Tuesday, 21 January 2014

ጎንደር ውስጥ አንድ ወታደር በሃይል ለመድፈር በሞከረበት ግዜ ሶስት ሰው ገደለ !

በጎንደር አካባቢ ማክሰኝት በተባለች ከተማ አንድ የታጠቀ ወታደር የሺ ተሻገር ተባለች የሆቴል ባለቤት በሃይል ለመድፈር በሞከረበት ግዜ ባሰማችው የእርዱኝ ጩኸት በወቅቱ ለመርዳት የመጡ አቶ መንግስቱ፤ የሆቴሉን ዘበኛ ኣቶ ዳኛቸው አለባቸውንና የሆቴሉን ባለቤት የሆነችው ግለሰብ ቦንብ አፈንድቶ ገድልዋቸው እንደተሰወረ ለማወቅ ተችልዋል::
ግድያው በተፈፀመበት ወቅት በመዋቾች ቤተሰብና ባአካባቢው ህብረተሰብ ከባድ ግርግር በመከሰቱ ምክንያትም በንፁሃኑ ወገኖች ላይ እሰቃቂ የግድያ ወንጀል የፈጸመው ኣካል ሳይያዝ ማምለጡ ያካባቢው የፀጥታና ያስተዳደር ድክመት ውጤት ነው ብለው እየገለፁ መሆናቸው ታውቀዋል::
በተመሳሳይ ሁኔታ ከደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች በታህሳስ 29/2006 ዓ.ም ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በስለት ተገድለው መገኘታቸውና። ከነዚህም- ፍሮምሳ ሃይለስላሴና ግርማቸው መኳንንት እንደሆኑ ተገልፅዋል:: መረጃው በማስከተል በዩንቨርስቲው ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ባለው ግድያ በከባድ ስጋት ላይ በመውደቃቸው ምክንያት፣ትምህርታቸውን በአግባብ እንዳይከታተሉ በማሸማቅቅ ላይ እንደሚገኙና፣ቤተሰቦቻቸውም ትልቅ ስጋት ላይ መውደቃቸውን መረጃው አስረድትዋል::
3333333
Source: ዴ.ም.ህ.ት

No comments:

Post a Comment