በህዝቡና በፌደራል ፖሊስ መካከል ግጭቱ የተነሳው ከትናንት በስቲያ ዳንኤል አስቻለ የተባለ በቡራዩ ከተማ ማረን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ይኖር የነበረ ወጣት በፌደራል ፖሊሶች መገደሉን ተከትሎ ነው ። በብዙ ጓደኞቹ ዘንድ በጸባዩ ተወዳጅ እንደነበር የሚነገርለት ወጣት ዳንኤል አኳ አዲስ በሚባል የውሃ ማምረቻ ድርጅት ውስጥ በሾፌርነት ተቀጥሮ ይሰራ ነበር።
ወጣት ዳንኤል በአንድ መዝናኛ ክበብ ውስጥ አንድ ሲቪል የለበሰን ሰው ገፋ አድርጎ ሲያልፍ፣ ሲቪል የለበሰው ሰው ለምን ተገፋሁ በሚል ስሜት ከሟቹ ጋር ጭቅጭቅ ውስጥ መግባቱን፣ ጭቅጭቁን ተከትሎም ገዳዩ በሟች ላይ ቦክስ ሰንዝሮ ከመታው በሁዋላ ጓደኞቹ እንዴት ተደፈርን በሚል ስሜት ሟችን በቦክስ ፣ በጫማ ጥፊ ከመቱት በሁዋላ እንደገና አስፋልት ላይ አውጥተው በጫማ ጥፊ ሲመቱት፣ ሟች በጀርባው ሲወድቅ ጭንቅላቱ ደም እንደፈሰሰውና ልጁ ለመሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ ወደ አካባቢው በሚገኝ ጤና ጣቢያ ቢወሰድም ጤና ጣቢያው ከሃቅሙ በላይ እንደሆነበትና አዲስ አበባ ወደሚገኘው ጥበቡ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወስዶ ህኢወቱ በዚያው አልፏል።
በእለቱ ልጁን ደብድበው የገደሉት ሲቪል የለበሱት የፌደራል ፖሊሶች፣ ሬሳውን ሲያዩ ከህዝቡ ጋር ጭቅጭቅ ውስጥ በመግባታቸው ፖሊስ በርካታ ጥይቶችን በመተኮስ ለማረጋጋት ሙከራ አድርጓል። በማግስቱ ትናንት የከተማዋ ነዋሪዎች አስከሬኑን በመያዝ የመንግስት ያለህ፣ ወንጀለኞች ይያዙልን የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች ማሳማት ሲጀምሩ፣ ቡራዩ ማዘጋጃ ቤት አካባቢ ሲደርሱ ከአመራር አካላትና ከፖሊስ ጋር ግብግብ ተፈጥሯል። የአካባቢው ወጣቶች ለመንገድ ስራ ተብሎ የተቀመጠውን ኮብል ስቶን ድንጋይ እያነሱ ድንጋይ በመወርወራቸው የመዘጋጃ ቤቱ መስኮቶችና በሮች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ መስሪያ ቤቶች ተዘግተው ውለዋል።
በዛሬው እለትም በተለይ ማረት በሚባለው አካባቢ የሚኖሩ ወጣቶች ገዳዮቹ ለፍርድ ይቀርቡና ፌደራል ፖሊስም አካባቢውን ለቆ ይውጣ በማለት ጥያቄዎችን ማቅርባቸው ታውቋል። ውጥረቱ እንደቀጠ ሲሆን፣ ፌደራል ፖሊስም በአካባቢው ተሰማርቶ ይገኛል።
ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ 4 የአካባቢውን ወጣቶች መግደሉ ታውቋል።
No comments:
Post a Comment