ረገብ ብሎ የሰነበተው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ተካሄደ
መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የጁመአን ስግደት ተከትሎ ዘወትር አርብ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሰሞኑን ረገብ ብሎ ቢቆይም ፣ በዛሬው እለት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ ቤኒን መስጊድ ተካሂዷል።
ሙስሊሞቹ እጅግ ለእጅ በመያያዝ አንድ መሆናቸውን አሳይተዋል። የአለፉትን 1 አመት ከ3 ወራት በከፍተኛ ጫና እና እንግልት ያሳለፉት ሙስሊሞች ” የታሰሩ መሪዎች ሳይፈቱና ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ” ትግላችንን አናቆምም እያሉ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አቃቢ ህግ በድምጻችን ይሰማ አመራሮች ላይ የጀመረውን የሰዎች የምስክር ማሰማት ሂደት ቀጥሎአል። ሂውማን ራይትስ ወች የፍርድ ሄደቱ ነጻ አይደለም በሚል መተቸቱ ይታወቃል።
አብዛኞቹ መስካሪዎች አጥንተውት የመጡትን ነገር በደንብ ለመናገር ሲቸገሩ መታየታቸውን የውስጥ ምንጮችን በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment