Monday, 14 October 2013

ወያኔ አንዳንድ የአማራ ክልል ከተሞችን ለራሱና ለሌሎች ለአጎራባች ክልሎች ሊሸልም መሆኑ ተሰማ

ከዚህ ቀደም ወልቃይት ጠገዴን ከጎንደር ገንጥሎ ትግራይ ዉስጥ የጨመረዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ያኔ የዘረፈዉ መሬት አልበቃ ብሎት አሁንም በአማራ ክልል የሚገኙ አንዳንድ የድንበር ከተሞችን ወደራሱ ወይም (ትግራይ ክልል) ለመጨመር ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን ኢሰት ቴሌቪዥንና ሬድዮ የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘገበ። የኢሳት ዘገባ በግልጽ እንዳስቀመጠዉ በድንበር አካባቢ የሚገኙ የአማራ ክልል ከተሞች የሚሰጡት ለኢያንዳንዱ አጎራባች ክልል ቢሆንም ወያኔ ይህንን የአማራን ክልል ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሁሉ የማሸጋሸግ ዕቅድ ያወጣዉ ለይስሙላ እንደሆነና ዋና አላማዉ አማራዉን ለማዳከምና የራሱን ክልል ለማስፋት ነዉ የሚሉ ብዙዎች ናቸዉ። በድንበር አካባቢ ከሚገኙ የአማራ ክልል ከተሞች አስተዳዳሪዎች በተገኘው መረጃ መሰረት የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ ፣ የራስዳሸንና የአዲአርቃይ አካባቢዎች ትግራይ ክልል ዉስጥ የሚጠቃሉ ሲሆን በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የየከተማዎቹ ባለስልጣናት ለኢሳት በሰጡት መረጃ መስረት ባለስልጣናቱ የህዝቡን የልብ ትርታ አዳምጠዉ የህዝብን ሀዘንና ድንጋጤ የተመለከቱ ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ደግሞ የችግሩን ስፋት ኢሳት ለህዝብ ይፋ እንዲያሳዉቅላቸዉ ተማጽነዋል። የወያኔ አገዛዝ ከአሁን በፊት በአማራ ክልል ስር የነበረውን የመተከል ዞን ለቢኒሻንጉል ጉምዝ ፤ራያና ቆቦን ፤ዳንሻንና ሁመራን በመተማ በኩል ለሱዳን ፤ቀሪውን የመተማ ክፍል ደግሞ ለቤንሻንጉል መሰጠቱን በማውሳት ፣ አሁንም ተጨማሪ መሬት እየተቆረሰ ክልሎችን ለማስደሰት ሲባል ብቻ እኛን እየተጎዳን ነው በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። የአንቀጽ 39 ትሩፋቶች የሰጡን ገፀ በረከቶች ናቸው ሲሉ ያማረሩት የድንበር ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ ”ጨለምተኛ አባት መሬት እየሸጠ ልጆቹን ርስት ያሳጣል፡፡ ጨለምተኛ መንግስት ደግሞ አገርን በመሸጥ ዜጎችን ያስደፍራል፡፤ ማንነታቸውን ያሳጣል፤ መንግስትም ማንነታችንን እየነጠቀን ነው ሲሉ” በወያኔ አገዛዝ ላይ ያላቸዉን ከፍተኛ ቅሬታ ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሁኔታው ያበሳጫቸው ነዋሪዎች በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ድርጅቶች ጉዳዩን አጽንኦት ሰጥተው ሊያዩት ይገባል ብለዋል። ይህ በእንዲህ አንዳለ የትግርኛን ቋንቋ የአማራ ክልል ተማሪዎች እንዲማሩት ለማድረግ ታስቦ በጎንደር በተካሄደው ፓይለት ጥናት ህዝባዊ ተቃውሞ በማስነሳቱ እንዲቆም ተደርጓል። ይህንን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቋንቋ ጥናት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ባየ ይማም በቅርቡ በአቀረቡት ጥናት የመንግስት ቋንቋ አጠቃቀም ‘የህዝብን ጉዳይ በህዝብ ቋንቋ’ የሚለውን መርህ የተከተለ ባለመሆኑ ህዝቡ ማግኘት ያለበትን መልእክት በትክክል እያገኘ፤ ለለውጥም እየተነሳሳ አይደለም ብለዋል፡፡ ባጭር ቃል በዚህ አይነት ቋንቋ የሕዝብን አእምሮ መቀየር እንደማይቻል የገለጹት ፕሮፌሰሩ፣ባለስልጣናቱ የአማረኛ ቋንቋ እንዲጠፋ የበኩላቸውን እየተወጡ ነው ብለዋል፡፡“ሀገራችን የቋንቋ ፖሊሲና የአጠቃቀም ደንብ ወይም ስርዓት እስካሁን የላትም፡፤ እስካሁን ድረስ ከህገመንግስታዊ የመብት ማረጋገጫ አንቀጾች ያለፈ፣ ቋንቋን እንደ ማንኛውም የሀገር ሀብት በእቅድ የሚያሳድግ፣ የሚቆጣጠር፣ አጠቃቀሙን ስርዓት የሚያሲይዝ ፖሊሲና ዝርዝር ደንብ የለንም፡፡ ባለመኖሩም ሁሉም እንደፈለገ የሚተረጉምበት፣ የሚጽፍበት፣ የሚያሰራጭበት ሁኔታ ውስጥ ገብተናል፡፡ ይህ ሊቆምና ቋንቋዎቻችን በዕቅድ ሊያድጉና ጥቅም ላይ ሊውሉ ይገባል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።
የአማርኛ ቋንቋ የሀገሪቱ የስራ ቋንቋ መሆኑ እየታወቀ ክልሎች በፍፁም ጥላቻ እንዲመለከቱትና እንዲሁም ክፍል ውስጥ ገብተው የመማርን መብት ለተወላጆች ብቻ ትቻለሁ በማለት የአማርኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ፤ በትግራይ ፤ በኦሮምያና ደቡብ ክልሎች ክፍት እንደሚሆኑ ታዉቋል። ተማሪዎች በቋንቋ ትምህርት በሚመዱበበት ወቅትም በአማርኛ ቋንቋ የሚሰጡ ደጋፊ ትምህርቶችን ላለመማር አሰጣ አገባ እንደሚገቡ ታውቋል፡፡በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በቤንሻንጉል እና ሶማሌ ክልሎች የክልሎቹን ቋንቋ የማይናገሩ ተማሪዎች ተመርቀው ስራ ለማግኘት አይችሉም። በመሆኑም ከአማራ ክልል የሚመጡ ተማሪዎች ከክልላቸው፣ ከአዲስ አበባ እና ከደቡብ ክልል ውጭ በሌሎች ክልሎች ተቀጥረው ለመስራት እየተቸገሩ ነው።አንዳንድ ልዩ ችሎታ ያላቸው ወይም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው ለመስራት ካልሆነ በስተቀር የአማራ ክልል ተማሪዎች ስራ ለመያዝ እንደሚቸገሩ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች ገልጸዋል። በሌላ በኩል ግን አማርኛ የሚችል የማንኛውም ክልል ተወላጅ በአማራ ክልል ተወዳድሮ ስራ የመያዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

No comments:

Post a Comment