ይህ እየሆነ ባለበት ሁኔታ የኑሮ ፈተና ፣ የፍትህ ማጣት ፣ ጭቆና እና እንግልት… የበዛበት ምስኪን ኢትዮጵያዊ ብሶቱ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጦ ዛሬ ለመፈንዳት ቋፍ ላይ ይገኛል፡፡ እንግዲህ ይህ በግልፅ የሚያመለክተዉ በስልጣን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት በታሪካችን እንዳየናቸዉ እና በነኮሎኔል ጋዳፊ እንደደረሰዉ ሁሉ የከፋ አወዳደቅ ለመዉደቅ ቀናቸዉን እየቆጠሩ እንደሆነ ነዉ፡፡
በተለይም የህወሓት ጠንሳሽና የኢህአዴግ መስራቹ እንዲሁም ሀገሪቱን ለ21 አመታት በመዳፋ አስገብቶ የገዛዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በህመም ከስልጣኑ ከተገለለበት ቆይቶም ከሞተበት ግዜ ጀምሮ በብሶት ተወጥሮ የኖረዉ ጭቁን ህዝብ ከምግዜዉም በላይ ለለዉጥ የበለጠ በማቆብቆብ ላይ ነዉ፡፡ እዚህ ላይ በቅርቡ በመዲናችን አዲስ አበባ እንዲሁም በጎንደር እና ደሴ ከተሞች የተካሄዱት ህዝባዊ ተቃዉሞዎች የሚያስብ ህሊና ላለዉ ሰዉ ብዙ ያስተላለፉት መልዕክት አለ፡፡

ምንም እንኳን የአንባገነኖች ከስልጣን አንለቅም ግብ ግብ ዉጤቱ እንዳየነዉ በጣም የከፋ ቢሆንም የወቅቱ የሀገራችን መሪዎችና ባለስልጣናቱ ከታሪክ መማር አቅቷቸዉ የህዝብ የሆነን ስልጣን እደግመዋለሁ የህዝብ የሆነን ስልጣን ሙጭጭ በማለት ወደ ዉድቀት አፋፍ በፍጥነት እየተንደረደሩ ይገኛል፡፡
እንደሚታወቀዉ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከስልጣን ዉረዱ አንወርድም ግብግቡን በ1997 ከተካሄደዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ ማግስት ጀምሮ በይፋ የጀመሩት ሲሆን ፤ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የተቀዋሚ ፓርቲዎችን አመራሮች እና አባላትን በማሳደድ እንዲሁም የነፃዉን ፕሬስ ዉጤቶች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ በማጥፋትና ጋዜጠኞቻቸዉንም በሐሰት ዉንጀላ በግፍ በማሰር አፈናዉን ከምን ግዜዉም በላይ አጠናክረዉ ቀጥለዋል፡፡

በተያያዘም አገዛዙ ለርካሽ ትርፍ ሲል የፈለሰፈዉ የጎሳ ፖለቲካ ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር መለሽ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በተነሳዉ የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት በራሱ በኢህአዴግ ላይ የማይጠግኑት ትልቅ ስንጥቅ እየፈጠረ ሲሆን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ስልጣናቸዉ መከታ በሚቆጥሩት ጦር ዉስጥም ትልቅ መከፋፈል እያመጣ ስለመሆኑ መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ አለማቀፋዊ ጫናዉ በዛዉ ልክ እየበረታ ሄዷል፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ ከህዝቡ ቁጣ ጋር ተደማምሮ አገዛዙን ከምን ግዜዉም በላይ ከዉድቀት አፋፍ ላይ አድርሶታል ማለት ይቻላል፡፡
ሆኖም ግን በጣም የሚያሳዝነዉ ለአንዳንድ ሰዎች ቁልቁለት ቁልቁለት መሆኑ የሚታወቃቸዉ ወርደዉ ወርደዉ ወድቀዉ ሲከሰከሱ ነዉ” ሲሉ “አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ” አገዛዙ እንዲህ ከዉድቀት አፋፍ ላይ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባለስልጣናቱ ከአጠገባቸዉ በሞት የተለዩትን የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚንስትር ስም እንደ ዳዊት ቃል እየደጋገሙ እና የማይጨበጥ ተስፋ እየሰበኩ ጭቆናቸዉን ለማስቀጠል ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡

በሰከነ አዕምሮ በማሰብ የህዝቡን የዲሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመመለስና ሌላም የህዝቡን ቁጣ ማብረጃ እርምጃዎችን በመዉሰድ ከፊታቸዉ እየመጣ ካለዉ አስፈሪ ሕዝባዊ ማዕበል እንደማምለጥ ፤ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ከሚመጣዉ መዓት እንደማዳን እነሱ ግን በጭፍን አዕምሮአቸዉ ስልጣናቸዉን ሙጭጭ እንዳሉ የማያዋጣ ግብ ግብ ከህዝብ ጋር ይዘዋል፡፡ የዚህ ግብ ግብ መጨረሻም እየየቀረበ ይገኛል፡፡
ምንም እንኳን ያለፉትን 22 አመታት አንዴ በጉልበት አንዴ በማምታታት ማለፍ ቢቻልም ከዚህ በኋላ ግን ያን መድገም የሚቻል አይመስለኝም፡፡
በፍትህ ፣ ዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሁም በድህነት እና ለቁጥር በሚታክቱ ማህበራዊ ችግሮች የሚያቃትትን ህዝብ አይዞህ ኮንዶሚንየም ልገነባልህ ነዉ ፣ ባቡር እየመጣልህ ነዉ ፣ 11 ፐርሰንት እድገት፣40/60 ኮንዶሚንየም ተደራጅ … ቅብርጥሴ ማለት ብዙ እርቀት አያስጉዝም ፤ ከሚመጣዉ መዓበልም አያድንም ባይ ነኝ ፡፡
ከሰብኣዊ Zekarias Asaye
ከሰብኣዊ Zekarias Asaye
No comments:
Post a Comment