Wednesday 25 September 2013

ፖሊስ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አሰረ ETHIOPIAN FORMER PRESIDANT AND UDJ’S CURRENT CHAIR MAN DR. NEGASSO GIDADA IS ARRESTED BY ETHIOPIAN GOVERNMENT

 
Ethiopian former Presidant and UDJ’s current Chair Man Dr. 
Negasso Gidada is arrested by Ethiopian government

አንድነት ፓርቲ መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር 
ለሚያደርገው ሰላማዊሰልፍ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የማነ አሰፋ፣ዳንኤል ሙላት፣ 
ወንድምአገኝ አስፋው ፣ መሳይ ትኩ፣ አብርሀም ታደለ፣ እስማኤል ዳውድ ፣ወርቁ 
እንድሮ የተባሉት የአንድነት ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን ተከትሎ ወደ ጉለሌ 
ሽሮሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ያመሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ 
መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ለፖሊሶቹ “እነዚህን ልጆች ለቅስቀሳ ያሰማራሁት 
እኔ ነኝ፤ እነሱን ለቃችሁ እኔን እሰሩኝ” ብለዋል፡፡ ፖሊሶቹም “አባሎቻችሁንም 
አንለቅም እርሶም አይወጡም” በማለት የቀደሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት 
አስረዋቸዋል፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የታሰሩት ሽሮሜዳ አካባቢ 
ሲቀሰቅሱ የታሰሩ አባላት እንዲፈቱ ለመጠየቅ ሄደው ነው 
የታሰሩት”

Saturday 21 September 2013

Gov’t rents 500,000 br/month mansion for outgoing president

By Muluken Yewondwossen   

The Office of the President is in the process of leasing a mansion for the outgoing president Girma Woldegiorgis with a monthly rate of 500,000 birr, Capital learnt.

Reliable sources indicated that the presidential office has already finalized the proper documentation process at the head office of the Documentation and Authentication Registration Office (DARO) early this week with Elias Arega, who was indicated as the owner of the house selected for the outgoing president.
Sources claimed that the house is fully equipped with the necessary amenities that suit an outgoing president. The deal also mentioned every goods that will be rented in detail.
Sources did not mention about the location of the residential house but they confirmed that it is in Addis Ababa.
The ‘Proclamation No. 255/2001 Administration of the President of the Federal Democratic Republic of Ethiopia’ states that the government have to deliver up-to-the standard residential house and other facilities for the outgoing head of state. The other proclamation issued in September 2009 stated that the government will provide benefits for outgoing head of state, heads of government and other top government officials.
Based on that the Office of the President, which is commonly known as ‘Palace Administration’ is now in the process of renting a residential house for president Girma, who will be completing his two, six-year terms.
The Office of the President has confirmed that it is assessing houses that are worth for an outgoing president.
“The proclamation states that an outgoing government official has to get full benefits for their service during the rest of their life. Due to this fact we are looking for a proper house that suits president Girma, who will step-down from his position in the beginning of October,”  Gebru Abraha, Public Relation and Communication Affairs Head of the Office of the President told Capital.
“We have been assessing about five houses in different parts of the city to select the one that meets the standard” Gebru added. “We did not come to any final decision but in the coming week we will finalise the process.”.
However the head confirmed that the house of Elias Arega is one of the short listed places.
Officials at DARO declined to comment about the issue saying that it is the secret between the two parities.
President Girma, who is also popular on his environmental activity, has severed for the last 12 years. According to the country’s constitution the president shall not be on the position for more than two terms or over 12 years. He is the first president that managed to complete two terms after the constitution was ratified. The first president Negaso Gidada (PhD) only served one term and resigned in 2001.
According to the proclamation number 653/2009 under article ‘Rights and Benefits of Outgoing Heads of State and Government, Senior Government Officials, Members of Parliament and Judges Proclamation’ an outgoing President, Prime Minister or Deputy Prime Minister shall be provided with a residential house having four-to-five bedrooms, the administrative costs of which, including remunerations of housekeeping staff, shall be covered by the government.
The proclamation also states that that an outgoing President, Prime Minister or Deputy Prime Minister and his family shall get local and overseas medical services at the expense of the Government.
“An outgoing President, Prime Minister or Deputy Prime Minister shall be provided by the government with three high standard transport vehicles,” the 2009 proclamation also states.

ኦሮማይ፣ ትግሉ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ!

ከቴዎድሮስ ሓይሌ (tadyha@gmail.com)
ሠሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኤርትራ ቆይታቸውና ስለድርጅታቸው ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴ ሠፊ ገለጻና ማብራሪያ በኢሣት ቴሌቪዠን ከሠጡ ወዲህ የዘረኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ደጋፊ የሆኑት መርገማዊ ልሳኖች( አይጋ ፎረም ፤ ትግራይ ኦላይንና አውራንባ ታይምስ) እና አንዳንድ ተንበርካኪ የመንደር ሬድዮኖች ሰፊ የውግዘትና የህዝብን መንፈስ ያሸብርልናል በተቃዋሚዎችም ላይ ጥርጣሬ ይዘራልናል በሚል ደካማ ግንዛቤ እያካሄዱ ካለው አሰልቺና ኋላቀር ፕሮፓጋንዳ እጅግ ተጋኖ እየቀረበ ያለው ከሻብያ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ የሃገር ክህደት ስለመሆኑ እፍረት የለሽ ኡኡታ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍም ያነሳሳኝ ይህ የወያኔ በቀቀኖች ልቅ ያጣ የፀረ ሻብያ ውትወታ ወያኔ የምትባለው የጠባብ ዘረኞች ቡድን ለዚህ ዛሬ ለደረሰችበት የዘረፋና የልዕልና ደረጃ የበቃችው ከቶ በማን ትከሻ ሆነና ነው ። ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ወደ ኤርትራ ስለሄዱ ይህ ሁሉ ውንጀላ ደጋፊ ተብዬቹ የሚነዙት ወያኔ በሻብያ ሁለገብ ድጋፍ የማቴሪያል የትጥቅ የዕቅድና የሃሳብ መመሪያ ውጪ እንኳን ሚኒሊክ ቤተመንግስት ልትደርስ ቀርቶ ተከዜንም ባልተሻገረች ነበር።በአንድ ወቅት የኤርትራው መከላከያ ሚንስትር ጀነራል ስብሃት ኤፍሬም ስለ ወያኔዎቹ ያለውን እጅግ የወረደ ንቀት የገለጸበትን አባባል እንዳስታውስ አሰገደደኝ ‘’እኛ ከነጀነራል ደምሴ ቡልቱና ከነጀነራል ረጋሳ ጅማ ጋር በመዋጋታችን ኩራት‘’ የሚሰማን በመሆኑ ከነዚህ የፍየል እረኛ ወያኔዎች ጋር ፈጽሞ ለንጽጽር የማይቀርቡ እጃቸውን ይዘን ለዚህ ያደረስናቸው እኛነን ሲል ነበር ከአመታት በፊት የተናገረው። ወያኔዎች በሻብያ የበላይ ሹማምንት ብቻ ሳይሆን በተራው ተጋደልቲ ጭምር የሚናቁና እንደ ሻብያ አገልጋይ የሚታዩ ስለመሆናቸው ከሁለት አስዕርተ አመታት በኋላ እንኳ አለመለወጡን በረባው ባረባውም በባነኑ ቁጥር የሻብያ ስም እንደሚያስበረግጋቸው ዘወትር ከአፋቸው አለመጥፋቱን የምናስተውለው ሲሆን የሰሞኑ ደግሞ ተባብሶ የሚታየው ጫጫታ አንዱ የወያኔዎች የፍርሃት ማሳያ ይመስለኛል።
የወያኔ መሪዎች የትግራይን ገበሬ ልጆች በግዴታ ለሻብያ አሰልፈው እያዘመቱ ፈንጅ ማምከኛና በማስደረግ የፈጸሙት የሎሌነት አሳፋሪ ገሃድ እየወጣ ባለበት በአሁኑ ወቅት አበው በቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ነው እንዲሉ እሱ ብቻ ሕልመኛ እሱ ብቻ ባለራዕይ የነበረውና በሞት ተለይቶ እንኳ ወሬው የገነነለት መለስ ዜናዊ እንዲህ ለራሱ የሚያሸረግድ አድርባይ የሎሌ መንጋ ትቶ እንደሄደ ትላንት እርሱም ለሻብያ ካድሬዎች ይንበረከክ እንደነበረ ታሪኩን የሚያውቁት ሲመሰክሩ ቆይተዋል በተለይም ወያኔዎች ከሻብያ ጫማ ስር ለመዋላቸው የሚቀርብባቸው ማስረጃ የኢትዮጽያን ተፈጥሯዊ የባህር በር አሣልፈው ከመስጠት አልፈው የኤርትራ ነጋዴዎች የጅማን ቡና የለገደንቢን ወርቅ ከማህል ሃገር በብር እየገዙ ለውጭ ገበያ በዶላር ያቀርቡ የነበረበትን ሁኔታ አንድ እግር ቡና የማታብቅለው ኤርትራ ከቡና ላኪ ሃገሮች ተርታ መሰለፍ እስክትደርስ ድረስ የተካሄደውን የወያኔ ተንበርካኪነት ስናስታውስ ሻብያ በአዲስ አበባው ኤንባሲ ውስጥ የጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሬውን ሲያደራ እዚያው ኤንባሲ ውስጥ እስር ቤት አቋቁሞ የፈለገውን ሲያደርግ የነበረበት የጌታና የሎሌ ታሪክ የተዘነጋ ይመስል ወያኔና ጭፍሮቿ ሻብያን ቀንድና ጭራ ልትቀጥልልለት የምታደርገው መፍጨርጨር ተመልካች የማይታደምበት ተራ ኮሜዲ ከመሆኑም በላይ እውነተኞቹ የትግራይ ልጆች እንደ አስራት አብረሃምና እንደ ገብረመድህን አርዐያ ያሉት ይህንን የሚታወቅ ታሪክ በተባ ብዕራቸው ትውልድ እንዲያውቀው ከትበው ያስቀመጡት በመሆኑ ዝርዝር ሃተታ አያስፈልገውም ።
ዘረኝውና ዘራፊው የወያኔ ጥርቃሞ በእንዲህ ያለ የሻብያ የጭን ገረድነት የገለማ ታሪክ እያለው ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ከሻብያ ጋር ቢተባበሩ ከኢሳያስ ጋር ቢነጋገሩ ከቶ ሊቃወም የሚችልበት የሞራል መሠረት የሌለው መሆኑን ወናፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ ሊረዱ በተገባ ነበር። የኢትዮጽያ ልጆች በመረጡት አጀንዳ በመሰላቸው የትግል ስትራቴጂ ከማንኛውም ምድራዊ ሃይል ጋር የመነጋገር የመተባበር ሙሉ መብትና የተሟላ የሞራል የበላይነት ስላላቸው ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ደም በመምጠጥ ላይ ያለውን ዘራፊ ሌባና ሰውበላው ወያኔን ለማስወገድ ከሻብያ ጋር አይደለም ከሴጣንም ጋር ቢዋወሉ የሚያስመሰግን እንጂ ከቶም የሚያስወቅስ አለመሆኑን ማንም ሊያሰምርበት የሚገባው አብይ ነጥብ ሃገራችንና ሕዝባችን ከወያኔ የከፋ ምድራዊ ጠላት የለውምና ነው። ኢትዮጽያዊ ሃይሎች ከማንኛውም ወገን የሚደረግላቸውን የገንዘብ የማቴሪያልና የስልጠና እገዛ ሃገርና ወገንን ለመታደግ እስካዋሉት ድረስ ከማንም ጋር ቢተባበሩ ከቶም በታሪክ ሊያስወቅሳቸው የሚያስችል ባለመሆኑ በያዙት ጎዳና በልበሙሉነትና በወኔ ሊጓዙ በመቃተት ላይ ያለው የወገናቸው የሰቆቃ ድምጽ ግድ ይላቸዋል። ነገር ግን የሃገርን ብሄራዊ ጥቅም በሚጎዳ ማናቸውም ውልና ስምምነት ውስጥ ቢገቡ ወያኔ ለሻብያ ቂጣ ጋጋሪና መንገድ መሪ በመሆን እንደፈጸመው የውርደት ታሪክ እነሱም እንዳይደግሙት ሊጠነቀቁና አካሄዳቸውን ከጊዜያዊ ፍላጎት አንጻር ሳይሆን ከዘላቂ ጥቅም አንጻር እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል።
ከዚህ ባሻገር ወያኔን ለመደምሰስና ለማስወገድ የሚደረገው ትግል በተቀናጀና ሁሉን ወገን ባሳተፈ መልኩ እንዲሆን ሠፊ የፖለቲካ የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ስራ በስፋትና በጥራት እንዲካሄድ ከህዝቡና ከአጋር ወገኖች የሚገኝ ትግሉን በጥንካሬ ለመወጣት እንዲቻል የሚያግዝ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም በማፈላለጉ ላይ ያለይሉኝታ ሊንቀሳቀሱ ይገባል። እዚህ ላይ ባለፈው ሰሞን እንደትልቅ የሃገር ክህደት ወያኔዎችና አንዳንድ ህዝባችን የተጫነበት ድቅድቅ የዘረኝነትና የግፍ ጭለማ ያልታያቸውና የሃገራችን እጣፋንታ ያልገባቸው በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ቅንጡ ፖለቲከኞች ሲያራግቡት የሰነበቱት የማጥላላት ዘመቻ ግንቦት 7 ከሻብያ ግማሽ ሚለዮን ብር የመቀበሉ ቱማታ በእኔ እምነት የሚያስወቅስ ሳይሆን የትግሉ እድገት አንድ ደረጃ እንደደረሰ ማሰያ በመሆኑ ከወያኔ ጋር ለሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የገንዘብም ሆን የቁሳቁስ ድጋፍ ከሻብያ አይደለም ከሠይጣንም ቢገኝ አመስግኖ መቀበል የሞራል ድጋፍ ያለው አካሄድ በመሆኑ አስፈላጊ አይደለም እንጂ የተገኘው ድጋፍ በአደባባይ ቢገለጽ የሚያኮራ እንጂ የሚያሳፍር አይደለም። በተለይ በተቃውሞው ጎራ ያለው ወገን ቆም ብሎ ሊያስብ የሚገባው መሠረት በሌለው እንቶፈንቶ ለመነታረክ ግዜ ከማጥፋት ይልቅ በየራሳችን ይዝን የተነሳንውን አላማ ከግብ ለማድረስ መትጋት ላይ ትኩረት ማድረግ ቢቻል ወያኔ ይህን ያህል ችግር አትሆንብንም ነበር ። ስለሆነም ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነንን የሌሎችን እንቅስቃሴ ሂደቱን ባንደግፍ እንኳ ተቋዋሚ ልንሆንበት የሚያስችላን አንዳች የፖለቲካ አመክንዮ ስለሌለን በመተባበር በጋራ መቆም ባንቸል በመከባበር በየራሳችን መንገድ መጓዙ የመከራውን መንገድ የሚያሳጥር በመሆኑ ላይ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል።
በኤርትራ በኩል የአመጽ ትግሉን እናካሂዳለን ብለው በድፍረት የቀረቡትን ወገኖች ስለቁርጠኝነታቸው አድናቆት መቸር ሲገባ አንዳንደ የዘረኛው ቡድን ተላላኪዎችና የመንደር ራድዮ ጣቢያዎች ጉዳዩን አጣመው ስላቀረቡት ብቻ ያን ይዞ የትችትና የስድብ ዘመቻ ማካሄድ ተገቢም ካለመሆኑም በላይ በእርስ በርስ ሽኩቻ የሕዝባችን መከራ እንዲራዘም ማድረግ ስለሚሆን ሁሉም ወገን ተገቢነት ባለውና ስልጡን በሆነና መቻቻልን ባሰላሰለ መንገድ ሁሉም የትግል ሃይሎች ቢቻል ጎን ለጎን ካልሆነም በመከባበር ግባቸው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ከጎንዮሽ መጠላለፍ እንዲታቀቡ የደጋፊው ህብረተሰብ አሰላለፍ ከስሜታዊነትና ከጠባብ የቡድን አመለካከት ባሻገር ሠፊውን አላማ ላይ ያነጣጠረ ብልህ አካሄድን ማቀናጀት ሁሉም አትራፊ የሚሆንበት የፖለቲካ ሂሳብ በመሆኑ ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል። ከዚህ ባሻገር ካሮጌ ፖለቲካችን የወረስነው የስማበለው የባልቴቶች የአሉባልታ ተረት ተረት ይዞ መጓዝ የደረስንበት ዘመን የማይዋጀውና የንቃተ ህሊና ደረጃ ወደማይፈቅድበት የማሰብ አድማስ የሰፋበት ሁኔታ መከሰቱን በመረዳት በሎጅክና በትንተና ሃሳባችንን እስካላስረገጥን ድረስ አዲሱ ትውልድ የማይቀበለው ባለመሆኑ በተለይ እድሜ ጠገብ ፖለቲከኞቻችን ከዚህ አንጻር የትውልድና የአመለካከት መጠነሰፊ ሽግሽግ በግዜ ሂደት መከሰቱን አውቃችሁ በየአቅጣጫው እየተካሄደ ያለውን ትግል በጥራትና በግልጽ ለውይይት እንዲቀርብ በማድረግ በአመጽ ጎዳና እንዘምታለን የሚሉትን ሃይሎች በነጠረ ሂስና ግለሂስ ጥንካሬና ድክመታቸውን እንዲለዩ ህዝባችንም አቅጣጫውን እንዲያስተካክል የሚረዳ ተሳትፏችሁ በጥበብ የተሞላ መሆን ይኖርበታል። አለያ የኔብጤው ወኔና እውቀት አጠር ዲያስፖራ ሠልፍ እንኳ ለመውጣት በደረቅ በጋ ስካርቭ የሚደርብና አርቴፊሻል ጢም የሚቀጥል ፍርሃት ያራደው አውታታ ፤ የወያኔን አገዛዝ ለመደምሰስ ዱር እንገባለን የሚሉትን ሃይሎች መደዴ በሆነ ቋንቋ ሲዘልፍና የግለሰቦችን ስብዕና ሲዘልፍ ላስተዋል ምን ያህል ከሞራል አልባነት ከኋላቀርነት ያልተላቀቀ ምስኪን ወገን በመኖሩ እንዲህ አይነቱ የስድብ ሱሰኛ በምክር አይደለም በጸበልም የሚተወው ባለመሆኑ ለእንዲህ አይነቱ የአስተሳሰብ ድውይ ከማዘን በስተቀር ሌላ ሃይል ማበከን ተገቢ አይመስለኝም ።
አዲሱ ትውልድ ይጠይቃል በበቂ መልስለት ይከተልሃል፤ ይህ ነው መሬት ላይ ያለው ሃቅ ቅንጅት ሚሊዮኖችን ያነቃነቀው ሕዝባዊ አጀንዳና የሚታይ ራዕይ ስላስቀመጠ ነበር። በቅርቡ የተመሠረተው ሠማያዊ ፓርቲ በመሪዎቹ ቁርጠኝነትና ባቀረቡት ወቅታዊ አጀንዳ አንጻር ከስምንት አመታት በኋላ ታላቅ ህዝባዊ ሠልፍ በማድረግ የፈጠሩት መነቃቃት ፓርቲው ከተመሰረተ አጭር ግዜው ቢሆንም ያለው ተደማጭነቱ ከአንጋፋዎቹ ልቆ እንዲገኝና ተስፋ እነዲጣልበት ያደረገው የድርጅቱ መርሆ በሎጅክ የተቃኘና አላማውን ግልጽ በማድረጉ ይመስለኛል። ሕዝብ የሚከተለው ትውልዱ ለትግል የሚነሳው ወቅቱ ከፈጠረው አዲስ ሁኔታ አንጻር እንጂ በታሪክ ቡልኮ ተጀቡኖ በተረትና ሃሜት በሚነዳ የፖሮፓጋንዳ ዘመቻ አይደለም፤ ያ በስማ በለው በደመነፍስ ትውልድ ከሚነዳበት የስብስቴ አመለካከት ላያዳግምና ተመልሶ ላይመጣ በማስተዋልና በስልጣኔ እየተሻረ በመሄድ ላይ በመሆኑ ብዙዎች ያወሩለትን ጥቂቶች ጀምረው ያቆሙትን የአመጽ ትግል በአዲስ መልክ እናስቀጥላለን ብለው የተነሱትን ሃይሎች የማይደግፍበት ምክንያት ቢኖረው እንኳ ከመርህ አንጻር ሊቃወም የሚችልብት ምንም በቂና ውሃ የሚቋጥር አሳማኝ ምክንያት ባለመኖሩ ሂደቱን በጥንቃቄ ይከታተላል።
በዚህ የስልጣኔና የጥበብ ዘመን ላይ ቆመን ከቶስ ስል አመጽ ትግል ማንሳት ለምን አስፈለገ ጦርነት የሰውን ልጅ የሚበላ እሳት ነው። አመጽ ሃገር የሚያወድም መሠረተ ልማትን የሚንድ ኋላቀር መፍትሔ ነው፤ የሰላሙን ትግል ማበረታታት ሲገባ ለምን የአመጽ መንገድ እንደ መፍትሔ ይቀመጣል የሚሉ ወገኖች በርካቶች ናቸው። እርግጥ ነው ዲያቢሎስ ካልሆነ በቀር ጦርነትን መልካም ነው የሚል አንዳችም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ፍጡር አለ ለማለት አይደፈርም። እንደምኞታችን ነገሮች በተቃውሞ ሠልፍና በሕዝባዊ እንቢተኝነት ቀለውልን ከላያችን የተጫነው ግፈኛ አገዛዝ አሽቀንጥረን ብንጥል መልካም ነበር። ይህ ግን ቀላል ሆኖ አልተገኘም የተከፈለውና በመከፈል ላይ ያለው መስዋዕትነት አንሶ አልነበረም አመጽ ታሳቢ የሆነው። ሃገራችንን የወረረው የወያኔ ቡድን ፖለቲካና ርዕዮተ ዓለምን መሠረት ያደረገ ሣይሆን ፤ የዘር አመለካከትን ዶግማና ቀኖናው በማድረግ ኋላቀር አካሄዱንና፤ ኢ ዲሞክራሲያዊነቱን የተቃወመውን ወገን በሙሉ የሚመለከትበት ሸውራራ አተያይ ፀረ ትግራይ በሚል በመሆኑ ከእንዲህ አይነቱ ጠባብና ድኩማን አመለካከት ባለው ሃይል ከሚመራ ቡድን ጋር የሚደረግ ስልጡን የፖለቲካ ትግል ውጤቱ ፍሬ አልባ በመሆኑ ሊገዳደረው የሚችል የሃይል እንቅስቃሴ አማራጭነቱ ሁሉን ወገን ከተረዳው የከረመ ቢሆንም አለመታደል ሆኖ የትግሉን እንቅስቃሴ ማቀናበሪያ ወሳኝ ኮሪደር በማግኘት ዙሪያ ስንቸገርና ባለውም ጠባብ አማራጭ ለመጠቀም ሳንችል የቆየንባቸው ትርምስ የተሞላ ሰፊና ወርቃማ ግዜያቶች ባክነዋል።
አመጽ የጭቁኖች ድምጽ ነው ሲል የተናገረው ጠቢብ ማን ነበር ፤ አዎን አመጽ የሰውነት ክብርን ማረጋገጫ የነፃነት እስትንፋስ ማግኛ የባርነት ሰንሠለትን የሚበጥስ ጽኑ መዶሻ ነው። በሃገራችን የዛሬን አያድርገውና እንኳን ሃብትና ንብረቱ እየተቀማ ከነ ቤተሰቡ ጎዳና ሊጣል ቀርቶ ክፉ ቃል ተናግሮ ስብዕናውን የተዳፈረውን አደብ ሳያስገዛ የማይኖር ከምንም ነገር በላይ ለክብሩ ዘብ የሚቆም ማንነቱ ተዋርዶ በሞቀ ጎጆው ከመኖር ይልቅ ክብሩን ለማስመለስ ዱርቤቴ ማለትን የሚመርጥ ጀግና ሕዝብ እንደ እባብ ተሽሎክሉኮ በገባው የማንም መደዴና ቀን የሰጠው ወፍዘራሽ ዘረኛ የወያኔ መቀለጃ ሆኖ ለስደት ለሞት ለእስርና ለምድራዊ ስቃይ የተዳረገው መብቱን ለማስከበር አመጽን አማራጭ ባለማድረጉ መሆኑን እያየንው ነው።
ወያኔዎች በለስ ቀንቶዐቸው ድፍን ኢትዮጽያን ሲወሩ በየሄዱበት ያገኙትን አሮጌ አካፋና ቀደዳ በርሜል ሳይቀር እየጫኑ ወደትውልድ ስፍራቸው ሲያግዙ ከነበረበት ቅራቅንቦ ሰብሳቢነት እድሜ ለታላቋ ሃገራችን ዛሬ ይህው እኒያ ከገላቸው እድፍና ከጎፈሬያቸው ተባይ ውጪ የረባ ጃኬት እንኳ ያልነበራቸው ሽፍቶች ይህው ዛሬ ድፍን ሃገር በጠኔ እየተመታ በረሃብ አለንጋ በሚለበለብበት ልጆቹን በፈረቃ የሚቀልብበት የኑሮ ምስቅልቅል ውስጥ ወድቆ ልጆቹ በየትምህርት ቤቱ ደጃፍ ረሃብ አዙሮ እየጣላቸው ባለበት ሁኔታ ላይ የወያኔው አባላት ጉቶ እየሞቁ ድብዳብ ላይ ተወልደው እዛው አጎዛ ላይ እንዳላደጉ ይህው የህዝብን ሃብት በመዝረፍ በህንጻ ላይ ህንጻ በሃብት ላይ ሃብት እያከማቹ ከራሳቸው አልፈው በድብቅ ላስቀመጧቸው እቁባቶቻቸው ወርቅና አልማዝ መኪናና ቪላ ስጦታ የሚያቀርቡበት ታጋይ ከበርቴዎችና ልማታዊ ዘራፊዎች ሕገ ወጥ ብልጽግና አካብተው ቅንጦት የሚያደርጋቸውን ባሰጣበት በዚህ ወቅት ትውልዱ ኑሮ ዳገት ሆኖበት የከፋውን ስደት ተያይዞት የሲናይ በርሃ አሸዋ ሲሳይ የቀይባህር አሳ ቀለብ እየሆነ እንደወጣ የቀረው የእምዬ ኢትዮጽያ ልጅ የሚደርስበት ሰቆቃ ዓለምን እስኪሰለች ድረስ የተለመደ የሰርክ ተግባር በመሰለበት በዚህ ዘመን ፤ በሃገር ውስጥ ያለው በገፍ በሚቀርብለት ጫት ደንዝዞ በምዕራቡ ዋልጌ ባህል ነፍዞ ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች በሆነ የሞራልና የተስፋ መቁረጥ ጭለማ ተውጦ የትግሬው ነጻ አውጪ አባላት ልጆች ከህዝብ በሚዘረፍ ገንዘብ በአውሮፓና በኣሜሪካ ውድ ኮሌጆች እንዲማሩ እየተደረገ ባለበት የፋሽስት አገዛዝ ውስጥ የአንድ አናሳ ብሄር ሰዎች ተጨፍልቆ እየቃተተ በስቃይ በሚኖርበት ሁኔታ ውስጥ ህዝባችን ቢያምጽ ይነሰው በእውነቱ ይህ ትውልድ እነዚህን የቀን ጅብ ወያኔዎች ለመታገል ከሰይጣንስ ጋር ቢተባበር ከቶ ወንጀሉ ምኑ ላይ ነው?
ተወልደው ካደጉበት ጎጆ ቀልሰው ትዳር ይዘው ጫካ መንጥረውና ከአውሬ ታግለው ከባዱን የኑሮ ዳገት በላብ በወዛቸው አቅልለው በሰላም ሃገሬ መንደሬ ብለው የእርሻን ጥበብ የአኗኗር ዘይቤን ሃይማኖትንና ግብረገብነትን በየሄዱበት አስተምረው በቋንቋና በባህል የተለያቸውብ ወገን የራሳቸው አድርገው ተዛምደውና ተጋብተው በሰላም ለዘመናት ከኖሩበት ቅዬ ሃገራችሁ አይደለም በሚል ያፈሩትን ሃብት ነጥቆ ተማሪዎች ከትምህርታቸው በግድ እንዲፈናቀሉ በማድረግ በክፋትና ቂም በቀል አንድን ህዝብ ለማጥፋት የሚያደባውን እርጉሙን የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ይህ ሕዝብ መፋለም ይነሰው በጉራፈርዳ በቤኒሻንጉል በአፋርና በጋንቤላ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች የተፈጸመው የዘር ማጥፋትና ሁን ብሎ በድህነት የመቅጣት ወያኔያዊ ሴራ በእውነቱ ከወንጀልም ወንጀል ከሃጢያትም ሃጢያት የሚሆነው ይህንን ሳጥናዔላዊ ቡድን አለመታገል ብቻ ነው።
ነብሳቸውን ይማረውና አያቴ ‘’ ጣሊያን ምን አጠፋ በከንቱ ኩነኔ ሃገሩን አጠፉት መለስና ላይኔ’’ ብለው ነበር ያኔ ገና ወያኔ ሃገር ስትወር ፋሽስት ጣሊያን ያልፈጸመውን ግፍ ኦርቶዶክስና አማራ የሚባል ተቋምና ህዝብን ለማጥፋት እቅድ ነድፎ መርዝ አዘጋጅቶ የመጣን አርዮሳዊ ሃይል ለሺህ ዘመናት የውጪና የውስጥ ሃይሎችን በጽናት በመመከት ህልውናዋን አስጠብቃ የኖረችውን የታሪክ ማህደሯን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንድትከፋፈል የዘረኞች ምሽግ በመሆን ሃዋርያዊ ሃላፊነቷን ዘንግታ የጥፋት አላማው ማራመጃ ለማድረግ በመለመላቸው ጥቅመኛና ዘረኛ ጻጻሳትና ፓትርያርክ ተብዬ በማዘጋጀት በቤተክርስቲያኒቱና በምዕመኑ ላይ ሲደርሰ የቆየው በደልና ግፍ በቀላሉ ተዘርዝሮ አያልቅም። ወያኔ በቤተክርሰቲያኒቱ ላይ ያለውን ጥላቻ በማስፋፋት ይደረጋል ተብሎ አይደለም ሊታሰብ እነኳ የማይሞከረውን ታላቁን የዋልድባ ገዳም ለስኳር ልማት በሚል በገዳሙና በመናኝ ባህታውያኑ ላይ የተፈጸመው ግፍ ስንቃኝ የውጭ ወራሪ ሃይል ይህን ያህል ይዳፈራልን? ታዲያስ ይህ ጉግማንጉግ ፀረ ኦርቶዶክስ የሆነ የወያኔ መንጋ ከቶስ ከሰይጣን የሚለየው በምንድን ነው? ይህንን ወንጀለኛና መንጋ ዘረኛ ይወገድ ዘንድ የዚህች ታላቅ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን አድዋ ላይ ጌቶቹ ጣሊያኖችን በጸሎትና በሰይፍ እንዳሸነፈ በዚህም ሃገር በቀል የፋሽስት ሎሌን ለማስወገድ የሚደረገውን ትግል በውግዘትም በሞራልም ማገዝ ለቤተክርስቲያኗ ሰላም መረጋገጥን ለምዕመኖቿ መረጋጋትን የሚያስገኝ ትርጉም ያለው መልካም ሁኔታ ሊገኝ የሚችለው ይህ የዘረኛ መንጋ ተጠራርጎ ሲወገድ ብቻ በመሆኑ ይህንን ትግል ማገዝ የቤተክርስቲያኒቱና የምዕመናኑ መንፍሳዊ ግዴታ ጭምር ነው።
የሃይማኖት ተቋማትን ማጥፋት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር እኩይና ሠይጣናዊ አላማ ሌላው ያነጣጠረበት የኢትዮጽያ ሙስሊም ማህበረሰብ ከአመታት በፊት ይህው ከፋፋይ ዘረኛ የወያኔ ቡድን የሙስሊሙን ማህበረሰብ የስልጣኑ ማደላደያ በማድረግ ከጎኑ ለማሰለፍ የሞከረበት እኩይ አላማው ከቅርብ አመታት ወዲህ ከታወቀ በኋላ መላው ሙስሊም በአንድ ድምጽ ያቀረበውን የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ በሃይለ ለመጨፍለቅ ከምዕመኑ ጋር ያደረገው ትንቅንቅ የሙስሊም ወንድሞቻችን ዓለምን ያስደመመ እጅግ ዘመናዊና ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ጨዋነትን ምንም ያህል መርሐቸው ቢያደርጉም የወያኔ ቡድን ሠላማዊ ቋንቋ የሚገባው ባለመሆኑ ለሠላት የወጣውን የሙስሊም ማህበረሰብ ህጻን ከአዋቂ ሣይመርጥ በተለያዩ ቦታዎች የፈጸመውን ጅምላ ፍጅት የምታስታውስ ሙስሊም ወገን ይህንን የደደቢት ጭራቅ ለማስወገድ የሚደረገው ትግል በመንፈሳዊ ቡራኬም ሆነ በቀጥተኛ ተሳትፎ
ክንድህን ሠብስበህ እንዳትታገለው ከቶስ የሚያግድህ ምንድነው? እየተጨቆኑ መኖር ለሃገርህና ለእምነትህ ታግለህ በክብር ማለፍ ነው።
ለማጠቃለል ኢትዮጽያ እንደሃገር ትቀጥል ዘንድ ትውልዷም ተሰዶ ከማለቁ በፊት ይህን ሃገር አፍራሽና መንጋ ቅጥረኛ ከቅድስት ሃገራችን ለማስወገድ እየተካሄደ ያለውን ማንኛውም እንቅስቃሴ ዘር ሃይማኖት ሳንለይ በጋራ ቆመን በጽናትና በብርታት የመደገፍ የማበረታታት የማገዝ ታሪካዊም ሞራላዊም ሆነ መንፈሳዊ ግዴታ አለብን። በትግል አለም መውደቅ መነሳት ያለና የነበረ በመሆኑ ትላንት በሄድንባቸው መንገዶች ውጤት ባናገኝም ስልታችንን በማስተካከል ጥበብ በተሞላበትና ቁርጠኝነት ባለው መልኩ እንጓዝ ዘንድ መሪ ሃይል ሆናችሁ የወጣችሁ ሃይሎች በየትኛውም የትግል ስልትና ያላችሁ ያለ የሌለ ሃይላችሁን በማስተባበር የወያኔን ተፍጻሜተ መንግስት ለማቅረብ የሚረዳ አመራር በመቀየስ ታግላችሁ እንድታታግሉን ግዜው ግድ ይላችኋል።
ታላቁ ደራሲ ኦሮማይ በሚለው መጽሃፉ የሳላቸው የገሃዱ ታሪካችን አካል የነበረው ቀይ እንቡጥ የተባለው በለጋ ወጣቶች የተመራው የሃገር ፍቅር ሰራዊት ውጤቱ የማታ ማታ ቢበላሽም በለጋ እድሜያቸው በቆራጥነትና በጀግንነት አንድ ስትራቴጂክ ተራራ ለማስለቀቅ የከፈሉት ወደር የሌለው መስዋዕትነት ይህ ትውልድ ዞር ብሎ በማሰብ ነፃነቱን ረግጠው በሃገሩ ባይተዋር ባደረጉትና ሃገራዊ ድርሻውን ነጥቀው ባቋቋሙት የንግድ ኢንፓየር እነሱ በቁንጣን ሲወጠሩ የሃገሬ ወጣት ከረሃብ ጋር ሲታገል በየድልድይ ስር የሚያድርበት የአፓርታይድ አገዛዝ እንዲያከትም መፍትሄው ያለው በአዲሱ ትውልድ መዳፍ ውስጥ በመሆኑ ያአህዛብ አሽከርና የችጋር ጓደኛ ሆኖ ተሰቃይቶ ከመሞት ታሪክ ሰርቶ ለታሪክም ለህሊናም የሚጠቅም በጎ ተግባር ፈጽሞ ለመገኘት በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ የሚደረገው ትግል በማገዝ ህዝባችንን ልንታደግ ሃገራችንን ልንጠብቅና ሃይማኖታችንን አስከብረን በነጻነት እንድንኖር ወያኔን ለማስወገድ የሚካሄደውን ሁለገብ ትግል በትጥቅ ይሁን በሰላም ከኤርትራ ይሁን ከሱዳን ከሱማሌ ይሁን ከጅቡቲ በሚነሳ የአመጽ ሃይል ይሁን በሕዝባዊ ንቅናቄ ሁሉን ባለን አቅምና ጉልበት ልናግዝ ታሪክ ትውልድ ሞራልና መንፈሳዊ ሕይወታችን ግድ ይለናል። በጽናትና በጋራ ቆመን ጠላቶቻችንን ለመደምሰስ እግዚያብሄር ሃይልና ብርታት ይሁነን።
ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር!!!

Friday 20 September 2013

ግልጽ ደብዳቤ ለኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማሪያም


Mengistu Haile Mariam 3.jpg
በቅድሚያ እርስዎንም ሆነ አንባቢውን ይቅርታ እየጠየቅሁ፤ የሚከተለውን ለማለት እፈልጋለሁ። ይህም እርስዎ ኮሎኔሉ በሕይወት እስካሉ ድረስ በታሪክ አጋጣሚነት የኢትዮጵያ መሪ በነበሩበት ወቅት ስላደረጕትም ሆነ ስላላደረጉት የመፃፍና የማስረዳት መብት የእርስዎ ወይንም እርስዎ የሚወክሉት ሰው ብቻ ነው። ምክንያቱም በሥልጣን ላይ በነበሩ ወቅት ያደረጉት የወሰኑት የጻፉትና የተናገሩት ሁሉ የኢትዮጵያ ታሪክ ስለሆነ። ስለዚህም ማንም ሰው ያለእርስዎ ፈቃድ በንዝህላልነት በግብዝነትና በትምክህተኝነት ተነሳስቶ የእዚህን የግልጽ ደብዳቤ ዋናና አንገብጋቢ ዓላማ ለመረዳት ባለመቻል ሊናገር ሊመልስ ሊጽፍ ሊበርዝ ሊጠግንና ሊያስተካክል መብት የለውም። ሊደመጥም አይገባም። ታሪክን ለታሪክ ሠሪው መተው ተገቢ ይመስለኛል።
በክፍል አንድ ላይ እንዳቀረብኩት፦ በንጉሥ ኅይለሥላሴ ላይ እንዲያዝኑና ቂም እንዲይዙባቸው ካደረገዎት አንዱ ምክንያት በመጽሐፍዎት ገጽ 259 ላይ ያሰፈሩት ነው። እርስዎ ሲገልጹትም “….በታሪክ ከሚታሰቡ አሳዛኝ ጉዳዮች አንዱ ደግሞ የቀዳማዊ ኅይለሥላሴ መሠደድ ነው። በጊዜው የኢትዮጵያ የነቁ መንፈሳዊ አባቶች፡ አረጋዊ የየህብረተሰቡ መሪዎች፡ ለነፃነት የታገሉ አርበኞችና በአገሪቱ ምሁራን ዘንድ የቀዳማዊ ኅይለሥላሴ ለአምስት ዓመታት አውሮፓ በተለይም እንግሊዝ መቆየት ሁለት ገጽታ ነበረው።
አንደኛ ያለጥርጥር ከፍ ያለ የመንፈስ ጉዳት የሚያደርስና ቅስም የሚሰብር የኅዘንና የፈተና ጊዜ ሲሆን….”
ይህ ምክንያት፦ በገጽ 271 እንደገለፁት፦ ንጉሡ እንደ ሌሎች አርበኞች አስከሬናቸው በቅዱስ ሥላሴ ፍትሀትም ሆነ ቀብር እንዲነፈጋቸው አድርጓል። እርስዎ የንጉሡን መሰደድ ከፍርሀት የመጣ ስለሆነ ሽሽት እንጅ ለስራ ወይንም የኢትዮጵያን ሕዝብ አቤቱታንና እሮሮን ለማሰማት እንዳልሆነ ወስነዋል። ሽሽት ለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጅያ ግን የለም። መንግሥቱ ኅይለማሪያም ስለሆንኩኝ እመኑኝ የሚሉ ይመስላል። የኢትዮጵያ ታሪክ ስለሆነ በዘፈቃድ የሚሆን አይመስለኝም። የኢትዮጵያ ታሪክ ፅሐፊዎችና ምሁራን ስለጉዳዩ ምን ይላሉ?
አምባሳደር ዘውዴ ረታ “የቀዳማዊ ኀይለሥላሴ መንግስት” በሚል አርዕስት እአአ በ 2012 ዓም ታትሞ በወጣው መጽሐፋቸው ምዕራፍ አስር የሚከተለውን ያሳስቡናል። “መጋቢት 22 ቀን 1928 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሠራዊት “መሐን” ከተባለው ስፍራ ተነስቶ ማይጨው ሰፍሮ የነበረውን የጠላት ሠራዊት ለመግጠም ወደ ስፍራው ሲቃረብ፦ ጦሩ ከበባ ሳያደርግና የጦር አዛዡን ትዕዛዝ ሳይጠብቅ አንዱ ስለተኮሰ ጦርነቱን ለመጀመር ታቅዶ ከነበረው ከአንድ ቀን በፊት ተጀመረ። ከዝያም ጦርነቱ እንዲቀጥል ንገሠ ነገሥቱ
ትእዛዙን ሰጡ። “ ይሁን እንጂ ማርሻል ባዶግሊዮ ገና ከመነሻው የአድዋ ታሪክ እንዳይደገምበት ካለው ሦስት የተሟላ ዲቪዚዮን የምድር ጦር ይልቅ፤ በአየር ኅይሉ በመተማመን ከፍ ያለ ዝግጅት አድርጎ ስለነበረ፤ መርዝ የሚረጩትና ቦንብ የሚጥሉት በአንድ ጊዜ ቁጥራቸው ከአንድ መቶ ሃምሳ በላይ የሆኑ አውሮፕላኖች፤ በአሥር መንታ እያንዣበቡ በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ እሳቱን እንደ ዝናብ እንዲያወርዱት አስደረገ። ኢትዮጵያውያኖቹም በአንድ በኩል ከሰማይ የሚወርድባቸውን መርዝና ቦንብ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከምድር የሚተኮስባቸውን መድፍና መትረየስ በድፍረት እየተጋፈጡ፤ በዚያ በያዙት በጥንታዊ የሰናድር ጠምንጃና ወጨፎ ውጊያቸውን ቀጠሉ። በዚህ አኳኋን፤ ጦርነቱ በተጀመረ አምስት ሰዓቶች ባልፈጀ ጊዜ ውስጥ፤ በማይጨው ላይ ጠላት የሰፈረባቸውን አምስት ምሽጎች በጀግንነት ለማስለቀቅና የጠላትን ወታደሮች ብዙዎቹን ገድለው ብዙዏቹንም ለማባረር ችለው ነበር። ይሁን እንጂ፤ የኢትዮጵያ ተዋጊ ኀይል እየቀናው መሄዱ ንጉሠ ነገሥቱን ቢያስደስታቸውም፤ በጠላት በኩል በተለይ በአየር ኀይል የተጣለው መርዝና ቦምብ ብርቱ ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ፤ ከሞት የተረፈው ጀግናው የኢትዮጵያ ሠራዊት ጥቂት እንዲያርፍና የሞተውም ሬሳው እየተነሣ እንዲቀበር፤ መጋቢት 23 ቀን ሮብ መሐን ላይ የአንድ ቀን ውሎ ይደረግ ሲሉ፤ የጦሩ ዋና አዛዥ ለየአዝማቹ ትዕዛዝ አስተላለፉ።….
ለዳግማዊ ምኒሊክ አድዋ ላይ ድልን ያስገኘው የየካቲቱ ጊዮርጊስ ለቀዳማዊ ኅይለሥላሴ ደግሞ የመጋቢቱ ፈረሰኛው ጊዮርጊስ የጉልበት ማጠናከሪያ ዕድል የሚሰጥ እንዲሆን ተስፋ በማድረግ፤ በማግስቱ ሐሙስ መጋቢት 24 ቀን ከጠላት ጦርነቱን እገጥማለሁ ብለው ንጉሠ ነገሥቱ ወስነው ነበር። ነገር ግን፤ በአራት ግንባር የተመደቡት ዋና ዋናዎቹ የጦር አዝማቾችና ከሞት የተረፉት የጦር አለቆች በሙሉ ተሰብስበው ይህን ንጉሠ ነገሥቱ ያቀዱትን ውጊያ ለመፈጸም የሚቻል አለመሆኑን አስረዱ። በተለይም ልዑል ራስ ካሣና ልዑል  ራስ ሥዩም በገለጹት አስተያየት፤ “….ሠራዊቱ መድከም ብቻ ሳይሆን አልቋል ማለት ይቻላል። ቢቆጠር ሕይወቱ ከተረፈው ይልቅ  በመርዝ የተቃጠለውና በመድፍ ተመትቶ የሞተው ይበልጣል። ….እግዚአብሔር ፈቃዱ ባይሆን ነው እንጂ፤ በትናንቱ ዕለት ጠላትን  ደህና አድርገን አድቅቀነው ነበር። ጠላታችን እኛን የበለጠን በምድሩ ውጊያ ሳይሆን፤ በማናውቀውና መሣሪያው በሌለን በሰማዩ ጦርነት  ነው። አሁንም ዛሬ ተነሥተን እንግጠመው ብንል፤ የሚያጠቃን ያው በተለመደው የፈሪ በትሩ ከሰማይ በሚያዘንብብን እሳትና መርዝ  ነው እንጂ፤ እንደ ወንዶቹ ፊት ለፊት ቢመጣብን አንበገርም ነበር። ስለዚህ፤ የሚሻለው ወደ ኋላ ተመልሰን ከሞት የተረፈው ሠራዊታችን የሚያገግምበት ዕድል እንዲያገኝ ማድረግና፤ ሌላም ተጨማሪ ጦር ለማዘጋጀት የሚቻልበትን መንገድ ማጥናት ይሻላል….”  አሉ። (ገጽ 246)
ንጉሠ ነገሥቱ ለዚህ የሚሰጡትን መልስ አንባቢው በተለይም እርስዎ ኮሎኔል መንግሥቱ በአንክሮ፤ በንጹህ ልቦናና በጥሞና እንዲያነቡና እንዲገነዘቡ አሳስባለሁ። ምክንያቱም እርስዎ የንጉሡን ወደ አውሮፓ ስደት ከታሪክ መዝገብ ሳይጠቅሱ እንደ ሽሽት እንጅ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል አገራት በተቀነባበረ ሴራ በተለይም በፋሽስት ኢጣሊያ ጦር በአገራቸውና በሕዝባቸው ላይ እየደረሰ የነበረውን ስቃይና በደል ለማሰማትና ዕርዳታ ለመጠየቅ የስራ ስደት እንደነበር ለመቀበል ፈጽሞ ስለማይፈልጉ ነው። ታሪኩ የኢትዮጵ ሕዝብ ስለሆነ ማንም ሊለውጠው፤ ሊያስተባብለው ወይንም እኔ ከማስበውና ከማምንበት የተለየ ስለሆነ አልቀበለውም ሊል አይችልም። እኔም ይህንን የምጽፈው አስተሳሰብዎትን አስለውጣለሁ ብዬ ሳይሆን፤ የአገሪቷና የንጉሡ ታሪክ የሁላችን ቅርስ ስለሆነ ሲገደፍ ዝም ብዬ ባልፈው ሕሊናዬ ሊወቅሰኝ እንደሚችል ስለተገነዘብኩ ነው።
ወደ ቁም ነገሩ እንመለስ። አምባሳደር ዘውዴ ረታ የንጉሡን መልስ እንደሚከተለው አስቀመጠዋል።
“ እኛ ከዚህ ካለንበት ቦታ ለቅቀን ወደ ኋላ ብናፈገፍግ፤ ድሉን ለጠላታችን አረጋግጥንለት ማለት ነው። እኔ እዚህ ጦር ሜዳ የመጣሁት ለኢትዮጵያ ነፃነት ደሜን ለማፍሰስ ቆርጬ ነው። ስለዚህ፤ ከዚህ በፊት ዓለሜን ከሕዝቤ ጋር እንደተካፈልኩት መከራውንም ከሕዝቤ ሳልለይ እካፈላሁ እንጂ፤ አገሬን ለጠላት አስረክቤ ወደኋላ በመመለስ ሕይወቴን ለማዳን አልሞክርም። ቀድሞውን እኔ እዚህ የመጣሁት፤ ድል አደርጋለሁ ብዬ አይደለም። ድል ብሆንም፤ ሕይወቴ እስኪያልፍ ድረስ ተዋግቼ ተግባሬን ፈጽሜ ሞትን ለመቀበል ነው። ሁላችሁም እንደምታውቁት አሁን ያለነው በሁለት ዓይነት ሞት መካከል ነው። አንደኛው ሞት፤ ከጠላት ጋር ተዋግቶ መሞት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ሲሸሹ በጠላት እጅ ወድቆ መሞት ነው። ከእነዚህ ከሁለቱ ይመረጥ ቢባል፤ ያለጥርጥር በጀግንነት ሲዋጉ መሞት ከሁሉም የበለጠ ክብር ነው። እኔ ዓላማዬ ይኽ ስለሆነ፤ የፈቀደ ከእኔ ጋር ይሙት። እኔ ግን ወደ ኋላ አልመለስም አሉ።” (ገጽ 246)
ከዚያም መኳንንቱና ሹማምንቱ በአቡነ ጴጥሮስ፤ በእጨጌ ገብረጊዮርጊስ እና በልዑል ራስ ካሳ ኅይሉ አማካኝነት ሽሽት ሳይሆን የእስትራተጅ ለውጥ ይደረግ ማለታቸውን አስረዱ። ከዚያም ንጉሡ የሚከተለውን አሉ። “ አሁን ሁላችሁም ጦሩ ወደ ኋላ ተመልሶ ሌላ ዝግጅት ቢደረግ ይሻላል ብላችሁ የተናገራችሁት፤ እኔን ለመደለል ሳይሆን ቁርጥ ሐሳባችሁ መሆኑን በመንፈስ አባቶቻችን ፊት በመሐላ አረጋግጣችሁልኛል። እንግዲህ፤ የሁላችሁም ሐሳብ እንደዚህ አንድ ከሆነ፤ እኔም ያቀረባችሁት እንዲፈጸም ይሁን እላለሁ።”
አምባሳደር ዘውዴ ረታ በጫካ እንዋጋ ? ወይስ በዤኔቭ እንሟገት በሚለው አርስተ ጉዳይ ላይ፤ ንጉሠ ነገሥቱ እንደ ኢ/አቆ ሚያዝያ 22  ቀን 1928 ከዘመቻ ተመልሰው አዲስ አበባ በገቡበት ዕለት የትግሉን ሂደት ለመገምገምና አማራጩን መንገድ ለመምረጥ በታላቁ ቤተመንግሥት ከፍተኛ ጉባኤ ተደርጎ ስለነበር፤ ሂደቱን እንደሚከተለው አስቀምጠዋል። ስብሰባውን የመሩት ንጉሠ ነገሥቱ ነበሩ። በስብሰባው የተካፈሉት በልዑል ራስ ካሣ አማካይነት ከመሳፍንቱና ከመኳንንቱ፤ ከሚኒስትሮቹና ከጦር አልቆቹ መካከል የተመረጡት ነበሩ። አምባሳደር ዘውዴ በገጽ 252 እንዳስቀመጧቸው ለውይይት ቀርበው የነበሩት ዐርስተ ጉዳዮች የሚከተሉት ነበሩ።
ሀ) ከእንግዲህ ወዲህ ጦር አሰባስቦ ጠላትን ፊት ለፊት ለመግጠም የሚያስችል መሣሪያም ሆነ በቂ ሠራዊት ስለሌለ ለነፃነት የሚደረገው ትግል በጫካ የሽምቅ ውጊያ በአርበኝነት ከማድረግ ሌላ አማራጭ መንገድ አለመኖሩን ሁሉም ተስማምተውበት በሙሉ ድምፅ ተወሰነ።
ለ) ጠላት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እየተቃረበ ስለሆነ፤ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት መምሪያ ሳይውል ሳያድር ወደ ይልባቦር ጠቅላይ ግዛት ጎሬ ከተማ እንዲዛወር ተወሰነ። በዚህም ጊዜ ጎሬ ላይ ለሚካሄደው የመንግሥት አስተዳደር ቢትወደድ ወልደጻድቅ ጎሹ፤ የቀዳማዊ ኀይለሥላሴ እንደራሴ ሆነው ተሾሙ።
ሐ) በመጨረሻው ብዙ የሐሳብ ልውውጥ የተደረገበት ትልቁ ጉዳይ፤ ንጉሠ ነገሥቱ ራሳቸው ዤኔቭ ሄደው የዓለም መንግሥታትን እርዳታ ቢጠይቁ፤ ይጠቅማል ወይስ አይጠቅምም በሚለው ሐሳብ ላይ ነው። በዚህ ጉዳይ ሦስት ሰዎች በየተራ የገለጿቸው አስተያየቶች የሁሉንም ሐሳብ ለውሳኔ ያመቻቸ ሆኖ ተገኘ።
ሶስቱ ሰዎች የሚከተሉት ነበሩ፤ ልዑል ራስ ካሣ ኅይሉ፤ ብላቴን ጌታ ሕሩይ ወልደሥላሴ እና አቶ መኮንን ሀብተ ወልድ። የሶስቱም አመለካከትና አቋም ተመሳሳይ ስለሆነ የብላቴን ጌታ ሕሩይ ወልደሥላሴን፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ አስተያየት እነሆ።
“ልዑል ራስ ደህና አድርገው ገልጸውታል። የአገርን ጠላት ለሚያህል ትልቅ ጉዳይ ጥረት ማድረግ የሚያስፈልገው፤ በሁሉም አቅጣጫ ነው። በጦር ሜዳውም፤ በፖለቲካውም፤ በፕሮፓጋንዳውም የሚከናወኑ ብዙ ነገሮች አሉ። ንጉሠ ነገሥታችን በጦር ሜዳ በሠራዊታቸው መካከል ሆነው ተዋግተዋል። መከራውንም በቆራጥነት ተቀብለዋል። አሁን ደግሞ በፖለቲካው ሜዳ ላይ ለመታገል፤ ዤኔቭ ሄደው ለመንግሥታት ማህበር የሚያቀርቡት አቤቱታ፤ ምን አልባት በእግዚአብሔር እርዳታ፤ የታላላቆቹ አገሮች ህሊና ተቀስቅሶ ለዚች በስቃይ ላይ ለምትገኝ አገራችን ይደርሱላት ይሆናል ብለን ተስፋችንን ማጽናት አለብን። ስለዚህ፤ ልዑል ራስ እንደተናገሩት የግርማዊነታቸው ወደ ዤኔቭ መሔድ ከልብ የምደግፍ መሆኔን በታላቅ ትሕትና እገልጻለሁ።” (ግጽ 253)
እንግዲህ እዚህ ላይ ኮሎኔሉንና አንባቢውን ማሳሰብ የምፈልገው፤ ከላይ ግልጽ እንደሆነውና ታሪክ እንደመሰከረው፤ ንጉሡ ወደ እንግሊዝና ዤኔቭ የተጓዙት የአገራቸውን ችግርንና የሕዝባቸውን ሰቆቃ ለድርጅቱ አባላትና ለሚመለከታቸው መሪዎች ለማሰማትና እርዳታ ለመጠየቅ ሲሆን፤ የኮሎኔሉ ክስ ታሪክን መሰረት ያላደረገ አሳዛኝ አሉባልታ መሆኑን ነው።
አምባሳደር ዘውዴ በገጽ 255 እና 256 የንጉሡን መልስ አስቀምጠዋል።
“ ሁላችሁም ለአገራችን ነፃነት የምትሰቃዩና መሥዋዕት ለመሆን ወደ ኋላ የማትሉ ናችሁ። በዚህም አኳኋን የምታቀርቡልን ምክር ሁሏ እውነተኛውንና በእግዚአብሔርም ሆነ በሰው ዘንድ የሚከበረውን ስለሆነ፤ ሙሉ ዕምነት እናሳድርበታለን።
ራስ ካሣ በተናገርካቸው ብዙዎች በሆኑት ፍሬ ነገሮች ውስጥ፤ ዤኔቭ ሄደን የምናቀርበው አቤቱታ አዳማጭ ካጣ፤ በአንደኛው ጠረፍ  በኩል ወደ አገራችን ተሻግረን የአርበኝነት ተግባር ለመፈጸም ይቻላል ያልከው፤ ከሐሳባችን ጋር የተገጣጠመ ሆኖ ስላገኘነው ደስ  ብሎናል።
ሕሩይ በተናገርከው ውስጥ፤ ለነፃነት መዋጋት በጦር ሜዳ ብቻ ሳይሆን፤ በፖለቲካውም፤ በፕሮፓጋንዳውም በኩል መሆን አለበት ያልከው፤ የምንስማማበት መልካም አስተያየት ነው።
መኮንን ሀብተወልድ የተናገርከው ከጠበቅነው በላይ ነው። ዤኔቭ ሄደን አቤቱታችንን የምናቀርብለት የመንግሥታት ማሕበር፤ጠላታችንን ከአገራችን ለማስወጣት በጦር ሠራዊት ሆነ በመሣሪያ ምንም ዓይነት እርዳታ እንደማይሰጠን ተስፋህን ቆርጠሀል። እንዳልከው፤ እኛም ይህን ያህል እናገኛለን ብለን ተስፋ አላሳደርንም። ተክለ ሐዋርያት በዤኔቭ በመጨረሻ ቀኑ ስለተናገረው የጠቀስከው ማለፊያ ነው። መቸም እሱ በጠባዩ ጥሩ ነገር ሲሰራ አይናገርም። እኛም የሰማነው እሱ ነግሮን አይደለም። የሚያሳዝነው ይህን የመሰለ ንግግር አድርጎ ከአዳራሹ ሲወጣ፤ ከጓደኞቹ የመንግሥታት እንደራሴዎች መካከል ያመሰገነውም ያደነቀውም አለመኖሩ ነው። ከዚህ ሌላ በተናገረው ውስጥ፤ ፈረንሣይ በሙሴ ላቫል መንግሥት ጉዳት ቢያደርስብንም፤ እንግሊዝም ፊት ለፊት ተጋፍጦ  ጠቃሚ እርዳታ ባይሰጠንም፤ ከአሜሪካም የጠበቅነውን ባናገኝም የወደፊቷ ኢትዮጵያን በማሰብ፤ ተስፋ መቁረጥ የለብንም። እነዚህ አገሮች ሁሉ ለዛሬው ባይሆኑን ነገ ተመልሰው አገራችንን ሊጠቅሙ ይችሉ ይሆናል ብለን ማሰብ ይሻለናል። ዛሬ ያለንበት ሁኔታ፤ በሞትና በሕይወት መካከል የሚያጣጥር ነው። የጦር መሣሪያ ባጠረን ጊዜ፤ ሠራዊታችንም ተዳክሞ በተበተነበት ሰዓት፤ ጥቂት ተዋጊዎች ይዘን ጠላትን እንመክታለን ብለን ብንነሣ፤ በመጀመሪያ ሰላማዊውን የአዲስ አበባን ሕዝብ እናስጨርሳለን። እኛም እናልቃለን። ስለዚህ፤ መንግሥታችን ወደ ጎሬ (ይልባቦር) ተዛውሮ በቢትወደድ ወልደጻድቅ ጎሹ እየተመራ እንዲቆይና፤ እኛም አቤቱታችንን ለዓለም መንግሥታት ማሕበር ለማቅረብ ወደ ዤኔቭ እንድንሄድ ያቀረባችሁልን ን ሐሳብ ተቀብለናል። በዚህ መሠረት፤ ቤተመንግሥታችንን ለቅቀን እንደወጣን፤ ጠላት የአዲስ አበባን ሕዝብ በመርዝና በጋዝ እንዳይፈጀው፤ ከተማው “ነፃ ከተማ” ተብሎ ይታወጅ።”
አንባቢው ከንጉሡ መልስ መገንዘብ የሚችለው፤ በቀውጢ ጊዜ ማሰብ መቻላቸውን ብቻ ሳይሆን አርቆ አስተዋይነታቸውንም ጭምር ነው። ምክንያቱም እንግሊዝን ፈረንሳይንና አሜሪካንን በችግራችን ወቅት ስላልደረሳችሁልን ወዳጅነታችሁን አንፈልግም ከማለት ይልቅ የወደፊቷን ኢትዮጵያን ብናስብ ጥሩ ነው ምክንያቱም ሊጠቅሙን ይችላሉና !
እንግዲህ የንጉሡ የትግል ታሪካቸው እንዲህ ሆኖ ሳለ፤ ኮሎኔሉ አዲስ እና ሊያውም አሳፋሪ የሆነ ለመፃፍ መነሳታቸው በጣም የሚገርምና የሚያሳዝንም ነው። የ ሰማኒያ አምስት/85 ዓመት ሽማግሌን ሕይወታቸው በእርስዎ በኮሎኔሉ ትዕዛዝ እንዲወሰድ ያደረጉት  አንስዎት፤ ታሪካቸውንም ለማጥፋት አቅደው መነሳትዎ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝም መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ። የእርስዎ አስራሰባት ዓመታት አገዛዝ ኢትዮጵያን በወጣት ልጆችዋ፤ በተማሪዎችዋ፤ በመሪዎችዋና በመኮንን ሰራዊቶችዋ ደም ያጠበ ሕዝቡ ሰላም አጥቶ በሁሉም ክፍለ ዓለም እንዲሰደድና እንዲበተን የሆነበት በአገሪቷዋ ታሪክ አሳፋሪ ምዕራፍ ሆኖ ለዘላም የሚኖር ይሆናል።
እዚህ ላይ አንባቢው ትንፋሹን ዋጥ በማድረግ “ሕይወታቸው በኮሎኔሉ ትእዛዝ ተወሰደ” ለሚለው ማስረጂያ የሚጠይቅ እንደሚሆን ይሰማኛል። ከመጽሐፍ ደራሲ ሻምበል ተስፋዬ ርስቴ ጋር ተዋወቁ። ኮሎኔሉ ሸሽተው አዲስ አበባን ከለቀቁ በኋላ፤ ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባና ሲይዝ፤ ሻምበሉ ከኮሎኔሉ ባለሥልጣናት ጋር የመታሰር ዕጣ ከደረሰባቸው አንዱ ናቸው። አምባሳደር ሞገስ ሀብተማሪያም ሻምበሉን ሲያስተዋውቁና ለመጽሐፋቸው ማሳሰቢያና ምስክርኑት ሲሰጡ (blurb)፤ የሚከተለውን ይላሉ።
“የመጽሐፉ ደራሲ ሻምበል ተስፋዬ ርስቴን በአንድ መሥሪያ ቤት ስንሰራ ዐውቀዋለሁ። በትምህርት ከተገነባው ዕውቀቱ ባሻገር፤ የግል ታታሪነት ባህሪውን አደንቃለሁ። ይህ ተሰጦው አብሮት ወህኒ ቤትም ገብቷል። የደርግ አባሎችንና በጊዜው የነበሩ ባለሥልጣናትን በአንድ ጣራ ሥር ስላገኛቸው ያልተጻፈውን የደርግ መንግሥት ታሪክ ለመክተብ በየትኛውም ቦታ ቢሆን የማይገኘውን ዕድል ተጠቅሞበታል። በተጨማሪም የተለያዩ መጽሐፍትን አንብቦ በዋቢነት አጣቅሷል። በሦስተኛ ደረጃ በሥራ ምክንያት የተለያዪ
ሁኔታዎችን ለመገንዘብ ስለቻለ የተሟላ ዝግጅት ሆኖለታል። እናም ይህ ታሪክ ተዝቆ የማያልቅን የወርቅ ማዕድን ይመስላል።”
ሻምበሉ “ምስክርንት በባለሥልጣናቱ አንደበት” በሚለው መጽሐፋቸው፤ ምዕራፍ አንድ ከገጽ 47-51 ስለንጉሡ አሟሟት የጻፉ ስለሆነ፤ አንኳሩን አቀርባለሁ። በረጋ መንፈስ ያነብቡ።
“ለውጡ የንጉሡን እና የመኳንቶቻቸውን ሥልጣን ብቻ ነጥቆ አላበቃም ሕይወታቸውን ጭምር ጠይቋል። ንጉሡ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ለአንድ ሙሉ ዓመት በሕይወት ለመቆየት አልታደሉም። በሻ/ መንግሥቱ ኅ/ማርያም ውሳኔ ኮትኩተውና ቀልበው በአዘጋጁት ጦር አባላት ታፍነው ተገደሉ። አሟሟታቸውን አስመልክቶ በምኒሊክ ቤተመንግሥት ውስጥ የመንግሥቱ ኅይለማርያም ጠባቂ የነበረው ልዩ ጦር የመቶ አዛዥ የነበሩት የመቶ አለቃ ወንድሙ አበበ “ ንጉሡ የተገደሉት በነሐሴ 20 ቀን 1967 ሲሆን የተቀበሩት በተከታዩ 21 ቀን  ነበር። ግድያው የተፈጸመው ከደብረብርሃን በመጡ ልዩ ጦር አማካይነት በሻ/ዳንኤል አስፋው ነው። ንጉሡ የተገደሉት ሰመመን ሰጭ
መድሐኒት በአፍንጫቸው እንዲያሸቱ ከተደረገ በኋላ በተንተራሱት ትራስ በማፈን ነበር። እንዲያፍን የተላከው ወ/ር ህሊናው እምቢ  ብሎት እየተርበተበተ በመቸገሩ ራሱ ዳንኤል አስፋው አፈናውን ፈጽሞታል በማለት ገልጽዋል።” መኮንኑ አክለውም “በዚያን ወቅት ቤተ መንግሥቱ ግቢ ውስጥ የተቀራረቡ ግን የተለያዩ ጥልቅ ጉድጓዶች ጦሩ መቆፈሩን አስታውሳለሁ። ምሽግ ለማድረግ እንዳይባል አጭር ነው የውሃ ማጠራቀሚያ እንዳይባል ደግሞ ሞላላ ነው ጥልቅ የሆኑ አራት ወይም አምስት ጉድጓዶች ተቆፍረው ውለው ሳያድሩ ደግሞ በስሚንቶ ተዘጉ በመለት የጉድጓዶቹን አቆፋፈርና መዘጋት ይገልፃሉ። ከላይ የተገለፅውን ሀሳብ ሻ/ል መንግሥቱ ገመቹ እውነት መሆኑን ገልጸዋል።” (እዚህ ላይ አንባቢውን ማሳሰብ የምፈልገው ሻ/ል መንግሥቱ ገመቹ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ድረስ  የኮሎኔል መንግሥቱ ልዩ ፀሐፊ ሁነው ያገለገሉ ናቸው) ሻምበል ተስፋዬ በመቀጠል “ በተለይ የታላቁ ቤተመንግሥት የጥገና ክፍል ኅላፊ ነበርኩ ጉድጓዶቹንም በወታደርች ያስቆፈርኩ እኔ ነኝ የሚሉት መሐንዲስ ጥላሁን ኪዳኔ” ሲገልጹ
“ግርማዊ ቀዳማዊ ኅይለሥላሴ እንደሞቱ ዐውቃለሁ የሞቱት ነሐሴ 20 ቀን 1967 ነበር። በነሐሴ 21 ቀን 1967 ከጧቱ 2:30  በመርዕድ ንጉሤ ተጠርቼ የከፈን ጨርቅና የሬሳ ሳጥን እንዳቀርብ ተጠይቄ ሰጥቻለሁ። መሐንዲሱ በመቀጠልም በሰባት ሰዓት ላይ ሦስት ጉድጓዶች 3 x 3 ሜትር አስቆፈርኩ። አራተኛ ጉድጓድም ተቆፍሯል። ቦታው በኋላ የፕሬዝዳንት ቢሮ ተሰራበት። አራት ጉድጓድ መቆፈሩ እኛ እንዳናውቅ መሰለኝ ጉድጓዶችን በዳንኤል አስፋው ትዕዛዝ በኮንክሪት ዘጋኋቸው፤ በአጭር ጊዜም በጉድጓዶቹ ላይ ቤት ተሠራ። ኢሕአዴግ ሲገባ ኮ/ል ስለሺ መኩሪያ ቦታውን ካሳየ በኋላ ስምንት ሜትር ተቆፍሮ ሦስት ሜትር ቱቦ ተገኘ፤ በኮ/ሉ መሪነትእንደገና ወደ ውስጥ ሦስት ሜትር ሲቆፈር የንጉሡ አጽም ተገኘ እና በሙሉ ወጣ በማለት ሰኔ 4 ቀን 1988 ለዋለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የምስክርነት ቃል ሰጥተዋል።” ( 47-48)
አንባቢው፤ ኮሎኔሉ ስለ ንጉሡ አሟሟት የሚሰጡትን መረጂያ እንደሚሻና መስጠቱም አግባብ ስለሆነ እነሆ።
“….ከታሰሩት ባለሥልጣኖች ብዙዎቹ የጤና ችግር እንደነበራቸው ሁሉ በሰኔ ወር 1967 ዓ.ም ንጉሡም በፊኛና በሽንት መሽኛቸው የጤና መታወክ ደርሶባቸዋል የሚል ሪፖርት ስለቀረብልን ሐኪማቸውን ፕሮፌሰር አሥራትን ጠርተን በማነጋገር ስለ ሁኔታቸው ከተረዳን በኋላ ከማረፊያቸው ወደ ሆስፒታል ሄደው አስፈላጊው ህክምና ይደረግላቸው ዘንድ በሙያው የላቁ ሐኪሞች ከውጭ እንዲመጡ በተጠየቀው መሠረት ታዝዞ መታከማቸውን ጤንነታቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደነበር አስተውለናል።
በነሐሴ ወር ከዚህ በፊት የታወቀው የጤና ችግራቸው ያገርሽ ወይም ሌላ ዛሬ የማላስታውሰው እንደገና ስለመታመማቸው ተነግሮን እንደተለመደው ተገቢው እንክብካቤ እንዲደረገላቸው ከታዘዘ በኋላ ማረፋቸው ስለተነገረን በብዙሃን ማሰራጫ ሕዝቡ እንዲያውቅ ተደረገ።” (270-271)
ከዚያም የሚከተለውን ስለወያኔ በመፃፍ ስለጉዳዩ ያላቸውን አስተያየት ያበቃሉ።
“ አብዮታዊው መንግሥት ከፈረሰና ኢትዮጵያ የወያኔ ቅኝ ከሆነች በኋላ፤ ወያኔ በሃገር ላይ የፈፀመውን ክህደት፤ የባዕድ ምንደኝነት፤ ፀረ አንድነት፤ የመገንጠልና የማስገንጠል ወንጀሉን የከለለና ከወንጀለኛነቱ የሚያፀዳው እየመሰለው አብዮታዊያንንና አብዮትን ለመኮነን ብሎ አውርቶ ያስወራቸውን ብዙ ወሬዎች ሰምተናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ ያለበት እውነት፤ ደርግ በቀዳማዊ ኅይለሥላሴ ሕይወት ላይ ምንም አይነት ውሳኔ ያልሰጠ መሆኑን ነው።” (271)
አንባቢውን አንድ የማሳስበው ዜና አለ። ይኸውም ኮሎኔሉ የንጉሡን ሐኪም ፕሮፌሰር አሥራትን ጠርተን አነጋግረን ነበር የሚለው ፍጹም መሠረት የሌለው አባባል እንደሆነ ፕሮፌሰሩ ለፕርፌሰር ጆን ስፔንሰር፤ የቀድሞው የንጉሡ የፖለቲካና የውጭ ጉዳይ አማካሪ የነበሩት፤
በሰጡት ቃለ ልውውጥ አስታውቀዋል። ፕሮፌሰር ጆን ስፔንሰር Ethiopia At Bay: A Personal Account of Haile Selassie’s  Years መጽሐፋቸው ውስጥ የሚከተለውን አስፍረዋል
“ The Dergue announced that Haile Selassie had been found dead in bed and that it had immediately summoned
the former emperor’s physician Dr. Asrat Woldeyes. With considerable courage, the doctor publicly denied any
such summons. He had been at home all day and no such call had ever reached him.”
ኮሎኔል፤ ከእርስዎ ጋር ይህንን የሐሳብ ልውውጥ ለማድረግ የስገደደኝ ዋናው ነገር፤ ንጉሡ ንጉሥ ተብለው ዘውድ ከጫኑበት ከመስከረም 27/1921 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ደርግ ከሥልጣናቸው እስካወረዳቸው ድረስ የንጉሡን አስተዳደር በታሪክ ትምህርት የሰለጠኑ ብዙ ምሁራኖች መረጃዎችን (data) በመሰብሰና በወቅቱ ከነበሩ ታሪካዊ ሂደቶች ጋር በማገናዘብ፤ ከእነርሱ ፍላጎትና ምርጫ ነፃ በሆነ መንፈስ መረጃዎችን ብቻ መሠረት ያደረገ ጥናተና ትንትና አድርገዋል። ማንኛውም ታሪክ ፀሐፊ ይህ ይጠበቅበታል። ንጉሡ በ ዤኔቭ በድርጅቱ አባል መንግሥታት መሪዎች ጉባኤ ተገኝተው አገራቸው ኢትዮጵያና ሕዝባቸው በፋሽስት ጣሊያን የወራሪ አውሮፕላኖች በሚዘንብባቸው የመስታርድ ጋዝ እየተቃጠሉና እየታፈኑ በስቃይ እየሞቱ ስለመሆናቸው እሮሮና አቤቱታ ማቅረባቸውን ማቃለልዎትና የሚገባውን ትኩረት አለመስጠትዎት፤ በተለይም በአሁኑ ወቅት የሲሪያ መንግሥት በሕዝቡ ላይ የተጠቀመውን የመርዝ ጋዝ በማውገዝ በአሜሪካና በረሽያ እንዲሁም በሌሎች መንግሥታት መካከል ከሚታየው የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ትግል አንፃር ሲታይ፤ የእርስዎ አመለካከት የቱን ያህል ኋላ ቀር እንደሆነ ያሳያል።
ኮሎኔል የሚከተለውን ጥያቄ በማቅረብ ከእርስዎ ጋር ያለኝን ውይይት አበቃለሁ፤
በመጽሐፍዎት ምዕራፍ አስር ገጽ 258 የኮሎኔል አጥናፉ አባተ ግድያ ለምን አስፈለገ ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ የሚከተለውን የደርግ መሠረታዊ መርሕን principle አስቀምጠዋል።
“ እዚህ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምናልባትም ዓለም ጭምር ስለደርግ ማወቅ ያለበት አንድ ነገር አለ። ለምንወዳት አገራችን ለኢትዮጵያ መሠረታዊ ለውጥ በመታገል ሕይወታችንን እንሰጣለን ብለን ለራሳችን ቃል ኪዳን ስንገባ፤ ከገባነው አብዮታዊ ቃል ኪዳን ዝንፍ ብንል፤ የኢትዮጵያ ትቅደም አብዮታዊ ሠይፍ ይረፍብን በማለት ምለን ነው።”
ጥያቄው እንግዲህ እርስዎ በዚያ ማለዳ ጥዋት ብላቴን የወታደር ሥልጠና በማግኘት ላይ የነበሩትን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን  ለማነጋገርና ለመጎብኘት በሚል ሰበብ ከአዲስ አበባ ተነስተው፤ የአውሮፕላኑን አብራሪ መንገዱን አስለውጠው፤ ጓዶችዎን ሳይሰናበቱ፤ ወደ ናይሮቢ ከዚያም አሁን መኖሪያዎ ወደ ሆነችው ወደ ሐራሬ መሄድዎን፤ ከደርጉ መሠረታዊ መርህ ጋር እንዴት ያስታርቁታል?
ጤና ይስጥልኝ !
ፕሮፌሰር ሰለሞን ተርፋ በ st2151@bellsouth.net አድራሻ ይገኛሉ

Thursday 19 September 2013

ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መስከረም12 ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ አስተዳደር ፓርቲው የሰልፉን ቦታ እንዲቀይር ጠየቀ

ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መስከረም12 ለሚያካሂደው ሰላማዊ ሰልፍ የአዲስ አበባ አስተዳደር ፓርቲው የሰልፉን ቦታ እንዲቀይር የጠየቀ ቢሆንም ፓርቲው ሰልፉን በመስቀል አደባባይ እንደሚያካሂድ በአፅንኦት በመግለፅ ዛሬ ደብዳቤውን ለአስተዳደሩ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊና ምክትል ኃላፊ በተገኙበት ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር አቶ ማርቆስ ብዙነህ አስፈርመው አስረክበዋል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ በፓርቲው በኩል የሰልፉ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ::

Challenge For Ginbot 7 leadership

This coming Sunday Sept 22 in Arlington, Virginia Ginbot 7 has called all Ethiopians for open public dialogue. On this public meeting Ginbot 7 chairman, Dr. Birhanu Nega and the Secretary, Andargatchew Tsige will be there. This is the “Mother of all Meetings”. Hope it will be aired live on ESAT.
Ginbot 7 has been on news recently after Dr.Birhanu’s leaked “embarrassing” audio and the interview Ato Andargatchew gave onESAT this month. Both are now to face the public on what they have said in public among many other questions.
Dr. Birhanu has a budget of 500,000 dollar from bankrupt Eritrea. The budget is used for Ginbot 7 and also for ESAT. Most of us believed that ESAT has nothing to do with Ginbot 7, that is now history, Ginbot 7 owns ESAT.
We all remember when Tamagne Beyne of ESAT fundraiser/Activist answered this question long time ago by saying if ESAT is aGinbot 7 media let it be, “Behonese”. Dr. Birhanu backed Tamagne positively thanks to the leaked audio that ESAT is financed byGinbot 7. It is no more “Behonese”, ESAT is a media wing of Ginbot 7.
Dr. Birhanu should be asked this coming Sunday why does he need to “Deceive” the public for almost three years. He should apologize for the public. ESAT should be judged by its own record so far the Ethiopian public see it as a positive media.
One thing ESAT can not do is to criticize its financiers, Isaias Afeworki and Ginbot 7. As long as it does that it will be on air. The Diaspora fundraising has to go on because Isaias Afeworki is not a reliable partner.
Ato Andargatchew is working hard to make sure Isaias finance is coming. That was the reason he came strongly to sell Isaias as “a man of the year of 2006″. Lionizing a dictator as a model for Africa “self rule and reliance”. If Ginbot 7 has such leadership in mind for future Ethiopia after Woyane it will not win any free and fair election.
Ethiopians should ask how could Ginbot 7 leadership defend working closely with Isaias Afewroki who on this new year of 2006 message to his subjects and the rest of Ethiopia said that Ethiopia is a creation of “Second World War” among many anti Ethiopia activities for more than two decades.
We all know that after Dr. Birhanu leaked audio that the fighting army of Ginbot 7 has yet to be formed. Eritrea will not send its army to overthrow Woyane in the near future. It is only the mass uprising of Ethiopians that is a strong possibility for which isaias is preparing itself to control such an event by sending ethnic armed groups to different part of Ethiopia for long term conflict.
We heard recently from Ato Andargatchew that “educated Ethiopians” are joining the Ginbot 7 fighting army. The braking news onESAT yesterday was about 4 Ethiopian Air Force pilots joining the army.
The Ethiopian army members that defected after the election 2005 massacre and many before that are now in Asmara fed and sheltered in their ethnic zones waiting to take power if there is a power vacuum in Ethiopia.
There is no armed rebellion in Ethiopia except low level skirmishes between Woyane and Ogaden National Liberation Front. The news of defecting members of the Ethiopian Army is a propaganda victory and should not be seen as a beginning of a military action against Woyane.
Ginbot 7 “Hulegeb Tigel” is not on field, it might be on air. Information is very important for the people of Ethiopia and ESAT has done its part on the last 3 years and should continue but ESAT can not liberate Ethiopia because it is not an armed organization.
If Ginbot 7 ”Hulegeb Tigel” means media and armed rebellion it is true it did very well on the media front but nothing on the battle front. If the media is not independent to criticize the armed part of its movement it is very troubling.
The challenge of Abune Filipose On Washington, D.C. recent ESAT organized meeting for the leaders of opposition/Ginbot 7 showed the dilemma of ESAT independence. Bishop Filipose challenged Ginbot 7 leaders where and what their army is doing.ESAT moderators/journalists did not ask follow up questions and the public questions regarding the Ginbot 7 army is surely censored.
This coming Sunday many people who care deeply for freedom to come to Ethiopia should be free to ask all questions. It is up to Ginbot 7 leadership to answer all, it will be a decision time for members and supporters of Ginbot 7.
For the rest of us who wish change in Ethiopia should not be shy in expressing our views regarding Dr. Birhanu and AtoAndargatchew led Ginbot 7 movement because we need them to succeed.
bbb

Wednesday 18 September 2013

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሻካሮቭ ሽልማት የ2013 ዕጩ ሆነው ተመረጡ።

ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ርዕዮት ዐለሙን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን  እና አሜሪካዊው  ኤድዋርድ  ስኖውደንን ጨምሮ  ሰባት  ሰዎች የአውሮፓ ህብረት ለነፃነት ታጋዮች በየአመቱ ለሚያዘጋጀው የ “ሻካሮቭ ሽልማት” የ2013  ዕጩ ሆነው ተመረጡ።
የአውሮፓህብረት የሻካሮቭ ሽልማት ኮሜቴ-ከህብረቱ የውጪ ጉዳይና ልማት ኮሚቴ እና ከሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ጋር በመሆን ትናንት ሰኞ ይፋ እንዳደረጉት  ማላላ ዩሳፍዛይ ከፓኪስታን፣ ኤድዋርድ ስኖውደን ከ አሜሪካ፣ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ ከ ኢትዮጵያ፣ አሌስ ቢያላትስ ኪ፣ኤድዋርድ ሌበር፣ እና ሚኮላስታትኬቪች ከቤላሩስ፣ ሚካኤል ኮድ-ኦርኮቭስኪ ከሩሲያ  ሲታጩ በቡድን በቅርቡ ቱርክ የነፃነት መናፈሻ እንዳይፈርስ ድምፃቸውን ያሰሙ ተቃዋሚዎች እና የሲ.ኤን.ኤን የነፃነት ፕሮጀክት ታጭተዋል።
የመጨረሻዎቹ ሦስት ዕጩዎች ከ15 ቀን በኋላ የፊታችን መስከረም 20  ቀን የሚለዩ  ሲሆን፤አሸናፊውም  መስከረም 30 ቀን በሚደረገው የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ ስብሰባ ይፋ እንደሚሆን  ከህብረቱ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አሸናፊው፤ ህዳር 11 ቀን በምስራቅ ፈረንሳይ በምትገኘው ስትራስበርግ ከተማ  በሚዘጋጀው ሥነ-ስርዓት ላይ ሽልማቱን ይቀበላል።
በ አውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባል በሚስ አና ማርያ ጎሜዝ የተጠቆሙት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ ጥቆማቸው በሌሎች 40 የፓርላማ አባላት ድጋፍ ማግኘቱ፤ ሽልማቱ  ከሁለቱ ኢትዮጵያውያን ሊያልፍ እንደማይችል አመላካች ነው ሲሉ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በሻካሮቭ ሽልማት አሸናፊ የሚሆኑ ከሚቀዳጁት ክብር በተጨማሪ  እስከ 50 ሺህ ዩሮ የሚደርስ የገንዘብ ሽልማትም ይበረከትላቸዋል።
የ ኢትዮጵያ ሳተላይት ራዲዮና ቴሌቪዥን ለርዕዮት ዓለሙና ለስክንድር ነጋ መልካም ዕድል ይገጥማቸው ዘንድ ልባዊ ምኞታቸውን ይገልጻሉ።
ESAT

አንድነት መስከረም 19 በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ ይወጣል አለ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን በመጪው መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ እንደሚወጣ አስታወቀ…
*መኢአድ በሰልፉ ላይ ንቁ ተሳትፎ አደርጋለሁ ብሏል
በዘሪሁን ሙሉጌታ
 የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በበኩሉ ሰልፉ እንዲሳካ ከሰልፉ ዋና አስተባባሪ አንድነት ፓርቲ ባልተናነሰ ሁኔታ ንቁ ተሳታፊ እንደሚሆን ገልጿል።
የአንድነት ፓርቲ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስራት ጣሴ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ሰላማዊ ሰልፉ ዋና ዓላማ ህገ-መንግስታዊ ጥሰትን መቃወምና መንግስትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ድርድር ለማምጣት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
ሰልፉን በዋናነት እያስተባበረ ያለው አንድነት ፓርቲ ለአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ባቀረበው ቅጽ ላይ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በግምት ግማሽ ሚሊዮን (500ሺህ) ሰው እንደሚገኝ ይፋ አድርጓል። በሰልፉ ላይ መጠሪያቸውን 33 ያደረጉ ወደ 23 የሚሆኑ ፓርቲዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
ቀደም ሲል የአንድነት ፓርቲ በሀገሪቱ ልዩ ልዩ ከተሞች ለሦስት ወራት ያህል ‘‘የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት’’ በሚል ርዕስ ሰላማዊ ሰልፎች ሲያካሂድ ቆይቷል። ከሕዝባዊ ንቅናቄው ዘመቻ መካከል የፀረ-ሽብር ህጉ ይሰረዝ የሚለው ይገኝበታል። ፓርቲው ይህንኑ ዘመቻ ማድረጉንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ፓርቲዎችን ማከራከሩ አይዘነጋም።
በመጪው መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በሚካሄደው ሰልፍ ላይ ሁሉም ፓርቲዎችን የጋራ መግባባት በደረሱበት ‘‘ህገ-መንግስታዊ ጥሰትን መቃወም’’ የሚል ጥቅል ሃሳብን በማንገብ፣ የፀረ-ሽብር ህጉና ሌሎች አፋኝ ሕጎች እንዲሰረዙ፣ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቄዬአቸው እንዲመለሱ፣ የሃይማኖት ነፃነት እንዲከበርና የኑሮ ውድነት እና የስራ አጥነት ጥያቄዎች በጎላ መንገድ በሰልፉ ላይ እንደሚንፀባረቁ ከአቶ አስራትና ከአቶ አበባው ገለፃ መረዳት ተችሏል።
‘‘የኢህአዴግ አባል መሆን ከኢትዮጵያዊ ዜግነት በላይ የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል’’ ያሉት አቶ አስራት፤ ኢህአዴግ አባል ያልሆነ ብዙሃኑ የሙሉ ዜግነት መብቱን እየተነፈገ ነው ብለዋል። ይህ ሁሉ የሚያሳየው በሀገሪቱ የሕግ የበላይነት ጠፍቶ ኢ-ህገመንግስታዊነት መስፈኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ፤ ለህግ የበላይነት ለህገ መንግስታዊነት ክብር የሚሰጥ የከተማዋና የአካባቢዋ ህብረተሰብ በሰልፉ ላይ በመውጣት ተቃውሞውን እንዲያሳይ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የመኢአድ ፕሬዝዳንት ፓርቲያቸው ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን ከዚህ ቀደም በመኢአድ ጽ/ቤት ሕዝባዊ ስብሰባ ማስተባበሩን በማስታወስ መስከረም 19 ቀን በተጠራው ሰልፍ ላይ መላ አባሎቹና መዋቅሩን በማንቀሳቀስ በሰልፉ ላይ በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የሰልፉ አላማ ህብረተሰቡ ያለበትን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ሃይማኖታዊ ችግሮች ገደባቸው እያለፉ መሆኑን በገሃድ የሚያሳይበትና መንግስትም ከገባበት ኢ-ህገመንግስታዊ አካሄድ ቆም ብሎ ወደ ውይይት እንዲመጣ ለማስገደድ እንደሆነም ከፓርቲ አመራሮቹ ገለፃ መረዳት ተችሏል።
ሰልፉን ለማስተባበርና ስኬታማ ለማድረግ በአንድነት በኩል ልዩ ግብረሃይል መቋቋሙን የጠቀሱት አቶ አስራት፤ ሕዝቡም ያለአንዳች ማወላወል ወደ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን እንደሚያሳይም እምነታቸውን ገልፀዋል። ከሰልፉ በኋላ መንግስትና ተቃዋሚዎች በጋዜጣና በሬዲዮ የሚያደርጉትን የአሉባልታ ዘመቻ በማቆም ወደ ህጋዊና በሁሉም ወገኖች ተአማኒነት ወደአለው የውይይት መድረክ ይመጣሉ የሚል እምነት አለኝ ብለዋል።
“መንግስት አንድነት ሰላማዊ ሰልፍ በጠራበት ዕለት በተመሳሳይ በየቀበሌው ስብሰባ መጥራቱን እንዲሁም በቅርቡ ከሰማይ ወርዷል የተባለ መስቀል በአቃቂ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የገብርኤል ቤተክርስቲያን በዕለቱ ሄዶ እንዲያይ መደረጉ በሰልፉ ላይ ህብረተሰቡ እንዳይገኝ ከወዲሁ የሚደረግ ጥረት ቢሆንም በእኛ በኩል ህብረተሰቡ ያለበትን አንገብጋቢ ችግር ስለሚገነዘብ ሰልፉ ላይ ከመገኘት ወደኋላ አይልም። መንግስት ትንንሽ ምክንያቶችን ሰበብ በማድረግ መሰናክል ለመፍጠር ቢሞክርም የሰልፉ አላማ ይመታል” ሲሉ አቶ አስራት ገልፀዋል።
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ )

የኤርትራ ጉዳይ በሶስት ትውልዶች ውስጥ


map of eritrea


የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ እንደቀልድ እና እንደ እልህ የጀመሩት ”ኤርትራ ኢትዮጵያዊ አይደለችም” ብሎም ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” አጀንዳን የሻብያ አጀንዳ እንዲሆን ካስደረጉ በኃላ ከእሳቸው በፊት የነበረው ትውልድ ባይቀበላቸውም የእሳቸውን ትውልድ ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” የሚለውን ገለፃ ለመንገር አላንገራገሩም። አቶ ኢሳያስ በአንድ ጎናቸው ተንቤን ትግራይ ቢወለዱም ያነሷት ጉዳይ ግን ኢትዮጵያን ለማዳከም ለዘመናት ከሚያልሙ አንዳንድ የአረብ ሀገራትም ሆነ ጎረቤት ሱዳንን የሚያማልል ብሎም ዳጎስ ያለ ድጎማ የሚያስገኝ የወቅቱ አዋጪ ”የገበያ ማስታወቅያ” መሆኑን የተረዱት ይመስላሉ።
ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዩንቨርስቲ በነፃ ትምህርት ዕድል ይማሩ የነበሩት አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ ”የኤርትራ ነፃነት ግንባር” (ELF) ከመቀላቀላቸው በፊት በቻይና የፖለቲካ እና የወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ተጉዘው እንደነበር ተወስቷል። አቶ ኢሳያስ እና ድርጅታቸው ከሰላሳ አመት ውግያ በኃላ ”ሁሉ ነገር ተፈፀመ!” ብለው ተናግረው ሳይጨርሱ ሌላ ጦርነት ”በባድሜ መሬት ሰበብ” እውነታው ግን የምጣኔ ሀብት የበላይነት ለመያዝ ከሕወሓትጋር በነበረ ግፍያ አዲስ ጦርነት ውስጥ ገብተው አስር ሺዎች ሲረግፉ አብረው ከአቶ መለስ ጋር ተዋናይ ሆነው ታዩ። ያ ”የቅኝ ግዛት ጥያቄ” ያሉት ጉዳይ አስመራን ከያዙ በኃላም ጥያቄው ተወሳሰበባቸው።
አቶ ኢሳያስ እና ድርጅታቸው ሻዕቢያ ስልጣን ከያዘ ሃያ ሁለት ዓመታትን አስቆጠረ። በእነኝህ ሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ የኤርትራ ተወላጆች ሲነገራቸው የነበረው ”የአፍሪካ ታይዋን ትሆናለች” ትንታኔ ሐሰት መሆኑን ተረዱት። ይልቁን ከአስመራ ዩንቨርስቲ ጀምሮ እስከ ቀድሞ በውሱን አቅም ይሰሩ የነበሩ ድርጅቶችን የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም ተዳከመ። በአስር ሺዎች በሱዳን፣በኢትዮጵያ፣በየመን አድርገው ተሰደዱ።ኤርትራ ከዲፕሎማሲ እስከ አካባቢ ሃገራት ድረስ እንድትገለል አደረጉ። የአቶ ኢሳያስ ”የዓለም እይታ ፍልስፍና” የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሆነ። እሳቸው አሜሪካንን የሚያዩበት እይታ የግል አስተያየት መሆኑ ቀረና የመንግስት ቃል አቀባይ የሚናገረው ”መዝሙረ-ኤርትራ” ሆኖት አረፈው። አምባገነንነት አስደናቂው እና አዝናኝ ገፅታው ይሄው ነው።መሪው ሲያስነጥሰው ሁሉም ለመሳል ጉሮሮውን ይጠራርጋል።
”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” የሚለው የአቶ ኢሳያስ ትውልድ ጥያቄ ዛሬም ፈተና ላይ ነው።
አቶ ኢሳያስ እና ትውልዳቸው የወቅቱ ገበያን ስሌት ያደረገው ”የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” አሁን በተነሳው ትውልድ የሚሞገትበት ጊዜ እሩቅ የሚመሰለው ካለ በሃሳቡ የመቀጠል መብቱን አከብራለሁ። ለእኔ ግን ይህ ጥያቄ በእራሱ የሚሞገትበት ጊዜ እንደሚመጣ አስባለሁ። የማኅበራዊ ትምህርት ሳይንስ ለምሳሌ የፖለቲካ ሳይንስ እንደ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ በቤተ-ሙከራ (ላብራቶሪ) ጥናት ውጤቱን ከወዲሁ ለመወሰን አይቻልም። የሚቻለው ነገር ካለፉት፣አሁን ካለው እና መጪውን ከመተለም አንፃር በምክንያታዊ አቀራረብ ከወዲሁ ሁኔታዎችን መመልከት ነው። ከእዚህ አንፃር የኤርትራ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሶስተኛው ትውልድ ላይ የወደቀ የእዚህ የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄም በእርሱ ታሪካዊ ሂደት የሚፈነዳበት ሁኔታ ይኖራል። የሶስቱ በኤርትራ ጉዳይ የተሳተፉ ትውልዶች ጥያቄዎች እንደዘመናቱ ”የፖለቲካ ገበያ አዋጭነት” እንደ አቶ ኢሳያስ ያሉ ተዋናዮች ተጫውተውበታል። ጥያቄው የሶስተኛውንም ትውልድ ጥያቄ አሁንም ”የፖለቲካ ገበያውን” ተመልክተው ጥያቄውን በመሞረድ የአቶ ኢሳያስ ቡድን ሊመራው ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ ፈታኝ ነው። መልሱ አይመስልም ነው።

ሶስቱ በኤርትራ ጉዳይ ላይ የነበሩ ትውልዶች

የመጀመርያው ትውልድ

የመጀመርያው ከአቶ ኢሳያስ በፊት የነበሩት የጣልያን እና የእንግሊዝን ቅኝ ግዛት ግፍ የሚያውቁቱ ሲሆኑ ይህ ትውልድ ከ 1900 ጀምሮ እስከ 1960ዎቹ የነበረ ትውልድ ነው። በእዚህ ዘመን ውስጥ ኤርትራ መከራ ፍዳ በቅኝ ገዢዎች ማየቷን በአይን የተመለከቱ፣ የምስራቅ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን እንደህልም የሚያልሟት እና የሚወዷት ኢትዮጵያ ክፉ እንዳይነካት እንደ አይን ብሌን  የሚሳሱላት ትውልድ ነበሩ። ይህ ትውልድ በግድም ይሁን በውድ በጣልያን የባንዳ ሰራዊት ውስጥ ገብቶ እስከ ሊብያ እና ኢትዮጵያ የዘመተ ቢሆንም ”ኢትዮጵያ ሀገሬን ቅኝ ገዢ አይዛትም” ብሎ እንደ አብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶምን አፍርቶ ግራዝያንን ያቆሰለ ትውልድ ነው። የኢጣልያ ስብከት  አላማው እና ግቡን ስለተረዳ ኢትዮጵያ እናት ሀገሬ አይደለችም የሚል አስተሳሰብ ማሰብ በራሱ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን እራስን መካድ መሆኑን ጠንቅቆ የተረዳ ትውልድ ነው።
መላከ ሰላም ዲመጥሮስ ገ/ማርያም (ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትዋሃድ እጅጉን ከገፉት የመጀመርያው ትውልድ የኤርትራ ተወላጅ)
መላከ ሰላም ዲመጥሮስ ገ/ማርያም (ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትዋሃድ እጅጉን ከገፉት የመጀመርያው ትውልድ የኤርትራ ተወላጅ)
ጣልያን ኤርትራን በያዘችበት ጊዜ በአስመራ ከተማ ውስጥ
  • ለነጮች የተከለሉ ምግብ ቤቶች እንደ አሸን መብዛታቸውን ፣
  • ከምሽቱ 11 ጀምሮ አንድም ኤርትራዊ በአስመራ ጎዳና እንዳይዘዋወር (ጣልያን እና ነጮች ብቻ የተፈቀደ ስለነበር) መታገዱን፣
  • በአውቶቡስ ውስጥ ሲሄድ ኤርትራውያን ከነጮች ጋር እንዳይቀላቀሉ በመጋረጃ እንዲከለል ተደርጎ እንደ ዕቃ ይሄድ የነበረ መሆኑን፣
  • እስላሙ እና ክርስቲያኑ እንዲጋደል የእስላም ቤት ከውጭ የቀይ ምልክት የክርስቲያን ቤት በነጭ ቀለም እንዲቀለም  መድረጉን ወዘተ ያውቃል።
ይህ ትውልድ የቀንም ሆነ የማታ ሕልሙ እናት ሃገሩ ኢትዮጵያን ማየት ነበር። ለእዚህም ነበር ብዙ ሺዎች በሁመራ -ጎንደር እያደረጉ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት እና በንግድም ሆነ በከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ሳይቀር ቦታ እያገኙ የመጡት። ይህ ትውልድ ነበር ”ኢትዮጵያ ወይንም ሞት!” ብሎ” የሀገር ፍቅር ማኅበር” መስርቶ የንጉሡ ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ ሆኑ ንጉሡ ሲያመነቱበት የነበረውን የተባበሩት መንግስታትን የፌድሬሽን ጥምረት ውሳኔ ከክህደት ቆጥሮ ንጉሱን መቆምያ መቀመጫ አሳጥቶ ወደ ውህደት የመራው። አምባሳደር ዘውዴ ረታ ስለነበረው ትውልድ ሲናገሩ ”ኢትዮጵያ ኤርትራ እንድትዋሃድ ለማድረግ ሞከረች ከሚለው ይልቅ ኤርትራውያን ውህደቱን አለመፈፀም በእራሱ ትልቅ ክህደት እንደተፈፀመ ከመቁጠራቸውም በላይ ኤርትራውያን በእራሳቸው ጥያቄ ውህደቱን ከመነሻው እስከመጨረሻው ድረስ በሁለት እግሩ አስኬዱት ማለት ይቀላል። እኔ በወቅቱ ምስክር ስለነበርኩ” ያሉት።

ሁለተኛው ትውልድ

ይህ ትውልድ ከ 1960ዎቹ እስከ 1990 ያለው ትውልድ ነው። ይህ ወቅት የሶሻልስቱ አብዮት፣ ወታደራዊ ደርግ፣ የኢትዮጵያ የለውጥ ማዕበል በተለያዩ ኃይሎች እጅ በመከፋፈሉ እና እንደ ድርጅትም ”ሻብያ” ጎልቶ ከመውጣቱ አንፃር የኤርትራ ጉዳይ በተወሰኑ መሳርያ በያዙ ኃይሎች እጅ ወደቀ። ሌላው ቀርቶ የቆላው የኤርትራ ሕዝብ ጥያቄ የሚሰማው ከማጣቱም በላይ ተወካዮቹ ወደ ደርግ መጥተው አቤት ለማለት ተገደዱ። የእዚህ ትውልድ ጥያቄ ከቀይሽብር መከራ ጋር ተዳምሮ ”ነፃነት!ነፃነት!መብት!” የሚሉትን ጥያቄዎች ሁሉ ከመለየት እና የእራስን መንግስት ከማቆም ጋር ተዛመደ። አምባገነንነትን መዋጋት የእራስ ሀገር ከመመስረት ጋር ያለው ተዛምዶ እና ቅራኔን የሚፈታ ጠፋ። የወቅቱ የብሔር ብሄረሰቦች ጥያቄ ማሰርያ ውሉ ጠፍቶ መገንጠልን መድረሻው ሲያደርገው የሚጠይቅ ጠፋ። ጉዳዩ ያሳሰባቸው የመጀመርያው ትውልድ አባላት የሚሰማቸው ጠፋ። ይልቁንም በዘመነ ደርግ  የተከበሩ የደጋው ሃማሴን እና  የኤርትራ ቆላ ተወላጅ  አባቶች በተለይ  ”የሀገር ፍቅር ማኅበር” አባላት እና መስራቾችም ጭምር ‘የኤርትራ እና የኢትዮጵያን አንድ ሕዝብ መሆን አትናገሩ’ ተብለው ድብደባ፣ዛቻ አንዳንዶቹም እስካሁን በሻብያ ወኪሎች እንደሆነ በሚታሰብ መልኩ ቤታቸው መግብያ ላይ የጥይት አረር ሆኑ። ይህንን እውነታ ወደፊት ታሪክ በሚገባ ይዘክረዋል። የሁለተኛው ትውልድ መነጋገርያ ውይይት፣ መግባባት እና ሃሳብን መግለፅ ሳይሆን ”ቀና ብሎ ያየህን በጥይት አረር ድፋው” መሰል የወረደ አስተሳሰብ ነውና ብዙዎች ደርግ እራሱ ሊታደጋቸው አለመቻሉን ሲመለከቱ ወደተለያዩ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ሃገራት ተሰደዱ። ዘመንን ዘመን ተካውና የአቶ ኢሳያስ ትውልድ በ 1983 ዓም ከሰላሳ ዓመት ጦርነት በኃላ አስመራ ሲገባ ሁኔታው አዲስ ምዕራፍ ያዘ።
አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ
አቶ ኢሳያስ አፈወርቅ
ትንሽ ቆይቶ ግን ነገሮች ተቀየሩ። በመጀመርያ በኤርትራ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንን ያገቡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የያዙትን ንብረት ትተው ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ ተደረጉ። በመጀመርያ ጊዜ የነበረው አወጣጥ በተለይ ህወሃትም በወዳጅነት ላይ ስለነበር የተፈናቃዮቹን መከራ የሚያደምጥ ጠፍቶ በአዲስ አበባ የሚታተሙ የግል ጋዜጦች ብቻ የምስኪን ስደተኞች ችግር ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስተጋቡ ብቸኛ ጠበቃዎች ሆኑ። ውሎ አድሮ ግን ሻብያ እራሱ ከህወሓት ጋር አዲስ ፍጥጫ ውስጥ ገባ። በለስ ቀንቷቸው አዲስ አበባ የገቡቱ ተፈናቃዮች በሳሪስ ቃሊቲ አካባቢ በድንክዋን ሆነው ቀይ መስቀል ይጎበኛቸው ገባ። ይህ በሆነ በሰባተኛው ዓመት ብዙም ስለ ጀት ማብረር ችሎታ የሌላቸው የአቶ ኢሳያስ አይሮፕላን አብራሪዎች ትግራይ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን በቦንብ ደበደቡ። ሕፃናት በትምህርት ገብታ ላይ ሳሉ ተቀጠፉ።
ከጥቂት ወራት በኃላ የበቀል እርምጃው ቀጠለ። ከሰባ ሺህ በላይ የሚሆኑ ቀኝ እና ግራ እጃቸውን ያልለዩ ሕፃናትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩ ትውልደ ኤርትራውያንን ህወሓት በማባረሩ ኢትዮጵያውያንን አሳዘነ። ብዙዎቹ ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት በአንዲት ጀንበር ሲነጠቁ አነቡ። ከቤት ወጥተው የማያውቁ ልጆች በአውቶቡስ እየተጫኑ በትግራይ በኩል ደቡብ ኤርትራ ላይ ተወረወሩ። ምናልባት የሁለተኛው ትውልድ (የአቶ ኢሳያስ ትውልድ) የመጀመርያው ትውልድ ሲናገረገው የነበረውን ሁሉ ማሰብ የጀመረው በእዚህ ወቅት ይሆናል።የሆነው ሆኖ ይህ ወቅት ”መንግሥታት” ተብለው የሚጠሩ ሁለት አካላት አስመራ እና አዲስ አበባ ላይ ሆነው በከረመ የመለያየት ፖለቲካቸው ሕዝብን ስያሰድዱት ተስተዋሉ። የሁለተኛው ትውልድ አባዜ በእዚህ አላበቃም በሻብያ እና በህወሓት መካከል የነበረውን የቆየ ቁርሾ ”ወደ ሀገር አጀንዳነት” ተቀየረ እና ሁለቱም የህዝብን ስሜት እየኮረኮሩ በባድማ መሬት ስም ውግያ ገጠሙ።በውግያው የኢትዮጵያ ሰራዊት ገፍቶ  አስመራ ሊገባ ሰዓታት ቀሩት። በውቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ የነበሩት ወይዘሮ ሶሎሜ በአሜሪካዊ እንግሊዝኛ በተቃኘ ንግግራቸው ለቢቢሲ ”ፎከስ ኦን አፍሪካ” ፕሮግራም ”we gave them our lesson” ”ዋጋቸውን ሰጠናቸው” አሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሁለቱም ወገን የአፈር ሲሳይ ሆነው ነበር።

ሶስተኛው ትውልድ

በኤርትራ ጉዳይ የሶስተኛው ትውልድ ታሪክ የሚጀምረው ከ 1992ቱ የባድሜ ውግያ በኃላ ነው። ኢትዮጵያ እናቴ! ያለው የመጀመርያው ትውልድ አለፈ። ”የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” ያለውም ሁለተኛው ትውልድ ብሎት ብሎት ደከመው። በመጀመርያ ኤርትራን በሀገርነት በማወጅ (በኤርትራ በኩል) እንዲያውጅ በማገዝ (በአቶ መለስ በኩል) ተፈፅሟል። ሺዎች ኢትዮጵያ ነክ ናችሁ ተብለው ከኤርትራ ተባረዋል። ሌሎች ሺዎች ኤርትራ ነክ ናችሁ ተብለው ከኢትዮጵያ ተግዘዋል። በድንበር ሰበብ ብዙ አስር ሺዎች አልቀዋል። ሁለተኛው ትውልድ ደከመው። ከእዚህ ሁሉ በኃላ የመጀመርያው ትውልድ የመከረውን የፍቅር ጥሪ እያሰበ ሳለ ሶስተኛው ትውልድ ተነሳ።
ሶስተኛው ትውልድ በተለይ ሁለተኛው ትውልድን የሚያደንቀው በጠበንጃ አያያዙ ካልሆነ በቀር ልማት እና እድገትን ሲያመጣ ማየት አልቻለም። ይልቁን ይህ ትውልድ በመረጃ ዘመን እንደመኖሩ ታሪክ ሲነገረው በደቂቃዎች ውስጥ የተባለው ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ ስለሚችል በአራዳ አነጋገር ”የማይሸወድ” ሆነ። ከሁሉም በላይ አቶ ኢሳያስ ቀደም ብለው ያነሱት ”የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” አባባል ውላ አድራ በእዚህ በሶስተኛው ትውልድ ከባድ ፈተና ገጠማት።
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከባለቤቱ ጋር
ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከባለቤቱ ጋር
  • ”ኤርትራ ቅኝ ግዛት ተይዛ የነበረው በኢጣልያ እና በሞግዝቷ እንግሊዝ ነው እንጂ በኢትዮጵያ መች ሆኖ ያውቃል?” የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄ ቀጠለ…
  • ”በደል እና ጭቆና ቢኖርም ይህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የመጣ መከራ አይደለም ወይ?”
  • ”የኃይለስላሴ አስተዳደርም ሆነ የደርግ ቀይሽብር በአስመራ ላይ በተለየ ተደረገ ወይስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የቀመሰው ገፈት ነበር?”
  • ”ይህ የሚያሳየው የአቶ ኢሳያስ ትግል መሆን የነበረበት ከደርግ አምባገነንነት እና ከንጉሡ ፍፁም ዘውዳዊ ስርዓት ለመላቀቅ ብሎም ስልጣንን ከማዕከላዊ መንግስት ለመንጠቅ መሆን የለበትም ነበር ወይ?” ወዘተ ጥያቄዎች አቶ ኢሳያስ እንዲመልሱለት ሶስተኛው ትውልድ የሚጠይቃቸው ናቸው።
ሶስተኛው ትውልድ ድንበር ከድንበር ቢዘጋበት በመከራ ላይ ሆኖ በስደት ሲገናኝ የሁለተኛውን ትውልድ ሥራ ማብሰልሰሉ አልቀረም። ጊዜ፣ ቦታ እና አጋጣሚ ሲገጥመው ግን የአቶ ኢሳያስ ”የቅኝ ግዛት ጥያቄ” ብለው የሰሩት ዶሴን ይዘት እራሳቸውን አቶ ኢሳያስን ይጠይቅበታል።
የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄ አልቆመም…
  • “ከኢጣልያን የዘር መድሎ የተላበሰ አገዛዝ ከእንግሊዝ ከሞግዝትነት ባለፈ ሌላ ቅኝ ገዢ ለመሆን ታደርገው ከነበረው ዝግጅት ኤርትራ የዳነቸው ከኢትዮጵያ ጋር በፌድሬሽን ከተቀላቀለች በኃላ አይደለም ወይ?”
  • “አስመራ በነፃነት ከ 11 ሰዓት በኃላ መሄድ የተቻለው፣የፈለጉበት ምግቤት (የነጮች የጥቁሮች) ሳይባል መመገብ የተቻለው ከፌድሬሽን በኃላ አይደለም ወይ?”
  • “በአስመራ መንገድ ላይ በእግር ለመሄድ ‘ነጮች በሚሄዱበት መንገድ ላይ መሄድ አይቻልም’ ተብሎ ለጥቁር በተከለለ መንገድ ላይ ብቻ ይሄድ የነበረው ኤርትራዊ በነፃነት በሁሉም የእግር መንገድ ላይ በዜግነቱ ኮርቶ መሄድ የቻለው ከፌድሬሽን በኃላ አደለም ወይ?”
  • ኢጣልያ ለኤርትራ ተወላጆች ትምህርት እስከ አራተኛ ክፍል ብቻ እንዲሆን መወሰኗ ያቆመው እና ኤርትራውያን የትምህርት ዕድል እስከፈለጉት ክፍል ድረስ መግፋት የቻሉት ከፌድሬሽን በኃላ አይደለም ወይ?
  • “ለመሆኑ  በኤርትራ የተወለደው ኢትዮጵያ ከተወለደው በምን ተለያየ?  በንግግር? ወይንስ በመልክ? በአመጋገብ? ወይንስ በሃይማኖት በምን ተለያይቶ ነው የዲሞክራሲ፣ የመብት እና የስልጣን ጥያቄ ”የቅኝ ግዛት ጥያቄ” የተባለው? የሶስተኛው ትውልድ ጥያቄ ይቀጥላል።
አበቃሁ
ጌታችው በቀለ (የጉዳያችን ብሎግ)
ኦስሎ

የቤተመንግስት ደህንነት ሃላፊ ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


የነአዜብ ቡድን እየተመታ ነው!!
 
የቤተ-መንግስት የደህንነት ጥበቃ ዋና ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት የሕወሐት አባል አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ምንጮች አስታወቁ። አቶ ጌታቸው ቀደም ሲል በክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽን የደሕንነት ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ሃላፊ ተደርገው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፣ ከዚያም ወደ ቤተ መንግስት ተዛውረው መመደባቸውንና በተጨማሪ የአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ሃላፊ በመሆን ከአቶ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል። የአቶ መለስና ወ/ሮ አዜብ የቅርብ ሰው የሆኑት አቶ ጌታቸው ተፈሪ በነበራቸው ታማኝነት የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ ተደርገው በአቶ መለስ ተመርጠው እንደተሾሙ ያስታወሱት ምንጮች፣ በማያያዝም እስከ 1994ዓ.ም የቤተመንግስት የደህንነት ጥበቃ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ዘርኡ መለስ በወቅቱ ከአቶ መለስ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ልይነት ምክንያት ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው የቀድሞ “ኮከብ ሬስቶራንት” የአሁኑ “ሚልክ ሃውስ” መኖሪያ ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ቤታቸው ውስጥ አንገታቸው በስለት ታርዶና በድናቸው ተበላሽቶ መገኘቱን አመልክተዋል። ይህን አሰቃቂ ግድያ ያከናወነው አሁን በእስር ቤት የሚገኘው የቀድሞ አገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊና የአቶ መለስ ቀኝ እጅ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል መሆኑን ምንጮቹ አጋልጠዋል።
የነ አዜብ ቡድን እየተመታ ነው!
የነ አዜብ ቡድን እየተመታ ነው!
አቶ ጌታቸው ተፈሪ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገው በደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮች፣ በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ጠቁመዋል። አቶ ጌታቸው ተፈሪ — የወ/ስላሴ መታሰር ቅር ሳያሰኛቸው እንዳልቀረና በተጨማሪም የነአዜብ ቡድን ደጋፊ መሆናቸውን ምንጮቹ አመልክተዋል።
 
በሌላ በኩል የኢ.ኤም.ኤፍ ምንጮች ቀደም ብለው እንደገለጹት፤ ባለፈው አመት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ “ቤተ መንግስቱን አንጠብቅም” ብለው ንዝህላልነት ካሳዩት መሃል እኚሁ የቤተ መንግስት ጥበቃ ሃላፊ ጌታቸው ተፈሪ አንዱ ነበሩ። በተለይም አዲሱ ጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከገቡ በኋላ የቤተ መንግስቱ ጥበቃ እንዲላላ ከማድረግ አልፈው፤ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር አክብሮት የማይሰጡ ሰው እንደነበሩ ይታወቃል።

Monday 16 September 2013

“የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ

አንዱ ሌላውን የማጥፋት እሽቅድድም!


tplf-vs-eplf


አምባገነነኖች ከሚታወቁበት አንዱና ዋንኛ መለያቸው መካከል ሁለተኛ ሰው አለማዘጋጀታቸው ነው። አቶ መለስ በድንገት ሲስፈነጠሩ በውል የታየው አስከሬን ደብቆ ድብብቆሽም የዚሁ ውጤት ነው። ኢሳያስ ከስልጣን ቢወገዱ ማን ይተካቸዋል? የሚለው ችግርም ጎልቶ የሚታየው ከዚሁ የአምባገነኖች በሽታ አንጻር ነው።
ግጭትና ችግር ከመፈጠሩ በፊት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያንጫርረው ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) ፍርሃቻም ከዚሁ የመነጨ ይመስላል። በኤርትራ ህዝቡ በቃኝ ወደ ማለቱ ደረጃ መቃረቡን የሚጠቁመው የዘንድሮው ዓመት ሪፖርት ኤርትራ በቅርቡ መንግስት አልባ የመሆን እድሏ ሰፊ እንደሆነ ያወሳል። በቅርቡ “የሚከሽፉ መንግስታት” በሚል ስማቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ አገሮች መካከል ኢትዮጵያም ተመልክታለች።
እኩል ወደ ስልጣን የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ ደረጃቸው ቢለያይም ሊድኑ በማይችሉበት ደረጃ መበስበሳቸው በገሃድ የሚታይ እውነት እንደሆነ አብዛኞች ይስማማሉ። ከበሰበሱበት ባህርና ችግር ለመውጣት አግባብ ያለውን መንገድ ከመከተል ውጪ አንዱ ሌላውን ቀድሞ ለማጥፋት እሽቅድድም መርጠዋል። የዚሁ የእሽቅድድማቸው መድረሻ መሰረት ደግሞ አንዱ ለሌላው ተቃዋሚ ምርኩዝና አጋር የመሆንና አንዱ በሌላው መንኮታኮት የግል ትርፍን አስጠብቆ ለመዝናናት እንጂ ህዝብን ማዕከል ያደረገ አይደለም።
ኤርትራ “በነጻ” ምድሯ ላይ “አቅፋና ደግፋ” የያዘቻቸው የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች የሚታይ ውጤት ባለማስመዝገባቸው ተግባር ለሚናፍቁ ወገኖች ጉዳዩ “ከበሰበሰ ባህር” አይነት ሆኖባቸው ዓመታት ተቆጥረዋል። ሰሞኑንን ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የግንቦት7 ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይፋ ያደረጉት መረጃ አዲስ የውይይት አጀንዳ ዘርግቷል።
በኤርትራ መንግስት በኩል የሚደረገው ድጋፍ “ባለ አራትና አምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ የመታገል ያህል ነው” በማለትandargachew ያሞካሹት አቶ አንዳርጋቸው “ታይቶ የማይታወቅ፣ ከሚገባው በላይ የበዛ” ሲሉ የገለጹት የኤርትራ ድጋፍ አስቀድሞም ቢሆን ውጤት ማስመዝገብ ያልቻለው ኤርትራ በከተሙ ተቃዋሚዎች ችግር እንጂ በኤርትራ መንግስት እንዳልሆነ በቅርብ ሆነው ማየትና መረዳታቸውን በመግለጽ ምስክርነት ሰጥተዋል።
ይህ መረጃ ከተሰራጨ በኋላ ከኢህአዴግ ወገን ሁለት አንኳር ጉዳዮች ተሰምተዋል። በኤርትራ ላይ መከላከልን መሰረት ያደረገው ፖሊሲ “ተመጣጣኝ ርምጃ መውሰድ” በሚል በመቀየሩ ኢህአዴግ ባልተጠበቀ ወቅትና ጊዜ አስቀድሞ ጥቃት ለመሰንዘር እንደሚችል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለኤርትራ ያዘጋጀላትን አዲስ የአስተዳደር ቅርጽ ተግባራዊ የሚያደርጉ ድርጅቶችን ወደ ግንባር መግፋት የሚሉት የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ ሁለተኛው ግን ከወትሮው ለየት ያለ ሆኖ ተገኝቷል።
አዲስ ራዕይ የሚባለው የኢህአዴግ ልሳን ይፋ እንዳደረገው ወደ ጎረቤት አገራትም ሆነ ሌሎች አካባቢዎች የሚሰደዱ ዜጎች በተቃዋሚ ወገን ለውትድርና እየተመለመሉ እንደሆነና ይህ ሁኔታ በዝምታ ከታየ ስርዓቱ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል አመላክቷል። ከዚህም ጋር ተያያዥነት ባለው መልኩ ሌሎች ወገኖች ግብጽ እጇን የዘረጋችላቸው ክፍሎች ስለመኖራቸው መረጃዎች እንዳሉ ለማሳበቅ ሲሞክሩ ሰንብተዋል። ከዚህ አንጻር ቀደም ሲል ከነበሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በተለየ መልኩ ኢህአዴግ ስጋት ውስጥ ስለመሆኑ ይሰማል።
ከላይ የቀረቡት ሁለቱ አንኳር ጉዳዮች መላምት ሳይሆኑ በውል የተቀመጡ እውነታዎች ናቸው። ኢህአዴግ አደራጅቷቸው የስደት ፓርላማ የመሰረቱ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ዝግጅታቸውን ተያይዘውታል። እነዚህ የብሔር ድርጅቶች የሚበዙበት ጥምረት ህወሃት እንደሚያስበው ወደ ስልጣን ከደረሱ ኤርትራን ቢያንስ በስምንት “ብሔር ተኮር” ክልል ይከፍሏታል። በአሜሪካ ኒው ጀርሲ ጠቅላይ ግዛት ሮዋን ዩኒቨርስቲ የማርኬቲንግ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር በርሀ ሃብተጊዮርጊስ በ9/8/2010 ለጀርመን ሬዲዮ እንደገለጹት “ኢትዮጵያ በራሷ ልክ የተሰፋ መንግሥት ነው ለማቋቋም የምትፈልገው፤ ይህ አይሳካም” በማለት ተናግረው ነበር። መምህሩ አያይዘው በቋንቋና በብሔር ኤርትራን የመተልተል እቅድ መያዙንም አጥብቀው ተናግረዋል። ህወሃት ይህንኑ አላማውን ለማሳካት ሲል ከሰላማዊ ድርድር ማፈግፈጉን አመልክተዋል።
ኤርትራ ጨለመች – “ከወያኔ ይልቅ ጨለማ !!”
በበርካታ የኤርትራ ተወላጆች ዘንድ አንድ ትልቅ ስጋት አለ። በኤርትራ ቆላማ ክፍል የሚኖሩ ሙስሊሞች ቋንቋቸው አረቢኛ እንዲሆን ምኞት አላቸው። ቁጥራቸው ከክርስቲያኑ ስለሚበልጥ ይህንኑ የብሔር ጥያቄ ላይ የተንጠለጠለ በራስ ቋንቋ የመስራት መብት እንዲከበር ይፈልጋሉ። ከዚህም በላይ በደገኞች እጅ የተያዘውን የስልጣን ሞኖፖሊ አጥብቀው ይቃወሙታል።
ከሐምሌ 24 – ነሃሴ 3 ቀን 2010 ዓ ም ድረስ “ብሔራዊ ጉባኤ ለዴሞክራሲ ለውጥ” በሚል ርዕስ አዲስ አበባ ተደርጎ በነበረው ጉባኤ ጥምረት የፈጠሩት አስር ተቃዋሚዎች ከበርካታ ጭቅጭቅ በኋላ አቋም አድርገው የወሰዱት “የቋንቋና የብሔር መብት ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው” በሚል ነው። በወቅቱ የተያዘውን አቋምና የጉባኤው የመጨረሻ ውሳኔ ይፋ ሲሆን የተገለጸው ኢሳያስ ሲወገዱ ስልጣን ተረክቦ ኤርትራን የሚያስተዳድር የስደት ፓርላማ ለማቋቋም ነበር።
eritrea-opposition-conferenceከ330 በላይ ተወካዮች ከተገኙበት ስብሰባ ውስጥ 55 አባላት ያሉበት አደራጅ ኮሚሽን በማቋቋም የተጠናቀቀውን ጉባኤ አስመልክቶ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ “ተቃዋሚዎች አቋማቸው ግልጽ አይደለም” በማለት ለመቃወም ጊዜ አልወሰዱም። ከእርሳቸው በተለየ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ትምባሆ ሞኖፖል ዋና ስራ አስኪያጅና የንግድ ምክር ቤት ጸሐፊ የነበሩት አቶ ረዘነ ሃብቱ በበኩላቸው ህግና ህገ መንግስት እንደማያውቅ የጠቀሱት ስርዓት አሁን ባሉት ተቃዋሚዎች ሊተካ እንደሚችል እምነታቸውን ያስቀምጣሉ።
በኮታ የሚሸጥ ቁራሽ ዳቦ ለመግዛት ሌሊት የሚሰለፉት የኤርትራ ተወላጆች፣ ኑሮ ቢግልባቸውም፣ የመኖር አቅም ቢያጡም፣ ውትድርናና የነጻ አገልግሎት ቢያንገሸግሻቸውም፣ በነጻነት የመደራጀትና በሰውነት ብቻ ሊያገኙት የሚገባቸው መብቶች ባይኖሩዋቸውም፣ ከሁሉም በላይ አሁን መብራት በሳምንት በፈረቃ አንድ ጊዜ ቢደርሳቸውና በሳምንት ስድስት ቀን በጨለማ ቢቀመጡም “ወያኔ” ያበጀው ስርዓት እንዲመሰረትላቸው አይመኙም።
አስገራሚው አቋማቸው ሁሌም የሚመዘነው ከ”ወያኔ” ጋር እንጂ ከጥቅል የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዳልሆነ በይፋ ይናገራሉ። የህወሃት ሰዎችና ደጋፊዎችም ይህንን አቋም ይረዱታል። ኢሳያስን ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት በተፈለገው ፍጥነት ሊተገበር ያልቻለበት አንዱና ትልቁ ምክንያት ይህ በመሆኑ “ኢሳያስን ከአህጉርና ከዓለም ኣቀፍ ፖለቲካ በመነጠል አስልሎ ማጥፋት” የሚለውን ሁለተኛው ስልት ኢህአዴግ ዘግይቶም ቢሆን ለመጀመር መገደዱንና በስተመጨረሻ ውጤት እንዳገኘበት ይገልጻሉ።
በዚሁ የማስለል ስልት ወንበራቸው የተፈረካከሰው አቶ ኢሳያስ “የኤርትራ ወጣቶች እንዲሰደዱ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት እየሰራ ነው” በማለት በጃንዋሪ 2013 የፈረንጆች አዲስ ዓመት ተናግረዋል። ችግር የሚቆላውን ህዝብ “የኤርትራ ህዝብ ችግር የለበትም ቀልማጣ ነው” ሲሉም አሙቀውታል። ኤርትራ በውጪ አገር መንግስታትና በኢትዮጵያ አማካይነት ጫና እንደተደረገባት መሆኑና መሸሸግ አልተቻላቸውም። ሰሞኑንን ለቅዱስ ዮሐንስ በቃለ ምልልስ መልክ ለህዝባቸው የደሰኮሩት ኢሳያስ የአገሪቱ ወጣቶች ለመኮብለላቸው ምክንያቱ ችግር ሳይሆን ኢትዮጵያንና አሜሪካንን ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አድርገዋል። የኢሳያስ ደጋፊ ምሁራን ሳይቀሩ ህወሃት ኤርትራን ከዓለምአቀፍ መድረክ በመነጠል እንደጎዳቸው ማመናቸውን የሚገልጹ እንደሚሉት ህወሃት “የኤርትራን መንግስት በሚገባ አስልሎታል። አቅም አልባና የቀጣናው ተራና ውዳቂ፣ ህግና ወግ የማያውቅ ዱርዬ መንግስት ተደርጎ እንዲሳል አድርጎታል” ይላሉ። አያይዘውም “ህወሃት በግብሩ ከሻዕቢያ ባይሻልም በጉዳይ አስፈጻሚነትና አፍሪካ ህብረትን በወጉ መቆጣጠር በመቻሉ የውጭ ገጹን ማሳመር በመቻሉ ከሻዕቢያ የተሻልኩ ነኝ ብሎ ማሳመን ችሏል፡፡”
eritreans in line
በኤርትራ የዳቦና ወተት ወረፋ (ፎቶ: ኒው ዮርክ ታይምስ)
በዚሁ መነሻና በውስጥ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ቀውስ እየወላለቁ አሉት ኢሳያስ ከስጋትና ከፍርሃቻ እንደሆነ በሚያስታውቅ ጎልዳፋ ፍልስፍና “ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዢ ስር ነበረች ተብሎ በተደጋጋሚ ሲወራ ለወያኔዎች ኩራት ሆኗቸዋል” ሲሉ ለተደገሰላቸው ድግስ የኤርትራ ተወላጆችን እልህ ውስጥ የሚከትት ንግግር አሰምተዋል። በርካቶች ኢትዮጵያን ዝቅ አድርገው የተመለከቱ መስሏቸው ቢናደዱም አቶ ኢሳያስ ግን በሳቸው ዘመን ኤርትራ በህወሃት ቅኝ ግዢ እንዳትያዝ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፋቸው እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ለጎልጉል ተናግረዋል። ጳጉሜን 2፤ 2005ዓም (በሴፕቴምበር 7፤ 2013) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ኤርትራ ለኢትዮጵያዊያን ነጻ መውጣት ሊታመን የማይችል ድጋፍ እየሰጠች ነው ባሉበት ማግስት ኢሳያስ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ የተፈጠረችው መቼ ነው?” በማለት እንደ አንድ ታሪክ አልባ አገር አበሻቅጠው ማቅረባቸው ቀደም ሲል የነበረውን ቅሬታና ጥርጣሬ እንዲያገረሽ አድርጎታል የሚሉ ወገኖችም አልታጡም።
ህወሃት ልክ እንደነ ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና መሰል ድቃይ ድርጅቶች ኤርትራን እንዲመሩ ያደራጃቸውን ክፍሎች አስተምሮና አንቅቶ ከመዘጋጀቱ ጋር ተዳምሮ ኢሳያስን ጤና የነሳቸው ጉዳይ ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) በዝርዝር ያስቀመጣቸው መሰረታዊ ጉዳዮች የኤርትራን መንግሥት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ስለከተቱት ነው። በጦር አመራሮችና በፖለቲካ ክንፎች ውስጥ የተከሰተ አለመተማን፣ ተሞክሮ ከሸፈ የተባለው መፈንቅለ መንግሥት፣ የማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት አሊ አብዶን ጨምሮ የቅርብ ታማኞች መክዳት፣ የወጣቶች አገር ጥሎ መኮብለል፣ እስር፣ የኑሮ ውድነት፣ የምንዛሬ ችግር መባባስ ህወሃት ለሚወስድባቸው ማንኛውም ርምጃ መቋቋም የሚችሉበት ትከሻ ስለሌላቸው እንደሆነ ከግምት በላይ አስተያየት የሚሰጥበት እውነት ነው። በስንቅና ትጥቅም ደረጃ አይመታጠኑም የሚሉ ባለሙያዎችም ካላይ በቀረበው ሃሳብ ይስማማሉ።
ምንም ሆነ ምን ህወሃት ኢሳያስን አስወግዶ አሻንጉሊት መንግስት ከሚያስቀምጥላቸው ይልቅ የኤርትራ ተወላጆች ከኢሳያስ ጋር በመሆን መሰቃየትን እንደሚመርጡ ቀደም ሲል ታጋይ የነበረችና አሁን በስደት ላይ የምትገኝ የኤርትራ ተወላጅ ትናገራለች። ባልደረባዋም ሃሳቧን ይጋራታል። “በየትኛውም መመዘኛ ህወሃት (ወያኔ) ኤርትራ ላይ አሻንጉሊት መንግስት አስቀምጦ አይገዛንም። ኢሳያስ ይሻለናል። በብሄር ሊበጣጥሱንና እኛ በማያቋርጥ ችግር ውስጥ ስንኖር እነሱ ሊስቁብን ነው” በማለት አንገቱን እያወዛወዘ አስተያየቱን ሰጥቷል። ሁለቱም ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀዋል።
ሻዕቢያ ኢትዮጵያ ጠንካራ ሉአላዊ አገር እንድትሆን ይፈልጋል?
“ለኢትዮጵያዊያን አገራቸው ክብራቸው ናት። ማንም በታሪካቸውና በማንነታቸው እንዲሳለቅ አይወዱም። መለስ የሚባሉት ክፉ መሪ ህዝብ እንደረገማቸው ያለፉት ኢትዮጵያንና ታሪኳን ከፍ ዝቅ በማድረግ በማራከሳቸው ነው። ታሪካችንን ወደ 100 ዓመት በማኮሰስ፣ ሰንደቃችንን ከተራ “የመገነዣቸው እራፊ” ጋር በማመሳሰላቸው ሲተፉና ሲወገዙ ኖረው መሞታቸውን በማውሳት  ኢሳያስ ደፍረውና ታብየው “ለመሆኑ ኢትዮጵያ ማን ናት?” ለማለት የተነሱበትን ምክንያት በማስቀደም አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
“በስብሶ ሊወድቅ የደረሰ ስርዓት የሚመራ፣ በልመናና ከስደት በሚገኝ ቀረጥ የምትተዳደር፣ ዳቦ በራሽንና በወረፋ የሚሸጥበት አገር እየመሩ፣ በ20ኛው ክፍለዘመን በኩራዝ የምትበራ አገር ይዘው  ራሱን ችሎ የሚኖርን ህዝብ መተንኮስ አግባብ አይደለም” በሚል ኢሳያስን የተቃወሙ ጥቂት አይደሉም። የኢሳያስ ንግግር በስደት “መብታቸው ተከብሮ” አዲስ አበባና የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የራሳቸውን አገር ሰዎች ጭምር የሚያስደስት እንዳልሆነ፣ ይልቁኑም የሚያሸማቅቅ እንደሆነ ነው የሚሰማው። የዚያኑ ያህል “ጨንቋቸው ነው። ምን ይበሉ? አዲስና ለህዝብ ጥቅም ያለው ወሬ ሲጠፋ ከታሪክና ከምኞት ጋር መጣላት የጊዜው አማራጫቸው ነው” በማለት ያጣጣሏቸውና ምላሽም እንደማያስፈልጋቸው የገለጹ ጥቂት አይደሉም።
አቶ ኢሳያስ ሲፈልጋቸው “ኢትዮጵያ በቅኝ ስትገዛን ኖራለች፤ ነጻነት እንፈልጋለን” በሚል በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ህይወትን የገበሩት ሳያንስ ዛሬ፣ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ መቼ ነው የተፈጠረችው” ሲሉ ጠይቀው “ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድል የተቀዳጁ ለጥቅማቸው ማስጠበቂያ ሲሉ የፈጠሯት አገር መሆኗን ነው እኔ የማውቀው” ማለታቸው ኢሳያስ መቼም ቢሆን ኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አመለካከት የጸዳ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ ይሆናል። ከዚህ አንጻር ብቻ ሳይሆን በበርካታ ጉዳዮች ችግር ቢኖርብንም “ኢሳያስን ጠንቀቅ” የሚሉ ወገኖች ለክብር ቅድሚያ እንዲሰጥ ይመክራሉ።
-   ማታ ነው ድሌ” ማን?
“ሻዕቢያና ኢህአዴግ ተመሳሳይ ፖሊሲ መከተል ጀምረዋል” የሚሉ የጎልጉል የዘወትር አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግ ሶማሊያ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ ሻዕቢያም እየተገበረው ነው” ይላሉ። አያይዘውም “ኢህአዴግ በሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር መስራትና፣ ኢትዮጵያ የምታስቀምጠውን አጀንዳ የሚሸራርፍ መንግስት በማዕከላዊ መንግስትነት እንዲቀመጥ እንደማትፈልግ ሁሉ፣ አሁን አሁን ኤርትራም የጀመረችው የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች በዚሁ መልኩ የማደራጀት ስራ ነው” በማለት ይዘረዝራሉ።
በሶማሊያ ከኢህአዴግ ሃሳብ ውጪ ለመንቀሳቀስ የሚያስብ ማዕከላዊ መንግስት ብቅ ቢል ወዲያው መብራቱን ያጠፉበታል። በደቡብ ሱዳን ያለው እውነታ ተመሳሳይ ነው። ደቡብ ሱዳን እየተመራች ያለችው በኢህአዴግ፣ በተለይም በህዋሀት ሰዎች መሆኑንን የሚያመለክቱት አስተያየት ሰጪ፣ “ያለ ምንም ማመንታት ኤርትራ ከውስጥ ያለባት ችግሯ፣ በዓለምአቀፍ ደረጃ የደረሰባት ኪሳራና በመንግሥቱ ውስጥ ከተፈጠረው መፈረካከስ ጋር ተዳምሮ የጎረቤቶቿ እድል ይገጥማታል። ኢሳያስ ያበቃላቸዋል። ኢህአዴግ የሰራው መንግስት ይቋቋማል” ብለዋል።
ኢህአዴግ በአገር ውስጥ ያለበት ቀውስ ቀኑን ጠብቆ የሚፈነዳ እንደሆነ ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ “የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ኢሳያስ አሁን ባሉበት ደረጃ ለኢህአዴግ ስጋት አይሆኑም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ኢህአዴግ በግፍ፣ በኑሮ ውድነት፣ ፍትሃዊ ባልሆነ የሃብት ክፍፍል፣ በሙስና፣ ወዘተ የፈጠረው ምሬት ከመጠን ያለፈ ቢሆንም እንደ ሻዕቢያ በቀላሉ የሚናድበት ደረጃ ያለ እንደማይመስላቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግን ከምንም በላይ የሚያሰጋውና የሚያስጨንቀው የከረረ ሰላማዊ ትግል ነው። በትክክለኛ መርህ ላይ የተመሠረተ እውነተኛ ሰላማዊ ትግልና ሕዝባዊ እምቢተኝነት ስለማይገባውና በጉዳዩ ላይ በቂ ተሞክሮ ስለሌለው የሚያሸብረውና አስገድዶ ወደ ድርድር የሚያመጣው እሱ ብቻ እንደሆነ አምናለሁ” ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል። በሌላ ወገን ደግሞ የተቃዋሚዎች አቅም ከቀድሞው በተለየ የተጠናከረና የፕሮፓጋንዳውን ዘመቻ በማሳደጋቸው ምን አልባት መከላከያ ሰራዊቱ አካባቢ የመከፋፈል ችግር ሊፈጠር ይችላል የሚል ግምት ያላቸውም ብቅ እያሉ ነው።