Thursday, 11 July 2013

የህወሀት ስትራቴጂ በአማራውን ህዝብ ቁጥር ቅነሳ



የተከበሩ የምክር ቤት የተቃዋሚ ተወካይ አቶ ግርማ ሠይፉ ምክር ቤቱ በቀኝ ክንፍ ሲያጠቃ ዋለ ሲሉ ያስነበቡን ፁሁፍ እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር እንዳክልበት አስገደደኝ። ለፌዴሬሽን ጉዳዬች ሚኒስቴር የቀረበ ጥያቄ በዋዛ የሚታይ አልነበረም ጥያቄዉም በብዙ የምክር ቤቱ አባል ለመጥቀስ ፈራ ተባ ሲሉ አንደኛዉ የምክር ቤቱ አባል ግን ደፍረዉ የአማራ ክልል ህዝብ በተለየ ሁኔታ በኤድስ ሞቷል መባሉ ትክክል ስላልሆነ ይቅርታ መጠየቅ ሲከፉም በሀላፊነት መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑ ሞግተዋል ብለዉ አቶ ግርማ ሠይፉ በፁሁፋቸዉ አስነቡበዉናል።
ይህ በእዉነቱ የምክር ቤቱ ተወካይ በአጋጣሚ አምልጧቸዉ ወይም ደግሞ እዉነታዉን ስለሚያውቁት እንጂ ይህ ለአማራዉ ህዝብ ህወሀት ኢትዬዽያን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ በፕሮግራም የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ በረጅም እቅዳቸዉ ላይ የተቀመጠ ነዉ። ይህንን ልል የቻልኩት እንደ ኢትዬዽያ ዘመን አቆጣጠር በ2002 ዓ፤ም በአለም ጤና ድርጅት እገዛነት በጤና ተቋማት ላይ የሚደረገውን ምዝገባ ወይም  ግምገማ  በአማራው ክልል ላይ ለመስራት እድሉን አግኝቼ በምሰራበት ወቅት ያየሁትን እይታዬ ለማጋራት ያህል ነው። ይህም ምዝገባ ወይም  ግምገማ  የሚያካትተው በኢትዬዽያ ዉስጥ ያሉት የጤና  ተቋማት ምን ያህል ባለሙያ፥ ታካሚ፥ የወሊድ አገልግሎት፥ የቲቢ እና ኤድስ አገልግሎት፥ የላብራቶሪ አገልግሎት ፥ የህፃናት ህክምና እና ክትትል እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎችን እና መድሀኒቶች ከመቼ ጀምሮ እጥረት እንደነበረ እና በተለይ የኤድስ በሽታ እድሜ ማራዘሚያው መድሀኒት እና የቅድመ ምርመራ መሣሪያ ቆጠራ ወይም ምዝገባ ይደረጋል። ነገር ግን የህወሀት መንግስት የተሰበሰበውን መረጃ እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ በመቀየር ለፖለቲካ ፍጆታ እና ገንዘብ ማግኛ ዘዴ ሆኖታል። እውነታው ግን ህብረተሰብ በተጏዳኝ በሽታዎች፥ በህክምና መሳሪያዎችና መድሀኒቶች እጥረት እንደሚሰቃይ እና እንደሚማት የአደባባይ ሚስጥር ነው።
የወያኔ መንግስት የአማራውን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ በኤድስና በተጏዳኝ በሽታዎች ዙሪያ ፩ኛ የህብረተሰቡ ጤና አጠባበቅ በተመለከተ ምንም አይነት ግንዛቤ እንዳይኖረዉ በማድረግ ፪ኛ  በኤድስ በሽታ ህብረተሰቡ መያዝ አለመያዙ የመመርመሪያ መሳሪያ በክልሉ ሆነ ተብሎ እጥረት እንዲኖርና ምንም አይነት የቅድመ ምርመራ ግንዛቤ እንዳይኖራቸዉ መደረጉ ፫ኛ በኤድስ በሽታ የተጠቁ ሰዎች የእድሜ ማራዘሚያ በአግባቡ እንደማይሰጣቸዉና የመድሀኒቱም ተጠቃሚዎች እንደማይቆጧጠሯቸዉ ከጤና ጣቢያም ሆነ ከሆስፒታል ምንም አይነት ክትትል እንደማይደረግላቸዉ እና ከዚህም በተጨማሪ ይህ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒትና ሌሎችም ተጏዳኝ በሽታ መድሀኒቶች ከአማራዉ ህዝብ ቁጥር አንጻር ተመጣጣኝ ስርጭት እንደሌለው ፬ኛ ደግሞ የመድሀኒቶቹ የመገልገያው ጊዜ (expired date) በጣም የቀረበ በተለይ ለነዚህ ለሁለቱ ክልሎች እንደሚላክ በጤና ጥበቃ ስር የሚገኘዉ የመድሀኒት ፈንድ ኤጀንሲ መስሪያ ቤት በምሰራበት ወቅት ይህ ከላይ የዘረዘርኳቸውን ለማስተዋል ችያለው ።
ይህንን እና በጤና ጥበቃ ስር ኢ-ፍህታዊ የሆነ የመድሀኒት ስርጭት እና ክፍፍል ዙሪያ ላይ ለተመረጡ ክልልሎች በተለይም ለአማራው እና ለኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ሆነ ተብሎ የህወሀት መንግስት እንዴት እንደሚጠቀምበት በቅርቡ በመረጃ በማስደገፍ በሰፊው እመለስበታለው።

No comments:

Post a Comment