Sunday, 1 December 2013

የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ከሰራዊቱ ሊቀነሱ መሆኑ ታወቀ በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን ነግሷል፤ የሕወሃት ጄኔራሎች ፈርተዋል


ምንሊክሳልሳዊ-

በሰራዊቱ ውስጥ የተነሳውን ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ተከትሎ የቀድሞ የኢሕዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት ከመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥእንደሚቀነሱ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል:: በየቀኑ ለስብሰባ የሚቀመጠው ሕወሓት መራሹ የጄኔራል መኮንኖች የአንድ ብሄር ቡድንተጠንቷል ባለው እና የተወያየበት ሰነድ እንደሚያመለክተው በሰራዊቱ ውስጥ የሚነሱ ማንኛቸውም ጥያቄዎች የሚፈጠሩት ከአማራው እናከኦሮሞው ወገን ከሆኑት መኮንኖች ሲሆን ይህንንም የሚመሩት የውስጥ መዥገር የሆኑት የብኣዴን እና የኦሕዴድ መኮንኖች ስለሆኑ ከሰራዊትውስጥ በመቀነስ በተለያዩ መንገዶች በወንጀል ለማጥመድ እና ከነማን ጋር እንደሚገናኙ አስፈላጊውን የደህንነት ክትትል ማድረግ ይገባል ሲልተነጋግሮበታል::
እነዚሁ የለውጥ ጥያቄ ያነሱት የሰራዊቱ መኮንኖች ከተለያዩ የታጠቁ የጠላት ሃይሎች እና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋርበመገናኘት የመንግስትን ህልውና እየተፈታተኑት ከመሆኑም ባሻገር የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ከቀድሞ ስርኣት የተወረሱ እና ለዲሞክራሲውእና ለልማቱ እንቅፋት ስለሆነ አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ተብሏል::ከግንቦት ሰባት እና ከተቃዋሚ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘትበሰራዊቱ ውስጥ ያለነበሩ እና ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች በመፍጠር ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ሰዎችንበማስኮብለል መረጃ በማቀበል እንዲሁም አለመተማመን እንዲኖር በመስራት ከፍተኛ ደንቃራ ሆነዋል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮቹ እንደገለጹት የቀረበው ሰነድ ለጄኔራል መኮንኖቹ ያልተበተነ ሲሆን የስብሰባው መሪ የሆኑት ኢታማጆር ሹሙ እጅበመሆን ሰነዱ እየተነበበ የተወያዩበት እና ይህም የሚያመለክተ በሕወሓት ጀኔራሎች መካከልም መተማመን አለመኖሩን ያሳያልብለዋል::በሙስና ከአስተዳደርዊ ባለስልጣናት በበለጠ የተዘፈቁት የሕወሓት ጄኔራሎች በስብሰባ እና አብዛኛው ንብረቶቻቸን በተዘዋዋሪበመሸጥ ስራ ላይ እየተንቀሳቀሱ ሲገኝ በሱዳን በኢምሬት እና በአውሮፓ አገሮች እንዲሁም በአሜሪካ በቤተሰቦቻቸው ስም የተለያዩንብረቶችን በመግዛት ላይ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮሽ ጨምረው ገልጼዋል::

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10271

Saturday, 30 November 2013

እስራኤል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 60ሺህ አፍሪካውያንን አስወጣለሁ አለች

Israeli-prime-minister-Be-001
ከ120 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሊቢያ ይመለሳሉ
እስራኤል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 60ሺህ የሚጠጉ አፍሪካውያን ስደተኞችን ከሃገሯ እንደምታስወጣ ያስታወቀች ሲሆን በህገወጥ መንገድ በሊቢያ የሚኖሩ ከ120 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡ የእስራኤል ካቢኔ ባለፈው እሁድ ስደተኞቹን የሚያስወጣ አዲስ ህግ ካፀደቀ በኋላ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያዊን ኔትያሁ፣ ህገወጥ ስደተኞቹን ከሀገራቸው እንደሚያስወጡ አስታውቀዋል፡፡ የአገሪቱ ካቢኔ ባፀደቀው መመሪያ መሰረት እስራኤል በመጀመሪያው ዙር 4ሺ ስደተኞችን የምታስወጣ ሲሆን በቀጣይም በዘላቂነት ህገወጥ ስደተኞች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ በዘላቂነት ለመከላከል ከግብጽ የምትዋሰንበትን ድንበር ጥበቃ እንደምታጠናክር ገልፃለች፡፡ ከሀገሪቱ ይወጣሉ ተበለው የሚጠበቁት አብዛኞቸ ሱዳናውያንና ኤርትራውያን ሲሆኑ ኢትዮጵውያኑም የገፈቱ ቀማሽ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊቢያን ማረፊያ ያደረጉ ከ120 በላይ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ካይሮ ባለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትብብር የጉዞ ሰነዳቸው ተዘጋጅቶላቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በአለማቀፍ የስደተኞች ተቋም (IOM) ትብብር እንደሚመለሱ ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በባህሬን በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ትሠራ የነበረች ኢትዮጵያዊት በሶስት ወንዶች ተጠልፉ መደፈሯንና በሴተኛ አዳሪነት እንድትሰራ መገደዷን ገልፃ፤ ድርጊቱን ፈጽሟል የተባለውን ባንግላዲሻዊ እንደከሰሰች ሰሞኑን ተዘግቧል፡፡ የ28 አመቷ ኢትዮጵያዊት ቆሻሻ ለመድፋት ወደ ውጪ ስትወጣ ሁለት ማስክ ያጠለቁ ወንዶች አፍነው በመውሰድ አፓርታማ ቤት ውስጥ ከነበሩ አራት የተለያዩ አገራት ሴቶች ጋር በሴተኛ አዳሪነት እንድትሰራ መደረጓን ገልፃለች፡፡ በቀን አስር ጊዜ ያህል ከተለያዩ ወንዶች ጋር ወሲብ እንድትፈጽም ትገደድ እንደነበርም ለፍ/ቤት አስረድታለች፡፡
Source-addisadmass.com

የ132 መንግስታዊና የግል ድርጅቶችን ማህተም እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችን እና የተለያዩ ግለሠቦችን ማህተም በመጠቀም ሃሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረው ተከሰሰ

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና የኢ/ር ሃይሉ ሻውል ቲተርና የፓርቲያቸው ማህተም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የበርካታ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ማህተም
የኦነግና የኢሜሬት ኢምባሲ ማህተሞች ተገኝተዋል
የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የ132 መንግስታዊና የግል ድርጅቶችን ማህተም እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችን
እና  የተለያዩ ግለሠቦችን ቲተር በህገወጥ መንገድ በመያዝ ለግለሠቦች ሃሠተኛ ማስረጃዎችን ሲሠራ ነበር የተባለው
ተጠርጣሪ ላይ በፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ የቀረበው ክስ እንዲሻሻል ፍ/ቤት ብይን ሰጠ፡፡
አቃቤ ህግ በተጠርጣሪው አቶ ኮከብ ጥላሁን አማረ ላይ ሁለት ክሶችን ያቀረበ ሲሆን በመጀመሪያው ክስ ላይ የውጭ
ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የኤምባሲዎች፣ የግልና የመንግስት
ዩኒቨርስቲዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የሃገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የአስተዳደሩን
የተለያዩ ቢሮዎች የክልል መንግስታት የተለያዩ መስሪያ ቤቶች የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ
ኮሚሽን  የቦሌ ኢምግሬሽን የኢትዮ ቴሌኮም እና የንግድ ሚኒስቴር የተለያዩ ቢሮዎችና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ማህተም
እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽነሮችና ኢንስፔክተሮችን ጨምሮ የተለያዩ ግለሠቦችን ቲተር በተጨማሪም የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ
ጋዜጠኞች ማህበርንና የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ማህተምና የሊቀመንበሮቻቸውን ቲተር ይዞ መገኘቱን
አመልክቷል፡፡
ተከሳሹ ከመንግስት ሚኒስቴር መስርያ ቤቶችና ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ባሻገር እንዲሁም አሜሪካ እና የግብፅ
ኤምባሲዎችን ማህተም፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ደግሞ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)፣ የአንድነት
ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ማህተሞች እና የሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ
ድርጅቶች ማህተም ይዞ መገኘቱ ተገልጿል፡፡ የኢ/ር ኃይሉ ሻውል እና የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ቲተሮችም ይዞ ተገኝቷል
ይላል የክስ ዝርዝሩ፡፡
ከግል ተቋማት መካከልም የእንይ ሪል ስቴት ማህተም፣ ብዛት ያላቸው የግል ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማህተም፣
የተለያዩ ባንኮችን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማህተም እንዲሁም መንግስት ወደ ግል ይዞታነት እንዲዞር በማሠብ ተደጋጋሚ
ጨረታ የሚያወጣበት የግዮን ሆቴሎች ድርጅት ማህተም ይገኙበታል፡፡
በአቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ላይ ተከሣሹ በድምሩ 132 ከሆኑት የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ማህተምና ቲተር እንዲሁም ህጋዊ
ሠነዶች በተጨማሪም ኮምፒውተሮች፣ ስካነር፣ ልዩ ልዩ የሃሠት ሠነዶች ተዘጋጅተው የሚገኙባቸው ሲዲዎችን ይዞ
በመገኘቱ፣ በፈፀመው የመንግስትን ወይም የመንግስት ባለስልጣናት ማህተሞችንና የህዝብ ጥቅምን የሚመለከቱ ነገሮችን
ሃሠተኛ አድርጐ ወይም አስመስሎ ለመስራት የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል፡፡
በኮሚሽኑ አቃቤ ህግ በሁለተኛ ክስነት የቀረበውም ግለሠቡ እነዚህን ማህተሞች፣ ቲተሮችና ሠነዶች በመጠቀም ለተለያዩ
ግለሠቦች ህገ ወጥ የትምህርት ማስረጃ፣ የልደት ሠርተፊኬት፣ የተለያዩ ድጋፍ ሠጪ ደብዳቤዎች፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የስራ
ልምድ፣ የንግድ ፈቃድ፣ የመኪና ሊብሬ፣ የኤምባሲ ደብዳቤዎች እንዲሁም ፓስፖርቶች እና ሌሎች ብዛት ያላቸውን
ህገወጥ ሠነዶች እጁ እስከተያዘበት ሐምሌ 2005 ዓ.ም ድረስ አስመስሎ በማዘጋጀት፣ ተከሣሹ በፈፀመው መንግስታዊ
እና የህዝብ ጥቅምን የሚመለከቱ ሠነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ተከሷል ይላል፡፡
የመንግስት እና የግል ተቋማት ሠነዶች መስለው በተከሣሹ የተዘጋጁ ሃሠተኛ ሠነዶች በተከሣሹ መኖሪያ ቤት በተደረገው
ብርበራ መገኘታቸውም በክሱ ተመልክቷል፡፡
ከትናንት በስቲያ ሃሙስ እለት የዋለውና የሙስና ጉዳዮችን የሚመለከተው የከፍተኛው ፍ/ቤት  1ኛ ወንጀል ችሎትም
ቀደም ባለው ቀጠሮ ከተከሣሽ የቀረበውን የክስ መቃወሚያ እና ከአቃቤ ህግ የተሠጠውን የመቃወሚያ መልስ ከመረመረ
በኋላ በሠጠው ብይን፤ ተከሣሹ ኮሚሽኑ ክሡን የማቅረብ ስልጣን የለውም በማለት ያቀረበውን ተቃውሞ
እንዳልተቀበለው አስታውቆ፤ ከሣሽም ሊያሻሽላቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ብርበራ
የተካሄደበትን ቤት አድራሻ በተመለከተ አቃቤ ህግ በተገቢው መንገድ አሟልቶ እንዲያቀርብ፣ “ሌሎች በርካታ ሃሠተኛ
ሠነዶች” ተብለው የተመለከቱ በዝርዝርና በቁጥር እንዲጠቀሱ እንዲሁም የመንግስት እና የግል ሠነዶች ተለይተው
እንዲቀርቡ ሲል ፍ/ቤቱ ብይን የሠጠ ሲሆን በአጠቃላይ አቃቤ ህግም ክሡን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ብሏል፡፡
ቀጣዩን ሂደት ለመመልከትም መዝገቡን ለታህሣስ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡
addis admas

Friday, 29 November 2013

የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ከተቃዋሚዎችን ጋር ተወያዩ

ለአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ካሪቢያን፣ፓስፊክና አፍሪካ ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙት የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በቢሮአቸው ከተቃዋሚዎች ጋር ተወያዩ፡፡ ከስፔን፣ ፖርቱጋል፣ ማልታ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የተወከሉ ልኡካን በኢትዮጵያ ስላላው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች በኩል ከመድረክ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአንድነት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ አስራት ጣሴ፣ ከመኢአድ አቶ አበባው መሀሪ፣ ከሰማያዊ ፓርቲ አቶ ይልቃል ጌትነት እንዲሁም ከኢዴፓ አቶ ልደቱ አያሌውና የፓርቲው ፀሀፊ ተገኝተዋል፡፡ ከተወካዮቹ በኩል የተነሱት ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡- 1. የፓርቲዎች ቁጥርስ ለምን በዛ? 2. በህግ አግባብ የተመዘገቡ ስንት ናቸው? 3. በፕሮግራምና በርዕዮተ ዓለም ልዩነታቸውና ተመሳሳይነታቸው ምን ይመስላል? 4. የምርጫ ሥርዓታችሁ የትኛው ነው? 5. በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ቁጥር ስንት ይሆናል? 6. ተቃዋሚዎች ከህዝብ ጋር ለመገናኘት ምን ዘዴ ትጠቀማላችሁ? በገጠርና በከተማስ ምን ይማስላል? 7. ከዲያስፖራ ጋር ያላችሁ ግንኙነትስ እንዴት ያለ ነው? 8. ከሌሎች ሀገራት ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ ወይ? 9. የአውሮፓ ህብረት ምን ማድረግ (ማገዝ) ይችላል? 10. ህብረ-ብሄራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የቁጥራችሁ ምጣኔ ከተሰጡት መልሶች የሚከተሉት የዶ/ር ነጋሶ ሀሳብ ይገኙበታል፡- ኢህአዴግና የመሰረተው መንግስት ህገ መንግስቱን በመጣስ መካናቸውን፤ ህገ- መንግስቱን የሚጥሱ ህጎችን ማውጣት ብርቁ እንዳልሆነ፤ የአንድ ፓርቲ አምባገነንነት ጥግ ድረስ ማድረሱን፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በውሸት ክስ እያሰሩ ፓርቲዎችን እንደሚያዳክሙ ለምሳሌ አንዱአለም አራጌና በቀለ ገርባ፤ ተቃወሚዎች ልሳን እንዳያሳትሙ እንደሚደረግና እንደሚዘጋባቸው ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲዋ ፍኖተ-ነፃነት፤ የቢሮና የአደራሽ ኪራይ መከለልከል፤ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማድረግ መከልከል፤ ቅስቀሳ ማድረግ መከልከል (ሰዎች፣ የቅስቀሳ መሳሪያዎችና መኪኖች እንደሚታሰሩ)፣ ሁል ጊዜ ያለው ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ድብደባ፣ ጠለፋ፣ ማሰቃየት፤ አባላትን ከመሬት፣ ከስራና ከቤታቸው ማፈናቀል፤ በውሸት ተቃዋሚዎችን ከአሸባሪዎች ጋር ማዛመድ፤ የስም ማጥፊያ ፊልሞችን መፈብረክ፤ እንቅስቃሴን መገደብ፤ መንግስት ፍትሃዊ የሆነና በህግ አግባብ የተቀመጠ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ ሲገባው ያለማድረግ፤ ዜጎችን ዘር ማጥፋት እስኪመስል ድረስ ከይዞታቸው ማፈናቀል፤ ለውይይትና ለድርድር እንቢ ባይ መሆን የሚሉ የኢህአዴግ ባህሪያት ቀርበዋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ምን ማድረግ ይችላል ለሚለው ደግሞ የሚከተሉት ማሳሰቢያዎች ተሰጥተዋል፡- —————————————— ለልማትና ለማህበራዊ ጉዳዮች ድጋፍ አትሥጡ ባይባልም ኢህአዴግ ግን የተሰጠውን ዕርዳታ 1. የራሱን ቢሮክራሲ እንደሚያጠናክርበት 2. አፋኝ የፀጥታና የፖሊስ ኃይሉን እንደሚያጠናክርበት 3. የፓርቲውን መዋቅሮች እንደሚያደራጅበት እንዲያውቁ ተብሏል፡፡ በቅርቡ እንኳ የአውሮፓ ህብረት የሰጠውን 217 ሚሊዮን ዩሮ ይህ ሳይጠና መሆን እንዳልነበረበት ተቃዋሚዎቹ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር ሥልጣን ተቆርሶ እንዲሰጣቸው ሳይሆን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው እንዳይገደብና እውነተኛ ምርጫ እንዲደረግ ምህዳሩ መስተካከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በአጠቃላይ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲከበር ጫና እንዲያደርጉ፤ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲደራደር እንዲያግባቡ የሚሉ ናቸው፡፡ አቶ ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ሁኔታው ወደ አስከፊ ደረጃ እያዘገመ በመሆኑና የኢህአዴግ ባህሪ ፍፁም አምባገነናዊ በመሆኑ ከንግዲህ ኢህአዴግ አጋር እንደማይሆናቸው ገልፀዋል፡፡ አቶ ልደቱ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የታይታ (window dressing)፣ በህብረተሰቡ፣ በተቃዋሚዎችና በመንግስት በኩል ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህል እንዳለ፣ ድህነት በበኩሉ የዴሞክራሲ ጠንቅ መሆኑ፣ ነፃ የዴሞክራሲ ተቋማት እንደሌሉና መንግስትና ፓርቲ እንደማይለዩ አስረድተዋል፡፡ ሰብሳቢዋ በበኩላቸው “COMPREHENSIVE SYSTEM OF DIALOGUE” እንዳላቸው፣ ጠ/ሚ/ሩን በአመት ሁለቴ እንደሚያገኟቸው፣ በፀረ ሽብር ህጉ ህገ ወጥነት እንደሚያምኑ፣ ለ2007ቱ ምርጫ ከወዲሁ ዝግጅት እንደጀመሩና የምርጫ ግብረኃይል እንዳቋቋሙ ገልጸዋል፡፡ አና ጎሜዝ በበኩላቸው ከኢትዮጵያኑ ባልተናነሰ የመንግስትን ባህሪያት ሲተነትኑ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ውይይት ብዙ ነገር እንደማይጠብቁ በማጠቃለያ ሀሳባቸው ገልጸውልናል፡፡
finote nesanet

በቤሩት አንዲት ኢትዮጵያዊት በአሰሪዎችዋ ተቃጠለች

በቤሩት አንዲት ኢትዮጵያዊት በአሰሪዎችዋ ተቃጠለች :: አዳነች የምትባል ኢትዮጵያዊ ቤሩት ከሄደች ሁለት አመት ሲሆናት አሰሪዎችዋ በርሜል ውስጥ ከተው እና ጋዝ አርከፍክፈው አቃጥለዋታል :: በዛ አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያኖች ይህን ለቆንጽላው ጽፈት ቤት ደውለው ቢነግሩ "አርፋችሁ ተቀመጡ" የሚል መልስ ነበር የተሰጣቸው :: ይህን ዜና ያገኘሁት zehabesha.com ነው http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10112

Thursday, 28 November 2013

የሦስትዮሽ ጉባኤና ኢትዮጵያ,ወይዘሮ አና ጎሜሽ በትናንቱ ጉባኤ በነበረዉ ክርክር ዋና ተሳታፊ ነበሩ

በ1997 ኢትዮጵያ ዉስጥ የምርጫ ሒደት የተከታተለዉ የአዉሮጳ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድንን የመሩት እና የኢትዮጵያ መንግሥትን አጥብቀዉ የሚተቹት የአዉሮጳ ሕብረት እንደራሴ ወይዘሮ አና ጎሜሽ በትናንቱ ጉባኤ በነበረዉ ክርክር ዋና ተሳታፊ ነበሩ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA - MARCH 18: A plaque stands outside the headquarters complex of the African Union (AU), which was a gift by the government of China and completed in 2012, on March 18, 2013 in Addis Ababa, Ethiopia. Ethiopia, with an estimated 91 million inhabitants, is the second most populated country in Africa and the per capita income is $1,200. (Photo by Sean Gallup/Getty Images)
የአዉሮጳ ሕብረት፥አፍሪቃ፥ ካራይብ እና ፓስፊክ (ACP) በምሕፃሩ የሚያስተናብራቸዉ ሐገራት የምክር ቤት እንደራሴዎች አዲስ አበባ ዉስጥ ያደረጉት የሰወስት ቀን ጉባኤ ትናንት ተጠናቅቋል። በጉባኤዉ የመጨረሻ ቀን ተሰብሳቢዎች የኢትዮጵያ የምጣኔ ሐብት ዕድገት፥ መርሕ እና የሠብአዊ መብት ይዞታን አንስተዉ ለግማሽ ቀን ያሕል ተከራክረዋል።በ1997 ኢትዮጵያ ዉስጥ የምርጫ ሒደት የተከታተለዉ የአዉሮጳ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድንን የመሩት እና የኢትዮጵያ መንግሥትን አጥብቀዉ የሚተቹት የአዉሮጳ ሕብረት እንደራሴ ወይዘሮ አና ጎሜሽ በትናንቱ ጉባኤ በነበረዉ ክርክር ዋና ተሳታፊ ነበሩ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ የስብሰባዉ ሒደት ተከታትሎት ነበር።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
 Audios and videos on the topic

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የመኪና አደጋ ደረሰ

ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 11 ሰዓት ላይ ከሰሜት ሆቴል ወደ ጊዮርጊስ ቁልቁል ሲሄድ የነበረ አንድ ከባድ የጭነት ማመላለሻ(SINO TRUCK)  መኪና ባጋጠመው የፍሬን ችግር ምክንያት ሹፌሩ መኪናውን መቆጣጠር አቅቶት ቀጥታ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጽርን ደርምሶ በመግባት ከፍተኛ አደጋ አድርሷል ፡፡  በወቅቱ በቦታው ላይ በእቅልፍ ላይ የነበሩ ሁለት ጎዳና ተዳዳሪዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የሆነ አደጋ ደርሶባቸዋል ፤ ከፍተኛ አደጋ የደረሰባቸው ሶስቱ ሰዎች ወዲያውኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች እና አካባቢው ላይ ባሉ ሰዎች ጥረት ራስ ደስታ ሆስፒታል ተልከው ጊዜያዊ እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል ፡፡ በአደጋው የቤተክርስቲያኑ መግቢያ በር እና ግንብ ከፍተኛ አደጋ የደረሰበት ሲሆን በተጨማሪ ሰው በፍርስራሽ ውስጥ ይኖራል ተብሎ በመገመቱ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፍርስራሹን የማንሳት ስራ ሲያከናውኑ ተስተውሏል፡፡ የደረሰው አደጋ አሰቃቂ መሆኑን በቦታው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል፡፡
ከአደጋው በኋላ የመኪናው ሹፌር በሰጠው ቃል መሰረት የመኪናው ንፋስ እምቢ በማለቱ አደጋው የደረሰ መሆኑን ተናግሯል፤ በአሁኑ ሰዓት  ፖሊስ የመኪናው ሹፌር ላይ ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
source.አንድ አድርገን