አገራችንን እና ህዝባችንን አንቆ ከያዘው ከዘረኛው (TPLF) አምባገነን ስርዓት ጋር እጅ እና ጓንት ሆነው በተፈጥሮ ሃብቷ የሚበለጽጉ ሙሰኛ ባለጸጎች (crony tycoons) በህዝባችን ላይ አየደረሰ ላለው ፍትህ ማጣት፤መንገላታት፤መቸገር፤መታሰር፤መፈናቀል እና ማንኛዉም አይነት ግፍ ከስርዓቱ እኩል ተጠያቂዎች ናቸው።
በንዋይ ሃይል ብልሹ ስነምግባራት ስንፈት፤ ዉሸት፤ ሌብነት፤ ሴሰኝነት ወዘተ (social decadence) በህዝባችን በተለይም በወጣቱ ትውልድ መካከል እንዲስፋፋ ምክንያት እየሆኑ ያሉ እነዚህ የበዝባዥ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ስርዓት (Extractive Political and Economic System) ከበርቴዎች የምያካብቱትን ሃብት የጥቅማቸው ምንጭ የሆነዉን ስርዓት እድሜ ለማስረዘም ሲሉ በስፖርት ስም ወደ ዲያስፖራው የሚረጩትን የደም ገንዘብ እኛ የወገናችን ሰቆቃ የሚሰማን ኢትዮጵያዊያን አጥብቀን የምንቃዎመው እና የምንታገለው ነው።
ለሰላሳ አመታት ኢትዮጵያኖች ተንከባክበው ያቆዩትን የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) ለስርዓቱ አገልጋይነት ለንዋይ ተገዢ ለማድረግ ሞክረው ያልተሳካላቸው ጥቂት ስብእናቸዉን ለገንዘብ ያስገዙ ግለሰቦች ህዝብን ለመከፋፈል ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ትግል አጋር የሆነውን ዲያስፖራ ኮሚኒቲ ለመቆጣጠር (AESAONE) በሚል ስም የሚያደርጉትን እኩይ ተግባር ወገኖቻችን በማወቅም ሆነ ባለማዎቅ እንዳይደግፉ ጥሪ እናቀርባለን።
ይህንን የህዝብ ጥሪ ችላ ብለው በዚህ ጸረ ህዝብ ድርጊት ላይ ለሚሳተፉ የንግድ ባለቤቶች ፤ የሙዚቃ ባለሙያዎች ወይም ማንኛዉንም አይነት ንግድ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያካሂዱ ወገኖችን ተከታትለን የምናሳውቅ እና ማህበረሰባችን ትብብር እንዲነፍጋቸው (boycott) የምንጠይቅ መሆኑን አስቀድመን ማሳወቅ አንፈልጋለን።
No comments:
Post a Comment