተጠይቆና ታውቆ መንግስት ራሱ ያመነውና እጅግ ሰላማዊ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲካሄድ ያደረገን ፓርቲ ውጭ የሚገኙ ኃይሎች ተላላኪ አድርጎ ማቅረብ የአብዬን ወደእምዬ እንደሚባለው መሆኑን እየገለፅን ይልቁንም በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰውን ፓርቲያችንን መንግስት ከልቡ ሊቀበለው እንዳልቻለ አስገንዝቦናል፡፡ በተጨማሪም ይህ አባባል ሰማያዊ ፓርቲን የማይመጥን፤ ፓርቲውም በተግባር እያሳየ ያለውን ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚጥስ በመሆኑ አጥብቀን እናወግዘዋለን፡፡ እኝሁ የመንግስት ባለስልጣን በሰላማዊ ሰልፉ የተላለፉት መልዕክቶች ህገ መንግስቱን የሚንዱ ናቸው በማለት በደፈናው ህዝብን ለማታለል ከመሞከራቸው በተለየ የትኛው ሃሳብ የትኛውን የሕገ መንግስት ድንጋጌ እንደሚፃረር ካለማመልከታቸውም በላይ ፓርቲው በፍርድ ቤት ጉዳይ ጣልቃ እንደገባ አድርጎ ለማሳየት መሞከር የመንግስትን ግብር ለሰማያዊ ፓርቲ መስጠት ከመሆኑም ሌላ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ያደርገዋል፡፡
በመጨረሻም የእስልምና እምነት ተከታይ ዜጎቻችን ማንኛውንም የመብት ጥያቄ ከሌሎች ወገኖቻቸው ጋር በሰላማዊ መንገድ የማቅረብ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው መሆኑን መንግስትም ሆነ ገዥው ፓርቲ እንዲያውቀው እያሳሰብን፤ ሰማያዊ ፓርቲ ከመንግስትም ሆነ ከገዥው ፓርቲ በሚሰጥ ማንኛውም ማስፈራሪያ ከጀመረው የሰላማዊ ትግል ጉዞ ፍፁም ወደ ኋላ እንደማይል፤ ይልቁንም የተነሱትን የሕዝብ ጥያቄዎች መንግስት በሦስት ወራት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ አሁንም በድጋሚ ማሳሰብ እንፈልጋለን፡፡
ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በወይዘሮ አዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደርግ ግፊቱ ጨምራል

ግፊቱ ጨምሯል!!አዜብ መስፍን የሙስና ንግስት ጉድ ፈላባት ዘንድሮ
እነመላኩ ፋንታን ተከትሎ በአዜብ መስፍን ላይ የሚቀርቡ የሙስና አቤቱታዎች ጨምረዋል::
የሙስና ኮሚሽን በአቶ ገብረዋህድ ቤት ባደረገው ፍተሻ እንዲሁም ከኣሁን ቀደም በመርማሪ ደህንነቶች ክትትል በተደረገ የስልክ ጠለፋ የቀድሞ ሟች ጠ/ሚ ባለቤት እና በአለም ትልቁ የሙስና አባት ኤፈርት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገብረዋህድ ባለቤት እና እህት ጋር በከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ስራ ይሰሩ እንደነበር እና ከታሰሩት ባለስልጣናት እና ባለሃብቶች ጋር የንግድ አጋርነት እንዳላት አረጋግጧል::ይህንን የሚጠቁሙ ሰነዶች እና ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡ ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች ምርመራው ወደ አዜብ መስፍን አምርቶ ለጥያቄ እንደምትፈለግ ፍንጭ እየሰጠ ነው ሲሉ የሙስና ኮሚጽሽን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
ለሙስና ኮሚሽን ከደረሱት አቤቱታዎች ከፊሎቹ :-ኤፈርትን ተገን በማድረግ የተለያዩ እቃዎችን ካለቀረጥ እያስገባች ነው:: ኤፈርት ለመንግስት መክፈል የሚገባውን ህጋዊ የግብርም ሆነ ሌላ ክፍያዎች እንዳይፈጸም አድርጋለች:: ዩዲ ኒሳን ዲዝል ገልባጭ መኪኖችን ካለቀረጥ ነጻ በማስገባት በአቶ ከተማ ከበደ/ኬኬ/ ስም ሸጣለች:: ከዚህ ቀደም እያሱ በርሄ ጋር በኋላም ከኮሎኔል ሃይማኖት ጋር የተከለከሩ የቴለኮሚኒኬሽን ኬብሎችን እና ቴክኖሎጊካል የመገናኛ መሳሪያዎችን ካለቀረጥ በማስገባት ሰርታለች::በነጻ ትሬዲንግ በኩል የተለያዩ ዘመናዊ መኪኖችን ካለቀረጥ እያስገባች በአቶ ነጋ ገ/ዝጌር ስም ትሸጣለች::በሰበታ አለምገና አከባቢ የአበባ ሰፊ እርሻዎች አላት :: በህገወጥ የዶላር እና የኢሮ ዝውውር ውስጥ መሪ ተሳታፊ ናት:: ባንክ ኦፍ ማሌዥያ እና የሲንጋፖር ባልሃብቶችን እንዲሁን ቻይናውያንን በህገወጥ አለማቀፍ የገንዘብ ዝውውር ተባባሪ አድርጋ እየሰራች ነው::በተለያዩ አረብ አገራት እና በሃገር ውስጥ ባስቀመጠቻቸው ደላሎች ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በሱዳን እና በየመን አድርጋ ወደ አረብ አገራት ትሸጣለች::በተለያዩ የቤተሰብዋ አባላት ስም ባወጣችው የኮንስትራክሽን ንግድ ፍቃዶች ጨረታዎችን በጉልበት ከመቀማት እየሰራሽ ሲሆን ሌሎች ባለሃብቶችን በስማቸው በመጠቀም የተለያየ ቢዝነሶችን እያካሄደች ነው የሚሉ አቤቱታዎች እና ጥቆማዎች ለሙስና ኮሚሽን የመርማሪዎች ቡድን ደርሷል::
ይህንን ተከትሎ ጠንካራዎቹ የወያኔ አባላት በወይዘሮ አዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደርግ ግፊት እያደረጉ ሲሆን ወይዘሮዋ በአሁን ሰአት ራሳቸውን በተለያየ ምክንያት ገኖ ለማውጣት ላይ ታች እያሉ መሆኑን ታውቋል::

ከ”ሻብያና ኦነግ ወደ “ግብፅ ጦርነት እየተፋጠነ ነው ?


እኔ እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የአባይን መገደብ እደግፋለው እንዲያውም ከሀይድሮኤሌክትሪክ ግድብ በተጨማሪ አባይን ለመስኖ ብንጠቀመው በምግብ እራሳችንን ለመቻል ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ያስገኛል ብለው ከሚያምኑት ወገን ነኝ።የጀብሀን፥ሻብያንና የወያኔን የኋላ ታሪክ ስናጠና ከምስረታቸው ጀምሮ አረብ ሀገሮችን በማስተባበር የጦርመሳሪያና ስንቅ ስትረዳቸው የነበረችው ግብፅ ነበረች።በናይል ወንዝ አለኝ ከምትለው ህገወጥ የይገባኛል ጥያቄ የተነሳ ኢትዮጵያን በተመለከተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲይዋን የቃኘችው “ከማዳከም አንፃር መሆኑ” ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነውና አዲስ ክስተት አይደለም ።ሀገርን በማስገንጠል እና በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጥቅም በተፃፃሪ በመቆም ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱን ሲያሳየን የኖረው ሟቹ አምባገነን መለስ ዜናዊ “አባይን ለመገደብ” ሲያስብ በአንድ በኩል እየተስፋፋ የነበረው የአረቡ አለም አብዮት ኢትዮጵያ ገብቶ ስልጣኔን አጣለሁ ከሚል ስጋት ፤ግድቡ ባይሰራ እንኳን ከሁለት አስረት አመታት በላይ ተወዝፎ የኖረ መሪ ስለነበር የታሪክሽሚያ በማድረግ የበታችነት ስሜቱን ይሞላለት ዘንድ “አባይን የደፈረ መሪ ” እየተባለ በሚጠላው ሕዝብ ላይ ለመኮፈስ ፤ ከእያንዳንዱ “ልማት” ጀርባ ኢፈርትና ህወሀታዊ ነጋዴዎችን መጥቀም ስትራቴጅው ስለሆነ ከፕሮጀክቱ ጀሌዎቹን ተጠቃሚ ማድረግ ፤ መርዘኛው አላማ ግን በሀገር ውስጥ ፖለቲካ ሻቢያ መጣባችሁ፥ኦነግ ሊበላችው ነው፥ አሸባሪዎች በፈንጅ ሊጨርሷችሁ ነው፥ግንቦት ሰባትና ሌሎች ድርጅቶች በሻብያ እየተረዱ ነው አይነት ፕሮፓጋንዳዎች በህዝቡ ውስጥ የተፈለገውን ውጤት አላመጣ ብለው “አሸባሪነት” ማላገጫ መሆኑን ሲገነዘቡ እውነተኛዋ ግን አደገኛዋ ጠላታችን ግብፅ ጋር “የአባይ ግድብ” ከስራው ይልቅ ፕሮፓጋንዳውን በማጦዝና ግብፃውያንን በማስቆጣት የጦርነትነጋሪት እንዲጎስሙ በመገፋፋት አንድም ለውጭ ወራሪ ሁሌም አንድ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብን ድጋፍ ለማግኘት መሞከር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የስርዓቱን ተቃዋሚዎች “በአሸባሪነትና በሻብያ እረዳትነት መፈረጅ”ለውጥ አለማምጣቱን ስለተረዱ “ጠንከር ጠንከር ያሉትን ተቃዋሚዎችን” በግብፅ ይረዳሉ ብሎ በማናፈስ በሕዝብ እንዲተፉ ማድረግ አብይ ምክንያቶች ይመስሉኛል።ለዚህም ነው ገና ተግባር ላይ ሳይውል “Project X” ሲባል ነበር የተባለውን የአባይ ግድብ እያንዳንዷን ጥቃቅን ነገር በማጉላት ከግብፅ ጋር እሰጣገባ መግባት እንደስትራቴጅ የታየው አንድ ግድብ ሲገደብ የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየር ተራና የተለመደ ክስተት ሆኖ ሳለ “አባይ ተቀየሰ” የሚለው ዜና ሆን ተብሎ የሚዲያ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ ግብፆችን አስቆጥተው “መጡባችው” የሚለው ፕሮፓጋንዳ አየሩን የሞላው። እንደ እውነቱ ከሆነ የግብፅ መንግስትና ወያኔ በጋራ እየሰሩ የሁለቱ ሀገር ሕዝቦች በየመንግስቶቻቸው ያላቸውን ቅሬታ በጋራ እያስቀየሱ ያሉ ይመስለኛል ስለዚህ ጦርነትም አይኖርም ግድቡም “እየተፋጠነ ነው” የሚለውን ዜና ለሚቀጥሉት “ብዙ” አመታቶች እንሰማለን።
ሀና መታሰቢያ 28/09/05