Monday, 16 December 2013

ኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የተከለለውን መሬት ህጋዊ ማድረጓ ተሰማ::

 የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ካርቲ “ከኢትዮጵያ ጋር ያለብንን የድንበር ልዩነት ለመፍታት ተስናምተናል” አሉ፡፡ ማክሰኞ ታህሳስ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ወደ ካርቱም የተጓዙት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከአልበሽር ጋር እንደተወያዩ ታውቋል፡፡ የሱዳኑ ሚኒስትር እንዳረጋገጡት ሁለቱ ሀገራት የሚወዛገቡበት የፋሻጋ አከባቢ ከንግድህ ያለመግባባት ምንጭ አይሆንም ብለዋል፡፡ የሱዳን ባለስልጣናትን እያጓጓ ያለው የሁለቱ ሀገራት መሪውች ስምምነት በኢትዮጵያውያን በኩል ከፍተኛ ጥርጣሬ አጭሯል፡፡
       ከድንበር በተጨማሪ በዚህ የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ የተካተቱት የደህንነት፣ የኢኮኖሚ፣ የግብርና፣ ትምህርትና ባህል ጉዳዮች ኢትዮጵያ ያጣችውን ድንበር ለመሸፈን የተደረገ ማጀቢያ እንደሆነ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ናቸው፡፡ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው አንድ አንጋፋ ፖለቲከኛ ኢህአዴግ የሀገርን የድንበር ሉዓላዊነትን ያስከብራል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡
በሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጮህ ወረጃ ነዋሪ የሆኑ ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው “ከዚህ በፊት ጥጃ ያሰርንባቸው መሬቶች ዛሬ ወደ ሱዳን ተከልለዋል፤ የራሳችንን መሬት ተከራይተን ነው የምናርሰው፤ ስለዚህ የፊርማ ስነ ስርዓቱ ይህንኑ ለሱዳን የተሰጠ መሬት ህጋዊ ለማድረግ ነው” ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment