Friday, 4 October 2013

ተስፋዬ ገ/አብ እንደ “ካቡጋ”

tesfaye and Kabuga 1


በጋዜጠኛነት ስም መድረክ በማበጀት በኢትዮጵያዊያን ሚዲያ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ህዝቧ እርስ በርስ እንዲባላ ተልዕኮውን ሲያስፈጽም የነበረው ተስፋዬ ገብረ አብ በሰነድ የተረጋገጠ ማንነቱ ገሃድ ሆነ። ዜናውን የሰሙ እንዳሉት ተስፋዬ ካሁን በሁዋላ “በቁሙ ሞተ” ነው የሚባለው ሲሉ ተደምጠዋል።
በኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ይሰሩ እንደነበር የገለጹ የጎልጉል መረጃ ሰጪ “ተስፋዬ አስቀድሞም ቢሆን ሆን ብሎ በተቀነባበረ ስልት ጦርነቱ ሊጠናቀቅ ሲል ወታደር እንዲሆን የተደረገ የሻዕቢያ ሰላይ እንደነበር ይታወቃል” በማለት ለጎልጉል ተናግረዋል። “ተስፋዬ አሁንም በደም ከሚገናኛቸው የህወሃት ሰዎችና የደህንነት የላይኛው መረብ ጋር ግንኙነት አለው” ያሉት እኚሁ ሰው አጋጣሚው “በወያኔ ላይ ጠጠር የሚጥል ሁሉ …” በሚል ጭፍን አመለካከት በጅምላ ለምንነዳ ወገኖች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ አመልክተዋል።
“ግሪን የሎ ሬድ” በሚል የፓልቶክ ተቀጽላ ስም የሚታወቁት አገር ወዳድ በተደጋጋሚ ተስፋዬን ሲሞግቱና ማንነቱን ሲገልጹት፣ ተስፋዬ በመለሳለስ ያልፍ እንደነበር ያስታወሱት እኚሁ ሰው “ተስፋዬ ላይ የሚሰበሰቡ መረጃዎች ከተጠናከሩና ከዜና አልፈው ወደ ህግ የሚያመሩ ከሆነ እሱ ላይ ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ማቅረብ የሚችሉ ወገኖች አሉ፤ በጽሁፍ እስካሁን ያሳተማቸው በበቂ መረጃነት ሊቀርቡ ይችላሉ” ብለዋል።
በሩዋንዳ በተካሄደው የዘር ማጥፋት (ጄኖሳይ) በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚዲያውን ኃይል በመጠቀም RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines) በተሰኘው የሬዲዮ ማሰራጫ አማካኝነት የተነዛው የዘር ጥላቻ ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህንንtesfaye andkabuga ተግባር ሲፈጽሙና ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ እንዲነሱ ያደረገውና ቱትሲዎችን “በረሮ” (“cockroaches”)  እያለ በመጥራት “እንዲገደሉ” በሬዲዮው አማካኝነት “ትዕዛዝ” ሲሰጥ የነበረው ፌሊሲዬን ካቡጋን (Félicien Kabuga) ዋነኛ ተጠቃሽ ነው፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሩዋንዳ ዘር ማጥፋት ዙሪያ ባደረገው ጥናት ካቡጋን እና የሬዲዮ ጣቢያው ልፈፋ ለ51ሺህ ሰዎች መገደል ቀጥተኛ ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ይህም በአጠቃላይ ከተጨፈጨፉት ሰዎች ውስጥ 10በመቶ መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
በዓለምአቀፉ ፍርድቤት በወንጀለኛነት ተከስሶ እየተፈለገ ያለው ካቡጋን እስካሁን ሳይያዝ ቀርቶ በአሁኑ ጊዜ በኬኒያ ራሱን ደብቆና በከፍተኛ ባለሥልጣናት ሽፋን ተሰጥቶት ይገኛል የሚል ግምት፡፡
የተስፋዬ ጉዳይ በህግ መታየት አለበት በማለት ሲወተውቱ የነበሩ ሁሉ ይህ አሁን የወጣውን መረጃና ሌሎች ዘርን ከዘር ጋር እንዲጋጭ ለማድረግ የሚዲያን ኃይል በመጠቀም የፈጸመውን ተግባር በሩዋንዳ ከሆነው ጋር ያገናኙታል፡፡ አክርረው ሲናገሩም “ተስፋዬ ማለት ካቡጋ ነው፤ የቡርቃ ዝምታ ደግሞ የካቡጋ ሬዲዮ RTLM ነው” ይላሉ፡፡ ስለሆነም “ሆላንዳዊው” ተስፋዬ እንደ ካቡጋ “ወደ አባት አገር” በመሄድ ከመሸሸጉ በፊት ውጤታማ ሥራ መሰራት ያለበት አሁን ነው ይላሉ፡፡
ዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻ ጊዜ ወስደው ያቀረቡት የአለማየሁ /ትንታግ/ ድንቅ የምርመራ መረጃ ውጤት ይፋ አንዳደረገው ተስፋዬ ክቡር በሆነው የጋዜጠኛነት ሙያ ተሸሽጎ በውጪ አገር ያሉትን ስደተኞችና ድርጅቶች የሚሰልል፣ በተቀነባበረ ትዕዛዝና መመሪያ በጀት ተመድቦለት ኢትዮጵያ ውስጥ ተስማምተው የሚኖሩ ቤተሰቦች ደም እንዲቃቡ የሚሰራ ወንጀለኛ ነው።
በልጅነቱ ወቅት በአንደበቱ “ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” በማለት ለአስተማሪው መናገሩን የመሰከረውና አስተማሪው ተናደው በጥፊ ስለመቱት መቆጨቱን የተናገረው ተስፋዬ “ከኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ጠላቶች በጀት ተመድቦለት የሚሰራ፣ ሆዱን ከሞላና ለሴሰኛነቱ ጥማት መወጫ ኪሱ ካበጠ ህሊና የሌለው ተራ ሰው በመሆኑ መረጃ ተገኘ በሚል የማይገባውን ደረጃ መስጠት አግባብ አይደለም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “ተራ ሰዎችን ህግ ፊት በማቅረብ ማስቀጣት ግን ለአፍታም ሊዘነጋ አይገባውም” ሲሉ በሰብአዊ መብት ዙሪያ እንሰራለን ለሚሉ ወገኖች የማስተባበሩን ስራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ “አድሚን” “ሙያዬ ምስክር” “የቡርቃ ዝምታን በመጻፍህ ህዝብን ይቅርታ ትጠይቃለህ?” በሚል ላቀረበችለት በማብራሪያ የተደገፈ ጥያቄ “ይቅርታ አልጠይቅም” በማለት ታብዮ መልስ ሰጥቶ የነበረው ተስፋዬ አሁን ለቀረበበት በማስረጃ የተደገፈ ወንጀልና የማንነቱ መገለጫ መልስ ሊኖረው እንደማይችል፤ አለኝ የሚል ከሆነም ፍርድቤት ቢያቀርበው የሚሻል እንደሆነ ይገመታል፡፡
በዲያስፖራ ውስጥ ላሉት ወገኖች ታላቅ ትምህርት እንደሚሆን የተነገረለት የተስፋዬ ማንነት መገለጽ አሁንም በተለያዩ ድረገጾች ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ አምዶች ጽሁፍ የሚለጥፉትን ሁሉ በርጋታ መመልከት እንደሚገባው የሚያመላክት እንደሆነም አስተያየት እየተሰጠ ነው።
አገር ቤት ሆነውም ሆነ በውጪ ተቀምጠው ሰዎች የመሰላቸውን ስለጻፉ ቅጽበታዊ “የጀግና ማዕረግ” በመስጠት ተራ “ሸብ እረብ” አስፈላጊ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች ተስፋዬ አስቀድሞ በወገን ሚዲያ ወገንን ለማፈራረስ ላቀደው ሴራ ድር ማድሪያ ሲገለገልበት የተቃወሙ፣ “ገብረ እባብ” በማለት ለማጋለጥ የደከሙ ወገኖች እንደነበሩ በመጥቀስ ለወደፊቱ በጅምላ ከመነዳት መቆጠብ ተገቢ እንደሆነ ይመክራሉ።
ከሰነዱ ከተገኙት መረጃዎች መካከል ተስፋዬ በእጁ የጻፈው ይህ መረጃ ይገኛል፡-
“ኢትዮጵያዊያን የኤርትራ ታሪክ በትክክል እንዲያውቁ ይረዳል። ይህም በአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አእምሮ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረችና እንደማትሆንም የአመለካከት ዘር መዝራት ያስችለኛል። ለዚህ ሥራም የናንተ መ/ቤት ሆነ ህገደፍ (ሻዕቢያ) ሰነዶችን እንድመለከት በመፍቀድ ያግዘኝ ዘንድ እመኛለሁ። እነዚህ መጻሕፍትን ጽፌ እስከምጨርስ ሁለት ዓመት ይፈጅብኛል። ቢያንስ በቢሮና በጽሕፈት መሣሪያዎች እንዳልቸገር ብደረግ እመኛለሁ።” …tesfaye hand written
“በኤርትራ ጉዳይ፣ በሻዕቢያ አላማዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ኢሳያስን በተመለከተ ያለኝ በጣም ግልጽ ነው። ከነሙሉ ችግራችን ኤርትራ በትክክለኛው ሃዲድ ላይ እየተጓዘች ነው ብዬ አምናለሁ። የሚታረሙ ነገሮች ካሉ ዋናው ጉዞአችን ሳይነካ እየተስተካከለ ሊሄድ ይችላል ብዬ አምናለሁ። የምጽፈውም ሆነ የምሠራው ይህን መሠረት ያደረገ ነው።” …
“አሻግሬ ስመለከት በርቀት ሰማያዊ ተራሮች ይታየኛል። ከተራሮቹ ስር ያለው ለጥ ያለ የእርሻ ሜዳ የአባቴ አገር ነው።” …
“ይህን ታሪክ እጽፈዋለሁ: 3 ተከታታይ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። ባህረነጋስያን በመጀመር የኤርትራን ታሪክ እጽፈዋለሁ። የሻቢያን የትግል ታሪክ እጽፈዋለሁ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ስለኤርትራ ተገቢውን ሃቅ እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። በዚህ መጽሐፍ ጠላት አፈራለሁ። ቢሆንም ግን እጽፈዋለሁ። ስለዚህ ከአሁኑ ፍንጭ መስጠቱ ጠቃሚ ነው። በተቃውሞ የምጽፍ የሚመስላቸው ስለሚኖሩ እስከዚያው ድረስ ይዝናኑበት። ኤርትራ ለመመለሴ ምክንያት ይሰጥልኛል።”
ይህ ታላቅ አገራዊ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ደባ በአገር ቤትም ሆነ በውጪ ያሉ ሚዲያዎች ህዝብን በማሳወቅ ረገድ የሚፈተኑበት አበይት ጉዳይ ነው፡፡
የደራሲው ማስታወሻ በታተመበት ወቅት በሽፋን ገጹ ላይ ሊነበብ የሚገባውና ታላላቅ ቁምነገሮች ያሉበት መጽሐፍ መሆኑን በመጥቀስ ኢትዮጵያውያን እንዲያነቡትና መጽሐፉም እንዲሸጥ በተገኘው ሚዲያ ሁሉ የማስታወቂያ ሥራ የሰሩም እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

የዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ “ጊዜ መስተዋቱ!” ተስፋዬ ገ/አብ ማነው? በሚል በማስረጃ ያቀናበሩት ጽሁፍ ከዚህ በታች ሰፍሯል፡፡ ጽሁፉን ከነማስረጃዎቹ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

“ጊዜ መስተዋቱ!”

ተስፋዬ ገ/አብ ማነው?
(ከወልደሚካኤል መሸሻ)
ከኢትዮሚድያ ዝግጅት ክፍል – የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ የተከበሩ ወልደሚካኤል መሸሻ ናቸው። ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ምርጫ 97ትን ተከትሎ በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን አደጋ ለማጣራት ተቋቁሞ በነበረው አጣሪ ኮምሽን አባል ነበሩ። ለግል ህይወታቸውና ለሚወዱት ቤተሰባቸው ሳይሳሱ፣ ከተበዳዩ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ከፍትህ ጎን በመቆም በስልጣን ላይ የነበረው የመለስ ዜናዊን አገዛዝ በወንጀለኛነት እንዲጠየቅ ወሰኑ! ውሳኔው ከፍተኛ መስዋእትነት እንደሚያስከፍል ጠንቅቀው ያውቁ የነበሩት ዳኛ ወልደሚካኤል ዛሬ በስደት በአውሮፓ ይኖራሉ። ዳኛ ወልደሚካኤል እና ተመሳሳይ ውሳኔ በማሳለፍ የሚታወቁት ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል፣ አቶ ተሾመ ምትኩ እና የተቀሩት ስዎች በኢትዮጵያ ታሪክ ልዩ የክብር ስፍራ ይዘው ይኖራሉ! ያሁኑ የዳኛ ወልደሚካኤል ጽሁፍ በኤርትራዊው ተስፋዩ ገብረአብ ላይ ያጠነጠነ ሲሆን በበርካታ ማስረጃዎች የተደገፈ ነው።
* * * * *
ውድ አንባቢያን ይህን ጽሑፍ ጀምሬ ያጠናቀቅሁት ወደ እ . ኤ. አ በ2012 መጀመሪያ ነው። ለምን እስከአሁን አቆየኸው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው ታዲያ። ተገቢ ጥያቄ ነው። የተለያዩ አቅጣጫዎችን የማየትና የማሰላሰል ሁኔታ በአንድ በኩል፣ በሌላ ደግሞ በአነሰኛ መጽሐፍ መልክ ባሳትመውስ የሚል አሳብ እየተደቀነብኝ መጥቶ ነው።
ሁለቱም ተራ በተራ ተፈታተኑኝ። የትኛውን እንደምመርጥ ማውጣት ማውረዱን ቀጠልሁ። ጽሑፍን እንድያዩትናአሳባቸውን እንዲሰጡኝ ለጥቂት ወዳጆቼ ላክሁ። አንዳንዶቹ ቶሎ ጽሑፉ እንዲወጣ የሚገፋፋ አሳብ ሰጡኝ።
አንዳንዶች ከማስጠበቅ ውጭ ላያልፉ ሆኑ። በዚህ ላይ እያለሁ ለጽሑፉ መሠረት የሆነው የእምዬ ጠላት በመርዘኛ ብዕሩ ብቅ ማለቱን ሰማሁ። ወዳጆቹ ከወዲህ ወዲያ እያሉ መሆኑንም አዳመጥሁ። እርሱም የእምዬ ልጆችን የማባላቱን  ሥራ ማጠናቀቁን ከወብሳይቱ ተመለከትሁ።
ይህ ሰው በዚህ ሰሞን “ላይፍ” ለተባለ በኢትዮጵያ ለሚታተም መጽሔት በሰጠው ቃለ-ምልልስ ላይ በኢትዮጵያ ላይ ያለውን ጥላቻ ግልጽ አድርጎታል። አማሮች ኦሮሞችን መበደላቸውን በይፋ አምነው ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው በሚልና በመሳሰሉት። አልፎ ተርፎም፣ በተለይ በዚያው ዕድሜ፣ የነበራቸውን ትልቅ የኑሮ ዕድል ትተው፣ ለበደልኩት ሕዝብ በአገልግሎቴ እክሳለሁ ብለው፣ አኩሪ ገድል እያከናወኑ ያሉትን ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ላይ ክፉኛ ታስልቆባቸዋል።
“ነጋሶ ጭንቅላታቸውን ተናግረው አያቁም።” በማለት። አንዳንድ አንድነት ምን እንደሆነ ብዥብዥታ ያላቸውን ኦሮሞችን ያስደሰተ መስሎት ስብዕናቸውን በዚህ ዓይነት ለመንካት ሞክሮአል። አንጀት የሚያቆስል ነው። እንዲህ ሰውዬው የሚቀበዘበዘው፣ ለሌላ አይደለም። የመጽሐፉ አሻሻጭ ለማመቻቸት ነው። እንዲያውም በዚህ ሰሞን እዚህ አምስተርዳም ያሉት የኦሮሞ ማህበረሰባችን አንድ ስብሰባ እንዲያዘጋጁለት አድርጎ በመገኘት አማሮች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሰሩትን ግፍ አምነው መቀበል አለባቸው። ይህ ግድ የሚል ነው በሚል ደስኩሮ ተመልሶአል የሚል ወሬ ሰምቻለሁ። ተስፋዬ መቼም ኢትዮጵያ የምትባል አገር ደብዘዋ ሳይጠፋ ላይቀመጥ የማለ ይመስላል።
እናም፣ ግራ ቀኙን የማየቱን አስቆመኝ። በእምዬ ኢትዮጵያ ላይ በሥውር ጨበጣ መሰርሰሩን ከሚቀጥል ምናልባትም በኔ በልጇ ላይ ቢቀጠል ይሻላል ወደ ሚል ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ ደረስሁ። በሽዋን ከማይ፣ ሞቷን ከማይ ሞቴን እመርጣለሁም አልኩ። እናም እንዲወጣም ወስንሁ።
መግቢያ፣
“ሰውን ውደደው እንጅ አትመነው” የሚል የጥንት የአበው አባባል አለ። ግራ የሚገባኝ አባባል ነው ለእኔ። ከወደድኩት እንዴት አላምነውም የሚል ጥያቄ በአእምሮዬ እያመላለሰብኝ። መቼም እየጠሉ ማመን የሚባል ነገር ከቶም ይኖራል ብሎ ማሰብ መኖሩን እጠራጠራለሁ። በዚያው መጠን ደግሞ በመካከላቸው አንዳች ነገር እስካልተከሰተ ድረስ፣ እየወደዱ ያለማመን ነገር እንዴት እንደሚኖር ማሰብም ያስቸግረኛል። ምናልባትም ያልጠረጠረ ተመነጠረ ዓይነት ለማለት ከሆነ ያስኬድ ይሆናል። አዲስ ሰው ስትቀርብ እየተጠራጠርህ ሊሆን ይችላል። አስቀድመህ አታውቀውምና። ትናንት ጠላትህ የነበረ ዛሬ ወዳጅህ ሊሆን ይችላል። ከወደድከው እስከሚመችህ ድረስ ታምነዋለህ። ለስሜት ሳትበገር ሰከን ካልክ በጉዞ ላይ ትፈትነዋለህ፣ ታየዋለህ። እውነቱ ላይ ደርሰህ ማንነቱን ትለየዋለህ። የብልህ ተግባር እንዲህ ነውና።
ዳኛ በተለይም በወንጀል ተከሶ የሚቀርበውን ተከሣሽ፣ ምንም ዓይነት የወንጀል ሪኮርድ ቢኖረውም፣ ምናልባትም ክስ ቀርቦበታልና በጥርጣሬ ከመመልከት ውጭ ወንጀለኛ አድርጎ አያየውም። ፊቱን አይቋጥርበትም። አያስፈራራውም።  አያስበረግገውም። ማንም በወንጀል ድርጊት የተከሰሰ ሰው በሕግ ወንጀለኛ ተብሎ እስከአልተፈረደበት ጊዜ ድረስ እንደ ንጹህ ሰው ሆኖ ይቆጠራል (Every one charged with criminal offence shall be presumed innocent until proved guilty according to law.)፣ ወይም (Presumption of Innocense) የምንለው ዓለም-አቀፍ ተቀባይነት ካገኘው የፍትህ ቃል አነጋገር በመነሳት። እኔ ዳኝነት ስጀምር፣ የችሎቱ ሰብሳቢ የነበሩ ሰው አንድ ተከሳሽ፣ በተለይም በሌብነት ወንጀል የቀረበን እችሎቱ ሲያነጋግሩ ትንሽ ሳት ካደረገ አልቀለት በቃ። “ፊትህ ራሱ ሌባ ይመስላል” ከሚል አነጋገር ጀምሮ ይወረዱበታል። አስቀድሞ የወንጀል ሪኮርድ ካለበትማ ማቆሚያ የላቸውም። ይዘህ ከወጣኸው ትምህርትና እውቀት ጋር ይጋጭብሃል። ታዲያ ከስብዕናም አመለካከት ውጭ ነውና ለእኔ እጅግ አስደንጋጭ ነበር በወቅቱ። የኋላ ኋላ ግን ይህንና የመሳሰሉ አነጋገራቸውና አመለካከታቸውን በትግል ከሌሎቹ ሁለት የችሎቱ ዳኞች ጋር ሆኜ አስቆምኳቸው። ለነገሩ ሰውዬው በንጉሡ ዘመን በፓርላማው አማካይነት ካላቸው የሕግ ሰርትፊኬት ጋር እንዲህ ዓይነቱን ገደብ የለሽ ልምድ ከነበረው ሥርዓት አዳብረውት ስለመጡና ሃይ የሚል ሰው በመጥፋቱ ነው ይዘው የቆዩት ለማለት ይቻላል።
ሦስት ዳኞች ወይም በሰበር ችሎት አምስት ዳኞች እንደተመደቡ በመጀመሪያዎቹ ውስን ጊዜያት ሥራዎችን የሚያከናውኑት እርስበርስ በጥርጣሬ እየተያዩ ነው። አንዱ አጥንቶ ያመጣውን የአንድ ጉዳይ መዝገብ ላይ ሲወያዩ አሰልችና አጓጉል ጥያቄዎች ይጎርፉለታል። መዝገቡን ሰርቶ ለፊርማ ሲያቀርብም እናነባለን በሚል ጊዜያት ይወሰዳሉ።
ውሎ እያደር ሲሄድ ግን አጥኚው ዳኛ ነጥቦቹን አስረድቶ ሲጨርስ ምን ይመስለሃል? የሚል ጥያቄ ይቀርብና አስተያየት ተሰጥቶበት በዚህ መልክ ሥራው ተብሎ ይታለፋል። አጠናቅቆ ሲያቀርብም እንደመጀመሪያዎቹ እናምብበው በሚል የጊዜ መፍጀት ነገር አይኖርም። ወዲያውኑ ፊርማቸውን ማሳረፍ ነው።
ሰዎች መዋደድ ላይ ደርሰውም፣ መተማመን ላይም ደርሰውም ውሉ የሚላላበት ሁኔታ የመፈጠሩ ዓይነት በፍ/ቤትም ይከሰታል። በዚህ በኩል አንድ ምሳሌ ጠቀስ ላድርግ። ወደ 1995 (2001) ላይ ይመስለኛል አንድ አስደንጋጭ ነገር በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ላይ ተከሰተ። ሦስት ዳኞች ያሉበት ችሎት ነው። በወቅቱ እኔ የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ ነበርሁ። ጉዳዩ የቀይ ሽብር ጉዳይ ነው። ብዙ ተከሳሾች የሚገኙበት ነው። እንደተለመደው አንዱ ዳኛ የመዝገቡን ጉዳይ አጥንቶ ለሁለቱ ያቀርባል። ተወያዩበትና የተወሰኑት እንዲለቀቁ፣ የተወሰኑት እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቶ እንዲያቀርብ ሁለቱ ይነግሩታል። እርሱም ተስማማበት። ዳኞች እርስበርስ መተማመን ላይ የደረሱበት ችሎት ስለነበር፣ በማግሥቱ እንደተነገረው ሰርቶ ማቅረቡን ዳኛው ሲነገራቸው፣ ሁለቱ ዳኞች በቀጠለው እምነት መሠረት ፈርማቸውን ያሳርፉበትና እችሎቱ ይሰየማሉ። እችሎቱ አዘጋጅው ዳኛ ብይኑን ሲያነብ ሁሉንም ከክሱ ነጻ አድርገን በዛሬ ቀን ለቀናል የሚል መደምደሚያ ያሰማል። ሁሉም ተከሳሾች በደስታ ይፈነድቃሉ። ሁለቱ ዳኞች ግን ሃዘን ውስጥ ይገባሉ። ከእምነታቸውና ከቃላቸው ውጭ የተሰራ ነገር በመስማታቸው።
ጉዳዮቹ ተስተናግደው ሳያልቁ፣ ሁለቱ ዳኞች ችሎቱ እንዲቋረጥ አድርገው ሁሉም ወደ ጽ/ቤት ይገባሉ። ጽ/ቤቱ ወደ አምባጓሮ ይለወጣል እንደሰማነው በወቅቱ። ከዚያም ለፍ/ቤቱ አስተዳደር ማለትም ለፕሬዚዳንቱ ይቀርብና ዳኛው ወዲያውኑ ከሥራው ይታገዳል። በወንጀል ጉዳይ ፕሬዚዳንቶች ውሳኔዎችን ማገድ ስለማይችሉ ውዲያውኑ ዐቃቤ ሕጉ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ብሎ የእግድ ጥያቄ እንዲያቀርብ ይደረጋል። ቀውሱ በዚህ ዓይነት ተስተካከለ።
ዳኛውም በዳኞች አስተዳደር ጉባኤና በተወካዮች ም/ቤት ውሳኔ ከሥራው ተባረረ። በኋላ ግን ይህ ዳኛ በቅንጅቶች ጉዳይ የሽመልስ ከማል ምክትል ዐቃቤ ሕግ ሆኖ በተሰጠ የምሽት ሹመት ብቅ አለና ጉድ አሰኘን። ሁሉ ነገር በወያኔ የተገላቢጦሽ አይደል?
እንደየሁናቴው ሰዎች በአብሮ መኖር ዙርያ ላይ እርስበርስ ይዋደዳሉ፣ ይተማመናሉ፣ ይጣላሉ፣ ይታረቃሉ። ሁሉንም ይሆናሉ። የሰው ልቦናው ተገልጦ አይታይም። ግን በሂደት እየተፈተነ ይጋለጣል፤ ይታያልም። ከርቀት ሰውን መገደብ፣ ስለትናንት እያነሱ ወደ ግድግዳ ማስጠጋት፣ ዛሬን መርሳት ይሆናል። ትናንት ዛሬ አይደለምና። ዛሬ ሌላ ነውና አጉል አካሄድ ነው። በስሜት ፈረስ ላይ መፈናጠጥ ስለሆነ። ታዲያም ጉዳት አለው። ከቶ ላያመልጠን ችኮላው ለምን? እናም ሰውን እንደአመጣጡ እንቀበለው። እንየው። እንፈትሸው። ጠላትን ከማብዛት ወዳጅን ማብዛት ሳይሻል አይቀርምና።
እናም፣ ዛሬ ባናገኘው ነገ ለምናገኘው ምን ያስቸኩለናል?
እምዬ ኢትዮጵያን አምላክ እንደሚጠብቃት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመልክቶ ይገኛል። እምዬ አገራችን በየወቅቱ ከውስጥም ከውጭም ፈታኝ ጠላቶች አልጠፏትም። የጡት ነካሾቿ ደግሞ ይብሳሉ። በርሳው ተወልደው፣ እትብታቸው ተቀብሮባት፣ አድገው ለቁም ነገር የበቁት ዛሬ ክዷት፣ ሊያጠፏት ጉድጓድ ሲቆፍሩ ማየትና መስማት የተለመደ ሆኖአል። ይህ ደግሞ ሕሊናን የሚያደማ፣ የሚያቆስል ቸነፈር ነው። ግና ምን ያደርጋል እንዲህ ዓይነት ሰዎችና ድርጊቶች ትናንት የነበሩ፣ ዛሬም ያሉ፣ ነገም የሚኖሩ ናቸው። ታዲያም ምንም ያህል ቢሯሯጡ፣ ምንም ያህል ቢሰባበሩ እምዬ የወላድ መካን አልሆነችም ፤ አትሆንምም፤ አላትና አንድዬ። እንዲህ እያልክ ወዴት ልትወስደን ነው? ምን ልትለን ነው? ሳትሉኝ እንደማትቀሩ ይሰማኛል። ጊዜው ደረሰና አንድ አፍጥጦ፣ አግጦ ስለወጣ ቁም ነገር ልተርክላችሁ ዕድል አግኝቼ ነው። ምንድነው እሱ? ልትሉኝ ነው ቀጥሎ። እሱንማ ከጽሑፉ ታገኙታላችሁ ይሆናል መልሴ። እናም፣ ተከታተሉት ውድ የኢትዮጵያ ልጆች።
ክፍል 1.
ጊዜ ደጉ!
ያ ቀን ሲደርስ፣ ጎሁ ሲቀድ፣ ሌቱም ሲነጋ ማንም፣ ምንም መጋለጡ አይቀርም። ክፉ ሥራው በክፋቱ፣ ደግ ሥራው በደግነቱ ይታያል። ጊዜ ማስጠንቀቂያ የለውም። ራሱን በራሱ ሁሉም እንዲፈትሽ ገደብ የለሽ መብት ግን ይሰጣል።
ላወቀበት ጊዜ ኩራት ነው። ላለወቀበትና ለታወረው ጊዜ ማፈሪያው፣ መሸማቀቂያው ነው። ጊዜ ቀኑን ጠብቆ ብቅ ባለ ሰዓት ይቅርታ የለውም። አጋልጦ እንደጅብራ አቁሞ ማሳየት እንጂ። በክፋት ታውሮ የሰራው ተንኮል ከተፍ ሲልበት አይ ጊዜ ክፉ ሲል፣ ተሸሽጎበት የነበረው እውነት ብቅ ያለለት ደግሞ አይ ጊዜ ደጉ! ይልና ይጽናናል። ቀደም ብሎ ወደ እ.ኤ.አ በ2008 ላይ፣ “ለሁሉም ጊዜ አለው” በሚል ርዕስ የፌዴራል ፍ/ቤቶች ሲያምስ የነበረው የፍ/ቤቶቹ አስተዳዳሪ ተብሎ ተሹሞ የነበረው ሰው ቀኑ ደርሶ በይፋ መጋለጡን ምክንያት በማድረግ አንድ ጽሑፍ አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል። እውነትን በጊዜ ስለአየሁ። ዛሬ ደግሞ “ጊዜ! መስተዋቱ!” በሚል ርዕስ አንድ አነስተኛ ጽሑፍ አዘግጅቼ ይዤ ቀርቤአለሁ።
ለነገሩ እኔ ከአገር ከወጣሁ በኋላ ተሸሽገው የነበሩ የፌዴራል ፍ/ቤቶች እውነቶችን እየሰማሁ ነው። መቆየት ደግ ነው።
አንድ ለአብነት ያህል ባነሳ። ከካቻምና ወዲያ2010 አጋማሽ ላይ አንድ ዜና ከኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ወጥቶ በወብሳይት ላይ አነበብሁ። በተለይም በአራጣ አበዳሪዎች ላይ የተሰጠ ፍርድ። ውሳኔ የተሰጠባቸውን ዝርዝር እንደአየሁ አሁንም ለራሴ ወይ ጊዜ!! አልኩ። ይዘገያል እንጅ እውነት ተቀብሮ እንደማይቀር ዳግመኛ ሰማሁ። ነገሩ እንዲህ ነው ታዲያ።
ከተወሰነባቸው መካከል አንዱ አቶ ሌንጫ ዘገየ የተበለው አራጣ አበዳሪ ነው። እኔ ነገረ-ፈጅ በነበርኩበት ወቅት ወደ ፍ/ቤት ብቅ ስል ይህን ሰው ተመልከተው። ምድረ ሀብታምን ያጠበ፣ ያሽመደመደ ሰው ነው። የዋዛ አይምሰልህ። እጅግ ሀብታም ነው በአራጣ አበዳሪነቱ። ጊዜ አዳልጧቸው በርሱ እጅ የወደቁ ያለቅሳሉ ሁሌ፣ ይከሱታልም ሁሌ። እርሱ ግን አልተቻለም። በርሱ ላይ የማይፎክር ዳኛ የለም። ግን ያገኘው የለም እያሉ ጓደኞቼ ይነግሩኛል። ለምን አያገኙትም? ለምን ይሆን? እያልሁ እነዚያን የነገሩኝን ስጠይቅ የተጨበጠ መልስ የላቸውም። ሰውዬው በዓይን ሲታይ ደም ያለው አይመስልም። ግራ የሚያጋባ ነበር።
በዚህ ላይ እንዳለ፣ በኢ . አ በ1986 ዓ.ም በዳኝነት ተሹሜ ወደ ፍ/ቤት ገባ አልኩ። በ1988 ግንቦት ላይ የፌዴራል ፍ/ቤቶች እንደ ተቋቋመ እየተገለባበጠ የመጣ አንድ ትልቅ ፋይል ገጠመኝ። ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ፣ ተከሳሽ ሌንጫ ዘገየ የሚል። ያ ሰው ይሆን እንዴ? ብዬ አሰብሁ። መዝገቡን ከፈት አድርጌ ሳነበው ነገሩ ከአራጣ ጋር የተያያዘ የወንጀል ድርጊት የሚል በመሆኑ፣ እርሱ መሆኑን ተረዳሁ። የልቤ ምት ጨመር ማለቱ አሁን ትዝ ይለኛል። ምክንያት? ውጭ ሆኜ እንደሌሎቹ እንዴት? ለምን? በሚል እንደመፎከር ዓይነት ብዬ ስለነበር እኔም እዚያው ውስጥ እንዳልገባ ፍርሃት፣ ፍርሃት ብሎኝ ይመስለኛል። ግና አጋጠመኝ።
እናም የሌንጫን መዝገብ ስመለከተው፣ ማስረጃ ሳይሰማ ለዓመታት እየዘለቀ የመጣ ነው። ምክንያቱ አይታወቅም።
የቀረበውን የማስረጃ ዝርዝር በመጀመሪያ ዳሰስሁ። ይዘቱን በአጭሩ ዘርዘር አድርጌ መዝገቡን እንደምሰራው ለሌሎቹ ሁለቱ ዳኞች ነገርኳቸው። እነርሱም ተስማሙ። እናም፣ ሰከን ብዬ ወደ እልህ ገባሁ። ቢሆን በዚህ ምታሃተኛ ሰው ላይ
ፍርድ ለማሳረፍ፤ ባይሆን ያው እንደቀድሞቹ ፎከራዬ በአጭሩ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ። አጭር ቀጠሮ ሰጥተን በመጀመሪያ ዐቃቤ ሕግን፣ ቀጥሎ የተከሳሹን የሌንጫን ማስረጃዎችን ሰማን። 43 ገጽ የወሰደ የውሳኔ ትችት ጽፌ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌንጫ ላይ በአራጣ ወንጀል የጥፋተኛነት ውሳኔ ተሰጠበት። በማግሥቱ በአምስት ዓመት ጽኑ እሥራት ፍርድ ተሰጥቶበት ወደ ከርቸሌ ማረሚያ ቤት እንዲገባ የተዛዘበት ትዝ ይለኛል። ጉድ ተባለ። በችሎቱ የነበሩና ጉዳዩን ይከታተሉ የነበሩ የሌንጫ ተጠቂዎች በወቅቱ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ዛሬስ ላንተ ዳኛ ተገኘ? እያሉ ቀና ብለው ለአምላክ ምስጋና እያቀረቡ መውጣታቸውም ትዝ ይለኛል።
ሌንጫ ዘገየ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ይጠይቃል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ይግባኙን ተቀብሎ ካከራከረ በኋላ የኛን ውሳኔ ሽሮ ሌንጫን በነጻ ለቀቀው። እናም ውሳኔው የሦስት ዳኞች ቢሆንም፣ የሰራሁት እኔ ስለነበርሁ ሌንጫ በእኔ ላይ ቂም እንደያዘና እንደሚፎክርብኝ ሰማሁ። መቼም ከፍተኛ ፍ/ቤት ውስጥ አይጠፋምና ዓይን ለዓይን ስንተያይ ኮምጨጭ እንደሚልብኝ አስተውል ነበር። በመሰረቱ በወንጀልም ሆነ በፍትሐብሔር አንድ ውሳኔ በተሰጠ ቁጥር፣ ውሳኔውን የሰጠው፣ ወይም የጻፈው ዳኛ አንድ ቂመኛ አያጣም። ዳኝነት ስይዙት ከስሙ በላይ ከባድና አስፈሪ ነው። እንደየግለሰቡ ሕሊና መለያየቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዳኝነት ሁሌ መጨነቅ፣ ሁሌ መጠበብ፣ ሁሌ በጉቦና በአድልዎ መጠርጠር የተለመደ መሆኑ የታወቀ ነው። እውነተኛና በራሱ የሚተማመን ዳኛ ግን ለእንዲህ ዓይነቶች አይበገርም። በወቅቱ አስገራሚው የሌንጫ እኔን እንደባላንጣው አድርጎ መከታተሉ አልነበረም። ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ውሳኔውን የሻረበት ምክንያት ወይም ትችት እንጅ። “አሁን መንግሥት በሚከተለው ነጻ ኤኮኖሚ መሠረት ሰዎች በማንኛውም የንግድ ዘርፍ መሰማራት ይችላሉ። ስለዚህ ሌንጫ በአራጣ አበዳሪ ዘርፍ ተሰልፎ እያበደረ ቢሰራ ወንጀል ሊባል አይችልም።” በሚል” የሰጠው መንደርደሪያ።
አገራችን የምትከተለው የኮንትኔንታል (ሲቪል) ሕግ ዘርፍ ነው። በዚህ መሠረት ዳኞች አስቀድሞ በሕግ አውጭው የወጣን ሕግ ነው የሚተረጉሙት እንጅ ራሳቸው ሕግ ሽረው፣ ሕግ አውጭ መሆን አይችሉም። ሥልጣን የላቸውም።
የወቅቱ የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ሌንጫን ከወንጀሉ ነጻ አድርገው የለቀቁት ትርጉምም የማያስፈልገውን በግልጽ የሚናገረውን የወንጀልና ተያያዥነት ያለውን የፍትሐብሔር ድንጋጌ የሻረ ነው። በወቅቱ ለካስ ሌንጫ ያልተቻለው በጤናው አይደለም አልንና አዘንን። በጊዜው የዳኞችን ውሳኔ የሚመረምር አካል አልነበረም። አሁንም ያለ አይመስለኝም። ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ ሌንጫም በድል ፈረስ ላይ እንደገና ተፈናጠጠ።
ሌንጮን ለማዳን ከሕግ ውጭ ተፈልጎ በተገኘ ምክንያት። ውሳኔውን የሻሩት የጠ/ፍ/ ዳኞች መስፍን ገ/ሕይወት የሕግ ትምህርት ቤት መምህሬ የነበረና ወደ 92 ዓ.ም አከባቢ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ፣ ፈጠነ ወንድሙ እስከወጣሁ ድረስ ጠበቃ የነበረ፣ አንድ ስሟን የዘነገኋት የሴት ዳኛ ነበሩ። ግና አሁን መንግሥት ለፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፣ ጊዜው ደረሰና በእርጅና እድሜው ሌንጫ አምና በዚሁ በአራጣ ወንጀል ተፈርዶበት ወደ እስር ቤት ገባ።
“ሁሉም ነገር ጊዜውን ይጠብቅለታል” ዘፋኙ ብሎ የለ። እናም ገረመኝ።
በዚሁ ወደ ተነሳሁበት ርዕስ እንግዲህ ልግባ። ሌላ አስገራሚ እዚሁ ሳይበሩ ከዳኝነት ቋት ውጭ አጋጠመኝ። የወያኔ አባላት የነበሩም ሆኑ፣ ከወያኔ ጋር ይሰሩ የነበሩ፣ በብዛት የሥርዓቱን እኩይ ተግባር በማውገዝ ወደ ሕዝባችን በአገር ቤት የተቀላቀሉ፣ ወይም ወደ ውጭ የወጡና የውጭውን ማህበረሰብ የተቀላቀሉ፣ አለዚያም አፋቸውን ዘግተው የተቀመጡ አሉ። በአንጻሩ ደግሞ በተቃዋሚነት ጎራ ተደራጅተውም ሆነ በተናጠል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለስቦችም በነጻና በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ወደ ውጭ ተሰደው ይገኛሉ። ከነዚህም ውስጥ በብዛት የነጻው ፕሬስ አባላት ይጠቀሳሉ። እንደዚህም የመንግሥት ጋዜጠኞችም ይገኙባቸዋል። በአገር ቤት ውስጥ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች የወያኔ መንግሥትን እኩይ ተግባር በየጊዜው በማጋለጥ እጅግ አኩሪ ታሪክ ሰርተዋል። ብዙዎችም ዋጋ ከፍለዋል። ለስደትም ተዳርገዋል። አብዘኛዎች የቀድሞውን ተግባራቸውን ያለመታከት ቀጥለዋል። አንዳንዶች በአገር ቤት ያሉት ዓይናቸውን ወደኋላ ላያዞሩ ሆነው ለመከራ ስቃይ እየተዳረጉ ይገኛሉ። የሽብርተኝነት ታርጋ የተለጠፋባቸው እንደነ እስክንድር ነጋ የመሳሰሉትን መጥቀስ ይበቃል።
በሌላ በኩልም፣ ከመንግሥት ሚዲያዎች ለቀው ከተሰደዱት አብዘኛዎቹ እንደዚሁ ሥራ ላይ በነበሩበት ወቅት ባይችሉም፣ አሁን ካሉበት ነጻ ቦታ ለሕዝባችን የተቻላቸውን አገልግሎት እያበረከቱ ይገኛሉ። በዚህ በኩል በቪ.ኦ.ኤ እና በጀርመን ሬዲዮ በአማርኛው ክፍል፣ እና በኢሳት ውስጥ የሚሰሩትን ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችን ልንጠቅስ እንችላለን። አንድ ሰው በነበረበት መንግሥት ሥራ ውስጥ ባለበት ወቅት አውቆም ሆነ ሳያውቅ ጥፋቶችን ሊፈጽም ይችላል። ዋናው ቁም ነገር ግን በነበረበት ቦታ የሰራውን፣ እየተሰራ የነበረውን መጥፎ ወይም እኩይ ተግባራትን ተረድቶ በመላቀቅ የበደለውን ሕዝብ ለመካስ ወደ ማገልገሉ ከመጣ እሰዮ ብሎ መቀበል ተገቢ ይመስለኛል። እናም በሥራው ይፈተናል። ይመዘናል። ካለው ባሕርይ፣ ወይም ይዞት ከመጣው ዓላማ የተነሳ ፈተናውን ሊያልፍ አይችል ይሆናል። ክትትል ማድረጋችን ስለማይቀር ስንደርስበት ማጋለጥ ደግሞ ተገቢ ነው። ይህ አካሄድ ያለና ወደፊትም የሚኖር ክስተት ነው።
እናም ወዴት ነው ነገርህ? ትሉኝ ይሆናል። እንዲያው ለተነሳሁበት ጽሑፍ የመንገድ ጥርጊያ ዓይነት ነው እንጅ ጉዳዬ ከወያኔ ጉያ ወጥቶ ስለተቀላቀለን አንድ ደራሲ ነኝ ባይ ነው። በአገር ቤት የወያኔ መንግሥት በሚያዘው ሚዲያዎች ውስጥ በሃላፊነት፣ ከዚያም የወያኔ መንግሥት አታሚ ድርጅትም ሥራ አስኪያጅም ሆኖ ሰርቶ ስለነበር ደራሲ ነው።
መቼም ጊዜ ደግ ነው። ደረሰና ስለደራሲው የቀድሞ ሥራውን ከአሁኑ ጋር እንዳሳይ ዕድል ሰጥቶኝ ብቅ ልል ቻልሁ።
” ትንሽ ቆሎ ይዞ ወደ አሻሮ። ትንሽ ቆሎ ይዞ ወደ አሻሮ. . .” ይሉታል አበው ሲተርቱ። በግርድፉ ትንሽ ዕቃ ወይም ነገር ይዞ ወደ ብዙ መጠጋት ለማለት ተፈልጎ ሲሆን፣ ግን ውስጠ-ምስጢሩ ብዙ ለማግኘት ትንሽ ግን ስሜት የሚነካ፣ አንጀት የሚበላ ነገር ይዞ ወደ ብዙ ሚገኝበት ጠጋ የሚለውን ለመነካከት ያህል የሚነገር ዘይቤ ይመስለኛል። ደግሞም “ትግላችን አስቸጋሪ፣ መንገዳችን ጠመዝማዛ ነው” የሚል አነጋገር እሰማ የነበረው በዘመነ-ደርግ ነው። ኮሙኒዝምን ለመገንባት ደርግ በተነሳሳበት ወቅት ካጋጠመው ውስብስብ ሁኔታ ተነስቶ ይመስለኛል ይህን አባባል ያወርደው የነበረው። ወደ ግቡ ለመድረስ እልህ አስጨራሽ እንቅስቃሴና ትዕግሥት ያስፈልጋል ለማለት። ደርግን የተካው የአሁኑ የወያኔ መንግሥት፣ “ነፍጠኛ”፣ “የብሔረሰቦች እኩልነት”፣ “በመፈቀቃድ አንድነት”፣ የራስን ዕድል በራስ እስከመገንጠል” በሚሉ እኩይ ቅመራና  አነጋገሮች ሕዝባችን እርስበርሱ ተማምኖና ተከባብሮ እንዳይኖር ያመጣብን ጣጣ እንዲህ በቀላሉ የሚነገር አልሆነም። ስለሆነም፣ ይህ መንግሥት የያዘውን መንገድ ለማስለወጥ ወይም ራሱን ለማስወገድ የሚደረገው ትግል አስቸጋሪና ጠመዝማዛ ሆኖ እየታየ ነው። ለዚህም ምክንያቶቹ ብዙዎች ይሆናሉ። ወያኔ በቀጥታና በሾሪኒ የሚሰራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አስመሳዮችና አድርባዮች፣ አይሰሩ ወይም አያሰሩ ሰዎች፣ ግለሰቦች የሚፈጥሩት፣ የሚያወርዱት ናዳ እና ያልታሰቡ ውስብስብ ሁኔታ ይመስላሉ።
በተለይ ከወያኔ ጉያ ወጣ ሲሉ አንዳንዶቹ የበግ ለምድ ለብሰው ይገቡብናል። እነርሱ የሚፈጥሩት፣ የሚቀምሩትና የሚቀብሩብን ፈንጅ ከሁሉም በላይ አደገኛ ነው። ግን ውሎ አድሮ ካልሆነ በስተቀር፣ ወዲያውኑ አይገባንም፣ አንደርስባቸውም። እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ዓላማቸውን ለማሳካት በተቀናጀ መልኩ ይዘው የሚገቡብን በሬት የተለወሰ ማር ቀላል አይደለም። መጀመሪያዉኑ በከፍተኛ ጥናት፣ ስትራተጅክ የሆነ ፕላን ነድፈው ስለሆነ። የሕዝብ ስሜትን ኰርኰር በማድረግ ጠጋ ይሉና የከፍተኛ ፖለቲካ ቀማሪዎችና አዋቂዎችን ልብ ጭምር ይሰርቃሉ። በቀላሉም የሚደረስባቸው ስለማይሆኑ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚረጩት መርዝ እንደዚሁ ቀላል አይደለም። እንዲህ መሰል ሰዎች ገባ ሲሉብን፣ ስሜትን ተቆጣጥሮ፣ በሰከነ አእምሮ ሁኔታዎችን ማየትና መገምገም ብልህነት ነው። ሁሉን እንደወረደ ከመቀበል ጎን ለጎን መጠርጠር ያስፈልጋል። ከዚያ ጉያ ወጥተው እስከመጡ ድረስ ልንጠረጥራቸው የሚያስችለን መነሻ ይኖረናልና። ክትትል ማድረግ ክፋት የለውም። ቢያንስ እንዴት? ለምን? የተሰኙትን ጥያቄዎችን እያነሳን ወደ ጫፍ ሊያደርሱን የሚችሉ መልሶችን ከእይታችን ጋር አዛምደን ልናገኝ እንችላለን። እናም ጥንቃቄ ማድረግ ለጥሩ ውጤት መዳረሻ ይሆናል።
ወጣቱ የቅንጅት ትንታግ፣ እቤትህ ልመጣ እችላለሁ?
ወደ የካቲት 2003 ዓ.ም አካባቢ ነው እ . ኢ . አ አንድ የማውቀው ወጣት ደውሎ እቤትህ ለአንድ ነገር ልመጣ እችላለሁ? የሚል ጥያቄ አቀረበልኝ። እንዴታ! ማን ከልክሎህ? አልኩት። እንዲያ መጠየቁ ወጣቱ ያው በፈረንጁ ባህል ውስጥ ራሱን ማስተካከሉንም እግረመንገዱን እየነገረኝ እንደነበረ ተስምቶኛል። ቀጠሮ መያዝ መሆኑ ነው። እናም በተቀጣጠርነው ቀንና ሰዓት ወጣቱ ከተፍ አለ። ኢትዮጵያዊ ሰላምታ ተለዋወጥን። ሻይ ቀርቦም እየጠጣን ዛሬ የመጣሁበት ምክንያት ከማለቱ እኔም እህ! አልኩት። አንተ ተስፋዬን የምታውቀው በደራሲነቱ ነው አይደል? ብሎ ጠየቀኝ። የቱ ተስፋዬ? ቀጠለ የኔ ጥያቄ። ተስፋዬን አጣኸው እንዴ? ያ የጋዜጠኛው ማስታወሻ፣ የደራ. . . ከማለቱ እ! በቃህ! በቃህ! በማለት አቋርጨው እንዲህ ስል መለስኩለት።
“አይ! እኔኮ ብዙ ተስፋዬዎች ስላሉ የትኛውን ለማለት እንደፈለግህ ለመለየት ነው የጠየቅሁ። የምትለውን ተስፋዬንማ እንዴት አላውቀውም? በመልክ ሳይሆን፣ በተግባሩ አሳምሬ አውቀዋለሁ። ግን ከደራሲነቱ ውጭ በሌላም ይታወቃል እንዴ? የሚል ጥያቄ አቀርብሁለት ከራሱ ጥያቄ ተነስቼ። ቀጠለም ወጣቱ፣ “ተስፋዬ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ያዘነ መስሎ ስዬን እየኮነነ፣ ስሜት ኮርኩሮ መርዛማውን የአዞ እምባውን በተለይም በሳይበሩ ላይ ረጨ። ወደ አገርም ዘልቆ በተለይ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የለኮሰው እሳት ፓርቲውን ክፉኛ አናውጦታል። እጅጉን አዝኜ ነበር። ለዚህም ነው እምነቴ አንተ ጋ ሆኖ ወደ አንተ ዛሬ የመጣሁት” አለኝ። ትንሽ ደንገጥ አልሁ። ትንፋሼን ሰብሰብ አድርጌ፣ እንዴት? ምን አገኘህ ደግሞ? አልኩት ምናልባትም ስለተስፋዬ የወጣ፣ ያነበበው አንድ ጽሑፍ ይኖራል ብዬ በመገመት።
“ቀደም ብዬ አንተ የምትላቸውን የተስፋዬን መጽሐፍት እኔም አንብቤአለሁ። በተለይ የጋዜጠኛ ማስታወሻ የተባለውን መጽሐፉን ካነበብሁ በኋላ ተስፋዬ ማነው? አላማው ምንድነው? የተሰኙትን ጥያቄዎች ማውጣት ማውረድ ጀመርሁ። እንዳጋጣሚ ሆኖ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር አዳረገው። እናም ተስፋዬን ለመከታተል ምቹ ሁኔታ ተፈጠረልኝ ማለት ነው። የተስፋዬን ማንነት እንደሚነገረን ሳይሆን፣ ይዞ ወደ ሳይበሩ የገባበትን አላማ የሚያሳዩ አንዳንድ መረጃዎችን ማግኘት ጀመርሁ። በመጨረሻም፣ ተስፋዬ ኢትዮጵያዊ ያለመሆኑን፣ የሻቢያ ሰላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃዎች ላይ  ደረስኩ። ክትትሌም ጠነከረ። ብዙ አስረጂዎችን በጄ ለማድረግ ቻልሁ። እናም፣ የተስፋዬን ማንነትና ምንነት ሊያሳዩ ይችላሉ ብዬ የገምትኋቸውን ሰነዶች ይዤ መጥቼልሃለሁ” ብሎ እርፍ አለ።
ኧረ እንዴትእንዴት!? አልኩት የሰማሁትን ማመን አቅቶኝ።
እንዲህ ነዋ! ብሎ ጀመረ ወጣቱ። ይዞ የመጣውን ቦርሳ ከፈት አድርጎ። አንዳንድ ያመጣቸውን ማስረጃዎችን እያሳየኝ ይዘረዝርልኝ ገባ። እንጨትም ይሸብታል ይሉታል የዕድሜ ባለፀጋውን አስተሳሰብ ለማጣጣል ሲከጅሉ። ገና በአፍላ ዕድሜ ውስጥ ያለው፣ ገና ወደ አስተውሎቱ ያልደረሰው እንደ አዋቂ ሲናገር፣ ሲያስብና ሲያስተውል የልጅ አዋቂ ይሉታል ደግሞ። እናም እኔም ወጣቱን የልጅ አዋቂ አልሁት በሆዴ። አልተያዝክለትም እንጅ ብይዝህ ኖሮ፣ ወያኔ አንተን በደህንነት በደምብ ይጠቀምህ ነበር የሚልም ጨመርሁለት ለቀልድ ያህል። ዳሩ ምን ያደርጋል አመለጥከው ስለው ከትከት ብሎ ሳቀና እየቀለድህብኝ ነው አይደል ጋሽ ወልዴ? ብሎ የማስረገጫ ጥያቄ አቀረበልኝ። ምን እቀልዳለሁ ከአንጀቴ ነው የምለው። ማንም ያደርጋል ብዬ የማልገምተውን ነው ያደረከው። እናም፣ ቢኖር ከዚህም በላይ ልልህ ይገባኝ ነበር አልኩት።
ቀደም ብሎ “የቡርቃ ዝምታ” መጽሐፉን በአገር ቤት አንብቤ እግዚአብሔር ደግሞ እንዲህ ያለ አሪዮስ ጸሐፊ ከየት አመጣብን? ብዬ ጀመርሁ። አሁን በሳይበሩ ደግሞ “የጋዜጠኛው ማስታወሻ” መጽሐፉን ካነበብሁለት በኋላ የፈረጅሁት በጋዜጠኛነቱ ሳይሆን፣ በበታኝ ሰላይነቱ ነው።” አየህ! ተስፋዬ ይህንኑ መጽሐፍ ጽፎ እንዳጠናቀቀ ወደ ውስጣችን የገባው፣ መጽሐፉ ብዙ ያልሰማናቸውና ያላየናቸውን የወያኔን ምስጢር እንደያዘ አድርጎ አስቀድሞ ፕሮፓጋንዳ ነዝቶብን፣ በመጀመሪያ ረድፍ የተወሰኑ ጋዜጠኞችን፣ ከዚያም ወደ ሚዲያዎች ጠጋ ብሎ ነው። አላነበብኸውም “እየተስተዋለ” በሚል ርዕስ አውጥቼው የነበረውን ጽሑፌን? ብዬ ጠየቅሁት። ያንን ጽሑፍ ለማውጣት የተገደድሁት፣ ከላይ ባልኩህ መሠረት ተስፋዬ ገብቶ እዚህ ያለውን ማህበረሰብ ሁለት ቦታ መከፋፈል መጀመሩን ደርሼበት ነው። እናም ሙከራዬ የነበረው፣ እየሸተተ የነበረውን ክፍፍል ለማክሸፍ፣ እየሰፋም ሂዶ ወደ አገር እንዳይደርስ ነበር። አንዳንዶቹ ተስፋዬ ስሜታቸውን እየኮረኮረ በመቀጠሉ የጽሁፌን መነሻና ይዘት ሊረዱ አልቻሉም። ይባስ ብለው በዚያ ጽሑፌ ወደ ወያኔነት የፈረጁኝም አልጠፉም። የትጥቅ ትግል ተቋሚ አድርገው የቆጠሩኝም አልጠፉም። እንደምታየው ተስፋዬ የአጻጻፍ ክህሎቱ ወደ በዓሉ ግርማ ይጠጋል። ለተወሰነ ጊዜ የማንንም ሕሊና የመግዛት ሃይል ያለው ነው። በዚህ መሠረትም፣ በትምህርት የላቁ፣ በልምድና በእድሜ የበሰሉ፣ በፖለቲካ ሥራቸው አንቱ የተባሉም ኢትዮጵያዊያንም ከወጥመዱ አላመለጡም። እናም ውሎ አድሮ የፈራሁት አልቀረ፣ የማይከፋፈል ማህበረሰብ ተከፋፈለ በተጻረረ መንገድ። እዚህ ውጭ ያለው የአንድነት ኃይሉ እንደዚያ ዓይነት አደጋ ውስጥ ሲገባ፣ ለአገር ቤቱም ተረፈ። መቼም ምንም ያህል ትምህርት ቢኖርህ፣ ምንም ያህል እድሜ ቢኖርህ ሰው ነህና አንዳንድ ጊዜ አስተውሎትህ የስሜትህ ተገዥ ይሆናል። እናም ሚዛንህ ትክክል አይመጣም።
አዎን አውቃለሁ። በወቅቱ እንዳልከው ጥቂቶቹ እንደዚህ ብሉህም ብዙዎች፣ በተለይም ተስፋዬን የሚያውቁ፣ መጽሐፉን ያነበቡና የመረመሩ ካንተው ጋር ነበሩ። እኔም አንዱ ነበርሁ። ጽሑፍህንም በደንብ አድርጌ አምብቤዋለሁ።
ትክክልም ነበር። አንዳንድ ሰው ስለሚቸኩል፣ ነገርን አዙሮ ወዲያውኑ ማየት ይሳነዋል። አሁን ግን ይረዱታል አለኝ።
እኔም ቀጠልሁ። በሕግ ትምህርት ቤት ውስጥ መምህራኑም ሆነ የሕግ መጽሐፍት የሚያስጠንቅቁት፣ በተለይም በዳኝነትም ሆነ፣ በሕሊና ፍርድ ጊዜ በተቻለ መጠን ስሜትህን ልትቆጣጠር ይገባሃል። አለዚያ ፍርድህ ፍርደ-ገምድል ይሆናል። ይህ ደግሞ ስዎችን፣ ሕዝቦችን በጣም አድርጎ ይጎዳል በሚል። እንደዚያም ተምረህ ወጥተህ፣ እንደዚያም አውቀህ ወጥተህ መቼም ሰው ነህና ስሜት ውስጥ ትገባለህ። የራሴን አንድ ምሳሌ ልጥቅስልህ አልኩት ወጣቱን። ወጣቱ ምንም ሳይለኝ ብቻ አትኩሮ እያየኝ ማዳመጡን ቀጠለ።
ፍየል ከመድረሷ. . . .
ወደ 1984 ዓ.ም ይመስለኛል ኦነግ ከጊዜያዊ መንግሥቱ እንደወጣ፣ በአባላቱ ላይ ያልተፈጸመ ግፍ ይኖራል ብዬ አሁን ማሰብ ይከብደኛል። አንድ ቀን የቴሌቪዥን ዜና ሳዳምጥ፣ የጎተራን ዲፖ ነዳጅ ሊያቃጥሉ ሲሉ የተደረሰባቸው የኦነግ አባላት ተያዙ በማለት የተወሰኑ ሰዎችን አሳዩን። ታውቃለህ በወቅቱ በልቤ ያልኩትን፣ እነዚህን የምን ፍርድ ቤት እንዳሉ ከነነፍሳቸው ማቃጠል እንጅ ነው ያልኩት። ነዳጁ እንደተባለው በፈንጂ ቢመታ አዲስ አበባችን የምትሆነው እየታየኝ። የሚያልቀው ሰው ብዛት እየታየኝ። ደግሞም በየወቅቱ ከሚነዛው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ጋር ተዳምሮ። ጊዜውም ገና ልጅ ስለነበረ የወያኔም አካሄድና መንገዱ በቅጡ ባልተለየን ወቅት ነው። ፍርዴም ታዲያ ሙሉ ለሙሉ ስሜታዊ ፍርድ ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ምግብ ኮርፖሬሽን የሚባል ድርጅት ውስጥ የሕግ አማካሪና ነገረፈጅ ነበርኩና ፍ/ቤት አልገባሁም። ባልገባም የሕግ ሰው ሆኜ እንደዚያ ማለት አይገባኝም ነበር። እንደዚያ ዓይነት ስሜታዊ ውሳኔ መስጠት የአስተውሎት ማጣት ነበር።
ግና በ1986 ጥር 1 የክልል 14 ይባል የነበረው በጊዜው አጠራር የዞን ወይም በኋላና በቀድሞው አጠራር ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ ሆኜ ተሾምሁ። ያጋጣሚ ሆኖ ከፍተኛ የሆኑ የወንጀል ጉዳዮች የሚታዩበት ችሎት ተሰየምሁ። የችሎት አሰራርን  እስክለምድ ድረስ፣ አንዳንድ የቆዩ መዝገቦች ይሰጠኝና ዝም ብዬ ለማሟያ ያህል የግራ ዳኛ ሆኜ እያነበብሁ እችሎቱ እቀመጣለሁ። በሁለተኛው ሳምንት ግን ያገኘሁት መዝገብ የሚያስደነግጠኝ መዝገብ ሆኖ ተገኘ። እሽፋኑ ላይ እነ ባየራ ይላል። የጎተራውን ዲፖ ነዳጅ ሊያቃጥሉ ሲሉ የተያዙ የኦነግ አባላት ይላል የወንጀሉ ርዕስ። ያ እውጭ ሆኜ የፈረድኩት ጉዳይ በፍርደ-መንበር ተቀምጬ ልፈርድ እፊቴ አፍጦ መጣ። ያጋጣሚ ነገር ያስደንቃል። ተከሳሾችን አሁን በትክክል አላስታውሳቸውም ወደ  ተከሳሾች ይመስሉኛል። መዝገቡ ሲታይ ለሁለት ዓመት ሙሉ ምስክሮች ባለመቅረባቸው በሚል ብቻ እየተቀጠረ የመጣ መዝገብ። ከሰብሳቢው ዳኛ ተከሳሾችን ጥራና ለሁለት ወር ያህል ቅጠራቸው ይሉኛል። ለምን ሁለት ወር? የኔ ጥያቄ። እባክህን ምስክር አሁንም አላመጡም ዐቃቤ ሕጉን እንደጠየቅሁት አሉኝ። ብዙም እችሎት ውስጥ መነጋገር አስቸጋሪ በመሆኑ ክርክሩን አልቀጠልኩበትም። እኔ ለሁለት ወር አልቀጥርም አቶ አሰፋ ብቻ አልኳቸውና የመዝገቡን ተከሳሾች ጠራሁ። እዱኳ ገቡ። ማንነታቸውን ጠይቄ ከማብቃቴ አቶ ባየራ የተባሉ አንደኛው ተከሳሽ፣ ኧረ ጌቶቼ ፍረዱብን ወይም ልቀቁን እያሉ ጀርባቸውን ዞር በማድረግ እዩት የተፈጸመብኝን ግፍ በማለት ልብሳቸውን ወደ ማጅራታቸው ከፍ አደረጉ። ለዓይን የሚዘገንን፣ የሰው ልጅ ጭካኔን የሚናገር፤ የመንግሥትን ፍጹም የሆነ ጭካኔ የሚያሳይ ነገር አየሁ። ጀርባቸው ተግተልትሎ ቁስሉ ገና በመዳን ላይ ያለ ነው። የአምላክ ያለህ! ያሰኛል። ታዲያ የሃዘኔን መግለጫዎችን በወቅቱ እንደምንም ተቆጣጠርሁ። የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሲጠራ የደህንነት አባሎች ስለሆኑ እና በየቦታው ስለሚዘዋወሩ ሊገኙ አልቻሉምና ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን የሚል መልስ የችሎቱ ዕቃቤ ሕግ ሰጠ። በዚህን ጊዜ ሰብሳቢው እባክህን ወደዚያ ራቅ አድርገህ ቅጠረው አቶ ወልደሚካኤል አሉኝ ዳግም።
መልስ አልሰጧቸውም። ብቻ ለሳምንት ቀጠርሁ። ተከሳሾቹ ደስ ብሏቸው ወጡ። ትዝ ይለኛል ሰብሳቢው አቶ አሰፋ (ከፌዴራል ፍ/ቤቶች መቋቋም በኋላ ጠበቃ ሆነው ሲሰሩ ቆይተው እኔ ከአገር ከወጣሁ በኋላ አርፈዋል እንደሰማሁት) ንዴታቸው በርትቶባቸው እያጉረመረሙ ቀጥሎ ያለውን ሥራ በቅጡ መሥራት አቃታቸው። እኔ ደግሞ በሆዴ ከመሾሜ መባረሬ እየታየኝ፣ እንዲህስ ከምሰራ የፈጠረኝ አምላክ ያውቃል ለምን አልወጣም፣ ለምን አልባረርም እያልሁ ራሴን በራሴ ማጽናናቱን ተያያዝሁ። በዚሁም መዝግቦች አለቁና ወደ ጽ/ቤታችን ገባን። አቶ አሰፋ ገና ካባቸውን ሳያወልቁ፣
“ፍየል ከመድረሷ፣ ቅጠል መበጠሷ።” በሚል ተረት ጀምረውኝ፣ አቶ ወልደሚካኤል ይህ ፍ/ቤት ነው። ሰብሳቢው በችሎት ያዘዘውን መፈጸም ግዴታ ነው አሉኝ። ሕጋዊ ያልሆነውንም? ብዬ ጠየቅኋቸው። በዚህን ጊዜ አራት ነበርና በተለይ እችሎቱ የነበረው ቀኝ ዳኛው፣ ሮመዳን ጣልቃ ገብቶ ምንድነው የሚሉት አቶ አሰፋ? ምን አድርግ ነው የሚሉት። ደግ አደረገ ብሎ ሲያፈጥባቸው በአንድ በኩል፣ በሌላው ደግሞ እጽ/ቤት የነበረውም ዳኛ፣ ይሁንም ተጨመረ። ወልዴ አድርጎት ከሆነ ትክክል ነው የሰራው። እኛ ተሸንፈን ነው መዝገቡ የቆየው። አሁንስ እርሶ አበዙት በማለት ተንጣጣባቸው። ሁለቱም የሆዳቸውን ቁስል ባጋጣሚው አከኩት። የእንግዳነቴን አጋጣሚ ተጠቅመው ከጧቱ ይህች ባቄላ ያደረች እንደሆነ . . . ሊሉኝ የነበረው በዚህ አከኋን ቀዘቀዘ። እናም በኋላ በቀነ-ቀጠሮው ዳግም ምስክሮቹ ስላልመጡ፣ በተለዋጩ ቀጠሮ ምስክሮቹ ካልቀረቡ ተከሳሾቹን የምንለቅ መሆኑ አስጠንቅቀን ትዕዛዝ ሰጠን።
በዚህ ርምጃ የተሸበረው ዕቃቤ ሕግ የደህንነት አባል የተባሉትን በቀጠሮ ዕለት አቀረባቸው። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር በወቅቱ የነበረው አራንሽን የተባለ ይመስለኛል ከሌሎች ሁለት የወያኔ አባላት ጋር ቀረቡ።
በወቅቱ የከፍተኛ ፍ/ቤት ጠባቂ ፖሊሶች የቀድሞዎቹ ስለነበሩ መሣሪያ ተቀምተው ባዶ እጃቸውን ነው የሚጠብቁት።
አንድ ምስክር መስክሮ ሲሄድ ለሌላኛው ጥያቄዎችን ለማስተላለፍ ቢሞክር ከልካይ የለም። በዚህ ላይ አሁን የቀረቡት ምስክሮች የወያኔ ባለሥልጣናትም ስለሆኑ የፈለጉትን ቢያደርጉ የሚቆጣጠራቸው የለም፡፡ እናም ዘዴ ፈጠርን። የችሎቱ ዳኞች አራት ነን። ሦስታችን ወደ ችሎቱ ስንወጣ አንዱ እጽ/ቤት ምስክሮቹን ይዞ ተቀምጦ፣ ምስክሮቹን አንድባንድ በጠራን ቁጥር እንዲልክ አደረግን። በዚህም የተዋጣ ውጤት አገኘን። አመሰካከራቸው ከመሣሪያ መያዝ ውጭ ወዲህና ወዲያ ሆኖ ተገኘ። እናም፣ በውጭ የሰጠሁት ፍርድ ተሻረ። በነጻ ከዋና ወንጀሉ ለቀን፣ መሳሪያ መያዛቸው ብቻ ስለተመሰከረባቸውና ሊያስተባብሉም ስላልቻሉ የታሰሩበትን በቂ አድረገን ለቀቅናቸው። ግና ውሳኔያችን ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ታገደ። በዚህም የተወሰንን ዋጋ ከመክፈል አልዳንንም በወቅቱ። ይህ ወደፊት ይገልጻል። ብቻ ይገበሃል? ለማለት የፈለግሁት፣ ማንም ሰው ቢሆን በተወሰነ ጉዳይ፣ በተወሰነ ወቅት እስሜት ውስጥ ይገባል።
እናም፣ እኔ እነዚያ በእኔ ላይ አንዳንድ ነገሮችን ባሉት ላይ አይደለም በወቅቱ ያዘንሁትና የፈረድሁት፣ ይኸ እርኩስ ከፋፋይ ሰው ላይ ነው። እነርሱ ሳይሆኑ ደመኛዬ አድርጌ የያዝሁት እርሱን ተስፋዬን ነው። እነርሱ ከልባቸውኢትዮጵያዊነት አይፋቅም፣ እንዲያውም ይኮሩበታል እንጅ። እነርሱ እውነትን ሲያውቁ ይረዱታል። እናም ይመለሳሉ። እርሱ ዘንድ ኢትዮጵያዊነት ስለሌለ፣ እውነት ስለሌለ ይብሱን ወደማጥፋት ይሄዳል እንጂ አይመለስም። እርሱ ገዳያዋ ነውና። ስለሆነም፣ ነገሬ እርሱን መከታተሉና ማሳደዱ ላይ ነበር የተሰማራሁት ብዬ አበቃሁ።
ከዚያም አለማየሁ የነገረከን ምሳሌ ሳይሆን፣ የሆነ ድራማ ይመስለኛል። እንዴት ደስ የሚል ነው? ካለ በኋላ፣ በዚህ ሰው ላይ በመጽሐፍ መልክ ሊጻፍ የሚችል መሰለኝ አለኝ። ሰነዶቹን ካየሁ በኋላ ብንነጋገር ይሻላል አልኩት። ለሁሉም ትምህርት ስለሚሆን መጻፍ አለበት አለኝ ከረረ አድርጎ። በመጠኑም ቢሆን የሕግ ሰው ብሎም ዳኛም ስለነበርሁ ሁሌም ለስሜት ቶሎ ብሎ ያለመገዛትን ስንቄ ስላደረግሁ፣ አሁንም ለወጣቱ መልሴ ያመጠሃቸውን ልያቸውና ላመዛዝናቸው  አልኩት። ወጣቱ ግን ይዞ የመጣቸውን ማስረጃዎችን ከተስፋዬ እጅ መንጥቆ ለማውጣት ካደረገው ተጋድሎ ጋር እያዛመደ አዎን ጋሽ ወልዴ በርግጠኛነት እለሃለሁ አንድ መጽሐፍ ይወጠዋል። ያለአንተ የማምነውና ይጽፈዋል የምለውም ሰው የለኝምና ቶሎ እባክህን ጀምር። አሁን በያዘው የስደተኛው ማስታወሻ ላይ ቀሪውን መርዝ ረጭቶ ከማውጣቱ በፊት ጣደፍ፣ ጣደፍ አድርገህ ቶሎ አውጣው የሚል ወታደራዊ ትዕዛዝ ዓይነት ሰጠኝ። ወጣቱ ልጅ ያልኩት ከመያድ ጀምሮ እስከ ቅንጅት የወጣት አባልና ሃላፊ ሆኖ የሰራ፣ ምርጫ 97 ባመጣው መዘዝ ከቅንጅት መሪዎች ጋር ለሁለት ዓመታት ያህል በቃሊቲ ዘብጥያ ተንገላቶ የወጣ፣ ከዚያም በአገር በሰላም መኖር ባለመቻሉ ወደ ስደት ወጥቶ የሚገኝ ነው። አለማየሁ ይባላል። እዚህ ኔዘርላንድ ለእኔ ጎረቤት በሆነች ህልቨርሱም በተባለች ወረዳ ውስጥ ይኖራል። ያ የትግል መንፈሱ አሁንም ከአለማየሁ ጋር አለ። ተስፋዬ በየማስታወሻዎቹ አልፎ አልፎ አለማየሁን “ትንታግ” ይለዋል። እኔም ቃሉን የተጠቀምሁት ለዚህ ነው። እናም፣ አለማየሁ ያመጣቸውን የማስታወሻ ሰነዶችን ለያይቼ ለማየትና ለማስተዋል እንደሞከርሁት፣ ከቡርቃ ዝምታ ጀምሮ ተስፋዬ ከሚያገለግላቸው ጌቶቹ ጋር የተለዋወጠበትን ጭምር አመላካቾች ናቸው። በመሆኑም፣ ሰንዶቹን እርሱ ከጻፋቸው መጽሐፍት ጋር እያመሳከሩና እያመዛዘኑ ቢጻፍ ለትውልድ በማስተማሪያነቱ የሚበቃ አንድ አነስተኛ መጽሔት፣ አለያም መጽሐፍ ለማውጣት ወደ ሚቻል መደምደሚያ ላይ ደረስሁ። እናም፣ በተቻለኝ መጠን በፈርጅ ፈርጁ ነድፌ አስቀመጥሁ። በዚህም ከአለማየሁ እየተረዳዳን መጽሐፍ እንደምንችል ነግሬው ተስማማማን። በዚህ መልክ ተጀመረ።
ተስፋዬም ገብረአብ በኤውሮፓ ኔዘላንድስ ለስደት የሚያበቃውን ወረቀት ካገኘ በኋላ በደባልነት የተቀመጠው አለማየሁ ቤት ነው። የተባሉትን ማስረጃዎችን አለማየሁ በነደፈው ጥበቡ ያገኘው ይህንኑ አጋጣሚ ተጠቅሞ ነው። ብቻ ነገሩ በሬ ከአራጁ ጋር ይውላል ዓይነት ሆነና ታየ። ቀደም ብሎ በፌዴራል ፍ/ቤቶች አስተዳዳሪ የነበረው ሰው በኮራፕሽን መጋለጡን እንደሰማሁ፣ “ለሁሉም ጊዜ አለው” በሚል ርዕስ በመጠኑም ቢሆን፣ ከፍ/ቤቶቹ ዋና ተዋንያን ጀምሮ ያለውን ኮራፕሽን ለመነካካት መሞከሬ ይታወሳል። ያ አገር ውስጥ ከነበረ፣ ከፍ/ቤት ጋር በተያያዘ ነበር። የዛሬው ግን በመግቢያው ላይ እንደተመለከተው ከአገር ውስጥ ሳይሆን፣ ከፍ/ቤት ጋር በተያያዘ ሳይሆን፣ እዚሁ እስከ ሳይበሩ የዘለቀ ነው ከላይ ለመጠቃቀስ እንደሞከርሁት። ተስፋዬ ገብረአብ በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያዊያን ላይ በደራሲነት ስም ዘው ብሎ ገብቶ ስለፈጸመው ደባና የስለላ መረብ።
ክፍል 2.
ተስፋዬ ገብረአብ ማነውዜግነቱ፣
ወያኔ-ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በዘር በጎሳ፣ በዘር ከፋፍሎን እያናቆረን ዓመታትን አስቆጥሮአል። ያልተጻፉ መርዘኛ መጽሐፎችን እያነባነቡና እየተረኩ ጨዋውን ሕዝብ ለበቀል ማዘጋጀቱን ቀጥሎአል። ሕዝብ እንዳይተማመን፣ ርስበርሱ እየተጨፋጨፈ እንዲለያይ፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ተበታትና እንዳትኖር ጉድጓድ መማሱን ቀጥሎአል።
የበደኖ፣ የአርባጉጉ ክስተት እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ የተፈጸመ ድርጊት እንዳልሆነ ቁልጭ ብሎ የታየው ግን ከተስፋዬ “የቡርቃ ዝምታ” መርዛም መጽሐፍ በኋላ ነው። “ነፍጠኛ” በሚል ተቀጽላ በታጀበ ስልታዊ የወያኔ ደህንነቶችና ካድሬዎች ርምጃ ያለቁት የአማራ፣ የጉራጌ እና የሌሎች ዘሮች ቤት ይቁጠረው ብሎ ብቻ ማለፉ ለጊዜው በቂ ነው። ታዲያም ተስፋዬ ደራሲ ነኝ ይላል። በተከታታይም መጻፎችን አውጥቶአል። ደጋፊዎችንም አትርፎአል። ለመሆኑተስፋዬ ማነው? እውነት ጋዜጠኛ ወይስ ደራሲ ወይስ ሰላይ? የሚሉ ጥያቄዎች በተወሰኑ ማህበረሰባችን አእምሮ መግባታቸው አይቀሬ ነው። ኢትዮጵያዊ መሆን ያለመሆኑ ላይ ግን ከጥቂቶቹ በስተቀር፣ አብዘኞቻችን አልተጠራጠርንም። ግና ጊዜው ደረሰና የብዙዎች ጥርጣሬ በተለይም የነዚያ የነጻው ፕሬስ አባላት ጩኸት እውን ሆኖ ሊታይ ብቅ አለ። እንዴት?
ተስፋዬ ገብረአብ በ1960 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ምድር፣ በደብረዘይት ከተማ ተወለድሁ ባይ ነው። እስከ አሥራ ሁለተኛ ድረስ ከተማረ በኋላ ወደ ሐረር ፖለቲካ አካዳሚ ሂዶ በ1980 ዓ.ም የጦር ሜዳ ጋዜጠኛነት ኮርስ ውስዶ ተመርቆአል። ከዚያም እንደሚለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ሂዶ በመሥራት ላይ እንዳለ በኢህአዴግ ጦር ይማረካል።
ወያኔ-ኢህአዴግ ኢትዮጵያን በ1983 ዓ.ም ሲቆጣጠር ከሠራዊቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ ገባ። በ1988 ዓ.ም ወደ አሜሪካ፣ ሲያትል ተልኮ የራዲዮ ጋዜጠኛነት ትምህርት ተከታትዬ ተመልሻለሁ ይላል እጁን ለሰጠበት አገር ሲል፣ በደራሲ ማስታወሻ ላይ ግን ወደ አሜሪካ ሲያትል የሄድኩት ለረፍት ነበር ይላል። የትኛው እውነት እንደሆነ መገመት የሚቻለው ግን የተስፋዬን ማንነት መገንዘብ ከቻልን በኋላ ነው። ተስፋዬ በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ውስጥ በሃላፊነት ሰርቶአል። እፎይታ የተባለ አሳታሚ ድርጅት፣ እና መጽሔት ሥ/አስኪያጅ እንደነበረም ይታወቃል። ከዚህ አልፎ ተርፎም ተስፋዬ ቀንደኛ የወያኔ ደህንነት አባልም የነበረ ለመሆኑ ወደ ፊት የምናይ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን ተስፋየ በሥራ ላይ በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ ተስፋዬ ከላይ የገልጽሁትን መጽሐፍ፣ “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ”፣ ጨምሮ ወደ ሰባት  የሚሆኑ መጽሐፍትን አሳትሞ ለንባብ አብቅቶአል። በአጻጻፍ ዘይቤውና አጣጣሉ ተስፋዬ የፈጠራ መጽሐፎችንና ተውኔቶችን አዘጋጅቶ ለማውጣት እና የአንባቢያን ቀልብ በግርድፉ ለመሳብ መቻሉን ማሳየት የሚችል ሰው ነው።
ተስፋዬ በተለይ እዚህ ውጭ በወጣበት ጊዜ እኛን ኢትዮጵያዊያንን ሊቀርበን የቻለው ኢትዮጵያዊ ለመሆኑ አጽንዖት በመስጠት ነው። ጠርጥረው ሲጠይቁት፣ እኔ ተወልጄ፣ ያደግሁባት፣ እና እትብቴ በተቀበረባት ቢሾፍቱ ወይም ደብረዘይት ኢትዮጵያ ነው። ማንም ኢትዮጵያዊነቴን ሊቀማኝ አይችልም ይለናል አስረግጦ። እናም በዚህ ጠንካራ አነጋገሩ ኢትዮጵያዊውን መንፈስ ጸጥ ያስደርጋል። ያው የሚባለውን የቢሾፍቱን ቆሪጥ ተስፋዬ ተጋርቶ ይሆን? የቢሾፍቱ ቆሪጥ ለመኖሩ፣ ወይም ተስፋዬ ለመገራቱ እግዚአብሔር ይወቀው ከምል ውጭ አልዘልም። አንዳንዴ ችግር ሲለን፣ የማናምነውን ነገር እያንሳን ወደ እውነትነት መለወጡ የሰው ባሕርይ ሆኖ ነው እኔም ጠቀስ ማድረጌ። የክርክሩ መሠረት ኢትዮጵያዊነት፣ ወይም የኢትዮጵያ ዜግነትን ላይ ነው። እናም ኢትዮጵያዊነቴን ማንም ሊነጥቀኝ አይችልም እያለ ተስፋዬ ፎክሮአል፣ ተሳልቆብናልም።
ለነገሩ ብዙዎቻችን ቀደም ብሎ አዎን! ማንም ይህን በመወለድ ያገኘውን የኢትጵያዊነት ዜግነቱን በሕግ ካልሆነ በስተቀር፣ ሊከለክለው፣ ወይም ሊነጥቀው አይችልም ብለናል። በኢትዮጵያ የዜግነት ሕግ መሠረት አንድ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ በመወለዱ ብቻ የሚያገኘው ስለሆነ። ታዲያም፣ ቁም ነገሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለመወለዱ ላይ አልነበረም። ወይም ኢትዮያዊነቴን ማንም አይነጥቀኝም በማለቱ ላይ አልነበረም። ቁም ነገሩ ተስፋዬ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለመሆኑ ላይ እና ተግባሩ ላይ ነው። እንደሚለው ከልብ ኢትዮጵያን አገሬ ናት ብሎ አምኖ እየኖረባት ነበር? በሚለው ጥያቄ ላይ ነው። የሚጽፋቸው ነገሮች ኢትዮጵያን የሚገነቡ መሆን ያለመሆኑ ላይ ነው። ጽሑፎቹ እውነት ላይ መመሥረት ያለመመሥረት ላይ ነው።
ከቡርቃ ዝምታ መጽሐፉ በኋላ የነቁ ኢትዮጵያዊያን፣ በተለይም የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ሰሚ ባያገኙም በወቅቱ፣ ተስፋዬን አንተ ኢትዮጵያዊ አይደለህም፣ ኤርትራዊ ነህ፣ የሻቢያ ቅጥረኛ ነህ፣ አገር ማፈራረስ ላይ፣ ደም ማፋሰስ ላይ የተሰለፍህ ነህ እያሉ ጩኸውበታል፤ ሽንጣቸውን ገትረው ተሟግተውታል። በዚህም ዋጋ የከፈሉም አይታጡም። ሙግታቸው የኢትዮጵያ ዜግነቱን ለማሳጣት አይመስለኝም። ከድርጊቱ በመነሳት፣ ድርጊቱን እየኮነኑ እንጅ። ግን ተስፋዬ የዋዛ ሆኖ አልተገኘም። በወያኔ የኋላ ደጀንነትና አይዞህ ባይነት እንዲሁም የካድሬነቱ እኩይ ጥበቡ ተጨምሮበት መልሶ መላልሶ ኢትዮጵያዊነቱ ላይ አጽንዖት በመስጠት ምሎ ሲገዘት ከርሞአል። የተወሰኑትንም ለማሳመን ችሎአል።
ግና “እውነት ትዘገያለች እንጅ አትቀበርም”፣ “እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” የተሰኙ አባባሎች በእንዲህ ያለ ወቅት ወደ ወዘናችን ገባ ይላሉ። እናም፣ የተስፋዬ የዜግነቱ ጭምብል ጊዜውን ጠብቆ ላይደበቅ እንደ ጅብራ በፊታችን ቀጥ ብሎ ሊታይ የግድ ሆነ። እናም፣ ሁሉም ነገር ጊዜውን ጠብቆ እመር ብሎ መውጣቱ አይቀሬነቱ በተስፋዬም ታየ። በእንዴት? ትንታጉ አለማየሁ ካመጣቸው ሰንዶች ውስጥ ነዋ። ከምን ዓይነት ሰነድ? መቼ? ሰንዱ የተስፋዬ መታወቂያ ሰንድ። ተስፋዬ ወደ ኬንያ እንደገባ ምንም ያህል ሳይቆይ፣ ከኤርትራ ኤምባሲ የኤርትራ መታወቂያ ደብተር ካገኘበት የኤርትራ ዜግነቱን ከሚያረጋግጠው ሰነድ። መታወቂያውና የሰፈሩት መለያዎች የሚከተለውን ይመስላሉ።
1. መታወቂያው፣
የተስፋዬ እንዲህ ይላልም፣
እ.ኤ.አ በ14-06-2001፣ በቁጥር 1665582 የተመለከተና ከአሥመራ በትግሪኛ እና በዐረብኛ ተጽፎ የተላከለት፣ “ግዝያዊ መንግስቲ ኤርትራ (ህ.ግ.ሓ.ኤ)፣ ኤርትራዊ ወረቅዋት መንነት” ብሎ የሚጀምረው መታወቂያ የሚከተለውን የተስፋዬን እንፎርሜሽን ይዞአል።
ስም፦ ተስፋየ ገብረኣብ ሃብተዴን
ጾታ፦ ተባ
/ልደት፦ 28.08.1968  
ቦታ ልደት ደብረዘይቲ
ቁጽሪ ER 1665582
ስራሕ፦ ጋዜጠኛ
ዓዲ/ከተማ ናይሮቢ
ዞባ፦ ኬንያ
ምምሕዳር፦ ናይሮቢ
ዝተዋህበሉ ቦታን ዕለትን፦ አስመራ 14.06.2001
ክታም በዓል መዚ ተብሎ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህተም አለበት። ከዚህም ሌላ በመታወቂያው በስተቀኝ በኤርትራ ሁለተኛ ቋንቋ በሆነው በዐረብኛ ይኸው ፎርም ተሞልቶአል። እንግዲህ አህዛብ ምን ትላለህ? ተስፋዬን በእንዲህ የጠረጠርን እነማን ነበርን? ለምን? የጥርጣሬዎቻችን መነሻው ምን ነበር? ያልጠረጠርንና ፈጽሞ ወደ ሃሳባችን ያላስገባን እነማን ነበር? ለማንኛውም ትዕግሥት ኖሮን እንከታተል ብቻ።
2. ራሱ መታወቂያው፡
የቀጠለ ቅጥፈት፣
ከዚህም በተጨማሪ፣ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ገጽ “247” ላይ የተለመደው የተስፋዬ ቅጥፈት፣
የወያኔ ዲፕሎማቶች ፓስፖርቴን ናይሮቢ ላይ መንጠቅ የቻሉ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያዊነቴን መንካት እንደማይችሉ ግን አልተረዱትምበሚል ተዥጎርጉሮ ተቀምጦአል። ከቅጥፈት ወደ ተሻሻለ ቅጥፈት። አዲስ አበባ ላይ ያልነጠቀው ወያኔ፣ በሰው አገር ናይሮቢ አሳዶ እንዴት አድርጎ ሊነጥቀው አሰበ? እንዴትስ ይቻላል? የማይመስል ወሬ ለሚስትህ . . . ይላሉ አባቶቻችን በዚያው ጊዜ በነበረው አስተሳሰብ። በእቁዱ መሠረት የተወሰነውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለመያዝ በመቻሉ ነው እንደዚህ የልብ ልብ ተሰምቶት እንደ እምቦሳ እየቦረቀብን የነበረውና ያለው። ከላይ ለማሳየት እንደተቻለው፣ ተስፍሻ እንደሆነ ገና ናይሮቢ ከመግባቱ ነው የኤርትራ ዜግነትና ፓስፖርት የተሰጠው። ጊዜ ጊዜን ወልዶ፣ ቀን ቀንን ተክቶ የውሸት ክር መዘዝ እስኪል ድረስ እንጂ እውነት እስከነካቴው እንደተሸሸገች እስከ ዘለዓለሙ አታሸልብም። ተስፋዬ ግን ያየው የፊቱን፣ በዚያ በዚህ ብሎ የሚያገኘውን ብቻ ነበር። አሁን ግን ሁሉም እየተናደ ሲመጣ ተስፋዬ ስርቅ፣ ስርቅ ሳይለው የቀረ አልመሰለንም። እናም የሚይዘውን የሚጨብጠውን ወደ ማጣቱ የደረሰ ይመስለናል። አይ የሰው ልጅ ሞኝና ተላላ ነው። የዛሬ መብለጥ የነገን መበለጥን ያስከትላል። ራስን መልሶ መላልሶ ካላዩት የቁም ሞትን ወደ መሞቱ ያደረሳል። ተስፋዬ በኢትዮጵያ ተወለደ እንጂ፣ በኢትዮጵያ አድጎ ለቁም ነገር በቃ እንጂ፣ የበላበትን ወጪት ሰባሪ ነው። እንዲህ ይሆናል ብሎ ከቶ ማን ያስብ ይሆን?
ተስፋዬ አሁንም አላረፈም። በኢትዮጵያዊነት ስም ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊነትን ለመግደል፣ ለማስገደል፣ ለማጥፋት የጀመረውን ሴራ። ወደ ኤርትራ፣ እንደገና ወደ ኤርትራ እንደ ውሃ መንገድ መመላለሱን ተያይዞታል። ለአለቆቹ እዚሁ ኔዘርላንድ እንዳልተመቸው፣ መሥራትም ካለበት ወደዚያው ወደ መጨረሻ አገሩ ሂዶ በነጻነት መሥራት እንዳለበት ማሳሰቢያ እየላከ ነው። የሚሄደውም መመሪያ ለመቀበል መሆኑን መገመት ይቻላል። እዚህ ዲያስፖራ ባለው ኢትዮጵያዊ ላይ እንዴት መጫወት እንደሚገባ። ግን እውነትን ለሚወስነው ቸሩ አምላክ ምስጋና ይግባውና አሁን ወደ ማብቂያው ደርሷል።
ባሕርይው፣
እኔ ቀደም ብዬ ተስፋዬ ገብረአብን በአካል ሳይሆን፣ በስም የማውቀው “ቡርቃ ዝምታን” መጽሐፍ ባወጣበት አከባቢ ሰው በየቦታው የተለያየ ግምታዊ ስንክሳሮችን ሲያወርድበት ሰምቼ መጽሐፉን አግኝቼ ካነበብሁ በኋላ ነበር። ብፈልግ ኖሮ ገጽታውን በወቅቱ ለማየት እችል ነበር። ግን መጽሐፉን አንብቤ ስጨርስ ተስፋዬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ አክሮባት የሚጫወት፣ ዋነኛ የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን ስለገመትሁ ላየው መፈለግ ብቻ ሳይሆን፣ አልተመኘሁም። እስከምረዳው ድረስ፣ ጋዜጠኛ ወይም ደራሲ ማለት “እውነተኛ፣ መንፈሳዊ፣ መምህር፣ አባት” ማለት ነው ልንል እንችላለን። አንድ ደራሲ፣ ወይም ጋዜጠኛ ከአጻጻፍ ችሎታው ወይም ክህሎቱ ይልቅ በያዘው ጭብጥና እውነት ይለካል። ያየውን፣ የሰማውና ያረጋገጠውን እውነት እንደወረደ ለእድምተኞቹ ያፈሳል። ደራሲያን እውነትን እንጂ የውሽት ፖለቲካ፣ ሕዝብን እርስ በርስ የሚያባላ፣ የሚያጋጭ፣ አገርን የሚከፋፍል አይጽፉም። ሕዝብ በገዢዎቹ የአስተዳደር በደል ሲደርስበትም፣ ሰብአዊ መብቱ ተረግጦ የሕግ በላይነት ሲደመሰስ እውስጡ ገብተው፣ እውስጡ ኖረው፣ ከውስጡ ያዩትን፣ የሰሙትን እውነታ አውጥተው ጩኸቱን በሚኖሩበት ማህበረሰብ ስም በግንባር ቀደምትነት እያቀለሙ የሚጽፉና የሚያደርሱ እውነተኛ ደራሲዎች ወይም ጋዜጠኞች ይባላሉ።
በርግጥ ጋዜጠኞች እውነትን ለማወጣጣት ሲሉ የቅስቀሳ ድርጊቶችን (provocative) አካሄዶችን ይጠቀማሉ። በዚህም አንዳንዶቻችን ሳናገናዝብ ቶሎ ብለን ወደ ቁጣ እናመራለን። እነርሱ ግን ወደ እውነቱ ለመድረስ ያስችላቸው ዘንድ ለማወጣጣት የሚያደርጉት ዘዴ ይመስለኛል ከአንዳንድ እኩይ ተግባር ካላቸው በስተቀር። እናም በዚህ ዓይነት የደረሱበትን ለቆሙለት ሕዝብ ያሰማሉ። ደራሲ ለእውነት ተነስቶ፣ እውነት እየጻፈ፣ ለቆመለት ሕዝብ ራሱን ለመስዋዕትነት ያቀርባል። እውነተኛ ደራሲ ፊት ሐሰት ጉልበት የላትም። እንደ ጓያ ወዲያውኑ ተቀነጣጥሳትወድቃለች። በዚህም በቀደምትነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ደራሲያንና ጋዜጠኞች አገራችን ነበሯት፤ አሁንም አሉን። ከቀደሞቹ ጳውሎስ ኞኞ፣ አቤ ጉበኛው፣ እና በዓሉ ግርማ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ። በተለይ በዓሉ ግርማ በደርግ ውስጥ ተወልዶ፣ በውስጡ አድጎ፣ በውስጡ ያያቸውን እውነትን አውጥቼ፣ ሁሉን ዘክዝኬ እሰዋለሁ በደራሲው መጽሐፉ እንዳለው ሁሉ፣ ቃሉን ጠብቆ፣ አክብሮ በሮማይ ማግሥት ለቆመለት ዓላማ ለቆመለት ሕዝብ ተሰውቷል። ሕዝብ የማይረሳው፣ ታሪክ የማይረሳው ጀግና ደራሲ። አሁንም አሉን።
የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች አሁንም በአገር ውስጥ እነ እስክንድር ነጋ የመሳሰሉት፣ እውጭ ኮብልለው ከወጡቱ መካከል የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞ አሁንም የጉሮሮ ላይ አጥንት እየሆኑ ያሉት ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ፣ ኤልያስ፣ ደረጀ ሀብተወልድ፣ ፋሲልን፣ የቪ.ኦ.ኤ ጋዜጠኞች ( በተለይም አዲሱና ሰሎሞን ክፍሌ)፣ በጀርመን የአማርኛው ክፍል የሚሰሩት (በተለይም ነጋሽ መሐመድ በአገር እያለ፣ በድፍረት መለስን ስለኢትዮጵያ ባንዲራ ጠይቆ፣ ሁሌ ወያኔዎች ባንድራችንን ጨርቅ አሉት እያልን የምንናገረውን ያስተፋ. . .ታሪከኛ ጋዜጠኛ፣ እና ጓደኞቹ) የመሳሰሉ ለአብነት ይጠቀሳሉ። ደሞም በአገር ውስጥ ባይሆንም እውጭ ወጥተው ሙያውን ሽክን አድርገው ወያኔን መደበቂያ እያሳጡ ያሉና እሳት የላሱ እንደነ አበበ በለው የመሳሰሉ አሉ። እነርሱ እንደሻማ ደግመው ደጋግመው እየቀለጡ፣ እየወደቁ፣ እየተነሱ ከእውነት ላይሸሹ ቃል ኪዳናቸውን ሁሉ እያደሱ ቀጥለዋል። በአንጻሩ ደግሞ እንደነ ተስፋዬ የመሳሰሉ የእናት ጡት ነካሾች በአገር የጀመሩትን ወኔ ሰለባቸውን፣ እውጭ ከወጡም በኋላ የያዛቸው አባዜ አላሳርፍ ብሏቸው ቀጥለውበታል። ተስፋዬ ተተፍቶ ይሁን፣ ወይም በዓላማ ወደ 1993 ዓ.ም ውጭ አገር በስደት መልክ ወጥቶአል። በመጀመሪያ ወደ ኬንያ ከዚያም ወደ ደቡብ አፍሪቃ፣ ቀጠል ብሎም ወደ አባት አገር ወደ ሚልበት ወደ ኤርትራ ዘምቶአል። ተስፋዬ የወያኔ ቁልፍ ካዲሬና ጸሐፊ ሆኖ፣ በተለይም ውጭ በወጣባቸው የአፍሪቃ አገሮች ተቀምጦ ውስጠ-ወይራና መርዛም መጽሐፍትን አውጥቶ አስነብቦናል፤ የጋዜጠኛው ማስታወሻ እና የደራሲው ማስታወሻ። መጽሐፎቹም በየክፍለዓለማቱ በሚገባ ተቸብችቦለታል። ተስፋዬ የሰዎችን ስሜት እየሰረቀና የአዞ እምቧን እያፈሰሰ የመጻፍ ክህሎቱን ለማሳየት ሞክሮአል። በዚህ በማር በተለወሰ አጻጻፉ የተወሰኑ የማህበረሰባችን ክፍሎች አካሄዱንና ዓላማውን እንዳይረዱት ለማፈን ችሎአል። አልፎ አልፎ እንደተውኔት የፍቅር ገጠመኞችን እየሣለ ስለራሱ ዋልጌነት ማሳየቱ፣ እና በተለይም የማህበረሳባችንን ስሜት በስዬ ኮርኩሮ መግባት መቻሉ ለዓላማው ስኬት ተጠቃሾች ናቸው። መቼም ውሻ በቀደደ ጅብ ይገባል እንዲሉ ነውና ተስፍሽ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ የተከሰተውን ክፍተት አጋጣሚው ሆኖለት፣ በስዬ ወሽመጥ ገብቶ እያሰፋው ወደ ጫፍ እንዳደረሰው አይተናል።
ተስፋዬ የጥገኝነት ፈቃዱን በኔዘርላንድ ካገኘ በኋላ በካምፕ ተቀምጦ እንደማንኛውም ስደተኛ የመንግሥትን እጅ አልጠበቀም። ከቶ ምን ጎሎት? እኛን እየሰለበን ያገኘው ገንዘብ አለና። በተለያየ መጣጥፉ እኔ ተስፋዬ ስደተኛ የሚባል ስም ለመስማት አልፈልግም ይላል። በጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋና በመስፍን አማን አማካይነት ወደ አለማየሁ ቤት ዘው ያለው ተስፋዬ፣ በሚያዝያ ወይም በግንቦት አወጣለሁ የሚለውን መጽሐፍ የሚጀምር መሆኑን ገልጾ ጉዞውን ወደ ኤርትራ “አባት አገር” ወደ ሚባልበት አድርጎታል። በተስፋዬ አባት አገር ማለት እንደኛ እናት አገር እንደማለት ዓይነት ነው።
የራስን አገር ፈረንጆቹ በሚጠሩት መልክ መሆኑ ነው። የኤርትራ ባለሥልጣናትን ልብ ለመማለልና ለመግዛት ተስፋዬ የመረጠው ጥበባዊ ስያሜ። እናም ተስፋዬ የመኖሪያ ቤትን እንኳን ሳይጠይቅ ነው ጉዞውን ወደ ኤርትራ ተጣድፎ ያደረገው። ሚስቱና ልጆቹ ወዳሉባት አባት አገር ወደ ኤርትራ ስለመሄዱ ግን በግልጽ አልነገረንም። የነገረን ወደ ፑሽክን ወደ ተወለደባት ወደ ሩሲያ ነበር። ለምን? ቢባል ያው የተለመደውን ማደናገሪያ አካሄዱን ሲጠቀምብን ነው። ተስፋዬ በቃ ኤርትራ ቀረ ሲባል፣ የመጽሐፉን ሰባ በመቶውን አጠናቅቄአለሁ በሚል ተመለሰ። ለምን ወደ ኤርትራ? ለምንስ መመላለስ? የተባሉትን ጥያቄዎችን መልሰን መላልሰን መጠየቁ ወደ ትክክለኛው መልስ ያደርሰን ይሆን?
በቡርቃ ዝምታ ተስፋዬ በአገር ቤት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ እንደፈለገው ተጫውቶአል። በጋዜጠኛው ማስታወሻና በደራሲው እውጭ ባለነው ጭምር መርዙን ረጭቶብናል። አንዳንዶቻችን ግና አሁንም አንቀላፍተናል። እንደገናም ሊጫወትብንም ጩቤውን በመሳል ላይ ነው። ተስፋዬ በመስቀለኛ መንገድ እያቆራረጠብን ወሬዎችን ከእኛው እየለቃቀመ መልሶ ለእኛው በሬት ለውሶ ያቀርብልናል። እኛም ተመችተነዋል። ተስፋዬ እስከተመቸው ድረስ ለአባት አገር እያለ የማይፈነቅለው ድንጋይ፣ የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም። ተስፋዬ በባሕርይው ለዚህም ለዚያም የሚበጅ ሰው አይመስለኝም፤ ወደር የሌለው ጥቅመኛ ነውና። እናም ምርመራችንን እንቀጥል።
ክፍል 3.
ተስፋዬን በመጽሐፎቹ ውስጥ፣
በቡርቃ ዝምታ
ተስፋዬ ሐረር ጦር አካዳሚ ገብቶ በጦር ሜዳ ጋዜጠኝነት ሰልጥኖ የወጣው በደርግ ዘመን ነው። ሥልጠናውንም እንዳጠናቀቀ ወደ ጦር ሜዳ ይሰማራል። ብዙውም በጦር ሜዳው ሳይቆይ እንደሚለው ተስፋዬ ተማርኰ (እኔ ግን አለመሰለኝም) በወያኔ-ኢህአዴግ እጅ ይወድቃል። የሰለጠነበትንም የጦር ጋዜጠኝነቱን ሙያ በሥራ ላይ አውሎ የተለማመደው በወያኔ ቤት ነው። ወያኔ ኢህአዴግ በለስ ቀንቶት በኢትዮጵያ መንግሥትነት በትረ-ሥልጣኑን ሲይዝ ተስፋዬ የመገነኛ ብዙሃን ውስጥ ሃላፊ ሆኖ ከመሥራቱም በላይ ወደ ደራሲነትም ዘው አለ። የስለላ ደራሲነት። እናም፣ ተስፋዬና ኢትዮጵያዊነትን የምናይባቸው መስተዋቶች ጥቂት አይደሉም። በገሃድ የሚታወቀው ግን የቡርቃ ዝምታ የተባለው ትምህርተ-በቀል መጽሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ ከደጎቹ የኦሮሞ ማህበረሰባችን ክፍሎች፣ በተለይ የአማራ ዝርያ ባላቸው ላይ በቀል አርግዘው እንዲነሳሱ ተስፋዬ ይህ ነው የማይባል ቅመሞችን ቀምሮአል። በመጽሐፉ ትረካ መሠረት ቡርቃ በአርሲ በጭላሎ አውራጃ ከሚገኘው ካካ ከተባለው ተራራ ሥር የምትገኝ መንደር ናት።ተራኪው ተስፋዬ ገብረአብ፣ “ቡርቃ የተመሠረተችው ከምኒልክ ጦር ጋር ሲዋጉ በነበሩ አመጸኞች ነው።” ብሎ ይጀምራል ገጽ 17 ላይ። ገጽ 28 ላይ ደግሞ የመርዙን ቅመማ ሲጀምር፣ “የገበሬዎቹ ጥያቄ ይልና፣ የቡርቃ ገበሬዎች መሆናቸው ነው። “የገበሬዎቹ ጥያቄ ፖለቲካዊ ስሜት አለው። የሚያነሱት ጥያቄ የብሔር ጭቆናን ነው። አማሮች ከአካባቢው እንዲወጡላቸው ይፈልጋሉ። የበቀል ስሜት አርግዘዋል። ይህን መሰል መርዝ የቋጠረ ሁኔታ አንዴ ከተለኮሰ እንደሰደድ እሳት ነው የሚያያዘው።” ብሎ ይደመድማል ተስፋዬ። ጉድጓድ እየቆፈረ መርዝ የኦሮሞ ማህበረሰባችን እንዲቋጥሩ ለማድረግ እየሞከረ በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል እሳቱን ራሱ እየሎከሰ አንዴ ከተለኮሰ ይለናል ተስፋዬ እያጃጃለን።
ከዚህም ለጠቅ ያደርግና ተስፋዬ ገጽ 29 ላይ፣ “ገበሬዎቹ ቡርቃ ከመሬት በታች ውስጥ ውስጡን የሚሄደው ኦሮሞዎች በአማራ ወራሪዎች በመገዛታቸው እፍረት ተሰምቶት ነው ብለው ያምናሉ። እንደገበሬዎቹ እምነት የቡርቃ ወንዝ ጥንት እንደዋቢሽበሌ ደረቱን ገልብጦ የኦሮሞን ምድር ሁሉ ይዞር ነበር። ምኒልክ አርሲን ሲወርና የገዳውን ሥርዓት ሲያጠፋው ግን የቡርቃ ወንዝ በኦሮሞቹ ተነበርካኪነት አዝኖና አፍሮ መሬታችሁን ካላስመለሳችሁ እኔን አታዩኝም ብሎ አካላቱን ሁሉ እንደ ዘንዶ ሰብስቦ ከመሬት በታች እንደቀበረ ከጥንት ጀምሮ ይነገራል።” ብሎአል። መርዘኛ አባባል።
በመጽሐፉ ገጽ 324 ላይ ተስፋዬ በገጸባሕርይ የሳለው አኖሌ የተባለው የኦሮሞ ተወላጅ፣ “የኦሮሞዎችን ክብር ለማስጠበቅ ነፍጠኞች መረን ሲለቁ በወይራ ዱላ መቀጥቀጥ ያስፈልጋል የሚል እምነት ነበረው” ይልና ወረድ ብሎ ደግሞ፣ አልፎ አልፎ ደግሞ “ነፍጠኞች የኦሮሞን ክንድ ማወቅ አለባቸው” በሚል የማገዳደያ ፈንጂ ቀበሮ እናያለን።
በገጽ 373 ላይ የቡርቃ አካባቢ ኦሮሞች ነፍጠኛ በተባለው የአማራ ዝርያ ላይ ለመዝመት መዘጋጀታቸውን ተስፋዬ እንዲህ በሚል አነጋገር ያስቀምጠዋል። “ነፍጠኛን አርሲ ጂራ! ቆንጮራ ካስኔ ጭራ!” የሚል ቀራርቶ ቡርቃን ያንቀጠቅጣት ያዘ። ጃለታውን የገደል ማሚቶ አቀባበለው። ካካ፣ ባቱና ጭላሎ ተራሮች የቡርቃዎችን ቁጣና ቀራርቶ እየተቀባበሉ በድፍን የኦሮሞ ምድር ነዙት።” የኦሮሞ ማህበረሰባችን አልተንቀሳቀሱም፣ እንዲያውም አልሰሙትም እንጅ እንደ ተስፋዬ ጥንስስ ቢሆን ኖሮ አገራችን በርስበርስ ውጊያ ደምበደም ትሆን እንደነበር ማሰብ እንችላለን።
”ገጽ 374 ላይ ደግሞ፣
ኦሮሞዎች ያልያዙት የመሳሪያ ዓይነት የለም። ክላሽንኰብ ጠመንጃ፣ ውጅግራ ጠመንጃ፣ አልቤን ጠመንጃ፣ ፋስ፣ መጥረቢይ፣ ድንጋይ፣ የወይራ ዱላ፣ ከአህያ ጆሮ ተክል የተበጀ ችቦ፣ ክብሪት….በጠንካራ እጆቻቸው ጨብጠው ወደ ፍልሚያ ጋለቡ።” በሚል የኦሮሞ ማህበረሰባችን ነፍጠኛ የተባለውን ክፍል በጅምላ ይፈጅ ዘንድ የተወጠነ ቅስቀሳ መደረጉን አሳይቶናል ተስፋዬ።
እልፍ ብሎ ገጽ 379 ላይ፣
“ለመቶ ዓመታት የተረገጠውን የኦሮሞ ብሔርተኝነት ስሜት ባፋጣኝ ማደስ ተገቢ መሆኑን አምነንበታል።” ያሉት ተስፋዬ በገጸባሕርነት የፈጠራቸው እጮኞቹ አኖሌና ሃወኒ ናቸው። ይቀጥልና ተስፋዬ አባቦኮ ኮረብታ ታሪክ አለው። አፄ ምኒልክ አርሲን ሲወሩ በአከባቢው የአባቦኮነት ሥልጣን የነበራቸው ሽማግሌ ኮረብታው ላይ ወጥተው “እጄን ለምኒልክ አልሰጥም”ብለው ማመጻቸው ይነገራል። መከበባቸውና ማምለጫ እንደሌላቸው የሚገልጽ መልእክት ተላከባቸው። አባቦኮ ታዲያ፣ “አላውቃችሁም እንጂ እናንተም በኦሮሞ ሕዝብ ተከባቸዋል።”የሚል ምላሽ ላኩ። መውጫና ማምለጫ የሌላችሁ እናንተ ናችሁ። እኔማ በአባቴ ምድር ላይ ነኝ። በዙሪያዬ ኦሮሞች አሉ። እናንተ ስግብግብ ነፍጠኞች! እስኪ ዘውር ብላችሁ ከጀርባችሁ ያለውን አንድ የኦሮሞ ገበሬ ተመልከቱ። አይኖቹ ደም ለብሰው፣ ፊቱ እንደነብር ተቆጥቶ ድርጊታችሁን ሁሉ ይመለከታል። እናንተ አዙራችሁ ማየት አልቻላችሁም። ልጅ ከአባቱ በላይ ይቆጣል። ያን ጊዜ ልጆቻችሁ ወዮላቸው የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይነገራል። አባቦኮን የከበቡት የምኒልክ ጦር አዛዥ ፊታውራሪ ሀብተሥላሴ እምሩ የአባቦኮ ምላሽ ሲደርሳቸው፣ “አንበሶቼ!፣ በአስቸኳይ የጋላውን ራስ ቆርጣችሁ አምጡልኝ በማለት አዘዙ።” ከሁለት ሰዓት ውጊያ በኋላ የአባቦኮ ራስ በጦር ላይ ተሰክቶ ቀረበላቸው። ሽበት የወረራቸው ሽማግሌ ራስ ቁጣ የተቸከቸከበት ግንባር፣ የፈጠጡ ዓይኖች፣ አባቦኮ የሞቶ አይመስሉም ነበር።
እስኪ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ ይህን መርዝ አንድባንድ እዩት፣ አስተውሉት። እንግዲህ ከዚህ አባባል ወዲያ ሕዝብን እርስበርስ ማጨራረስ፣ ማገዳደል፣ ደም እንዲቃባ ማድረግ ሌላ ምን ሊኖር ይችላል? ከዚህስ ውጭ አገርን ማለያየትና ማሰነጣጠቅ ሌላ ምን ሊኖር ይችላል? ከዚህ ውጭ ተልዕኮን መፈጸም ሌላ ምን ሊኖር ይችላል? ከዚህስ ወዲያ የአገር ደመኛ ከየት ሊገኝ ይችላል? አስተውሎት ካለን መልሱ ከአንድ ወዲያ እንደማያልፍ እርግጠኛ ነኝ። ተስፋዬ በቡርቃ ዝምታ ምዕራፍ 1. “ነፍጠኞች ወዮላችሁ! የቡርቃ ዝምታ አብቅቶአል” በሚል የማስጠንቀቂያ ጥይት ይጀምራል። የቡርቃን ዝምታ ሰብረው፣ ከአማሮች (ነፍጠኞች) ነጻ ያወጣሉ ብሎ በመጽሐፉ በአክራሪነት ወይም በብሔርተኝነት ገጸ-ባሕርይ የሳላቸው አኖሌና እጮኛው ናት የተባለችውን ሃወኒ ናቸው። ብዕር እየቀለመች ታስተምራለች፣ ትጽፋለች፣ ታስታውቃለች፣ ታዋጋለች፣ ታስታርቃለች። ብዕር ለክፉም ለደጉም ናት። እናም እውቁ ዘፋኝ መልካሙ ተበጀ “ብዕር፣ ብዕር” በተሰኘው ተወዳጅ ሙዚቃው በተዋበ ቅላጼው የነገረን ብዕር ሁሉም፣ ለሁሉም መሆኗን ነው።
ይህ የወያኔ-ኢህአዴግን የከፋፍለህ ግዛን አላማ ይዞ የተነሳው የተስፋዬ ብዕር ግን፣ ዝንተዓለም አንድ ላይ ተዋልዶና ተከባብሮ አንድ ሆኖ የሚኖረውን የኦሮሞና የአማራ ቤተሰቦችን ለማጨራረስና ለማለያየት የተነደፈ ነው። እኩይ ብዕር ነው። እባብ ብዕር ነው። በተዥጎረጎረ የበቀል ቀለም ብዕሩን ስሎ ተስፋዬ ገና በጧቱ በኢትዮጵያዊነት ላይ በእንዲህ ተነሳ። ሰይጣናዊ ጭንቅላት፣ ጋኔላዊ አስተሳሰብ። ሕዝብን እርስበርስ የማበላላት ብዕር። ፍጹም ኢሰብአዊ የሆነ አደገኛ መርዘኛ። የትልልቆቹን እንተውና ይህንኑ መጽሐፍ ያነበቡ የኦሮሞ ወጣቶች፣ በያለበት ምንም በማያቀው የአማራ ዝርያ አለው በተባለበት ቤተሰብ ላይ እየቋጠሩ የመጡት ቂም-በቀል በየትምህርት ቤቱ ቢዘልቅ ከቶ ምን ያስደንቃል? እናም፣ የወያኔና የተስፋዬን የአዞ እንባን በቅጡ ለመረዳት ሳይችሉ የቸኮሉት የኦሮሞ ልጆች እመረባቸው ውስጥ ገብተዋል። በዚህ ዘመን ሊታሰብ የማይችል ጉዳትም አድርሰዋል። ለአብነት ያህል የበደኖንና የአርባጉጉን ማንሳት ይቻላል። ተስፋዬም ተልዕኮውን ለማሳካት በር በመክፈቱ በየዋሁ የኦሮሞ አባቶችና ልጆች በወቅቱ ሙገሳ ተችሮታል። “ጆሌ ኬኛ” ተብሎለታል። የኛ ልጅ እንደማለት። በመሰሪና በእኩይ ተግባር እንዲህ መወደስ የሚቀበል ሕሊና ከቶ ምን ዓይነት እንደሆነ መረዳቱ የሚቸግር አይሆንም። ቡርቃ ዝምታ በወያኔ የደህንነት ቁንጮ በሆነውና ለንጹህ ኢትዮጵያን ያለአግባብ መውደቅ ሌት ከቀን ይሰራ በነበረው በክንፈ አማካይነት የተሰራ ለመሆኑ መጽሐፉን ያነበበ ሊረዳው ይችላል። ከዚህም አልፎ ተርፎ ተስፋዬ ቀንደኛ የደህንነት አባል ለመሆኑ ራሱ ራሱን ያጋለጠበት ሁኔታንም እናያለን።
ይህ መጽሐፍ በኤርትራዊያን አማካይነት በወቅቱ በየቦታው ይቸበቸብ የነበረ መሆኑን ስንረዳ ደግሞ የተስፋዬ ደብል ጌም ተጨዋች እንደሆነ ማረጋገጥ እንችላለን። ተስፋዬም መቼም የኛን ሆድ ለመብላት መላ ሁሌ ይፈጥራል። ቀዳዳ ሁሌ ያገኛል። እናም ይገባብናል። እስኪ በገጽ 294-295 ላይ ያለውን ለአብነት እንይው። የቡርቃ ዝምታ ታትሞ እንደተሰራጨ ጠላቶችንም ወዳጆችም በብዛት አፈራሁ። የመጀመሪያውን አስተያየት የሰጡኝ ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ነበሩ። ማኪያቶ ጋብዘውኝ እንዲህ አሉኝ፣
“አሪፍ መጽሐፍ ጽፈሃል። አሪፍ መጽሐፍ ጽፌአለሁ ብለህ ካበጥክ ግን አለቀልህ። ገና አልጻፍኩም ብለህ አስብና ከዜሮ ጀምር። ሰዎች ሲያደንቁህ አትኩራራ። ሲያጥላሉህ ደግሞ አትደንግጥ። የሚረግሙህም የሚያደንቁህም ሰዎች በብዛት ይፈጠራሉ። መልስ እንዳትስጥ። ይህን እርሳውና ሌላ መጽሐፍ ጀምር። ይህች ደግሞ የፀጋዬ ገብረመድህን ዘዴ ናት . . .” አይ ስብሃት! “አሪፍ መጽሐፍ ነው” አለ። እኔ ለነገሩ መንግሥቱ ኃይለማርያም በዓሉ ግርማን አላስገደለውም፣ ሊያስገድለውም አይችልም የሚወደው ጓደኛው ስለሆነ ያለ ጊዜ ነው የስብሃት አስተያየት የበቃኝ። እናም ምናልባትም ስብሃቱ መጽሐፉን አላነበበውም ወይም የመጽሕፉን ይዘት እና ውስጠ-ሴራውን በትክክል አልተረዳም፣ አለዚያም እንዳንዶቹ በኢትዮጵያ መፈራረስ ሴራ ውስጥ ዘው ብሎ ገብቶአል ማለት ነው። ብቻ ክፉ ቀን ጥሩ ነው። ወዳጅና ጠላትን ያስለያልና።
በዚያ ሰሞን ጦቢያ ጋዜጣ እንዲህ ሲል ጻፈ፣
“የቡርቃ ዝምታ ሻቢያና ወያኔ በግለሰቦች ስም የጻፉት መጽሐፍ ነው። አላማውም አማራውንና ኦሮሞውን በማናከስ ይህቺን ሀገር ማፈራረስ ነው። ደራሲው ከነመጽሐፉ ተቃጥሎ ከምድራችን የሚወገድበት ዕለት ሩቅ አይሆንም።” በሚል የሌሎችንም ጨምሮ በአጭሩ ጫር፣ ጫር አድርጎታል። እንዲሁም አንድ አንባቢ አጭር ማስታወሻ ጋር መጽሐፉን በፖስታ ልኮልኛል። ማስታወሻዋም “ይህን ችሎታህን ለቅዱስ ተግባር ብትጠቀምበት ምናለበት? እግዚአብሔር የእጅህን ይስጥህ። ጦቢያ መጽሔት ለመጻፍህ በመርዝ የተቦካ ቂጣ ሲል ስም መስጠቱ እውነት አለው። ለማንኛውም የመርዙ ቂጣ ቤቴ እንዲቀመጥ ስላልፈለግሁ መልሼ ልኬልሃለሁ። የምትል ናት። አስቀድሞ የነቁ ውድ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞቻችን ተስፋዬን በእንዲህና በመሳሰሉት አብጠልጥለውታል። ግና ጌቷን የተማመነች በግ ላቷን . . . ታሳድራለች እንዲሉ ሆነና ይኸው የሕዝብ ቁጣ ለተስፋዬ ምንም አልመስል ብሎት ነበር።
ገጽ 296 ላይ፣
“በፈረንሣይ የስለላ ድርጅት የሚዘጋጀው Indian Ocean Newsletter በቁጥር 949 እትሙ እንዲህ ሲል ጻፈ፣ “Yeburka Zimta (The silence of Burka), a fictional account a bit too close to reality since it led to accusations of his having wanted to stir up passions between the Oromo and the Amhara communities.” ወረድ ብሎ ደግሞ አበበ ባልቻ ጋር በስልክ፣ በጣም ወድጄዋለሁ። በተለይ ሃወኒ ዋቆ እስር ቤት ያገኘቻቸው ወጣቶች . .  በጣም ሳቅሁ . . . መዓዛ (ባለቤቱ) ግን በትክክል አልቀረጽከውም ብላ አስባለች። ደውልላት። ብዙ አስተያየት አላት።” የሚልም ተስፋዬ አስፍሮአል። አበበ ባልቻ ከሕግ ትምህርት ቤት የተመረቀ የሕግ ሰው ነው። ምነው ሕግን የተማረበት ጭንቅላት ድንጋይ በሆነ፣ ሲማር የጻፈበትና ሲመረቅ የማለበት እጁ በተቆረጠ ታዲያ አሰኘኝ። ከርሱ ይልቅ ወደ ሕግ ትምህርት ቤት ደጃፍ ያልደረሰችው ባለቤቱ እውነተኛ ዳኝነት በመጽሐፉ ላይ የምትሰጥ ይመስላል። ከተማረ የተመራመረ ብለው የለ አበው። የተመቸው አንዳንዱ እንኳንስ እናቱን ይረሳ የለ እንደነ አበበ ባልቻ የመሳሰሉ። ስንቱ ተወርቶ ይዘለቃል? ጊዜ ሁሉንም መፍረዱ፤ ማሳየቱ መቼ ይቀራል? ብቻ እንቀጥል።
2. በጋዜጠኛው ማስታወሻ
ተስፋዬ በቡርቃ ዝምታ የኦሮሞንና የአማራውን ቤተሰብ እና ሌሎችን አናክሶአል፣ አገዳድሎአል። በተለይ በኦሮሚያ ከጥንት ጀምሮ ተዋልዶና ተደባልቆ የኖረውን የአማራ ዝርያ መግቢያ እስከሚያጣ ድረስ አስኮንኖታል፣ ከምድረ ኦሮሚያ እንዲጠፋ ለማድረግ ሞክሮአል። በወቅቱ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሁሉ ከጥቂት የመሳፍንት ስሜት ውስጥ ከገቡት በስተቀር፣ ዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ኢትዮጵያዊያን በተስፋዬ ላይ ጥርሳቸውን ነክሰውበታል። ቀና ብለውም ወደ እግዚአብሔርም ሃዘናቸውን ገልጸዋል። ስለውድቀቱም ተማጽነዋል። ታዲያም ተስፋዬ በቡርቃ ዝምታ የደረሰበትን ያንን  ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የማጨራረስ ወራዳ ሥራውን በተለይም ኮብሊያለሁ ብሎ በወጣበት ውጭ አገር ባለው የኢትዮጵያን ዘንድ ጎልቶ እንዳይወጣ ለማድረግ መሰሪ ዕቅዱን ይዞ ወጣ በመጽሐፈ-የጋዜጣ ማስታወሻ። ይህንኑ እውነታ የሚያሳዩ ክሮችን አለፍ፣ አለፍ ብዬ እንደ ቡርቃው ዝምታ ዓይነት መዘዝ፣ መዘዝ አድርጌ ለእይታ አቀርባለሁ።
እኔ በተፈጥሮዬ ሰው አይለውጥም ብዬ አልነሳም፣ አልከራከርምም። እንዲህ ከምል የመጨረሻውን ማየት እመርጣለሁ፡፡ ይደረስበታልና። ይህን የጋዜጠኛው ማስታወሻ የተባለውን የተስፋዬን መጽሐፍ ለመግዛት ምናልባትም ከመጀመሪያዎቹ ረድፍ ከተሰለፉት መካከል ሳልሆን አልቀረሁም። እንዲህ እንድፈጥን የዌብሳት፣ እና የፓልቶክ ሚዲያዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። መጽሐፉን እንደገዛሁ ጊዜም ሳልፈጅ ወዲያውኑ እያጋላበጥሁ ማንበብ ጀመርሁ። አዲስና ምስጢር የሆነ ነገር አገኝ ይሆን እያልክሁ በጉጉት ጎዳና ላይ ሩጫዬን አሳመርሁ። ጨርስሁ። ግና እንደጉጉቴ ሳይሆን ቀረና አሳብ ውስጥ አስገባኝ። ይህ ሰው ዳግም ያንን ሕዝብ ለማበጣበጥ፣ ለመግደል፣ አገራቷን ለማጥፋት አሁንም ብዕሩን ከመምዘዝ አልተቆጠበም? ኧረ ምኑ ሰይጣኑ ነው? እያልሁ አሰላስል ገባሁ። ይሁንና ተስፋዬ ልባቸውን በሰረቃቸው ሰዎች አማካይነት የሚተኩሰው ቀስት እያከሸፈ ተስፋዬን በይፋ እንዲጋለጥ አላስቻለም። እዚህም ላይ በማይካደው ውብ የአጻጻፉና በማር በተለወሰ መርዛም አጣጣል የተመሰጡ ኢትዮጵያዊያንም በጽሑፉ ውስጥ የተመለከቱትን እንደአዲስና ምስጢር አድርገው አምነው ክብር ስለሰጡትም እንደፈለገ እንዲዝናና ዕድል ሰጥተውታል። ይህንኑ ወደ ፊት ከመጽሐፉ አለፍ፣ አለፍ አድርጌ ስጠቃቅስ ግልጽ ሊሆነን ይችላል።
የተንኮል መረብ፣
ከመጽሐፉ መግቢያ ገጽ 5 ላይ ተስፋዬ፣ “የቢሾፍቱ ልጅ የሆነ አንድ ዜጋ ይህቺን መጽሐፍ ሊጽፋት ሲጀምር ለራሱ ታማኝ ለመሆን ከሕሊናው ጋር ብርቱ ትግል አድርጎአል።” ይልና ደግሞም አለፍ ብሎ ገጽ 6 ላይ፣  “ያለኝን ሁሉ የመዘርገፍ ዓይነት የአጻጻፍ ስልት ተጠቅሜአለሁ። ይህ ለታሪክ ጸሐፊዎች መነሻና ምንጭ ሆኖ ያገለግል ዘንድ ምኞቴ ነው።” በሚል ልብ በሚያንጠልጥል አጓጊ አነጋገር የተንኮል መረቡን መዘርጋቱን ዳግም ይጀምራል።
አዲስ ነገር ያወጣልን ለማስመሰል፣ በርግጥ የተደበቀ ምስጢር ያጋለጠ ለማስመሰል የመሞከር አነሳስ። እናም፣ ታሪክ ጸሐፊዎች የወያኔን የተንኮል መረብ ከዚህ ከጽሁፉ አግኝተው ሊጽፉ። ጉድ ነዋ!። ተስፋዬ እንዲህ ይቀባጥር እንጂ ገና በጧቱ እነዚያ መስዋዕትነት ሲከፍሉ የነበሩት የግል ጋዜጠኞች ነቅተውበታል። በተለያየ ጊዜም፣ በተለይም ከቡርቃ ዝምታ በኋላ ብለውበታል። ከዚህ ከተስፋዬ መጽሐፍ አዲስ ነገር የታሪክ ሰዎች አግኝተው ታሪክ የሚጽፉበት አንዳች ነገር ይኖር አይኖር እናየዋለን።
ሠራዊቶቻችንን ለጭዳ አሳልፎ ስለመስጠት፣
ኢትዮጵያዊ ተብሎ በሠራዊቱ ውስጥ በጦር ጋዜጠኛነት ሰልጥኖ ወደ ግንባር በተሰማራ በጥቂት ቀናት ነው ለወያኔ እጁን ተስፋዬ የሰጠው። በዚህ በኩል በመጽሐፉ ገጽ ’46-48’ ላይ ተስፋዬ ከኮፍጣናው አምዴ ጋር የቀባጠራቸውን እንመልከት። ተስፋዬ የጦር ሜዳ ጓደኛው ሆነውን አምዴን፡-  “እጃችንን ለምን ለወያኔ አንሰጥም”? ብሎ ይጠይቀዋል። አምዴም አብደሃል!? . . . የፕሮፓጋንዳ ሰራተኞች ስለሆንን ምላሳችንን ነው የሚቆርጡት በማለት ይመልስለታል። ተስፋዬ መቼ አብዶ? የሚያደርጋት ሁሉ ተለክታና ተቀምራ ስለሆነ ጊዜም ሳይፈጅ ለአምዴ፣ “አይነኩንም ግድየለህም! ይህ መንግሥት ፈራሽ ነው። በዚህ ሁኔታ መሞት ደግሞ ቂልነት ነው።” በማለት ይመልስለታል። በአሳቡና በአመላለሱ የተገረመው፣ እና ግራ የተጋባው አምዴ፣ ዘመዶችህ ስለሆኑ ነው የተማመንክባቸው? ሲል ይጠይቀዋል። አዎን የአምዴ ጥያቄ የጥርጣሬ ብቻ ሳይሆን፣ ትክክለኛ ጥያቄ ነበር። ያነሳሳውም ራሱ ተስፋዬ የአምዴን ሥጋት ለማስወግድ ይመስላል “ግድየለህም! አይነኩንም” በሚል አነጋገር አፉን ለማስዘጋት፣ ሕሊናውን ለማሸጥ የሞከረው።
እንግዲህ በዚህ አነጋገሩ ተስፋዬ ምንኛ እርግጠኛ፣ ምንኛ የወያኔን ውስጥ እንደሚያውቅ አመላክቶልናል፤ አረጋግጦልናል። ይህ ማለትም ተስፋዬ ቀደም ብሎም ከወያኔም ሆነ ከሻቢያ ጋር ግንኙነት እንደነበረው ነው። በግንኙነቱ ተስፋዬ ከዚያው ከየዋሁ ሕዝባችንና ሠራዊታችን የሚያገኛቸውን ምስጢራዊ መረጃዎችን ያቀብል እንደነበረም መረዳቱ የሚከብድ አይሆንም። ተስፋዬ እዚህ የሳይበሩን ማህበረሰባችንን ልብ ሰንጥቆ ለመግባት የተጠቀመባትን አነጋገር በአምዴ ላይ ለመጠቀም ሞክሮአል።  “አምዴ እመነኝ! እኔ የቢሾቱ ልጅ ነኝ። እንደዚያ አስቤ አላውቅም። ሆኖም ለማንመሰገንበት ነገር መሞት ኪሣራ ነው” በሚል። ግና የተስፋዬ አካሄድና ሁኔታውን በቅጡ ያስተዋለው ቆፍጣናው አምዴ፣ በአጭሩ እንዲህ ሲል መለሰለት። “አንተ እጅህን ስጥ! እኔ ግን አላደርገውም።” በሚል። እኔ ለአገሬ አጥር ልሆን እንጅ፣ ምስጋና ልፈልግ አይደለም። የምዋጋው ለአገሬ አንድነት፣ ለሕዝቧ ልዕልነት ለገባሁ ቃል እንጅ ውዳሴ ፈልጌ አይደለም። እኔ የተጣለብኝን አደራ ለመወጣት እንጅ የተሰለፍሁት እጄን እንደ አልባሌ ለመስጠት አይደለም በማለት አምዴ በክብር ከተስፋዬ መረብ አምልጦአል።
“የቢሾፍቱ ልጅ ነኝ” የሚለው የተስፋዬ እኩይ አነጋገር የአምዴን ሆድ አልበላውም፤ እንዲያውም ፍጹም አደፋፈረው እንጂ። “የሆነው ሆኖ እኔ እርምጃዬን ስቀንስ አምዴ ፍጥነት ጨመረ። እንዲያም ሆኖ ከወያኔ ጋር በሰላም የመቀላቀል ዕድል አልገጥመኝም” ይለናል ተስፋዬ ገጽ 47 ላይ። እንዲሁም ቀጠል አድርጎ፣ “የዓለምሳጋን ሁለተኛውን ሰንሰለታማ ተራራ ሽቅቡን ወጥተን ቁልቁለቱን ስንደረደር የወያኔ የደፈጣ ቡድን በተኮሰብን የመትረየስ ጥይት ውርጅብኝ በተራራው ተዳፋት ላይ ተረፈረፍን። ከአሥር ያላነሱ ወታደሮች አናታቸው እየተበረቀሰ፣ ልባቸው እየተነደለ ሲያሸልቡ፣ እኔ ግራ እጄ ተቀልቤ እንደ ሙቀጫ ከላይ ተንከባልዬ ከአንድ የግራር ግንድ ጋር ተጋጨሁ” ይለናል ተስፋዬ። መቼም ሆድ ያባውን ብቅል ያወጠዋል እንዲሉ ነውና ተስፋዬ ከላይ ለአምዴ ሽፋፍኖ ለማለፍ የሞከረውን እዚህ ወረድ ብሎ ግልጽ አድርጎታል። ተስፋዬ እነዚያን አብረውት ለዕለታዊ የውትድርና ተግባር የወጡትን ኢትዮጵያዊያንን ወስዶ ጭዳ አስድርጓቸዋል ለማለት ይቻላል። የተስፋዬን ሁኔታ የተረዳው አምዴ ግን ወደፊት ፈጠን፣ ፈጠን ብሎ በመሄዱና በማለፉ ከተስፋዬ መረብ አምልጦአል። ኪዚያ በኋላ ከአምዴ ጋር አዲስ አበባ ነው የተገናኘነው ብሎናልና ተስፋዬ። ያላወቁ አለቁ ሆኖ ነገሩ፣ ያላወቁት ሌሎቹ ተስፋዬ በገለጸው መልክ በእጀ መንሻነት ወስዷቸው ተማገዱ። ተስፋዬ እጄን ተቀልቤ፣ እንደሙቀጫ ቁልቁለቱን ተንከባልዬ ወርጄ ከግራር ግንድ ጋር ተጋጭቸ ተረፍሁ በሚል በተለመደው ቅጥፈቱ ውብ የአጻጻፍ ልዩ ተሰጥዖ ታክሎበት ሊያሳምነን ሞክሮአል። ይሁንና እውነት ለጊዜው ትደበቅ ካልሆነች በስተቀር፣ ትዘገይ ካልሆነች በስተቀር፣ ተውጣ አትቀርም፤ አትሞትም። ልብ ብለን ቀጥለን እናስተውል።
ምርኮኛነት 
ተስፋዬ በጽሑፉ ላይ እናዳሳየው፣ በጁ ላይ ተመትቶ ከፍ ካለ ጋራ ላይ ቁልቁል ተንከባልሎ ወርዶ ያውም ከግራር ግንድ ጋር ተጋጭቶ ነው የተረፈው። ተአምረኛ ሆነ ማለት ነው። ግና ተስፋዬ አለፍ ብሎ ገጽ 49 ላይ፣ “በጣር ላይ እንደነበሩ እንደ ሌሎቹ እኔንም በአንድ ጥይት ያሰናብቱኛል ብዬ ተስፋ በመቁረጥ እመለከተው ጀመር። እኔ አጠገብ ሲደርሱ ቀና አልሁ በሕይወት መኖሬን ለማሳየት አለን። እናም አጠገቡ የደረሰው ታጋይ፣ “ተጎድተሃል? ሲል በትግሪኛ ጠየቀኝ።  ደህና ነኝ ስል በአማርኛ መለስኩ።  ተነስ እሞ ምጣ! አለኝ በተኮላተፈ አማርኛ።” ተነስቼ አጠገቡ እንደደረስኩ ከሐረር ከተማ በ15 ብር የገዘኋትን ዲስኮ ሰዓቴን ፈታሁና እንዲቀበለኝ ብዘረጋለትም አልተቀበለኝም ይላል። በአንድ በኩል እጄን ተመትቼ ከአቀበት ወደታች ተወርውሬ ከግንድ ጋር ተጋጭቻለሁ ያለው ተስፋዬ፣ ምንም ሳይዘገይ ደግሞ ስለጉዳቱ ሲጠየቅ ደህናነኝ ብሎ መመለሱን እናያለን።
በተጨማሪም ወደ ገጽ 50 ላይ ስናልፍ፣
“. . . እንደተማረክሁ ታጋዮቹን ወደ አዛዣቸው እንዲወስዱኝ በተሰባበረ ትግርኛ ጠየክሁኝ። ወስደው ጆቤ በትግል ሜዳ ስሙ፣ በጊዜው ስሙ ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት ዘንድ ወሰዱኝ። ከተዋወቅን በኋላ የደርግን ሥርዓት ለመጣል በሚደረገው ትግል መሳተፍ እፈልጋለሁ አልኩት።” ይለናል ተስፋዬ። እንግዲህ ከላይ ለፈታሾቹ ደህናነኝ፣ ምንም አልሆንኩም ያለውና ምንም ዓይነት ዕረፍትና ሕክምና ሳይሻ ደርግን ለመፋለም ወደ ግንባር መሄድ አለብኝ ብሎ ፎክሮ መነሳቱ ካልታወርን በስተቀር፣ የተስፋዬን ድርጊትና ማንነት ቁልጭ አድርጎ እንደመስተዋት ያሳየናል። ምንም ዓይነት ጉዳት በወቅቱ ያልደረሰበት መሆኑን። አይ እኔን ምርኮኛ ያድርገኝ የሚያሰኝ ነው በአግቦ አነጋገር። መቼም እንዳናየው፣ እንዳንመራመረው በቢሾፍቱ ቆሪጥ አስዙሮብን የለ?
በበረከት ሽፋን፣
ደሞም ተስፋዬ የርሱ ኤርትራዊነት እንዳይጋለጥ፣ ሽፋን ፍለጋ ሲሮጥ መንገድ ላይ ያገኘው በረከት ስምዖንን ነው።
በመጀመሪያም ይህንኑ አባባል ለማስደገፍ ገጽ “79” ላይ፣ “የሆነው ሆኖ ከበረከት ጋር አለመግባባታችን እየከረረ የሄደው የቡርቃ ዝምታ በሚል ርዕስ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄዎች ላይ መሠረት አድርጌ የጻፍኩት ታሪክ ቀመስ ልበ-ወለድ መጽሐፍ ከታተመ በኋላ በረከት አነበበው። ኢህዲን የተባለው ድርጅት የሕወሃት የአማራ ክንፍ መሆኑ ከመገለጹ በስተቀር የተተረከለት ገድል ያለመኖሩን በማንሳት በረከት ወቀሰኝ።” ይልና ለጉዳይ እቢሮው በሄድሁ ወቅት እንዲህ ሲል ነበር ቅሬታውን የገለጸልኝ፣ “ሻቢያ አራት ታንክ ይዞ ስለገባ ያን ሁሉ ገድል ጫንክለት። የኢህዴንን የትግል አስተዋጽዖ ግን ሙሉ በሙሉ ዘለልከው።” ብሎኛል በማለት ያሰፈረውን እናስተውል።
ተስፋዬ በዚህ አባባሉ ግልጽ ያደረገው፣ የበረከትን ኤርትራዊነት፣ ወይም በረከት ለኤርትራ ያለውን ወገናዊነትን ሳይሆን፣ የራሱን ወገናዊነቱን አባት አገር ብሎ ለሚጠራው ለኤርትራ ያሳየበትን ነው። እናም፣ ምንም ያህል ስለኤርትራ ገድል ቢያወራ፣ ቢጭን ምን ያስደንቃል? ምናልባትም በረከት በወቅቱ የተስፋዬ ዓላማና መንገዱ እስከምን ድረስ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር ለማለት ይቻል ይሆናል። ወገን በወገኑ ላይ ቂም እያበቀለ፣ አገራችን በዘር በጎሳ እንድትከፋፈል ተስፋዬ በጋዜጠኝነቱ፣ በደራሲነቱ የሚያደርገው ለበረከት ምንም አልነበረም። ያስጨነቀው እርሱ እየመራው የመጣበት ኢህድን ወይም በኋላ ብአድን የተባለው የወያኔ ውላጅ ሥራን እንደሚፈልገው ዓይነት ተስፋዬ በመጸፉ ላይ ባለማውደሱ ነው። ወደ ገጽ 83-85 ስናልፍ፣ የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት እንደተከሰተ ከበረከት ጋር በከረረ ሁኔታ ለመጋጨት በቅተን ነበር ይላል ተስፋዬ። ግጭቱን በተመለከተ በበረከት ጸሐፊነት ኢህአዴግ ያወጣውን መግለጫ በተሳሳተ መንገድ ጋዜጣችን ላይ አትመን ስናወጣ፣
“የሻቢያ ርምጃዎች ጦርነቱን ያቃርበዋል” የሚለውን አረፍተ ነገር “ጦርነቱ ተቃርቦአል” በሚል ባደረግነው ስህተት እንደገና ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ገብተናል ይለናል። ማንም ሊገነዘበው እንደሚችለው ይህ በስህተት የተፈጸመ ነው ብሎ ማመን ፍጹም አስቸጋሪ ይሆናል። ሆን ተብሎ በመላ የተቀመመ አሳሳች ድርጊት ነው። ኤርትራ በጸብ ጫሪነት እንዳትጠቀስ የተደረገ የተስፋዬ ሴራን ያሳያል ጽሑፉ። በትክክል በረከት ተስፋዬ ላይ የደረሰበትን ሁኔታ ነው አነጋገሩ የሚያስረዳው። ቀጥሎም በረከት፣ “ሀገሪቱ ባስጨናቂ ሁኔታ በተያዘችበት በዚህ ወቅት ስህተቱ ለምን አላማ እንደተፈጸመ ንገረኝ?” ብሎ ሲጠይቀው፣ ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ሆን ብዬ ሻቢያን ለመጥቀም እንዳደረግሁት እየነገርከኝ ነው? ብዬ ስሜታዊ በሆነ መልክ ስጠይቅ፣ በረከት “እሱንማ አንተ ንገረኝ! ሲል ጮኸ” ይላል የተስፋዬ ጽሑፍ። በረከት እንደዚያ ካለ እቅጩን ነግሮታል ለተስፋዬ ማለት ነው። ታዲያም እንዲህ እቅጩ የተነገረው ተስፋዬ፣
የሻቢያ ደጋፊ አድርጋችሁ ከጠረጠራችሁኝ ሥራውን ልልቀቅ? ብሎ ይጠይቃቸዋል በረከትንና አለምሰገድን። እነርሱም ለሹፈት ያህል አይ በሻቢያ ደጋፊነት እንኳን አልጠረጠርንህም። ግና ባለፈው በመለስ ቃለ-መጠይቅ ላይ እንድትገኝ ተነግሮህ ለምን ቀረህ? ብሎ አለምሰገድ መስቀለኛ ጥያቄውን ያሳረፍበታል። አቅጣጫ ማስለውጥ፣ ተስፋዬ የሻቢያ ዋናው ቅጥረኛና ሰላይ መሆኑን እንዳንጠራጠረው የሚያደርገን በማሳሳቻው (ማስክ) ቃላቱ ነው ማለት ይቻላል። ይህንኑ ለማስረገጥ ዘንድ በገጽ “290” ላይ የረጨውን መርዝ እንመልከት። “ጋዜጣኛ ነኝ። ወደ ጩኸተ-ባሕሩ ገባሁ። አንድ ፈረሰኛ ዓይኔን ሳቡት። ፈረሳቸው ተንቆጥቍጧል። እርሳቸውም ፈረሳቸውን መስለዋል። እኒህ ሽማግሌ ያቅራራሉ፣ ጃሎታውን ያስነኩታል። በኃይለ ሥላሴ፣ በደርግ ዘመናት ክፉ በደል ደርሶባቸው ይሆን? ወይስ መሬትና ቤት የተወረሰባቸው? ለማንኛውም የግንቦት ሀያ አንደኛ ዓመት በዓል የፈጠረባቸውን የደስታ ስሜት መሽከም አለመቻላቸው ግልጽ ነበር። ቀረብ ብዬ ለቃለ-መጠየቅ ጋበዝኳቸው ካለበኋላ፣ ባህሩ ከበደ የተባሉትን እኒህን ሰው፣ በዛሬው ዕለት እንዲህ አምረውና ተውበው ፈረስዎንም አንቆጥቁጠው ወደ መስቀል አደባባይ የመጡበትን ምክንያት ቢያብራሩልኝ? በማለት ጠይቋቸው፣ እርሳቸውም በአፄውም በደርግም፣ አሁን በወያኔም የድጋፍ ሰልፍ አለ በተባለ ጊዜ የክት ልብሴን ለብሼ፣ ፈረሴን ጭኜ ብቅ ነው።” በሚል የኢትዮጵያዊያንን አስተሳሰብ አቅጣጫ ለማስለወጥ መለስ እንደሚያደርገው አቅጣጫ ካስለወጠ በኋላ፣ ደርባን የተባለች ከተማ ላይ የተዋወቅሁት አንድ የሻቢያ ጋዜጠኛ ያጫወተኝን ላውጋችሁ ብሎ ይጀምራል ተስፋዬ በለመደው የፈጠራ አሰያየሙ። ሕዝቡ ከየቦታው ግልብጥ ብሎ ወጥቶአል። . . . ሕዝቡ ከበሮውን እየደለቀ . . .ፈንዲሻውን እየበተነ . . . ወደ ጎዳና ሃርነት።” ጋዜጠኛው አንዲት ሴት ወይዘሮ ካይኑ ገቡለት የተባሉ ከበሮ ይዘዋል። ዘፈን አውራጅ ናቸው። ሽሩባቸው ከማማሩ የተነሳ አንበሳ መስለዋል። ነጭበነጭ ለብሰው በደስታ አብደዋል። ጋዜጠኛው እኒህን ወይዘሮ ያነጋግራል። እናቴ አንድ ጊዜ ያዳምጡኝ። አንድ ጊዜ! ወይዘሮዋ ከበሮ መደለቃቸውን ገቱ። “እንኳን ለኤርትራ የነጻነት በዓል አደረስዎት!። እንኳን አብሮ አደረሰን! ደስ ብሎኛል። ኤርትሪያ ሃገራችን ከኢትዮጵያ አገዛዝ ነፃ በመውጣቷ ደስ ብሎኛል። የዛሬዋ ዕለት የልደት በዓላችን ናት” አሉት ብሎ ለማስተላለፍ ወደ ፈለገው ወደ ኤርትራ ነፃነት ማግኘትና የጀግንነት ገድል ትረካ እንደተሸጋገረ ከመጽሐፉ ማየት ይቻላል።
ገጽ “86” ላይ ተስፋዬ በቋንቋ የመናገር አስፈላጊነት በምሳሌ ለማስረዳት ከሞከረ በኋላ፣ የበረከትን ኤርትራዊነትን ለማሳመን ሲል በእንዲህ ይነግረናል። “በረከት ስምዖን የአማራው ድርጅት መሪ ነኝ ብሎ ሲያበቃ VOA ላይ በትግሪኛና በእንግሊዝኛ ካልሆነ በአማርኛ አልናገርም ማለቱ ብዙ ያስገርመኛል። ከዚህ አቋሙ ጥላቻ ማፈሱ ግልጽ ነው።” በማለት።
እንግዲህ ተስፍሽ ራሱን ፍጹም ኢትዮጵያዊያነትን፣ በረከትን ኤርትራዊነትን አጉልቶ፣ በርሱ ላይ የተያዘውን ጥርጣሬ በእንዲህ አክሮባት ለማለፍ ከሚያደርገው ሙከራ አንደኛው ገጽታ መሆኑን የምንረዳ ይመስለኛል። ከእውነት ለመሸሽ ጮቤ መርገጥ መጣ ማለት ነው። ተስፋዬ በሽፋን ሊጠቀም በእንዲህ ሲሞክር ሳያውቅ ግልጽ ያደረገልን ነገር ቢኖር፣ በረከት በትውልደ-ቤቱ ኤርትራዊ መሆኑን፣ በተግባር ግን እንደርሱ የኤርትራ ሰላይ ያለመሆኑን ነው። በሌላ በኩልም፣ በረከት በወቅቱ እንደዚያ ዓይነት ርምጃ ላይ የደረሰው፣ በቪኦኤ በአማርኛው ክፍል የሚሰሩ ውድ ኢትዮጵያዊያን በቃለመጠይቅ አላላውስ ስለአሉት ያመለጣቸው መስሎት እንጂ፣ በአማርኛ መናገሩን ጠልቶት አይመስለኝም።
ኦሮሞንና ነፍጠኛ የሚባለውን ክፍል ማናደፉን ስለመቀጠሉ፣ ቀደም ሲል ልጅ እያለሁ ጃንሆይ ቆሪጥ ከቢሾፍቱ እየሳቡ መች ይጨበጣሉ ሲባል እሰማ ነበር። መንግሥቱም ፈለጋቸውን ተከትሎአል ይባል ነበር። ታዲያም ሲመስለኝ ጃንሆይም እንደሰው ፍላጎት ከመንበራቸው አልነቃነቅ ብለው በመቆየታቸው በውርደት መንበራቸውን ተነጠቁ፤ መግሥቱም እንደዚሁ። እኔ ደግሞ ባላምንበትም፣ ተስፋዬ ገብረአብ ልባችንና አንጀታችንን እየከፈተ የሚገባው “እኔ የቢሾፍቱ ልጅ ነኝ” እያለ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያደረሰውና እያደረሰ ያለው ግፍና የማፈራረስ ትልሙ በግልጽ እንዲህ በዚህ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይ ራሱ ቁልጭ አድርጎ እያሳየ እያለ፣ እንዳናይ ዓይናችንን፣ እናዳናስተውል አእምሮአችንን ያስዘጋው የቢሾፍቱ ቆሪጥን እየሳበ ይሆን? ብዬ መጠይቅ ጀመርሁ። አባባሌን በገጽ 89-90 ላይ፣  “በሻይ ሰዓት አብረውኝ የነበሩት ኦሮሞች ጥልቅ የሆነ ስሜታቸውን ገልጸውልኛል በማለት የሚከተለውን ጽፎአል። ለመገንጠል የምንመኘው የዚህች አገር መሪዎች ጭንቅላት ተቀይሮ፣ የሕዝቦችን መብት የሚያከብሩበት ጊዜ እንደማይመጣ ተስፋ በመቁረጥ ነው እንጂ አንድ መሆን ታላቅነት መሆኑ ጠፍቶን አይደለም።”
“በጉልበት ከተፈጠረ አንድነት ውስጥ በባርነት ከመኖር፣ ተበታትኖ በነጻነት መኖር ይሻላል ብለን ነው። ብሔራዊ ጭቆና ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ እናንተ አይገባችሁም። አታውቁትም! አልቀመሳችሁም! የራስን ባህል ማጣት፣ በራስ ቋንቋ መጠቀምን መከልከል፣ ራስን የመሆን መብት ማጣት፣ በባዕዳን ገዢዎች መተዳደር፣ ከሁሉም በላይ ሀገርህ ተነጥቀህ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ዝቅ መደረግ እንዴት ፈታኝ እንደሆነ እናንተ አይገባችሁም።” ሲሉኝ አባባላቸውና ከገጽታቸው ላይ ያነበብሁት ስሜት ዛሬም ድረስ ትናንት ያየሁት ያህል ይሰማኛል።” ብሎ ተስፋዬ የቡርቃ ዝምታ መጽሐፉ ትክክለኛ የኦሮሞችን መልእክት የያዘ መሆኑን ለማስረገጥ ከመሞከሩም በላይ በተለይ ገጽ90 ላይ፣ “ኦነግን የጭራቆች ስብስብ አድርጎ የማየቱን የወቅቱን ዝንባሌ እንደማልጋራው ለራሴ ማረጋገጥ የቻልኩ ሲሆን፣ ኦሮሞች የገዛ ሃብታቸው ጠላት እንደሆነባቸውም ማስተዋል ችዬ ነበር።” በማለት በነደፈው አሳብ ላስደግፍ።
መቼም ያዶቀነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይቀርም እንዲሉ፣ ተስፋዬ በሕዝባችን ውስጥ ያንን መርዛም ቅመራውን እውጭ ከወጣም በኋላ አላቆመም። ይልቁንም በረቀቀ መንገድ ገባብን እንጅ። አንጋች ቅቤ አንጓች እንዲሉ፣ ከኦሮሞች በላይ ለኦሮሞ ማህበረሰባችን ያዘነ ተስፋዬ በመምሰል በቡርቃ ዝምታ የጀመረውን ማላዘን በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይም ቀጥሎበታል። በተለይም “ኦሮሞች የገዛ ሀብታቸው ጠላት እንደሆነባቸውም ማስተዋል ችዬ ነበር” የሚለው አነጋገር፣ እንዴት ተስፋዬ ለኦሮሞ ማህበረሰባችን በሌሎች ማህበረሰቦች ወይም በፈረደበት ነፍጠኛ ወይም አማራ በተባለው ዘር ላይ እንዲነሳሱ የማድረግ ትልሙ እንዳላበቃ አመላካች ነው። ይህም የሚያሳየን፣ ኢትዮጵያ ተበጣጥሳ ከምድረገጽ እስካልጠፋች ድረስ ተስፋዬ እረፍት የሌለው መሆኑን ነው። የተሰለፈበት አላማ ነውና አይፈረድበትም። ምንም ያህል ጉድጓድ ተስፋዬ ከጌቶቹ ጋር ቢቆፍርና ቢቆፋፍር በኢትዮጵያ ያሉት ሕዝቦቻችን በፍጹም እንዳይለያዩ ተማምለዋል። ከንቱ ልፋት። ግና ስንቶቻችን ነን መጽሐፉን ስናነብ ይህንኑ የተስፋዬን ሥውር ደባ የተገነዘብን? የሚፈረድብም ቢሆን የሚፈረድብን እኛው የርሱን መሰሪ አካሄድ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማንረዳው ላይ ነው።
አንድ ልክ ልቅም አድርጎ አንብቦ ይህችን አከባቢ የተረዳ ጓደኛዬ፣ ይህ ተስፋዬ የሚባል እሾህማ ሰው አማሮች ምን አደርገውት ነው? እንዴት፣ እንዴት አድርጎ ነው እንዲህ አማሮችን ለማጨራረስ የሚጽፈው? ለነገሩስ የኦሮም ሕዝብ እንጅ የኦሮሞ አገር በታሪክ ይታወቃል ወይ? ብሎ አፋጠጠኝ። እኔ ምን አውቅልሃለሁ። እርኩስ ጸሐፊ መሆኑን ልገነዘብ ችያለሁ። እኔም የማውቀው የኦሮሞ ሕዝብን እንጅ ኦሮሞ፣ ወይም ኦሮሚያ ተብሎ አገር መኖሩን የሚያሳይ ታሪክ አላየሁም ብዬ መመለሴ አሁን ትዝ ይለኛል።
ብለላ
ገጽ 225 ላይ፣ “ከኮበለልኩ በኋላ ጦቢያ ጋዜጣ በግንቦት 2፣ 1993 ዓ.ም እትሙ፣ የሻቢያ ሰላይ ሆኜ ቆይቼ ሥራዬን አብቅቼ እንደወጣሁ ጽፎአል። አያይዞም በፕሮፓጋንዳው ዙሪያ ያሉ ካድሬዎች የሚሰማን አጣን እንጂ ተናግረን ነበር ብለው መቆጨታቸውን ዘግቦ አንብቤአለሁ። Indian ocean news letter በቁጥር 949 እትሙ እኔን በተመለከተ በአብዘኛው ሃሰት የሆነ ዘገባ አትሞአል በሚል ለኮብለላው ምክንያት የሆነውን ነገር ሸፋፍኖ ለማለፍ ሞክሮአል። ተስፋዬን ሃቀኛ ኢትዮጵያዊ፣ ሃቀኛ የኢትዮጵያ ተቆርቋሪ አድርገን እንድናመልክበት አንዴ ስላደረገን፣ እና በርሱ ላይ የሰላ ሂስ የሚያቀርበውን ወይም የሚያጋልጠውን ሁሉ እስከማስኰነን ስለደረሰ፣ እነዚህን ውሽታሞችን አትስሟቸው እያለን ነው በዚህ አካሄዱ። ተስፋዬ ከላይ የተባለውን ከመጻፉ በፊት፣ ኢትዮጵያን ለቅቄ ከመውጣቴ በፊት በረከት ስምዖን ቢሮው አስጠርቶኝ፣ “በገዛ ገንዘባችን በሚታተም መጽሔት እየተሰደብን ልንቀጥል አንችልም። ጎንደር ሄደህ በሰራኸው ሥራ ብዙ ጓዶችን አቁስለሃል። ስለዚህ የምትመራው ድርጅት የሚዘጋም ከሆነ ወይም ሌላ የሚደረግ ካለ በቅርቡ ውሳኔያችንን እንነግረሃለን!” ስለኝ ካለ በኋላ ቀጥሎ፣ የደህንነት ክፍሉ ክንፈ ደግሞ በሶስተኛው ቀን ጠርቶኝ፣ “ለሻቢያ መረጃዎችን የማቀበል ሥራ እንደምሰራ ከተለያዩ ምንጮች ጥቆማዎች እንደደረሳቸው ነገረኝ።” ይለናል። እንግዲህ በእንዲህ አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ተስፋዬ እግሬ አውጭኝ ያለው ከዚህ በኋላ መሆኑን መረዳት የሚቸግረን አይመስለኝም።
በደህንነት ጊዜ፣
ኑዛዜ እንዳይሉት ገረፍ፣ ገረፍ አድርጎት አለፈው። እጅህ ከምን? ሳልባል ዓይነት እሽቅድድሞሽ ሆነ። ያው በለመደው የማጭበርበርና የማደናገሪያ ጉዞውን ለማሳመር ያህል በደህንነት ሥራው ወቅት በኢትዮጵያዊያን ላይ ከፈጸማቸው ጭካኔና ከፋፋይ ተግባራት መካከል ቀጥሎ በተመለከተው ዓይነት ለመጠቃቀስ ሞክሮአል።
ገጣሚ አበራ ለማ፣ ጋዜጠኛ ማዕረጉ በዛብህ፣ ፕሮፌሰር ታዬ ወልደሰማያት፣ እና አሰፋ ማሩን። ከአሰፋ ማሩ በስተቀር ሌሎቹ ከአገር እንዲኮበልሉ በደህንነቱ ስልታዊ ሙከራ እንደተደረገባቸው ሊነግረን ከጀል ብሎታል። አንዳንዶቹ ዕድሉን ሲጠቀሙ ሌሎቹ አልተጠቀሙም አለን ገጽ 226 ላይ።
ቀሪዎችን በአጭሩ እንመልከት።
ሀ. በተለይም የመምህር አሰፋ ማሩ ግድያ በሚመለከት፣
አሰፋ ማሩ በጥይት ተደብድቦ የተገደለው በእንግሊዝ ሰላይነት ተጠርጥሮ እንጂ የደህንነቱ መሥሪያ ቤት የተጨበጠማስረጃ አልነበረውም በሚል እርሱ ተሳታፊ የነበረበትን የደህንነቱን መ/ቤት ራሱን እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ለማድረግ እየከጀለ። ከቶስ ምን ያድርግ፣ በልዩ የአጻጻፍ ዘዴው፣ “የደብረዘይት፣ የቢሾፉቱ ልጅ ነኝ” በሚለው የብልጣብልጥ መፈክሩ እንደለመደው አጃጅሎን የለ!። እናም ከዚህ ከራሱ አነጋገር ተነስተን እንኳ በአንክሮ ስንቃኝ፣ ያለምንም ጥርጥር አሰፋ የተገደለው ይህ ሰላዩ ደራሲ ተስፋዬ ሳይሳተፍበት ያለመሆኑን ነው። ይህንኑ ይበልጥ ለመረዳት ቢያስፈልግ ወደ ገጽ “198” እንመለስ። ተስፋዬ የሚከተለውን ብሎን እናገኛለን።
“ከዕለታት አንድ ቀን አሰፋ ማሩ ተገደለ። ፖሊሶች ግንብ አስደግፈው የጥይት ሩምታ አወረዱበት። የግል ጋዜጦች ድርጊቱን በመኮነን እሪታቸው በዛ። ከመምህራን ማህበር አመራር አባላት አንዱ የነበረው አሰፋ ማሩ ለምን ተገደለ? ፖሊስ የገለጸው እጅህን ስጥ ሲባል አሻፈረኝ በማለቱ ነው። አስቂኙን ምክንያቱን ማንም ያመነ አልነበረም። አሰፋ ማሩ ሳምሶናይቱን አንጠልጥሎ ከቤቱ ወደ  ሥራ በእግሩ ይጓዝ ነበር። መሮጫና መደበቂያ በሌለው ግንብ ጥግ ሥር ከአምስት ያላነሱ የታጠቁ ፖሊሶች ባረንጓዴ የፖሊስ ላንድሮቨር መንገድ ዘግተው እጅህን ስጥ ሲባል አሰፋ ማሩ ከቶ በምን ስሌት ነው እጁን ለመስጠት ፈቃደኛ የማይሆነው?” የሚል።
“ፖሊሶች ግንብ አስደግፈው የጥይት ሩምታ አወረዱበት። አሰፋ ማሩ ሳምሶናይቱን አንጠልጥሎ ከቤቱ ወደ ሥራ በእግሩ ሲጓዝ፣ መሮጫና መደበቂያ በሌለው ግንብ ጥግ ሥር ከአምስት ያላነሱ የታጠቁ ፖሊሶች በአረንጓዴ የፖሊስ ላንድሮበር መንገድ ዘግተው እጅህን ስጥ አሉት” በማለት ስለአሰፋ ማሩ አያያዝና አገዳደል ሁኔታ እየነገረን፣ እኛ ደህንነቶች ሳንደርስበት፣ ማስረጃ ሳይኖረን ተገደለ በሚል ራሱን ከደሙ ንጹህ አድርጎ ሊያሳምነን ይሞክራል። በቦታው ያልነበረ ሰው እንዲህ የአሰፋን አገዳደል ልቅም አድርጎ ሊነግረን አይችልም። ደግሞም ከእገሌ እንደሰማሁት ብሎ እንኳ አልተነሳም። ምናልባትም ገዳይ ባይሆን፣ ተስፋዬ የመምህር አሰፋ አስገዳይ አልነበረም ለማለት ይቻላልን? እንዲያው የኩኩሉ ጨዋታ መሆኑ ነው። ተስፋዬ ሳያውቀው ኧረ ስንቱን እየነገረን እንደሆነ ማወቅ የምንችለው መጽሐፎቹን ባንክሮ አብጠርጥረን ማንበብ ስንችል ነው። ግና የተወሰንን ክፍሎች ያደረግን አልመሰለኝም ወገኖቼ።
ለ. ነገረ ፈጅና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ታደሰ መታረድ፣
የኪራይ ቤቶች ነገረ ፈጅና የመስታዋት ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረው ተስፋዬ ታደሰ እምሽት ላይ እቤቱ በራፍ ደፈጣ ተደርጎበት እንደበግ ጭዳ በካራ አንገቱ ላይ ታርዶ ወደ 89 ዓ. ም አከባቢ እንደተገደለና ደሙም እንደ አሰፋ ማሩ ደመ-ከልብ ሆኖ እንደቀረ ይታወቃል። ተስፋዬ ታደሰ በተጠቃሿ ጋዜጣ ላይ በሚያወጣቸው ግላጭ ተቃውሞ ብዙ ጊዜ እየታፈነ እየተወሰደ ዱካው ሲገኝ በሐቤስኮርፐስ እየቀረበ ሲፈታ ቆይቶ፣ በወያኔ ደህንነቶች ተብሎ በሚነገረው አስቃቂ ግድያ ለአንዴና ለመጨረሻ አንድ ሕጻን ልጁን ትቶ እንዲያሸልብ ተደርጎአል። ተስፋዬ ታደሰ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ነበር። አንድ ጊዜ  ካመነበት ፍንክች የማይል ነው። እንዲህም እንደሚደርስበት ያውቅ እንደነበር አንድ ቀን እቢሮዬ መጥቶ ስንጫወት እንደነገረኝ። ታዲያም ግድየለህም ተስፋዬ! ጠንቀቅ ማለቱ ሳይሻልም አይቀርም አልኩት። ግና ተስፋዬ ተወኝ እባክህን! ምናባታቸው ይሆናሉ? ብሎ እርፍ አለ ኮምጨጭ ባለ አንደበት። ተስፋዬ እንዳለውም እስከ ዕለተ-ሞቱ ያሰበውንና የተሰማውን ከማለትና ከመጻፍ አልተገታም ነበር። ታዲያም ለተስፋዬ ሞት፣ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው የወያኔ ቀንደኛ ካድሬና የደህንነት አባሉ የተስፋዬ ገብረአብ እጅ አይኖርበትም ለማለት ይቻል ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ብቻ ምን ያደርጋል ቤት ይቁጠረው ነው ነገሩ። ማደናገር፣ መዋሸት ሲበዛ ያስተፋል፣ የተለየ ተልዕኮ ያላቸው ሰዎች፣ እንደነ ተስፋዬ ያሉት የማደናገሪያ ቋታቸው ሁሌ እንደሞላ ነው። ወቅት እያዩ፣ ስሜት እየለኩ ወጣ ማድረግ ብቻ ነው። ተቀባይ ባገኙ ቁጥር ያሳምሩታል። እናም የተስፋዬን ማየታችንን እንቀጥል።
ገጽ “311-312” ላይ፣
“ወደ አሜሪካ የመጣሁበት ዋና ምክንያት ለዕረፍት ቢሆንም፣ በእግረመንገድ አንዳንድ ሥራዎች ተሰጥተውኝ ነበር። ከወያኔ ጋር የመቀጠሉ ፍላጎት ግን ስላልነበረኝ ላለመመለስ ሃሳብ ነበረኝ። እንደማይሆን ግን አወቅሁ። አሜሪካ ሃገር መኖር እንደማልችል ተገነዘብሁ።” አለን ጮሌው ተስፋዬ።
ከላይ እንደተገለጸው ደግሞ ተስፋዬ ኔዘርላንድ በስደት ቃለመጠይቁ ላይ፣ አሜሪካ ሲያትል የሄደው ለጋዜጠኝነት ትምህርት ነው ብሎን እንደነበር አመላክቻለውሁ። ውሸት መቼም ጊዜ ሳይሰጥ እንደንፋስ በኖ ይጠፋ የለ? የተስፋዬ ውሸት እየበዛበት ሂዶ እያነቀው ያስተፈዋል። ውሸቱ ላያልቅ ሆኖአል። እናም ይቀጥላል።
ተስፋዬ ሊነግረን ባይከጅልም፣ ከአባባሉ በእንዲህ ልንረዳ እንችላለን። ተስፋዬ በእንዲህ በወጣበት ወቅት፣ እንደ ተስፋዬ የመሳሰሉት የእምዬ ኢትዮጵያ ጠሮች አሜሪካ ውስጥ በቀላሉ ሊኖርቧት አይችሉም ነበር። እናም ለራሱ ለሕይወቱ በመስጋት ወይም ወደ አገር ተመልሶ የጀመረውን እንዲጨርስ ጌቶቹ አዘውት ይሆናል የአሜሪካ ስደቱን ያቆመው እንጂ በአሜሪካ መሰደዱን እንደሚለው ጠልቶት አይመስለኝም።
በዚህም ሆነ በዚያ በዚህ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይ ተስፋዬ ያደረገው እና የተሳካለት ነገር ቢኖር፣ የወያኔን ምስጢር አወጣለሁ በሚል በዋናነት ስዬ ላይ በማተኮር እውጭ ባለው ማህበረሰብ ውስጥ ሰብሮ ሰርጎ በመግባት የውጭውን ማህበረሰብ ልብ ለሁለት መሰንጠቅ መቻሉ ነው። በዚህም፣ ቀሪውን የስለላ ሥራውን ለማከናወን ምቹ መድረክ ለማግኘት መቻሉ ነው።
ጨቋኝ መንግሥታት ሁሌ የሚነቁት ሁሉም ነገር ከተበላሸና ካለቀ በኋላ ወይም የሚፈልጉት ነገር እስከተጠናቀቀ ድረስ ነው። እናም፣ ተስፋዬ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያነት ላይ ብዙ ነገር ሰርቶ ካበቃ በኋላ ከኤርትራ ጋር እስጥ-አገባ ላይ ሲደርስ ነው ወያኔ የነቃበት። ለነገሩ ወያኔዎች እዳር ማድረሱን ያውቁበታል። ካደረሱት በኋላ እንደ ተመጠጠ ጥንቅሽ አውጥተው መወርወሩን ተክነውታል። ተስፋዬ በጋዜጠኝነቱ፣ በካዲሬትነቱ፣ በደህንነቱ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያን ሲገድልና ሲያስገድል አሥር ዓመታት አሳልፎ ተወረወረ፣ ተተፋም ማለት እንችል ይሆናል። እናም፣ የተለመደው ርምጃ ሊወስዱበት ወያኔዎቹ ሲቃጡ፣ እርሱ በሻቢያ በተዘጋጀለት ባቡር ከወጥመዱ አምልጦ ወጣ ማለት ነው።
3. በደራሲው ማስታወሻ፣
ተስፋዬ እንግዲህ የውጭውን ማህበረሰብ ልብ “በጋዜጠኛው ማስታወሻ” ሰብሮ ገብቶ ምንም ለማለት፣ ምንም ለማድረግ እንደሚችል ከተረዳ በኋላ፣ ከየሰው ከቃረመው ተነስቶ በረቀቀ መንገድ ቀሪውን ሥራ እስከሚችለው ድረስ ለማድረስ በዚህ በደራሲው ማስታወሻ ቀጠለ። በደራሲው ማስታወሻ ያነጣጠረው በአገር ቤት በሚንቀሳቀሱት ጠንካራ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ ነው። በተለይም በአንድነትና በመድረክ ላይ። የስዬንና የዶ/ር ነጋሶን ማስክ ተላብሶ። ለምን? ምክንያቱን እንመረምረዋለን።
ዘመቻ 1. በስዬ ሽፋን፣
ወያኔ ኢህአዴግ በትረ-ሥልጣኑን ይዞ የአለሙን ማህበረሰብን ለመሳብም በነጻ አሳብን መግለጽ ከሚል መነሻ ነጻ ጋዜጦች በአገሪቱ እንዲንቀሳቀሱ ፈቅዶአል። አጋጣሚውንም በመጠቀም አንድ ወቅት ነጻ ጋዜጦች እንደአሸን ፈልተው ነበር። በኋላ ግን ወያኔ የጭቃ ጅራፉን ሊያሳርፍባቸው ገባ። ብዘዎች ገፈቱን ቀመሱት። ማጋነን አይሁንብኝና ከማንም በላይ ሳይታክቱ ወያኔ የያዘውን ዘረኛና ከፋፋይ ባሕርይውን በጽናት ተዋግተዋል። በወቅቱ አብዘኛው ኢትዮጵያዊም ሰምቷቸዋል፤ አበጃችሁም ብሏቸዋል፣ ተከትሏቸዋልም። ከቡርቃ ዝምታ ማግሥት ፊት ለፊት የብዕር ጦራቸውን በተስፋዬ ላይ ክፉኛ አሳርፈውበታል። በወቅቱ ወያኔዎች የቡርቃ ዝምታ የያዙትን አላማቸው ይሳካ ዘንድ ዓይነተኛ መሣሪያ በመሆኑ መከራ አበሳ እንዲቀበሉ ከማድረግ ውጭ ጆሮ አልባዎች ሆነው ነበር።
ከፍ ሲል እንዳልኩት ተስፋዬ ስደትም ከወጣ በኋላ በትሩን በኢትዮጵያዊነት ላይ ማሳረፉን ጥበባዊ በሆነ መንገድ ቀጥሎበታል። ተስፋዬ በዚህ በሳይበሩ ማህበረሰብ ውስጥ ሰርጎ ሊገባ የሚችልበትን ዘዴ አመራር ከሚሰጠው ከአባት አገር ሆኖ በሚገባ ቀይሶአል። ሰዎች ምን ይላሉ? እነማን ይወደሱ? ለዚህ ድልድዮች እነማናቸው የሚሉ ክራይቴሪዎችን ነድፎ ነው የተንቀሳቀሰው። ይህንኑ ከጋዜጠኛው ማስታወሻ እንደወጣ ከማስታወቂያው ጀምረን፣ ወደ ኤዎሮፓ የገባበትን፣ ከዚያም የደራሲውን ማስታወሻ እንዴት እንዳሳተመና እንደሸጠ አንስተን ስንመረምረው የምናገኘው ነው።
ታዲያም ተስፋዬ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይ የበለጠ ትኩረት የሰጠበት በቡርቃ ዝምታ የጀመረውን ኦሮሞንና አማራውን ማለያየቱን በውጭም ማህበረሰባችን ከመቀጠሉም አልፎ በአገር ቤት ወደ ሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥም ዘው ብሎአል። አገር ቤት የጀመረው ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨቱ ትልም እንደፈለገው ሳይሳካለት ቀርቶ ነው መሰለኝ በደራሲው ማስታወሻ ውስጥ በተለየ የጥበብ ክህሎት በየመንገዱ ግለሰቦችንም እየጠራረበ ሄዶበታል። በውስጡ በቀመራቸውና በሰበሰባቸው እውነቶች ሳይሆን፣ በስውር አምባቢያንን ስቦ ወደ ራሱ የማሳብ ሃይሉን ተጠቅሞ በተለይም እዚህ ሳይበሩ የማይናቁ ወዳጆችን ተስፋዬ አትርፎአል። በዚህ ዓይነት ወደ ሳይበሩ ማህበረሰባችን የገባው ተስፋዬ ኢትዮጵያንን የማከፋፈል በሽታ ወደ ሕብረ-ኢትዮጵያን ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ አሸጋግሮ እናያለን። ወደፊት ስንጓዝ የእውነታውን ገሃድነት እንመለከታለን።
ሁለቱ ዝሆኖች በሚል፣
ጮሌው ተስፋዬ ገጽ 57 ላይ ሁለቱ ዝሆኖች በሚል ርዕስ በመለስና በስዬ መካከል ነበረ ስለሚለው የሥልጣን ሽኩቻ መተንተን ከመጀመሩ በፊት ከሁለት ገጣሚዎች መግቢያ እንዲሆነው ቀንጨብ፣ ቀንጨብ አድርጎ አቅርቦ እናያለን። እኔ በተለይ “የጌትነት እንየውን” ወደ ራሱ አዙሬ አየሁ። ግጥሙ እንዲህ ይላል።
“ናላ በጭጋግ ሲሸፈን – ልቦና በስጋት ሲባባ፣
መርሳት በራስ ቤት ሲሰራ – ፍርሃት ግንቡን ሲገነባ፣
ጭንቀት ጓዙን ሲያሳፍር – መጠርጠር ጫፉ ሲተባ፣
ላወቀ መንቃት ያኔ ነው – የሕይወት ክረምት ሲገባ።”
አዎን መንቃት ያኔ ነው ለሆነለት። ታዲያም እስካልተቀደሙ ዘግይቶም ይሆናል። ትክክለኛ አእምሮ ያለው ሰው ሁልጊዜ ከማሰብ፣ ከማስተዋል፣ ከማገናዘብ፣ ክፉንና ደጉን ከመለየት ርቆም አያውቅምና። የኛው መንቃት እየዘገየ ሲሄድ፣ የርሱ የንቃት ደረጃው አብቅቶ ሊመክረን ገብቶአል ተስፍሽ። እስቲ አለፍ እንበል። ተስፋዬ በመጠኑም ቢሆን በገጽ “58-59” ላይ የመለስንና የስዬን ክህሎቶችን ለመተንተን ከሞከረ በኋላ ጠረባውን በስዬ ላይ እንዲህ ይጀምራል።
“ስዬ በመድፍ ተኩስ አይደነግጥም። ተሳስቼ ነበር የምትለዋን ቃል ግን ከመድፍ በላይ ይፈራታል። ስዬ ይቅርታ የምትለውን ቃል ካንደበቱ ሊያወጣ አይቻለውም። ዶ/ር ኃይሉ አርአያ እንደሚሉት ሲቪላዊ ጀግንነት የባህላችን አንዱ አካል ሊሆን አልቻለም። ስህተቱን ከማመንና የፈጸመውን ወንጀል ይፋ ከማድረግ አንጻር ስንመዝነው ስዬ ፈሪ ብቻ ሳይሆን፣ ቦቅቧቃ ጭምር ነው።” በሚል።
አይ ይገርማል የተስፋዬ ብልጠት። የጋዜጠኛው ማስታወሻን በሽፍንፍኑ ይዞ በወጣበት ወቅት የቡርቃ ዝምታን ቀደም ብለው ያነበቡና ተስፋዬን የሚያውቁ እያቀረቡበት የቀጠሉትን ተቃውሞ ለማብረድ ሲል የቆጡን የባጡን ቀባጠረ። መቼም ተስፋዬ በተከፈተ ቀዳዳ እንዴት እንደሚገባ ነው የምንመለከተው ከዚህ አባባሉ። አንድ ወቅት የውጭው ማህበረሰብ ስዬ ከእስር እንደወጣ ላደረገው ስህተት ይቅርታ አልጠየቀም እያለ የሰላ ትችት ሲያወርድበት ሲሰማና
ሲያስተውል የነበረው ይሁዳው ተስፋዬ በመሃከላችን ዘው ለማለት ምቹ ሁኔታ አገኘ። እናም፣ “ሆድ ያባውን ብቅል ያወጠዋል” እንዲሉ ዓይነት ሆነና ስዬ ላይ ሰንቆ የነበረውን የብቀላ ክር መተርተሩን ጀመረው። አጋጣሚውንም በደንብ ተጠቀመበት። እኛም ስዬ በወያኔ ካምፕ ከነበረበት ሁኔታ ውስጥ በስሜት ባቡር ፈጥነን ተቀላቀልነው። ለጊዜውም ቢሆን ተመቸነውና ሜዳ እንዳይበቃው አደረግነው። እናም እስኪ እንቀጥል።
በተለይም ገጽ “59” ላይ ወረድ ብሎ ተስፋዬ፣
“ስዬ በረጅም ርቀት የመገናኛ ሬዲዮ ከአዲስ አበባ ከጻድቃን ተከታታይ ሪፖርት እየተቀበለ መመሪያ ይሰጥ ነበር። ከጋዜጠኞቹ ጓደኞቼ ጋር እዚያች ቁጭ ባልኩባት ደቂቃ ስዬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ በተመለከተ መረጃ ደረሰው።” አለን። ቀጠለም ትርተራውን ተስፋዬ። ስዬ መመሪያ ከሰጠ በኋላ እዚያው ለነበርነው ጋዜጠኞች፣ “ለምነን ኢትዮጵያዊ አንሆንም። ካልፈለጉ ማይጨው ላይ በታንክ ዘግተን ቁጭ እንላለን”። ደግሞም አለ ተስፋዬ፣ በወቅቱ የስዬ ፍርሃት ወለል ብሎ ታይቶኝ ነበር። የጦር ሜዳውን ውጊያ በድል ያጠናቀቀው ጀግናው ስዬ ከሰላማዊው ትግል ፊት ሲርበተበት አየሁት። ከደርግ ግዙፍ ብረት ለበስ ጦር ይልቅ እሰላማዊ ትግሉ ፊት ሲንቀጠቀጥና ወደ ማይጨው ስለማፈግፈግ ሲያወራ በጆሮዬ ሰማሁት።” ብሎ ይደመድማል።
ታዲያም በየሚዲያዎች ስለ “ቡርቃ ዝምታ” መጽሐፍ ተስፋዬ ሲጠየቅ በትክክል ነው የጻፍኩት። እውነቱን ነው የጻፍኩት። እንደዚያ በመጻፌ የፈጽምሁት ጥፋት የለም። የፈጸምሁት በደል የለም የሚለን ተስፋዬ፣ ስዬ ይቅርታ አልጠየቀም ብሎ ስንክ ሳሩን ያወርድበታል። ተስፋዬ ለነገሩ በስዬም ላይ አላቆመም። በዶ/ር ነጋሶ ላይ መዓቱን ያወርድ እንደነበር የምናስታውሰው ነው። እነዚህ ሰዎች አስቀድሞ ለሰሩት፣ ለተሳሳቱ በወሬ ሳይሆን በተግባር ወደ አንድነት ሃይሉ ተቀላቅለው ጠጠር እየወረወሩ ይገኛሉ። ባገር ቤቱ የሕዝብንም አመኔታ እያገኙ ነው። ይህ ደግሞ ለተስፋዬ ራስ ምታት ሆኖበታል። እናም፣ ከላይ እንዳልኩት ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባበታል ዓይነት ነገር ሆነና እንደመስክ ብቅ ያሉለት ስዬና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናቸው። ለምን ግን? ወደ ኋላ ጠቅለል አድርገን እናየዋለን።
ተስፋዬ በዚህ በቀመረው የአዲስ አበባ ተማሪዎች ዙሪያ ሳያውቅ እየነገረን ያለው የስዬን እኩይ ተግባር ወይም ጨካኝነት ሳይሆን፣ የስዬን አርቆ ማሰብን መሰለኝ። ተማሪዎቹ ከጠሉን ከነርሱ ጋር ግብግብ ውስጥ ሳንገባ፣ ጉዳት ሳናደርስ ወደነበርንበት እንመለሳለን ዓይነት ይመስለኛል እንደእኔ አተረጓጎም። ከዚህ ውጭ በዚያን ወቅት በነበረው ሁኔታ ስዬ በላቸው!፣ ቸርሳቸው፣ ፍጃቸው ማለት ነበረበት? በመሠረቱ መነሻው ትክክል ያልሆነና ውሸት ነገር፣ መንገዱም ሆነ መድረሻውም እንደዚሁ ትክክል ያልሆነና ውሸት ሆኖ ይደመደማል። የሎጅክ አካሄዱ እንዲህ ነው። ለነገሩ ከጅምሩ እንዴት ተስፋዬ ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ጋር ስዬን ለማገናኘት እንደቻለ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም፣ እንዳልኩት ስዬን ለማጋለጥ ተነሳስቶ፣ የስዬን ጀግንነትና አስተዋይነትን የነገረን ይመስለኛል። ታዲያም ሙከራው ከምንም በላይ የራስን የውስጥ ሽረባና ተንኮል አጉልቶ ከማሳየት በስተቀር፣ ሲነቃ ከንቱና ፋይዳ ቢስ ከመሆን የሚያልፍ አይሆንም። ለነገሩ ስዬ በወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር እንጂ የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ወይም የሕዝብ ደንነት ሃላፊ አይደለም። የማይፈለጉትን ሰዎች እያሳሰረ የሚገድለውና የሚያስገድለው የመከላከያ ሚኒስቴር ሳይሆን፣ የሕዝብ ደህንነቱ ከአፋኝ ድርጅት የፌዴራል ፖሊስ ከተባለው ጋር ነው። ተስፋዬ የፕሮፓንዳ ካድሬና የደህንነት ሥራም ሲያከናውን እንደነበረ በመጽሐፉ በግልጽ እንደነገረን ከላይ ተመልክተናል። እናም፣ እንዲያው ነገሩ “የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን” ዓይነት አይመስልምን?
 የስዬና የመለስ ሽኩቻ፣
ገጽ 61 ላይ ተስፋዬ የመለስና የስዬ ሽኩቻ መቼ እንደተጀመረ እንደማያውቀው ይግልጽና ቀጠል አድርጎም፣ “የሁለቱ ዝሆኖች መጠላለፍና ሽኩቻ የጀመረው ‘ደቂ አድዋ’ እና ‘ደቂ ተምቤን’ መልክ ይዞ ይፋ የወጣው ስዬ የመከላከያ ሚኒስትር በነበረበት በ1985 መጀመሪያ ላይ ነው።” ይለናል። እንዲሁም ደግሞ ወደ መጨረሻው አካባቢ ፕሮፌሰር መስፍን ይልና፣ፕሮፌሰር መስፍን፣ “ስዬ አብርሃ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ አጀንዳ ከመለስ ጋር በፈጠረው ልዩነት ሥልጣኑን ተነጥቆ ወደ መቀሌ በቅጣት መዛወሩን ገለጸልን። ”በወያኔ ጓዳ ዙሪያ ለነበርነው የፕሮፌሰሩ መረጃ አዲስ ባይሆንም፣ ጉዳዩን አንስቶ ለመወያየት ግን በር ከፍቶልን ነበር። በዚህ ሳቢያም ከመቀሌ ከስዬ ጋር ቃለ-መጠይቅ ላደርገው ተስማማን። ወደ አዲስ አበባ ስዬ እንደተመለሰም፣ ቃለ መጠቅ አደረግሁት። በውይይታችን ወቅት የማይታተም በሚል በህወሃት አመራር ውስጥ የመከፋፈል አደጋ ተከስቶ ነበር የሚል ወሬ መኖሩን ጠቆም አድርጌ ነበር። ስዬ ባጭሩ “ውሸት ነው ሲል አስተባበለ። እንዳለ ወረድ ብሎ ደግሞ ስዬን የማላምንበት ምክንያት አልነበረም። እና ወሬው ውሸት የመሆን ዕድል ሊኖረው እንደሚችል ግምት ወስጄ ወደ ቀጣዩ ሥራዬ አመራሁ።” በማለት የወያኔ ባለሥልጣን ስለነበርሁ ሁሉን ነገር አውቃለሁ ስለን የነበረው ተስፋዬ፣ እንዲህ ዓይነቱን መንግሥታዊ ምስጢርን ከሌላ ሰው መስማቱን ይነግረናል።
ገጽ 63ን ስንመለከት፣
ስዬ አብርሃ መቀሌ ከገባበት ዕለት ጀምሮ እንደ ትግሉ ጊዜ አንገቱ ላይ ክሹክ መጠቅለሉን ሆን ብሎ ቀጠለበት። ከኤርትራ ጋር በድንበርና በጉምሩክ ነክ ጉዳይ መተናኮል አበዛ። ይህም መለስን የሚረብሸው ሆኖ ተገኘ። ወደ ኤርትራ የሚያልፉ ኤርትራዊያን መንገደኞችን እያስፈተሸ ግማሽ ኪሎ በርበሬ መውረስ በመጀመሩ መለስ ወደ ስዬ ደውሎ፣ “የፖለቲካ ዝምድናውን ወደ በርበሬና ሽሮ ደረጃ እያወረዳችሁት ነው።” ብሎ ስለማለቱ የአንድ ሰሞን የሰፈራችን ወሬ ለመሆን በቃ አለን ተስፍሽ።
ይህ የተስፋዬ አባባል የሚያስረግጠው፣ ቀደም ሲል “እየተስተዋለ” በሚለው ጽሑፌ ላይ ስዬና ተከታዮቹ ምናልባትም ከትግል ሜዳ ጀምሮ ከነመለስ ግሩፖች ጋር ፍትግያ እንደነበራቸው የገለጽሁትን ነው። ኤርትራ የቡና እግር ሳይኖራት አንድ ወቅት በቡና አቅራቢነት ከዓለም ሦስተኛ ሆና እንደነበር የማንረሳው ነው። እናም፣ ተስፋዬ ስዬን ለማዋረድ በጠነሰሰው በዚህ ጽሑፉ፣ ስዬ በአንድ ወቅት ከአቅሙ በላይ የሆነውን ነገር ወደ ነበረበት ለማስመለስ ያደረገውን ጥረት ቁልጭ አድርጎ እያሳየን ነው።
መቼም ተስፋዬ መለስን በአጨዋችነት ገጸ-ባሕርይ ከስዬ ጋር ለማወዳደር ተጠቀመ እንጂ የተነሳበት አላማ ልብ ላለው በግልጽ እንደመስተዋት ቁልጭ ብሎ ይታያል። ታዲያም ተስፋዬ በዚሁ የቆጥ-ባጥ ትረካው እግረ መንገዱንም ፕሮፌሰር መስፍንን በአግቦ ነካ ሳያደርጋቸውም አላለፈም፤ የስዬ ምስጢር ተካፋይ ዓይነት አድርጎ ለማሳየት። ተስፋዬ ትክክለኛ አእምሮ ያለው ሰው ሊረዳው በሚችለው መልክ እየነገረን ያለው፣ ስዬ በኢትዮጵያዊያን ላይ ስለሰራው አስነዋሪ ነገር ሳይሆን፣ ስዬ የአባቱ አገር የኤርትራ ጠላት መሆኑን፣ እና በእንዲህ ዓይነት ዘዴም ስዬን ከኢትዮጵያዊያን ጋር አጋጭቶ፣ ከትግል ሜዳው ለማስወጣትና ለሻቢያ እፎይታ ለመስጠት እንደሆነ ከአተራረኩ በቀላሉ ለመረዳት ይቻል ይመስለኛል።
ይቀጥላል የተስፋዬ ቅዠት ገጽ 64 ላይ እንዲህ በሚል፣ “ሁለቱ ዝሆኖች በኤርትራ ላይ ያላቸው አመለካከት ግልጽ ነበር። ስዬ ሻቢያን፣ እና ኤርትራን ሕዝብ በአንድ ላይ ጨፍልቆ የሕወሃት ጠላት ሲል ፈርጆአቸዋል። ስዬ የኤርትራን ሕዝብ በጠላትነት የሚመለከተው ከዚያው ከተለመደው፣ ይንቁናል ከሚለው ዘፈን ተነስቶ ነበር። መለስ በአንጻሩ ሻቢያንና ኤርትራን ሕዝብ ለያይቶ የማየት ዝንባሌ ነበረው። የሁለቱ አገሮች ግጭት እንደተከሰተም ስዬ የውስጥ ሕመሙን ለመፈወስ ይህን አጋጣሚ ሊጠቀምበት ወገቡን ባጭሩ ታጥቆ ተነሳ። መለስ ሻቢያ እንዲወገድለት አጥብቆ ቢፈልግም፣ የኤርትራን ሕዝብ እንደሕዝብ ዘሩን የመደምሰስ ቂም በቀል ዝንባሌ አሳይቶ አያውቅም። ስዬ ሕዝቡንም ሻቢያንም የመጨፈላለቅ ዓይነት በቀል አርግዞ ነበር።”
ገጽ 65 ላይ ደግሞ፣ እነ ስዬ በወቅቱ ኢትዮጵያ የአሰብን ወደብ እስከ መያዝ ልትደርስ እንደምትችል ለሕዝቡ ተስፋ “በመመገብ ሰፊ ድጋፍ ለመሸመት መቻላቸው ግልጽ ነበር። እንደገናም ይላል ተስፋዬ፣ “ገብሩ አሥራት በስዬ ሴራ ከተጠለፉት የመጀመሪያዎቹ ነበር። የትግራይ ካዲሬዎችን ሰብስቦ፣ ኤርትራያዊያን አንድ ድመት ለአምሳ አይጥ፣ አንድ ፍሊት ለሃምሳ ዝንብ ይሏቸዋል ሲል ሚዲያ ላይ ቀርቦ ቀሰቀሰ። የትግራይን ሕዝብ በአይጥና በዝንብ መምሰሉ ግን የስዬና የገብሩ ንጹህ ፈጠራ ነበር። ዝንብ እና አይጥ ወይም ድመትና ፍሊት የሚሉ ቃላት ከኤርትራ ወገን ስለመነገራቸው ግን ማስረጃ አልነበረም።”
ገጽ 66 ላይ፣
“ከመነሻው ስዬ በመለስ ደካማ ጎን ገብቶ ወቅታዊ ቅስቀሳ ማድረግ በመቻሉ ከፍተኛ ድጋፍ አገኘ። የስዬ መከራከሪያ የማያሻማ ነበር። ሻቢያ ድንበራችንን አልፎ ገብቶአል። ስለዚህ ሏላዊነታችንን ማስከበር አለብን። ሻቢያን ከድንበራችን ማስወጣት ብቻ ሳይሆን፣ ልንጨርሰው ይገባል። ይህን ማድረግ እንችላለን የሚል ግልጽ አላማ ይዞ ተነሳ። መለስ ደግሞ በድርድር ብቻ ውዝግቡን ማስወገድ ይቻላል የሚል አቋም ነበረው። በውይይትም ወቅት ሚዛን ወደ ስዬ ወገን ሆነ።” አለን ተስፋዬ።
ገጽ 68 ላይ እንዲህ ይላል ተስፋዬ፣
“የመለስና የስዬ ሽኩቻ በጦፈ ሁኔታ ውስጥ ውስጡን ቢቀጥል አንዱ ሌላውን ጥሎ ለማለፍ የሚያደርጉት ትግል ግን አማራውን ኦሮሞውን ወደ ሥልጣን እስካላመጣ ድረስ ብቻ ነበር። ትግላቸውና ሽኩቻቸው እስከሕይወት መጠፋፋት ሊዘልቅ የማይችልበት መነሻውም ይኸው ነው።” እንግዲህ ሆድ ያባውን ብቅል ያወጠዋል ዓይነት ሆነና ተስፋዬ በአእምሮው ሊደብቅ የሞከረውን ሳያስበው እየወጣበት ነው። አለዚያም እኛን እንደእውር ቆጥሮናል ማለት ነው። እዚህ ላይ ለምን ተስፋዬ ስዬን ጠመደው? እውነትስ ለኢትዮጵያ ተቆርቁሮ ነው ወይስ ከበስተጀርባው ሌላ ነገር ይኖራል? የሚሉትን ጥያቄዎችን ለሚያነሱ ሰዎች ግልጽ መልስ ይገኛል። እንዳለ ይህንኑ የተስፋዬን እኩይ ቅመራ ለተቀበሉትም ሁኔታዎችን እንደገና እንዲያዩ መንገድ ይከፍታል ብዬ እገምታለሁ። ተስፋዬ ሽንጡን ገትሮ ስዬን ቢሆንለት ለማጥፋት የተነሳው፣ ስዬ በዚያን በጦርነቱ ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም፣ ቀደም ሲል እርሱና ጓደኞቹ ባልነቁበት ወቅት የተፈጸመውን ስህተት ለመመለስ ቁርጥ አቋም ይዞ መነሳቱ ነው። ይህን አካሄዱን ለማስቆም ነው።
የተፋው ምራቅ እንኳ ሳይደርቅ ተስፋዬ
ገጽ 71 ላይ፣
“ከክፍፍሉ በኋላ ዘግይቶ እንደሰማነው መለስ ከመቀሌ ሲመለስ በጦር ጄት አየር ላይ እንዲመታ እቅድ ተይዞ ነበር። መለስን አየር ላይ እንዲመታ የተዘጋጀው ፓይሌት ይልማ መርዳሳ የተባለ የSU27 አብራሪ የኦሮም ተወላጅ እንደነበር በወቅቱ ተነግሮአል። የተዘጋጀውም ምክንያት፣ መለስን የያዘው አይሮፕላን በሻቢያ ስለተጠለፈ ይመታ የሚል ነው። ዳቦ በሚል የቅጽል ስም የሚታወቀው የትግራይ ተወላጅ ፓይሌት ይልማን ባየር ላይ ወዲያውን እንዲመታ ተዘጋጅቶ ሃይሌ ጥላሁንና ክንፈ ገብረመድኅን አከሽፉት። ግድያ ሴራውን ሃይሌ ጥላሁንና ክንፈ ገብረመድኅን አከሸፉት ተብሎ የነመለስ ሰዎች ርስበርሳቸው ሲሞጋገሱ ሰነበቱ። በየግብዣዎቹ ላይ ለማንም እንዳትናገሩ እየተባለ ከማስጠንቀቂያ ጋር ለእኛ ይነገረን ነበር። በዚያን ሰሞን ዳቦ ኮብልሎ ወደ ካናዳ ሲገባ፣ ይልማ መርዳሳ ከመለስ የገንዘብ ሽልማትና ሹመት ተቀብሎአል በማለት እውነቱን ተስፋዬ ከተፋ በኋላ፣ ይህች ወሬ በወቅቱ አልጣመችኝም። የህንድ ፊልም ትመስላለች በሚል ያሳርጋል።
እንግዲህ የዋጠውን እውነት በእንዲህ መትፋቱ ትዝ አለውና “ይህች ወሬ አልጣመችኝም። የህንድ ፊልም ትመስላለች” በሚል በተለምዶው ሽወዳ ሊያልፈን ሞከረ። በእንዴት? ትሉ ይሆናል። ልብ በሉ። ከላይ እነርሱ (መለስና ስዬ) ለሥልጣን ሽኩቻ ካልሆነ በስተቀር አይጠፋፉም ብሎናል። ነገሩ የማይመስል ነበር። ቀጠል አድርጎ እነ ስዬ መለስን ሊያጠፉት የተንኮል መረብ ሸርበው እንደነበር ተስፋዬ ነገረን። የተፋውን ለመመለስ እየሞከረ። ግን የማምለጫ በሩን ራሱ አስቀድሞ ዘግቶታል። እንዴት? የህንድ ፊልም የማስመሰል ከሆነ ፓይሌት ዳቦ ለምን ኮበለለ? ይህን ጥያቄ መመለስ በቂ ይሆናል የውሸት ድርቶውን ለማስረዳት። ብቻ ውሸት ሲያንቅ እውነት ይተፋል ዓይነት ሆነና ተስፋዬ ሲጎነጉን የቆየው መርዝ ፈልቶበት አስተፋው ብለን ማለፉ ይሻላል። በዚያ በ2002 ምርጫ አካባቢ በአንድነት ፓሪቲ ውስጥ የተፈጠረውን ቀዳዳ በመጠቀም ባይሳካለትም ፓርቲውን ሁለት ቦታ እንዲከፈል ተስፋዬ የሞከረው “ሁለቱ ለሥልጣን እንጅ አይጠፋፉም” በሚል መርዘኛ አነጋገሩ ነበር።
ገጽ 212 ላይ ወረድ ይልና አቦይ ስብሃት ስለ ስዬ ተጠይቀው፣
“ስዬ አብርሃ የሰገራ ቤት አይጥ ሆኖአል።” ሲሉ ተናገሩ ይልና ይቀጥላል። አቦይ ስብሃቱ ስዬን ለምን እንዲያ እንደሰደቡት ቤትኞች እናውቃለን። ህወሃትን እንደጣውላ ለሁለት በሰነጠቀው ስብሰባ ወቅት ስዬ ሽማግሌውን “ሰካራም” ሲል ሞልጯቸው ነበር። ስዬ ተሳዳቢ ነው። ክንፈን “አሽከር” ሲል ሰድቦታል። አቦይ እንግዲህ ለዚያች ምላሽ መስጠታቸው ይሆናል አለን። ተስፋዬ ስዬ መለስን “አንተ የባንዳ ልጅ” ይለዋል ብሎም ነግሮናል።
በዚህም ስዬ በህወሃት ውስጥ ትግሉን የጀመረው ትናንት በወጣበት ሰሞን ሳይሆን፣ ቀደም ብሎ በጧቱ እንደሆነ ስንረዳ በአንድ በኩል፣ በሌላም ትጉሉም በአጎብዳኞች ላይ በበረታና ጽናት ባለው መንገድ መሆኑን ነው። ከዚህም በላይ ይህ የተስፋዬ በስዬ ላይ አሰሱን ገሰሱን ከምሮ የማስመታት ጥንስስ፣ ስዬ እንደሌሎቹ መለስ እንደፈለገው ሊያሽከረክረው የማይቻለው ሰው እንደሆነ በገሃድ አመላካች ነው። ይህ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ የምንለው ሲጠፋን ስዬንና መለስን ያጋጫቸው የፖለቲካ ልዩነት ሳይሆን፣ የኤኮኖሚ ጉዳይ ነው የምንለውን አነጋገር የሚያስሰርዝ ነው። ተስፋዬ መቼም ስዬን በተገኘው ቀዳዳ እየገባ ለማስመታት ጉድጓድ በቆፈረ ቁጥር ሳያስበው ስለስዬ ጠንካራና ጥሩ ጎን እየነገረን ያልፋል። አንዳንዶቻችን የተስፋዬን አባባል በግርድፉ ወስደን፣ ከስዬ ላይ ካለን ቅሬታ ጋር አዛምደን ተርጉመን አየነው እንጂ እንደተስፋዬ አባባል ከሆነ፣ ከምንም በላይ ስዬን ያወደሰ፣ የስዬን ጀግንነት የነገረን እርሱ ነው ለማለት ይቻላል። ነገሩ “የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን” መሆኑ ነው።
ራሱን መልአክ ሌላውን ሰይጣን፣
ከፍ ሲል ለመጠቃቀስ እንደተሞከረው ተስፋዬ ከነበረበት ከወያኔ ካምፕ ውስጥ ሆኖ የፈጸማቸው ሥራዎች አይደሉም ለጽሑፌ መነሻዬ። ብዙዎቻችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በወያኔ ሥርዓት ውስጥ እኔን ጨምሮ ስናገለግል ነበር። በነበርንበት ቦታ የሠራናቸው ሕገ-ወጥ ተግባሮች ካሉ፣ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት፣ ነጻ ማህበረሰብ፣ ነጻ የሆነ የፍትሕ ተቋማት ቦታውን ሲረከቡ እንደህዝቡ ጥያቄ የሚታይ ይሆናል። ይህንኑ እግንዛቤ ያስገባው የውጭው ማህበረሰባችን ወደ ውጭ እንደወጣን እንኳን መጣችሁ ብሎ ተቀብሎናል። ያንን ጨቋኝ መንግሥት ለመጣልና በቦታው ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ለመመሥረት ከወጣነው የተግባር እንቅስቃሴ እየጠበቀ። ተስፋዬም ከነበርኩበት ከወያኔ መንግሥት ተላቅቄ ወደ እናንተ መጥቻለሁ ሲል ሰው ቅሬታ ቢኖረውም፣ እስቲ እናየዋለን በሚል መልኩ እንደማንኛችን እጁን ዘርግቶ ተቀብሎታል። እናም “እመኑኝ፤ ስሙኝ፣ ተቀበሉኝ” ሲል፣ አዎ እናምናሃለን፣ እንሰማሃለን፣ ግን አሳየን ብሎ ነው የተቀበለው። ነገር ግን እሱ ከነበረበት ተመሣሳይ ካምፕ የመጡትን እነ ስዬንና ዶ/ር ነጋሶን የመሳሰሉትን ግን አትመኗቸው፣ አትቀበላቸው፤ የወያኔ ተልዕኮ አስፈፃሚዎች ናቸው” በማለት ደጋግሞ እስኪሰለቸን መንገሩን ተያያዘው። ከጅምሩ ግራ የሚያጋባ ነገር። ትልቅ የጥርጣሬ መነሻ የሚሆነን፣ እርሱ መልአክ ሆኖ ሊታመን፣ ሌላው እርኩስና አርዮስ ሆኖ እንዲታይ መሞከሩ ነው። ነገሩ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ መሳይ። ግን ለምን? ትልሙ በፊት ገጽታው በግለሰቦች ላይ ከነበረው ጥላቻ ተነስቶ ሊመስለን ይችላል። ከበስተጀርባው ያለውስ?
ነገሩ ልብ ያለው ልብ ያድርግ ነው። እናም እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ተስፋዬ እንዲህ ዓይነት ችቦውን የለኮሰበትን ጊዜ፣ እና ሁኔታ ነው። ጊዜው በሁለት ሺህ ምርጫ መቃረቢያ አከባቢ በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የትብብር ጥያቄ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ በሆነበትና ሕዝቡ ልክ እንደ 97ቱ ተቃዋሚዎችን፦”ተባበሩ፤ ወይ ተሰባበሩ” እያለ ባለበት ሰዓት መሆኑን ነው። እንዲህ ሕዝቡ ከማለት ጋር ቀደም ሲል በኢህአዴግ ውስጥ ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ የነበራቸውንና በግል ይንቀሳቀሱ የነበሩትን ስዬ አብርሃንና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ወደ ሕብረ-ብሔር ፓርቲዎች እንዲቀላቀሉ ጠይቆ እነርሱም ተቀብለው አንድነት ፓርቲን በተቀላቀሉበት ወቅት ነው።
እንደዚህ እንደ ወያኔ ዓይነት አሸባሪ መንግሥትን ለመጣል የግለሰቦችም ሆነ፣ የድርጅቶች ሕብረት ልክ እንደ 97ቱ በጅጉ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ ነው። ከአንድ ብርቱ ሁለት መድኃኒቱ ተብሎአልና። በደራሲው ማስታወሻ ገጽ 323 ላይ ራሱ ተስፋዬ፡ “ዛሬ ይህች አገር በጎሳ ፖለትከኞች፣ እና በኢትዮጵያዊነት አራማጆች ጽንፋዊ ትግል መካከል የስንግ ተይዛለች። ኢትዮጵያዊነት ማሸነፉ አይቀርም። ምን ያህል ዋጋና ጊዜ እንደምንከፍል ግን ገና አልታወቀም። ‘የትብብር ጩኸት’ የሚባል ነገር አለ። ይህችን ቃል ያገኘኋት ሙሉጌታ ሉሌ በ1997 ከጻፈው አንድ መጣጥፍ ላይ ነበር። ባለንበት ዘመን የሚያስፈልገን ግን ከዚያም በላይ ‘የትብብር ቁጣ’ ጭምር ነው።” በማለት አጽንዖት ሰጥቶ ለኢትዮጵያኑ ነግሮናል። የሚነዝር ቃል፤ የሚነዝር አነጋር።
ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ሆ ብለን ወደኋላ ላንመለስ ቀበቶአችንን ጠበቅ አድርገን ልንናሳ ይገባል ነው እንደገባኝ ይኸው የተስፋዬ አነጋገር። እናም፣ ትክክል ነው በዚህ ዘመን የሚያስፈልገን ይህ ነው። ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ነው።
እንዲህ የሚለንና ያለን ተስፋዬ በተግባር ሲታይ ግን ያስተዋልነው የአባባሉ ተቃራኒ ነው። አገር ቤት ያሉ ፓርቲዎች ከምርጫ 2002 ከመድረሱ በፊት ሕብረት እየፈጠሩ እና እየገዘፉ ለወያኔ የራስ ምታት እየሆኑ መምጣት ሲጀምሩ፣ ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ ያለበት መድረክ (ወደ 9 ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው) ላይ ተስፋዬ በሆዱ ያባውን የተንኮል መረብ መዘርጋት መጀመሩን አየን። በተለይም በህዝቡ ጥያቄ ወደ አንድነት ፓርቲ በተቀላቀሉት በዶ/ር ነጋሶ፣ እና በስዬ ላይ አጠቃላይ ዘመቻ ከፍቶ አየነው። ከሁሉም በላይ ወደዚህኛው ጎራ ሲቀላቀል ለተቃዋሚ ሀይሎች ህብረት፣ መግባባትና ተፋቅሮ መስራት በመትጋት ፋንታ፤ የልዩነት ወንጌል እየሰበከ መምጣቱ እጅግ ልብን ያደማ ክስተት ነው።
እየሰበከ ባለው የልዩነት ወንጌል የተነሳ፣ የአንድነትና የመድረክ ፓርቲዎች በሕዝቡ ዘንድ በጥርጣሬ ዓይን እንዲታዩ ተደርገዋል በወቅቱ። ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን፣ በ2000 ዓ.ም ምርጫ ዋዜማ “መድረክ ምርጫውን ሳያሸንፍ አይቀርም” የሚል ወሬ በተሰራጨበት ሰሞን፤ ”ምንጮቼ ገለፁልኝ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ፅሁፍ ተስፋዬ፣ መለስ እና ስዬ ስልጣን ሊቀባበሉ እንደሆነ” በሚል ሰፊ ትንተና አቀረበ። አንዳንዶቻችን በስሜት ተጠምደን ይህንኑ እንዳለ ተቀብለን አራጋፍንለት። ሆኖም በምርጫው ማግሥት በተግባር የታየው እውነታ የዚህ ተቃራኒ ሆኖ መገኘቱ ነው። በኋላ ደግሞ ይህ የነደፈው ሰይጣናዊ ትልም እንዳይነቃበት ሲል፣ ተስፋዬ “ዘግይቶ የደረሰኝ ምስጢር” በሚል ርዕስ መለስና ጭፍሮቹ ስዬና አራጋሽ እንዳይመረጡ ለማድረግ ኢህአዴግ ምክር ቤት ምርጫው ሲቃረብ መክረው ወስነው እንደነበር ምንጮቼ ገለጹልኝ በሚል አሾፈብን። እኛም ሰምተን ዝምበል አንተ ቀጣፊ። ደርሰንብሃል አላልነውም። እናም እርሱም ቀጥሎበታል።
ተስፋዬ አንዳንዴ ከማስታወሻዬ ላይ እያለ፣ አንዳንዴም ደግሞ ከእውነተኛ ምንጮች እያለን ከሰጠን መላ-ምት መረጃዎች ውስጥ ምን ያህሉን እውነት ናቸው የሚሉ ጥያቄዎች ሊያስጭሩ ይችላሉ። “አዛኝ ቅቤ አንጓች” እንዲሉ ከራሳቸው ከኦሮሞ ማህበረሰባችን በላይ ለኦሮሞች አሳቢ በመምሰል የውጊያ ጦር ሜዳውን በቡርቃ ዝምታና በጋዜጠኛው ማስታወሻ ላይ ሲያስቀይስ የነበረው ተስፋዬ ያሰበው አልሳካለት ሲል፣ በዚህ መጽሐፍ ገጽ 172 ላይ፣ “ገናናነቱ ሲነገርለት የነበረው የኦነግ ሠራዊት ግማሽ ቀን ባልሞላ ውጊያ ፍርክስክሱ ወጣ! ኢህአዴግ የማይደፈር ሕዝባዊ ሃይል መሆኑ ተረጋገጠ!። የኦነግ ሠራዊት እንደ አቧራ ቦነነ!።” በሚል በሆዱ ይዞት የቆየውን ጉድፍ ዘረገፈው።
በወቅቱ ኦነግ ከምክር ቤቱ እንዲወጣ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው ደህንነቱ ነው። ከዚያም የኦነግ አባላት ላይ መከራና ግፎች እንዲፈጸሙ ሲያደርግ የነበረው የገሃነም እሳት በሆነው ደህንነቱ ነው። ከራሱ ጽሑፍ ስንነሳ ደግሞ ተስፋዬ ከክንፈ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራ የነበረ ነው። እናም፣ እንደዚያ ሲክብ የነበረውን የኦሮሞን ሕዝብ፣ እንደዚህ ሲክብ የነበረውን የኦነግን ትግል በአንዴ አውርዶ እንደማይረባ ዓይነት ዘጭ አደረገው አጅሬ ተዋናዩ “የኦነግ ሠራዊት እንደ አቧራ ቦነነ” በሚል አነጋገር።
ምኑ ቅጡ የተስፋዬ ትረካ ገጾች እንዲበዙለት፣ የሰውን ስሜት ለመግዛት ያልቀየሰው መንገድ፣ ያልገባበት ቀየ የለም። እናም ገጽ 342-343 ላይ፣ “ሮሮ እና ይቅርታ” በሚል ርዕስ፣ ጄኔራል ታደሰ ብሩ በኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበሩት አክሊሉ ሀብተወልድ ጋር በተደረገ ውይይት ምክንያት ወደ ኦሮሚያ ነጻ አውጭነት እንደተሸጋገረ ተስፋዬ ነገረን። ከዚያም ከዚህም እያመጣ ንጹህ ኢትዮጵያንም ላይ ጭምር ጥላሸት መቀባት የተስፋዬ ውሎ ነው ያሰኛል።
ላናያቸው፣ ላንሰማቸው አልፈው ተገኙ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ በሳልና የነገሮችን አካሄድና አመጣጥ ጠንቅቀው የሚያውቁ ብልህ የሕግ ምሑር እንደነበሩ የኃይለሥላሴ አማካሪ የነበሩ አሜሪካዊው ስፐንሰር በደንብ ነግረውናል። እንደተነገረው ኤርትራዊያን ጦር መዘው ወደ ጫካ የገቡት፣ ፌዴሬሽኑ ከፈረሰ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ፣ ንጉሡ ፌዴሬሽኑ እንዲፈርስ አድርገው፣ በውህደት ኤርትራ ወደ እናት አገሯ ወደ ኢትዮጵያ እንድትቀላቀል ሙከራ ሲጀምሩ፣ አዝማሚያውን ያዩትና የዳሰሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ፣ ኧረ ጌታዬ ይህ ነገር አላማረኝም። ባሉበት በፌዴሬሽኑ ለምን አይቀጥሉም? በማለት ምክንያቶችን ዘርዝሮ ለንጉሡ ሲነግራቸው፣ አንተ እኛ ያልንህን ለመሥራት እንጂ የተሾምከው ልታዘን አይደለም ብለው ጸጥ አደረጉት ይላል ጆን ኤች. ስፐንሰር። ልክ ውህደቱ እንደታወጀ ነው እነ ጀባህ ወደ ጫካ የገቡት እንደሚባለው። እናም እንዲህ ያለ አርቆ አስተዋይ መሪ እንዲህ በከፋፋይ ሰው ሲጎድፍ መስማትና ማየት ልብ ያደማል።
ሌላው እውነት አልነገረንም እያለ ተስፋዬ እርሱ በደህንነት አባልነት ከክንፈ ጋር ሆኖ በስውር ስለፈጃቸው ንጹህ
ኢትዮጵያዊያን አንዳችም ፍንጭ ሳይሰጠን፣ ግን በዚህ እውነት በሚመስል ሽፋን አነጋገር ሽው ብሎ ለማለፍ ሞክሮአል። ለጊዜውም ተሳክቶለታል። ትግል ከሕሊና ጋር ከተባለ ከራሱ መጀመር ነበረበት። የነገረን የመሰለን አዲስ ነገር ሳይሆን፣ የምናውቀውን ብቻ ነው። ግን ድብቅ እና በደህንነቱ ወቅት የሰራውን ሁሉ መዘክዘክ ይጠበቅበት ነበር። ግን ከሽውዳ በስተቀር ተስፋዬ አንድ መንገድ እንኳ ፈቀቅ አላለም። ለምን? ትዕግሥቱ ይኑረን።
ክፍል 4.
ተስፋዬን በማስታወሻዎቹ
እንግዲህ ይህን ያህል ተስፋዬን በመጽሐፎቹ ካየን፣ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ ወደ ሆነው ወጣቱ አለማየሁ ከተስፋዬ ጓዳ ደክሞ ሰብስቦ ወዳመጣቸው ማስታወሻዎቹ እንለፍ። አባት አገር፣ ቀጥሎ በምትመለከቷት ረቂቅ ሰንድ ላይ ተስፋዬ ጉዞው ወዴት እንደሆነ በቀስት አሳይቶን እናያለን። “አባት መሬት” በሚል ርዕስ ስለኤርትራ ትግል ሙሉ በሙሉ አንድ መጽሐፍ ለመጻፍ ያለመበትን የሚያሳይ ረቂቅ ሰነድ አለማየሁ ከተስፋዬ በተለየ ዘዴ ያገኘውን እንመለከታለን። በዚህች ረቂቅ ሰንድ ላይ ተስፋዬ የነደፋቸውን ክፍሎችን እናያለን። በቅደም ተከተልም፣ “አባት መሬት” ይልና አተራከኩን በሚመለከት በጎኑ “አንድ ለእናቱ ዓይነት” ኢሳያስን ለማሞገስ   የታቀደ ርዕስ ይመስለኛል፣ ከዚያም ውቃቢው ሙሉ በሙሉ፣ የልጅነት ታሪክ፣ ከነጻነት በኋላ ይልና አቤልና ቃየል ስታይል፣ ከልጅነት እስከሞት የአንድ ሰው ታሪክ፣ አዲስ አበባ ሙሉ ታሪክ ያለበት (ማወናበጃ)፣ መሬት ላይ ስለመቀበር፣ የኢሳያስን ቃለመጠይቆች በሙሉ ማንበብና፣ ማጠራቀምና መሰብሰብ::” የሚሉ ይገኙባቸዋል። ማስታወሻዋም ቀጥሎ የምትታየው ነች።
እንግዲህ ከዚህ ተነስተን የአስተውሎት አድማሳችንን ብናሰፋ፣ በቀጥታም ባይሆን ተስፋዬ በመስቀለኛ ባሕርይውንና እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባሩን ነግሮናል። በሚቀጥለው “የስደተኛው ማስታወሻ” ላይ ገና ጉልህ አድርጎ ይነግረናል። እንደለመደውም መስኮችን አሰባስቦአል። እነርሱንም እንመለከታቸዋለን። በሕሊና መነጽርም እንጓዛለን።
ተስፋዬ ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ የቢሾፍቱ ልጅ ነኝ፤ አሁንም ነኝ፣ ይህንኑ ማንም አይከለክለኝም ስለን የነበረው መረን የለቀቀ የአስመሳይነት ባሕርይው ይኸውና ቀኑ ሲደርስ ብቅ አለ። ታዲያም ተስፋዬ የራሱን እንዲህ ዓይነት ጉዱን በጉያው ወትፎ፣ እኛን እያሞኘን እግሌ እውነቱን አልነገረንም፣ እገሌ እንዲህ ዓይነት ሰው ነው እያለ ተዘባብቶብናል። በዚህም እየገባብን መጽሐፎችን እንድንቸበችብ አድርጎናል። ገንዘቡንም ከእኛው ወስዶ፣ እኛን እያቆሰለ ለአባት አገር አድርጎታል። እናም፣ እውነት ትዘገይ እንጂ አትመነምንም የተባለው የአበው ብህል እውን ሆነ።
ተስፋዬ በሬት በተቀለመው ብዕሩ የሌላውን ያለ የሌለን ኃጢአት እያሽጎደጎደ አንዳንዶቻችን ጉድ!፣ ጉድ! እስከሚያሰኘን ቀባጥሮልናል። ግን የጉድ ጉዱን ተሽክሞ የሚዞረው እርሱ ሆኖ መገኘቱ ምናልባትም ለጆሮና ለአእምሮ የሚከብድ ነገር ሳይሆን አይቀርም። እንዲህ ተስፋዬ እንደፈልገው በአፍሪቃ አገሮች ሲንከባለል ኖሮ አሁን በኔዘርላንድ ጥገኝነት ጠይቆ ተቀባይነት አግኝቶአል። የደቡብ አፍሪቃው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ተስፋዬ ሦስተኛ ዜግነት ሊያገኝ ነው ማለት ነው። ከዚህ በተጨማሪ አልተረጋገጠም እንጅ ተስፋዬ በሞዛምቢክ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪቃ ከመሻገሩ በፊት ወደ ዝምባዌ ጎራ ብሎ ለተወሰነ ጊዜ ከቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት፣ ከመንግሥቱ ኃይለማርያም ወንድም ዘንድ ተቀምጦ እንደነበረ፣ አካሄዱና አቀማመጡም መንግሥቱ ኃይለማርያምን ሲሆን ሊያሳፍን፣ ሳይሆነው ገድሎ፣ ወይም አስገድሎ የተሰጠውን ሚሽን ለማጠናቀቅ እንደነበርና በኋላም ተነቅቶበት ሊያዝ ሲል ወደ ደቡብ አፍሪቃ ማምለጡ ተወርቶአል።
ዕቅዶች፣
ከላይ ከተመለከተው ማስታወሻ ጋር በተያያዘ ሌላ አንድ ማስታወሻ እንመለከታለን ዕቅዶች በሚል ርዕስ። ዕቅዶቹ ተስፋዬ ለጌቶቹ እንዲያጽድቁት የሚያቀርበው ይመስላሉ። አምስት እቅዶች፣ አራት ዕቅዶች እያለ መጥቶ ሦስተኛው ላይ የረጋ ይመስላል። እንደሚታዩት መግቢያ ብሎ ስለታማኝነቴና ስለዲስፕሊን በማለት ጀምሮ እቅዶቹን በንድፍ ደረጃ ለማስቀመጥ ሞክሮአል ተስፋዬ በሚቀጥለው ሁኔታ።
  1. አስተማማኝ የኑሮ ሁኔታ ይመቻችልኝ ይልና አገር፣ ሥራና ሚስት፣
  2. ሁለቱ መጽሐፍት ታትመው ይሰራጩ!፤ ያወጣሁት ወጪና ሊገኝ የሚችለው ገቢ፣
  3. አባት መሬት የሚል መጽሐፍ እንዳዛጋጅ የሦስት ዓመት ጊዜ ይሰጠኝ በሚል።
በዚሁ ማስታወሻ ወረድ ይልና ተስፋዬ፣ ከኢሳያስ ተቃዋሚዎች ጋር ብዙ ጊዜ እንገናኝ ነበር። ተግባብተን አናውቅም፣ ለአብነት ብሎ የጠቀሰው ሰው ስም የሚነበብ ሆኖ አልተገኘም። በዚህ ማስታወሻ ላይ በተለይ ልንገነዘበው የምንችለው የተስፋዬ መጽሐፍቱን እየተቆጣጠረ በበላይነት ሽያጩን የሚያካሄዱት ኤርትራዊያን መሆናቸውን ሲሆን በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በተስፋዬ ታማኝነት ላይ የኤርትራ ባለሥልጣናት ጥርጣሬ እንዳላቸው ነው። ለነገሩ ከፍ ሲል ለማመልከት እንደሞከርሁት የተስፋዬ ጉዞ ከገቢ፣ ከጥቅም ጋር በጅጉ የጠበቀ ትስስር ያለው ከመሆኑም በላይ ዋልጌነቱ መረን የለቀቀ ነው። የዚህ የዋልጌንት ድርጊቱን ተፈጥሮ ነው በሚል ማሳሳቻና የመደለያ አነጋገሩ ራሱን እየደለለ ይኮራበታል።
ተስፋዬ እንዲህም ሲል ራሱ ሰው ያለመሆኑን እየካደ እንደሆነ የተረዳው አይመስልም። ሰው ሲወለድ ዋልጌ ሆኖ አይፈጠርም። ወይም ከአግባብ ውጭ የሆነ ባሕርይ ይዞ ከእናቱ ማህጸን አይወጣም። ግና ሰዎች በእድገታቸው የተለያዩ ባሕርዮችን ይዘው ሊወጡ ይችላሉ፤ መልካም ወይም መጥፎ። የሰው ልጅ ከባድ ፍጡር ነው። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ የዚህ ዓለም ገዥ እርሱ ነውና። አለምንም እየለወጠ ያለው እርሱ ነው። እንደየሁናቴ ራሱንም ከጊዜያት ጋር ለመለወጥ ይችላል። እንዲህ ሆኖ ሳለ፣ ተስፋዬ ለዋልጌነቱ መጥፎ በሕርይው ራሱን ሳይሆን፣ ተፈጥሮን ጥፋተኛ ለማድረግ ይሞክራል። መስሎት ነው እንጅ ይህ አካሄድ፣ ያው በለመደው የሽውዳ ምት ጥሎ ሊያልፈን መሞከሩ እንደሆነ ልብ ልንለው ይገባል።
ከዚህ ከተስፋዬ ዕቅድ ልንረዳው የምንችለው ሌላው ቁምነገር፣ ኑሮ በኤርትራ እንዲመቻችለት በአንክሮ እየጠየቀ መገኘቱ ነው። በሚፈልገው ዓይነት ባይሆን፣ በለመደው መልክ ይገለባበጣል። ችግር የለበትም። ሌላው ተስፋዬ እኛን ሽጦን፣ አሻሽጦን ባገኘው የኤርትራዊነት እምነቱ “አባት አገር፣ አባት መሬት” በሚል ርዕሱ ገና ያልተቆረጠለት ከስደተኛው ማስታወሻ ቀጥሎ የሚያወጣው መጽሐፍ እንዳለው አስረግጦ እየነገረን ነው። ከላይ ከተመለከተው ማስታወሻ በተጨማሪ አለማየሁ ካገኛቸው ውስጥ ለአቶ አለም ሰላምታ (ምናልባት ተቆጣጣሪው ሊሆን ይችላል) ብሎ በነደፈው ረቂቅ ላይ እንዲህ በሚል በአምስት ተከፍለው የሰፈሩ ቁም ነገሮችን እናገኛለን።
1. “ለመጀመሪያ ጊዜ ከሻቢያ ጋር በመገናኘት ኤርትራ ለተባለች ሃገሬ ቀጥተኛ አገልግሎት ለመስጠት የወስንኩት የ29 ዓመት ጎረምሳ ሳለሁ ነበር። አሁን 41 ዓመቴ ነው። ኤርትራዊነት ይሰማኝ  3የነበረው ግን ገና ሕጻን ሳለሁ ጀምሮ ነበር። የሻቢያ ታጋይ ብሆን ምኞቴ ነበር። በታሪክ አጋጣሚ አልሆነም። ዘግይቼም ቢሆን ሃገሬን ማገልገል በመቻሌ ግን እኮራበታለሁ። በአንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። እኔ ከኤርትራ ፕሬዚዳንት እኩል ኤርትራን አፈቅራታለሁ። ይህ የእምነቴ እና መድረሻ ነው። ብዙ የባሕርይ ችግር ቢኖርብኝም እዚህ ላይ አልታማም። በኤርትራና በኤርትራዊነት ጉዳይ ላይ ፅኑና እልኸኛ ነኝ።”
2. “ባለፉት ዓመታት አብረን ስንሰራ የኔን ደካማና ጠንካራ ጎን አውቃችሁታል። መያዥያ መጨበጫ የለውም ብላችሁ እንደምታስቡኝ እገምታለሁ። አያያዛችሁም ደግሞ ጠባዩ መጥፎ ቢሆንም አንዳንድ ጥሩ ሥራዎች ስለሚሰራ መታገስ ይሻላል ብላችሁ እንደምታሰሩኝም እገምታለሁ። የሆነው ሁኖ ጥሩ ጠባይ እንዲኖረኝ እኔም እፈልግ ነበር። አልቻልኩም። ይኸ የተፈጥሮዬ እንጂ የኔ ጥፋት አይደለም። የተፈጥሮ ስል፣ ስነጽሑፋዊ ሰውነቴን ማለቴ ነው።”
3. “በፖለቲካ አመለካከት ደረጃ እኔ ፀረ-ወያኔ አቋም የያዝኩት ወያኔ ፀረ-ኤርትራዊያን ወይም ፀረ-ሻቢያ አቋም በመያዙ ብቻ ነው። ከወያኔ ጋር ሌላ ፀብና ችግር የለብኝም። ወያኔ እኔን በግል የበደለኝ ነገር የለም። የኤርትራን ሕዝብና በትግሉ ወቅት ለዚህ ያበቃው አጋር ላይ የትግል ግን ክህደት ፈጽሟል። እኔ ግለሰብ ነኝ። በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ግን ወያኔ ለዚህ ክህደቱ ዋጋውን ማግኘት እንዳለበት አምናለሁ። ለዚሁ እታገላለሁ። ሕይወቴን ለመክፈልም ዝግጁ ነኝ። እንደግለሰብም የወያኔን ቡድን እየተበቀልሁት ነው። እስከእለተሞቴ ደሞ እበቀለዋለሁ። ይህ ሥራ የኤርትራ ሕዝብ የሚጠቅም ሥራ መሆኑን በማመን ነው በፍላጎት ስሰራ የቆየሁት።”
4. “ላለፉት 10 (16 ካለ በኋላ ነው ሰርዞ ወደ ሃሰቱ የገባው) አመታት ለሻቢያ መረጃና ጥቆማ በመስጠት ሰርቻለሁ። ከሰጠሁት ጥቆማ በላይ ግን እነዚያን ጥቆማዎች ለመስጠት በተደረገ እንቅስቃሴም ሁለት መጽሐፍት (የጋዜጠኛው ማስታወሻ እና የደራሲው ማስታወሻ ለመጻፍ ችያለሁ። እነዚህ ሁለት መጽሐፍት ያስገኙት ፖለቲካዊ ፋይዳ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ለመገንዘብ በአንድ ባለሙያ ማስጠናት ብቻ በቂ ነው። ወያኔ እነዚህ መጽሐፍት እንዳይሰራጩ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው። በቀጣዩ የሚጻፈውን መጽሐፍ ይዘት ለማወቅ ሰላዮቹን አስማርቶአል። ስለዚህ ጉዳይ ሰፊና ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።
5. “ያለፈውን ገድል በማንሳት ጉራ መንዛት ብቻውን ዋጋ የለውም። ወደሚቀጥለው ተግባር መሸጋገር ያስፈልጋል።” ምንም እንኳ ጡት ነካሾችዋ ቢበዙባት፣ ምንም እንኳ አስመሳዮች ቢያሴሩባት ምን ጊዜም ቢሆን አምላክ እምዬን ይጠብቃታል። ተስፋዬ ከኛው ለቃቅሞ፣ ለኛው አስመስሎ የሚያዘጋጅልንን መጽሐፍት እኛው እየገዛን የርሱንና አገሬ ነው የሚላትን የኤርትራን ኤኮኖሚ እንገነባለን። ዛሬ በወያኔ ያሳብብ እንጂ ተስፋዬ ከሕፃንነቱ ጀምሮ ልቡ አባት አገር ከሚለው ከኤርትራ ጋር እንደሆነ በትክክል ገልጾ እያየነው ነው። ደሞም እዚችው በዚችው ይዋሸናል ተስፋዬ። ለኤርትራ አገሬ ማገልገል የጀመርሁት በ29 ዓመቴ ነው በሚል። ከተባረረ በኋላ ለማለት። ነገር ግን ከፍ ብሎ እንደገለጽሁትና ማስረጃዎችንም እንዳያችሁት ራሱ የቡርቃ ዝምታ እስከ ሦስት ጊዜ የታተመ ሲሆን፣ የመጀመሪያው 1992፣ ሶስተኛው በ2001 ታትሞ የተሸጠው በኤርትራዊያን መሆኑ አባባሉን ውድቅ ያደርገዋል። አስገራሚው ነገር ደግሞ፣ ይህን መጽሐፍ ስደት ከወጣም በኋላ አሳትሞ መሸጡ ነው። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ለኛ ምስጢር ሊሆነን የሚገባ አይመስለኝም። ሌላ አንኳር ቁም ነገርም እናያለን ከዚህ ከተስፋዬ ማስታወሻ። የርሱ ግጭት ከወያኔ ጋር ብቻ መሆኑን፣ ያውም ወያኔ ኤርትራን ስለተቃረነ፣ በተቀረ ግን ኢትዮጵያ ለምትባል አገር፣ ለኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ ምንም ዓይነት ደንታ የሌለው መሆኑን ነው።
“Nov. 10, 2010 ተመልክቶ አንዳንድ ነጥቦች” ተብሎ ለአቶ አለም ሰላምታ ተብላ የተነደፈች፣ “የጋዜጠኛው ማስታወሻ ወደ ትግሪኛ እየተተረጎመ እንደነበር ከ7 ወራት በፊት ገልጬ ነበር። ተርጓሚዎችሁ አሉላ ፍሰሃየ (መከላከያ የሚሰራ ታጋይ)፣ ወዲአዲ (ህግድፍ የሚሰራ) ነበሩ። ሥራውን ጨርሰው ከማስታወቂያ ሚኒስቴር (እንደዜና) ፈቃድ አግኝተው ማተሚያ ቤት አስገብተውታል። ከመጽሐፉ ትርጉም በስተጀርባ የፕሮፌሰር አስመሮም፣ ሳንዲያጎ እና አምባሳደር ጣሂር ባዱሪ አስተያየት ሰጥተውበታል። ገቢው ለተርጓሚዎቹ ሲሆን፣ አሳታሚው አክሊሉ ነው። ህዳር 25 ህትመቱ እንደሚያልቅ ነግረውኛል።” ትላለች ባጭሩ። ተስፋዬ ከኛው አፍ ለቅሞ፣ ፖለቲካ ሰርቶበት፣ ለኛው በማር ለውሶ አቅርቦልን ባገኘው ገንዘብ እየተመጻደቀ ይገኛል።
እስቲ ይህ መጽሐፍ ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ማበብ ያግዛል ብሎ ተስፋዬ ጽፎት ከሆነ ወደ ትግሪኛ መተርጎሙ ለምን አስፈለገ? መቼም ለብልህ አይነግሩም፤ ለአንበሳ አይመትሩም ይባላልና እንመርምር። ብልህ እንሁን።
የመጽሐፍት ሽያጭ፣
ከቡርቃ ዝምታ ጀምሮ እስከ የደራሲው ማስታወሻ ድረስ የተሸጡት በኤርትራ የበላይ ተቆጣጣሪ ሃላፊዎች አማካይነት በየውጭ አገራት ባሏቸው ወኪሎቻቸው ተከፋፍለው እንደሆነ ከአለማየሁ እጅ ከተገኙት ሰነዶች ለመረዳት ይቻላል።
ለዚህም ጠቋሚ የሚሆነን፣ በአንድ ሰነድ ላይ በየክፍለ ዓለማቱና በየአገሩ መጽሐፍቱን እንዲሸጡ ሃላፊነት የወሰዱ ሰዎችን ስም ዝርዝር እንመለከታለን። መጽሐፍቱ የተከፋፈለበት አገር የሚያሳየው ቢን ካርድ (BIN CARD) ፎርም ወይም ሰንጠረዥ በትግርኛና በእንግለዘኛ ተጽፎ ይገኛል። መግለጺ (Description) ተብሎ በተመለከተው ሰንጠረዥ ሥር የቡርቃ ዝምታና የጋዜጠኛው ማስታወሻ መጽሐፎች ለሽያጭ የተላኩበት አገሮችን ዝርዝር እናገኛለን።
ለማስረጃም ይሆን ዘንድ ከዚህ ቀጥሎ ተያይዞ ይገኛል።
የተሸጡበት አገር፣ የሻጮችን ስም፣ እና ብዛቱን ዝርዝር የሚያሳየው፣ ከዚህ በላይ በሻጭነት የተመለከቱትን ምናልባትም በየአገራቱ ከምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ቢያንስ አንዳችሁ አንዱን ታውቁ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ። እናም፣ ከእንግዲህ ልብ ልንል ይገባል። ባለማወቃችን፣ ባለማስተዋላችን ተታልለናል። ካወቅን በኋላ ደግሞ እንነቃለን። በቃህ! ወደዚያ! እንላለን። ኢትዮጵያዊነት ኩራት መሆኑን እንነግራቸዋለን ማለት ነው።
በስልክ ሃሳቤን የመግለጽ ችግር፣ ተስፋዬ በለመደው ቋንቋ፣ በለመደው መሰሪ አነሳሱ ሊያቀርብልን የተዘጋጀው “የስደተኛው ማስታወሻ” የሚባል መጽሐፍ ነው። ይህንኑ በተመለከተ ከነደፋቸው ማስታወሻዎች መካክል፣ “በተፈጥሮ እንደዚህ በስልክ ሃሳቤን መግለጽ ችግር አለብኝ። ለማንኛውም ትናንት በስልክ ያደረግነው ውይይት ላይ የተሰማኝን ተጨማሪ አስተያየት በዚህ ልኬልሃለሁ።” በማለት ምናልባትም አለም ለተባለው የጻፈው ይገኝበታል። በዚህ ማስታወሻ ውስጥ፣ “ከይመር ጋር ሥራው እንደሚቀጥል ነግረኸኝ ነበር። ይመር ግን ከአበበ ጋር ባደረገው የስልክ ውይይት ተፈላጊነቱ እንዳበቃ መረዳቱን በተዘዋዋሪ ነግሮኛል። ቃል በቃል እንደዚያ አላለኝም። ሆኖም ንግግራችን እንደቀድሞው አይደለም። የማስፈልጋችሁ አልመሰለኝም ብሏል። የማያስፈልገን ከሆነ ቅሬታ ሳያድርበት ብንለያየው ደስ ይለኛል።” ብሎ ይቀጥላል።
“እኔን በተመለከተ እዚህ ሆኜ የደራሲው ማስታወሻን ገቢ ለኑሮዬ እንድጠቀም ነግሮኛል። እስካሁን የሰጡኝ 10ሺህ ዩሮ ነው። ይህንን ደግሞ ባለፉት አራት ወራት እየተጠቀምኩበት ቆይቼ አሁን ወደ ማለቁ ነው። መቼም ትዳር መስርቼ ልጅ ወልጃለሁ። ሃላፊነት ይሰማኛል። ብዙ መጠየቄ ሳይሆን፣ ኤርትራ ውስጥ ሰዎች ቤት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። እኔም ገጠር ውስጥም ቢሆን ቤት ቢኖረኝ ብመኝ ኃጢአት አይደለም። ደግሞስ እናንተ በጀት ካልመደባችሁ እኔ እዚህ ምን አደርጋለሁ። እዚህ የመጣሁት ለሃገሬ ልሰራ እንጂ እኔ ሆላንዳዊነትን ፈልጌ አይደለም። በጀት ካልመደባችሁ ሥራ የለኝም ማለት ነው።” ይቀጥላል።
“በሽያጭ ደረጃ “የጋዜጠኛው ማስታወሻ” ያልተሸጠ ከ2000 በላይ expo መጋዘን አለ።…..ለካርጎ የተከፈለውም ተጨምሮ፣ ሌላም ወጪ ካለ ተጨምሮ ዕዳዬ ታውቆ በየቦታው ያለው ተሰብስቦ ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ ነኝ። ዕዳ ይሰረዝልኝ አልልም። የፖለቲካው ግብና ጥቅም ለኔም ለግሌ አላማዬ ስለሆነ ልከስርበትም ዝግጁ ነኝ። ….. ይህን ለማድረግ እዚያ አስመራ መምጣቴ ጠቃሚ ነው።” በሚል ያሰፈረውን እናገኛለን።
ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነኝ እያለ የሚፎክረው ሰው ውስጡ ሲገለጥ እንዲህ ሆኖ እናገኛዋለን። ትዳርና ልጅ እንደሌለውና ዋልጌነቱን የሚደሰኩርልን ተስፋዬ ሲገለጥ እንዲህ ዓይነት ሰው ሆኖ እናገኘዋለን። መቼም ከገሙ ላይቀር ብሽቅጥ ነውና ተስፋዬ አልገኝም በሚል አባዜ ተወጥሮ ለእንዲህ ደረሰ። የነገውን ማን ያውቃል? ጊዜ ደግ ነው። ሁሉን እንደመስታዋት ቁልጭ አድርጎ ያሳያልና።
“እኔ ልኑር እንጅ እንደየጊዜያቱ፣
ሰው ያየውን ሳላይ አልቀርም በጊዚያቱ”
ብሎ ታምራት በዚያን ጊዜ ያዜማት መዚቃ የግጥም ስንኝ ሁሌ አንድ ደረጃ ላይ ስደርስ ትዝ ትለኛለች። ዕድሜ የሰጠውና የቆየ ሰው በደረሰበት ዕድሜ የሚያጋጥመውን ክፉውንም ሆነ ደጉን ያያል ማለት ነው። እስቲ ደሞም አለፍ እንበል።
ደደብ? እናያለና!
ይህ ምዕራፍ ሁለት ብሎ ጀምሮ “እሪ በል አንበሳ፣ እሪ በል ከርከሮ” ብሎ የሚጀምረው የተስፋዬ ማስታወሻ ቀጥሎ ያለውን ቁም ነገር ይነግረናል።
“ወሬው አዲስ አበባን እንደአደይ አበባ አልብሶት ማደሩን የተረዳሁት ገና በማለዳው ነበር። ወደ ቢሮዬ ከመግባቴ በፊት ፒያሳ ቲ-ሩም ማኪያቶ የማጣጣም ልማድ ነበረኝ። ዛሬ ቲ-ሩም በወሬ ተቃጥላ ነበር የደረስኩት። ኤርትራና ሻቢያ በግላጭ ይከተፋሉ፣ ይታኘካሉ፣ ይደቆሳሉ፣ ይዘለዘላሉ። በአብዘኛው ገጽታ ላይ ጭንቀት አሊያም መከፋት አይታይም። ይልቁንም ደማምቀዋል። ወሬው ከወፍራም ቡና ጋር ይጠጣል። . . . በሰዎች ገጽታ ላይ ስላነበብሁት ደስታ እያሰላሰልሁ ቢሮዬ ገባሁ። የአሳታሚ ድርጅቱ የጠቅላላ አገልግሎት  ሃላፊ፣ “መግለጫውን ሰማህ?” በሚል ጥያቄ ተቀበለኝ። ሰማሁ። አሳዛኝ ነው። ሕዝቡ ግን ይገርማል ሲል ቀጠለ።”
“. . .ጨፍጋጋ ግማሽ ቅዳሜ አሳልፍኩ። ሥራ የመሥራት ፍላጎቴ ስለተበላሸ በግድየለሽነት ጋዜጦችን ማገላበጥ ጀመርኩ። እያንዳንዷ ደቂቃ አዲስ ነገር እየወለደች እንደምትሄድ እየተሰማኝ ነበር . . .።” በማለት ከህወሀት ማዕከላዊ ኮሚቴ አንዱ የሆነው አብርሃ ማንጁስ ደውሎለት ከዛሬ ጀምሮ ተስፋዬ በሚያዘጋጀው ጋዜጣና መጽሔት ላይ ኤርትራን አስመልክቶ የሚጻፈው ሁሉ በቅድሚያ ወደርሱ ተልኮ ብቻ ለሕትመት ሊበቃ እንደሚችል እንደነገረው ይተርካል። ቀጥሎም በኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር ዕድሉ እንዳበቃበትም ተንብዮአል። ሥራውን ያውቃልና። ይህ ርዕስና በውስጡ ተስፋዬ የቀባጠረው በስደተኛው ማስታወሻ ላይ ይሁን አባት አገር ብሎ ለመጻፍ ባቀደው መጽሐፍ ሊያካትት ያሰበው አልታወቀም። ግና ከማስታወሻው በአንኳራነት የወስድኳቸው እንዲህ ይመስላሉ። የተባለው መግለጫ ምናልባትም 1991 የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት እወጃ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ። ተስፋዬ ጦርነቱ ከተጀመረ የኢትዮጵያ ወታደር ኤርትራን እንደሚደመስስ የገመተ ይመስላል። እናም በእጅጉ ተስፋዬ ድንጋጤ ውስጥ የወደቀበትና ተስፋም የቆረጠበት ሁኔታን የሚያሳይ ኑዛዜ በአንድ በኩል ሲመስል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሆድ ያባውን ብቅል . . .እንዲሉ አፍኖ ውስጥ ውስጡን ሲሰረስር የነበረው ግንድ በራሱ ላይ ሊወድቅበት ሲቃረብ የተፋው ማስታወሻ ነው።
አንዳንድ የማብራሪያ ነጥቦች፣
አንዳንንድ የማብራሪያ ነጥቦች ይላል የሚቀጥለው የተስፋዬ ማስታወሻ። በዚህ ላይ ተስፋዬ ለመጠቃቀስ ከሞከራቸው ውስጥ በዋነኛነት፣ “ኤውሮፓ ላይ ሥራ የምሰራ ከሆነ፣ በእግረመንገዴም የጽሑፍ ሥራ እየሰራሁ የተሳካ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል አምኜ እንደነበር አይዘነጋም። እዚህ ከመጣሁ በኋላ ግን ሥራውን በሚፈለገው ደረጃ መሥራት የሚቻል አለመሆኑን ቀደም ባለው ደብዳቤዬ ገልጫለሁ። በናንተም በኩል ቀደም ሲል ይደረግልኝ የነበረው ወርሃዊ ክፍያ የተቋረጠውም በዚሁ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ገምቻለሁ። . . . በሌሎች ሰዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ በደባልነት በመኖር ይህን ዓይነት ሥራ መሥራት እንደማይቻልም ተረዳሁ። ስልክ መደወል አለ። የምጽፈው አለ። ይህን ሁሉ በምስጢር ለመያዝ የሚደረገው ጥረት ከሥራው ባሕርይ ጋር ሊሄድ አልቻለም። ስለዚህ ሥራው ባይኖር እንኳ እኔ በስደተኛ ደርጃ ለመኖር እንደማልፈልግ ተረዳሁት። . . . ሻዕቢያና ኤርትራ ላይ ጥርጣሬ ካላቸው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደባል ቤት ተከራይቼ ይህን ሥራ ልሰራ ግን አልችልም።” የሚሉ ይገኙበታል። ተስፋዬን የኢትዮጵያ አምላክና እውነት ከዚሁ ከሳይበሩም ያስበረገጉት ይዘውታል። የጠረጠረውም አልቀረለትም። እዋዛ ሰው ጋ አልተጠጋም። እናም ተሰርቶለታል። የዚህ ሙሉው ከበስተጀርባው ተያይዞአልና ማየት ይቻላል።
የመንገዴ አበቦች፣
“ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ልክ ነበሩ። ማስተባባል አይቻልም። በርግጥ በደራሲው ማስታወሻ ላይ ከበረሃ ወደ በረሃ በሚለው ምዕራፍ ላይ የራሴን ደካማ ጎን ቢያደበዝዝልኝ በሚል የሌሎችን ኋጢአት አዝርክርኬው ነበር። መጽሐፉ ከታተመ በኋላ አንባቢያን አልወደዱልኝም። የጻፍኩት እውነት ቢሆንም፣ ያን በመጻፌ ተጸጽቻለሁ። አስፈላጊ አልነበረም። ሰከን ብዬ ካስብኩበት በኋላ ደግሞ ዶክተር ነጋሶ ስለኔ የሰጡት አስተያየት እውነት መሆኑ ይበልጥ እየተሰማኝ መጣ። በአጭሩ ነጋሶ ጊዳዳ እንደገለጹት የሴት አያያዜ ልክ አልነበረም። ስልቹ ነኝ።” በማለት በዚሁ በዋልጌነቱ እስከ ዕለተ-ሞቱ እንደሚቀጥል ይነግረናል።
ተስፋዬ አስተዋይነት የሚጎድለው መሆኑን መንገሩ ብቻ ሳይሆን፣ በዚህ ሰይጣናዊ ባሕርይው የስንቱን ቤት እንዳፈረሰ፣ ለፖለቲካ ግቡ ሲል የስንቱን ስም ጠላሸት እንደቀባ፣ ድርጅትንም እንዳፈረሰ፣ የስንቱን እንስቶችን ሕይወት እንዳበላሸም ጭምር ነው ሳያውቀው እየወረወረልን ያለው። ይህ እንግዲህ ከአጻጻፉ መረዳት እንደሚቻለው፣ በስደተኛው ማስታወሻ ላይ የስደተኛውን ልብ ለመብላት፣ የመጻፉ እውነተኛ ገጽታ ለመሽፈን የሚያደርገው ጥረት አንዱ ክፍል መሆኑ ነው። የብልጠቱ አካል ነው። አሁንም አንነቃ ይሆን? እንቀጥል።
የስደተኛው ማስታወሻ ማውጫ በሚል፣
1. የተነቀሉ ዛፎች፣ 2. የቤተልሔም ልጆች፣
3. ቢንያም ቦረና፣ 4. አባሻውል አመሸሁ፣
5. የሌንጮ ራዕይ፣ 6. የሰለሙና ሌሊት፣
7. የሕይወት ቁስለኞች፣ 8. የጁገል ወጎች፣
9. የሻምቡ ንጉስ፣ 10. በነጻነት በዓል ዋዜማ፣
11. የተባላሹ ዜጎች፣ 12. የመዓዛ ደስታ፣
13. የግጥም ምሽት፣ 14. የስለላ ሥራ፣
15. በኤውሮፓ ሁዳዴ ላይ፣ 16. የተንሴኦ ፕሮፓጋንዳ፣
17. የሳጥናኤል ጉዳይ፣ 18. የሀብታም ልጅ በኤርትራ፣
19. ታሪክና ትረካ፣ 20. በጨለመ ጉም ውስጥ፣
21. ረጃጅም ሌሊቶች፣ 22. የስደተኛው ፀሎት፣
ተጨማሪ በሚል ደግሞ፣
1. በጎ ቃላት፣ 2. አዳምና ሔዋን (እኔና አባቴ)
3. ጉዞ ወደ ሞት (ይህን የተረኩሉኝ ሞት የተፋቸው ናቸው)፣ 4. የወደብ ጉዳይ (ልጅ ተክሌ)
5. የመገንጠል ጥያቄ፣ 6. ከሽማግሌዎች ቤት (በጣም አስቀያሚ ትዝታ ያሳለፍኩት እዚህ ግቢ ነው)፣ ዘርዝሮታል።
በማውጫው ዝርዝር እንደሚታየው ቢንያም ቦረና፣ የሌንጮ ራእይ፣ የሻምቡ ንግሥ፣ የነጻነት በዓል ዋዜማ፣ የስለላ ሥራ፣ የመገንጠል ጥያቄ በተባሉት ክፍሎች ሥራ ተስፋዬ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚረጨው መርዝ በጣም የከበደና ጥበባዊ እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት ይቻላል። በተለይም ቢንያምም ቦረና፣ የሌንጮ ራእይ እና የሻምቦ ንጉሥ የተባሉት ርዕሶች ተስፋዬ ያው እንደለመደው የአማራንና የኦሮሞን ማህበረሰቦችን የማከፋፈል አጀንዳውን በሚገባ እንደሚስል ይጠበቃል።
የስደተኛው ማስታወሻ ፋይዳ፣
የስደተኛው ማስታወሻ ሆላንድ ሆኜ መሥራት አልቻልኩም። በጣም ሞከርኩ ግን አልሆነም። መሥራት ካለብኝ ኤርትራ መመለስ አለብኝ።ኤርትራ ከተመለስኩ ያገኘሁት የሆላንድ ዜግነት ሊቋረጥ ይችላል። ምክንያቱም በስደተኛ ሕግ መሠረት ከሆላንድ ውጭ መቆየት የሚፈቀድልኝ 3ወራት ብቻ ነው። ጥቅምና ጉዳቱን ስመዝነው ግን ሆላንድ ላይ ያገኘሁት ዜግነት ተሰርዞ ወደ ኤርትራ ብመለስ የስደተኛው ማስታወሻ የተባለውንመጽሐፍ ጽፌ መጨረስ የተሻለ ነው። ምክንያቱም “የስደተኛው ማስታወሻ” ፖለቲካዊ ፋይዳው የላቀ ነው። ይህን አሳብ ያቀረብሁት በርካታጥቅምና ጉዳቶችን ግራና ቀኝ ተመልክቼ ነው።
እንግዲህ ተስፋዬ አለቆቹን የሚማጸነው ለምን እንደሆነ መገመት ይቻላል። ተስፋዬ ከቡርቃ ዝምታ ጀምሮ የወላዲቷን የእምዬ አገራችንን ሕዝቦች አለያይቶ የማፈራረስ እቅዱንና ዘዴውን እየለዋወጠ ቢሄድም፣ በዚያው መጠን ኢትዮጵያዊያንም እየነቁበት መምጣታቸውን እያነበበ መጥቶአል። በተለይም በዚህ መጽሐፍ እስከዛሬ ሊደብቅ የሞከራቸውን አንዳንድ እውነታዎችን ፈረጥረጥ ለማድረግ እየሞከረ ነው። አባሻውል አመሸሁና ሀብታም ልጅ በኤርትራ የተሰኙት ግልጽ የሆኑ መሪ ደጋፊ ምሳሌዎች ናቸው። ስንቀጥል ደግሞ የባሰ እናገኛለን።
የስደተኛው ማስታወሻ ተገባድዶአል፣
“አምስተርዳም የተባለችው ኤውሮፓዊት ከተማ ላይ ለኔዘላንድስ መንግሥት እጄን ሰጠሁ። . . .ለፖሊስ እጅ የሚሰጥበትን ሊያሳየኝ አብሮኝ የመጣው ሰው ሄኖክ ይባላል (የአለማየሁ የቤት ስሙ ነው ሄኖክ እንደነገረኝ)። ከቅንጅት ትንታጎች አንዱ የነበረ የፈረንሳይ ለጋሶን ልጅ ነው። የስደተኛው ማስታወሻ ተገባድዶአል። ርዕሰ-ጉዳዩ ሰፊ ቢሆንም እንኳ፣ በስደት ሕይወትና ፖለቲካ ላይ ተወስኜ መጻፉን መርጫለሁ። መጽሐፉን የተሟላ ለማድረግ ኤውሮፓና ሰሜን አሜሪካን ጎብኝቼ የአበሾችን ሕይወት መመርመርና አስፈላጊ የታሪክና የፖለቲካ ሰዎችንም ማግኘቱን በእቅድ ይዤ ከፊሉን ያህል ፈጽሜአለሁ። የስዊድን፣ የጀርመን፣ የሆላንድና የቤልጅየምን ጓዳ በመጠኑም ቢሆን ለማየት ሞክሬአለሁ። በቅርቡ ወደ ራሽያ የምሄድ ሲሆን፣ የማክሲም ጎርኪይ አያት ይመላለሱበት የነበረውን የቮልጋ ወንዝ ዳርቻ ለማየት እንዴት እንደጓጓሁ ልነግራችሁ አልችልም። በስዊድን ቆይታዬ ጽጌረዳ እቤቷ የጋበዘችኝ ሲሆን፣ ከባሏም በመግባባት በመቻላችን በጣም ደስ ብሎኛል። ሆላንድ ኡትል በተባለች ከተማ ከሌንጮ ለታ ጋር ተግናኝቻለሁ። ወደ ኖርዌይ ሄጀ ሌንጮን ለማናገር ዳግም ቀጠሮ ይዤአለሁ። ፓሪስ፣ ለንደን እና ዋሽንግተን ዲሲን እጎበኛለሁ።” ይላል ተስፋዬ በዚህ ሰነዱ።
ተስፍሽ አመች ከሆኖለት የኤውሮፓ አገሮች ስዊድን፣ ጀርመን፣ ከሚኖርበት ሆላንድና ቤልጅየም፣ አመች ሰዎችን በማገኘት እንዳለው የሚፈልገውን ቦርቡሮአል። ለነገሩ ሆላንድ ችግር ያለበት አይመስለኝም። ጋዜጠኛ ክንፉን እንደማይነቃነቅ ግምብ አድርጎ ይዞታል። እናም ክንፉም በጣሙን ተመችቶታል። ሌንጮም በቀላሉ በእጁ ወድቆለታል። የአማራውን ማህበረሰብ ከኦሮሞው ጋር ማጋጨቱንና ኢትዮጵያ ተበታትና እንድትጠፋ ለጀመረው፣ እና ለቀጠለበት ሩጫ ምናልባትም ከሌንጮ አንዳች መጠምዘዥያ አግኝቶ ሊሆን ይችላል። ከዘረዘራቸው አገሮችንም እንደዚሁ ስሜተኞችን የሚያጣ አይመስለኝም። በአስመሳይ መፈክሩ፣ “የቢሾፍቱ ልጅ ነኝ” በሚል። እንዲያውም ስዊድን ውስጥ ጽጌረዳ ባለትዳሯን አግኝቷታል። ከባሏ አስተዋውቃው ወደ መግባባት እንደደረሱ ይነግረናል። እርሱ መቼም በሁለት ቢላዋ መብላትን ተክኖታልና ያደረገውን እርሱ ነው የሚያውቀው። በተጨማሪም ከነርሱ አንዳች ነግሩኝን አሽትቶ ይሆናል። እናም በመጽሐፉ ቀባብቶ ያስቀምጠዋል። በዝርዝሩ መግለጫ ላይ ትንታጉ የሚለው ልጅ ግን ጉድ እንደሰራው ተስፋዬ አላወቀም። በብልጥ ላይ ብልጥም እንዳለ አልተገነዘብም። የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ ይባል የለ? እናም ሁሉን ማየት መታደል ነው። እንቀጥል።
ሌላው ይላል የቀይ ወጎች (Inside the Dark Fog)
“ጉሙ ተራራውን ሽፍኖታል። አምስት ነን። አማኑኤል፣ እኔ፣ ቢንያም ብርሃኔ (ደቡብ አፍሪቃ) ለምለምና ሚለኑ ተቀላቅለው (አንድ ሴት) ይፈጥራሉ። አንዲት ስዊድናዊት ነጭ አብራን አለች። የእብዶችና የፖለቲካ ክስተቶች በትረካዎቹ ውስጥ ይገባሉ። ከድንበር ማካለል ጋር የተያያዘ፣ አገልግሎትና የኑሮ ውድነት ጋርም የተያያዙ ቀልዶች በወጎች መሃል ይካተታሉ። . . . የቢንያም ታሪክ በደንብ ይተረካል። የባከኑ አበሾች በሌላ ርዕስ የምተርክበት መጽሐፍ ነው የሚሆነው። . . . አስመራ ስለገጠመኝ ከሴቶች ጋር የተያያዘ ሁላችም እንተርካለን። . . .ስለኤርትራ ተራሮችና መልክዓ ምድር በሰፊውና ያለማቋረጥ ይገለጽ። የኤርትራ ቱሪዝም አርማ፣ የትምህርት ፖሊሲ ላይ ጭቅጭቅ፣ የኤርትራ መንግሥት ርዮተዓለም ምንድነው? የሚለው ላይ ጭቅጭቅ።” የተሰኙት ይገኙባቸዋል።
ከፍ ሲል እንደገለጽሁት ተስፋዬ በዚህች ማስታወሻ ላይ ያሳየን በግልጽ ወደ እውነታ እየገባ መምጣቱን ነው። አያችሁ ወገኖቼ የአካሄዱ ዘዴ? አሪፍ የኳስ ተጨዋቾች፣ የእግር ማለቴ ነው፣ ወደ ግራ አሳይተው ወደ ቀኝ ኳሷን ያሳልፏታል። አብዶ ሠራ፣ ወይም አታለለ ይባልለታል። ይደነቃልም። ሽወዳ በሚሉት የኳስ አጨዋወት ስልት። ተስፋዬም እንግዲህ የኢትዮጵያ ልጆችን እንደለመደው ሊሸዋውደን ግማሽ መንገድ ተጉዞአል። በግላጭ የሚጽፈው የኤርትራን ታሪክ ነው። የ ኤርትራን ውበት ነው። የአባት መሬት የሚላትን አገር ተራሮቿን፣ ወንዞቿን ለቱርዝም መሳቢያ ዓይነት። በእንዲህም አጋጭቶ ከሁለቱ፣ ከኤርትራዊያንና ከኢትዮጵያዊያን ዳጎስ ያለ ገንዘብ መሰብሰብ ዕቅድ።
የኤርትራ ንቀት መቀነስ፣ አማራን መናቅ
(የህወሃት የረጅም ጊዜ ግብ)
በዚህ ርዕሰ ማስታወሻ ሥር የሚከተሉትን አንኳር የተስፋዬ ንድፍ እናገኛለን። ተስፋዬ ገብረአብ በሆላንድ የስደተኛ ካምፕ ሕይወት ማየት ችሎአል። በቴራፕልና ኺልዚ በተባሉት ካምፖች የነበረውን ቆይታ ራሱን በቻለ ምዕራፍ እንደሚተርከው ገልጾአል ይልና በሕይወት መንገድ ላይ የማገኛቸው ሰዎች ሁሉ የመጽሐፌ አካል መሆናቸው የማይቀር ነው የሚል ገጽ አንድ ላይ ያሳያል። ገጽ ሁለት ላይ 1. መለስና ብርሃኑ (ሳቅ)፣ የወደብ ጉዳይ ብሎ ወረድ ይልና የወደብን ጉዳይ ወደ ታሪክ ከሄድን ዳረሰላምና ጅቡቲ የኢትዮጵያ አካል መሆናቸውን ማሳመን ይቻላል። ወደ ክርክር ከገባን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ከተባለ በኋላ ተሰርዞ አስተዳደር ነበር ተብሎአል። ይቀጥልና ኦስትሪያ ወደብ ይገባት እንደነበር አሁንም ታምናለች። በተሰረዘ ጽሑፍ ውስጥ የወደብ አልባ አገራት ስብሰባ ላይ ኦስትሪያ ወያኔን ለማነሳሳት ለመሞከሯ መረጃ አለ ተብሎ ታልፎአል። እናም ይላል ተስፋዬ በሕግ የሚሞከር ነገር የለውም። የተዘጋ ነው። ስዬ አብርሃ ወያኔን ለመጣል ሰላማዊ ትግልን ይመርጣል። አስብን ለማስመለስ ግን የሃይል ርምጃ ይመርጣል ካለ በኋላ የሃይል ርምጃ መጨረሻ ሊኖረው አይችልም ብሎ ያጠቃልላል።
ከዚህ ማስታወሻ የምናገኘው ነገር ይበልጥ ተስፋዬ ማንነቱን እያጎላ መሄዱን፣ ለየት ባለመልኩ ግን የሥዬ ነገር ሁልጊዜ እንደሚያስጨንቀው እንመለከታለን። ለምን? ስዬ ሥልጣን አከባቢ ከመጣ፣ ሥልጣን በሆነ ነገር ቢይዝ አሰብን ለማስመለስ ጦርነት መክፈቱ አይቀርም ይሚል ስጋት ስላለው ይመስላል። ይህንኑ በመጽሐፉ ላይ ከኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ጋር በተያያዘ በገለጸው ላይ ስዬን በሚመለከት ብዙ ብሎበታልም። ስዬ የጉሮሮ ላይ አጥንት ሆኖበታል ማለት ነው።
ኢትዮጵያ የተባለችው ሃገር በመፈራረስ መንገድ እየተጓዘች መሆኑን ማሰብ ያለመቻል መታወር ብቻ ነው
“የኃይለገብረሥላሴ ታላቅ ወንድም ኡትሬክት የተባለች ከተማ ላይ ምሳ አዘጋጅቶ ተግኝቼ ነበር። ባለቤቱ እንዲህ ስትል ጠየቀችኝ። ትግሬዎች (ኤርትራና ትግራይን ማለቷ ነው) እኛን ለምንድነው የሚጠሉን? ለምንድነው ልባቸው በጥላቻ የተሞላው? መልሼ እንዲህ ስል ጠየኳት። ለምን ይመስልሻል? በተፈጥሮ ክፉዎች ስለሆኑ ይመስለኛል። ይህን ከመስማቴ  አምስት ቀን በፊት መለስ ወደ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ሲሄድ ትግሬና ሌላው በሚል የዘር ልዩነት ድጋፍና ተቃውሞ ተመልክቼ ነበር። ኢትዮጵያ የተባለች ሃገር በመፈራረስ መንገድ ላይ እየተጓዘች መሆኑን ማሰብ አለመቻል የአእምሮ መታወር ብቻ ነው። ትግሬ በድፍኑ ክፉ ነው ብሎ የሚያስቡ ሰዎች መኖራቸውን አውቃለሁ። ኒወርክ ላይ ደግሞ ከበሮ ተደለቀ።” አለን ተስፋዬ ያነቀውን እየተፋ።
ተስፋዬ እዚህ ላይ ሊነግረን እየከጀለ ያለው፣ በመርዛሙ ብዕር እየረጨ ያለው ትልም እየተሳካለት መሆኑን ነው። ደስታውን እየገለጸልን ነው። ግና ተስፋዬ ኢትዮጵያንና ልጆቿን ከሥረ መሠረታቸው አያውቃቸውም ማለት ነው። ኢትዮጵያ ትፈራርሳለች ብሎ ማመን የሕልም እንጀራ እንደመብላት ነው። እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች፣ የቁርጥ ልጆች
አሉና። ተስፋዬ የነዘራይ ድረስን ታሪክ፣ የነ አሉላ አባነጋን ታሪክ እነ አብዲሳ አጋን ታሪክ አላነበበ ይሆናል። ዛሬም አሉ ብዙ ዘራአዮች፣ ዛሬም አሉ ብዙ አሉላዎች፣ ዛሬም አሉ ብዙ አብዲሳዎች። ደግሞም ምርጫ 97ን ተስፋዬ ራሱ ሳይታወር ቢያስተውል ኖሮ፣ እንደዚህ በእብሪት ልቡን ሞልቶ አይልም ነበር። ዳሩ ምን ያደርጋል ብቻ. . . .
በሌላ ማስታወሻ ላይ ደግሞ፣
ተስፋዬ “ትግራይ (ሌላው ገጽታ)” በሚል ርዕስ ሥር፣ “የመስቀል በዓል ዕለት ክንፉ አሰፋና ባለቤቱ እንዲሁም እኔ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ በጣም ከሚታወቅና ከተከበረ ሰው ቤት ምሳ ተጋብዘን ሄደን ነበር። አሪፍ ምሳ ከተጋበዝን በኋላ ጠጅ፣ ቢራ፣ እና ዊስኪ ቀረበልን። የክንፉ ባለቤት ለስላሳ ያዘች። ክንፉ መኪና ስልምነዳ አልጠጣም በማለቱ አንዲት ብርጭቆ ወይን ብቻ ያዘ። እኔና ጋባዣችን ደግሞ Black label የተባለውን ውስኪ እንደ አድአ ጥቁር አፈር ለእርሻ ጠመድነው። የጋባዣችን ሚስት ባለቤት የቡና ዕቃ አቀራረበችና ወደ ጦፈ የፖለቲካ ወግ ገባን። የጋባዣችን ባለቤት እኔ በዘር ኤርትራዊ መሆኔን አታውቅም። አንድ ወግ አነሳች፣ አንድ ነገር ልጠይቅህ? አለችኝ። ጠይቂኝ አልኳት። “ትግሬዎች ለምንድነው የሚጠሉን? ለምንድነው በጥላቻ የተሞሉት? ለምንድነው እንዲህ ጨካኝና ዘረኛ የሆኑት? ከባድ ጥያቄ ነበር። የጋባዣችን ባለቤት “ትግሬ” ስትል ኤርትራና ትግራይ ደባልቃ መሆኑ ገብቶኛል። ደባለቀችውም፣ ለያየችውም በቅንነት ይህን ጥያቄ ላቀረበችልኝ የጋባዣችን ሚስት ምላሽ ለመስጠት ለኔ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ይህን ጥያቄ ልመልሰው የምችለው አልነበረም። የምመልሰው ከሆነ ገና ከመነሻው፣ ትግሬዎች በጥላቻ ተሞልተዋል የሚለውን ማመን አለብኝ።” ይላል።
እንግዲህ አተኩረን ስንመረምር ሁለቱም በተለያዩ አገላለጾች ይቀመጡ እንጅ አንድ ናቸው። ያው የኃይሌ ገብረሥላሴ ታላቅ ወንድም ተክዬ ገብረሥላሴ ቤት የተፈጸመን ሁኔታን ነው የሚነግረን። በአንደኛው ማስታወሻ ለኃይለገብረሥላሴ ሚስት መልስ ለመስጠት እንደተቸገረ ሲነግረን፣ በሌላኛው ደግሞ መልስ እንደሰጣት እናያለን። ከዚህም መረዳት የምንችለው፣ ተስፋዬ እንዴት ዓይነት ወሽካታና ቆርጦ ቀጥል እንደሆነ ነው። በሌላም፣ የኃይለገብረሥላሴ ወንድምና ሚስቱ ሰው አግኝተው፣ ኢትዮጵያዊ አግኝተው፣ ክብር ሰጥተው መጋበዛቸው ነበር። ግን ውስጠ-ማንነቱን እንደሌሎቹ ሳይረዱ ቀርተው ነው። እንዴትስ ይችላሉ? ተስፋዬ በጣም አስቸጋሪ፣ እማንም ውስጥ ለመግባት በሚችል መልኩ ራሱን ሁሌ የሚያዘጋጅ ሸፍጠኛ ነው።
የተከበራችሁ አንባቢያን ዋናው ኮፒዎች ቀጥለው የተመለከቱት ናቸው። የተስፋዬ እጀ-ጽሑፍ። በየትኛውም መልኩ የማይክደው።
ተስፋዬ ግን በአጋጣሚውም አንድ ትልቅ፣ በጣም ትልቅ እውነታ ተፋ አድርጎአል። ኢትዮጵያን የማፈራረሱ ትልሙ ግብ እየመታ መሆኑን። ለዚያውም በኩራት መንፈስ። በሌላውም፣ ለአባት አገሩ ሥራው የተሳካለት መሆኑን እያበሰረ። አልፎ ተርፎም ደግሞ ተስፋዬ አሁን እየያዘ የመጣው አማራውን ከኦሮሞ ማህበረሰባችን ማገጨት ጎን ለጎን ከመላው የትግራይ ማህበረሰብ ጋር ለማድረግ ፍሙን እፍ ይል ጀምሮአል። አዎን ተስፋዬ የጀመረው ኢትዮጵያ የማፈራረሱ ትልም እየተስካለት መስሎታል። የሕልም እንጀራ ነው። ከቶውንም ቢሆን የሚሆን አይሆንም። ወያኔ ሥልጣን በያዘበት የመጀመሪያ ሁለት ዓመታት እርሱና ጓደኞቹ እንደነታምራት ላይኔ የመሳሰሉት ምን ትጠብቃለህ ባዮቹ ሕዝባችን ርስበርስ እንዲፋጁ ያደረጉት ሴራ በራሱ በሕዝቡ አልበገር ባይነት መክሸፉን፣ እና በ1997 ምርጫ ሕዝባችን በዘር ሳይከፋፈል ሆ ብሎ የወጣበትን ተስፋዬ ዞር ብሎ አላስተዋለውም ማለት ነው። በአሁኑ ጊዜ የየብሔረሰቦች ወጣቶች ተባብረው ስለአንድነት እየሰበኩ ባለበት ወቅት፣ ተስፋዬ በዚያው ባረጀ ባፈጀ አስተሳሰቡና ቅመራው ድልድይ ላይ መጓዙን አላቋረጠም። ይገርማል። ከመቼውም በላይ አዲሱ ትውልድ የአንድነት ዛፍ፣ የአንድነትን አርማ ጨብጦ ተነስቶአል። ተስፋዬ እርሙን ማውጣት ይኖርበታል። ልፋት በከንቱ ይሉታል እንዲህ ነው። እብድ እርሱ እንጅ ማንም ኢትዮጵያዊ እብድ አይደለም። ሆኖም እንቀጥል አሁንም።
ከዚህ በኋላ ስለሚኖረኝ ፕሮግራም፣
ተስፋዬ ከዚህ በኋላ ስለሚኖረኝ ፕሮግራም ብሎ ከአናቱ ላይ በጻፈው ማስታወሻ ላይ፡ “ከስደተኛው ማስታወሻ ቀጥሎ የምጽፈው መጽሐፍ ምናልባት “የቀይ ወጎች” የሚል ሳይሆን አይቀርም። ይህንንም የምጽፍላችሁ እዚያው ድባርዋ ሆኜ ነው። ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ምክንያት በድንገት ወደ ኤርትራ ብቅ ካላችሁ ድባርዋ በየት በኩል ነው? ብላችሁ ጠይቁ። እዚያው ከአያቶቼ እርሻ አጠገብ ከዋርካ ዛፎች ሥር ተቀምጬ ስሞናጫጭር ታገኙኛላችሁ።” ይልና ወረድ ብሎ ደግሞ፣ መጽሐፉ የሚያካትታቸውን ክፍለ-ርዕሶችን እንደሚከተለው ዘርዝሮአል።
1. የባሕረ ነገሥታት ዘመን፣
2. የኤዎሮፓዊያን ወረራ፣
3. ጃንሆይና ደርግ፣
4. የኤርትራ ሕዝብ ትግል፣ እና
5. ነጻነት በሚሉት።
በዚህ ዝርዝር ጎን ላይ፣ “ከሻቢያ ጋር ግንኙነት አለው የሚለውን ወደ ኤርትራ መግባቴን ትርጉም ሚዛን ይሰጥልኛል ብዬ አስባለሁ።” የሚል ሃይለ ቃል አስፍሮአል ተስፋዬ። ጉድ ነው ተስፋዬ የኢትዮጵያዊያን ወዳጅ ሆኖ፣ ተናፍቆ ሊጠይቅ? ብቻ የአካሄድ መንገዱን ማስተዋል ደግ ነው።
አዚማሙ ተስፋዬ ይለናል እንደገናም ወረድ ብሎ፣ “መጪው የኢትዮጵያ ትውልድ የኤርትራን ታሪክ በትክክል እንዲያውቅ ያደርገዋል። ይህም በአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አእምሮ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረችና እንደማትሆንም የአመለካከት ዘር መዝራት ያስችለናል። ለዚህ ሥራም የናንተ ም/ቤትም ሆነ ህገፍ ሰነዶችን እንድመለከት በመፍቀድ ያግዘኝ ዘንድ እመኛለሁ።” በማለት ኢትዮጵያዊ ነው። እውነተኛ ነው ብለው ሽንጣቸውን ገትረው ለሚከራከሩት ኢትዮጵያዊያን መርዶ አረዳቸው ማለት ነው ተስፋዬ። እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ይሉ የለ አበው።
“ኢትዮጵያዊያን የኤርትራ ታሪክ በትክክል እንዲያውቁ ይረዳል። ይህም በአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አእምሮ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረችና እንደማትሆንም የአመለካከት ዘር መዝራት ያስችለኛል። ለዚህ ሥራም የናንተ መ/ቤት ሆነ ህገደፍ ሰነዶችን እንድመለከት በመፍቀድ ያግዘኝ ዘንድ እመኛለሁ። እነዚህ መጻሕፍትን ጽፌ እስከምጨርስ ሁለት ዓመት ይፈጅብኛል። ቢያንስ በቢሮና በጽሕፈት መሣሪያዎች እንዳልቸገር ብደረግ እመኛለሁ።” በሚል ይደመድማል።
አዎ ተስፋዬ የቀረውን አዲስ ታሪክ አርግዞ ሊወልድልን፣ በለመደውም የሽምጥ ግልቢያው ሊያልፈን እየከጀለ ነው። አዲሱን ትውልድ እንዲህ እንደዋዛ ቆጥሮታል ተስፋዬ። እጅና እግሩ ተከርችሞ እንጅ አዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ ነገርን ሲረዳ ከነበልባል የሚፈጥን ትውልድ ነው። እንዲህ እንደዋዛ ከቶውንም የሚበገር ትውልድ አይደለም። ነገርን አይቶና ገምቶ ነው የሚነሳው።
የስደተኛው ማስታወሻ 60%፣ በዚህ ማስታወሻ ርዕስ ሥር ተስፋዬ የነደፋቸው እኩይ ነጥቦች ሲታዩ፣ በየወብሳይቶች፣ ሚዲያውች ላይ ከወዲሁ ስለ መጽሐፉ ዝግጅት ቅስቀሳ ለማድረግ ወደ መንደርደሩ ላይ መሆኑን የምንመለከት ይመስለኛል። የስደተኛው ማስታወሻ ግንባታ 60%ቱ ተጠናቅቆአል ይለናል። ሌንጮ ለታ ከደራሲው ጋር የአንድ ሙሉ ቀን ቆይታ ያደረገ ሲሆን፣ ከዶ/ር ነገደ ጎበዜ ጋር ለመገናኘት በስልክ መነጋገሩ ታውቋል ይልና በመጽሐፉም ውስጥ ከሚያካትታቸው መካከል ታማኝ በየነን “የታማኝ በየነ ሰሸክም” በሚል፣ “መለስና ብርሃኑ” በሚል የሁለቱን የፖለቲካ ሰዎችን አመለካከት፣ ታክቲክ፣ ስትራተጂና ስብዕና በሚዳስስ መልኩ የሚጨምር መሆኑን ገልጾአል። ቅመም መሆኑ ነው። አቅጣጫ የማስቀየስ ቅመም፣ ለተልእኮው ያዘጋጀው ሽፋን (ማስክ) መሆኑ ነው። ለነገሩ እንደገልጸው ዶ/ር ነገደ ጎበዜን ሊያነጋግራቸው ሞክሮ አልታሳካለትም። የዋዛ ሰው ሆነው አልተገኙለትም። ምናልባትም የተስፋዬን መሰሪነት ተረድተው ይሆን? እናም ተመልከቱ የፖለቲካው ፋይዳ ለአባት አገሩ ግን እናት አገራችንን በተለያየ መልኩ እየቦረቦራት፣ እያቆሰላት መጽሐፎቹን ተሻምተን የምንገዛው እኛው። ምን አዙሮብን ይሆን? ከሌንጮ ለታ ጋር ተስፋዬ ያደረገው ንግግር ቁም ነገር ቀጥሎ በቁጥር 16 ማስታወሻ ላይ የተመለከተው ነው።
ወረድ ይልና ተስፋዬ፣
“ጎጉል እንደጎለጎለው ከሆነ የስደተኛው ማስታወሻን ከማንበብዎ በፊት በሳቅ ብዛት ለመሞት መዘጋጀት አለብዎ። ለሳቅ ብቻ ሳይሆን ለመደንገጥም ይዘጋጁ።” ካለ በኋላ ይቀጥላል። ወደ አሜሪካ በመጓዝ አስፋ ጫቦንና ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ ታማኝ በየነን ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ ሰዎችን የማግኘት እቅድ መያዙን ገልጾአል።”
የአራድ ሰው ሥራ መሆኑ ነው ይህ። ደግሞም ተስፋዬ እውነትም አራዳ ነው። ለነገሩስ ጡት ነካሽ ሆነ እንጅ የቢሾፍቱ ልጅ አይደል። እኛ እስከተመቸንለት ድረስ የአራዳ አራዳ ቢሆን ምን ያስደንቃል? እርሱ ከአራዳነትም አልፎ የሚሄድበትን መንገድ በእቅድ እቅዱ፣ መላ በመላ እየለካ ይጓዛል። ለወገኑ በሳል ፖለቲከኛ ሊባልም ይቻላል። በአሜሪካ  ማህበረሰባችን መሃል ዘው ብሎ ለመግባት ያስችለው ዘንድ ሰዎችን በጥንቃቄ መርጦአል። በተለይ አትኩሮቱ በውድ ልጃችን በታማኝ ላይ ይመስላል። ታማኝ እንዲህ የዋዛ መስሎት። ታማኝ ለእንዲህ መሰሪ ቀበሮ ቀርቶ ለቀድሞ ጌቶቹ ያልተበገረ፣ ግንባሩን ያላጠፈና የማያጥፍ ቆፍጣና ኢትዮጵያዊ ነው። እስከዛሬም የእግር እሳት ሆኖባቸው እያቃጠላቸው ይገኛል። በኢትዮጵያዊነት ላይ ወለም ዘለም እርሱ ዘንድ የታለና?
ቀድሞ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ይመስላል ለአሰፋ ጫቦ ያዘጋጀው ንድፈ-ደብዳቤም አለ። ይላከው አይላከው የሚታወቅ አይደለም። “የተከበርከው አሰፋ ጫቦ!” ብሎ ይጀምርና የአሰፋን አንጀት ለመብላት ያህል ይመስላል መለስና በረከት ሆን ብለው ከአገር እንዲወጣ ያደረጉትን ሴራ ይተርካል። ተስፋዬ የራሱን ጉድ በጉያው ይዞ፣ ወደ ሌሎች ማላከኩን መቼውንም ይቀጥልበታል። የማይፈነቅለው ድንጋይ፣ የማይቆፍረው ጉድጓድ ይኖራል ብሎ ማሰብም የሚቻል አይሆንም። ራሱ በራሱ የሕዝብ ደህንነት አባልነቱን ባንድ በኩል እየነገረን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከደሙ ንጹህ እንደነበረ ሊነግረን ይከጅላል።
ደግሞም ሌላ ቁም ነገር አስፍሮአል ተስፋዬ በስደተኛው ማስታወሻ ላይ፣
“ሃቦ ዘለዎ፣ ኤርትራዊ ሆኜ ሳለ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ድራማ እንድሰራ ሃሳቡን ያቀረብኸው ራስህ ነህ። አሁን ቢያንስ አንባቢና ደጋፊ አፍርቻለሁ። የግዴታ ጥቆማ ማፈላለጉ ለዚህ ሥራ በሚጠቅም መልኩ መታቀድ አለበት።” የሚል አስፍሮአል። እውነትም ድራማ። ከድራማም ድራማ። ምን ያድርግ ተስፋዬ እኛ በእጅጉ ተመቸንለት። በሩን ከዳር ዳር ከፍተን አስገባነው። ሜዳውም፣ ፈረሱም ያውህልህ አልነው። እናም አይፈረድበትም። በዓላማ ለአባቱ አገሩ መሥራቱ ነው። እኛ እንባላለን፣ እርሱ እሳቱን ያቀጣጥልናል።
በማስታወሻው ላይ ሌላ ገዘፍ ያለ ነገርም አለ እንዲህ በሚል።
“በኤርትራ ጉዳይ፣ በሻቢያ አላማዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ኢሳያስን በተመለከተ ያለኝ በጣም ግልጽ ነው። ከነሙሉ ችግራችን ኤርትራ በትክክለኛው ሃዲድ ላይ እየተጓዘች ነው ብዬ አምናለሁ። የሚታረሙ ነገሮች ካሉ ዋናው ጉዞአችን ሳይነካ እየተስተካከለ ሊሄድ ይችላል ብዬ አምናለሁ። የምጽፈውም ሆነ የምሠራው ይህን መሠረት ያደረገ ነው።” በሚል። አሁንም የቀይባሕር ማስታወሻ በተባለ ሰንድ የሚከተለውን ተስፋዬ አስፍሮት ይገኛል። “አሻግሬ ስመለከት በርቀት ሰማያዊ ተራሮች ይታየኛል። ከተራሮቹ ስር ያለው ለጥ ያለ የእርሻ ሜዳ የአባቴ አገር ነው።”
“ይህን ታሪክ እጽፈዋለሁ: ሶስት ተከታታይ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። ባህረነጋስያን በመጀመር የኤርትራን ታሪክ እጽፈዋለሁ። የሻቢያን የትግል ታሪክ እጽፈዋለሁ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ስለኤርትራ ተገቢውን ሃቅ እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። በዚህ መጽሐፍ ጠላት አፈራለሁ። ቢሆንም ግን እጽፈዋለሁ። ስለዚህ ከአሁኑ ፍንጭ መስጠቱ ጠቃሚ ነው። በተቃውሞ የምጽፍ የሚመስላቸው ስለሚኖሩ እስከዚያው ድረስ ይዝናኑበት። ኤርትራ ለመመለሴ ምክንያት ይሰጥልኛል።”
ቀደም ሲል “ከዚህ በኋላ ስለሚኖረኝ ፕሮግራም” በሚለው ማስታወሻው ላይ ጠቀስቀስ ተስፋዬ አድርጎ ባለፋቸው ንድፈ ሓሳቦች መሰረት ራሱን ከመጋረጃ ፊት ለፊት አሁን አድርጎታል። በዚህ በተጠቀስው ርዕስ ሥር ወደ ኤርትራ ተመልሶ የአባቴ አገር ነው፣ መንደር ነው በሚልበት በድባርዋ ተቀምጦ ስለኤርትራ አገሩ ታሪክ በሚጽፍበት ወቅት ምናልባትም በነጻነት ትግል ወቅት ብቅ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ይጠይቁት ዘንድ ጥሪ አድርጎአል። አዎ ምን ያደርግ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ትልሙ ወደ እውን የተጠጋ መስሎታል። ትልሙን ያጠናቀቀ መስሎታል። ደሞም አለን፣ እንዲህ ስጽፍ በተቃውሞ መልክ የምጽፍ የሚመስላቸው ስለሚኖሩ እስከዚያው ይዝናኑበት። አዎ የሚዝናኑ አይጠፉም በመርዘኛ ብዕሩ ካፎት ውስጥ የገቡ። እንዴት አድርጎ ገምቶን፣ እንዴት አድርጎ ተስፋዬ እንደናቀንና እንደተጫወተብን ከዚህ አነጋገር ውጭ የሚያረጋግጥልን ሌላ ምንም ነገር ይኖራል ተብሎ አይገመትም። እንደዳማ ተጫውቶብናል። ግና ጊዜው ሮጦ ከተፍ ብሎአልና ከአሁን ውዲያ ራሱን ካልሆነ በስተቀር ማንንም ተስፋዬ ሊያሞኝ ስለማይችል፣ ራሱን በራሱ ከማዝናናት አይልፍም። አሁን የመጨረሻውን ማብቂያ ጨዋታ መሰናዶ ጨርሶአል በስደተኛው ማስታወሻ። ጉዱ እንግዲህ ፈጦ ወጥቶአልና።
በዚህ “በስደተኛው ማስታወሻ 60%” ላይ በርግጠኛነት ስለኤርትራ ትግል ታሪክና ሌሎች የኤርትራ ዕድገትን የሚመለከቱ ነገሮችን ጨምሮ ሃቦ ዘለዎ ኤርትራዊ ሆኖ እያለ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ድራማ እንዲሰራ በቀረበለት የጌቶቹ አሳብ መሰረት ያከናወነ መሆኑን ይነግረናል። ከዚህ በላይ የለጠፍኩት የማስታወሻው አንኳር ክፍሉን መሆኑን ትረዱልኛላችሁ ብዬ አስባለሁ። የሙሉ ክፍል ቅጅ በእጄ ይገኛል። የሙሉ ክፍል ከፍ ሲል እንዳለ ወደ ጽሑፉ ቀይሬ አስቀምጨዋለሁ።
August 2010,
ለአቶ አለም ሰላምታ፣
ደብዳቤውን ሲጀምር ተስፋዬ፣ august 9, 2010 የግማሽ ቀን ቆይታ አድርገናል ከገመቹ ጋር አለን። በዚህ ቆይታችን በርካታ ጉዳዮችን አንስቶ የነገረኝ ሲሆን፣ አብዘኛዎቹ ዝርዝራቸው በሕዝብ የማይታውቁ ናቸው። ዝርዝሩ ለአንተ ግልጽ ስለሚሆን ዋና ዋና ነጥቦቹን ብቻ እገልጻለሁ። ከ6 ሳምንት በኋላ እርሱ ከሚኖርበት ሃገር በድጋሚ ሄጄ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘናል ብሎ ትረተራውን ተያይዞታል።
1. የናንተ ቁጥር 1 ደርግ ከመውደቁ በፊት አሜሪካ ደርሶ ከተመለሰ በኋላ በሽግግር መንግሥቱ ለመግባት አሳብ ነበረው። አሜሪካኖቹ “Transitional Government” ሳይሆን፣ “Transitional Arrangement” በሚል ቅርጽ ኢትዮጵያን ጠቅልሎ እንዲመራ አሳምነውት ነበር። ሦስታችን በተገናኘንም ጊዜ ይህንኑ ነግሮናል። (ሦስቱ ማለት ዮሐንስ የናንተና ገመቹ) በኋላ ግን ፊታውራሪው አሜሪካ ሄዶ ከስቴት ዲፓርትመንት ጋር ከተነጋገረ በኋላ ይህንኑ ይፋ በማድረጉ በሻቢያ ታጋዮች አካባቢ ከፍተኛ ጫጫታ በመከተሉ ቁጥር 1 ወዲያውኑ በሬዲዮ ቀርቦ ማስተባበያ ሰጠ ሲል ይገልጻል። በቀጣይ ለምጽፈው መጽሐፍ ግባት ይሆን ዘንድ በሚል ዝርዝሮቹን ሰፋ አድርጎ ገልጾልኛል።
2. የሽግግር መንግሥቱን ቻርተር ለማዘጋጀት ተሰነይ ላይ የተደረገውን ስብሰባም ገልጾልኛል። አማረ እና በረከት ተገኝተው ነበር። አሊሰይድ አብደላም ነበር። የናንተ ቁጥር 1 ቻርተሩን በማጽደቁ ሂደት መሪ ነበር። በመካከሉ ፊታውራሪው አሰብ ወደብ በተመለከተ መግለጫ በመስጠቱ አልሰይድ እንዴት እንደተቆጣ ትነተነልኝ። በናንተ ቁጥር 1 እና በአሊሰይድ መካከል ጭምር የሃለቃል ንግግሮች እንደነበሩ ነገረኝ። ቻርተሩ የጸደቀበትን ሂደትና የነበሩ ንግግሮችን ገለጸልኝ።
1. በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ለሁለቱም ቁጥር 1 ሰዎች ደብዳቤ መጻፉን ይገልጻል። ከናንተ ቁጥር 1 ምላሽ ማግኝቱን “ገለልተኛ ልትሆን ስለማትችል ና!” እንዳለውና ጥሪውን ግን እንዳልተቀበለ ይገልጻል። እነ ዮሐንስ በራሳቸው ኮሚቴ ደብዳቤውን መርምረው እንዳልተቀበሉት ያወሳል።
2. ኦነግ ራሱን update ማድረግ አለመቻሉንና አንድ ቦታ መቀርቀሩን ያነሳል። የመጀመሪያው ሙከራ እርቅ መፍጠር ሲሆን፣ ሁለተኛው ሙከራ ሊስማማ የማይችለውን ክፍል በማስወገድ ኦነግን እንደ አዲስ ማቋቋም ይሆናል።
3. ስዬ አብርሃን የተመለከተ ያልተነገሩ ጠቃሚ መረጃዎችን ነግሮኛል። ይህ መረጃ ዞሮዞሮ የስዬን ሆነ የህውሃትን እብሪት የሚጠቁም ነው። በአንድ ስብሰባ ላይ ቃል በቃል “ጀኖሳይድ ልናካሄድባችሁ ችሎታ አለን” እንዳለው ይገልጻል የሚሉት አንኳር ነጥቦች ናቸው።
ንግግሩ ከማን ጋር? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ተስፋዬ ወደ መጨረሻው አካባቢ ከየማነ ጋር ኖርዌይ ላይ መገናኝታቸውን ገለጸልኝ የሚለውን አነጋገር በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ከላይ በቁጥር 1 ላይ ሌንጮ ለታ (የቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ለታ) የሚኖረው በኖርዌይ ከመሆኑ ጋር ሲታይ፣ ይኸው ታሪኩን ተናጋሪው ሌንጮ ለታ መሆኑን እንገነዘባለን።
በዚህ ውስጥ “የናንተ ቁጥር 1” የተባለው ኢሳያስ አፈወርቂ መሆኑን ማወቅ ይቻላል። ልክ ወያኔ በትረሥልጣኑን በያዘበት ሰሞን፣ ምናለ ኢሳያስ ይህችን አገር ከሚከፋፍል ጠቅልሎ ቢገዛት የሚለውን ምኞት የሚያናፍሰው ኢትዮጵያዊ ቁጥር አነስተኛ አልነበረም። በዚህ መሃል ኢሳያስ ኢትዮጵያን ጠቅልሎ እንዲይዝ ሲ.አይ.ኤ ሥራ እየሰራ ነው እየተባለ በሰፊው ይወራ እንደነበር ትዝ ይለኛል። ከዚህ ከተስፋዬ ማስታወሻ ተነስቼ፣ በአሁኑ ላይ ሆኜ ወደኋላ ሄጄ ሳስታውሰው በወቅቱ ይነፍስ የነበረው ወሬ ትክክል እንደነበር ለመገመት ቻልሁ። እናም ኢሳያስ በንጉሡ ዘመንም ሆነ በደርግ የፌደሬሽን አስተዳደር ከተመለሰ ሰላም ለማውረድ ፈቃደኛ እንደነበር ሲነገር እሰማ ነበር። እናም ከዚህ ከተስፋዬ ማስታወሻ ይህንኑ ቁም ነገር ለማየት ተችሎአል።
ሌላው የተስፋዬ ነጥብ በየትኛውም መንገድ ስዬን እንድጥንጣኝ ከመሰርሰር የማያርፍ መሆኑን ነው። ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንዲሉ ዓይነት ይመስላል ሁለ-ነገሩ። ግን ለምን የመስላቸዋል? እውነትስ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ተቆርቁሮ ይሆን? ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ተቆርቁሮ እንዳልሆነ ከላይ በየፈርጀ-ማስረጃዎች ለማሳየት የሞከርሁት ግልጽ ያደርገዋል ብዬ አምናለሁ። እናም ለምን እንደመዥገር? እንመርምር። ቀደም ሲል “እየተስተዋለ” በተሰኘው ጽሑፌ ለወያኔ ለሁለት መሰነጠቅ ትልቁን ሚና ስዬ መጫወቱን፣ እፍ/ቤት ቀርቦ ያለአግባብ መከሰሱን ምክንያት አድርጎ ያደረገውን ንግግር፣ አሳሪው ክፍል ክሱን ለማስረዳት ማስረጃ ያላገኘበት መሆኑን የማስታውሰውን ያህል ገልጬ  እንደነበር ይታወሳል። ስዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ያጠፋው ነገር ካለ ፍታዊ መንግሥት ሲቋቋም እንደየሁናቴው እፍትህ ፊት አቅርበው ሊያስመረምሩት የሚችሉት ኢትዮጵያዊያን ናቸው እንጅ ማንም አደናጋሪ ወንበዴ፣ በሁለት ቢለዋ በሊታው አይሆንም።
ለምን ስዬን ይህን ያህል?
እንኳንስ ውሸት እውነት ሲደጋገም ሬት፣ ሬት ማለቱ አይቀሬ ነው። ተስፋዬ በዚያ በመጽሐፈ-ርኩሳት ላይ ስዬን ባማንቸውም መልክ አላንሳም። ነገር ግን ከጋዜጠኛው ማስታወሻ ጀምሮ፣ የደራሲው መጽሐፍ ውስጥ ብሎም በየሚዲያ፣ ጽሑፎቹ ሁሉ ስዬ የተስፋዬ ጆከር ከሆነ ሰነባበተ። እንዲያው የጉሮሮ ላይ አጥንት ዓይነት ሆኖበታል ለማለት ይቻላል። ለምን? በዚያ በ92 ጦርነት ወቅት ስዬ አጋጣሚውን በመጠቀም መለስ ባያከሽፈው ኖሮ አሰብን ለመያዝ ያደረገው ሙከራና ከዚያም በሻቢያ ላይ ያለው ጽኑ አመለካከት ነው ለማለት ይቻላል። እንዲህ ስዬን ከወዲያና ወዲህ አድርጎ ያብጠለጥለው እንጅ ተስፋዬ መለስና ታምራት ላይ ሲደርስ እጁ ይያያዛል፣ አፉም ወለም ዘለም ይልበታል።
በመሠረቱ እኔ ከሲቢል ሰርቪስ ከተባለው ትምህርት ቤት ከወጡት እና እዳኝነቱ ውስጥ አብረውኝ ሲሰሩ ከነበሩት በተለያዩ ጊዜ የወያኔን ምስጢራዊ እንፎርሜሽን፣ በተለይም ከክፍፍሉ በኋላ አገኝ ነበር። ደርግ እንደወደቀ ምንም ሳይቆዩ ነው ስዬና ሟቹ አየሎም ከመለስና ተከታዮቹ ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ የገቡት እንደነገሩኝ። ስዬ የደርግ ወታደሮች እና ፖሊሶች በሙሉ እንዲባረሩ አይፈልግም እንደነበር፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ከግራ ቀኙ መሳለመሳ ሆኖ ተወጣጥቶ እንዲመሰረት አሳብ አቅርቦ ለመግፋት ሞክሮ እንደነበር፣ አየሎምና ሌሎች የተወሰኑ ይህንኑን ደግፈው እንደነበር፣ በኋላ ግን የመለስ ወገን በተጠናከረ መንገድ ተነስቶ እንዳከሸፈው አስረግጠው ከመንገራቸውም በላይ፣ ስዬ ከፍተኛው የሆነ አስተዋይነት ያለው ሰው፣ በሠራዊቱም ከፍተኛ ተደማጭነት የነበረው ሰው መሆኑን፣ ሁላችም የርሱን አሳብ በጊዜው ብንከተል ኖሮ ይህ ሁሉ አይመጣም ነበር። ውለን ስናድር ነበር የገባን እያሉ በተለይ ቤተሰቦቻቸው ከስዬ ጋር አብረዋል ተብለው ከወያኔ ድርጅት የተባረሩቧቸው በቁጭት ይናገራሉ።
አጠቃላይ ጉዳዮች፣
ቀጥሎ በሚታየው አጠቃልላይ ጉዳዮች በሚል ማስታወሻ ላይ ምናልባትም የሚጽፈው መጽሐፍ ንድፈ-ርዕሰ ዝርዝር ሊሆን ይችላል የተለያዩ ጉዳዮችን ተስፋዬ ለማካተት ማቀዱን እናያለን። የወያኔ-ኢህአዴግ ጊዜያዊ መንግሥት በቻርተር ሲቋቋም፣ ተስፋዬ ሀቢሶ የሃዲያን ሕዝብ ወክሎ እምክር ቤት ከመግባቱም በላይ የምክር ቤቱ ጸሐፊ እንደነበርም የሚታወስ ነው። ታዲያም፣ የፌዴራል መንግሥቱ ከሕገ-መንግሥቱ መውጣት ጋር ሲቋቋም፣ በምርጫ ያልተሳካለት ተስፋዬ ሃቢሶ፣ ለወያኔ-ኢህአዴግ እጁን ሰጠ። ወያኔ መቼም የሌላውን ጓዳ በርግዶ የመግባት ጥበቡ ከጉልበት ጋር ታግዞ ይሳካለታል ቢባል የሚሻል መሰለኝ። እናም፣ የሃዲያን ሕዝብ በተለመደው መንገድ ለመያዝ ሲል ተስፋዬን በደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ መንግሥት አምባሳደር አድርጎ ሾሞታል። ተስፋዬ በመባረር ይሁን በሥራ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ሰደርስ ተስፋዬ ሀቢሶ እዚያው ጠብቆታል። ምናልባትም ተገናኝተውም ሊሆን ይችላል። አለያም ቆርጦ ቀጥል ሊሆን ይችላል። ይሁንና በዚህ በተጠቃሹ ማስታወሻ ላይ ተስፋዬ እንደ አንድ ርዕስ የያዘው፣ ከተስፋዬ ሃቢሶ ተነገረኝ የሚለውን ፕሮፌሰር መስፍን ሃዲያነት ነው። ተወርቶም፣ ተሰምቶም የማይታወቅ ነገር። እንደለመደው በተስፋዬ ሀቢሶ ስም የቆርጦ-ቀጥል ወሬው ይሁን፣ እውነትም ተስፋዬ ሀቢሶ ብሎት እንደሆነ አይታወቀም። ሊታወቅ የሚችለው ይህን መጽሐፍ ተስፋዬ ሀቢሶ ደርሶት ካነበበው በኋላ ወይም ያነበቡ ሰዎች ወሬውን ካደረሱት በኋላ ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይህ ተስፋዬ በለመደው ዓይነት እንዲህ ቃርሞ መጸሐፍ አድርሶ ሊያስነብበን ጉድጉዱን ቀጥሎአል። ዝርዝሯን መመልከትና ማጤን ብልህነት ነው።
ስሙ በርሄ ሃጎስ ብሎ ይጀመራል ተስፋዬ በዚህ ማስታወሻ ሥር እንደሚታየው። በዚህ ውስጥ ከሚዘረዝራቸው ሰዎች መካከል ለጥቀው የተመዘገቡት ፕ/መስፍን ሃዲያነት ጉዳይ ተስፋዬ ሃቢሶ በሚል። ተስፋዬ ሃቢሶ ኢህአዴግ ሥልጣን እንደያዘ በጊዜያዊ መንግሥት ውስጥ በደቡብ ሕዝቦች የሃዲያ ተወካይ ሆኖ፣ የምክር ቤቱ ጸሐፊ እንደነበር ይታወቃል። ከሕገ-መንግሥቱ መውጣት ጋር ከነበረው ሥልጣን ወርዶ ወደ ደቡብ አፍሪቃ በአምባሳደርነት ተሹሞ መሄዱም  ይታወቃል። ተስፋዬ ወደ ኤዎሮፓ ከመምጣቱ በፊት የኖረው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው። እናም፣ በዚያን ወቅት ተስፋዬ ሃቢሶን አናግሮ ፕሮፌሰር መስፍን ሃዲያ እንደነበሩ ነግሮኛል ሊለን ነው። ደህና የመጽሐፉ መቸብቸቢያ ምክንያት አገኘ ማለት ነው። መቼም የዚያ የወያኔ በዘር ኢትዮጵያን ከፋፍሎ የማጥፋት ጥንስስ ጋር ተስፋዬ እስከወዲያኛው ሳያሸልብ እንደማይቀር ቁልጭ አድርጎ እያሳየን ነው። ምንም አለ ምን፣ ዞሮ ዞሮ ግን ተስፋዬ የኛን ትኩሳትና ስሜት እየለካ፣ ወዲያና ወዲህ እያለ፣ ወደ መጽሐፍ እየለወጠ ለእኛው እየሸጠ ዓላማውን ማሳካት ነው። እርሱ እስከሆነለት ድረስ የኛው ሰው ስም ቢጠፋ፣ ቢጨማለቅ፣ ከላይ እንዳለው ኢትዮጵያ ፍጹም ፈራርሳ ለማየት እስከሰራና እስከተመኘ ድረስ ደንታ ያለው አይመስለኝም። አዎን እንዴት ደንታ ሊኖረው ይችላል? ወትሮስም ቢሆን፣ የእባብ ልጅ እባብ አይደል?
ይህ ደግሞ ለጽሑፌ መነሻ ስለሆነው ስለአጅረ ተስፋዬ ማንነትን የበለጠ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። “አደራ ጌታዬ ክፉ ቀን አታምጣ ወዳጅ እንዳላጣ” አበው ይሉት የለ። ያ ክፉ ቀን ደረሰና ወዳጅችንን ተስፋዬን ልናጣው የኢትዮጵያ አምላክ ወሰነው። እውነት ይዘገያል እንጅ መውጣቱ አይቀርም። ከነገሩ ከላይ እንዳልሁት፣ ከራሱ ጽሑፍ ብቻ ስንነሳ ተስፋዬ  የወያኔ-ኢህአዴግ አባል በዚያ በ92 ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ይሰልል የነበረው አባት አገር ለሚለው ለኤርትራ እንጅ ለኢትዮጵያ ለተወለደባት፣ እትብቱ ለተቀበረባት፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ድረስ ላደረሰባት አገር አልነበረም። ካገናኙት ከነዚህ ሰዎች ጋር ተስፋዬ የተቀጣጠረው፣ ከነርሱ የኤርትራ ሕዝብ እና ሠራዊቱ ያለበት ሁኔታ በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብና ሠራዊት እንዲሁም ያገኘውን ምስጢራዊ ወሬ ለማቀበል ይመስለኛል።
ማሳሰቢያ፣
የተወደዳችሁ ውድ ኢትዮጵያን ይህን ጽሑፍ ሳቀርብ ከወያኔ-ኢህአዴግ ወጥተው የሚቀላቀሉንን ለመጻረር እንዳልሆነ ተረዱልኝ። በጭፍኑ ስለትናንት ሥራው እያነሳን ወደ ኋላ መግፋት ጤነኛ የፖለቲካ አሰራርና አካሄድ ነው አልልም። የመጣውን ሰው ተቀብሎ ያ ጊዜ፣ ያ ቀን እስከ ሚመጣ ድረስ፣ የበደለውን ሕዝብ ፈቀደኛ ሆኖ ከጀመረ በሥራ እንዲክስ መጠበቅ ነው። እንዲህ ስንፈቅድለትም በሥራው እናየዋለን። እንገመግመዋለን። ያ ጊዜና ቀን ሕዝባዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ መንግሥት ይዞ የሚመጣበትን። በዚህን ወቅት በድሎናል የምንለውን ወደ ወሳኙ ህዝብ ዘንድ፣ ወይም በነጻው ፍ/ቤት ቀርቦ ዳኝነት እንዲያገኝ ማድረግ ነው።
ከፍ ሲል እንደገለጽሁት፣ እኔ ተስፋዬን በአገር ቤት በሥራው በተለይም በመርዘኛ መጽሐፉ በቡርቃ ዝምታ ባውቅም፣ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቂም ብይዝበትም ወያኔን ተላቆ ወደ ውጭ መውጣቱን ስሰማ ደስታ ነው የተሰማኝ። ስለዜግነቱ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መገመት ቀርቶ ተጠራጥሬም አላውቅም። ዘሮቹ ኤርትራዊ ስለሆኑ፣ እርሱም ወደዚያ ያዘነብላል የሚል ሕልም አልነበረኝም። የዘር አባዜ ስለለሌለኝ። ሁሌም ሰውን የምመዝነው በይሆናል ሳይሆን በተግባሩ ነው። እናም፣ አንዳንድ በሚናገራቸውም፣ የበደለውን ሕዝብ ሊክስ ነው ብዬ በርግጠኝነት ተማምኜ ነበር።ግና የጋዜጠኛ ማስታወሻ መጽሐፉን አምብቤ ስጨርስ ከላይ እንደገለጽሁት፣ ወደ ውጭ ተስፋዬ የወጣው የጀመረው ኢትዮጵያዊያንን የማባላቱን፣ የማጨራረሱን ሥራ ለማጠናቀቅ እንጅ ለመካስ እንዳልሆነ ተረዳሁ። ለማውቃቸውና ለወዳጆቹ ከርሱ እንዲላቀቁ ለማስረዳትና ለመንገር ብሞክርም፣ በአጻጻፉ ይሁን፣ በማላቀው ሁኔታ ሊረዱኝ አልቻሉም። እንዳላዋቂም እየቆጠሩኝ ሄዱ።
ውድ ኢትዮጵያዊያን ፣ ተስፋዬ ካለው የኤርትራ ዜግነቱ ጋር፣ በዚያ በጦርነቱ ወቅት ከፈጸመውም ድርጊት ተነስተን አሁን ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ካላት ግንኙነት ጋር አጋጭታችሁ ለወያኔ-ኢህአዴግ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ እንዳንሆን እንጠንቀቅ። የሞተ ነገር እያነሳን፣ ኤርትራ መቼ ይታመናል? በማለት። በዚያ የሚንቀሳቀሱትን የኢትዮጵያ ጀግኖችን አካሄድ ለማደብዘዝ። “በፖለቲካ ዘለዓለማዊ ወዳጅነት የለም። እንዲሁ ዘላለማዊ ጠላትነት የለም” ተብሎአል። መባሉ ብቻ ሳይሆን፣ ካየናቸውም፣ ከምንሰማቸውም ማረጋገጥ የምንችል ይመስለኛል። በተጨማሪም “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው።” ይህም እውነተኛ እና ቋሚ ሎጅክ ነው። ከቤተሰብ ተነስተን እስከ አገር ግንኙነት ብንሄድ የሚሆን፣ የሚሰራ እውነታ ነው። ጠላትን ለማሸነፍ የሚደረግ የህብረት ዘዴ ነው። በአለም ላይ በዚህ በኩል አእላፍ ምሳሌዎችን መዘርዘር ይቻላል። ማናችንም ብንሆን፣ ማንም ቢሆን ጠላቱን ለመርታት ወይም ለማሸነፍ የማይቆፍረው ጉድጓድ ይኖራል ተብሎ ከቶውንም አይታሰብምና። ታዲያም አንዳንዶቻችን ቃሉ ሲነሳ በዚህ ላይ አይሰራም እንላለን። ለማይሰራበት አስረጂያቸው የትናንት ቆፋፍሮ መወርወር ነው። እንዲህ ዓይነቱ ወኔ ሰበራ አካሄድ የሚጸናወናቸው ትላልቁና በ ዕድሜ በገፉት ላይ ነው እንደምሰማውና እንደምሰማው። ይገርማል ነው ታዲያ። መቼም የእናት ልጆች እንኳ እርስበርስ በአንዳንድ ነገር ይሳለላሉ። እንደዚሁም እንኳንስ በጦርነት በሰላሙ ጊዜ እንኳ ወዳጃም አገሮች እርስበርስ እንደሚሰላሉ ከስነውደን መግለጫ መረዳት ተችሎአል። አሜሪካ በእጅጉ የቅርብ ወዳጇን ብሪታንያን ትሰልል እንደነበረ ነው። ይኸ ደግሞ የሚቀጥል ነው። ይህ ያለ፣ የሚኖርም ነው።
በዚህ አጋጣሚ ምናልባትም የአሳትሚው ድርጅት ነጻት አሳታሚ ሊጎዳ ይችል ይሆናል። በጣም አድርጌ አዝናለሁ። ከአገር የሚበልጥ የለምና ይቅርታ እጠይቃለህ። ከሁሉ በፊት ዘወትር ተስፋዬን ባሰብሁ ቁጥር፣ ዘወትር ተስፋዬን ባየሁ ቁጥር ይደማ ለነበረው አእምሮዬ ፈውስ ለሰጠው ለትንታጉ አለማየሁ ወሰን የሌለው ምስጋና አቀርባለሁ። ሥራ ማለት እንዲህ ነው። ኢትዮጵያዊ ማለት እንዲህ ነው። ማንም ያልሰራውን ነው አለማየሁ በወኔ የሰራው። የተገኘን አጋጣሚ እንዲህ የሚጠቀም ለመኖሩ እጠራጠራለሁና።
እናም፣ ውድ የአገሬ ሰዎች ወያኔ-ኢህአዴግን ለማጣል ትግላችን ዘርፈ ብዙ ነው። ሁላችንም ሁሉንም የትግል ዘርፎችን መደገፍ ያለብን ይመስለኛል። ይህ መንግሥት ያለነፍጥ አስገዳጅነት ሥልጣን ይለቃል የሚል ሕልም ባይኖረኝም፣ በዚያ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ላይ ሆነው በሰላማዊ ትግል ዋጋ እየከፈሉ ላሉ ሁል ወሰን የሌለው አድናቆት አለኝ።
የኢትዮጵያ ጠላቶች ይወደሙ። ኢትዮጵያ በነጻነቷ ኮርታ ለዘላለም ትኑር።
ወልደሚካኤል መሸሻ።
ኢትዮሚድያ – October 1, 2013

No comments:

Post a Comment