Wednesday, 13 November 2013

የ 19 አመት ኢትዮጵያዊ በሳውዲ ወረበሎች የመደፈርዋ አሳዛኝ ታሪክ

እንዲሉ ኢትዬጵያኖች እራሳችን የተውነውን መብታችንን ሌሎች እንዲያከብሩልን መፈለጋችን ላም አለኝ በሰማይ አይነት ነው የሆነብን ።የ አገራችን ችግር ምን እንደሆነ ለማወቅ የሚፈልግም እውቀቱ ያአለውም ያለ እስከማይመስል ድረስ የመክራ መአት በዜጐች ላይ እየደረስ ይገኛል።
መንግስት ነኝ ባዩ ቡድን ዜጐች ከሃገራቸው በስራ ሲወጡ የሚያስፈልገውን ደንብ እና ስርዐት ተክትለው መውጣት ሲገባቸው ኤጀንሲ ነን በሚሉ ወሮበሎች ዜጎች ሲሽጡ በግልጽ እየታየ አንድም ሃላፊነት የሚሰማው የአገር ተቆርቆቋሪ ባለስልጣን እንዴት አገራችን አጣች ? እንዴት በንግዱ እና በፓለቲካው መስክ የ እረጅም ግንኙነት የነበራት አገር እና ሕዝቦቿ በኢትዮጵያዊያን ዜጎች ላይ ይሄን አይነት እርምጃ ሊወስዱ ቻሉ ?እነዚህን እና ሌሎች ጥያቂወች ጠይቄ መልስ ለማግኘት በጣም በመጨነቅ ምንም እንደማይጣ ስለተረዳሁ ጥያቄዎቸን አቁሜ ከሳውዲ አካባቢ የስማሁትን እንደወረደ ላካፍላችሁ ወደድሁ ምን አልባት ስተነፍስው ይቀለኝ ይሆናል በማለት ታሪኩን እነሆ፦
በሰሞኑ የዜጎቻችን ለቅሶ ያላሳዘነው እና ያልተቆጨ መችም የለም ይሄ ግን ጨርቅን አስጥሎ ያስኬዳል ነገሩ እንዲህ ነው
አባት፥ጎረምሳ ወንድ ልጅ እናት እና የ 19 አመት ልጅአገረድ ሴት ልጅ አንድ አፓርትመንት ውስጥ እንዳሉ ቤታቸው በ6 የሳውዲ ጎረምሶች በሩ ተሰብሮ አባት ፥እናት እና ጎረምሳ ወንድም እያየ የ 19 አመት ልጅአገረድ ልጃቸው እና እህቱ ለ 6 ስትደፈር እያዩ ምንም ማድረግ አለመቻል እናት ስታነባ ማየት የ ልጃቸውን ደም እና ህመም የ እህቱን ስቃይ እያየ ምንም ማድረግ ያልቻለ ወንድም ይሄን ሁሉ ስቆቃ እየሰማ ዝም ያለ መንግስት የሌሎች አገር መንግስቶች እና መገናኛ ብዙሀኖች ስምተው ጥያቄ ሲጠየቊ ህገ ወጦች ናቸው ብለው የሚመልሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማየት እና መስማት በ ልጆቹ እና በወገኖቹ ላይ የሚደርሰው መከራ የማያሳስበው ሕዝብ ማየት እረ ሰዎች ምን ነካን እዚች እህታችን እና ቤተሰቧ ጋ የደረሰው የ እኛ እህት ላይ አይደለም የደረሰው እኛ ልጅ ላይ አይደለም የደረሰው እስኪ ሁላችንም እራሳችንን በቦታው ላይ እንዳለን እናስብ እራሱ ዲና ሙፍቲ ተብየውም የ እራሱን ልጅ 6 አረቦች አይኑ እያየ እንደ እንደ እንስሳ ሲደፍሩአት ምን ይሰማዋል;አንገት የተፈጠረው አዙሮ ለማየት ነው::ከዚህ በላይ ለመቀጠል የሞራል ብቃት ስላጣሁ ፍርዱን ለ አገሬ ሰዎች እተዋለሁ።
እግዚአብሄር የኢትዮጵያውያን እንባ ያብስ።
Samuel Ali
SOURCE: freedom4ethiopian

No comments:

Post a Comment