Friday, 10 May 2013

ያልተመዘገበ ቦንድ በኖርዌይም ይሁን በአውሮፓ ህብረት መሽጥ በህግ የተከለከለ ነው::


942239_10151621553164743_376386664_nበኖርዌይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤት አባላት የወያኔ የአባይ ቦንድ ሽያጭ ህገወጥ እንደሆነ ለኖርዌይ ባለስልጣናት ማብራሪያ ሰጡ::
በኖርዋይ የሽግግር ምክርቤቱ ሰብሳቢ በአቶ ግሩም ዘለቀ የተመራው እና አባላቶቹን ያቀፈ ቡድን ለኖርዌይ የገንዘብ ሚኒስቴር እና ለገንዘብ ቁጥጥር ባለስልጣን ከፍተኛ ሃላፊዎች እና ባለስልጣናት ዲፕሎማቶች ከኖርዋይ የንግድ ህግ አኳያ የቦንድ አሻሻጥን በተመለከተ እያደረጉ ያለውን ህገወጥ ተግባር በዝርዝር አስረድተዋል::
የኖርዌይ መንግስት ባለስልጣናት እንዳሉት ያልተመዘገበ ቦንድ በኖርዌይም ይሁን በአውሮፓ ህብረት መሽጥ በህግ የተከለከለ ነው::ማንኛውም ለህዝቡ የቦንድ ሽያጭ ከማቅረቡ በፊት በኖርዌይ ህግ መሰረት ማስመዝገብ አለበት::
እንዲሁም በሌላ ወገን በስዊዲን የወያኔ አንጋች የሆኑት ወይዘሮ መብራት ዲፕሎማት ሆነው ወደ ኖርዌይ በመምጣት በኦስሎ ውስጥ ከሚገኘው የኢሚግሬሽን ዳይርክቶሬት ቦንድ ሊሸጡበት የሚችሉበትን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን
በተመለከተ በኖርዌይ ህግም ይሁን በአውሮፓ ህብረት ህግ ማንኛውም ዲፕሎማት በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ እንደማይችል ህጉ አስቀምጧል::በዚህ ጉዳይ ላይ የሚደረግ ማንኛውም የቦንድ ንግድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል የኖርዌይ የገንዘብ ሚኒስቴር ባለስልጣናት::
በኖርዋይ የሚገኙት የሽግግር ምክርቤቱ አባላት በጠበቃቸው አማካኝነት ይህንን ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱት ተናግረዋል::ይህነኑ የወያኔን ህገወጥነት በኖርዌይ እና በመላው አውሮፓ ለማጋለጥ እና ህገወጥነቱን ለማሳወቅ የሚችል ግብረሃይል ተመስርቷል::

No comments:

Post a Comment