Monday, 1 July 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓባይ የመጠቀም መብቱንማ አሳልፎ አይሰጥም!

ኢሕአፓ
EPRP Official Logo.gifየኢትዮጵያ ሕዝብ በዓባይ የመጠቀም መብቱንማ አሳልፎ አይሰጥም!  በአንዲት አገር ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ለሀገሪቱ ሕልውናና ጥቅም የማይቆም፤ አገራዊ ወይንም ብሔራዊ ስሜት የሌለውና የሕዝብን ፍላጎትና አስተያየት የማይቀበል አምባገነን አገዛዝ ሥልጣን በያዘ ጊዜ ይህን የተረዱ የዚያች አገር ታሪካዊ ጠላቶች ደግሞ በሀገሪቱ ህልውና ላይ አደጋ ለማድረስ የወራሪነት ክንዳቸውን እንደሚያነሱ ታሪክ ደጋግሞ  አሳይቶናል። ለዚህም በዓለም ዙሪያ የተከሰቱ ዕውነታዎችን በማገናዘቢያነት ማንሳት  ይቻላል። እኛ ማንሳት የምንፈልገው ግን በራሳችን አገር ቀደም ባሉት ዘመናት ውስጥ የተከሰቱትን ሃቆች ነው።

No comments:

Post a Comment