Tuesday, 2 April 2013

አቶ ናትናኤል መኮንን የረሀብ አድማ ጀመሩ


አቶ ናትናኤል መኮንን የረሀብ አድማ ጀመሩ

መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአቶ አንዱአለም አራጌ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል ተከሰው 18 አመት እስራት የተፈረደባቸው አቶ ናትናኤል መኮንን የረሀብ አድማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አቶ ናትናኤል አድማውን የጀመሩት  ቤተሰቦቻቸውን ለአንድ ወር ያክል እንዳይጠቁ በእስር ቤቱ ሀላፊዎች ማእቀብ ከተጣለባቸው በሁዋላ ነው። በአቶ ናትናኤል ላይ የተጣለው ማእቀብ ፣ ከእስር ቤቱ ሀላፊዎች ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ነው።
ባለቤታቸውን ልጆቻቸውን በመያዝ ባለፈው ቅዳሜ ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ቢያቀኑም ሳይጠይቋቸው መመለሳቸውን ለኢሳት ገልጸዋል
አቶ ናትናኤል በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ በእስር ቤት ሀላፊዎች የተለያዩ በደሎች ሲደርሱባቸው  እንደነበር ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment