Thursday, 9 January 2014

ጆሮ ዳባ ልበስ.......

Jan 9,2014

ከኤልሳቤጥ ግርማ
ከኖርወይ
ezewege@gmail.com
   የማነሽ ከየት ነሽ ሲሏት ትናገር ነበር በሙሉ ማንነቷን ሳትፈራ ሳትሸማቀቅ አንገቷን ሳትደፋ በአባት አርበኞቿ ደም ተጋድሎ ስትኮራ ብሎም አልፎ ተሻግሮ ለአፍሪካ ተምሳሌትነቷን ነጻነትን ሳትደብቅ በኩራት ስትመሰክር ይህች ነበርች ታዲያ ኢትዮጵያ ዛሬ ግና ባያድላት ሆንና ያኔ ኑ ብላ ተቀብላ ባኖረቻቸው አንድንትን፣ፍቅርን በለገሰቻቸው እንግዳ ተቀባይነቷን ባሳየቻቸዉ ሃገራችን ሃገራቹ፣ኑሮዋችን ኑሮዋቹ፣ሃይማኖታቹ ሃይማኖታችን እንዳላለቻቸው ያ ሁሉ ቀረና ዉለታ ቢሶች ሆነን በደም መለሱልን።
 ይህ ብቻ መቼ ሆነና የአያት ቅድም አያቶቻችን መሰዋትነት ክብር ሞገሳችን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዬ የሚያሰኘው ማንነታችን በተመጽዋችነት፣በስደት ናፋቂና ተዋራጅነት እንደ እንስሳ ደማችን በየሃገሩና በየጎዳናው ፈሶ ክብራችን ተገፎ ማየት ከጀመርን ከሁለት አስርተ አመታት በላይ ሆነው።
   ፍትህ፣ ነጻነትና ዴሞክራሲ ያጣው ወጣት እግሬ አውጪኝ እያለ ራሱን ለአውሬና ሰባዊ ርህራሄ ለሌላቸው መስጠት ከጀመረ አመታቶች ተቆጠሩ። ባለፉት ወራቶች በእኛ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን በደል ያየ የሚዘነጋ ያለ አይመስለኝም እንዲሁም ለቡ በሃዘን አይኑ በእንባ የተራጨው ቤቱ ይቁጠረው። ዛሬም በተለያዩ ሃገራት እንደቀጠለ ያለውን ስቃይና በደለ ሰው በላውና አረመኔዉ ወያኔ ደገሞ እንደወትሮ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ሁኔታውን ለመሸፈንና ለማዘናጋት በቡችሎቹና በጀሌዎቹ ለኢትዮጵያ አንድነት የቆምን ድርጅት ነን ባዬች መረቡን ወደ ሌላ አቅጣጫ በመዘርጋት ለማስቀየር እየሞከረ ነው።
    ስለዚህ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ የወገን አለኝታችንን፣አንድነታችን በመቀጠል ለወገኖቻችን መቆምና ወያኔን ማንበርከክ አለብን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
እግዚሐብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

No comments:

Post a Comment