Tuesday 28 April 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ ነው – አደጋ ላይ ነን!

ካስደነገጥኳችሁ አዝናለሁ ግን በጣም መደንገጥ አለባችሁ፡፡በመላው የአዲስ አበባ የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምርህት ቤቶች ማለት ይቻላል በነSave The Children ፊት አውራሪነት እየተሰጠ ያለው የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ሳረዳችሁ ከፍተኛ ሀዘን እየተሰማኝ ነው፡፡እስካሁን ከ40 በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች ውስጥ ለውስጥ በአንድ ክፍለ ጊዜ በ120 ብር በተቀጠሩ የየትምህርት ቤቱ የባዮሎጂና የአይሲቲ መምህራን አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ሁለት አይነት ነው ትምህርቱ፡፡Life Skill (ላይፍ እስኪል) እና Comprehensive Sexuality Education (ከምፕሬኤንሲቭ ሴክሽዋሊቲ ኤጁኬሽን) የሚባሉ፡፡በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዙር ስልጠናው አልቋል፡፡ሁለተኛ ዙሩ የተግባር ትምህርት ነው፡፡ በቪዲዮና በተግባር እንቅስቃሴ የተደገፈ፡፡ ከሚሰጡት ትምህርቶች መካከል FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) እና MASTERBATION (ማስተርቤሽን)የሚባሉ የልቅ ወሲብ አይነቶች አሉበት፡፡ ልቅ ስል በ FREE KISSING (በፍሪ ኪሲንግ) ጊዜ ጾታ ሳይለይ የፈለጉትን ደፍሮ መሳም ሲሆን በ MASTERBATION (ማስተርቤሽን) የሚለው ደግሞ ሴቶችም ወንዶችም በቪዲዮ የታገዘ የ Pornography (የፖርኖ) ፊልሞች እያዩ እንዲተገብሩት የታሰበ ነው፡፡ ለዚህም አላማ ከየትምህርት ቤቱ ጎበዝ የተባሉ ተማሪዎች ተመርጠው ተዘጋጅተዋል፡፡

ጉዳዩ እስከ ትምህርት ሚኒስተርና ቢሮ ቢደርስም እስካሁን መልስ ሊሰጡ አልቻሉም፡፡አንዳንድ የክፍለ ከተማ ሀላፊዎች እንዳሉት እነSave The Childern (ሴቭ ዘቺልድረን) በኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎች ስለሚሰሩልን አቁሙ ብንላቸው ግንኙነታችን ይበላሻል፡፡በላይ አመራሩም ዘንድ ያለው እሳቤና አቋም ይሄ ነው ብለዋል፡፡የተከበራችሁ የአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፤ ወላጆች ፤ቤተሰቦች ይህ የምነግራችሁ ነገር ተራ አሉባልታ አለመሆኑን በተለያየ ጊዜ ለማሳያ የተለጠፉ መረጃዎችን አይታችሁ መፍረድ ትችላላችሁ፡፡ የተከበራችሁ ተማሪዎች ወላጆች እና በዚህ ጉዳይ እንደ እኔ የተንገበገባችሁ ሁሉ አደጋ ላይ ነን፡፡በተለይ ድርጅቶቹ ነገሩን እንዲሰሩላቸው የመረጧቸውን ሰዎች ለመግዛት እያወጡት ያለው ምራቅ የሚያስውጥ ገንዘብ በየክፍሉ ከሚያስተምሩላቸው መምህራንና ከተባባሪ የትምህርት ቤት አስተዳደሮችም አልፎ እስከ ላይ ድረስ ኪስ ሳያሞቅ አልቀረም፡፡ የእናንተ እርዳታ ቆፍጠን ያለ ውሳኔ ያስፈልጋል፡፡
ተማሪዎችና ወላጆች በአዲስ አበባ በብዛት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ቢያነጣጥርም ነገሩ በኦሮሚያ፣ በአማራና በሌሎች ክልልሎች ግን እስከ ታችኛው ክፍል ድረስ በስነተዋልዶ፣በጸረኤድስና በስርአተ ጾታ ሰበብ የግብረሰዶማዊነት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ሳረጋግጥላችሁ በአውነት ነው፡፡ ስለዚህም ተማሪዎች፣ ወላጆች የሚመለከታችሁ ሁሉ አይናችሁን ወደ ትምህርት ቤት አንሱ!! ተማሪዎች በገንዘብ በተደለሉ ግለሰቦች እተረጨባቸው ያለውን መርዝ አስቁሙ፡፡በተለይ በአሁኑ ወቅት አስረኛና አስራ ሁለተኛ ክፍሎች ትምህርት በጨረሱበት ጊዜ እየሆነ ያለው ተማሪዎችን በክረምት ትምህርትና ስልጠና ሰበብ ለዚህ ተግባር እየመዘገቡ ያሉ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ ልነግራችሁ እችላሁ፡፡ሴቭ ዘቺልድረን በክረምት ወራት ትምህርት ቤቶችን በክረምት ትምህርት አሳቦ በመከራየት የሰዶማዊነት ትምህርት ሊሰጥ መሆኑን ስነግራችሁ ያለምንም ጥርጥር ነው፡፡አስካሁን የግብረሰዶማዊነት ትምህርት ሁለተኛ ዙር ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነው ካሉ ትምር ቤቶች መካከል፡ ሚኒሊክ፤መድሀኒአለም፣ባልቻ አባነፍሶ፣ኤስኦኤስ፣ህዳሴ፣አፍሪካ ህብረት፣የካቲት 23 ፣መነን፣አየርጤና እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ይህ ነገር ሀሰትነው ብላችሁ የምትጠራጠሩ ከሆነ በተለይ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተለይ ወላጆች አንደኛ በየክፍለ ከተማ የሚገኙ የስርአተ ጾታ ሀላፊዎችን ፣በአዲስ ትምህርት ቢሮ በተለይ አቶ ሀይለ ስላሴ የተባሉ የስራ ሀላፊን መጠየቅ ይቻላል፡፡በተጨማሪም በኢትዮጵያዊነት ድምጽ ላይ የተለጠፉ የመማሪያ ሰነዶችን ማየት ይቻላል፡፡ወላጆች ልጆቻችሁን አድኑ!!
የተከበራችሁ ተማሪዎች በየትኛውም አጋጣሚ በትምህርት ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጪ በስነተዋለዋልዶና ስርአተ ጾታ ስም የሚሰጠውን ፍጹም የግብረሰዶማዊነት ትምህርት አንማርም ንድትሉ ብትሉም እራስን የማዳንና የመከላከል ተግባርና እርምጃ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ መምህራንም ሆኑ በገንዘብ ተደልለው ሊያስተምሩ የተዘጋጁ ተማሪዎችን አምርራችሁ እንድታገሉ ሁላችንም በፈጠረን አምላክ ስም እለምናቿለሁ!!
ኢትዮጵያ የግብረሰዶማዊነት መቀበሪያ ትሆናለች እንጂ መቼም ከግብረሰዶማዊነት ጋር አትጋባም!!
ጭንቀት ካደረበት መምህር

ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት የከፈተበትን የጥላቻ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳሰበ

መንግስት ሊቢያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ እርምጃ የወሰደውን አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ ከህዝብ የገጠመውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰማያዊ ላይ የጥላቻ ዘመቻ እንደከፈተበትና ይህንን የጥላቻ ዘመቻውን እንዲያቆም ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳስቧል፡፡Semayawi Parties latest press conference
መንግስት የጠራውን ሰልፍ ከማንም ተቃዋሚ ፓርቲ ቀድሞ የደገፈው ሰማያዊ እንደሆነ የገለጸው መግለጫው ‹‹የዜጎችን ስቃይ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል የፈለገው ህወሓት/ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው በደል መፍትሄ እንዲሰጥ መወትወቱ፣ የፖለቲካ ልዩነታችንን ወደ ጎን አድርገን በሰልፉ ላይ መገኘታችን እንዳላስደሰተው ከሰልፉ ቀን ጀምሮ በፓርቲያችን ላይ የተከፈተው ዘመቻ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡›› ብሏል፡፡
ከሰልፉ ማብቃት ጀምሮም ጉዳዩን ገና ፖሊስ ሳይመረምረው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን ሰማያዊ ፓርቲ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት እየጣረ ነው በሚል መወንጀላቸውን፣ የመንግስት ሚዲያዎች ሰማያዊ ፓርቲ ሁከትና ብጥብጥ ሊያስነሳ ነው ብለው ሚዛናዊ ያልሆነ መረጃ ማሰራጨታቸውንና አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም ተብለው በተጠሩ ሰልፎችም ሁሉ መንግስት ሰማያዊ ፓርቲ ለመቃወም እየተጠቀመባቸው መሆኑን መግለጫው አትቷል፡፡
በተጨማሪም በሰልፉ ዕለት የሰማያዊ አባላት ገና ሰልፉ ሳይጀመርና መስቀል አደባባይ ሳይደርሱ እንዲሁም ሰልፉ ካበቃ በኋላ እየታደኑ ሲታሰሩ መስቀል አደባባይ ላይ የተያዙት የኢህአዴግ አባላት ከቀበሌ ደብዳቤ እያመጡ መፈታታቸው መንግስት ሰማያዊን በሀሰት ለመወንጀል መነሳቱን ያሳያል ብሏል፡፡ በሌላ በኩል 6 ያህል የሰማያዊ አባላት በታሰሩበት ሁኔታ መንግስት 7 አመራሮችና 20 ያህል አባላት ታስረዋል ማለቱ ትክክል አለመሆኑንና ከመጀመሪያውም 6 አባላቱ የታሰሩበት መንገድና አሁንም በሰማያዊ ላይ የሚቀርበው ክስ መሰረተ ቢስ ነው ብሎታል፡፡
‹‹ይህ በህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት አማካኝነት እየቀረበ ያለው ክስ እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ህወሓት/ኢህአዴግ ለዜጎች ህይወት የማይጨነቅ እና በዜጎች ሞት የራሱን የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ እና ጠንካራ ተቃዋሚ የሆነውን ሰማያዊ ፓርቲን ለማጥቃት እየተጠቀመበት መሆኑን በተጨባጭ የሚያሳይ ነው፡፡›› ሲልም የመንግስትን ተግባር ተቃውሟል፡፡ በፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተሰጠበትን ጉዳይ ተጠርጣሪ ከማለት ይልቅ ወንጀለኞች ናቸው በማለት በህገወጥ ስራ እንደተሰማራ ያሳያል ሲልም ወቅሷል፡፡
‹‹መንግስት እና የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከዚህ አኩይ ተግባራቸው የማይታቀቡ ከሆነ፣ የሰማያዊን ስም በሀሰት በማጠልሸት ስራ ላይ የተሰማሩ የመንግስት ተቋማትን እና ግለሰቦችን በህግ ፊት ለማቆም ይገደዳል›› ያለው መግለጫው ሌሎች ተከታታይነት ያላቸውን እርምጃዎችም እንደሚወስድና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሰማያዊ ፓርቲ ለሚያደርጋቸው ህዝባዊ ጥሪዎች በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

“መንግሥት የላሇው እዙህ ብቻ ነው!”

“መንግሥት የላሇው እዙህ ብቻ ነው!” የአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መግሇጫ ባሇፈው እሁዴ አይሲስ ባሰራጨው ቪዱዮ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በሁሇት የተሇያዩ ቦታዎች ሲገዯለ ተመሌክተናሌ። ስሇ ቪዱዮው ብዘ ማሇት ቢቻሌም ወገኖቻችን ከአገራቸው ወጥተው ወዯ ተሻሇ ኑሮ ፍሇጋ መንከራተታቸው ሇዙህ ዓይነቱ አሰቃቂ ሞት ዲርጓቸዋሌ። ከአገራቸው የወጡት እየኖሩ ከመሞት ሇመትረፍ ቢሆንም በስዯት ዯግሞ እጅግ መራራውን የሞት ጽዋ ጠጥተዋሌ። ይህ የወገኖቻችን ዕሌቂት በዓሇማችን ሊይ በሚገኝ በምንም ዓይነት ቋንቋ፣ አገሊሇጽ፣ አጻጻፍ፣ እንባ፣ ወ዗ተ ሉገሇጽ የማይችሌ ነው። ረዲት አሌባ ሆነው የተመሇከትነው ትዕይንታቸውም በውስጣችን ሇ዗መናት የማይሽር ቁስሌ ይዝ ይቀመጣሌ። የአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዲይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሁለንም ኢትዮጵያውያን ዗ር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ቦታ፣ ወ዗ተ ሳይሇዩ ይህ በአገር ወገን ሊይ የዯረሰው ሏ዗ን በጋራ በመሆን እርስ በርስ በመጽናናት፣ በመበረታታት እንዱወጡ፤ ላልችንም በተመሳሳይ የስቃይና የመከራ ሁኔታ ሊይ የሚገኙትን ወገኖች ሇመርዲት የሚችለበትን መንገዴ እንዱቀይሱ አሳስበዋሌ። አቶ ኦባንግ ሲቀጥለም፤ “በዓሇም ዘሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእነዙህን ሇሃይማኖታቸው የቆሙ ጀግና ወገኖቻችንን ተመሌክቷሌ፤ የሞት ከበሮ ቢዯሇቅባቸውም ሳይፈሩና በዴፍረት ሰብዓዊነታቸውን በናቁባቸው አረመኔዎች ፊት ሇእምነታቸው ቆመዋሌ፤ “እኔም ሆንኩ በጋራ ንቅናቄያችን ሥር የሚገኙ ቤተሰቦችና ላልች እጅግ በርካታ ወገኖች የተሰማንንን ጥሌቅ ሃ዗ን በምንም ዓይነት ቃሊት መግሇጽ አንችሌም፤ ይህንን ፍጹም አረመኔያዊ የሆነ፤ አንዲች ሰብዓዊነት የላሇበት ዴርጊት ባለት ቃሊት ሁለ ተጠቅመን እናወግዚሇን፤ ሌጃቸውን፣ ወንዴማቸውን፣ አጎታቸውን፣ ወገናቸውን፣ ወ዗ተ ሊጡት ቤተሰቦች እንዯ እነርሱ እኩሌ ማ዗ን ባንችሌም የአንዱት ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባሌ እንዯ መሆናችን ይህንን መራር ሃ዗ን የራሳችን አዯርገን በመውሰዴ አብረናችሁ እናዜናሇን፤ እናሇቅሳሇን፤ እናነባሇን። በዙህ ሃ዗ን ውስጥ ከፈጣሪ የተሰጠንን የአብሮነት እና የመተባበር መንፈስ በማጎሌበት ሁሊችንም ሃይማኖታችንን፣ የፖሇቲካ አመሇካከታችንን፣ ጾታችንን፣ ዗ራችንን፣ ዕዴሜያችንን፣ ወ዗ተ ሳንመሇከት እንዯ አንዴ ሰብዓዊ ፍጡር ከወገኖቻችን ጋር አብረን እን዗ን፤ እናንባ፤ ከመሰሌ ሰቆቃ የምንሊቀቅበትን እና ዲግም የማናሇቅስበትን መንገዴ በትብብር እንፈሌግ” በማሇት መሌዕክታቸውን አስተሊሌፈዋሌ። በአገር ውስጥ በህወሃት/ኢህአዳግ አማካኝነት ከሚዯርስባቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ስዯት፣ የመሬት ንጥቂያ፣ ጭቆና፣ የ዗ር መዴሌዖ፣ አሰቃቂ ዴህነት፣ ወ዗ተ ወዯ ተሻሇ ኑሮ ፍሇጋ በየአገሩ እንዯ ጨው ዗ር የተበተነው የአገራችን ሕዜብ ባሇፉት ትቂት ሳምንታት ውስጥ በተሇያዩ አገራት የተቀናጀ ጥቃት ሲዯርስበት ቆይቷሌ። በዯቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስዯተኞች ከመዯብዯብ አሌፈው ተገዴሇዋሌ። ሁሇት ኢትዮጵያውያን ጎማ ተዯርጎባቸው በእሣት ተቃጥሇዋሌ፤ ነዴዯዋሌ፤ እነርሱ ጨምሮ በአጠቃሊይ ሶስት መሞታቸው ተነግሯሌ። የዯረሱበት ሇማወቅ ባሇመቻለ እንዯ ሞቱ ሳይቆጠሩ የቀሩ ላልች በርካታ ኢትዮጵያውያን እንዯሚኖሩ መረጃዎች ይጠቁማለ። በቅርቡ እንዯተነገረው የውጭ ፓስፖርት የያ዗ ወይም የዯቡብ አፍሪካ መታወቂያ ካርዴ የላሇው ማንም ሰው አዯጋ ሉገጥመው እንዯሚችሌ በስፋት በመነገሩ በርካታዎች የሚሄደበት ባይኖራውም አገሩን ሇቅቀው ሄዯዋሌ። ከዙህም ላሊ ባሇፈው እሁዴ ከ700 እስከ 950 ስዯተኞችን ከመጠን በሊይ አሳፍራ ከሉቢያ ወዯ ጣሉያን ስትጓዜ የነበረች ጀሌባ ሜዱተራኒያን ባህር በመገሌበጧ እጅግ ብዘዎቹ በውሃው ሰጥመው ሲሞቱ ጥቂቶች እንዯተረፉ ተነግሯሌ። ከሟቾቹ አብዚኛዎቹ ኢትዮጵያውያን እንዯሆኑ በስፋት ይታመናሌ። ባሇፈው ወር በየመን የሚገኙ ወገኖቻችን እዙያ በሚካሄዯው ጦርነት ምክንያት መሄጃ አጥተው በመከራ ውስጥ መሆናቸውን ሰምተናሌ። ከዙህ ባሇፈ መሌኩም የስዯተኛ ካምፓቸው በቦምብ ተዯብዴቧሌ ቁጥራቸው ስንት እንዯሆነ ሇመናገር ባይቻሌም ወገኖቻችን በስዯት ምዴር ህይወታቸው አሌፏሌ። ወዯ መቶ ሺህ የሚጠጉ ወገኖቻችን በዙያ እንዯሚገኙ ሲታመን ከየመን መውጣት የሚፈሌጉት እጅግ በርካታ ቢሆኑም ወዯ ኢትዮጵያ መመሇስ የሚፈሌጉት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው። ይህ መረጃ የጋራ ንቅናቄያችን በዙያ ከሚገኙትና መከራው ከሚዯርስባቸው ጋር በየጊዛው በሚያዯርገው የቅርብ ግንኙነት እነርሱንም በዓሇምአቀፍ ዴርጅቶች ረጂነት ከዙያ ሇማስወጣት በሚያከናውነው ሥራ ያገኘነውና ከራሳቸው ከኢትዮጵያውያኑ የተነገረን ነው። በዙህ ሁለ ቀውስ ውስጥ በሉቢያ የተከሰተው ጭፍጨፋ ከሁለ የበሇጠና በምንም መሇኪያ የማይሰፈር ነው። እንዯ ኢትዮጵያዊነታችን በየጊዛው ከምንሰማውና ከምናየው እጅግ የከፋ በመሆኑ ሃ዗ናችንን የመረረ ያዯርገዋሌ። አረመኔዎቹ ነፍሰበሊዎች ወገኖቻችንን ሲያርደ የተናገሩት ነገር ይህንን የሚያዯርጉት ሇፈሰሰው የሙስሉም ዯም ሇመበቀሌና ኢትዮጵያ የመስቀሌ አገር ስሇሆነች ነው ብሇዋሌ። ሇመቀበሌ ያሌፈሇጉት ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ የሙስሉም፣ የክርስቲያን፣ የአይሁዴ (ፈሊሻ) ዕምነት ተከታዮች በጣምራነት ተጋብተው፣ ወሌዯው፣ ተዋሌዯው፣ የኖሩባት አገር ናት። በዙህም ሇዓመታት በ዗ሇቀው አብሮ የመኖር ህይወት ኢትዮጵውያን በአንዴ አገር ዛግነት ብቻ ሳይሆን በዯምም ተሳስረዋሌ። ከ዗ር፣ ከሃይማኖት፣ ከቋንቋ በሊይ ኢትዮጵያዊነት በሚባሌ ጠንካራ ገመዴ ተገምዯዋሌ፤ በሰንሰሇቱ ሊይሇያዩ ተቆራኝተዋሌ። ሇዙህም ነው ኢትዮጵያውያን ሙስሉሞች ይህንን አሰቃቂ፣ አረመኔና አሸባሪ ተግባር በገሃዴ ወጥተው የኮነኑት፤ ያወገዘት። ንጹሃን በመገዯሊቸው የተሰማቸውን ጥሌቅ ሃ዗ን በኢትዮጵያዊነት ስም ወጥተው ኮንነውታሌ። መግሇጫው በግሌጽ እንዲስቀመጠው የአይሲስ ተግባር “ኢግብረገባዊ፣ ሕገወጥ፣ አረመኔያዊ እና ከዕምነታን ጋር በቀጥታ የሚጋጭ” ነው በማሇት ገሌጸዋሌ። “ስሇዙህ በሉቢያ የኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ግዴያ እጅግ በከረረ መሌኩ የምናወግ዗ው ሲሆን ይህንን በፈጸሙ ሊይ ፍትሕ እንዱበየን እንጠይቃሇን” በማሇት መግሇጫው ዴርጊቱን አውግዞሌ። ስሇዙህ ይህ የአይሲስ የጭከና ተግባር ከሃይማኖት ጋር የተገናኘ ሳይሆን የአምሊክን ሥራ እየፈጸምን ነው በሚሌ ሽፋን የፈጣሪን ሕግ እየጣሱ የራስን ምኞች፣ ስግብግብበት፣ የሥሌጣን ጥማት፣ ጥሊቻ እና የግሌ ጥቅም ማሳዯጃ ጸያፍ ዴርጊት ነው። ሇላልች እነዙህ በግፍ የተገዯለ ወገኖች ቁጥር ሉሆኑ ይችሊለ፤ ሇእኛ ኢትዮጵያውያን ግን ስም፣ ዕዴሜ፣ የሕይወት ታሪክ፣ ማንነት፣ ያሊቸው የራሳችንና የቅርባችን የሆኑ ወንዴሞቻችን ናቸው። አንዲንድቹ እየታወቁ በመሆናቸው የእናቶቻቸው፣ የአባቶቻቸው፣ የእህቶቻቸው፣ የወንዴሞቻቸው፣ ሃ዗ን ቅስማቸውን ሰብሮታሌ። እስካሁን ያሌታወቁም አለ፤ አንዲንድቹም ሳይታወቁ ሉቀሩ ይችሊለ። እነዙህ ወገኖቻችን የተሻሇ ኑሮ ፍሇጋ ከአገራቸው ተሰዯደ፤ ኑሮ ሲዯሊቸው መሌሰው ቤተሰባቸውን ሇመርዲት ዓሊማ አዴርገው፤ አሌመው ከቀዬአቸው ወጡ፤ “የት ዯረሱ” እያለ አብረዋቸው ሲጨነቁ፣ ሲሰቃዩ፣ የነበሩ ቤተሰቦቻቸው ይህንን ዗ግናኝ መሌዕክት ሲሰሙ በህይወታቸው የተፈጠረው ጉዴጓዴ እጅግ ጥሌቅ ብቻ ሳይሆን መዴረሻም የሇውም። ስሇ ወገኖቻቸው እያሰቡ ፍትህን ይመኛለ፤ ግን በዙህ ዗መን ሊያገኙ ይችሊለ። ላሊ የሚፈርዴ ግን አሇ፤ በፍርዴ የማያጓዴሌ፤ መማሇጃን የማይቀበሌ፤ እንዯ ሰው ያሌሆነ! መጽሏፉ እንዱህ ይሊሌ “እግዙአብሔር ሥራን ሁለ የተሰወረውንም ነገር ሁለ፥ መሌካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወዯ ፍርዴ ያመጣዋሌ።” መክብብ12፡14። ላሊው የወገኖቻችን ጭፍጨፋ ኢህአዳግ በሚመራት ኢትዮጵያ እንዯ አንዴ ተራ ዛና መቅረቡ ሃ዗ናችንን ይበሌጥ ያስመረረና ያስከፋ ነው። አናሳ በሆኑት የትግራይ ተወሊጆች ነን በሚለ ቁጥጥር ሥር የሚገኘው ህወሃት/ኢህአዳግ የተጨፈጨፉትን ወገኖቻችንን ጉዲይ ዓሇም እየተነጋገረበት ባሇበት ወቅት “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እናጣራሇን” ማሇቱ ሇብዘዎቻችን ሁሇተኛ ሞት፤ ሁሇተኛ መታረዴ ነበር። እንዱህ ዓይነት በጣም መረን የሇቀቀ ስግብግብነትና ራስወዲዴነት ሥርዓት በሆነባት ኢትዮጵያ መኖር ስሊቃታቸው ነው ወገኖቻችን አገራቸውን ጥሇው የተሰዯደት። ጥቂቶች ሲበሇጽጉ እነርሱ የበዪ ተመሌካች መሆናቸው፣ የሃብት ክፍፍሌና የሥራም ሆነ ማንኛውም ዕዴሌ ሇጥቂቶች የሥርዓቱ አቀንቃኞች በመፈቀደና እነርሱ እንዯ ላሊ ዛጋ በመታየታቸው፤ “አገር እያሇኝ ከላሇኝ ሇምን አገር ፍሇጋ አሌወጣም” በማሇት አገርና ኑሮ ፍሇጋ ወጥተው በበረሃ የቀሩ ናቸው። ማነው ሇዙህ የዲረጋቸው? ከህወሃት/ኢህአዳግ ላሊ ማን ሉሆን ይችሊሌ!? አገራችንን ከሁሇት ዓስርተ ዓመታት በሊይ በመቆጣጠር እየገዚ ያሇው ኢህአዳግ የሚመራው በአናሣዎች መሆኑ ግሌጽ ነው። ሇስሙ “ኢትዮጵያ” የሚሌ በዴርጅቱ መጠሪያ ሊይ በመኖሩ ሁለን ዓቀፍ ሇመሆን ቢጥርም እውነታ ግን ከኢትዮጵያ ሕዜብ ጋር ሲነጻጸር አናሣ በሆነው ህዜባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቁጥጥር ሥር ያሇ ዴርጅት ነው። ከኢትዮጵያ የህዜብ ብዚት አንጻር ትግሬዎች 6በመቶ መወከሊቸው ሇዙህ ጉሌህ ማስረጃ ነው። የማዕከሊዊው ኮሚቴም በአናሳ ትግሬዎች የሚመራ በመሆኑ የአገሪቱ ቁሌፍ ክፍሇ ኢኮኖሚዎች የሚቆጣጠሩትና የሚመሩት እንዱሁም ውሳኔ የሚያስተሊሌፉት እነርሱው ናቸው። ስሇሆነም ኢትዮጵያን እየገዚ ያሇው አናሳው የትግሬ ዴርጅት መሆኑን ይህም ዯግሞ በትግራይ ተወሊጆች ስም የሚነግዴና እወክሇዋሇሁ የሚሇውን ሕዜብ በስሙ የሚያጭበረብር አሸባሪ ዴርጅት እንዯሆነ ታሪኩ ይመሰክራሌ። ዴርጅቱ በበረሃ በነበረበት ወቅት በተሇይ የአሸባሪነት ተግባራት ተሰማርቶ እንዯነበር፤ በረሃብ የሚንገሊቱ የትግራይ ተወሊጆችን የዕርዲታ እህሌ እንዲያገኙ በመንፈግ እና ላልችን እጅግ ሰቅጣጭ የሆኑ ኢሰብዓዊ ተግባራትን በመፈጸም ሇራሱ የፖሇቲካ መጠቀሚያ ማዋለን የቀዴሞ አባሊቱ ብቻ ሳይሆኑ በዓሇምአቀፍ ዯረጃ የተመ዗ገቡ ማስረጃዎች ይመሰክራለ። ይህ የህወሓት አሠራር አሁንም አንዱት ለዓሊዊት አገርን በነጻ አውጭ ስም እየገዚ ባሇበት ወቅትም ቀጥሎሌ። እኩይ ተግባሩን ሇሚዯግፉ ጭፍን ዗ረኞችና ላልች በገን዗ብ ሇተገዘ ሆዴ አዲሪዎች የአገራችንን ሃብት እንዯፈሇጉ እንዱመ዗ብሩ ያሇከሌካይ ፈቅድሊቸዋሌ። ይህንን ሇማጣፋት ላሊውን የኢትዮጵያ ሕዜብ “አገሪቱ በዴርብ አኻዜ ዕዴገት ሊይ ትገኛሇች” በማሇት ቀን ሇላት ራሱ በተቆጣጠረው ሚዱያ ያሇማቋረጥ ይሇፍፋሌ። ሇሚገዚው ሕዜብ ዯንታ የላሇው በመሆኑ በአገራቸው እንዯ ዛጋ መቆጠር ያሌቻለና ተመጣጣኝ የሃብት ክፍፍሌ ዕዴሌ ሇማግኘት ያሌቻለ በአገኙት ቀዲዲ ከኢትዮጵያ መሰዯዴ ቀዲሚ ተግባራቸውና የሕወታቸው ህሌም ከሆነ ቆይቷሌ። የወገኖቻችን መታረዴ እና በጥይት መረሸን በዓሇም ዘሪያ እንዯተሰማ ህወሃት/ኢህአዳግ “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እናጣራሇን” በማሇት የተናገረው እስካሁን የብዘዎችን ስሜት የረበሸና እያንዲንዲችን በቁም ያሳረዯ ጸያፍ ተግባር በመሆኑ ሇአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ያወግ዗ዋሌ፤ ይኮንነዋሌ። ሆኖም ራሱ አሸባሪ የሆነው ህወሃት/ኢህአዳግ የሕዜብ ቁጣ እያየሇ ሲመጣ የዛናውን መንፈስ በመቀየር “አሸባሪነትን እዋጋሇሁ፤ አወግዚሇሁ” በማሇት ቢሇፍፍም ያቆሰሇውንና ያዯማውን የህዜብ ሌብ ሉጠግን አሌቻሇም፤ አይችሌምም! ጋዛጠኞችን፣ የፖሇቲካ ተቀናቃኞቹን፣ የሃይማኖት መሪዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ ወ዗ተ ያሇ አንዲች ጭብጥ እና ማስረጃ እስርቤት በመወርወር አገሪቱን ወዯ ከፍተኛ እስርቤትነት የቀየረው ኢህአዳግ በዙህ ተግባሩ ብቻ ሳይሆን ንጹሃንን በማሰቃየት፣ ከአገር እንዱሰዯደ በማዴረግ፣ ከመኖሪያቸው በማፈናቀሌ፣ በመግዯሌ፣ ወ዗ተ ተግባራት “ዜነኝነትን” የተረፈው ህወሃት/ኢህአዳግ በጥቅም በሚዯሌሊቸው ጥቂቶች አማካኝነት ገጹን ሇማስተካከሌ ቢሞክርም የአሜሪካው ውጭ ጉዲይ ሚ/ር መ/ቤት በኢዳሞክራሲያዊነቱና በመብት ረገጣው ሊይ ያወጣበት ዗ገባ በራሱ ምስክር ነው። አቶ ኦባንግ ከዙህ ጋር በተያያ዗ በተሇይ ሰሞኑን የአሜሪካው ውጭ ጉዲይ መ/ቤት (ስቴት ዱፓርትመንት) አራተኛ ባሇሥሌጣን በሆኑት ዌንዱ ሸርማን አስተያየት ዘሪ የኢትዮጵያውያን መቆጣታቸውን አስመሌክቶ ሲናገሩ “ኢትዮጵያውያን በሳውዱ አረቢያ፣ በሉባኖስ፣ በየመን፣ በኬኒያ፣ በማሌታ፣ በዯቡብ አፍሪካ፣ በግብጽ፣ በሱዲን፣ በዑጋንዲ፣ ወ዗ተ ከፍተኛ ስቃይ የሚዯርስባቸው እንዯው በአጋጣሚ አይዯሇም፤ ምናሌባት በርካታዎች ይህንን የወገኖቻችን ሰቆቃ በተዯጋጋሚ ከመስማት የተነሳ ሉሰሇቻቸው ይችሊሌ፤ ሆኖም ግን እንዯ ዌንዱ ሸርማን ሇጆሮ የሚከብዴ ጭፍን አስተያየት ቢሰማም ግፉና መከራው ግን ሇእኛ አዱስ ነገራችን አይዯሇም፤ “በዖጋዳን በህወሃት/ኢህአዳግ ነፍጥ አንጋቢዎች የተፈጸመው እጅግ ሰቅጣጭና ዗ግናኝ የ዗ር ማጥፋት ወንጀሌ፤ በአማራ ክሌሌ እየተካሄዯ ያሇው ስሌታዊ ጭፍጨፋና የወገን ምክነት፤ በ424 አኙዋኮች ሊይ የተፈጸመው ግዴያና ዗ር ማጥፋት፤ የ1997ቱ ምርጫ ተከትል በአዱስ አበባ ብቻ በ197 ወገኖቻችን ሊይ የተፈጸመው ግዴያ፤ ሇቁጥር የሚያታክቱ ኦሮሞ ወገኖቻችን በየጊዛው መገዯሊቸውና እስርቤቱን ማጣበባቸው፤ በአፋር ሕዜብ ሊይ የሚዯርሰው የማያቋርጥ ግፍ፤ በእያንዲንደ የአገራችን ክሌሌ በወገናችን ሊይ የሚዯርሰው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ስንቱን ቆጥረን ሌን዗ሌቀው እንችሊሇን። በአይሲስ ከተገዯለት አንደ ወገናችን ህወሃት/ኢህአዳግ ኦሮሞዎችን ከአዱስ አበባ ዘሪያ በሚያፈናቅሌበት ወቅት ተቃውሞውን ያሰማና የተማሪዎች መሪ የነበረ ሲሆን በዙህ ተግባሩ እንዯሚታሰር በሚያውቅበት ጊዛ አገር ጥል የወጣ ነው። ስሇዙህ እውነተኛው የአገር ውስጥ አይሲስ ህወሃት/ኢህአዳግ ካሌሆነ በስተቀር ማን ሉሆን ይችሊሌ በማሇት ብዘዎች ሇጋራ ንቅናቄያችን ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ መሌዕክቶች በመሊክ ምሬታቸውን እየገሇጹ ነው” በማሇት አስተያየታቸውን ሰጥተዋሌ። “ሟቾቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እየመረመርኩ ነው” በማሇት በሞቱት ወገኖቻችን ሊይ ሲያሊግጥ የነበረው ህወሃት/ኢህአዳግ ሁኔታው አሊምር ሲሇው ሶስት ቀን የሃ዗ን አዋጅ አወጀ። ዴርጊቱ የሇበጣ እንዯሆነ እና በግዳሇሽነት የተዯረገ ሇመሆኑ አንደ ማስረጃ ራሱ በተቆጣጠረው 547 ወንበር ባሇው ፓርሊማ ጉዲዩ ቀርቦ ሲታወጅ የተገኙት 300 አካባቢ የሚሆኑ የፓርሊማ አባሊት ወይም 56በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። ላልቹ የት ሄደ? ጉዲዩ አይመሇከታቸውም? “በሌማት ሥራ ተጠምዯው” ነው? ሟቾቹ ወገኖቻቸው ስሊሌሆኑ ይሆን? ወይስ የሟቾቹ ጉዲይ በክሌሌ የሚታይ ይሆን? ወይስ የ30 ወገኖች ህሌፈት የአንዴ ሟች ጠ/ሚ/ር ህሌፈት ጋር የሚወዲዯር አይዯሇም? ሕዜብ እስኪበቃው ታዜቧሌ፤ ጉዲዩንም መዜግቧሌ!! ይህ ብቻ አይዯሇም ሃ዗ኑን እንዱገሌጽ የተጠራው ሕዜብ ህወሃት/ኢህአዳግ ኢትዮጵያውያን ከእምነታቸውና ከባህሊቸው ውጭ እንዳት ሃ዗ናቸውን መግሇጽ እንዲሇባቸውና ማ዗ን እንዲሇባቸው “ንቃት” ሇመስጠት የሞከረበት እንዯሆነ ሇማየት ችሇናሌ። ሇመሇስ ዛናዊ በየመንገደ፣ በየቱቦውና በየተገኘበት ቦታ እንዱሇቀስ ፈቃዴ ሲሰጥ፤ ሲዯሰኮር፣ ሲተወን፣ ወ዗ተ አሁን ሇምን ተከሇከሇ? ሇምንስ ሇቅሶ በትዕዚዜ ሆነ? ይህ በእውነት እጅግ የ዗ቀጠ የህወሃት/ኢህአዳግ ጸያፍ ተግባር ነው። ሰሌፈኛውም ሇዙህ ነው “መንግሥት የላሇው እዙህ ብቻ ነው” በማሇት ምሬቱ የገሇጸው፡፡ ከአገራቸው የሚሰዯደትን “ህገወጥ” በማሇት ሇመጥራት ምንም የማይጨንቀው ህወሃት/ኢህአዳግ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎችን ዛጎች አገር ጥሇው እንዲይሰዯደ እንዱመክሩ ትዕዚዜ እየሰጠ እንዯሆነ ተሰምቷሌ። ካሌሆነ ቀዴሞውኑ “ህገወጥ” ይሊቸው እንዯነበር አሁን ዯግሞ ሇሞታቸው ተጠያቂው ራሳቸው መሆናቸውን የሃይማኖት መሪዎች እያስጠነቀቁ እንዱነግሩ ተጽዕኖ እያዯረገ ነው። በመሠረቱ የሃይማኖት መሪዎች የዕምነታቸው ቀኖና በሚያስተምረው መሠረት ሃይማኖታቸውን መከተሌ እንዱችለ ነጻነት ሉሰጣቸው ይገባሌ። እውነትን እንዱናገሩ፤ ግብረገብነትን ያሇፍርሃት እንዱያስተምሩ፤ ሕዜቡን ሃይማኖታዊ መብቱን እንዱያስተምሩ ነጻ መሆን ይገባቸዋሌ። ችግሩ ያሇው ህወሃት በሚከተሇው እኩይና ኢግብረገባዊ ሥርዓት መሆኑን ያሇፍርሃት ያመኑበትን በጨዋነት እንዱያስተምሩ፤ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍሌ ሉኖር እንዯሚገባ፤ ፍትሕ በሚገባ መበየን እንዲሇበት፣ ፈጣሪ ሁለንም በማያዲሊ የፍርዴ ወንበር ፊት እንዯሚያቀርብና ቀኑን ጠብቆ ፍጹም ፍርዴን እንዯሚሰጥ፣ ሃብት፣ ወርቅና ዜና እንዱሁም የሃሰት እንባ በዙያ የፍርዴ ቀን ሉያስጥለ እንዯማይችለ፤ አገር ማሇት ክቡር መሆኗን፤ የአባቶችና ቅዴመ አያቶች አጥንትና ዯም አገራችንን እንዲስከበሯት ሁለ አሁን ጥቂቶች የሚፈነጩባት ሳትሆን የሁለም መሆኗን፤ ብሌግና፣ ዋሌጌነት፣ በሥሌጣን መባሇግ፣ ስግብግብበት፣ ዗ረኝነት፣ ራስ ወዲዴነት፣ ጥሊቻ፣ ጭከና፣ ወ዗ተ እኩይ ተግባራት መሆናቸውን በመግሇጽ ሕዜቡን ግብረገባዊነት እንዱስተምሩ ፍጹም ነጻነት ሉሰጣቸው ይገባሌ እንጂ የህወሃት/ኢህአዳግ የፖሇቲካ መጠቀሚያ ሉሆኑ ፈጽሞ አይገባም። እስካሁንም በመሆን ራሳቸውንና ኅሉናቸውን የሸጡ የሃይማኖት መሪዎች ከዙህ እጅግ እርኩስና ጸያፍ ተግባራቸው መታቀብ፤ ካስፈሇገም እንዯ ቀዴሞ አባቶቻቸው የሰማዓትነት ጽዋ በመጠጣት አርአያ መሆን ካሌቻለም ሇእውነት ሲለ ከያዘት የኃሊፊነት ቦታ በራሳቸው ፈቃዴ ሉነሱ ይገባቸዋሌ። ይህ ብቻ አይዯሇም የራሱን የሚሰነፍጥ ቁሻሻ ሇመሸፈን የሚጥረው ህወሃት/ኢህአዳግ ሰው አስተሊሊፊዎችን ሇዙህ ተግባር ሇመወጀሌም ይፈሌጋሌ። አቶ ኦባንግ በዙህ ጉዲይ ሊይ ሲናገሩ፤ “እርግጥ ነው ሰው አስተሊፊዎች ራሳቸውን ሇአዯጋ ባጋሇጡ ወገኖች ሊይ የራሳቸውን ጥቅም እንዯሚያሳዴደ ይታወቃሌ፤ ግን ዋናው የችግሩ ሥር ምንዴነው? ሇምንዴነው ይህንን ዓይነት አዯጋ እያሇ እጅግ በርካታ ዛጎች ከአገራቸው አሁንም የሚሰዯደት? ህወሃት/ኢህአዳግ ችግሩን ወዯላሊ ሇማሊከክ ከመሞከሩ በፊት ራሱን በመስታወት ሉያይ ይገባዋሌ፤ እንዱያውም ከአንዲንዴ ዗ገባዎች ሇመረዲት እንዯቻሌነው በዙህ ዛጎችን ሇአዯጋና ሇሞት በሚዯርስ ህገወጥ የሰው ማስተሊሇፍ ንግዴ ውስጥ የህወሃት/ኢህአዳግ ጥቅመኞች እንዲለ ማስረጃዎች አለ” በማሇት አስተያየታቸውን ሰጥተዋሌ። ኢህአዳግ የመረጃ አፈና ሉያዯርግ ቢሞክርም በተሇያዩ የዛና አቀባዮች በግሌጽ እንዯታየው ሕዜባችን ሏ዗ኑን በነቂስ በመውጣት ገሌጾዋሌ። ከዙህ ጋር በተያያ዗ አቶ ኦባንግ ሲናገሩ፤ “ሌክ በመጽሏፍ ቅደስ ሊይ እንዯተመሇከተው መሌካሙ ሳምራዊ ሃይማኖትን፣ ዗ርን፣ ጎሣን፣ የፖሇቲካ አመሇካከትን፣ ወ዗ተ ሳይመሇከት መንገዴ ሊይ ተ዗ርሮ ሇነበረው ወገን ሰብዓዊነት አነሳስቶት ዕርዲታውን እንዯሇገሠ ሁለ የጋራ ንቅናቄያችን የማንንም ጎሣ፣ ዗ር፣ ሃይማኖት፣ ወ዗ተ ሳንመሇከት ዕርዲታ መሇገስ በሚገባን ቦታ ሁለ ፈቃዯኝነታችንን ማሳየት እንዲሇብን ያምናሌ፤ ኢትዮጵያውያን ዯግሞ በዙህ የታወቅን ብቻ ሳንሆን በተግባርም የምንፈጽም መሆናችንን በተዯጋጋሚ እንዲሳየነው ሁለ አሁንም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኘው ወገን ሁለ ከእኛ ሇተሇዩን ወገኖች ያሳየው የሃ዗ን ትብብር የሁሊችንንም ስሜት የነካ ነው፤ ይህም ዯግሞ ማንም የፈሇገውን ያህሌ ኢትዮጵያዊነትን ሇማፍረስ ቢሞክር፤ የፈሇገውን ቢጥር እንዯማይሳካሇት ያረጋገጠ ተግባር ነው፤ ኢህአዳግም ከዙህ ሉማር የሚገባው ታሊቅ ትምህርት ቢኖር ሇ25 ዓመታት አፈረስኩ ብል ያሰበው ኢትዮጵያዊነት የተዲከመ ቢመስሌም ፈጽሞ እንዯማይፈርስ፤ መሠረቱም የጸና፤ አዱሱ ትውሌዴ እንኳን ሳይቀር በጽናት የሚጠብቀው እንዯሆነ ነው። ከዙህ አንጻር የህወሃት/ኢህአዳግ የ዗ር ፖሇቲካ መርዜ እንዲሌሰራ ይበሌጡንም የከሰረ መሆኑን ያረጋገጠ ሃቅ ነው። “ስሇዙህ የእነዙህ ወገኖቻችን ዕሌፈት ሁሊችንንም በአንዴነት ሉያስተሳስረን የሚገባ መሆን አሇበት፤ ሌዩነቶቻችንን በመከባበር የምንመሇከትበትና ኢትዮጵያዊነታችን ከምንም በሊይ እንዯሆነ የምናሳይበት ሉሆን ያስፈሌጋሌ፤ እንዱህ ባሇው ኅብረት ሇወገኖቻችን መሰዯዴና መከራ ማየት ምክንያት የሆነውን ሁለ የመታገሌ ኃሊፊነት የእያንዲንዲችን ነው፤ በየአረብ አገራትና በየቦታው በስዯት እንዱሁም በላሊ ምክንያት ወገኖቻችን እስከመቼ እያሇቁ ይኖራለ? ይህንን የማስቆምና ዲግም በወገኖቻችን ሊይ እንዲይዯርስ የማዴረግ ሃሊፊነት ያሇው በህወሃት/ኢህአዳግ እጅ ሳይሆን በእያንዲንዲችን ዗ንዴ ነው፤ መብታችን በማንም የሚሰጠን ወይም እየተቆጠበ የሚሰፈርሌን ሳይሆን ስንወሇዴ አብሮን የተወሇዯና ከፈጣሪ የተሰጠን የማይገሰስ፣ የማይሻር፣ የማይሇወጥ፣ የማይነካ ነው፤ ስሇዙህ አስቀዴመን በማንም የማይገሰሰውን መብታችንን እንወቅ ከዙያም እናስከብር ቀጥልም በተግባር እናውሇው ሇላልችም አርአያ እንሁን” በማሇት አቶ ኦባንግ ሇኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተሊሌፈዋሌ። ሇአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ እነዙህን ህይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ያሇፈውንም ሆነ ከዙህ በፊት በህወሃት/ኢህአዳግ እኩይ ተግባር ህይወታቸውን ያጡትን ወገኖቻችን ሁሌጊዛ ሲያስታውስ፣ ሲ዗ክር ይኖራሌ። ሇቤተሰብና ወዲጆቻቸው ሁለ ከፈጣሪ ዗ንዴ መጽናናትን ይመኛሌ። ሁሌጊዛ ግን በሃ዗ንና በቁ዗ማ ብቻ አንኖርም፤ ይህ የሚያበቃበት ዗መን እንዱመጣ ከምንጊዛውም በበሇጠ ይሰራሌ፤ አንገታችንን ዯፍተን ሳይሆን አባቶቻችን ባጎናጸፉን ነጻነት እንዯገና እኛም ይህንን ነጻነት ሇወጪው ትውሌዴ የምናስተሊሌፍበት አዱስ ኢትዮጵያ እንዴትመሠረት ተግባሩን በትጋት ማከናወኑን ይቀጥሊሌ። ዓሊማውን የሚዯግፉ ሁለ ከጎኑ እንዱቆሙ በዴጋሚ ጥሪ ያቀርባሌ። የሃይማኖት መሪዎች ህዜባችንን በማጽናናት ብቻ ሳይሆን ሞራለንም ከፍ በማዴረግ የሚጠበቅባችሁን ተግባር እንዴትፈጽሙ የጋራ ንቅናቄያችን ጥሪ ያዯርጋሌ። ያሊችሁ ኃሊፊነት በሰውና በፈጣሪ መካከሌ ያሇ በመሆኑ በሁሇቱም ተጠያቂ መሆናችሁን አውቃችሁ እውነትን በትጋት በመስበክ የህዜባችንን መንፈስ ወዯ ሊቀ ዯረጃ የማዴረስ አምሊካዊ ግዳታ አሇባችሁ። የወሰዲችሁት ስምና “ማዕረግ” የሹመት ወይም ራስን ከፍ የማዴረጊያ እንዲሌሆነ ከእኛ በሊይ እንዯምታውቁት ሁለ ሇተሰጣችሁ ስም ኑሩ! ኃሊፊነታችሁ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑን የምትከተለት የተቀዯሰ መጽሏፍ ተግባራዊ ምሳላ እየሰጠ የሚያስተምር መሆኑን እንዯምታውቁት ሁለ ታሪካቸውን እንዯምታነቧቸውና እንዯምትሰብኳቸው የሃይማኖት አባቶች የሰማዕትነት ህይወት መኖርን በቃሌ ብቻ ሳይሆን በተግባር እንዴትፈጽሙ የጋራ ንቅናቄያችን በጥብቅ ያሳስባሌ። ይህም የግዴ ህይወትን መሰዋት ሊይሆን ይችሊሌ፤ መስዋዕትነት ከትንሽ የሚጀምርና በየዕሇቱ የሚያጋጥም የግሌ ጥቅምን ከመሰዋት የሚጀምር መሆኑን በውሌ ትረደታሊችሁ ብሇን እናምናሇን። የሃይማኖት አባቶች የሚያስተምሩት መንገዴ ከማንኛውም የፖሇቲካ ፓርቲም ሆነ ዴርጅት መርሃግብር ፍጹም የሊቀ እንዯመሆኑ የህዜባችንን የመንፈስ ሌዕሌና ከፍ የሚያዯርገውና ከፈጣሪ ሇተሰጠው መብቱ በጽናት እንዱቆም የሚያዯርገው እንዯሆነ ሇአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ያምናሌ። ስሇሆነም ሁሊችንም በዙህ ሃ዗ን ተቆጭተን ብቻ ሳንቀር ይሌቁንም በህዜባችን መካከሌ ሰሊም ፈጣሪዎች፣ ዕርቅ መስራቾች፣ ስምምነት አዴራጊዎች ሆነን በትጋት መስራት አሇብን። ይህ ካሌሆነ እና ሁሊችንም ነጻ ካሌወጣን ማናችንም ሇብቻችን ነጻ መሆን አንችሌም። መውዯቃችንም ሆነ መነሳታችን እርስበርሱ የተገመዯና የተሳሰረ ነው። አሁንም በአዯጋ ሊይ ያለትን ወገኖቻችንን አምሊክ እንዱታዯጋቸው እንመኛሇን፤ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚዯርስብንን ግፍና መከራ ተመሌክቶ ሰሊምን እና ዕረፍትን የምናገኝበትን ዗መን ያቅርብሌን። ሁሊችንንም በትጋት ሇመሥራት እንዴንችሌ ጽናቱ ይስጠን። በዴጋሚ ሇወገኖቻችን እና ሇቤተሰቦቻቸው፣ ወዲጅ ዗መድቻቸው ከፈጣሪ ዗ንዴ መጽናናትን እንመኝሊቸዋሇን። ኢትዮጵያችን ሇሁሊችንም ትኑርሌን!! ሇተጨማሪ መረጃ የአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዲይሬክተር ኦባንግ ሜቶን በዙህ ኢሜይሌ አዴራሻ ማግኘት ይቻሊሌ፡- Obang@solidaritymovement.org

Sunday 26 April 2015

“የምንታረድበት ቀን ደርሷል፣ ጓደኞቻችን ታረዱ፤ እኛም አሁን ተራችንን እየጠበቅን ነው”

ሰሞኑን በሊቢያ በኢትዮጵያኖች ላይ የደረሰው አረመኔያዊ ድርጊት ሁላችንንም መሪር ሃዘን ውስጥ ከቶናል። እንቅልፍ ነስቶናል። መደበኛ ስራችንን ሳይቀር ማከናወን ተስኖናል። ምክንያቱም ድርጊቱ በሰው ልጅ ላይ ሊደረግ ቀርቶ የማይታሰብ ሰይጣናዊ ድርጊት ነውና። በህይወት የሚገኙትን ከዚህ አሸባሪ ሰይጣናዊ ቡድን ማዳን አለመቻላችን ደግሞ ሃዘናችንን እጥፍ ድርብ አድርጎብናል። በሰማዕትነት ላለፉት ክርስቲያን ወንድሞቻችን አንብተናል፣ አልቅሰናል፣ ውስጣችን ደምቷል፤ እኛም እንደ እነሱ በመንፈስ ታርደናል።
ብዙዎች በተለያየ መልኩ ሐዘናቸውን እየገለጹ ነው። ለዚህ ያበቃንን መንግስት ነኝ ባዩን በመኮነን ላይም እንገኛለን። ለብዙዎች የስደት ዋናው ምክንያት የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መሆኑ የታወቀና የተረጋገጠ ነው። በመተባበር ለአገርና ለህዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔን ማሶገድ  ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን እንደሚገባም ብዙዎቻችን እንስማማለን።
እስከዛው ግን በስቃይና በመከራ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን በሚቻለው ሁሉ መታደግ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው ብዬ አምናለሁ።
ዛሬ በቅርብ ከማውቀው ሰው ከሊቢያ በቫይበር መልእክት ደረሰኝ። ስደውልለት ማናገር እንደማይችል መልእክት ላከልኝ።  ፎቶግራፉን ሲልክልኝ ማመን አቃተኝ። እጅግ በጣም ተጎሳቁሏል፣ የሐዘን ስሜት ይነበብበታል። እኔም የት እንዳለ እና በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ጠየኩት። ተስፋ በቆርጠ አነጋገር “የምንታረድበት ቀን ደርሷል፣ ጓደኞቻችን ታረዱ፤ እኛም አሁን ተራችንን እየጠበቅን ነው” አለኝ። እጅግ ከባድና አስቸጋሪ ነው ማጽናናት እንኳ የማይቻልበት ወቅት። እኔም ግራ ገባኝ እንደማነኛውም ሰው ሐዘን ተሰማኝ ይበልጥ ደግሞ  ምንም ማድረግ አለመቻሌን ሳስበው።
37 ኢትዮጵያውያን በአንድ ጠባብ ቤት በሊቢያ እና ሱዳን ጠረፍ ደንጉላ በምትባል ስፍራ ታስረው እንዳሉ ገለጸልኝ። ሊወጡ የሚችሉበት መንገድ  እንዳለም ጠየኩት፤ ለእያንዳንዳችን 2000 የሱዳን ገንዘብ መክፈል ከተቻለ የመለቀቅ እድል እንዳላቸው ነገረኝ። ያን መክፈል ካልተቻለ ግን ለአይ ኤስ አይ ኤስISIS) አሳልፈው እንደሚሰጧቸው አስረዳኝ። ብዙ ኢትዮጵያውያን ጓደኞቻቸው በዚህ መልኩ እንዳለቁ ነገረኝ። እንዴትና በምን መልኩ ገንዘብ ሊደርሳቸው እንደሚችል ጠየኩት፤ ሱዳን በሚገኝ ደላላ አማካኝነት ለአሳሪዎቹ ገንዘቡ ሊደርሳቸው ይችላል አለኝ። የደላላይ ስልክም ተቀብዬ ደጋግሜ  ብደውልም ላገኘው  አልቻልኩም። አማራጭ ስልክ እንዲሰጠኝ በጠየኩት መሰረት በደላላው የቅርብ ጓደኛ ደጋግሜ ደውዬ ሳናግረው ገንዘብ መክፈል ከተቻለ እንዲለቀቁ እና ወደ ሱዳን እንዲመለሱ  ማድረግ እንደሚቻል አረጋገጠልኝ።
ይህን መረጃ ለኢሳት ለማስተላለፍ ወደ ዲሲ ስቲዲዮ ደጋግሜ ደወልኩ ግን የስራ ቀን ባለመሆኑ ስልኩ ሊነሳልኝ አልቻለም። አሁን ብቸኛ አማራጭ ሁኖ  ያገኘሁት ይህን መረጃ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ለኢትዮጵያውያን ማድረስ  ነው።
ውድ ኢትዮጵያውያን፦ በሰማዕትነት የተሰውትን ነፍሳቸውን በክብር ከቅዱሳን ጋር ይደምርልን እኛንም አምላከ ቅዱሳን መጽናናቱን ይስጠን ከማለት ውጭ ምንም ማድረግ አንችልም። ስለዚህ በሞትና በህይወት መካከል በብዙ ስቃይና መከራ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን በሚቻለን አቅም እንድረስላቸው። የሰው ደም ከጠማው አረመኔና ጨካኝ አይ ኤስ አይ ኤስ አሸባሪ ቡድን እንታደጋቸው። ቢያንስ አንድ ንጹህ  ሰው ማትረፍ ለህሌናችን ትልቅ እረፍት እናገኛለን።
ወገኖቼ ምን እናድርግ??? እርዳታችንን በግል ከምናደርገው በህብረትና በመመካከር ቢሆን ብዙ ነፍስ ማድን እንችላለን በማለት ወደ እናንተ  ማድረሱን ወደድኩ።
አስፈላጊ መረጃዎቹንስልክ ቁጥሮችንእርዳታ ለማድረግ ለሚፈልግ ሁሉ እሰጣለሁ።  ለቤተሰብ እና ለአንዳንድ ጥንቃቄዎች ሲባል ስልክ ቁጥርና ፎቶ ግራፉን እዚህ ላይ ከማውጣት ተቆጥቢያለሁ።

ይበልጣል 
http://yibeltalethiopia.blogspot.no/2015/04/blog-post.html

Thursday 23 April 2015

ኢትዮጵያኖቹ በ ISIS ሲገደሉ በግድ እንዲያይ የተደረገው ታዳጊ ህፃን


አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2007(ኤፍ.ቢ.ሲ) የ16 ዓመቱ ኤርትራዊ ስደተኛ ናኤል ጎይቶም የኤይ ኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያውያኑን እና ኤርትራውያኑን በግፍ ሲቀሉ እና ሲረሸኑ እንዲመለከት መደረጉን ይናገራል።

ታዳጊው ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ ከተሰኘው ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደተናገረው፥ ታጣቂው የአይ ኤስ ቡድን ይህን አሰቃቂ ድርጊት አስገድዶ እንዲመለከት አድርጎታል።

ይህ አሰቃቂ ድርጊት ከተከናወነ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከሌሎች አራት ኤርትራውያን ጋር በሊቢያ ታስረውበት ከነበረው ካምፕ ማምለጣቸውንም ተናግሯል።

በእዚህ አረመኔ ቡድን ከመቀላት ለማመለጥ መሞከር አዋጭ መሆኑን የተናገረው ናኤል፥ ከቡድኑ ካምፕ ካመለጡ በኋላ እርዳታ የሚያገኙበት ስፍራ እስኪደርሱ ድረስ ለአራት ቀናት ያህል በሊቢያ በረሃ ውስጥ መጓዛቸውን ይተርካል።

ከአንድ ወር ለሚበልጥ ጊዜ በፅንፈኛው አይ ኤስ ቁጥጥር ስር በነበሩበት ወቅትም “ከመሞት እና እስልምናን ከመቀበል የቱን ትመርጣላችሁ”? የሚል ምርጫ እንደተቀመጠላቸው እና በወቅቱ ሙስሊም መሆንን እንደሚመርጡ እና እንዋጋላችኋለን ሲሉ መናገራቸውንም ያስታውሳል ታዳጊው።

ናኤል ኢትዮጵያውያኑ እና ኤርትራውያኑ በአይ ኤሴስ ከተያዙ በኋላ በአንድ ትልቅ ጉድጓድ መቀመጣቸውንም ተናግሯል ።

ከእለታት በአንዱ ቀንም 47 ያህል ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን ጥቋቁር እና ብርቱካናማ ልብሶችን አልብሰው ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ እንዲሁም ሊቢያ በረሃ እንደወሰዷቸው እና እሱም ይህን ይመለከት ዘንድ አብሯቸው እንደወሰዱት ከዚያም ይህን ጭካኔ የተመላበት ድርጊት እንዲመለከት መደረጉንም ይናገራል።

ታዳጊው በአይ ኤስ እንዴት ተያዘ?

ናኤል እንዴት በፅንፈኛው የአይ ኤስ እጅ እንደተያዘም ያብራራ ሲሆን፥ 10 ኤርትራውያን ሴቶችን እና 8 ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 61 ከሚሆኑ ስደተኞች ጋር ከአንድ ወር በፊት በሱዳን አድርግው ደቡብ ሊቢያን ሲያቋርጡ በአይ ኤስ ታጣቂዎች መያዛቸውን እና ሀይማኖት ነክ ጥያቄዎች መጠየቃቸውን ያስታውሳል።

ከመካከላችሁ ማን ነው ሙስሊም? ብለው እንደጠየቋቸው ነገር ግን ክርስቲያን የሆንነው መስቀል እና ክርስቲያን መሆናችንን የሚያሳዩ መንፈሳዊ ምስሎችን በመያዛችን በወቅቱ ማንነታቸንን መደበቅ አላስቻለንም ብሏል።

በአይ ኤስ ካምፕ ውስጥ ከ300 እስከ 400 የሚሆኑ የፅንፈኛው ቡድን አባላት የሚገኙ ሲሆን፥ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ተይዘው በካምፑ ውስጥ እንዲገቡ ሲደረግ፣ ሶማሊያውያን ግን መሄድ ወደፈለጉበት እንዲጓዙ ይፈቀድላቸው እንደነበር ይተርካል።

ናኤል ኤይ ኤስን አስቀድመው የተቀላቀሉ እና ለሽብር ቡድኑ የሚዋጉ ሶስት ኤርትራውያን የነበሩ ሲሆን፥ እነሱ ይረዱናል ብለን ስንጠብ ግን ስለኛ ምንም ስሜት አልተሰማቸውም ሲል ታሪኩን ያወጋል።

ናኤልን ጨምሮ ዮሃንስ መብራቱ፣ ቶማስ ገብረህይወት፣ አብርሃም ናይዝጊ፣ አማን ሺሻይ የተሰኙ ታዳጊ ኤርትራውያንም ከአይ ኤስ ካመለጡ እና ከአራት ቀናት አድካሚ የበረሃ ጉዞ በኋላ አንድ ሱዳናዊ አግኝቷቸው በሰሃራ በረሃ በርካታ ስደተኞች ወደሚገኙበት የስደተኞች መጠለያ እንዳደረሳቸው ገልጿል።

ታዳጊው ህይወቱን ማትረፍ ቢችልም ባየው እና በደረሰበት መከራ እና እንግልት ሳቢያ ውስጡ መጎዳቱን ነው የተናገረው።

አይ ኤስ ከ30 ደቂቃ በማያንስ የተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በአለም ዙሪያ ባሰራጨው መልዕክቱ 30 ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ንፁሃን ዜጎችን ገሚሱን በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ ሲቀላ፥ ገሚሱን ደግሞ በሊቢያ በረሃ በጥይት በመተኮስ ሲገድል ማሳየቱ ይታወሳል።
ምንጭ፦ http://www.ibtimes.co.uk

የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ

የተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።
ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች ስብዕናችንን ገፈፉን።
የዘመኑ ጥቂት የህወሓት ቱጃሮች ፎቆችን እየገነቡ በነሱ መጥገብ እኛ እንድናገሳላቸው ይፈልጋሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መራቡ፣ መታረዙ፣ መደህየቱ እውነት ነው፤ ሆኖም ግን “ተራብኩ”፣ “ታረዝኩ”፣ “ደኸየሁ” ብሎ መናገር አይችልም። እውነት መናገር ያስቀጣል፣ ያስወነጅላል። በፍርደ ገምድል ችሎት እውነት መናገር “ሽብርተኛ” ያስብላል። እስር ቤቶችን የተሞሉት ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለነፃናትና ለእኩልነት በቆሙ ሰዎች አይደለምን?
በአይ ሲስ ያሳረደን ማነው? መልሱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው። እንደ አገርና እንደ ሕዝብ የደረሰብን ውርደት የትም ብንሄድ የምናመልጠው አልሆነም። በአገር ውስጥ የደረሰብንን ውርደት ለማምለጥ ስንሰደድ ውርደት ተከትሎን ይመጣል።
ወገኖቼ፤ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ሊኖረን አይችልም። ዛሬ የመሸሻ ጊዜ አይደለም። አገራችንን ከወያኔ ነጥቀን፤ በአገራችን ኮርተን በሰላም መኖር እንሻለን። ይህ መብታችን ነው። አገራችን የኛ ነች። አገራችን የጥቂት ወያኔዎች መፈንጫ አይደለችም።
ወገኔ፤ ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም በአርበኖች ግንቦት 7 ስም የማደርግልህ ጥሪ አድምጠኝ። በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በጾታ ልዩነት ሳታደርግ ዛሬ በአንድነት እንደተሳህ አንድነትህን እንደጠበቅህ ቀጥል። አንድነትህን ለመሸርሸር ወያኔ የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም፤ ለወያኔ ዱለታ ጆሮህን አትስጥ። የወያኔ አገዛዝ እንዲያበቃ በአንድነት ተነስ። ዛሬ የጀመርከው ትግል እዳር ሳይደርስ እረፍት የለንም።
አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር በመጣመር የአገር አድን ኃይል የመገንባት ሥራውን እያጠናቀቀ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት ሳንከፋፈል፤ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ባካተተ ስብስብ ውስጥ አብረን ህወሓትን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የአንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ነው። የትግሉም የአገሪቷም ባለቤት አንተ ነህ። ስለሆነም ተነስ! “እንቢኝ” በል። ዘርፈ ብዙ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ወያኔን አዳክም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በትግልህ ፍሬ የአገርህ ባለቤት ሁን።
የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። የደረሰብንን ብሔራዊ ውርደት እያያችሁ፤ እሮሮዓችን እየሰማችሁ በሕዝብ ላይ መተኮስ በራሳችሁ ጭንቅላት ላይ መተኮስ ማለት መሆኑን ለደቂቃ እንኳን አትዘንጉ። ይልቁኑ ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ የወጣትነት የፈጠራ ችሎቻችሁ መፈተኛው አሁን ነው። ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ መመሪያ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ። እያሰላችሁ፣ እያጠናችሁ፣ እያደባችሁ፣ ወያኔን ታገሉ።
የታፈረች፣ የተከበረችና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።


ብርሀኑ ነጋ
የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር
ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም

Monday 6 April 2015

ከአርበኞች ግንቦት 7 ለወጣቱ ከወጣቱ አጠር ያለ መልዕክት፡፡ ይህንን መልዕክት ሸር በማድረግ ይተባበሩን

ከአርበኞች ግንቦት 7 ለወጣቱ ከወጣቱ አጠር ያለ መልዕክት፡፡ ይህንን መልዕክት ሸር በማድረግ ይተባበሩን

Saturday 4 April 2015

የት ሂዱ ነው? (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

መስፍን ወልደ ማርያም (አዲስ አበባ)
ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን ‹‹የሙጢኝ!›› ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን ‹‹የሙጢኝ!›› እንላለን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞት ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ ጥንት ኢሰመጉ በምሠራበት ጊዜ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን በማስፈራራት ሰላማቸውን ለመረበሽ ወደስደት ወይም ወደወንጀል ተግባር የሚመሩ የወያኔ አባለች ነበሩ፤ አሁን እንደገና ብቅ ማለት ጀምረዋል፤ ሕጋዊ ሥርዓት እየላላ ጉልበተኞች በግላቸው ለዘረፋና ለቅሚያ እየተሰማሩ ይመስላል፡፡
ስለራሴ ላውራ፤ ከእኔ የሚፈልጉት ምን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፤ የሚፈልጉት የምኖርበትን አፓርትመንት እንደሆነም አላውቅም፤ በእኔ ቤት ያለ ሀብት የሚባል ለወያኔ አገልጋዮች የሚጠቅም ሁለት የገብረ ክርስቶስ ስዕሎች ብቻ ናቸው፤ (በዚህ አጋጣሚ እነዚህን ስዕሎች ለመግዛት የሚፈልግ ያነጋግረኝ)፤ ከዚህ ሌላ ለወያኔ ዋጋ የሌላቸው መጻሕፍት ናቸው፤ ስለዚህም አሁን በእኔ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት እኔን ወደስደት ለመግፋት የሚደረግ ሙከራ ይሆናል፤ በ1992 ግድም ተሞክሮ ነበር፤ አልሠራም፤ ዛሬ ይበልጥ አይሠራም፤ ለማናቸውም ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ባልችልም በእኔ ላይ ዘመቻ መጀመሩን አንድ በቅርብ ከማውቀው ወያኔ በትክክል ተረድቻለሁ፤ ይህንን ዘመቻ በመምራት ላይ ያለውንም ሰው ማንነት ተነግሮኛል፡፡
ይህ አገር የአንድ ጉልበተኛ ቡድን ነው ብዬ አልቀበልም፤ የአባቶቼና የእናቶቼ፣ የኤቶቼና የቅድማያቶቼ አጥንትና ደም የገነባው አገር ነው፤ ማንም ለስደት አይዳርገኝም፤ ማንም አስፈራርቶ ኢትዮጵያዊነት መብቴን መግፈፍ አይችልም፤ አልፈቅድለትም፤ በግልጽ በማያጠራጥር ቋንቋ ኑሮዬም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም እዚሁ ነው፤ ከኢትዮጵያ አፈር የሚለየኝ የለም፡፡
እኔን ለማጥቃት ላሰፈሰፉት ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው አንድ እውነት ልንገራቸው፤– በፈለጉትና በተመቻቸው መንገድ በእኔ ላይ በጉልበታቸው ግፍ ቢፈጽሙ ነገ በነሱ ላይ የባሰ ግፍ እንደሚደርስባቸው ይወቁት፤ ሁልጊዜም ከሕግ የወጣ ጉልበተኛነት ጉልበተኛነትን ያነግሣል፤ በመግደል ድል ይገኛል ብለው የሚያምኑ ወያኔዎች ትንሽ ቆም ብለው ያስቡ፤ በመሞትም ድል ይገኛል፤ በመሞትም ማሸነፍ ይቻላል፡፡
በእኔ ላይ የዘመተው ወያኔ ወይም ሎሌ ማናቸውም ሥራ ውጤት እንዳለው ማወቅ አለበት፤ አንድ ነገር አድርጎ ምንም ዓይነት ውጤት አያስከትልም ብሎ ማሰብ ድንቁርና ነው፤ ይህ የሳይንስ ሕግ ነው፤ For every action there is a reaction ይላል!

Friday 3 April 2015

ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!

ለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።
ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።
አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል።
ዛሬ ከዚህ በፊት ያልተሞከሩ የትግል ስልቶች ተግባራዊ እየሆኑ ነው። በዚህ ረገድ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የተቀናጁ ርምጃዎች በአርዓያነት የሚጠቀሱና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ የሚሹ ናቸው። እነዚህ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ተግባራት የእምነት አጥር ሳይለያየን ፍትህ የተጠማን ዜጎች ሁሉ ልንተገብራቸው የሚገቡ ናቸው።
ለምሳሌ፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በተወሰኑ ቀናት መዝጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከተደረገ ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ የሚችል፤ በሙስሊም ወገኖቻችን ግንባር ቀደም መሪነትና አስተባባሪነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል መሆኑ የታየ አንድ የትግል ስልት ነው።
በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለው ሣንቲሞችን የመሰብሰብ ዘመቻም ሌላ ከዚህ በፊት ያልተሞከረ፤ በተጨማሪ እርምጃዎች ከታገዘ ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን ገንዘብ መቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርስ የሚችል ጉልበት ያለው ስልት ነው። ውሳኔው ሣንቲሞችን ብቻ ሳይሆን የወረቀት ኖቶችንም ሲያካትት በዝውውር ላይ የሚኖረውን ገንዘብ ብዛት የሚቆጣጠረው ህወሓት ሳይሆን በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ ይሆናል። በባንኮች ያለ ተቀማጭ ገንዘብ በማውጣትም የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን ማሽመድመድ ሌላ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በእነዚህ እርምጃዎች የተለማመደ ሕዝብም ወደ ግዢ እቀባ፤ ለተወሰኑ ቀናት ከቤት አለመውጣት ብሎም “ግብር አልከፍልም” ወደማለት ሊሸጋገር ይችላል።
እንዲህ ዓይነቱ ስልቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ግን የመላው ሕዝብ ተሳትፎ እና የተቀናጀ አሠራርን ይፈልጋል። ለምሳሌ፣ ሰብስቡ ሲባል መሰብሰብን፤ በትኑ ሲባል መበተን ይጠይቃል። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በአምባገኑ የህወሓት አገዛዝ ላይ ከሚያደርሱት ጥቃት በተጨማሪ በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን መግባባት ያጠናክራሉ። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በማኅበረሰብ ቡድኖች መካከል አዎንታዊ መስተጋብር ለመፍጠር የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው።
አሁን አገራችን የምትገኝበት ሁኔታ በጥሞና ሲጤን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይነጋገር መግባባት፣ እርስ በርሱ መናበብ የሚችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑ መረዳት ይቻላል። ይህ ስነልቦናዊ ዝግጅት ደረጃ በደረጃ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያዘጋጀናል።
በማናቸውም የጋራ እርምጃዎች ለግል ጥቅሞቻቸው ቅድሚያ የሚሰጡ፤ ራሳቸው “ብልጥ” አድርገው በማየት በተፈጠረው ሁኔታ መጠቀም የሚፈልጉ፤ በሌላው ድካም ለማትረፍ የሚሯሯጡ ሰዎች መኖራቸው የማይቀር ነው። ህወሓት ለሃያ አራት ዓመታት ኮትኩቶ ያሳደገው የአድርባይነት ባህልም ሌላው እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ነው። ድህነት ደግሞ በገዢዎች ላይ ጨክነን የመነሳት አቅማችንን እንደሚያዳክም የታወቀ ነው። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፊቱ የቀረበለት ምርጫ “ባርነት ወይስ ነፃነት” መሆኑን የተገነዘበበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
በዚህም ምክንያት ለህወሓት ባርነት ከመገዛት ነፃነትን የሚመርጥ ዜጋ ሁሉ ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት ይኖርበታል። ለሁላችንም የሚሆን የትግል ዘርፍ መኖሩ የሕዝቡን ተሳትፎ ከፍ ያደርገዋል። የሁለገብ ትግል ስትራቴጂ ጥቅሙም እዚህ ላይ ነው። ማንም የማንም ነፃ አውጭ አይደለም። ሁላችንም ተባብረን ሁላችንንም ነፃ እናወጣለን።
አርበኖች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ትግላችን ዘርፈ ብዙ ነው፤ ተግባራዊ ትግል የሚደረገውን በሁሉም ቦታዎች ነው፤ እርጃዎቻችን እናቀናጅ፤ ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!