Monday, 6 January 2014

የህወሓት ስራ እስፈጻሚ ኣካል ዉስጣዊ ኣጀንዳቸው በተመለከተ በመቀሌ ከተማ ያደረጉት ስብሰባ ካለ መግባባት ተበተነ፣

ህ.ወ.ሓ.ት ክፍተኛ የስራ ኣስፈጻሚ ኣካላት ሁነው በተለያየ የሃላፍነት ቦታ የሚገኙ የስርኣቱ ባለስልጣናት፤ በ ታህሳስ 8 2006 ዓ/ም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ባካሄዱት ምስጣራዊ ስብሰባና በተነሳው ኣጀንዳ መስማማት ላይ ሳይደርሱ፤ ተበታትነው እንደወጡ ከዉስጥ ኣዋቂዎች የደረሰን መረጃ ኣመለከተ።

መረጃው ኣክሎ በስብሰባው የህ.ወ.ሓ.ት ኣስፈጻሚ ኣካል ሁነው በሚንስተር መኣርግ ደረጃ ያሉና የክልሉ ኣስተዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆኑ፤ በዉስጣቸው የሚፈጸም የህዝብ እና የኣገር ሃብት ብክነት በነማን እየተፈፀመ እንዳለ በግልጽ መታወቅ ኣለበት የሚል ኣጀንዳ በመነሳቱ ምክንያት ያልተዋጠላቸው እንዳንድ የስራኣቱ ኣመራሮች የተነሳው ኣጀንዳ እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችለዋል::

ከነዚህ የህዝብ ገንዘብ በመዝመት ሃብት ያካበቱ ተብለው የተገለጹ ኣባይ ወልዱ፤ በየነ ምክሩ፤ ኪሮስ ቢተው፤ ኣለቃ ጸጋይና የሱ ሚስት የሆነችው ቅዱሳን ነጋ ሲሆኑ በስብሰባው ወቅት በመጀመርያ ሙሱና የመፈጸም ተግባር በዉስጣችን መጽዳት ኣለበት የሚል ጥያቄ መነሳቱ ደስታ ስላልፈጠረላቸው ያላቸው ሃላፍነት ተጠቅመው ስብሰባው ያለ ምንም ፍሬ እንዲበተን የሚቻላቸውን እንዳደረጉ የደረሰን መረጃ ኣክሎ ኣስረድተዋል::

source ዴ.ም.ህ.ት

cv

No comments:

Post a Comment