Friday, 21 June 2013

ከግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል ለቀረበልን ጥያቄ የተጠራ አስቸኳይ የስብሰባ

dceson
እንደሚታወቀው ውዷ ኢትዮጵያ አገራችን በዘረኛው፣ በአፋኙ እና በፋሽስቱ የTPLF/EPRDF አገዛዝ ቀንበር ስር ወድቃ በታሪኳ አጋጥሟት የማያውቅ የውርደት ማጥ ውስጥ ትገኛለች፣ በተለይ ከቀን ወደ ቀን በሕዝባችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝ ግፍ እና በደል እየጨመረ የሰው አይምሮ ሊገምተው እና በቃላት ሊገለጽ የማይችል የመጨረሻ የስቃይ ደረጃ ላይ ደርሷል ድርጊቱንም የከፋ የሚያደርገው በገዛ ወገን ላይ ቀርቶ በጠላት ላይ ሊደረግ የማይታሰብ ዘር እና ሃይማኖት ሳይለይ በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ላይ በእቅድ እየተከናወነ መሆኑ ነው::
በመሆኑም ይህ ግፍ አንገብግቧቸው ለአገራቸው እና ለህዝባቸው ነጻነት፣ ፍትህ ዲሞክራሲ ለማስፈን  የነጻነት ታጋዮች ወያኔን በለመደው ቋንቋ ለማናገር ቆርጠው ተነስተው ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋእትነት በመክፈል ላይ ሲሆኑ በማያያዝም ይህንን የነጻነት ትግል በሁለንተናዊ መንገድ እንድንደግፍ ታሪካዊና ወቅቱን የጠበቀ የድጋፍ ጥሪ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አቅርቦልናል::
ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር እና ለጥያቄያቸው አፋጣኝ ወገናዊ ምላሽ ለመስጠት የድርጅታችንን አባሎች በሙሉ አስቸኳይ ስብሰባ ለመጥራት ተገደናል በመሆኑም ማንኛውም የድርጅታችን አባል አራተኛ ፎቅ በድርጅታችን ቢሮ ጎን ባለው የስብሰባ አዳራሽ እሑድ ጁን 30/2013 ከ14:00 ጀምሮ የምክክር ስብሰባ ላይ ተገኝተው መወሰድ ስላለበት ወቅታዊ አፋጣኝ ታሪካዊ ምላሽ አሳቦን እንዲሰጡ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሲያስገነዝብ በማያያዝም በዚህ ስብሰባ ላይ የግድ አባላት በሙሉ እንዲገኙ ያሳስባል::
የስብሰባ ቀን: - እሑድ ጁን 30/2013
ስብሰባ ቦታ: - አራተኛ  ፎቅ በድርጅታችን ቢሮ ጎን ባለው የስብሰባ አዳራሽ
የስብሰባ ሰአት: - ከ14:00 ጀምሮ
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
ኖርዌይ፣ ኦስሎ፥ ጁን 21/2013

No comments:

Post a Comment