Friday, 21 February 2014

“የረዳት አብራሪ ኃይለመድን እህት ታስራለች፣ ቤተሰቦቹ በግዳጅ ሊናገሩ ነው”

Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin's sister)
Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin’s sister)
ቦይንግ 767-300 ጄኔቭ አርፎ፣ መንገደኞቹ ወደየመድረሻቸው ተጉዘው አውሮፕላኑም ወደ ሀገሩ ተመልሷል። ነገር ግን የወሬው በረራ ማረፊያ ቦታ እንዳጣ ነው። የኃይለመድን ጉዳይ በየቦታው የመወያያ ርዕስ እንደሆነ ነው፣ ይቀጥላልም። የግምት ወሬዎች እዚህም-እዚያም እየተረጩ ነው። በተለይ የመንግስት ካድሬዎችን “ቢዚ” አድርጓቸዋል። በምን መልኩ የድራማውን ድርሰት እንደሚጽፉ ግራ ግብት ብሏቸዋል የአዕምሮ ሕመምተኛ ሊሉት ፈለጉ …ከዚያ ትዝ ሲላቸው አዕምሮ ታማሚ ሆኖ አየር መንገዱ መንግስት እንዴት እንዲያበር ፈቀደ፣ ለአብራሪዎቹ ምርመራ አያደርግም ወይ የሚሉት ጥያቄዎች ሊከተሉ ሆነ። ቀጥለው አባትዬው እቁብ ሰብሳቢ፣ አራጣ አበዳሪ… ተደርገው ተሳሉ። እእ..ደራሲዎቹ የቤተሰብ ጣጣ መሪ ተዋናዩ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ አልታይ አላቸው። የኃይለመድን እህት ሆነው የተዋቀረ እና የተዋቃ ጽሑፍ በፌስቡክ ላይ አከታተለው ጻፉ…በርግጥ ይሄኛው የወጭ የዜና አውታሮች ዘንድ ደርሶላቸው ተራግቦላቸዋል። ተአማኒነት ባያገኝም።
በነዚህ መጨበጫ በሌላቸው ወሬዎቹ አንድ ሊገባን የሚችል ነገር ቢኖር ካድሬዎቹ ደራሲዎች የአበራሪው ስም እና ስብዕና በአሉታዊ ጎኑ ብቻ እንዲነሳ መፈለጋቸው ነው። ከአየር መንገዱ ይልቅ የመንግስታቸው ህልውና እንቅልፍ ነስቷቸዋል። ምክንያቱም ኃይለመድን የጠየቀው የፖለቲካ ጥገኝነት ነው፣ ዝርዝር ባይኖረውም ይቺ ቃል የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ስቧል። የHuman Rights Watch ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ስለክስተቱ ተጠይቀው የኢህአዴግ አምባገነናዊ እና ኢ-ሰብአዊነት የትኛውንም ዜጋ የሚያሰድድ እንደሆነ ሳያመነቱ ተናግረዋል። የእንግሊዙ Telegraphም በመረጃ አስደግፎ “ኢትዮጵያውን ያላማቋረጥ የሚፈልሱት በድኅነት እና በጭቆና ነው” ሲል ቁልጭ አደርጎ አስቀምጦታል። እና እንደዚህ ያሉ የኢህአዴግ መታወቂያዎች ከሀገሬው አልፈው ለተቀረው ዓለም እየደረሱ መሆናቸው ካድሬዎቹን አሰበርግጓቸዋል። አውሬ ደግሞ ሲበረግግ የሚያደርገውን አያውቅም።
አሁን የልጁን ቤተሰቦች አስገድደው እንደለመድነው ETV ላይ ድራማ ሊያሰሯቸው እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው። “ፌስቡኬ በሌሎች ሰዎች ጥቅም ላይ ውሏል” ያለችው እህቱም በእስር ላይ እንደምትገኝ ተሰምቷል።
እስኪ የሚያስብሏቸውን እንስማ መቼም ምንም ቢቧጥጡ እውነታዋ ያለችው ረዳት አብራሪ ኃይለመድን ጋ’ ስለሆነ ሊያጠፏት አይቻላቸውም። እኛም እሱ እስኪናገር ከይሆን-ይሆናል አሉባልታዎች ተቆጥበን በድርጊቱ መፈጸም በፊት ባንዲራችንን ተሸክሞ ከአድማስ አድማስ አውሮፕላናችንን እያበረረ ሀገሩን ሲያገለግል ለቆየው ኋይለመድን የምንሰጠው ክብር ይቀጥል።

No comments:

Post a Comment