Thursday, 31 October 2013

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው
ከደቡብ ጎንደር : ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም : ከሴሜን ወሎ ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚመጡ ወገኖቻችን ባሰሪወቻቸው አና ባካባቢው በዚህ ሥራ በተሰማሩ ( የትግራይ ተወላጆች ) ግፍ እየተሰራባቸው ነው :: ባለፉት 2 ወራት ብቻ የ16 ሰወች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ጎዳዩን ቀለል በማድረግ እና እውነቱን ሰው እንዳይገነዘብ ሲባል የተለያዩ መላምቶች በመንግስት ሆን ተብሎ ተሰጦታል ::
ለምሳሌ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በተደጋጋሚ የተፈፀመውን እሄን ድርጊት በቀጥታ በብሔሮች መካከል በተነሳ ግጭህት ( የወሎ እና የጎጃም በሚል ) እርስ በርስ በጩቤ እየተዋጉ ነው በማለት ጉዳዩን አድበስብሶት የቀረ ሲሆን ሌሎች ገለልተኛ ሚዲአወችም እሄንኑ በማስተጋባት እውነቱ ተደብቆ ወንጀሉ ግን ቀጥሏል ::
በሁመራ ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር በስፋት የሚፈፀም ሲሆን በዚህ ሥራ የተሰማሩት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ከሱዳኖች ለሚቀበሉት መሳሪያ ክፍያ እንዲሆን የሚሰጠው የገበሬወችን ኩላሊት ነው ::
እንዲህ አይነት ሥራ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤለ በህገወጥ መልኩ የሚጉዓዙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለ እንደሆነና አልፎ አልፎም በሱዳን በገድሃሪት እና አጎራባች አካባቢወች ድረስ በመምጣት ካምፕ ዉስጥ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች አፍኖ በመያዝ ብዙ እሺ ዶላር በማስከፈል ይለቁአቸዋል መክፈል ያልቻሉትን ግን ኩላልታቸውን በማውጣት ለእልፈተሞት ይዳረጋሉ ::
ለወገኖቻችን እንድረስላቸው !!
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ
ሰሜን ጎንደር

የምእመናን ቆጠራና ምዝገባ በአህጉረ ስብከት ሓላፊነት ይካሄዳል: የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ መግለጫ

holy-synodtikmit-meeting
ቅ/ሲኖዶስ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊነትና ቀዳሚነት እውነታውንና ትክክለኛውን የሚገልጽ ጽሑፍ እንዲዘጋጅ ለሊቃውንት ጉባኤው ትእዛዝ ሰጠ
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ለምልአተ ጉባኤው ስብሰባ የሰጠው ሽፋን ‹‹የጉርሻ ያህል ነው›› በሚል ተነቀፈ
‹‹ጉባኤው አገር አቀፍ ብቻ ሳይኾን ዓለም አቀፍም ነው፤ የምንሰጠው ትምህርት ነው፤ የምንወድቀው የምንነሣው ስለ ሀገር ጉዳይ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን በዐይን የሚታይ በእጅ የሚጨበጥ ታሪክ ነው ያስረከበችው፤ በምን ምክንያት ነው [የአየር ሽፋኑ]ቀለል የሚለው›› /ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ/
‹‹ከባለሥልጣናት[ከመንግሥት] የምናገኛቸውን መልእክቶች እናስተላልፋለን፤ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ እናቶች በሆስፒታል እንዲወልዱ ደጋግማችኹ አስተላልፉን ብለው ነግረውን በቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ሺሕ ሕዝብ በተሰበሰበበትና በየአጋጣሚው እናስተላልፋለን፤ እኛም እዚህ ስለ አገር ጉዳይ እንነጋገራለን፤ የምንነጋገረው ግን የሚተላለፈው የጉርሻ ያህል ነው፤ ለሕዝቡ እንዲተላለፍ እንጂ የሚዲያ ሱሰኛ ኾነን አይደለም፤ የሚነገረው ነገር ለሕዝቡ በአግባቡ ቢተላለፍ መልካም ነው›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ቆጠራና ምዝገባ በእያንዳንዱ አህጉረ ስብከት ሓላፊነት እንደሚካሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ፡፡
‹‹ቤተ ክርስቲያን በሥሯ ያሉ ምእመኖቿን ቆጥራ መመዝገብ እንድትችል›› የሚካሄደው ይኸው ታላቅ አገራዊ ክንዋኔ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ በሚያዘጋጀው ቅጽ አማካይነት እንደሚከናወን ነው ቅዱስ ሲኖዶሱ የገለጸው፡፡
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ በ፳፻፮ ዓ.ም. በጀት ዓመት የምእመናን ቆጠራ ለማካሄድ ከብር 29 ሚልዮን በላይ የበጀት ጥያቄ ለቅ/ሲኖዶስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ማቅረቡን መዘገባችን የሚታወስ ሲኾን ዛሬ በቅ/ሲኖዶሱ መግለጫ እንደተጠቀሰው፣ በአህጉረ ስብከት ሓላፊነት የሚካሄደውን ቆጠራ ክንውን በቀጣይ የምንመለከተው ይኾናል፡፡
በተያያዘ ዜና፣ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊነትና ቀዳሚነት ሁሉም ሰው መጻፍ ሲገባው እውነት ያልኾነውን፣ በማስመሰል የሚነገረውንና የሚጻፈውን ማስተካከል እንደሚያስፈልግ ቅዱስ ሲኖዶሱ አሳስቧል፡፡
በመኾኑም እውነተኛውንና ትክክለኛውን አስተካክሎ ለሕዝብ፣ ለትውልደ ትውልድ ማስተላለፍ እንዲቻል መነሻ ይኾን ዘንድ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የኮሚቴ አባልነት ተጠንቶ የቀረበውን ጽሑፍ ምልአተ ጉባኤው በንባብ ሰምቶ ጉዳዩ ወደ ሊቃውንት ጉባኤ እንዲቀርብ ትእዛዝ መስጠቱን ቅ/ሲኖዶሱ አስታውቋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ እንደሚያመለክተው፣ ሊቃውንት ጉባኤው ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊነትና ጥንታዊነት በምልአተ ጉባኤው ላይ የተነበበውንና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የተዘጋጀውን የመነሻ ጽሑፍ አብራርቶ፣ አስፍቶና አምልቶ ለግንቦት፣ ፳፻፮ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ እንዲያቀርብ ተወስኗል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የኾኑ ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡- ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እና ብፁዕ አቡነ እንድርያስ በቅርቡ በተካሄደው ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ፥ ኢትዮጵያ ከአይሁድ በፊት ጀምሮ በአምልኮተ እግዚአብሔር ጸንታ መኖሯን፣ ክርስትናም ወደ ኢትዮጵያ የገባው ክርስቶስ ባረገበት ዓመትና ቅዱሳን ሐዋርያት ገና ከኢየሩሳሌም ባልወጡበት በ፴፬ ዓ.ም. መኾኑን ጠቅሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ታሪካዊነትና ቀዳሚነት በማስረዳት ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ጋራ መጠያየቃቸው ይታወሳል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤው ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በመክፈቻ ሥርዐተ ጸሎት የጀመረውንና ለዐሥር ቀናት ያህል ሲያካሂድ የቆየውን የመጀመሪያ ዓመታዊ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብስባ ዛሬ፣ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በጸሎት አጠናቋል፡፡
ምልአተ ጉባኤው መደበኛ ስብሰባውን ሲያጠናቅቅ ያወጣው ባለ28 ነጥብ መግለጫ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አካትቷል፡-
ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ድረስ በባለሞያዎች ተጠንቶ የቀረበውና በስላይድ የታየው የሥራ መዋቅር ወደ ታች ወርዶ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ውይይት ዳብሮ በሚገባ ተጠንቶና ተስተካክሎ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲቀርብና ቋሚ ሲኖዶሱም አይቶና ተመልክቶ በሥራ ላይ እንዲያውል ምልአተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ወደፊት የምታከናውነው ማኅበራዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በዕቅድ የሚመራ እንዲኾን ለማስቻል በግንቦቱ ርክበ ካህናት ጉባኤ ፳፻፭ ዓ.ም. ተቋቁሞ የነበረው ኮሚቴ ያዘጋጀውን ጥናት ለጉባኤው አቅርቦ ጉባኤው ማብራሪያውን ካዳመጠ በኋላ ኮሚቴው ያላለቁ ሥራዎችን እንዲቀጥል በማለት መመሪያ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊትና ታሪካዊ እንደመኾኗ ኹሉ በቀጣይም አጠቃላይ ማኅበራዊም ኾነ መንፈሳዊ ሥራዎቿን በመሪ ዕቅድ በመምራት ሙስናና የመልካም አስተዳደር ዕጦትን ከሥሩ መቅረፍ እንዲቻል በባለሞያዎች የተጠናውን የመሪ ዕቅድ ዘገባ በመገምገም በቀጣይ ዕቅዱ ዳብሮ በሥራ መተርጎም በሚቻልበት ኹኔታ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
አሁን ያለው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተሻሽሎ እንዲቀርብ በተወሰነው መሠረት የተሻሻለው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ረቂቅ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዲመለከቱት የታደለ ሲኾን እንዲሁም በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ታይቶና ሐሳብ ተሰጥቶበት በ፳፻፮ ዓ.ም. ግንቦት ርክበ ካህናት ውይይት እንዲካሄድበት ምልአተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
በውጭው ዓለም ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት ነን በሚል የሚገኙ ወገኖች ወደ እናት ቤተ ክርስቲያናቸው እንዲመለሱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
በውጭ አገር ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋራ ተጀምሮ የነበረው ዕርቀ ሰላም ወደፊት እንዲቀጥልና የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲጠናከር ጉባኤው ተስማምቷል፡፡
ገዳማቱን መልሶ ማቋቋምና ማጠናከር ብሎም በነበሩበት ኹኔታ አደራጅቶ ሥራቸውን መቀጠል ይችሉ ዘንድ የሚያመለክት በመምሪያው በኩል ሰፊ ጥናት የተደረገ በመኾኑ ገዳማቱ የሚገኙትም በየአህጉረ ስብከቱ ስለኾነና ብፁዓን አበው የሌሉበት ጥናትም አጥጋቢ ውጤት ስለማይኖረው የተወሰኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከመምሪያው ተጠሪ ጋራ ተገናኝተው ገዳማቱ እንዴት መቋቋምና መልማት እንዳለባቸው ጥናት ይደረግበት በሚለው ጉባኤው ተስማምቶ ጠለቅ ያለ ሐሳብ ከነመፍትሔው አጥንተው ለግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም. ርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ እንዲያቀርቡ፡-
1. ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ – የምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
2. ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል – የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ፣ የሕንፃዎችና ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የበላይ ሓላፊ
3. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ – የከምባታ ሐዲያና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመምረጥ ምልአተ ጉባኤው በሙሉ ድምፅ ተስማምቶ ወስኗል፡፡
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን በተመለከተ ኮሌጁን ማጠናከር አስፈላጊ ኾኖ በመገኘቱ ለኮሌጁ ዋና ዲን እንዲሾም ጉባኤ ውሳኔ አሳልፏል፡
Source- ethiopanreview.com

Tuesday, 29 October 2013

የአቶ መለስ ዜናዊ “ያልተገለጡ ገፆች”

220px-Meles_Zenawi_-_World_Economic_Forum_Annual_Meeting_2012

ከበትረ ያዕቆብ
ዉድ የሀገሬ ልጆች ከሁሉም በማስቀደም እንደምን ናችሁ ? ደህና ናችሁ ? 2006 እንዴት ይዟችኋል ? ስል የጠበቀ የወዳጅነት ሰላምታየን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ እዚህ ላይ ይህ ሰዉ ምን ነካዉ!? ባልተለመደ መክኩ ሰላምታ አበዛሳ !? ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም አትፍረዱብኝ፡፡ “አሸባሪ ፣ አክራሪ ፣ ጅሀዳዊ ፣ ተለጣፊ ፣ ነጭ ለባሽ”… ወዘተ የሚል ቅፅል ስም ለሀገር ወዳድና ለመብታቸዉ መከበር ድምፃቸዉን ለሚያሰሙ ሁሉ በጅምላ እየተሰጠ ዜጎች በሀሰት በሚወነጀሉበት ሀገር ፤ በእያንዳንዷ ቀን እንደ መልካም ተግባር መሰል ዜጎችን ጠልፎ ለመጣል የተንኮል ወጥመድ ሲጠመድ በሚዋልበት ጊዜ ፣ ንፁህ ዜጎች በግዳጅ ያልፈፀሙትን ኃጢያት እንዲናዘዙ በሚገደዱበት ዘመን ፤ በልቶ ማደር ፍፁም በከበደበት በዚህ የጭንቅ ወቅት አጥብቆ ደህንነትን መጠየቁ ተገቢ ሆኖ ስለታየኝ ነዉ፡፡ እንደዉም ከዚያም በላይ ብዙ ብል እንኳ የሚበዛ አይመስለኝም፡፡ የሆነ ሆኖ ለሰላምታ ያህል ይህን ካልኩ ወደ ዋናዉ ርዕሰ ጉዳየ በቀጥታ ልለፍ፡፡
እንደሚታወቀዉ ምንም እንኳን የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዝብ ከሰራቸዉ በጎ ስራዎች ይልቅ ያጠፋዉ ለሚዛን የከበደ ቢሆንም ህልፈቱን ተከትሎ በፓርቲዉና በዙሪያዉ በተሰባሰቡ ጥቂትጥቅመኛ የህብረተሰብ ክፍሎች እስከዛሬ ያለ እረፍት እየተወደሰ ይገኛል፡፡ ጀግና ፣ የልማት አርበኛ ፣ የዲሞክራሲ ዘብ ፣ የአፍሪካና የዓለም ምርጥና ድንቅ ባለራዕይ ፣ አስታራቂ አባት ፣ የሰላም ሰባኪ ፣ ብልህ ሽማግሌ ፣ ጥበበኛ ፣ መለኛ ፣ የደሀ ተቆርቋሪ ፣ የፍትህ ሰዉ ፣ ፈላስፋ ….ብዙ ብዙ እየተባለና በርካታ ከንቱ ዉዳሴ እየተዥጎደጎደለት ነዉ፡፡ ሀሰተኛ ታሪክ እንደ ልብ ወለድ እየተፃፈለትና እየተተረከለትም ይገኛል፡፡
ለምሳሌ በቅርቡ አንድ በየኢትዮጵያ ቴሌቭዥን “ያልተገለጡ ገፆች” በሚል በቀረበ ዘጋቢ ፊልም የሰዉየዉ ታሪክ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከምንኮራባቸዉ የዘመነ አድዋ ጀግኖች ታሪክ ጋር ተነፃፅሮ የቀረበ ሲሆን ፤ “ኢትዮጵያን በብቃትና በታማኝነት ያገለገለ ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሪ” ተብሏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አንድ ጉዳዮን የሚያዉቅ ወዳጄ ፊልሙ በተለያዩ የሀገር ዉስጥ ቋንቋዎች ሰፋ ባለ መልኩ ዳግም እየተዘጋጀ እንደሆነ ሹክ ብሎኛል፡፡ እንዳጫወተኝ እነዚህ ፊልሞች ለህዝብ እይታ በቅርቡ ይቀርባሉ፡፡
ኢህአዴግ/ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን እዉነተኛ ታሪክ በማድበስበስ ህዝብን ለማሳሳት እያደረገ ያለዉ ሙከራ መጠነ ሰፊ ነዉ፡፡ ከቴሌቭዥንና ራዲዮ ባሻገር ከእዉነት የራቁ አሳሳች ታሪኮች በተለያዩ ድህረ ገፆች አማካኝነትም ለህዝብ እየቀረቡ ይገኛል፡፡ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪም በተለያዩ የዉጭ ቋንቋዎች መሰል ታሪኮች እንዲሰራጩ በመደረግ ላይ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያየ አንድ የዉጭ ዜጋ የሆነ ወዳጄ በፕሮፖጋንዳዉ አለቅጥ መለጠጥና እየተሰራጩ ባሉት ታሪኮች ተደንቆ “መንግስታችሁ ስራ አጣ እንዴ!?..” ሲል በቅርቡ ተርቦኛል፡፡ አያይዞም “እንዴት ነዉ እኛ የማናዉቀዉ መለስ ዜናዊ የተባለ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበራችሁ?” ሲል ፈገግ አድርጎኛል፡፡ እንደማስበዉ ኢህአዴግ/ህወሓት ለምን የመለስን ታሪክ ማሰማመር እንደፈለገ ለብዙዎች ሚስጥር አይመስለኝም፡፡ እንደሚታወቀዉ ሰዉየዉ የዚህችን አገር የፖለቲካ መዘወሪያ ለ21 አመታት ያለተቀናቃኝ በጫንቃው የተሸከመና በሁሉም ነገር ላይ አራጊ ፈጣሪ የነበረ እንደመሆኑ የእርሱ ታሪክ የገዥዉ ፓርቲ እንዲሁም የሌሎች አመራሮች ታሪክ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነዉ፡፡ ስለሆነም ስልጣኑን ተቆጣጥሮ የቀጠለዉ ፓርቲና አመራር ለራሱ የተሻለ ገፅታ ለመስጠት የግድ የሰዉየዉን መልካም ያልሆነ ታሪክ ማስተካከል አለበት ማለት ነዉ፡፡ እንግዲህ አሁን እየተደረገ ያለዉም ይህ ይመስለኛል፡፡
ዉድ አንባብያን እንግዲህ እኔም ይህችን ፅሑፍ ለመፃፍ ምክንያት የሆነኝ ይህ ኢህአዴግ/ህወሓት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን እዉነተኛ ታሪክ በማድበስበስ ህዝብን ለማሳሳት እያደረገ ያለዉ ሰፊ ሙከራ ሲሆን ፤ እዉነቱ ይፋ ወጦ የህዝብ መወያያ ሊሆን ይገባል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡ ምክንያቱም የሰዉን እዉነተኛ ታሪክ (ያዉም ሀገርን ያህል ትልቅ ነገር ለረጅም ጊዜ የመራን ሰዉ) ሰርዞና ደልዞ ለህዝብ ማቅረብ በጣም አደገኛ ዉጤት የሚያስከትል ተግባር ነዉና፡፡ እንዲህ አይነት ተግባር ሰዎች በሰሯቸዉ ስህተቶች ተወቃሽ እንዳይሆኑና ትዉልድም ከታሪክ እንዳይማር የሚያደርግ ፣ ተተኪ ወጣቶች ትናንት አባቶቻቸዉ ባለፉበት የስህተት ጎዳና ደጋግመዉ እንዲያልፍ በር የሚከፍት ነዉ፡፡ ስለሆነም ሊደበቅ እየተሞከረ ያለዉን የአቶ መለስን ማንነት በዚች አጭር ፅሑፌ በትንሹም ቢሆን ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ ሰዉየዉ በስልጣን ዘመኑ በማናለብኝነት በሀገርና በህዝብ ላይ የፈፀማቸዉን ወንጀሎች በመዘርዘር ለሕዝብ ዳኝነት እተወዋለሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ በፊት ግን ለግንዛቤ ያህል የሰዉየዉን የህይወት ታሪክ ጠቅለል ባለ መልኩ አስቀምጨ ልለፍ፡፡
እንደሚታወቀዉ የትናንቱ ለገሰ ዜናዊ የዛሬዉ አቶ መለስ ዜናዊ በወርሃ ግንቦት 1947 ዓ.ም ነበር በአድዋ ከተማ የተወለደዉ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአድዋ ንግስተ ሳባ ትምህርት ቤት የተከታተለ ሲሆን ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በጀኔራል ዉንጌት አጠናቋል፡፡ ከዚያም ከፍተኛ ዉጤት በማስመዝገብ አዲስ በበባ ዩኒቨርስቲ ህክምና ለማጥናት መግባት የቻለ ቢሆንም ብዙም ሳይገፉበት ነበር ወታደራዊዉን አምባገነን የደርግ ስርዓት ለመታገል ወደ በረሀ የወረደዉ፡፡ በወቅቱ በኢትዮጵያ ያለዉ ጭቆና የብሔር ጭቆና ነዉ የሚል እምነት የነበረዉ ወጣቱ ታጋይ ፤ መፍትሄዉ ትግራይን ከቀረዉ የኢትዮጵያ ክፍል በመገንጠል የትግራይን ሪፐብሊክን መመስረት ነዉ የሚል ፅኑ እምነት ነበረዉ፡፡
በትግሉ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ በተለያዩ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃዎች ህወሀትን በሙሉ አቅሙ ያገለገለ ሲሆን ፤ በድርጅቱ ዉስጥ ከነበረዉ ቁልፍ ሚና አኳያ የትግሉ አርክቴክት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ አቶ መለስ በ1983 ትግሉ በድል ሲጠናቀቅ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት መሆን የቻለ ሲሆን ፤ ቆይቶም ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት በመሸጋገር እስከ እልፈተ ሞቱ ሀገሪቱን ያለአንዳች ተቀናቃኝ በማንአለብኝነት መምራት ችሏል፡፡
1. የኤርትራ መገንጠል
አቶ መለስ ዜናዊ 21 ዓመት መዝለቅ በቻለዉ ያስተዳደር ዘመኑ በሀገርና ህዝብ ላይ ከባድ ወንጀሎች ፈፅሟል ፤ እነርሱም በተለያዩ የታሪክ መፅሐፍት ላይ በዝርዝር ተጠቅሰዉ ይገኛል፡፡ ሰዉየዉ ከፈፀማቸዉ እነዚህ ወንጀሎች መካከል በዋነኝነት ተጠቃሹና በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥም ሁሌም የሚታወስበት በግብፅና በአንዳንድ የአረብ ሀገራት አጋዥነት ኤርትራን እንድትገነጠል ማድረጉ ነዉ፡፡ እዚህ ላይ ምንም እንኳን የበርካታ የህወሀት አመራሮች እጅ በዚህ ወንጀል ዉስጥ ቢኖርበትም የአንበሳዉን ሚና የተጫወተዉ እሱ ነበር ለማለት የሚያስደፍሩ በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡
በርካታ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት የኤርትራ መገንጠል ህግን እና ህጋዊ አካሄድን ያልተከተለ ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያን ጥቅም ከግምት ዉስጥ ያላስገባ ፤ የአረቦችን ፍላጎትና የኢሳያስን ገደብ የለሽ የስልጣን ጥም ለማሟላት ሲባል ብቻ ሆን ተብሎ የተደረገ ነበር፡፡ በወቅቱ በርካታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን (ለቁጥር የሚታክቱ ኤርትራዉያንም ጭምር) ድርጊቱን በመቃወም ድምፃቸዉን ሲያሰሙ የነበረ ሲሆን ፤ ለነርሱ የአቶ መለስ ምላሽ ስድብ ነበር፡፡
በትግል ወቅት አቶ መለስ የኤርትራ ባለቤት ነን ከሚሉት የሻብያ መሪዎች በላይ ስለኤርትራ መገንጠል ያቀነቅን ነበር፡፡ ተስፋ ወደ መቁረጡ በተቃረቡበት ወቅትም “አይዟችሁ ኤርትራን በቅርቡ ከኢትዮጵያ ትገነጥላላችሁ ፣ በርቱ” እያለ ከመደገፉ ባሻገር ትግላቸዉን የሚያግዝ አስትራቴጅክ መፅሐፍም ፅፎ አበርክቶላቸዋል፡፡ ኤርትራ ከእናት ሀገሯ ከተገነጠለች በኋላም አለም እንደ ሀገር ይቀበላት ዘንድ እንደ መለስ ወዲያ ወዲህ ያለ የለም ማለት ይቻላል–ኢሳያስ አፈወርቂም ቢሆን እንኳ፡፡ በዚህም ምክንያት የወቅቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በነገሩ ግራ እስከመጋባት ደርሶ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንዶችም የሰዉየዉን ኢትዮጵያዊነት እስከመጠራጠር ደርሰዉ ነበር፡፡
2. የኢትዮጵያ የባሕር በር (አሰብ)
አሰብ በታሪክና በህግ የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ የበሀር በር የመሆኗ ጉዳይ አሌ የማይባል እዉነት ነዉ፡፡ ይህንንም በርካታ ምሁራን ሰነድ እያጣቀሱ ደግመዉ ደጋግመዉ በግልፅ አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ግን አቶ መለስ ዜናዊ እዉነቱን እያወቀ (ለእርሱ ብቻ ግልፅ በሆነ ምክንያት) ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ሀብታችንን ከእጃችን አይናችን እያየ እንዲያመልጥ አድርጓል፡፡ ይህም የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ልብ የሰበረና እስካሁን እንቆቅልሹ ያልተፈታ ጉዳይ ነዉ፡፡
አቶ መለስ አሰብን በተመለከተ ጥፋት ያጠፋዉ ከአንድም ሁለት ሶስቴ ነዉ፡፡ የመጀመሪያዉ ጥፋት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጠል ወደቡ ወደ ኢትዮጵያ እንዲጠቃለል ማድረግ እየተቻለ (ህጉም እየፈቀደልን) ለኤርትራ መሰጠቱ ነዉ፡፡ በወቅቱ ለምን የሚል ተቃዉሞ ሲነሳ አቶ መለስ ይግረማችሁ ብሎ ለኤርትራ ሽንጡን ገትሮ በመከራከር ኢትዮጵያ ጥንታዊ የባህር በሯን በተመለከተ አንድም ጥያቄ እንዳታነሳ አድርጓል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በ1989ዓ.ም የኤርትራን ዉረራ ተከትሎ ኢትዮጵያ አሰብን በእጇ የምታስገባበት ሌላ እድል ተፈጠሮ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ያላደላት ሀገራችን የዚያን ሁሉ ልጆቿን ህይወት ገብራ ጦርነቱን በድል አድራጊነት ብትወጣም በአቶ መለስ ትዕዛዝ ወደ አሰብ ድርሽ እንዳትል ተደርጓል፡፡ ከዚህም በኋላ የአልጀርስን ድርድር ተከትሎ ብዙ ኢትዮጵያዊ ምሁራን ተስፋ ሳይቆርጡ መንግስት ወደቡን በተመለከተ ለአደራዳሪዉ አካል ጥያቄ እንዲያነሳ ከመማፀን ባሻገር ለድርድሩ የሚረዱ ጠቃሚ የታሪክ ፣ የህግና የፖለቲካ መረጃዎችን በዝርዝር ማቅረብ ችለዉ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ የፈየደዉ አልነበረም፡፡ የሆነዉ የብዙዎችን አንገት ያስደፋ ነበር፡፡ አቶ መለስና ግብር አበሮቻቸዉ ከኤርትራ ጎን ቆመዉ ለኤርትራ ጥቅም በመከራከር በገንዘብ የማይተመነዉን እጅግ ጠቃሚ የሀገር ሀብት ለኤርትራ አስረክበዉ ተመለሱ፡፡ እነዚህን በሀገርና ወገን ላይ የተፈፀሙ ክህደቶችና ወንጀሎችን በተመለከተ ዶክተር ያዕቆብ አሰብ የማናት በተሰኘዉ መፅሐፋቸዉ ላይ በደንብ አንድ ባንድ ያብራሩዋቸዉ በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ማግኘት የሚፈልግ ሰዉ መፅሐፉን ማንበብ ይቻላል፡፡
ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ወደብ ከሌላቸዉ ጥቂት ሀገራት ዉስጥ ትልቋና ብዙ ህዝብ ያላት ስትሆን ፤ በየቀኑ ከ4 ሚሊዩን ዶላር በላይ ለጅቡቲ የወደብ ክራይ እንድትከፍል ተገዳለች፡፡ ይህም የሁላችንን ኪስ የሚፈታተን ከፍተኛ የዋጋ ንረት እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወደብ አልባ መሆናችን ሙሉ በሙሉ በሌላ አገር ላይ ጥገኛ እንድንሆን ምክንያት የሆነ ሲሆን ፤ የደህንነት አደጋም ጋርጦብናል፡፡ የአለማችን ዋና እስትራቴጅክ አካባቢ ከሆነዉ የቀይ ባህር አካባቢ መራቃችንን ተከትሎም በዲፕሎማሲዉ መስክ የነበረን ተፅዕኖ ፈጣሪነት እጅግ ተዳክሟል፡፡
3. የባድመ ጦርነት
ሻቢያ በ1989 ዓ.ም በድፍረት ድንበር ተሻግሮ ኢትዮጵያን መዉረሩ በተሰማ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ነበር በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵዉያን ለነፍሳቸዉ ሳይሳሱ የአገራቸዉን ዳር ድንበር ለማስከበር ወደ ጦር ግንባር የተመሙት፡፡ ይህንን ተከትሎ ኢትዮጵያ ጦርነቱን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን እግረ መንገዷንም ሌሎች ጥቅሞቿን ታስጠብቃለች የሚል ግምት በብዙዎች ዘንድ ነበር፡፡ በተለይም አሰብ እንደገና በኢትዮጵያ ህዝብ እጅ የመግባቱ ጉዳይ ላይ ማንም አልተጠራጠረም፡፡ ሆኖም ግን በጣም ዘግናኝ ከሆነ ጦርነት በኋላ የመከላከያ ሰራዊታችን ወደ መሀል ኤርትራ መገስገስ ሲጀምር አቶ መለስ ዜናዊ በአስቸኳይ እንዲመለስ ትዕዛዝ በመስጠት ለወገኖቻችን ህይዎት መጥፋት ምክንያት የሆነዉን የሻብያ መንግስት ታደገ ፤ የዚያን ሁሉ ወጣት ኢትዮጵያዊ ህይወት ትርጉም አሳጣ ፣ ተሳለቀበት፡፡
በዚህም ያልተገታዉ አቶ መለስ ዜናዊ በአልጀርሱ ድርድር ላይ ሌላ አሳፋሪ ተግባር ፈፀመ፡፡ ተገቢነት የሌላቸዉና ፍርስ የሆኑ የ1900 እና የ1902 የቅኝ ግዛት ዉሎችን ለድርድር በመምረጥ የሻቢያን ህልም እዉን አደረገ፡፡ የዚያ ሁሉ ወጣት ደም የፈሰሰለትን ባድሜን ፣ ኢሮብን እና ፆረናን ለሻቢያ አስረክቦ በዶ እጁን ተመለሰ፡፡
4. የመተማ መሬት
አቶ መለስ ዜናዊ በስልጣን ዘመኑ በሀገር ላይ ከፈፀማቸዉ ወንጀሎች መካከል አንዱና የቅርብ ጊዜዉ የመተማ ጉዳይ ነዉ፡፡ ሰዉየዉ የተጠናወተዉ ሀገርን እየቆረሱ ለባዕዳን የመስጠት አባዜዉ አለቀዉ ብሎ ሰፊ የመተማን ለም መሬት ከኢትዮጵያ ህዝብ እዉቅና ዉጭ ሸንሽኖ ለሱዳን ያስረከበ ሲሆን ፤ ይህንን ተግባሩን በተቃዎሙት የአካባቢዉ አርሶ አደሮች ላይም ብዙ በደል ፈፅሟል፡፡ በቅርብ የወጡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ሰዓት መንግስት ለህዝብ በግልፅ ባላሳወቀበት ሁኔታ ኮሚቴ በማቋቋም አዲሱን ድንበር የማካለል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
5. ታሪክ ማጠልሸት
አቶ መለስ ዜናዊ ከሚታወስባቸዉ ተግባራቶቹ መካከል ከታሪክ ጋር የነበረዉ መረን አልባ ቅራኔ ነዉ፡፡ ይህ ሰዉ የ5 ሽህ ዓመት ታሪክ ባለቤት የሆነችዉን ሀገራችንን የመቶ ዓመት ዕድሜ ባለቤት ናት ከማለት ጀምሮ በርካታ የታሪክ ክህደት ፈፅሟል፡፡ ለእርሱ ሰንካላ የፖለቲካ ፍልስፍናና እረጅም የስልጣን እድሜ ያመቸዉ ዘንድ የፈለገዉን ታሪክ ሰርዟል ፣ ደልዟል፡፡ ያሻዉን ታሪካችን ነዉ ሲል ተከራክሯል፡፡ የአክሱም ታሪክ ለወላይታዉ ምኑ ነዉ …ወዘተ ሲል በሀገርና በህዝብ ላይ ቀልዷል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለማችን ከሚገኙ ጥቂት ቀደምት ታሪክ ካላቸዉ ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠቀስ ናት፡፡ ከዚህም ባለፈ የሰዉ ልጅ መገኛ መሆኗ ልዩ ያደርጋታል፡፡ የሚገርመዉ ይህን ታሪካችንን በርካታ ምሁራን የመሰከሩለትና በምርምር የተረጋገጠ በመሆኑ ጠላቶቻችን እንኳን የሚቀበሉት ነዉ፡፡ ሆኖም ይህ ሁሉ እዉነት ለአቶ መለስ አልሰራም፡፡
6. ኢትዮጵያዊ አንድነትን ማዳከም
ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች አገር ናት፡፡ እነዚህ የተለያየ ባህል ፣ ቋንቋና ሐይማኖት ያላቸዉ ህዝቦች ለበርካታ ዘመናት በአብሮነት ተከባብረዉና ተዋደዉ ኖረዋል፡፡ በአንድነት የደስታ ዘመናትን እንዳሳለፉ ሁሉ በርካታ አሳዛኝ ጊዚያትንም ተጋርተዋል፡፡ ተጋብተዉ ወልደዋል ፣ ከብደዋል፡፡ አብረዉ የዉጭ ጠላትን በደምና ባጥንታቸዉ ተከላክለዋል ፤ ደማቅ ታሪኮችን ሰርተዋል፡፡ ሆኖም የአቶ መለስን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ይህ ኢትዮጵያዊ አንድነት ችግር ላይ የወደቀ ሲሆን ፤ ዛሬ እየተባባሰ መጦ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ደህንነት ላይ ጥላ አጥልቶበታል፡፡
አቶ መለስ ሲመቸዉ አንዱን ብሔር ጨቋኝ አንዱን ተጨቋኝ አድርጎ በማቅረብ እንዲሁም አንዳንድ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል የተከሰቱ ያለፉ አለመግባባቶችን እየነቃቀሰ ህዝቦች በተለመደዉ አብሮነት እንዳይቀጥሉ በርካታ ጥረት አድርጓል፡፡ አንድ የሚያደርጉንን የጋራ እሴቶቻችንን በማደብዘዝ በመሀከላችን ልዩነት እንዲፈጠር ተግቶ ሰርቷል፡፡ ይህንን ሁሉ ያደርግ የነበረዉ ደግሞ ያን የሚሳሳለትን ስልጣን ለማስጠበቅ ብቻ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሀገሪቱ ፍቱን ነዉ ሲል የፈለሰፈዉ ብሔር ተኮር ፌደራሊዝምም ቢሆን ከመስማማት ይልቅ አለመስማማትን እያጎለበተና ሌላ መዘዝ እያመጣብን ይገኛል፡፡
7. ምርጫ 97
እንደሚታወቀዉ ህወሀት/ኢህአዴግ ወደስልጣን ከመጣበት 1983ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያዉያን በአቶ መለስ ትእዛዝ በግፍ ተጨፍጭፈዋል ፣ በወጡበት ቀርተዋል፡፡ ለቁጥር የሚታክቱ ተደብድበዋል ፣ ታስረዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በጋምቤላና በሶማሊያ ክልል የተፈፀሙትን መመልከት በቂ ነዉ፡፡
ምርጫ 97ን ተከትሎ ድምፃችን ይከበር በሚል አደባባይ በወጡ ንፁሐን ዜጎች ላይ የተፈፀመዉ ዘግናኝ ወንጀል አንዱ በአቶ መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተፈፀመ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነዉ፡፡ በወቅቱ ስልጣኔ ለምን ተነቀነቀ በሚል አዉሬ የሆነዉ አቶ መለስ የሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊት በእርሱ እዝ ስር እንዲሆን በማድረግ በሰጠዉ መመሪያ መሰረት በአዲስ አበባ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ፣ ህፃናትና አዛዉንት የጥይት ሲሳይ ሆነዋል፡፡
እንደ ማጠቃለያ
አቶ መለስ ዜናዊ በሀገርና ህዝብ ላይ የፈፀመዉን ወንጀል ዘርዝሮ ለመጨረስ ይከብዳል፡፡ ሀገርን ከመካድና ከመናድ ባሻገር በርካታ ግፍ ፈፅሟል፡፡ ዜጎችን አስጨፍጭፏል ፤ በግፍ ንፁሀንን በእስር ቤት አሳጉሯል ፤ ምስኪን ደሀ ቤተሰቦችን ከቀያቸዉ አስፈናቅሏል ፤ የሀገርና የህዝብን ሀብት አስመዝብሯል ፣ መዝብሯል፡፡ እንግዲህ ይህ ነዉ የአቶ መለስ ዜናዊ ትክክለኛ ማንነት ፤ ይህ ነዉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለአፍታም ሊዘነጋዉ የማይገባዉ ነጥብ፡፡

የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ…(አቤ ቶኪቻው)

የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ…
ዳዊት ከበደ እና ተስፋሁን ጫመዳ
ተስፋሁን ጫመዳ የተባለ አንድ ወጣት ኢትዮጳያዊ ነበር፡፡ የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ስራ አልመችህ ቢለው በተለያየ አጋጣሚ ተው  ማለት ጀመረ፡፡ ኢህአዴግዬ ግን ተው ባይ አይወድምና በክፉ አይኑ ተመለከተው ይሄኔ ተስፋሁን የሚመጣበትን ጦስ ሸሽቶ መጪው ጊዜ መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርጎ እስኪያልፍ ያለፋል ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ፡፡ ኢህአዴግ ግን ዝም አላለውም ከተሰደደበት ሀገር አፍኖ ወደ ሀገርቤት መለሰው፡፡ መመለስ ብቻም አይደለም እስር ቤት ዶለው፡፡ መዶል ብቻም አይደለም በቅርቡ ተስፋሁን በእስር ቤት በቂ ህክምና አጥቶ ህወቱን ተነጠቀ፡፡
ዳዊት ከበደ የተባለ ሌላ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነበር፡፡ እርሱም የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ስራ አልጣመውም እና መምከር ጀመረ፡፡ ኢህአዴግዬ ግን በሚመክሩት ላይ መከራ የሚያበዛ ነውና በክፉ አይኑ ተመለከተው፡፡ ይሄኔ ዳዊት ከጎልያድ ጋር ይጋፈጥበት ወንጭፍ በእጁ አልነበረምና ቀን እስኪልፍ ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ፡፡ ኋላ ላይ ግን እንደ ተስፋሁን አፍነው ሳይወስዱትም ራሱ “እንደውም አልፈራችሁም” ብሎ ወደ ሀገርቤት ተመለሰ፡፡ “ይገሉኝም እንደሁ ይሰቅሉኝም እንደሁ ይሄው መጣሁልዎ ያለምጣም ኢህአዴግ ብዬ ሰደብኩዎ” ብሎ ሁሉ ልክ ልካቸውን ነገሯቸዋል ነው የሚባለው…  ነገር ግን እንደ ተስፋሁን እስር አልጠበቀውም፡፡  እንኳንስ ህወቱን ሻንጣውም አደጋ ላይ አልወደቀም፡፡
ሶስተኛ አንቀጽ እኔ
“አውቶብሱ መጣ ጎማው ሸተተኝ እኔም ከሰሞኑ ተሳፋሪ ነኝ” ብዬ ዥው ብዬ ወደ ሀገሬ ብሄድ የሚጠብቀኝ ምን ይሆን… እንደ ተስፋሁን ታስሮ ህይወት ማጣት፣ እንደ ውብሸት ታስሮ ይቅርታ ማጣት፣ እንደ ርዮት ታስሮ ጠያቂ ማጣት፣ እንደ እስክንድር ታስሮ ቤተሰብ ማጣት ወይስ እንደ ዳዊት ታስሮ አሳሪ ማጣት!? (በቅንፍም የሆነውስ ሆኖ ግን ስንት አመት ሰው ሀገር እቆያለሁ የሆነ ቀንማ ሄጄ መቀወጤ አይቀርም፡፡ (በሌላ ቅንፍም ደግሞ ሳላግጥ፤ ቢያንስ ግን ለጨዋታም ለቃለ ምልልስም እንዲመች የባቡር ግንባታው እንኳ ይለቅና እንተያያለን…!))

Sunday, 27 October 2013

የትርፍ ሰዓት ትግል

ኢዮብ ይስኃቅ
ከዕለታት አንድ ቀን ባልተለመደ ድፍረት የሙስና ኮሚሽን ሰይፉን ትላልቅ የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ አሳረፈ። እንደመድኃኒት ብልቃጥ እዚህም እዚያም ተወሽቆ የነበረ ብርና ንብረት እያስቆጠረ ወንጀለኞቹን ዋስ እየከለከለ ወደ ወህኒ ወረወረ። ሚኒስትሮች ከቦታቸው ተፈናቀሉ፤ የሙስና እናት የሚለውን ሜዳሊያ ያጠለቀችው ወ/ሮ አዜብ ከኤፈርት ተባረረች። ያዲሳባ ከንቲባነትም ሱሚ ነው ተባለች። ከሁለት ብቻ ሳይሆን ከብዙ ያጣች ሆነች። ህዝቡ እልል ለማለት ቢፈልግም ወያኔን ስላላመነ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ያዘ።
 የተፈራው አልቀረም ጉዱ ቀስ በቀስ ይወጣ ጀመር። በትሩ አንደኛው ጠንካራ ሙሰኛ ሌላኛውን ደካማ ሙሰኛ የሚያስገብርበት ሂደት ነበር። ህወሓትን ሊጋፋ ይችላል ተብሎ የተጠበቀው በረከት ስምኦን ጉዋደኞቹን ካስበላ በኋላ ተደራድሮ ለሌላ ሥልጣን ታጨ። ምናልባት ትግርኛ መናገሩ ከአደገኛው ሰይፍ ሳይታደገው አልቀረም – ለዛሬ።
ሰሞኑን የተስፋዬ ገብረአብ እና የተመስገን ደሳለኝ ከቅርብ ምንጮች ተገኘ ተብሎ የተጻፈውን የኢህአዴግን መበላላት የሚያሳይ ጽሑፍ ሳነብ፤ በተጨማሪ የተገነዘብኩት ነገር እስሩና መጠላለፉ ለሀገሪቱ ጥቅም ሳይሆን የወያኔን የሥልጣን ግዜ ማራዘሚያ መሆኑን ነበር። በተለይ ተመስገን አቶ ስብሃት ነጋ “በውራይና” ጋዜጣ ላይ የፃፉትን ሲያስነብበን የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር በፍፁም ሥልጣኑን የማስረከብና ለኢትዮጵያም ምንም አይነት የሚጠቅም ራዕይ እንደሌለው ያረጋገጠ ነበር። ምናልባት ራዕይ እንኳን ቢኖራቸው፤ በሥልጣን ላይ እስከነድዳቸው የመቆየት ሊሆን ይችላል። መቆየታቸው ባልከፋ! ነገር ግን ለዚች ድሃ ሀገርና ህዝብ የሚጠቅም አንድም ፖሊሲ የመቅረፅ ሃሳብ የላቸውም። እያንዳንዱ ልማት ተብዬ ከጀርባ ለነሱ ሙስና የተጋለጠ ካልሆነ በስተቀር ለሀገር ተብሎ የሚወጣ ዕቅድ የለም። ለሰው ልጅ ምን ያህል ሀብት ይበቃዋል ብለን እስክንገረም ድረስ በአጥንቱ የቀረውን ህዝብ እየጋጡት ይገኛሉ።
የመገናኛ ብዙኀኖቻችን
ባለፉት ሃያ ዓመታት ኢትዮጵያንና ህዝቧን ስንመለከት በአዲስ ዘመንና አጋር የመንግሥት ሚዲያዎች እንደሚነገረን የጥጋብ ሀገር አልሆነችም። ወይንም በዘመናዊው አዲስ ዘመን “ሪፖርተር” ጋዜጣም እንደሚቀርብልን የኢትዮጵያ ችግር የጠንካራ ተቃዋሚ መጥፋት ብቻ አይደለም። ስታትስቲክ ብቻውን ዜና አይደለም ብሎ በአሉ ግርማ እንዳለን፤ የተመደበውን በጀት ድምር፣ የሚሠሩ ልማቶች ወጪና የተገኘውን ብድር በደማቅ ርዕሶች መፃፍ ብቻውን ጥሩ ጋዜጣ አያሰኝም። በሀገሪቱ የተንሰራፋውን ድህነት፣ በየትምህርት ቤቱ ለሁለትና ለሦስት ቀናት እህል ባፋቸው ሳያልፍ በየክፍላቸው የሚወድቁትን ህፃናትና በየቀኑ በልማት ስም የሚፈናቀሉትን ቤተሰቦች ዜና እንደግል ጋዜጣነቱ ሲያስነብበን አናይም። አልፎ አልፎ ተኝቶ ቤቱ ድረስ የሚቀርቡለትን ትኩስ መረጃዎች ለማጀብ ቀላል ትችቶችን በርዕሰ አንቀፁ ያቀርብልናል።
እንደአለመታደል ሆኖ በሌሎችም የግል ጋዜጦች የምናገኘው ዜና ጽንፈኝነትን የተሸከመ ከመሆኑም ሌላ መንግሥትን ከመሳደብ ውጪ በተቃዋሚ ጎራ ያለውን ችግር ግልፅልፅ አድርገው አያቀርቡም። እየተሳደደም ቢሆን ሁሉንም በአንድ ሚዛን የሚያስቀምጠው አንድ ለናቱ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ ብቻ ነው።
በሀገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚ
በርግጥም ወደ ተቃዋሚ ጎራ ስንመጣ ቀላል የማይባል ችግር አለ። በመጀመሪያ ባገር ውስጥ ያሉትን ስንመለከት አብይ ችግር ሆኖ የምናገኘው ሥልጣንን ሙጭጭ የማለት ጉዳይ ነው። የሊቀመንበርነቱን ቦታ አስረከቡ ሲባል አረፍ ብለው ይመለሱበታል። በዚህ ሃያ ዓመት ውስጥ የትኛውም አንጋፋ ፓርቲ በአዲስ ወጣት መሪ ተተክቶ አላየንም። ተተካካን ያሉትም በአጋፋሪነት ከኋላ በምክትልነት ያስከተሉዋቸውን ሰዎች ነው። እነዚህ ሰዎች እንደአስፈላጊነቱ ቦታውን ሊለቁ የሚችሉ ታማኝ ሰዎች ናቸው። በተቃዋሚነት ዘመኑ ዲሞክራሲን ያላለማመደን መሪ በአጋጣሚ የመንግሥት ሥልጣን ቢረከብ እንዴት አይነት አምባገነን እንደሚሆን ለመገመት ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም። ለጠንቋዩ የታሰበውን እራሳችን እየበላን እራሳችን እንገምታለን።
 ስደተኛው ተቃዋሚ
ወደውጪው ተቃዋሚ ስንመጣ ሰሞኑን “ሰላቢ ፀሐፊዎች” በሚል በተስፋዬ ገብረአብ የቀረበውን ጽሑፍ በማስታወስ ነው። ተስፋዬ ይህን ያለው በብዕር ስም ጎርፍ የሚለቁትን ፀሐፊዎች ለመንካት ነው። እኛ ደግሞ ሰላቢ ፖለቲከኞች እንላለን – ቁርጠኝነት ጎሎዋቸው የሌላውን የትግል ስሜት ይሰልባሉና። በትክክል የምንስማማበት አንድ ነጥብ አለ። ይኸውም ኢትዮጵያ ፋታ በማይሰጥ አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለች። ይህ ማለት ማቄን ጨርቄን ሳንል የምናምንበትን ወይም የምንሰብከውን ትግል መከተል ይሆናል። ወድድንም ጠላንም የዛሬዎቹ መሪዎች በረሃ በገቡበት ወቅት ወጣትነታቸውን ጨምሮ ብዙ ጥቅሞቻቸውን መስዋዕት አድርገው ነው።
ለምሳሌ መለስን እና ኢሳያስ አፈወርቂን ብንወስድ፤ አንዳቸው የተከበረ ዶክተር፣ ሌላኛቸው ደግሞ ኢንጅነር የመሆን ተስፋ የነበራቸው ወጣቶች ነበሩ። በሀብትም ቢሆን ደጃዝማች አባቶቻቸው መሶባቸው ሙሉ፣ ጎተራቸው ካመት ዓመት የማይጎድል ባላባቶች ነበሩ። ጥሩ ኑሯቸውንና የነገ ትልቅ ሰው የመሆን ዕድላቸውን በሳጥን ቆልፈውበት ነው ወደ በረሃ የገቡት። አይ! አሸንፈው መሪ ለመሆን ነው የሚል የዋህ ያለ አይመስለኝም። ኃይለሥላሴም ሆኑ ደርግ ይወድቃሉ ብሎ እንኳን ሰዉ እግዜሩም እርግጠኛ የነበረ አይመስለኝም። የራሱን ጀግኖች እየበላ መንገዱን ጠርጎ ያስገባቸው ወደድንም ጠላንም ኮሌኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ነው።
ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ የዛሬዎቹ ተቃዋሚዎች በተለይ ደግሞ ብቸኛው አማራጭ የትጥቅ ትግል ነው የሚሉት፣ እንኳን ሕይወታቸውን፣ ደሞዛቸውን ሲሰዉ አናይም። ኢትዮጵያ ያለችበት ችግር አጣዳፊና ግዜ እንደማይሰጥ ከተስማማን ፈጣን እርምጃ መወሰድ ነበረበት። ከዚህ ይልቅ መግለጫዎችን በመስጠቱ ላይና ገቢ ማሰባሰቡ ላይ በርትተው ሲንቀሳቀሱ እያየን ነው።
ከጥቂት ዓመታት በፊት በድል ማግስት አዲስ አበባ የሚያስገባ ካርድ በገንዘብ የሚታደልበት ዝግጅት ተደርጎ ነበር – በግንቦት ሰባት። በዚህ አጭር ጊዜ ወያኔ ወድቆ አዲስ አበባ ይያዛል የሚል የየዋህ ግምት ባይኖረኝም በኢትዮጵያ ተራሮችና ጫካዎች ውስጥ እየተሽሎከለከ ወያኔን የሚያሸብር ታጋይ መጠበቄ አልቀረም። በኢንተርኔት መስኮቶች ወዛቸው ግጥም ያለ ባለስካርፍ ታጋዮችን ተመልክተናል። ግን የዋሉበትን የትግል አውድማ በስህተት እንኳን ሰምተን ወይንም አይተን አናውቅም።
አንድ እየተሠራ ያለ ነገር ቢኖር ይሔ እንደጉድ ድህነትንና ግፍን እየሸሸ በረሃና ባህር የሚበላው ወጣትና ወደ ዐረብ ሀገር የሚሰደዱ እህቶች ምርጫቸው ሽሽት ሳይሆን የችግሮቻቸው ምንጭ የሆነውን መንግሥት ለመጣል ትግሉን መቀላቀል ነበር። ይህ መሆኑ ቀርቶ ግን በኢትዮጵያ ጫካዎች ልናያቸው የሚገቡ ወታደራዊ ልብሶች እንደእንቁጣጣሽ ቀሚስ እነታማኝ በየነን በፈንድሻ ለመቀበል በየስደቱ መድረክ ላይ ሲጌጥባቸው እናያለን።
 ኢትዮጵያን ከህወሓት ጥፋት ለማዳን ያለን ምርጫ
ሀገራችን በህወሓት መራሹ መንግሥት እጅ ከቆየች ያለማጋነን በሚቀጥሉት ዓመታት ዛሬ ያለችበት ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ እንደማይኖራት ማወቅ አለብን። ህዝቡም በዘርና በኃይማኖት ተከፋፍሎ እርስ በእርሱ የሚበላላባት ምድር ትሆናለች። ስለዚህም የትርፍ ጊዜ (part time) ትግል ለዚች ሀገር እንደማይመጥን አውቀን የመረጥነውን የትግል መስመር በቁርጠኝነት መቀጠል አለብን። በሰላማዊ ከሆነ በሰላማዊ፣ በትጥቅ ትግል ከሆነ በቦታው እታች ወርዶ መታገል ያስፈልጋል። ይህ ካለሆነ ግን የቁርጠኛ ልጆችን መንገድ በመሪነት ስም በመዝጋት በእጅ አዙር የወያኔ መንግሥት ዕድሜ እንዲራዘም ማገዝ አይገባም።

ትንሽ መልዕክት ለተስፍሽ (ተስፋዬ) ገብረአብ
በመጨረሻ ከላይ ስሙን ለጠቀስኩት ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የምለው አንድ ወንድማዊ ምክር አለ። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ አሁን በቅርብ ደግሞ ለላይፍ መጽሔት በሰጠው ቃለመጠይቅ ስለኤርትራ ለምን እንደማይፅፍ ተጠይቆ “ሰዎች የማላውቀውን እንድጽፍ ለምን ይጠብቃሉ” የሚል መልስ ሰጥቷል። ወይንም በሚቀጥለው መጽሐፉ በአንዲት ምዕራፍ እንደሚያወጋን ተናግሯል። እኔ ግን የቡርቃ ዝምታን የሚያክል መጽሐፍ ለመጻፍ አርባጉጉ ወይ በደኖ ካሳለፈው ጊዜ የበለጠ በኤርትራ ቆይቶዋል የሚል ግምት አለኝ። በእናቱ ኤርትራዊ ቤተሰብ ውስጥ ማደጉ የኤርትራዊያንን ሕይወትና ኑሮ ከሌላው ሰው በተሻለ የማወቅ ዕድሉ አለው። ለአንድ አይደለም ለዕድሜ ልኩ የሚበቃ መጽሐፍ የሚወጣው ግፍ በኤርትራ ምድር እየተፈጸመ ነው። ተስፍሽ ደራሲ ድንበር እንደማይወስነው ላንተ መንገር የለብኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለህ ማመንህም ቢሆን ስለጎረቤት ሀገር ህዝብ መበደል ስለመጻፍ ሊገታህ አይገባም። ብዕርህ ስለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት ብቻ ሳይሆን ስለመላው አፍሪካ ህዝብ መዘመር ይገባታል።
ይህቺን ትንሽ ጽሑፍ ከጫርኩ በኋላ በኢንተርኔት የተለቀቀውን “የስደተኛው ማስታወሻ” አነበብኩ። ሌላ ጊዜ በሰፊው ብመለስበትም አሁን ተስፋዬን አንድ ቀላል ጥያቄ መጠየቅ እፈልጋለሁ። አሁን ማን ይሙት ከአስመራ ተነስተህ እስከ ናቅፋ ተራራ በደራሲ ዓይን የታዘብከው አስፋልት የሚያቁዋርጡ የደረቁ ወንዞችን ብቻ ነው? አለምክንያት በየድንጋዩ ስር ውሃ እንዳጣ ዛፍ የጠወለጉ ወጣቶችን አላየህም? ወይንስ ያንተን መምጣት አስመለክቶ እንዳታያቸው ደብቀዋቸው ነው? ብዕርህ ደፋርና ግልፅ ናት ብዬ አስብ ነበር፤ ግን የዘር ልጉዋም ሳያደናቅፋት አልቀርም።
እኔ ጨርሼአለሁ።
ነፃነትና ሰላም ለመላው አፍሪካ ህዝብ!

ኢዮብ ይስኃቅ
eyobisack@yahoo.it  

ወ/ሮ አዜብ መስፍን Azeb Mesfin

Friday, 25 October 2013

ወደ ሶማሌ ክልል አቅንቶ የነበረው የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ቡድን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የመኪና አደጋ ገጠመው

ለሃገር ልማት ግንባታ እና የመንገድ ዝርገታ ሂደት የተሰኘውን ጉዙ ለማየት ከአዲስ አበባ ወደ ሶማሌ ክልል ያቀናው የወያኔ መንግስት ባለስልጣናት ቡድን በጉዞው ወቅት ከፍተኛ የሆነ የመኪና አደጋ ገጥሞት እንደነበር ምንጮቻችን ጠቁመዋል ።እንደምንጮቹ ገለጻ ከሆነ ባለስልጣናቱ እና የክልል አስተዳደር በአጠቃላይ ተሰባስበው የሚሄዱበት መኪና ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ይገልጻል ።በሶማሌ ክልል በቀብሪደሃር የደረሰው ይህንን አደጋ አስመልክቶ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል መዲያዎች እንዳይዘግቡት ተብሎ ማስጠንቀቂያ በቅርቡ ለነበሩት ድደህንነቶችም ሆነ ሌሎች ባለስልታናት የተገለጸ ቢሆንም ይህ ወሬ አፍትልኮ መውጣቱን ምንጫችን ይጠቅሳል ።ከ250 በላይ የሚሆኑትን ባለስልጣናት እና እንዲሁም ባለሃብቶችን የያዘውን አባሎች በብሄራዊ ቴሌቪዝን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበልበአብዲ ሞሃመድ ሁመር ጎዴ አየር መንገድ ጣቢያ ላይ የሚያደርጉትን የአቀባበል ስነ ስርአት የሚያሳይ ብቻ ምስል ማቅረባቸው የሚዘነጋ አልነበረም ሆኖም ግን ስለ ግጭቱ አንዳችም
ነገር ሊጠቆም አልተቻለም ።Somali Regional Chief Abdi Mahamoud Omar receiving the delegation led by DPM Demeke Mekonnen at Gode airport
የአደጋው መረጃ ተብሎ የተገለጸውም ብሄራዊ የኦጋዴን ግንባር የተሰኘው የተቃዋሚ ድርጅት በመንግስት ባለስልጣን ላይ በከፈተው የማጥቃት ዘመቻ ለማምለጥ ሲሉ ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨት አደጋው ሊፈጠር እንደቻለ መረጃው አጠናክሮ ይገልጻል ።ይሄው መኪና ምክትል ጠቅላይ ሚስንትሩን አቶ ደመቀ መኮንን ይዞ የነበርው መኪና እንደነበር የማለዳ ታይምስ ምንጮች አክለው ገልጸዋል ።
እንደ ዘገባው ከሆነ በወቅቱ ይህንን አይነት ጥቃት ሲፈጸምባቸው በፍጥነት ሊጠመዘዝ የሞከረው የምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ተሽከርካሪ በእግረኛ መንገድ ላይ ይጓዙ የነበሩ ሁለት ሰዎችን በመምታቱ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ መሆኑን እና የካሳ ክፍያ በጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ 300፣000 የሚጠጋ ብር ሊከፍሉ እንደፈለጉ እና በልመና ላይ እንደነበሩ አሳውቆአል ።በየጊዜውም በመንግስት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለማሳየት በተለያዩ መንግስታዊ ድርጅቶች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙት የኦጋዴን የተቃውሞ ሃይል ዛሬም እንቀጥላለን ሲሉ ዛቻቸውን በመንግስት ላይ አስፍረዋል ።ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ http://africaim.com/gov-source-refutes-ethiopias-deputy-pm-was-involved-in-car-accident/

ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ

ህወሃትን ገልብጦ “ከየትኛው ክልል ድጋፍ ሊገኝ?”

sebhat nega


ስብሃት ነጋ የኢህአዴግ አባትና ፈጣሪ የሆነው ህወሃት የመጨረሻው ታሪኩ ጠቦ እንደሚቋጭ ይፋ አደረጉ። ችግር የህወሃት ልዩ በረከትና ስጦታ እንደሆነ በማመልከት ህወሃት ውስጥ ልዩነትና መፈርከስ አደጋ ተከስቶ እንደማያውቅ ሸመጠጡ።
አቶ ስብሃት ጠቦ የሚጠናቀቀውን የህወሃት ስውር አጀንዳ የገለጹት ከጋዜጠኛ ደረጃ ደስታ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነበር። በኢህአዴግ የመከላከያ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈልና የኩዴታ አደጋ ሊያስከትል የሚችል አደጋ እንደተረጋገጠ ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ስብሃት “አዲስ አበባ መንግስት ገልብጠው የክልሎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ማን እሺ ይላል” በማለት ነበር የመለሱት። አንዴ በመከላከያ ውስጥ የመከፋፈልና የመበታተን አደጋ ሊያጋጥም የሚችልበት አግባብ እንደሌለ፣ ጠያቂው እንዳለው የመፈንቅለ መንግስት አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የህወሃት ስጋት እንዳልሆነ አስመስለው አቶ ስብሃት የመለሱት የክልሎችን ስም በመጥራት ተቀባይት እንደማይኖረው ነው። ይህም አባባላቸው እኛን ገልብጦ አገር አንድ አድርጎ መምራት አይቻልም የሚል እንደምታ ያለው ቢመስልም፤ “ሪፑብሊክ” ለመመሥረት የተነሳውና እስካሁን በነጻአውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን ህወሃት የመጨረሻ የመጥበብ ዓላማ በማስረጃ የገለጹበት ነው፡፡
ህወሃት “ኢህአዴግ” የሚባለውን ድርጅት ሲያበጀው የአገልግሎት ዘመን መድቦለት እንደሆነ ስለ ድርጅቱ የወደፊት መድረሻ ድንበሩ ከሚያወሱ የድርጅቱ የተለያዩ መረጃዎችና ነባር አባሎቹ መጠቆሙ ይታወሳል። ህወሃት 40ና 50 ዓመት ኢትዮጵያን በብሔር ፖለቲካና በዘር እያጋጨ ለመግዛት የሳለው ስዕል እንዳሰበው ካላዘለቀው እንዴት ጠቦ እንደሚጠናቀቅ የጠቆሙት ስብሃት፣ አስተያየታቸው አካሄዱ የገባቸውን በሙሉ አበሳጭቷል።
በ1997 የምርጫ ወቅት ተፈጥሮ በነበረውና በራሱ በቅንጅት ሰዎች ሽኩቻ በተኮላሸው ህዝባዊ ድል ግለት ወቅት ኢንዲያን ኦሽን የተሰኘው ጋዜጣ “ህወሃት ወደ ትግራይ የማፈግፈግ እቅድ ይዟል” በማለት የዘገበውን ዘገባ በማስታወስ በአቶ ስብሃት መልስ ላይ አስተያየት የሰጡ፤ በቅድሚያ አቶ ስብሃትን “አቦይ ብላችሁ አትጥሩት። አባታዊ አንደበትና ምግባር የለውም” በሚል ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ “የስብሃት ንግግር ህወሃት ታሪኩ ሲጠናቀቅ ጠቦ እንደሚቋጭ ነው። ለዚህ ሲል ነው ህዋሃት ከአንቀጽ 39 ጋር ቅበሩኝ የሚለውና የአማራ ክልል መሬትን እየዘረፈ የመውጫ ቀዳዳ ፍለጋ ሌት ከቀን መሬት እየቆረሰ አዲስ ካርታ የሚያመርተው፤ ዓለምአቀፋዊ ድንበርም ለትግራይ እንዲኖራት ያደረገው” ብለዋል።
“ህወሃት ካለውና ከተፈጠረበት  ክፉ ዓላማ አንጻር በቀጣይዋ ኢትዮጵያ ‘ቦታ አይኖረኝም’ የሚል ድምዳሜ ላይ ስለደረሰ ሁልጊዜ ሲጨንቀው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ስዕል ያሳያል። የስብሃትም ንግግር ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው” በማለት ምልከታቸውን የተናገሩት የጎልጉል የዘወትር አስተያየት ሰጪ “ውሳኔውና ህልሙ ስኬት የናፈቀው የቅጥረኞቹ የህወሃት ሰዎች ጭንግፍ ምኞት ቢሆንም መላው የትግራይ ህዝብ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥርት ያለ አቋም በመያዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚቆም መሆኑን ማሳየት እንደሚገባው” አመልክተዋል።azeb 3
ከህወሃት ሊቀመንበርነታቸውና ከስራ አስፈጻሚነታቸው አራት ጊዜ ማመልከቻ በመጻፍ በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ያመለከቱት ስብሃት ነጋ በኤፈርት ጉዳይ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ስምምነት እንዳልነበረቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። አያይዘውም ህወሃት የመከፋፈል አደጋ አጋጥሞት እንደማያወቅ፣ እንዲያውም በየጊዜው የሚነሱ የሃሳብ ልዩነቶች የድርጅቱ ልዩ ስጦታውና በረከቱ አንደሆነ ተናግረዋል። ልዩነትና በልዩነት ጥግ ድረስ ደርሶ መፋጨት የህወሃት የጥንካሬው መሰረት እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ስብሃት በድህረ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ህወሃት ለሁለት ተከፍሎ አደጋ ላይ የወደቀበትን ጊዜ አስተባብለዋል። እነ አቶ ስዬንም “የተባረሩ” ሲሉ አቅመ ቢስ አድርገው ስለዋቸዋል።
ኤርትራ ራሷን በወጉ መከላከል እንኳ የማትችል አገር እንደሆነች የጠቆሙት ስብሃት ኤርትራን ተማምኖ የሚከናወን የተቃውሞ ትግል የጤና ነው ብለው እንደማያምኑ “እብደት ነው” በማለት ኢህአዴግም ሆነ እሳቸው በእንቅስቃሴው ላይ ስጋት እንደሌለባቸው ለመግለጽ ሞክረዋል። ስብሃት በአሜሪካ ከተለያዩ ወዳጅ ሚዲያዎች ጋር እየተወደሱ ጥያቄና መልስ ያካሄዱ ሲሆን በተለይም ስለ መለስ ቅንድብ ከዘፈነው ሰለሞን ተካልኝ ሲቀርቡላቸው የነበሩት ጥያቄዎች የሚያዝናኑ ነበሩ። ጥያቄና መልሱን የተከታተሉ “ጠያቂው መልሱን አስቀድሞ ጥያቄ ማስከተሉ ጥሩ ተማሪ መሆኑንን በማረጋገጥ የምስክር ወረቀት የፈለገ አስመስሎታል” ሲሉ የለበጣ አስተያየት በማህበራዊ ገጾች ላይ አስፍረውበታል። አቶ ስብሃት በአሜሪካ ከጠባቂዎቻቸው ጋር በመሆን መደባደባቸውና በፖሊስ ይፈለጉ እንደነበርም መዘገቡ ይታወሳል። አቶ ስብሃት ከፖለቲካው ፈላጭ ቆራጭነት ወጥቻለሁ ቢሉም የሚሰጡዋቸው አስተያየቶችና ትንቢቶች አሁንም “የህወሃት የኋላ ዘዋሪ” እንደሆኑ አመላከች እንደሆነ ተጠቁሟል።

የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ Journalist Dawit Kebede
“እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው” ሀገር ቤት ያሉ ጋዜጠኞች

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 25, 2013)፦ በሀገር ቤት ይታተም የነበረው “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ እና የድረ ገጹ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሁለት ዓመት በሰሜን አሜሪካ የስደት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚበር ገለጸ። በጉዳዩ ላይ ከአቶ ያሬድ ጥበቡ ጋር በቪዲዮ ቃለምልልስ አድረጓል።
የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ዛሬ ከዋሽንግተን መነሳቱንና ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ገልጸዋል። የጋዜጠኛ ዳዊት ውሳኔን አስመልክቶ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ከኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የዚህ ዜና አጠናካሪ አነጋግሯል። እነዚሁ በሀገር ውስጥ የሚገኙት ጋዜጠኞች ዜናውን አለመስማታቸውን ገልጸው፤ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አስተያየት ሲጠየቁ፤ “እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው” በማለት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት በተለይ በመንግሥት እና በደጋፊዎቹ መገናኛ ብዙኀን ከፍተኛ የሥም ማጥፋት ዘመቻ፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲሰነዘርበት ስለነበር ለስደት መዳረጉንና በአሜሪካ ጥገኝነት ጠይቆ እንደነበር ይታወቃል። ጋዜጠኛ ዳዊት በዚሁ ቃለምልልሱ፤ “ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው፤ እነዚያን ጫናዎችና ፈተናዎች መቋቋም ይቻል ነበር ብዬ አምናለሁ። ያኔ የተሳሳተ ምርጫ አድርጌአለሁ” ሲል ገልጿል።
ከሀገር ቤት ሳይወጣ በፊት በእሱ ላይ ተከፍተው ለነበሩት ዘመቻዎች መንስዔ ነው ብሎ የሚያምነው፤ በሥልጣን ላይም ሆነ በተቃዋሚው ጎራ ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች በሚዲያው ጠንከር ያለ ትችት ሲሰነዘርባቸው ትችቱን ያለመታገስና የመቋቋም ክህሎት ስለሚያንሳቸው ነው ሲል ጋዜጠኛ ዳዊት ገልጿል።
ዛሬ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጠኞች እስር ቤት እያሉ ወደ ሀገር ቤት መመለሱ “ኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬስ ነፃነት አለ” ለማሰኘት ነው በሚል ትችት ቢቀርብበት ያለውን ምላሽ ሲጠየቅ፤ የአውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት ዓለሙ እሱ ከመሰደዱ ከ5 ወር በፊት መታሰራቸውን፣ እስክንድር ነጋ ደግሞ ከመሰደዱ 3 ወር በፊት መታሰሩን ገልጾ፤ የእሱ ወደ ሀገር ቤት መመለስ እንደቅድመ ሁኔታ ሆኖ መታየት የለበትም ብሏል።
“እኔ በግሌ በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ እንዳለ አንድ ዜጋ የበኩሌን አስተዋጽዖ ማድረግ የምችለው (ውጤታማም ሆነ አልሆነ) ኢትዮጵያ ውስጥ በማኅበረሰቡ መሃል ሆኜ ነው የሚል ቁርጠኛ ሃሳብ ነው ወደ ኢትዮጵያ እንድመለስ ያደረገኝ እንጂ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፕሬስ ነፃነት ከመሻሻሉና ካለመሻሻሉ ጋር አይደለም። ከመሰደዴም በፊትም የታሰሩ ጋዜጠኞች ናቸው፤ አሁንም ስደት ላይ ሆኜም፣ በምመለስበት ጊዜም እስር ቤት ያሉ ጋዜጠኖች ናቸው። ስለዚህ መሻሻልን ያሳያል በሚል እየሸሸን የምንቀር ከሆነ፤ ተገቢ አይመስለኝም።” በማለት ለጥያቄው ምላሽ ሰጥቷል።
ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በሚኖርበት በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ በፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ግለሰቦች፣ ከተለያዩ ድረ ገጾችና የመገናኛ ብዙኀን፣ … ጠንከር ያለ ትችት ሲሰነዘርበት፣ የሥም ማጥፋት ውንጀላ ሲደርስበት መቆየቱ፣ እሱም እሰጥ አገባ ውስጥ መግባቱ፤ ወደ ሀገር ቤት በመግባቱ ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ እንዳላሳደረበት ገልጿል።
እ.ኤ.አ. 2010 ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የሲ.ፒ.ጄ.ን ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት የተሸለመ ሲሆን፣ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ በወቅቱ “ኀዳር” የተሰኘውን ጋዜጣ በዋና አዘጋጅነት ሲሠራ ስለነበር ከቅንጅት መሪዎች ጋር የዕድሜ ልክ እስራት ከተፈረደበት በኋላ በ”ይቅርታ” መለቀቁ አይዘነጋም።
ባላፉት ሁለት ዓመታት በስደት በቆየበት በሰሜን አሜሪካ በተለይም ከኢትዮ ሚዲያ ድረ ገጽ ጋር ለረዥም ጊዜ የዘለቀ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው እንደነበር አይዘነጋም። ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በተለይ በኢሳት እና በግንቦት 7 ላይ ይሰነዝር የነበረው ትችት ከብዙ ወገኖች ጋር አቋስሎት የነበረ ሲሆን፣ የገዥው ፓርቲ ደጋፊ ነው እስከመባል ከመድረሱም በላይ እስካሁን ድረስ አከራካሪ ከሆኑ ግለሰቦች ውስጥ አንዱ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።
አቶ ያሬድ ጥበቡ ከጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ያደረገው ቃለምልልስ ከዚህ በታች ቀርቧል።(ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን 

Wednesday, 23 October 2013

በሁለት የቀድሞ የህወሀት ባለስልጣናት ቤቶች በርካታ የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን አቃቢ ህግ ገለጸ

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ህግ አንድ ግለሰብ ከመንግስት በማስፈቀድ አንድ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲይዝ ቢፈቀደልትም ፣ በተግባር ግን አብዛኛው ህዝብ በመሳሪያ አሰሳ ስም የግል መሳሪያውን መቀማቱን በተለያዩ የመገናኛ ብሀን ሲዘገብ ቆይቷል።
በ1997 ምርጫ ወቅት የአንድ ብሄር አባላት በገዢው ፓርቲ ህወሀት  ራስን የመጠበቂያ መሳሪያ እንዲታደላቸው መደረጉ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል።
የፌደራል አቃቢ ህግ በቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋ/ዳይሬክተር መላኩ ፋንታ መዝገብ ላይ ባቀረበው ክስ፣ በህወሀቱ አባል ምክትል ዳይሬክተሩር አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት ውስጥ 2 ታጣፊና ባለእግር ክላሾች፣ 4 ማካሮቭ ሽጉጦች፣ 2 ኮልት ሽጉጦች፣እና አንድ ስታር ሽጉጥ በድምሩ 9 የጦር መሳሪያዎች መገኘቱን ጠቅሷል።በሌላው የህወሀት አባል በ24ኛው ተከሳሽ በቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ በነበሩት በአቶ ወልደስላሴ /ሚካኤል ቤት ደግሞ 2 ባለሰደፍና ታጣፊ ጠመንጃዎች፣ አንድ ኡዚ ጠመንጃ፣ አንድ እስታር ሽጉጥ፣ አንድ የጭስ ቦንብ እና የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ መገኘቱ ተገልጿል።
ግለሰቡ ከቀድሞው ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር የጠበቀ ቁርኝት እንዳላቸው  በተቃራኒው ደግሞ ከደህንነት ሚኒስትሩ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ለእስር መዳረጋቸው በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ሲዘግብ ቆይተዋል።
 በተመሳሳይ ሴና ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ፋንታ ባለትዳር በማማገጥ ወንጀል አቃቢ ህግ ክስ እንደመሰረተባቸው ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግባል። ዐቃቤ ህግ  አቶ መላኩ የስራ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ለስራ ጉዳይ የመጣችን ሴት፤ ትዳሯን ፈታና በትዳር ውስጥ ያፈራቻቸውን ሦስት ልጆች በትና አብራቸው እንድትሆን አድርገዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ብሎአል።  ሰንደቅ አቃቢ ህግን ጠቅሶ እንደዘገበው ” ወ/ሮ መቅደስ ለማ የተባሉት እኚሁ ሴት የቀድሞ ባለቤታቸውን ንብረት የሆነውን ሳንክቸሪ ኢንተርናሽናል ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር በ2001 ዓ.ም የስራ ግብር ለመክፈል ወደገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሲሄዱ 144 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸውና በዚህም ምክንያት አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለአንድ አመት ከ4 ወር መጉላላታቸውን ለማስረዳትና መፍትሄ ለማግኘት ወ/ሮ መቅደስ ለማ የአቤቱታ ደብዳቤ ይዘው ወደተከሳሹ ዘንድ በቀረቡበት ወቅት የፍቅር ግንኙነት” ጀምረዋል።  ተከሳሽ የነበረውን ስልጣን መከታ በማድረግ ባለጉዳዩዋ ቀደም ሲል ከከፈሉት ብር ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ብር ተመላሽ እንዲሆን አድርጓል፤ በትዳር ውስጥ ያለችን ሴትም አማግጧል ሲል አቃቢ ህግ ክስ አሰምቷል።
ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ “በጋብቻ ውስጥ ያለችን ሴት በመንግስት ተሽከርካሪና ነዳጅ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ክብረ በዓል ላይ እንድትገኝ ከማድረጉም በላይ ቀኑ በውል ባልታወቀበት ዕለትም፤ በጋብቻ ውስጥ የነበረችው መቅደስ ለማን በግል ሾፌሩ አማካኝነት ወደ ባህርዳር ከተማ እንድትሄድ በማድረግ ሰመርላንድ ሆቴል ለአንድ ሳምንት አብረው እያደሩ እና በሾፌሩ አማካኝነት ከተማ ውስጥ እንድትዝናና ” አድርጋል ብሎአል።
አቃቢ ህግ ባቀረባቸው በርካታ የወንጀል ዝርዝሮች ውስጥ የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲንና በጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሚመራው በመከላከያ ውስጥ የሚገኘው የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን እቃዎች ያለቀረጥ እንዲገባላቸው ቢደረግም፣ ሌሎች ኩባንያዎች ሲከሰሱ ሁለቱ ድርጅቶች እና የኩባንያው መሪዎች አልተከሰሱም። አቃቢ ህግ እነዚህ ሁለት ግዙፍ ኩባንያዎች በሙስናው ውስጥ እንዳሉበት መረጃ ቢኖረውም ለመክሰስ ለምን ፈቃደኛ እንዳልሆነ አልታወቀም።

20 ሚሊዮን ገደማ የፈጀው ስታዲየም 3 አመት ሳይሞላው ፈረሰ

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ 13ኛውን የአርብቶ አደሮች ቀን ለማክበር ደቡብ ኦሞ ዞንን ለማክበር በተገኙበት ወቅት ለእርሳቸው ክብር መገለጫ እንዲሆን እስከ 20 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ የሚነገርለት ስታዲያም  በጅንካ ከተማ ተስርቶላቸው ነበር።
ይሁን እንጅ ስታዲየሙ ሶስተኛ አመቱን ሳይደፍን ለሁለተኛ ጊዜ ፈርሷል። በመጀመሪያ ከክቡር ትሪቡኑ በስተቀኝ በኩል ያለው ክፍል ፈርሶ ጥገና ሲደረግለት፣ አሁን ደግሞ ክቡር ትሪቡኑ ጥቅምት 10 ቀን ሙሉ በሙሉ ፈርሷል።
ስታዲየሙ አቶ መለስ ሊመጡ ነው  በሚል በ20 ቀናት ውስጥ በይርጋለም ኮንስትራክሽን መገንባቱ ታውቛል።
በሌላ ዜና ደግሞ በጅንካ ከተማ የሚኖሩ በተለይ የኮንሶች ተወላጆች ቤቶች እንዲፈርስ መደረጉን የዞኑ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው ገልጸዋል።
የከተማው አስተዳደር አናፈርስም ብለው ቃል ቢገቡም እንደገና ወደ ማፍረሱ እንደገቡ አቶ ስለሺ ተናግረዋል።
ጀንካ ውስጥ ኮንሶ እየተባለ የሚጠራ ሰፍር ሲኖር፣ ብዙዎቹ የኢህአዴግን የፖለቲካ አቋም ስለማይደግፉና የግንባሩ አባል ለመሆን ብዙዎች ፈቀደና ባለመሆናቸው ብቀላ እንደተወሰደባቸው አቶ ስለሺ ተናግረዋል በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ስታዲየሙ አቶ መለስ ሊመጡ ነው  በሚል በ20 ቀናት ውስጥ በይርጋለም ኮንስትራክሽን መገንባቱ ታውቛል።
በሌላ ዜና ደግሞ በጅንካ ከተማ የሚኖሩ በተለይ የኮንሶች ተወላጆች ቤቶች እንዲፈርስ መደረጉን የዞኑ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ስለሺ ጌታቸው ገልጸዋል።
የከተማው አስተዳደር አናፈርስም ብለው ቃል ቢገቡም እንደገና ወደ ማፍረሱ እንደገቡ አቶ ስለሺ ተናግረዋል።
ጀንካ ውስጥ ኮንሶ እየተባለ የሚጠራ ሰፍር ሲኖር፣ ብዙዎቹ የኢህአዴግን የፖለቲካ አቋም ስለማይደግፉና የግንባሩ አባል ለመሆን ብዙዎች ፈቀደና ባለመሆናቸው ብቀላ እንደተወሰደባቸው አቶ ስለሺ ተናግረዋል በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

በቅርቡ ከቴሌ ጋር ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ውል የተፈራራመው የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ንብረት ሊወረስ ነው

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ኩባንያው ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ እቃዎችን ታክስ ሳይከፍል በቴሌ ስም ሲያስገባ በመገኘቱ ንብረቱ እንዲወረስ እንደሚደረግ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል።
ቴሌ ለኩባንያው እቃዎችን እንዲያስገባ ፈቃድ አለመስጠቱን በመግለጹ ችግሩ ይፋ መውጣቱን ጋዜጣው ዘግቧል።
ሁዋዌ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በአይነት ከ235 በላይ እቃዎችን አስገብቷል፤
ይኸው ኩባንያ ከሶስት ወር በፊት የማስፋፋት ስራ ለመስራት በሚል የ800 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከቴሌ ጋር መፈራረሙ ይታወሳል።

ዶ/ር መረራ የፍንዳታውን ዜና “እንጠራጠረዋለን” አሉ

"በአዲስ አበባው ፍንዳታ የሞቱት ኢትዮጵያዊያን ናቸው"
bole 1


በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ሰፈር የደረሰውን ፍንዳታ አስመልክቶ ኢህአዴግ ያሰራጨውን ዜና የሚቃረኑ መረጃዎችና አስተያየቶች ቀረቡ። ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ አስተያየት ሲሰጡ ዶ/ር መረራ “አትፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም” ሲሉ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በፍንዳታው የሞቱት ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ስም ገልጾ የኢህአዴግን ዜና አጠጥሎታል።
በፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቁት ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚታሙ ፓርቲዎች “የጸረ ሽብርተኞች አዋጅ ሊጠናከርና ሊጠብቅ ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የኢራፓ፣ የኢሴዳፓ፣ ቅንጅትና አዲአን ተወካዮች በየተራ የኢህአዴግን ዜና የሚቃወሙና በጥርጣሬ የሚመለከቱትን አውግዘዋል። በወቅቱ የቴሌቪዥን ጣቢያውም አንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ጠርተውት በነበረው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ “የጸረ ሽብርተኛነት አዋጅ ለሌላ ተግባር መዋሉን እንቃወማለን” በማለት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ በማሳየት ዜናውን ለማጀቢያነት ተጠቅሞበት ነበር።
በግል አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው “ብዙዎች፣ እኔም ጓደኞቼም በጥርጣሬ ነው ያየነው” ሲሉ ከተቆረጠው ንግግራቸው ተደምጧል። ዶ/ር መረራ “አጥፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ ራሱን አያጠፋም” ካሉ በኋላ “ስለዚህ እውነት ተደርጓል?” የሚለው ትልቁ ችግርና የጥርጣሬው መነሻ እንደሆነ አመልክተዋል።
ስለዚህ በሚል ድምዳሜ “ሰው አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ስራ ነው” እንደሚል ዶ/ር መረራ በተቀነጨበው አስተያየታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል። በተቃራኒ ከላይ በስም የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማና የአልሸባብ ስጋት ላይ ያለች አገር በመሆኗ ኢህአዴግ ህዝብን የመጠበቅና ደህንነትን የማስጠበቅ አደራ ስላለበት እነሱን ጨምሮ እንዲጠብቃቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ የሚነሳውና በታጣቂ ሃይሉ ፈርጣማነት የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ  /ትህዴን/ በቦሌ ክፍለ ከተማ በቤት ውስጥ ፈነዳ በተባለው ፈንጂ ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸው ሁለት የሶማሌ ዜጎች አይደሉም ሲል ከሁሉም ወገን የተሰራጨውን ዜና በዜሮ አጣፍቶታ። በፈንጂው የሞቱት ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ስማቸውም “ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው” ሲል የገለጸው ትህዴን የሟቾቹ ስም በመታወቂያ መረጋገጡን አመልክቷል።የመታወቂያውን ቅጂ ግን በገጹ አላተመም። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በስፍራው ታይታችኋል በሚል በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን በመግለጽ የሶስት እስረኞችን ስም ይፋ ያደረገው ኦክቶበር 19 ቀን 2013 በራሱ ኦፊሳላዊ ድረገጽ ላይ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን ሞቱ የተባሉትን ሰዎች ይህ ዜና እስከተጻፈበት ቀን ድረስ በሰነድ አስደግፎ አላቀረባቸውም።
በሌላ በኩል ኦክቶበር16 ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 3ቀን 2006ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ማዞሪያና ቦሌ ሚካኤል መግቢያ አካባቢ በቦምብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው ሁለት ሶማሊያውያን ሽብርተኞች መሆናቸውን ማረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ማስታወቁን ዘግቧል።
Bomb-Blast-Addisየአንድ ግለሰብ ሰርቪስ ቤት ተከራይተው ከነበሩት ሶማሊያውያኑ መካከል፣ አንደኛው ከ20ቀናት በላይ የቆየ ሲሆን፣ ሌላኛው ፍንዳታው ከመድረሱ ከሁለት ሰዓታት በፊት የደረሰ መሆኑን ግብረ ኃይሉ ማረጋገጡን ያመለከተው ሪፖርተር ሽብርተኛ የተባሉት ሶማሊያውያኑ ካፈነዱት ቦምብ በተጨማሪ መጠናቸው ያልተገለጸ ቦምቦችና አንድ ሽጉጥ ከሁለት ካርታ ጥይት ጋር መገኘቱን፣ የፈንጂ ማቀጣጠያና የአደጋ መከላከያ ጃኬቶች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሊያና ቀበቶዎች መገኘታቸውም ጠቁሟል፡፡ ከሶማሊያውያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎችና የቤቱ አከራይ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄባቸው መሆኑንም ግብረ ኃይሉ አክሏል በማለት ሪፖርተር ዘግቧል። አዲስ አድማስ በበኩሉ አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነት መውሰዱን አድራሻው አልተመዘገበ የትዊተር ማረጋገጫ በማመላከት ከዚህ በታች ያለውን ዜና አስነብቧል።
ባለፈው እሁድ በቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ሁለት ተጨማሪ የፍንዳታ ጥቃት ለማድረስ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ቡድን እንደዛተ የገለፀው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ የዛቻው ተአማኒነት ባይረጋገጥም በኢትዮጵያ የሚገኙ አሜሪካዊያን ጥንቃቄ እንዳይለያቸው ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ በመግለጽ ዜናውን የከፈተው አዲስ አድማስ፣ “የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ቡድኖች ግጥሚያ በሚካሄድበት ሰዓት ጥቃት ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ሁለት ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በማወጅና ሽብር ለመፈፀም በመዛት የሚታወቀው አልሸባብ “ድርጊቱ በኔ አባላት የተፈፀመ ነው” ብሏል በማለት አልሸባብ በቦሌ ሚካኤል ለተከሰተው ፍንዳታ ሃላፊነት እንደሚወስድ በትዊተር እንዳስታወቀ ማሰራጨቱን፤ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አካባቢ የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እንደዛተም ገልጿል፡፡
በቦሌ ሚካኤል በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተከሰተው ፍንዳታ ሁለት የሶማሊያ ተወላጆች መሞታቸውን የገለፀው ፖሊስ፤ ከሟቾቹ አንዱ የኢትዮጵያ ማሊያ በመልበስ ከኳስ ተመልካቾች መሃል የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደነበር መጠቆሙን አዲስ አድማስ በዜናው አውጇል። አዲስ አድማስም ሆኑ ሪፖርተር ፖሊስ የነገራቸውን ከመዘገብ ውጪ ከሌሎች ሚዲያዎች፣ በተለያዩ ማህበረ ገጾችና በቅርበት ከህብረተሰቡ የሚሰጡትን አስተያየቶች አስመለክቶ ዜናውን ላቀበላቸው ክፍል አላቀረቡም።
የኢህአዴግ አንደበትና የንግድ ድርጅት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የደረሰው የፈንጂ ፍንዳታ በሁለት ሶማሊያውያን አሸባሪዎች የተፈፀመ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አብዩን ጠቅሶ አስታውቋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳለው ፍንዳታው የደረሰው በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ቀበሌ 01 በተለምዶ ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በአንድ የመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። ፖሊስ ፍንዳታው ፈንጂ መሆኑንና በጥቅም ላይ የዋለው ቲ ኤም ቲ የተባለ የፈንጂ ዓይነት መሆኑን እንደደረሰበት አረጋግጧል። ፍንዳታውንም ሁለት ሶማሊያውያን ማቀነባበራቸውን ፖሊስ እንዳረጋገጠና ግለሰቦቹ የአሸባሪ ቡድኑ አልሸባብ አባል መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን ጄኔራል አሰፋ አብዩ መናገራቸውን የጠቆመው ፋና ከሁለቱ አሸባሪዎች መካከል አንደኛው ወገቡ ላይ የታጠቀና ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር የተዘጋጀ መሆኑን ያመላክታል ብሏል።
ሌላኛው አሸባሪ በሻንጣ ፈንጂ የያዘ ሲሆን፥ የፈነዳውም ፈንጂ በሻንጣው ውስጥ የነበረ መሆኑን ነው ጀነራል አሰፋ ያስረዱት። ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር ሲዘጋጅ የነበረው ግለሰብ የታጠቀው ፈንጂ ግን እንዳልፈነዳ አመልክተዋል። አሸባሪዎቹ በአጠቃላይ ሶስት ፈንጂዎችንም ይዘው ነበር። አሸባሪዎቹ ህዝብ ባለበት ስፍራ አደጋ ለማድረስ ተከራይተው በነበሩበት ቤት ውስጥ ሲዘጋጁ ፍንዳታው ደርሷል ብሎ ፖሊስ እንደሚጠረጥር ነው የጠቆሙት። ከአሸባሪዎቹ ጋር ፖሊስ የእጅ ቦምቦችንና ሽጉጥ ከነጥይቱ አግኝቷል።
የፋናን ዜና ተንተርሶ የተሰነዘሩ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ሪፖርተር በፈነዳው ፈንጂ ህይወቱ ያለፈው አንደኛው ሰው ሰውነቱ መበታተኑና የአይን እማኞችን ገልጾ መዘገቡን ያስታውሳሉሉ። ፈነዳ የተባለው ፈንጂ ከፈነዳ በሁዋላ አጥፍቶ ለመጥፋት የተዘጋጀው ሰው የታጠቀው ፈንጂ አለመፈንዳቱ መገለጹ ከሙያ አንጻር ጥያቄ የሚያስነሳ እንደሆነ፣ ከዚህም በላይ ድርጊቱን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ጋር ለማገናኘት የብሔራዊ ቡድን መለያ ሹራብ ተገኘ መባሉ ድርጊቱን ድራማ ያስመስለዋል ባይ ናቸው። (ፎቶ: ሪፖርተር)

ጎበዝ ምንድን ነው ነገሩ? – ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለ7 ሰዓታት በመብራት እጦት ሥራ አቁሞ ነበር

black_lion_hospitalየኃይለማርያም ደሳለኝ መንግሥት እንዴት ይጠየቃል? ከመሐመድ አሊ መሀመድ የገዥው ፓርቲ ልሳን እንደሆነ የሚታወቀው ፋና FM ሬዲዮ በቀትር የዜና እወጃው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከትናንት 10 ሠዓት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ የሆስፒታሉ ታክሚዎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አረዳን፡፡ ሬዲዮው የሆስፒታሉ ዲዝል ጄኔሬተርም

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

ህወሓት ኢህአዴግ ለምን ግን በልጆቼ ላይ ዘመተ?

   


የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጄ ክብሮም አስገደ እንደ ወንድሞቹ የእስር ሰለባ ሆነ፡፡ እኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ፉጹም ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደለሁም። መጀመርያ ደርግን 17 ኣመት በመታገል ፋሽሽታዊ ሥርዓትን በማስውግድ ኣስተዋፅኦ ነበረኝ። ህውሃት ኢህኣደግ ስልጣን ከያዘ በኋላም ለኑሮየ፣ ለደሞወዝ ሳላስብ 17 ኣመት ሙሉ የታገልኩለት ኣላማ ስለተቀለበሰ በተጨማሪ የህውሓት መሪዎች ለኢትዮጵያ ሉኣላዊነትና ኣንድነት ታማኝነት ስላጎደሉ የኢትዮጵያ ሕገመንግስት በሚፈቅደው መሰረት በግልም በፓርቲ ተደራጅቼ እየታገልኩ ቆይቼ ኣሁንም እታገላለሁ። ታድያ እኔ በሃገራችን ህገመንግስት በሚፈቅድልኝ መሰረት መታገሌ እንደ ሃጠያት ተቆጥሮ የቂም በቀል ፖለቲካ ሰለባነቱ ከኔ አልፎ ወደ ልጆቼ ወርዷል።
የማነ ኣስገደ ልጄ ምንም ሳይፈፅም በገጠር ቤተሰብ ለመጠየቅ ሄዶ ታስሮ ብዙ ግፍ ተፈፅሞበታል። በተፈፀመበት ግፍ ጠንቅ ታሞ እናቱ የመከላክያ ኣባል ስለሆነች በመከላክያ ሚኒስተር ሆስፒታል ብዙ ጥረት ተደርጎ ሊያድኑት ስላልቻሉ ወደ መቀሌ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከስልጣን በላይ ብለዉት ሂወቱ ተርፎ ኣሁንም በቤቱ የኣልጋ ቁራኛ ሆኖ ይገኛል፡፡ በተማረው መሰረት ለሃገሩ እንዳያገለግልም እንደማይሰራ ኣካል ጉዳተኛ ኣድርገዉታል። ወደ ውጪ ወስድን እንዳናሳክመው ኣቅም የለም፡፡
ኣሕፈሮም ኣስገደ ልጄም ከስራ ገብታው ኣፍነው ወስደው እነሆ በፖሊስ ጣብያ አስረውት ክስ ሳይመሰረትበት ከ6ወር በኋላ በቀዳማይ ወያኔ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎት ከ 15 ጊዜ በላይ ቀጠሮ ጊዜ እየተባለ ሲመላለስ ከርሞ በመጨረሻ ክሱ የዋስ መብት የሚከልክለው የፀረ ሙስና ኣንቀፅን ይመለከታል አሉ። በሙስና የተከሰሰ የዋስ መብት ኣይፈቅድም በሚል ሽፋን ልጄን ከእስር ቤት ነፃ ላለመልቀቅ ክሱ ወደ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በማዞር፤ የፀረ ሙስና ጉዳይ ደግሞ በወረዳ ስለማይታይ 6 ወር ሙሉ ሲያንገላቱት ከርመው ክሱ በመቀሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደ ኣዲስ ተመስርቶ በ 28/1/2006 ዓ.ም በዞኑ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ደግሞ ሌላ ተጠርጣሪ ስላለና ስለታጣ በጋዜጣ ኣሳውጀን እስከ ምንፈልግ ኣሕፈሮም በወህኒ ቤት ይግባ በማለቱ ልጄ ያለ ፍርድ በወህኒ ቤት ተወርውሮ ይገኛል የጊዜ ቀጠሮ እየተባለ 7 ወሩ በስቃይ ይገኛል፡፡
ሌላ ያሁኑ ይባስ። ክብሮም ኣስገደ የሚባል የ10ኛ ክፍል ተማሪ የስብእና መሳት ስነ ኣእምሮ ችግር ያለው ይህም በሃኪም ክትትል ላይ ያለ በፍርድ ቤትም ታይቶ ያደረ አስረውቷል። ኳስ ሜዳ እየተጫወተ እንዳለ ፖሊሶች መጥተው ወሰዱት። በኣንድ ጨለማ ቤት ለብቻው ኣስረው ከወላጆቹ ከሃይማኖት ኣባት፣ ከህግ ኣማካሪ እንዳይገናኝ ኣድርገው ኣፍነዉት ይገኛሉ። የምንሰጠው ምግብ ለማን እንደሚሰጥ ኣናውቅም። ለፍትህ ቢሮ ፖሊስ ኣዛዞች ኣመለከትን ፍትህ ኣልተገኘም። ዳኛ እንድያገናኙን በስልክ ነግሮዋቸው ፖሊሶች ኣልተቀበሉትም። ኣሁን ከ80 ሰኣት በላይ ታስሮ ቤተሰብ ልናገኘው ኣልቻልንም። ይህ ዘመቻ በእኔ የጀመረው ልጆቼም የግፍ ሰለባ ሆነዋል። የኔ ጉዳይም የህወሓት የ17 ኣመት ታሪክ በመፃፌ፣ ከኣንድ ዜግነቱ ኣሜሪካዊ ትውልድ ኢትዮጵያዊ በሰዎች የተቀናበረ ሴራ ተከስሼ 3 ኣመት ባስቆጠረ ክስ ላይ ነኝ ገና መቋጫ ኣላገኘም፡፡
ይህ ጉዳይ የእኔና የልጆቼ ብቻ ችግር ኣይደለም ብዙ የሚናገርላቸው ያጡ ዜጎች በስቃይ ላይ ይገኛሉ ስለሆነ ሁሉም ዜጎችና ለፍትህና ለዲሞክራሲ ለሰብኣዊ መብት የምትታገሉ ያላችሁ ተቃዋሚ ሃይሎችም ዝምታ ከመምረጥ ብትነጋገሩበትና ብትቃወሙት ጥሪየን ኣቀርባለው፡፡
በተለይ በኣሁኑ ጊዜ ኣንዳንድ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች የታሰረው ልጄ ኣሕፈሮም ኣስገደ ከታሰረበት ድረስ በመሄድ ・ኣባትህ ኣስገደ ተው ኣርፈህ ተቀመጥ፣ ትእግስት ኣድርግ በለው!・ እያሉ እስከማስፈራራት ድረስ ሄደዋል። ለዚሁ አንደ ምሳሌ ኮማንደር ገ/ሂወት ካሕሳይ የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ዋና ኣዛዠ ይጠቀሳል። በዛ በሰጠው ማስፈራርያ ታድያ ልጄ ኣሕፈሮም በትልቅ ስጋት ላይ ይገኛል ታድያ ከዝሂች ኣገር ኣገሬ የት ልሂድ ንፁህ ዜጋ ነኝ እና በዚህች ኣገር የዳኝነት እና የህግ የበላይነት መረጋገጥ ኣለበት ወተደራዊ ኣገዛዝ እንዳይደገም እንጠንቀቅ ፡፡
እባካችሁ የቂም በቀል ፖለቲካ ለልጆቻችን ኣናውርሳቸው ሰላም ፍትህን ዲሞክራሲን እናውርሳቸው፡፡

Sunday, 20 October 2013

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት አይሏል::

ethiopian_troops_pickup
ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገው ሩጫ ተቃውሞ ገጥሞታል::
ከፍተኛ ጄኔራሎች ምስጢራዊ ስብሰባዎችን አብዝተዋል::የምስጢራዊ ስብሰባ ቃለ ጉባዬ የምትይዝ የሆነችው የአንድ ከፍተኛ ጄነራል ጸሃፊ ትክዳ ወይም ትገደል አልታወቀም::ለሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል የተሰጠው የሌ/ጄ ማእረግ የታሰበው ሌ/ጄ ሳሞራን ይተካሉ ተብለው ለነበሩት ለሜ/ጄ አበባው ታደሰ የነበረ ቢሆንም በምን ምክንያት እንደተዘዋወረ አልታወቀም::
በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በከተማ እና በሌሎች የእዝ መምሪያዎችም መቀጠሉን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየኡ መሆኑ ተጠቁሟል::
ሰራዊቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሳው ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው:: በቅርቡ ከስልጣን ይነሳል የሚባለው ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን በሜ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀል ለመተካት የሚደረገውን ጥረት የብኣዴን ታጋይ መኮንኖች የተቃወሙት ሲሆን እኛም ከማንም ያላነሰ የታገልን ስለሆነ ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው ብኣዴን እያለው ለምን እንዲህ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አንስተዋል::
ከፓርቲ አጣብቂኝ ያልተላቀቀው የመከላከያ ሰራዊቱ የበላይ አመራር ህገመንግስታዊ መዋቅር እንዲይዝ ለማድረግ ምንም አይነት ስራ አለመሰራቱ በሰራዊቱ አዳዲስ መኮንኖች ዘንድ አቤቱታ ቢያስነሳም ጄኔራሎቹ የሚያደርጉት ምስጢራዊ ስብሰባ እንዴት መፍታት ሳይሆን ማክሸፍ እንደሚቻላቸው እየመከሩ ሲሆን አዳዲስ ወታደራዊ ደህንነቶችን በየእዙ አስርጎ በማስገባት እንዲሁም የሰራዊቱን አቤቱታ ያስተባብራሉ የሚባሉትን በስራ ምክንያት በየማእዘኑ በመበተን ለመስራት የታቀደ ሲሆን የአበታተኑን ሁኔታ በማስጠናት ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በተጨማሪ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ይረዳቸው ዘንድ ኮማንዶዎችን እና ንቁ የደህንነት ጠባቂዎችን ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ለመመደብ ተነጋግረዋል::
መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ምዽር ጦር መምሪያ እንዲሁም ደብረዘይት እና አስፈላጊም ሲሆን በመኖሪአ ቤቶቻቸው የሚያደርጉትን ስብሰባ ቃለጉባዬ የምትይዘው የአንድ ጄኔራል ጸሃፊ ከድታ ይሁን ተገድላ ሳይታወቅ ካለፈው ሳምንት ጀምራ በስራ ገበታዋ ላይ ያልተገኘች እና የት እንዳለች የማይታወቅ ሲሆን ስልኳም መዘጋቱን ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል::
ምንሊክ ሳልሳዊ

አቶ ስብሃት ነጋ ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ልዩነት እንደነበራቸው አመኑ

“ህወሓት መለስ ከነበረበት በጣም የጠነከረ ድርጅት ይሆናል” አቶ ስብሃት ነጋ
22
Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. Nov. 20, 2013)፦ ሰሞኑን በአሜሪካ ለሚገኙት የህወሓት መስራችና የቀድሞ ሊቀመንበር ለአቶ ስብሃት ነጋ የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ደረጀ ደስታ እስከዛሬ ተጠይቀው የማያውቋቸውን ጥያቄዎች አቅርቦላቸዋል። ቃለምልልሱን ጋዜጣው ላይ በቅርብ ይዞት የሚወጣ ሲሆን፣ ይኸንኑ ቃለምልልስ ለኢትዮጵያ ዛሬ በድምፅ ልኮልናል። ከተጠየቋቸው ጥያቄዎ ውስጥ ከህወሓት ማዕከላዊ አባልነት እንዴት ወደ ተራ አባልነት እንደተሻገሩ፣ ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ያላቸውን ጠብ፣ ከአቶ መለስ ጋር የነበራቸውን አለመግባባት፣ የአቶ መለስ ደካማ ጎን፣ ሙስኝነትን፣ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ላይ ያላቸውን ውግዘት፣ ስለፕሬሱ፣ … ይገኙበታል። (ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

Friday, 18 October 2013

A Somali-Norwegian man has been identified as a suspect in the Westgate Mall attack which left 67 people dead.

Fotor01018145042
A Somali-Norwegian man has been identified as a suspect in the Westgate Mall attack which left 67 people dead.
23 year old Hassan Abdi Dhuluhow is reported to have spent the early years of his life in Somalia before moving with his family to Norway in 1999.
The suspect was identified on CNN’s Newsnight from a CCTV footage of the attack which showed various parts of the Westgate Mall on the first day of the siege.
Norwegian authorities report that several of the suspect’s former classmates have also positively identified him on the footage.
The Norwegian Police Service say the suspect has been on their radar since he established contact with Profetens Ummah, a Norway-based Islamic group, in his high school days.
Presently, the whereabouts of the suspect is unknown. It is unclear if he escaped the building or was killed by Kenyan security forces during the raid to free hostages in the mall.
Investigators say charred bodies on the scene have been delivered to a morgue where they are expected to be identified in the next few weeks.
Although Norwegian authorities claim the suspect may have placed a call to his family from inside the mall, his relatives say the last time he made contact with them was in summer.
Since Kenyan authorities began investigating the attack, there have been numerous speculations about the identifies the attackers. Earlier there were reports that about 15 suspects carried out the attack, this number was subsequently reduced to 6 and later 4. The names of 4 suspects the authorities had released also turned out to be nom de guerres.
The Norwegian Police Service says investigators were sent to join Kenyan officials in uncovering the identities of the attackers after reports revealed that a Norwegian citizen was involved in the attack. Investigators are apparently trying to trace any connections between Hassan and other terrorist groups or individuals in Norway and Somalia – where he is said to have frequented in the past few years.
The identification of Hassan gives some weight to numerous speculations by witnesses that the attackers at the mall included foreign nationals.
Increasingly, Islamic extremist groups, including Al Shabab, have made several attempts to expand their recruitment fields to include communities populated by African immigrants in Europe and the United States.

ወያኔና አሸባሪነት ምንና ምን ናቸው


26351fb59e29fb0a1375427042የወያኔ ጉጅሌ ሰሞኑን የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ በእጅጉ ሊያስቅ የሚችል ቧልት ላይ ተጠምዷል። የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ሳይቀር ህብረተሰቡን በየተቋሙና በየመኖሪያው እየሰበሰበ ስለሽብርተኝነት ማብራሪያና ገለፃ በመስጠት ዜማ ላይ ተጠምዷል።
የወያኔ የሽብረተኝነት ገለፃ ዘመቻ ሚስጥር ደግሞ ብዙ ምርምር የሚሻ አይደለም። የሀገራችን ሰዎች ዶሮ ጭራ ልታወጣው የምትችል የሚሉት አይነት ሚስጥር ነው። አላማው ነጻነት አማረኝ፣ እምቢ ዘረኝነት እና ቢያንስ መሰረታዊ ሰበአዊ መብቴ ይገባኛል በማለት መብቱን እየጠየቀ የመጣው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ታይቶታል።
የማእበሉ የመጀመሪያ ንቅናቄዎች ከወዲያ ወዲህ መታየት ጀምረዋል። የገለፀው ሽርጉድ ዋና አላማ ይህ መብቱን የሚጠይቅና አጎንብሶ መኖር የሰለቸው ህዝብ ለመብቴ የማደርገውን ትግል ሽብርተኛ ያስብለኛል ብሎ እንዲፈራና ይበልጥ እንዲያጎነብስ መሆኑ ነው። ይህን ደግሞ ህዝቡ አውቆታል። ሰሞኑን በአለምያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለገለፃው ለመጡ ካድሬዎች የሰጧቸው አጸፋዊ ገለጻ ይህንኑ ያሳያል፡፡
ሽብርተኝነት አንድና በነጻነትና በዴሞክራሲ ለመኖር የሚመኝና የወሰነን ህዝብ ሰላም በመንሳት የፖለቲካ አላማዪን አሳካለሁ ብለው የሚያምኑ ቡድኖችና ድርጅቶች የፖለቲካ መሳሪያ ነው። የወያኔ መሪዎች የሽብርተኝነት ትርጉም አልገባቸው ከሆነ ሰብስብ ብለው መሰዋእት ፊት ቢቆሙ ሽብረተኝነትን አፍጥጦ ሊያዩት ይችላሉ፡፡ ሽብርተኛው ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው።
ህዝቡ ፊት በቆሙ ቁጥር ግን ህዝቡ ሽብርተኞችን ያያል። ሰለባውን ለማስተማር መሞከር ለእናት ምጥ የማስተማር ያህል ነው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ሁሉንም የዲሞክራሲና የሰላም ጥያቄ ሁሉ በጉልበትና ባፈና የደፈጠጠ አሸባሪ ቁጥር አንድ ወያኔ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከሽብር ጋር የመረረ ችግር ላለባቸው ሀገሮች ሎሌነት ገብቶ ሌሎች ሽብርተኞችን ወደሀገራችን የሚጎትተው ራሱ ወያኔ ነው።
ዛሬ በማንም የባእድ አሸባሪ በህዝባችን ላይ ለሚደርስ ጉዳት ዋናው ተጠያቂ ወያኔ የሚሆነውም ለዚህ ነው። ለምእራብያውያን ጸረ ሽብር አጋራችሁ ነኝ እያልኩ ራሴ በምገዛው ህዝብ ላይ የምፈጽመውን ሽብር እንዳለ ያዩልኛል፣ ፍርፋሬም አገኝበታለሁ በሚል ስሌት የተገባበት መሆኑንም የማያውቅ ኢትዮጵያዊ ቁጥሩ ትንሽ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡- ነጻነት የናፈቀህ፣ አጎንብሶና በገዛ ሀገርህ ተዋርዶ መኖር የሰለቸህ፣ በወያኔ ተሰደህ በባእድ ሀገር የምትሰቃይ፣ የምትሞት የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ወያኔዎች ከግፍ አልፈው ሊቀልዱብህ፣ በቁምህ ሊገሉህ፣ ሊከፋፍሉህ አይገባም። ወያኔ የፈሪ አብራሪ ነው። አሻፈረኝ ሲሉት እንጂ ቢሸሹለት በቃኝ ብሎ አይመለስም፡፡
ግንቦት 7 ንቅናቄ እንደሁልግዜው ዛሬም ወገን ሆይ፡- የሀገርህን ህልውና ለመታደግ ተነሳ፣ ተቀላቀለን፤ የመከራችንን ቀን አጭር እንደርገው ዘንድ ጸሃይ ሳትገባብን፣ ሳይመሽብን ኑ ተቀላቀሉን የሚለውን ጥሪ ዛሬም አጠናክሮ ያቀርብልሃል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ሃበሻው ዶክተርና ልጁ – በአሜሪካ (አርአያ ተስፋማሪያም)

ww

ዶ/ር ጳውሎስ ይባላል፤ ሃበሾችን ጨምሮ የሚያውቁት በርካታ ወገኖች ስለዶ/ር ጳውሎስ ተናግረው፣ አድናቆትና ምስጋናቸውን ሰጥተው አይጠግቡም። በዲሲ ከተዋወቅኳቸው እጅግ መልካም ሰዎች አንዱ ነው። ትብብር ለጠየቁት ሁሉ የነፃ ህክምና እርዳታ ያደርጋል። በተለይ የቁርጥማትና አጥንት ወዘተ ሕመም ለሚያሰቃያቸው በዘመናዊ መሳሪያ ፈውስ ይሰጣል። እረፍት በሆነ ቀን የህክምና መሳሪያውን እንደያዘ ነው የምታገኘው። « ገንዘብ እንክፈልህ..» የሚል ጥያቄ በጭራሽ መስማት አይፈልግም።..በአብዛኛው ከመናገር ይልቅ ማድመጥን ያዘወትራል። ለወገኖቹ አዛኝ፣ እንዲሁም አገሩን የሚወድ ሰው ነው። ንግግሩ ቁጥብ ነው፤ ከእርሱ ጋር ቁጭ ስትል ብዙ የህይወት ልምዶችን ትቀስማለህ።
ዶ/ር ጳውሎስ በመደበኛ ስራው ከአሜሪካ መንግስት ጥሩ ክፍያ ያገኛል። የተቸገሩ ወገኖችን በገንዘብ ጭምር ይረዳል። በደርግ ዘመን የኢህአፓ አባል ነበር። በትግል ተፈትኗል፣ እስርና ስቃይን ቀምሷል።…የዶ/ር ጳውሎስ ልጅ ሮቤል ይባላል፤ በትግል አብራው ከነበረች የቀድሞ ፍቅረኛው በአሜሪካ ተወልዶ ያደገው የ19 አመቱ ወጣት ሮቤል ከወላጅ እናቱ ጋር በቦስተን ይኖራል። …ከ6 ወር በፊት አፕሪል 15 ቀን 2013 በቦስተን ከተማ አስደንጋጭ ነገር ይከሰታል። በእለቱ ኢትዮጲያዊያን አትሌቶች በድል አድራጊነት ያጠናቀቁበት የማራቶን ውድድር ላይ ሁለት ወንድማማቾች ቦንብ በማጥመድ ንፁሃንን ገደሉ፣ በመቶዎች አቆሰሉ።..ድርጊቱ ከተፈፀመ ከሶስት ቀን በኋላ በርካታ የF.B.I አባላት መሳሪያ ወድረው፣በጎማ የሚንቀሳቀስ ታንክ አስከትለው የነሮቤልን መኖሪያ ይከባሉ። በር ሲቆረቆር… ወላጅ እናት ባየችው ነገር ክው ብላ ትደርቃለች።
ከተፈፀመው የሽብርተኝነት ድርጊት ጋር በተያያዘ ሮቤል ተጠርጥሮ እንደሚፈለግ ገልፀው ..ይዘውት ይሄዳሉ። አራት ቀን ለታሰረው ሮቤል ሶስት ታዋቂ ኢትዮጲያዊያን ጠበቆች ጥብቅና ሊቆሙለት ፈቃደኝነታቸውን አሳዩ። ..ከሁለቱ የድርጊቱ ፈፃሚ ወጣቶች አንዱ እነሮቤል መኖሪያ ቤት መጥቶ መፅሃፍ ሲቀበለው የሚያሳይ ቪዲዮ በምርመራው የቀረበ ቢሆንም፣ የሶስተኛ አመት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነው ሮቤል ከዚህ ወጣት ጋር አብረው የሚማሩ የት/ቤት ጓደኛሞች መሆናቸውንና የሰጠውም መፅሐፍ የትምህርት እንደሆነ መፅሐፉን -ጭምር በማቅረብ ያስረዳል። ..የምርመራ ቢሮው ይህን ከተገነዘበ በኋላ ነበር – በ4ኛው ቀን እንዲፈታ ያደረገው።..ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ በመሆኑ ሮቤል በመኖሪያ ቤቱ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ።
በአንዱ እግር ብቻ (እንደ እጅ ሰአት የሚታሰር አይነት) “tether ankle monitor” የሚባል ኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ ተጠልቆለታል። ይህ መሳሪያ የሚገጠምለት ሰው ከተፈቀደለት ክልል ውጭ አልፎ ከሄደ መሳሪያው ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣል፣ በደቂቃዎች ውስጥ ፖሊስ ይደርሳል።…ዛሬ አርብ ኦክቶበር 18 ቀን ሮቤል ፍ/ቤት ይቀርባል።….ዝርዝር ጉዳዩን ያጫወተኝ ወላጅ አባቱ ዶ/ር ጳውሎስ፣ በመከፋት ስሜት ቅዝዝ ብሎ ፥ « አልፎ…አልፎ ልጠይቀው እሄዳለሁ፤ ተሰናብቼው ስወጣ ከቤቱ በር ማለፍ ስለማይችል አይኖቹ ውስጥ ቅሬታ አነባለሁ።
እኔም ሆዴ እየተላወሰ ይከፋኛል። ትንሽ ይረብሻል። ..ሞራሉ ግን ጥሩ ነው፤ ቤት ሆኖ ትምህርቱን ያጠናል፣ ያነባል። ሮቤል ልጄ ስለሆነ ሳይሆን፣ የዚህ አይነት የሽብር ወንጀል ላለመፈፀም ኢትዮጲያዊ መሆን ብቻ በቂ ነው!! ሃበሻ አሸባሪ አይደለም!! » አለኝ።…