Wednesday, 18 September 2013

የቤተመንግስት ደህንነት ሃላፊ ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


የነአዜብ ቡድን እየተመታ ነው!!
 
የቤተ-መንግስት የደህንነት ጥበቃ ዋና ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት የሕወሐት አባል አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ቀደም ሲል በክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የደሕንነት ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ከዚያም ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው መመደባቸውንና በተጨማሪ የአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሃላፊ በመሆን ከአቶ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። የአቶ መለስና ወ/ሮ አዜብ የቅርብ ሰው የሆኑት አቶ ጌታቸው ተፈሪ በነበራቸው ታማኝነት የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ ተደርገው በአቶ መለስ ተመርጠው እንደተሾሙ ያስታወሱት ምንጮች፣ በማያያዝም እስከ 1994ዓ.ም የቤተመንግስት የደህንነት ጥበቃ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዘርኡ መለስ በወቅቱ ከአቶ መለስ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ልይነት ምክንያት ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ “ኮከብ ሬስቶራንት” የአሁኑ “ሚልክ ሃውስ” መኖሪያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው በስለት ታርዶና በድናቸው ተበላሽቶ መገኘቱን አመልክተዋል። ይህን አሰቃቂ ግድያ ያከናወነው አሁን በእስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ አገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊና የአቶ መለስ ቀኝ እጅ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መሆኑን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
የነ አዜብ ቡድን እየተመታ ነው!
የነ አዜብ ቡድን እየተመታ ነው!
አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገው በደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮች፣ በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። አቶ ጌታቸው ተፈሪ — የወ/ስላሴ መታሰር ቅር ሳያሰኛቸው እንዳልቀረና በተጨማሪም የነአዜብ ቡድን ደጋፊ መሆናቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።
 
በሌላ በኩል የኢ.ኤም.ኤፍ ምንጮች ቀደም ብለው እንደገለጹት፤ ባለፈው አመት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ “ቤተ መንግስቱን አንጠብቅም” ብለው ንዝህላልነት ካሳዩት መሃል እኚሁ የቤተ መንግስት ጥበቃ ሃላፊ ጌታቸው ተፈሪ አንዱ ነበሩ። በተለይም አዲሱ ጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከገቡ በኋላ የቤተ መንግስቱ ጥበቃ እንዲላላ ከማድረግ አልፈው፤ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር አክብሮት የማይሰጡ ሰው እንደነበሩ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment