ኤሌሣቤጥ ግርማ
ezewege@gmail.com
ezewege@gmail.com
ከኖርዎይ
ተወዳጁ የሰብአዊ መብት ተከራካሪና የአዲሲቱ ኢትዩጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ እንዲሁም የኦጋዴን ክልል ፕሬዘዳንት የሆኑት ኦማር አብዲ ሞሐመድ የቀድሞ አማካሪ የነበረዉ ዛሬ የወያኔን የግፍ አገዛዝን በመቃወሙና እዉነታዉን በማሳወቁ ከሀገሩ ኢትዩጵያ እዲሰደድ የተገደደዉ አቶ አብዱላሂ ሁሴን በጋራ ከኖርዌጂያኗ አርቲስት እና አክቲቪስት ሶልፌግ ሲፈርሰን በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ የክርክር መድረክ በኖርዌ ኦስሎ ከተማ ተካሄደ።
ማርች፮ ፣፳፩፬ የተዘጋጀዉ ይህ የክርክር መድረክ ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች በመጡና ኦስሎ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና እንዲሁም በኦስሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኖርዌጅያንን ያካተተ ነበረ። መድረኩ ዋና አላማ አድርጎ የተነሳዉ የነበረው በኢትዮጵያ ዉስጥ በአንባገነኑ ገዢ የሚደረገዉን የሰባዊ መብት ጥሰት ቁልጭ ባለ መልኩ እና በመረጃ የተደገፈ የቪዲዮ ምስል በአቶ አብዱላሂ መቅረቡና እንዲሁም የኢትዮጵያን መሬት ያለአግባብ እየተሸነሸነ እና እየተቆረሰ ለባዕድ ሀገራት እየተሰጠ ያለበትን ሁኔታ በጥሩና ግልጽ በሆነ የምስል መረጃ በአቶ ኦባንግ መቅረቡ ነበር።
በማስከተል ክርክሩን አጓጊና ግንዛቤ አስጨባጭ እንዲሆን ካደረገዉ አንዱ አንድ ተጋባዥ ኖርዌጂያዊ በሆኑ የኢትዮጵያን ዕድገት በ ፮ ፐርሰንት ማደጉዋን፣ የኢንፈርስትራክቸር ለዉጡዋን ፣ በነጻነት መጓጓዝ መቻሉንና የጸጥታ ደህንነቷ የተረጋጋ መሆኑን የወያኔን ዲስኩር መደስኮራቸዉ ነበር።
በሌላ ጎኑ ደግም ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ እንዳለች የማያውቁ ኖርዌጄያንን ጥሩ ግንዛቤ ፈጥሮላቸዉ እንዳለፈ ከአንዳንዱ የተረዳሁት ነው።ይህ እንቅስቃሴ ጅምርታውን አሳይቷል ተግባሩን ፣ ጉዞውን ረጅም ህልሙ እንዲሰምር ለማድረግ እኛ በአዉሮፖና በተለያዩ ክፍለዓለማት የምንኖር ኢትዮጵያውያን ድጋፍና ትብብር ያስፈልጋል እሱም የሚሆነዉ የተለያዩ በምስልና በቪዲዬ የተደገፈ መረጃዎችን በመስብሰብና ይህን መሰል መድረክ በተለያዩ ዐለምት ተቀናጅተን በመፍጠር የወያኔን ደባ ማክሸፍ እንችላለን ብዬ አምናለሁ።
No comments:
Post a Comment