Monday, 16 December 2013

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በኖርዎይ በርገን ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሔደ

2

በበርገን ከተማ ለመጀመርያ ግዜ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  በርገን ቅርንጫፍ አስተናጋጅነት በዲሴምበር 14፥2013 የተዘጋጀው ህዝባዊ ስብሰባ በደመቀ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ100 በላይ የሚገመት ህዝብ የተገኘ ሲሆን ከተለያዩ የኖርዎይ ከተሞች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱም ላይ ተገኝተዋል፥፥
በዝግጅቱ ላይ ተጋባዥ እንግዶች የነበሩት
1ኛ. ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግንቦት7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚ አባል
2ኛ. አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ  ዋና ሊቀመንበር
3ኛ. ዶ/ር ሙሉአለም አዳም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ በኖርዎይ የድርጅት አባል ናቸው፥፥
የውይይት መድረኩ ከመጀመሩ በፊት በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ፥ እየተገደሉ እንዲሁም በግፍ ኢሰብአዊ ድርጊት ለተፈፀመባቸው ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  የበርገን  ቅርንጫፍ ጽ/ት ሰብሳቢ አቶ ሹሜ ወርቁ አጭር የመክፈቻ ንግግር ካረጉ በኋዋላ ተጋባዥ እንግዶቹ በየተራ ስለሚመሩአቸው ድርጅቶችና የወቅቱን የሃገራችንን አስከፊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተና ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አብረው በስምምነት የሚሰሩበትን ሁኔታ ማምጣት እንዳለብን እንዲሁም ስለ  መደራጀት አስፈላጊነት ሰፋ ያለ ማብራርያ  ሰጥተዋል፥፥
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ስለ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዓላማ ራእይና ግብ እንዲሁም ስለውጭ እምቢተኝነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከሰጡ  በኋላ ሁሉም ኢትዮያዊ ግንቦት7ትን እንዲቀላቀልና ሃገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ተባብረን እንታደጋት በማለት  ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተለያዩ ድርጅቶች ስር ተደራጅቶና ታቅፎ መንቀሳቀሱ ያለውን ጠቀሜታና የሐይማኖትና የሲቪክ ማህበራትን ማደራጀትና ማጠናከር ጠቃሚ መሆኑን አሳስበዋል፥፥ ፥፥
 አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ  ዋና ሊቀመንበር ስለ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ አመሰራረትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ በሰፊው ገለጻ  ያደረጉ ሲሆን  ከህዝቡም  ለቀረበላቸው ጥያቄም  ምላሽ ሰጥተዋል፥፥
በተጨማሪም ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም በኖርዎይ የስደተኞች አኗኗር ዙሪያ ያለውን ችግር እንዲሁም ሁሉም የተቃቃሚ ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነው እንዲሰሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ የበርገን ቅርንጫፍ በተቋቋመ በአጭር ግዜ ውስጥ የደረሰበት ደረጃም በእጅጉ አስደሳች እንደሆነ በመግለፅ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ህዝቡ ለነጻነት ለሚደረገው  ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፥፥
እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ በሐና ሰመረ ሐቅ ተሰደደ በሚል ርእስ አጭር ግጥም የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በሎሚታ ገብረሚካኤል በምስል በተደገፈ በቀረበው የኢትዮጵያ የታሪክ ጉዞ ከነገስታት ስርአት እስከ ሐገራችን በወያኔ አገዛዝ ስር ወድቃ አሁን የደረሰችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ዘገባ ለታዳሚው ቀርቧል፥፥
በመጨረሻም ለእንግዶቹ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ ዝግጅቱ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሐይል መዝሙርን በመዘበር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥፥
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  የበርገን  ቅርንጫፍ ጽ/ት

Wednesday, 11 December 2013

አንዱዓለም አራጌ ከእስር ቤት “እኔ እስሩ አልከበደኝም፤ በጣም ያሳዘነኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም” አለ

(ዘ-ሐበሻ) የ2005 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ተብሎ የተሰየመውና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ወጣቱ ታጋይ አንዱዓለም አራጌ እስር ቤት ሊጠይቁት ለሄዱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መልዕክት አስተላለፈ። በጣም ማዘኑንም ገለጸ። ዕድሜ ልክ እስራቱን ተቀብሎ እስር ቤት የሚገኘው አንዷለም አራጌ “ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል እስካሁን በእስር ቤት እየማቀቀ ሲሆን “በእኔ መታሰር ብዙ ልትጠቀሙበት ስትችሉ አለመጠቀማችሁ ያሳዝነኛል:: እኔ አሁን በእስር ባለሁበት ሰዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግሉን ወደ ፊት ለመግፋት አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ቢችልም አልተጠቀማችሁበትም ” ሲል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መውቀሱን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
 
“እኔ መታሰሩና፤ በእስር ቤት እየደረሰብኝ ያለው ስቃይ አልከበደኝም። የከበደኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አለመቻላችሁ ነው። በኔ መታሰር መንግስት ብዙ ጫና ውስጥ እንዳለ ይታወቃል። በኔ መታሰር ብዙ ሥራ ልትሰሩበት፤ ትግሉን ወደፊት ልታስኬዱበት ስትሉ ይህን አላደረጋችሁም” ያለው አንዷለም አራጌ አሁንም የመንፈስ ጥንካሬው አብሮት እንዳለ በ እስር ቤት ካነጋገሩት ወገኖች መካከል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
 
አንዷለም አራጌ የፌደራሉ ማረሚያ ቤት የሚጠይቁህን ሰዎች ስም ዝርዝር አስመዝግብ ተብሎ ተጠይቆ የነበረ ሲሆን እርሱ ግን ማንም ሰው መጥቶ ሊጠይቀኝ መብቱ ነውና ስም ዝርዝር አውጥቼ አልሰጥም ሲል ፈቃደኛ አለመሆኑን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም።

Tuesday, 10 December 2013

ማንዴላን በተመለከት ለግማሽ ዓመታት የተደበቅ ምስጢር

                                  ሻምበል ጉታ ዲንቃ የማንዴላን ህይወት ያተረፉ ጀግና   

guta dinqa


ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል። በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ መንግስት ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች።
ከዘመናት በኃላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት  የግድያ ሙከራ ሴራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንን ዛሬ ጥቅምት 15/2006 ዓም ለመጀመርያ ጊዜ በሸገር ራድዮ የዜና እወጃ ላይ ገልፀዋል።
ሻምበል ጉታ ዲንቃ በንጉሡ ዘመን የፖሊስ መኮንን ነበሩ። ማንዴላን በከፍተኛ ሚስጥር እንዲጠብቁ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ በወቅቱ ኮ/ል የነበሩ)፣ኮ/ል ፍቃደ እና ሻምበል ፈቃደ ውስጥ ነበሩ።ዛሬ የ76 አምቱ የእድሜ ባለፀጋ  ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሸገር ሲናገሩ እንዲህ አሉ።
ማንዴላን እንድጠብቅ ኃላፊነት የተሰጠኝ እኔ ነበርኩ።ማንዴላ የሚያድሩበት እና ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱበት የኮልፌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቦታ ነበር ።በተለይ እርሳቸው የሚገኙበት ቦታ ‘የፈንጅ ወረዳ’ ነበር የሚባለው።ከአራታችን በቀር ማንም ወደ እርሳቸው ቦታ ዝር ማለት አይችልም። ሲተኙ መስኮት ከፍተው ነው የሚተኙት።…አንድ ቀን ታድያ አብሮኝ ከሚሰራው የፖሊስ ባልደረባዬ በጥብቅ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ።ጣይቱ ሆቴል ተቀጣጠርን እና ሃሳቡን ገለፀልኝ።” ካሉ በኃላ  አሁን አዲስ አበባ ላፍቶ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ሻምበል ጉታ በመቀጠል እንዲህ ብለዋል-
ጣይቱ ሆቴል የወሰደኝ ሰው ለጊዜው 2000 ፓውንድ በወቅቱ አስቡት 2000 ፓውንድን እና  ሰጥቶ እንዲህ አለኝ- ‘ሁለት ዕድል ከፊታችን ተቀምጧል።ሊያመልጠን አይገባም።ከፍተኛ ገንዘብ እናገኛለን።ቀጥሎም ወደ ውጭ ሀገር የመሄድ ዕድል አለን።ከአንተ የሚጠበቀው ማንዴላ በተኛበት ዛሬ ሌሊት በመስኮት ገብተህ በገመድ አንቀህ ግደል እና ውጣ እንደወጣህ መኪና ተዘጋጅቶ ይጠብቅሃል ከእዚህ የውትድርና ሕይወት እንገላገላለን’ አለኝ። እኔም ጉዳዩን ከሰማሁ በኃላ በጉዳዩ የተስማማሁ መስዬ ቀጥታ  ለጀኔራል ታደሰ ነገርኩኝ። ጉዳዩ በሚስጥር ተይዞ ይህንን ያደረጉት ሰዎች ተደረሰባቸው እና ከሀገር እንዲወጡ (እንዲባረሩ) ተደረጉ ይህ ሚስጥር ለዘመናት ከእኔ ጋር የኖረ ነው።ጉዳዩን ማንዴላም አያውቁትም።” ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ የሰጠቻቸው ፓስፖርት
ኔልሰን ማንዴላ በወቅቱ እንደ ሻምበል ጉታ ዲንቃ አይነት ታማኝ የኢትዮጵያ የፖሊስ መኮንን ባይገጥማቸው ኖሮ የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታሪክ ሂደትም ሆነ የነፃነት ትግሉ ታሪክ ሌላ መልክ በያዘ ነበር።ይህ ጉዳይ እጅግ ትልቅ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ ፖሊስ ለአፍሪካ ያደረገው አስተዋፆ የሚያጎላ በመሆኑ በኢትዮጵያ የዜና አገልግሎቶች ሁሉ ትኩረት ተሰጥቶት የዓለም አቀፍ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ለኢትዮጵያ ፋይዳው ብዙ ይመስለኛል። እስካሁን ድረስ ማንዴላ በኢትዮጵያ ምን ያህል ድጋፍ ተደርጎላቸው እንደነበር የማያውቅ አፍሪካዊም ሆነ ደቡብ አፍሪካዊ እንዲሁም የዓለም ሕዝብ አለ። በመሆኑም ይህ ጉዳዩን ለማጮህ የሚረዳ ወርቃማ አጋጣሚ ነው።
በመሆኑም ቢያንስ ለሻምበል ጉታ ዲንቃ የኢትዮጵያ ፖሊስ ጠርቶ ማዕረግ እና ሽልማት ከእዚህ ባለፈም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት እና  ማንዴላ  በሕይወት ዘመናቸው ሳሉ ሻምበል ጉታ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሄደው እንዲያገኙዋቸው ማድረግተገቢ ይመስለኛል። ጉዳዩ የደህንነት ሚስጥር የነበረ በመሆኑ በወቅቱ ግድያውን ሊፈፅም የሞከረው አካል ወይንም ሀገር (ማንነቱን ሻምበል ጉታ የተባረሩት ዜጎች የየት ሀገር እንደነበሩ አልገለፁም) ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ላይ ጥላ እንዳያጠላ ስጋት ስለሚሆን ዜናው በተፈለገው ደረጃ ለዓለም ሕዝብ እንዳይደርስ የሚደረጉ ስውር ስራዎች እንደማይጠፋ ማጤን ሌላው ሥራ ሊሆን ይችላል።
በመጨረሻም ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሕዝብ ወጥተው ዛሬ ላይ ምንም ምስጢርነት የሌለውን ጉዳይ ለሕዝብ በመንገራቸው ሊመሰገኑ ይገባል።
(ምንጭ- ሸገር ራድዮ ፣ ቅንብር- ጉዳያችን ጡመራ ፣ ቀን ዓርብ ጥቅምት 15/2006 ዓም)



አዳዲስ መረጃዎች በኢትዮጵያውያን የሳዑዲ አረቢያ ውሎ ዙሪያ (ከነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ)

ጅዳና ጀዛን – በጅዳ እና በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞች በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ተበራክቷል። “ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል! ” እያሉ ነው! የሰሚ ያለህ!

ጅዳ – ከጅዳ ወደ ሃገር ቤት የሚተመለሱ ዜጎች ቁጥር ወደ 60 ሽህ መጠጋቱን መረጃ ደርሶኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ከአሰሪዎች ጋር የትሰሩ ማናችሁም ዜጎች ያለማወላወል በሰላም ወደ ሃገር ግቡ በሚል ባሳለፍነው ያሰራጨው ጥብቅ ማሳሰቢያን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት የሚዘጋጁት ዜጎች ቁጥር ከፍ እያለ መጥቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዥ “የሳውዲ ህግ ተለዋዋጭ ነው ፣ የምህረት አዋጁን ያራዝሙት ይሆናል!” በሚል ያልተጨበጠ ተስፋን የሰነቁ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መዘናጋት አግባብነት እንደሌላውና ” ህገ ወጥ ” በሚል የተፈረጁ ከሃገር ይውጡ የሚለው ትዕዛዝ ከሳውዲው ንጉስ ቀጥተኛ የተላለፈ የማይታጠፍ ትዕዛዝ መሆኑን መራጃ ስለሆነ ዜጎች መዘናጋትን አስወግደው ያለማወላዎል ቁርጣቸውን አውቀው ይህን መልካም እድል ተጠቅመው ወደ ሃገር ቢገቡ ይሻላል ” በሚል የሳውዲና የመንግስታችን ተወካዮች በአጽንኦት በመምከር ላይ ናቸው!
ደማም – ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በደማም የሚገኙ ኢትዮጵያንን ወደ ሃገር መግባት ለማመቻቸት የሄዱት ልዑካን ከፊል ስራቸውን ሰርተው ቢመለሱም እጃችሁን ለመንግስ ት ስጡ የተባሉ ዜጎች አሻራ ለመስጠት እየተጉልሉ በመሆኑ ተሰምቷል። “ከስራ ወጥተን ከምንኖርበት ቤት ተፈናቅለን እየተቸገርን ነው !” ብለዋል።
ጀዛን – መኖሪያ ፍቃድ እያለን በመኖሪያ ቤታችን፣ በስራና በየመንገዱ በሚደረግ ፍተሻ ወደ ለእስር የተዳረጉ ዜጎች ጅዳ ለሚገኙት የጅዳ ቆንስል ም/ ኃላፊ ለአቶ ሸሪፍ በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያሰሙም ሃላፊው ከማረጋገት ከመርዳት ይልቅ እያበሳጩን ነው ብለውኛል። ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ አልሰሙ ይሆን?
ሪያድ – በመንፉሃና በአካባቢው የሚኖሩ ቪዛን በደላላ ገዝተው የመጡ ዜጎች ትናነት ከእኩለ ቀን እስከ ምሽት የሚከተሉት ጥያቄዎች ተሰብስበው በሪያድ ለኢትዮጵያ ኢንባሲ አቅርበዋል ። የማመልከቻና ጥያቄዎቻቸውን በጽሁፍ ልከውልኛል …
” ይድረስ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ዋናው ጽህፈት ቤት ሪያድ ።በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን በመቀጠል መልስ የሚሹ ጥይቄዎችን ለተከበረው ኤምባሲ በማቅረብ ኤምባሲያችንም ከሚመለከታቸው የሣዑዲ አራቢያ መንግስት ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ይፈታልን ዘንድ ቀጣይ ጥያቄዎችን እናቀርባለን ።እነሱም
1: ነፃ የሙያ ቅየራ /free professional change/ ይፈቅድልን ።
2 : ነቅል ከግለሰብ ወደ ሸሪካ እንድናደርግ ይፈቀድልን ።
3 : በሆነ ባልሆነ ምክንያት የሚደረግ የእቃማ በላግ ይቁምልን ።
4 : ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5 : ፖሊስ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ እያንገላታን ያለ ፍርድ ከፍለህ ውጣ እያሉ የሚፈፅሙት ምዝበራ ይቁምልን ።
6 : ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚፈፅሙት የአየር በአየር ንግድ ከአንዳንድ ሳኡዲዎች ጋር በመሆን ቀርቶ ስራ እና ሠራተኛው በቀጥታ እንዲገናኙ ይደረግልን ።
7 : ለዕድሳት የሚሰጡ ኢቃማዎች በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን።
8 : የሳኡዲ ወጣቶች በራሳችን እና በሴት እህቶቻችን ላይ የሚፈፅሙት እንደ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር አጠቃላይ ወከባ እና በደል ይቁምልን ።
9 : ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ የተከበረው ኤምባሲያችን ያወጠነውን የዕቃማ ሙሉ ወጪ ከነሞራል ካሳው ጠይቆልን በሰላማዊ መንገድ ወደ ሃገራችን የምንገባበትን ሁኔታ ይጠይቅልን።
በማለት ለተከበረው ኤምባሲ የምናቀርበው እኛ ሪያድ የምንኖር. ቁጥራችን በቀላሉ 1000 የሚጠጋ በመንፉሃ እና በዙሪያ ያለን ኢትዮጵያዊያን ነን።እቃማ ይዘን ስራ ተከልክለን ያለን የተበደልን እና ነገን ያላወቅን የኢትዮጵያ ዜጎች ነን አፋጣኝ መፍትሔ ይፈለግ ” የሚል ማመልከቻ ከ1000 በላይ ፊርማ ያሰባሰቡ ወገኖች በትናንትናው እለት የሪያድ ኢንባሲንና ከሃገር ቤት የመጡትን ከአምስት በላይ ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን መፍትሔ ፈልግው አቤት ቢሉም መላ ማግኘቱ ቀርቶ ” ጥያቄያችሁ አግባብነት የለውም ፣ ይህንን የማይሆን ጥያቄ እንዳትንገላቱ ወደ ሃገር በሰላም ግቡ! ” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ገልጸውልኛል!
ወደ ሃገር የሚገቡ ዜጎች ስጋት: የሳውዲን ሁከት ተከትሎ “ወደ ሃገራችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ! ” ያለን መንግስት በአስከፊው ስደት ከምንበላው ቆጥበን የጠራቀምነውን ንብረት ይዘው ሰገቡ መመሪያ እየተባለ የሚቀረጡበትና የንብረት መውረስ በማዋከቡ ዜና ሃገር ውስጥ በሚወጡ መገናኛ ብዙሃን እየተነገረ ነው ። ይህ መሰል አሰራር ጉዳይ ነዋሪውን በጣሙን አሳስቦታል።መንግስት ከቀረጥ ነጻ ለተቸገሩት ይፈቅዳል ተብሎ ሲጠበቅ ይህ አሳዛኝ ዜና በእርግጥም አሳዛኝ እስከፊ ነው።
ተቃዋሚ ተብለው የተፈረጁት ስጋት: በተለያየ አጋጣሚዎች መንግስት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች በመቃዎም ሃሳብ የሰጠ ፣ በድምጻችን ይሰማ ደጋፊነት የተጠረጠረ እና በሳውዲ የመንግስት ተወካዮች የአስተዳደር በደል የሰላ ሂስ በማቅረባቸው በአይነ ቁራኛ እንታያለን ያሉ ዜጎች ወደ ሃገር ስንገባ እንዳንዋከብ እንሰጋለን በሚል ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ይህን ስጋት ይዥ የጠየቅኳቸው አንድ የጅዳ ቆንስል ከፍተኛ ሃላፊ ” ስጋቱ አይኖር ማለት ባይቻልም ይህን መሰል ስራ እስካሁን በገቡትበላይ አልተሰራም ፣ ከዚህ በኋላም ማሳደድ ማዋከብ ማሰር ብሎ ነገር አይኖም። ያመ ሆኖ በአልም አቀፉ ኢንተር ፖል ተፈላጊ የሆኑ ካሉ ይጠየቃሉ! ” ብለውኛል!
መረጃው በሹክሹክታ ቢደርሰኝም መረጃው እውነትነት አለው ፣ እናም በጅዳና በሪያድ የሚገኙ የመንግስታችን ተወካዮች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት በነዋሪው የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ይመልሱ ዘንድ እመክራለሁ!
ጀሮ ያለው ይስማ!

የሀረር እስላማዊትነት እንዴት ያለ ነው? (ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተሰጠ ምላሽ)

ላሊበላን አላየሁትም፡፡ ላየው ግን እፈልጋለሁ፡፡ ፍጹም በሆነ የቀረጻ ጥበብ ከድንጋይ ተፈልፍለው የወጡትን አስራ አንዱንም አብያተ ክርስቲያናት ለመጎብኘት እጓጓለሁ፡፡ ዕድሉን ካገኘሁ እዚያ ያየሁትንና የተሰማኝን ስሜት ለመጻፍ እመኛለሁ፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የግዴታ ክርስቲያን መሆን አይጠበቅብኝም፡፡ ሰው መሆኔ ብቻ በቂ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ የታሪክና የኢትኖግራፊ ጸሐፊ በመሆኔ ደግሞ ስለ ላሊበላ የማውቀውን የማሳወቅ ግዴታ አለብኝ፡፡
ላሊበላ ክርስቲያናዊ መሬት ነው፡፡ ጠሊቅ የሆነ ክርስቲያናዊ ባህል፣ ታሪክና ትውፊት ይታይበታል፡፡ በዚህ ድንቅ የስልጣኔ ምድር ያሉትን ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ያሳነጹት የኢትዮጵያ ክርስቲያን ነገሥታት ናቸው፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን ላሊበላ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ሀብት ሆኗል፡፡ ሁሉም እንደ ራሱ ሀብት ነው የሚያየው፡፡
ሀረር እስላማዊት ከተማ ናት፡፡ ከጥንቱ ዘመን ለዐይነት የተረፈች የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የስልጣኔ መዘክር ናት፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ባህል፣ ታሪክና ትውፊት የምትዘክር ህያው ሙዚየም ናት፡፡ ፈጣሪ እድሉን ሰጥቶኝ በዚህች ከተማ ለስድስት ዓመታት ያህል ኖሬባታለሁ፡፡ ታሪኳ እና ባህሏ በጣም ስለማረከኝ የምችለውን ያህል ከመረመርኳት በኋላ “ሀረር ጌይ፡ የአስገራሚዋ ከተማ የኢትኖግራፊ ወጎች” የተሰኘ መጽሐፍ ጽፌአለሁ፡፡
*****
“ሀረር እስላማዊት ከተማ ናት” የሚለውን አባባል ለመጀመሪያ ጊዜ በጽሑፍ ያሰፈረው ማን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ከሀያኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ጀምሮ በጽሑፍም ሆነ በንግግር የሚዘወተር ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ ስለከተማዋ የጻፉት ኤንሪኮ ቼሩሊ፣ ኢዋልድ ዋግነር፣ ኡልሪች ብራውኬምፐር፣ ካሚላ ጊብ፣ ኤልሳቤት ሄክትና ሌሎች በርካታ አውሮጳዊያን አባባሉን ይደጋግሙታል፡፡ የጽሑፋቸው ርዕስ አድርገው የተጠቀሙበትም በጣም ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ፈረንጆች “Islamic city in Ethiopia, The Muslim City in Ethiopia, The City of Saints, the Fourth Holy City of Islam ከመሳሰሉት አንዱን መጠቀማቸው የተለመደ ነገር ነው፡፡ ከሀገራችን ጸሐፍትም ከአንጋፋው ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሄር ጀምሮ ሌሎችም ጸሐፍት “ሀረር እስላማዊት ከተማ” ወይንም “ሀረር የቅዱሳን ከተማ” እያሉ መጻፋቸው በስፋት ይታወቃል፡፡ እኔም በሀረር ጌይ መጽሐፌ አባባሉን ተጠቅሜበታለሁ፡፡
ግን…ግን… “ሀረር እስላማዊት ከተማ ናት” ሲባል ምን ማለት ነው? በሸሪዓ ህግ መተዳደር አለባት ማለት ነው? ክርስቲያኖች ከከተማዋ መውጣት አለባቸው ማለት ነው? ከኢትዮጵያ ተገንጥላ በራሷ አሚሮች መተዳደር አለባት ማለት ነው? በጭራሽ! እንዲህ ብሎ የጻፈ ደራሲ የለም፡፡ እንደዚህ የሚል ጸሐፊ ያለም አይመስለኝም፡፡ “ሀረር እስላማዊት ናት” ሲባል ሁለት ነገርን ነው የሚወክለው፡፡ አንደኛ ሀረር በጥንት ዘመኗ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአስተዳደር፣ የትምህርትና የሀይማኖት ማዕከል ነበረች ማለት ነው፡፡ ሁለተኛ በዛሬው ዘመን እስላማዊ የስልጣኔ ታሪክ፣ ባህልና ትውፊት ይታይባታል ማለት ነው፡፡ በከተማነቷ፣ በቅርስነቷና በብሄራዊ ሀብትነቷ ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ናት፡፡
*****
በትናንትናው ዕለት (ህዳር 28/2006) በወጣው “ፋክት” መጽሔት ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ አቅርቧል፡፡ የመጣጥፉ አርዕስተ ነገር የአካባቢውን ፖለቲካ መተቸት ይመስላል፡፡ እንደ ማጠንከሪያ የተጠቀመባቸው ማስረጃዎች ግን ከጭብጡ ጋር የሚሄዱ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ በገጽ 32 ላይ “አፈንዲ ሙተቂ የተባሉ ጸሐፊ “ሀረር ጌይ” በተሰኘ መጽሐፋቸው “ሀረር እስላማዊት ከተማ ናት” ብለዋል” ይልና እንዲህ ዓይነት አባባል ያለበት መጽሐፍ መዘጋጀቱን በመጥፎነት ያነሳዋል፡፡ ይህንን አባባል የያዘ መጽሐፍ በመንግሥታዊው የሀረሪ ህዝብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መታተሙንም በህገ-ወጥነት ሊፈርጅ ይሞክራል፡፡
ተመስገን የኔን መጽሐፍ አለቦታው ማንሳቱ አስገርሞኛል፡፡ በርሱ ቤት ካድሬ ሆኜ የፕሮፓጋንዳ ስራ የምሰራ መስሎት ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁንና መጽሐፉ ለሶስት ዓመታት በተደረገ የኢትኖግራፊ ጥናት የተዘጋጀ እንጂ በጨበጣ የተጻፈ የካድሬ ድርሳን አይደለም፡፡ እኔ ደራሲው በህይወቴ የምኮራበት ብቸኛው ስራዬ እርሱ ነው፡፡ ሌሎች ድርሰቶች ቢኖሩኝም የርሱን ያህል አልሳሳላቸውም፡፡
“ሀረር ጌይ”ን የጻፍኩት በራሴ መንገድ ተመርቼ ነው፡፡ ማንም ሰው አልኮረኮረኝም፡፡ በመጽሐፉ የተጻፈው ሁሉ የራሴን እምነት ነው የሚያንጸባርቀው፡፡ በመጽሐፉ የምመታው ሀይማኖታዊም ሆነ ፖለቲካዊ ግብ የለም፡፡ ዓላማዬ ታሪክን፣ ባህልንና የህዝቦቻችንን ውብ የቋንቋና የኑሮ መስተጋብር ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ ላሊበላንና አክሱምንም ብጎበኝ ኖሮ ተመሳሳይ መንገድ ነበር የምከተለው፡፡
መጽሐፉን የጻፍኩት ብቻዬን ሆኜ ነው፡፡ አንዳንድ ምሁራን በምክር ቢያግዙኝም ሁሉንም የተወጣሁት በራሴ ነው፡፡ በመጽሐፉ ያለውን መረጃ የሰበሰብኩት፣ የመረመርኩት፣ ያመሳከርኩት፣ በጽሑፍ ያሰፈርኩት፣ ለህትመት እንዲሆን አድርጌ ያዘጋጀሁት እኔው ነኝ፡፡ የሀረሪ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ህትመቱን ስፖንሰር ያደረገው ሌሎች አሳታሚዎች ለህትመቱ የሚያስፈልገውን ወጪ ለማውጣት ስላልደፈሩ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ በኔና በቢሮው መካከል የተለየ ግንኙነት የለም (ቢኖር እንኳ የሙያ ጉዳይ እስከሆነ ድረስ ወንጀል አይደለም)፡፡ በነገራችን ላይ ቢሮው መጽሐፉን እኔ እንዳቀረብኩለት ነው ያሳተመው፡፡ በመጽሐፉ አስኳል ላይ የተቀነሰም ሆነ የተጨመረ ነገር የለም፡፡ አንድ የተደረገ ነገር ቢኖር ቢሮው “መልዕክታችን” የሚል ሁለት ገጽ ማስታወሻ ከመጽሐፉ ጋር እንዲታተምለት በጠየቀው መሰረት በመግቢያው ላይ መካተቱ ብቻ ነው (እርሱንም የጻፍኩት እኔ ነኝ)፡፡ ቢሮው ነጻነቴን ጠብቆ “ሀረር ጌይ”ን እኔ እንደጻፍኩት ለማሳተም በመስማማቱ አደንቀዋለሁ፤ አመሰግነዋለሁ፡፡ ይህም በሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ዘንድ የሌለ ባህል በመሆኑ በጣም ተገርሜበታለሁ፡፡
“ቢሮው እስላማዊት ከተማ የሚል አባባል ያለበት መጽሐፍ ለምን አሳተመ” የሚል ጥያቄ ከተነሳ ደግሞ መልሱን መመለስ ያለበት እርሱ ራሱ ይመስለኛል፡፡ ለመረጃ ያህል ግን ቢሮው እንዲህ ዓይነት ድርሰቶችን ሲያሳትም የመጀመሪያ ጊዜው አለመሆኑን ለመግለጽ እሻለሁ፡፡ ቢሮው “እስላማዊት ከተማ” የሚለውን አባባል የሚረዳው ሌሎች ጸሐፍት ከሚረዱበት በተለየ መንገድ አይመስለኝም፡፡
ተመስገን “ሀረር እስላማዊት ከተማ ናት” የሚለው አባባል አደናግሮት ይሆን? በዚህ ተደናግሮ መጽሐፉን አለቦታው እንዳላነሳው እገምታለሁ፡፡ ይህንን አባባል ከዚህ በፊት ካልሰማ (ካላነበበ) ግን ሌሎች መጽሐፍትን እንዲመረምር እጠይቀዋለሁ፡፡ በተረፈ ነገሮችን በጥልቀት ሳንረዳ ሰዎችን በተሳሳተ አቅጣጫ ለመፈረጅ ባንቸኩል ጥሩ ነው፡፡
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 29/2006

Saturday, 7 December 2013

አቃቤ ህግ በእነ አቶ ያረጋል አይሸሹም ላይ ቅጣቱ እንዲከብድ ጠየቀ

የፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ በከባድ ሙስና ወንጀል ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠውን የቀድሞው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሠ መስተዳደር አቶ ያረጋል አይሸሹምን ጨምሮ በሁሉም ተከሣሾች ላይ የሚወሠነው ቅጣት እንዲከብድ ጠየቀ፡፡ አቃቢ ህግ ጉዳዩን ሲከታተል ለቆየው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 15ኛው ወንጀል ችሎት በፅሁፍ ባቀረበው የቅጣት አስተያየት፤ በአንድ ክስ ጥፋተኛ የተባሉት አቶ ያረጋል እና በሶስት ክሶች ጥፋተኛ የተባሉትን የቀድሞው የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባኤ እና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ሂካ እንዲሁም በመጀመሪያው ክስ 3ኛ እና 4ኛ ተከሣሽ ሆነው ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠው፡፡ አቶ ጌድዮን ደመቀ እና አቶ አሠፋ ገበየሁ ላይ ቅጣቱ ይክበድልኝ ሲል አመልክቷል፡፡ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶቹም 1ኛ እና 2ኛ ተከሣሽ ከፍተኛ ስልጣን የነበራቸው በመሆኑ፣ 3ኛ እና 4ኛ ስልጣን ባይኖራቸውም በልዩ ወንጀል ተካፋይ በመሆናቸውና የቅጣት እርከኑም ከፍተኛ ስልጣን ባላቸው ስር የሚታይ በመሆኑ እንዲሁም ሁሉም ተከሣሾች በመንግስት ላይ ከባድ አላማ በመያዝ በጣም ከፍተኛ ጉዳት ያደረሡ በመሆናቸው የሚሉት ናቸው፡፡ በተመሣሣይ አቃቤ ህግ ከ2ኛ እስከ 3ኛ ባሉት ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት ሁሉም ተከሣሾች በከፍተኛ ስልጣን፣ በጣም ከፍተኛ ጉዳት እና ከባድ አላማ በሚሉ የወንጀል ደረጃ መግለጫዎች እንዲያዝለት በቅጣት አስተያየቱ አመልክቷል፡፡ ቅጣቱ በሁሉም ተከሣሾች ላይ እንዲከብድለት የጠየቀው አቃቤ ህግ አቶ ሃብታሙ ሂካ፣ አቶ ጌዲዮን ደመቀ፣ አቶ አሠፋ ገበየሁ በ3 ግዙፍ ክሶች ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ የእያንዳንዱ ክስ የቅጣት ውሣኔ ከተላለፈ በኋላ የእስራትና የገንዘብ መቀጮው ተደምሮ እንዲወሠን አመልክቷል፡፡ በአንድ ክስ ብቻ ጥፋተኛ የተባሉት አቶ ያረጋል አይሸሹም፣ የጋድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ አድገህ፣ የየኮለን ኮንስትራክሽን ስራ አስኪያጅ አቶ መክብብ ሞገስ ላይም ቅጣቱ ከብዶ እንዲወሠን አቃቤ ህግ ጠይቋል፡፡ ፍ/ቤቱም የተከሣሾችን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ለመቀበል መዝገቡን ለታህሣስ 15 ቀጥሯል፡፡

ወያኔ የካደው = ግንቦት ሰባት የተነፈሰው = አና ጎሜዝ ያልሸሸጉት አዲስ ነፋስ (“ድርድር”)

ከምኒልክ ሳልሳዊ
ይህን ሰሞን በሃገር ውስጥ እና በውጪው ሃገር ኢትዮጵያውያን ዘንድ የመወያያ ርእስ
andargachewየሆነው እና ይየወያኔ ካድሬዎችን ቀልብ የገፈፈው እና ከሰል ያለበሳቸው ወያኔ ለግንቦት ሰባት ያቀረበው የድርድር ጥያቄ ነው::በስፋት አሁንም እየተከራከሩበት ያለው ይህ ጉዳይ አገሩን በጡዘት አምሶት የሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት አንድ ተስፋ የሰጠ ሁኔታ እንደሚታይ እየተተነበየ ነው::
ወያኔ በእርግጥ በማይጥም የፖለቲካ እሰጥ አገባ የተጠመደ ቢሆንም የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ለላውን ከማዘናጋት ውጪ ምንም አይነት ፋይዳ እንዳሌለው እና ራሱን እየፈተሸ እንደሆነ ያጋለጠ ጉዳይ ነው:: የድርድር ጥያቄ አላቀረብኩም ያለው ወያኔ እንደለመደው ከኦነግ ከኦብነግ ከሻእቢያ ጋርም እየተደራደረ ጥያቄውን እራሱ እያቀረበው ሲክድ የቆየ ሲሆን በቅርቡ እንኳን በኬንያ ከኦብነግ በጀርመን ከሻእቢያ ጋይ ያደረጋቸውን ድርድሮች እየታከካቸው አልፏል::
ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው:: በእርግጥ በተለያዩ ጊዜያት ለወያኔ እና ለግንቦት ሰባት የቅርብ ርቀት የሆኑ ሰዎች ይህንን ጉዳይ በግል አንስተውት የሆነ ቢሆንም ባይሆንም ግን የአና ጎሜዝ የአዲስ አበባ ምላስ ተከትሎ ግንቦት ሰባት ለህዝብ ይፋ ያደረገው ጉዳይ አሁንም ሚዛኑ ወደ ግንቦት ሰባት እንዲሆን አድርጎታል::
እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ ባለስልታናት የቀን ተቀን የስብሰባ መቀመጫቸው ግንቦት ሰባት ነው:; በወታደሩ በደህንነቱ እና በታማኝ ካድሬው ዙሪያ ውይይቱ ምስጢሩ ግንቦት ሰባት ነው:: እነዚህ የሚስጥር ተወያዮች እንደሚጠቁሙት ሲሰበሰቡ በውይይት ወቅት ግንቦት ሰባትን አሸባሪ ብለው አይጠሩትም:; አሸባሪ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታቸው አደባባይ ላይ መሆኑን በይፋ የተረጋገጠ መረጃ ይጠቁማል::
በቅርቡ ከአባቱ ሻእቢያ ጋር ጀርመን ላይ የተወያየው ወያኔ ግንቦት ሰባት የራስ ምታት ስለሆነበት እንዲያደራድረው አሊያም እንዲገላግለው ተማጽኖ ቢሆንስ??? ወይኔ ሻእቢያ የሚፈልጋቸውን ተቃዋሚ ኤርትራውያንን እያፈነ እንደሚሰጥ የህን ሰሞን ሃተታዎች እየጠቆሙ ነው እንዲሁም በሱዳን በኩል እያሽከረከረም እንደሚያስረክብ::ነገሩ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት ነው ….
የአቶ ታምራት ላይኔም ወደ ፖለቲካው ለመቀላቀል ማቆብቆብ እኮ የዚሁ የድርድር አንዱ አካል ነው:; ብኣዴን ታምራት ላይኔን ይፈልገዋል:: አገሬ በፈለገችኝ ሰአት ለማገልገል ተዘጋጂቻለሁ የሚለው ታምራት ጠጋ በል እየተባል መሆኑስ የወያኔ አንድ የጭንቀት ምልክት አይደል?! … ወደ ሚዲያዎች አያሰገገ መምጣቱ ሌላ ምስጢር የለውም::
Ana-Gomezአና ጎሜዝ ከአዲስ አበባው ቆይታቸው ሁለት ንግግሮችን ከአንደበታቸው ሰምተናል:: አንዱ “ከባለስልጣናት ጋር ያደረኩት ውይይት በጎ እና ገንቢ ነው መልካም ምላሽ እንዳገኙም በእርካታ ተናግረዋል:; በመተማመን ስሜት ደሞ “አዲስ ንፋስ አለ” ሲሉ ተስፋቸውን አብርተዋል:: ይህንን የፖለቲካ ስሜታቸውን ያልተረዱ የደፈናው ጋዜጠኞች የወያኔን የሞተ እስትንፋስ ሊያበረቱ ቢሞክሩም የሚሳካ ካለመሆኑም ሌላ ወያኔም …ጌታ….ተላላኪ…;;እያለ ቢዘላብድም ታምኝነት ሊያገኝ አልቻለም:: አና ጎሜዝ ይህንን ሲናገሩ ከባለስልጣናት አንደበት የሰሙት እና የተላኩት መልእክት እንዳለ ይጠቁማል:: አና ጎሜዝ ወደ ግንቦት ሰባት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የለውጥ ጠያቂዎችም የብሄራዊ ድርድርን ጉዳይ አስረግጠው አዋይተዋል:;በእርግጥ ስለግንንቦት ሰባት ባያነሱም ይህ የእንደራደር ጥያቄ የመልስ ምቱን ወያኔ ለማወቅ ፈልጎ ያደረገው ሊሆን የሚችል የማጭበርበሪያ የፖለቲካ ስልት ቢሆንም የድርድሩ ጥያቄ ግን የአና ጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ እና የአዲስ ነፋስ ምልክታን ተከትሎ መነገሩ እውነታውን ያጎላዋል:; ይህ የሚያሳፍረው ወያኔን ቢሆንም ወያኔ ግን ምንተእፍረቱን አይኑን በጨው አጥቦ ቢክድም አሁንም ግንቦት ሰባትን እንዲያደራድሩት ከትን እንዲያደበጀርባ እየተለማመጠ እንደሚገኝ ለማስገንዘብ እወዳለሁ