Friday 26 July 2013

በኦሮሚያ 10 ተጠርጣሪ ሙሰኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ


በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ተመዝብሯል
owwce


  • ተጠርጣሪዎቹ ሽፈራው ጃርሶ የሚመሩት ቦርድ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ናቸው
ከሙስና ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አሥር የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባለፈው ሰኞ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡
ኮሚሽኑ በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው ከእነዚህ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪ፣  ሌሎች 15 የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ፍለጋ መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ግዥና የመንግሥትን የፋይናንስ ሕግ ባልተከተለ መንገድ ኪራይ ፈጽመዋል በሚል ጥርጣሬ መሆኑን፣ የክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ለአንድ ዓመት ባካሄደው ጥናታዊ ምርመራ በዚህ የሙስና ወንጀል መንግሥትን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንዳሳጣው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኮሚሽኑ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በቁጥጥር ሥር የዋሉት የክልሉ ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢፋ በዳዳ፣ ምክትላቸው አቶ ጎዳና ዳባ፣ የፋይናንስ ቡድን መሪ አቶ ተሾመ አዱኛ፣ አቶ ተክሉ ተፈራ፣ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት ወ/ሮ መስከረም ኤጀርሳ እና አቶ ግርማ ቂጣታ፣ የመጋዘን ኃላፊዋ ወ/ሮ ራሔል አሰፋና የክፍያ ሰነድ አዘጋጅዋ ወ/ሪት ሳምራዊት ግርማ፣ የጨረታ ኮሚቴ አባላት አቶ ዘለቀ ጎንፋና አቶ ዱላ ማሞ ናቸው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከተመሠረተ ሁለት አሥርት ዓመታትን ያስቆጠረ የክልሉ ግዙፍ የልማት ድርጅት ነው፡፡
ኢንተርፕራይዙ በኦሮሚያ ክልልና በሌሎች ክልሎች የሚካሄዱ የመስኖ ግድቦችና የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንገዶችንና ስታዲየሞችን ከመገንባቱም በላይ፣ በፌዴራል መንግሥት የሚመራውን ለደዴሳ ስኳር ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ግድብ በደዴሳ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
ኢንተርፕራይዙ ሁለት ቢሊዮን ብር የተመዘገበና 500 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ባለቤት ነው፡፡ ኢንተርፕራይዙ የሚተዳደረው በሥራ አመራር ቦርድ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሥራ አመራር ቦርዱን በመምራት ላይ የሚገኙት ቀደም ሲል የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር በኋላም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ሽፈራው ጃርሶ ናቸው፡፡
በጉዳዩ ላይ የክልሉን የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታከለ እንኮሳ አስተያየት እንዲሰጡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ (ሪፖርተር)

“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”


ሃይሌ! ወደ ፓርላማ?
haile gebreselasse


የዛሬ 10 ወር የሻለቃ ሃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ፖለቲካ የመምጣት ሁኔታን አስመልክቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሃተታ አቅርቦ ነበር፡፡ (እዚህ ላይ ይመልከቱት) ሰሞኑን አትሌቱ ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጎቱንና “በምርጫ” ለመወዳደር መፈለጉ ብዙ እየተባለበት ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን ላለው ሁኔታ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ሃተታ በድጋሚ አትመነዋል፡፡

“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው።
ሃይሌ ይህንን የተናገረው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ ም ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ጋር በመንግስት ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) አስተያየት በሰጠበት ወቅት ነበር። የቀድሞውን ስርዓትና ትውልድ “ድንጋይ ዳቦ በነበረበት፣ ፍራፍሬ ከጫካ ያለምንም ድካም ከሚሰበሰብበት” ዘመን ጋር ያወዳደረው ሃይሌ፣ “የአሁኑ ትውልድ” በማለት ያሞካሸውን ስርዓት ከተፈጥሮ ጋር ጦርነት በማካሄድ ለውጥ ማስመዝገበ መቻላቸውን አስምሮበታል።
“የባለ ራዕዩ መሪ” አቶ መለስ ገድል ለመዘከር በተዘጋጀ ቅንብር ላይ  በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጥ የታየው ሃይሌ “አሁን የት ነው ያለነው?” በማለት ጠይቆ “አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ለማግኘት ነው የምንጋፋው? አውሮፓ ሄደን እዛው ለመቅረት ነው…” በማለት ስደትን መርጠው ከአገራቸው የሚወጡትን ሸርድዶ አልፏል። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ለስደት የሚዳርግ ጉዳይ የለም ወደ ማለት አዝምሞ ተናግሯል። ሃይሌ ይህን ይበል እንጂ በተቃራኒው እስረኞች እንዲፈቱና የፖለቲካ እርቅ እንዲሰፍን እሰራለሁ ከሚሉት ፕሮፌሰር ይስሃቅ ጋር በሽምግልና እያገለገለ መሆኑ በአገሪቱ ውስጥ የሚታው እስርና እንግልት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቅሱ አስተያየት ሰጪዎች የሃይሌን አስተያየት “ለንብረት ዋስትና የሚከፈል የንግግር ቫት” በማለት አጣጥለውታል።
ከኤርትራ ጋር ከተደረገው በቀር በኢትዮጵያ ይህ ነው የሚባል ጦርነት እንዳልተካሔደ ኢህአዴግን የሰላም አባት አስመስሎ ሃይሌ አመልክቷል። በዚሁም ምክንያት ቀደም ሲል ለጦርነት ይውል የነበረው የአገሪቱ በጀት ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ዞሯል ብሏል። የኢህአዴግ ተወካይ መስሎ አስተያየት የሰጠው ሃይሌ “ይህ አሁን የታየው ለውጥ በአስርና አስራ አንድ ዓመት ውስጥ የታየ ነው። አሁን ባለው አካሄድ ከአስር ዓመት በኋላ እንደርሳለን?” ሲል የራሱን ትንቢት አስቀምጧል።
ተቆራርጦ በሚቀርበው አስተያየት እነ ፕሮፌሰር እንድሪያስን በማጀብ ሃይሌ  በመዝገበ ቃላት ላይ ኢትዮጵያን “ረሃብ” በማለት የሚተረጉማት ቃል እንደሚቀየር በልበ ሙሉነት ተናግሯል። “ከሃያ ዓመት በኋላ” አለ ሃይሌ “በመዝገበ ቃላት ላይ የኢትዮጵያ ውርስ ትርጉም ሃብታም በሚል ይቀየራል” ብሏል።
“ድሮ ትረዱን ነበር፤ እናመሰግናለን። አሁን ደግሞ እንረዳችሀዋለን እንላቸዋለን” ሲል አውሮፓና አሜሪካን የመሳሰሉ ታላላቅ አገሮች የኢትዮጵያን እጅ እንደሚናፍቁ ሃይሌ ከምኞት ባለፈ ስሜት ውስጥ ሆኖ ተናግሯል። አገሪቱን ለሃያ አንድ ዓመታት ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ ባልገለጹበት ሁኔታ ሃይሌ ከአስር እስከ ሃያ ዓመት ኢትዮጵያ ሃብታም አገር እንደምትሆን መናገሩ ከምን የመነጨ እንደሆነ ሊገባቸው እንዳልቻለ ብዙዎች እየገለጹ ነው።
“ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል” ሲል ኢህአዴግን የመከረው ሃይሌ የበታች ባለስልጣናት መንግስትን እንዳያሰድቡ መክሯል። “መንግስት ይህንን አድርጉ ላይል ይችላል” የሚለው ሃይሌ የበታች ባለስልጣኖች የሚፈጽሙት ሙስና “መንግስትን ያስወቅሰዋል” በሚል ተቆርቋሪነቱን በይፋ አስታውቋል። ዋናዎቹን የሙስና ተዋናዮች ነጻ በማውጣት የታች ባለስልጣኖችን “እያንገዋለለ” አሳጥቷቸዋል።
“… ለህሊናቸው ሲሉ እንደ መንግስት በማሰብ መስራት አለባቸው” ሲል ትዕዛዝ አዘል ምክርና ማሳሰቢያ ለበታች ባለስልጣናት ያስተላለፈው ሃይሌ የአስተያየቱ መነሻ ከኢህአዴግ ጋር የፈጠረው ዝምድና ውጤት እንደሆነ እየተነገረ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ “ሃይሌ ሃብቱ እየበዛ ሲሄድና የተበደረው ገንዘብ ሲጨምር ኢህአዴግን ወክሎ መናገር ጀመረ” ብለዋል።
አትሌቶችን ሰብስቦ የአቶ መለሰን ሃዘን ሳግ በያዘው ድምጽ እያለቀሰ የገለጸው ሃይሌ ነፍሳቸውን ይማረውና በአቶ መለስ አይወደድም ነበር። በህይወት እያሉም በተደጋጋሚ ያናንቁት ነበር። ሃይሌን እንደሚያደንቁት ተጠይቀው አርቲስት ቻቺን በማሞገስ ጭራሹኑ እንደማያወቁት ዘለውት አልፈውት ነበር። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት ለሃይሌ ቁብ እንደሌላቸው የሚያውቀው ሃይሌ ከአንድ ማስታወቂያ ሰራተኛ ልቆ በፕሮፓጋንዳ ተግባር ላይ መሰማራቱ በቅርብ ጓደኞቹና በአድናቂዎቹ ዘንድ መነጋገሪያ አድርጎታል።
በአዳማው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ በመገኘት ውድ ሽልማቱን ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በማበርከት የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ የታየው ሃይሌ፤ በዚያው ጉባኤ ላይ አቶ መለስንና ኢህአዴግን ማሞገሱ በወቅቱ በርካታ አስተያየት እንዲሰነዘርበት ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም። የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ ያነጋገራቸው እንዳሉት ሃይሌ ወደ ፖለቲካው መንደር በፍጥነት እየተንደረደረ መሆኑን በማስረዳት የሚያውቁትንም ተናግረዋል።
ጣና ሃይቅ ዳርቻ ከልማት ባንክ በአርባ ሚሊዮን ብር የገዛውን ሆቴል ከሁለት ወር በኋላ ሼኽ መሃመድ አላሙዲ በትዕዛዝ እንደነጠቁት በታላቅ ቅሬታ ለህዝብ አስታውቆ የነበረው ሃይሌ የባህር ዳርን ቤተ መንግስት የመጠቅለል ታላቅ ፍላጎት እንዳለው ነው የቅርብ ወዳጁ ለመረጃ አቀባያችንየተናገሩት።
በኦሜድላ ስፖርት ክለብ ውስጥ ሰራተኛ የነበሩትና ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሃይሌ ቅርብ ሰው “ሃይሌ ቤተመንግስትን ይወዳል። ኢትዮጵያንም የመምራት ህልም አለው” በማለት ጭራሽ ተሰምቶ በማያውቀው ጉዳይ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
የአማራ ክልል መንግስት ለሲድኒ ኦሊምፒክ ጀግኖች ግብዣ ባደረገበት ወቅት የባህር ዳር ቤተ መንግስት ጎብኝተው እንደነበር አስተያየት ሰጪው ያስታውሳሉ። ሃይሌ የጃንሆይን መኝታ ክፍል ከተመለከተ በኋላ አሰበ። ከአፍታ በኋላ አልጋቸው ላይ ተቀመጠ። አልጋውን ወደ ላይ ወደታች ካወዛወዘው በኋላ “… ይህንን ቤተ መንግስት…” በማለት እንደሚኖርበት መዛቱን አስታውሰው ተናግረዋል።
ሃይሌ ዝም ብሎ እንደማይናገር ያወሱት እኚሁ በቅርብ የሚያውቁት ሰው ሃይሌ ይህንኑ ህልሙን ተግባራዊ ለማድረግ ዘመቻ የጀመረ እንደሚመስላቸው አስታውቀዋል። በቀጣዩ 2005 ምርጫ ሃይሌ እንደሚሳተፍ በርግጠኛነት ተናግረዋል። ሃይሌ ሁለት ጊዜ በግል ፓርላማ ለመግባት እንደሚወዳደር ካስታወቀ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ራሱን ከምርጫ ዘመቻ ማግለሉን መግለጹ ይታዋሳል።
ሃይሌ ፖለቲከኛ የመሆን የኖረ ህልም እንዳለው ያወሱት ባልደረባው ከተናገሩት በተቃራኒ ሃይሌ የፈለገውን መሆንና ማድረግ የግል ውሳኔው እንደሆነ የሚከራከሩለት አልጠፉም። ሃይሌ ሃብት አለው፣ ከፍተኛ ዝና ገንብቷል። ኢትዮጵያዊያን የማይረዱት እውቅናና ክብር በውጪው ዓለም እንዳለው የሚገልጹት ተከራካሪዎች “አንድ ሰው በተናገረ ቁጥር ለንግግሩ ቀንድና ጭራ መቀጠል ነውር ነው። ሰዎች የመሰላቸውን እንዳይናገሩም የሚገድብ ክፉ ልምድ ነው” ባይ ናቸው። “አያይዘውም ሃይሌ የኢህአዴግ አባል ቢሆን እንኳ አስገራሚ አይሆንም” በማለት ጠርዝ ደርሰው ይሟገታሉ።
በርካታ አትሌቶች የኦህዴድ አባላት እንደሆኑ የሚጠቁሙት እነዚህ የሃይሌ ተከራካሪዎች “ሃይሌ ኢህአዴግን ቢቀላቀል መነጋገሪያ የሚሆነው ጉዳይ ብአዴን ወይስ ኦህዴድ ይሆናል የሚለው ነው” ብለዋል። አርሲ የተወለደው ሃይሌ በሩጫ ከተሳካለት በኋላ በተለያዩ ጉዳዮችና መጠነኛ ግንባታ ወደ ባህር ዳር መጠጋጋቱ በትውልድ አካባቢው ተወላጆች ቅሬታ እንዳስነሳበት በተለያዩ ጊዚያቶች መዘገቡ የሚታወስ ነው።

Saturday 13 July 2013

የአንድነት ፓርቲ መሪዎች ታስረው ተፈቱ

የነገው ጎንደር እና የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል

masasebiya
በደሴ ከተማ በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 5 ቀን 2005ዓ.ም. የአንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ጠዋት ከአራዳ የፓርቲው የደቡብ ወሎ ዞን ጽህፈት ቤት ለሚጀምረው ሰላማዊ ሰልፍ ፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ በላይ ፈቃዱ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራ፣አቶ ፍቃዱ ሰጠኝ ከአዲስ አበባ፤ አቶ ብስራት አቢ፣ አቶ መኳንንት፣ አቶ አንዋር፣ አቶ ከበደ፣ አቶ ሰይድ እና ሌሎች አንድነት ፓርቲ የደሴ ነዋሪዎች በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በአማራ ክልል ልዩ ፖሊስና በአድማ በታኝ እንዲያቆሙ በማድረግ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸው ነበር፡፡

ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ

(ነቢዩ ሲራክ)
unemployed


መብት አስከባሪ አላቸው ለማለት ግን አልደፍርም
“በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም!”
አልጀዚራ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለስደት ስለሚዳረጉ ዜጎች ዙሪያ ያሰራጨው መረጃ ቀልቤን ቢስብው በማለዳ ወጌ ልተነፍስ ብዕሬን አነሳሁ ። የአልጀዚራ ቴሌቪዥን Escaping Ethiopia’s unemployment “በኢትዮጵያ ስራ አጥነትን ለመሸሸ ” ያለው ዘገባ ስለ ስደቱ ከስደተኞች አንደበት፣ ለቀጣዩ ስደት እየተዘጋጁ ስላሉት ፣ ሰለ ህገ ወጥ አሸጋጋሪዎችና ስደቱን ለመገደብ መንግስት እየወሰደ ስላለው ጥረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እማኝ አድርጎ በዘገባው አሳይቶናል ። በዚሁ ዘገባ ላይ በቀረበው መረጃ ስደትን ለማስቆምና የአዘዋዋሪዎችን ወሽመጥ ለመቁረጥ የተጠና ስራ ላቀረቡ ወጣቶች ስደትን ለመገደብ በመንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ 27 ሽህ ዶላር ያበድራል ተብሎ ሰምቻለሁ። የተባለው በእኛ ሃገር ይሆን ? ስልም ጠየቅኩ ! ” ጀሮ ለራሱ ባዳ ነው ” ብየ አላየሁ አልሰማሁም ብየ ልለፈው! አሁን ሰምቻለሁና ይሰጣልም ብየ ለቀበለው ። ግናስ ለብድር አሰጣጥ መስፈርቱ ምንድን ነው? ይህ ግን አልገባኝም ! መስፈርቱ ወሳኝ ሆኖም ይህንንም አድልኦ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከት በሃይማኖትና በዘር ሳይለዩ እኩል ታይተው ድጋፉ ይደረጋል በሚል ልቀበለው ። የተባለው ሁሉ እውነት ቢሆን እንኳ የተጠናን ስራ አውርቦ ጠቀም ያለ ብድር የማግኘት እድሉ ተምሮ ስራ ላጣው አለያም ለነቃው እና ለተደራጀው የከተማ ወጣት እንጅ ለቀረው መፍትሄ አይደለም ። ይህ መፍትሄ በዘገባው ቀርበው ላየናቸው በማንኛውምወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራ ለመሰደድ ለተዘጋጁት እና ከህጋ የሃገራት ሁለትዮሽ ስምምነት ውጭ ለሰደዱት ከገጠሩ ክፍል የሚጋዙት ቁጥራቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱት እህቶች የሚፈይደው ነገር የለም ።
በአረብ ሃገር በኮንትራት ስም የሚሰደዱ እህቶችን እንዳይሰደዱ ለማገድ አሸጋጋሪ ደላላዎችን ከመቆጣጠሩ ጎን ለጎን ዜጎችን ከድህነት የሚወጡበትን መንገድ መንደፍ ፣ የዜጎችን ነጻነት ማክበር እና ሁሉንም ዜጎች እኩል በማየት መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት የስራ እድል መክፈት ዋናው መፍትሔ ሊሆን ይገባል። “ኢኮኖሚያችን አደገ ተመነደገ” እየተባለ አቅማችን ይህunemployed 1ን ማድረግ ካልቻለ ብቸኛው መፍትሄው ” አትሰደዱ” ብሎ መለፈፉና እና “ለሚሰሩት እድሉ ” አለ ብሎ መደስኮሩ ከመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም !
ስደት ክፉ ነገር ነው ፣ እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑት እያላቸው ካላቸው ለመጨመር ከሚሹ ስግንግቦች ውጭ ብዙው ስደተኛ ለመሰደዱ የስራ ማጣት ፣ የድህነትና የኑሮ ውድነት በቂ ምክንያት እናዳለው በስደቱ አለም ስኖር ካገኘኋቸው ስደተኛ ወገኖቸ የተረዳሁት ሃቅ ነው ። የኑሮ ውድነት ሳያንገሸግሽ ፣ ሳያጨናንቀው ስደትን የሚፈልግ የለም ፣ በሃገሩ ተምሮና ሰርቶ እሱንና ቤተሰቡን መደገፍ እየቻለ ስደትን የሚመርጥ የለም! የመንግስት ሃላፊዎች ለገጽታ ግንባታ የሚለቋቸውን መረጃዎች ገታ አድርገው በስደተኛው ችግር ላይ ቢያንስ ትክክለኛ መረጃ ቢሰጡን መልካም ነበር ።
ከሁሉም በላይ ወደ አረብ ሃገራት በኮንተራት ስራ ስም የሚላኩ ዜጎችን ጉዳይ ቆም ብለው ሊመረምሩት ይገባል። ሰው ” በሃገሬ ተቸገርኩ ፣ ተምሬ ስራ አጣሁ !” እያለ ስደቱን ማቆም ይከብዳል። ያም ሆኖ በህገ ወጥ ደላላ ተታልለው በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደዱትን ለማስቆም መንግስት በስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ስም እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥ የበከተ ድለላ በሰውር የሚሰራውን ስራ ሰንሰለቱን ከቁንጮው ሊበጣጥሰው ይገባል ። ስደትን ማሰወቆም ካልቻልን አማራጩ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሃገር እና ሊሰሩት ስለሚችሉት ስራ ትክክለኛ መረጃ እና ቅድም ዝግጅቶችን በትክክል አሟልቶ ማቅረብ አማራጭ ሊታይ ይገባል። ከዚህ ሁሉ አስቀድሞ ግን ዜጎችን በሃገራት መካከል በሚደረግ የሰራተኛ ውል መሰረት በህጋዊ ኮንትራት ስራ ዜጎችን መላክ እና ከተላኩም በኋላ በመብት ማስከበሩ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስረትር መስሪያ ቤት በፖለቲካ ታማኝነት ሳይሆን ዲፕሎማሲው ጥብብ የተካኑትን ከሃላፊዎች በበቂ ሁኔታ በአረብ ሃገራት ሊመድብ ይገባል!
ያለንት የስልጣኔ ዘመን ነውና መረጃን በመደባበቅ እውነትን ማጥፋት አይቻልም። ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ማቀበል ያዋርዳል እንጂ አያስከብርም ፣ ከሃቅ የራቀ መረጃ ገጽታን ያጨለማል እንጅ ፈካ አድርጎ ቀይሮ አያሳይም ! በአልጀዚራ ዘገባ እንደተነገሩት አንዳንድ መረጃዎች አጋጣሚውን ገጽታ መገንቢያ አድርገን እውነቱን የምንሸፋፍን ከሆነ ትልቅ ስህተት ተሳስተናል ! እውነትን በውሸት ለመድፈን ስንቆፍር ነገም እንደ የትናንቱ ከመከራ መውጣት አይቻለንም ! ዛሬም ጉዟችን ቅጥፈት ከሆነ በምናየው የወገን ሮሮ ፣ የሰቆቃ ድግግሞሽ ስናለቅስ እንደኖርን ስናለቅስ እንኖራለን ! አባቶች “በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! ” እኛው ራሳችን በሽታችን ስንነግራቸሁ ስሙን ፣ መድሃኒቱንም ፈልጉልን ! የማለዳ ወጌን አበቃሁ !
በሽታችን ተረድቶ መድሃኒት ጀባ የሚል የህዝብ አገልጋይ ይስጠን!

ዲሲ 2013

(ክንፉ አሰፋ)
dc esfna



ስለ ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያውቁ ፈረንጆች ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጠንቀቆ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። “ስለ ሕዝቡ ለመጻፍ የሚፈልግ አንድ ሰው ኢትዮጵያ በገባ ማዕግስት አንድ መጽሃፍ ሊጽፍ ይችላል፤ ይህ ሰው ሳምንት ሲቆይ አንድ መጣጥፍ ይጽፋል፣ ወር ሲቆይ ግን የሚጽፈው ይጠፋበታል።” ይላሉ። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ይመስለኛል። ኢትዮጵያ የብዙ ባህል፣ የብዙ ቋንቋና የበርካታ እምነት ሃገር ስብስብ በመሆንዋ ታሪኳን ጠለቅ እያልን ለማወቅ በሞከርን ቁጥር ሊወሳሰብ ስለሚችል እጅግ ብዙ ጥናት ማድረግ ይገባል ለማለት ነው። ጸሃፊው ለረጅም ጊዜ በቆየ ቁጥር የሚጽፈው ጠፍቶት ሳይሆን ግራ ተጋብቶ መጻፉን ያቆማል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

Thursday 11 July 2013

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የሰላማዊ ሰልፍለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ በአዲስ አበባ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ።

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ-ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ- መድረክ ለእሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚቆይና ከስድስት ኪሎ ተነስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጎዳና በማድረግ  መዳረሻው ድላችን ሐውልት የሚያደርግ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደተመለከተው በመጥቀስ፤ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት የጉዞ መስመር  በአሁኑ ጊዜ እየተዘረጋ ባለው የባቡር መስመር የትራፊክ መስመር እየተጨናነቀ ስለሆነ ለሰልፉ እውቅና እንዳልሰጠ ገልጿል።
በደብዳቤው ከምኒልክ አደባባይ እስከ አትክልት ተራ ድረስ ያለው  መንገድ በባቡር መንገድ ሥራ በመዘጋቱ አሁን ያለው ብቸኛ መንገድ የፒያሳና የቸርችል ጎዳና ነው ያለው መስተዳድሩ፤እንዲሁም ከመገናኛ ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱና ለሰልፉ የተመረጠው መንገድ ማስተንፈሻ በመሆኑ ፤ከዚህም በላይ በአካባቢው የመንግስት ተቋማትና ሆስፒታሎች ስለሚገኙና እነዚህም ስፍራዎች በአዋጁ የተከለከሉ በመሆናቸው ለሰላማዊ ሰልፉ እውቅና ለመስጠት አንችልም ብሏል።
የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን መከልከሉን አረጋግጠዋል

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲዘጋ ተማሪዎቹም ከግቢ እንዲወጡ ፓትርያርኩ ደብዳቤ መጻፋቸው ተሰማ

ደብዳቤውን ተከትሎ አባ ሉቃስና አባ ጢሞቴዎስ ዱላ ቀረሽ መዘላለፍ ውስጥ ገቡ
abune_mathias_7
ሰሞኑን ተጠናክሮ የቀጠለውን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን ጥያቄ አልቀበል ያሉትና ሲኖዶሱ የወሰነውን ውሳኔ ለማስፈጸም ዝግጁ ያልሆኑት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን አባ ጢሞቴዎስ ወዳጃቸውን ፓትርያርክ ማትያስን ደብዳቤ በማጻፍ ኮሌጁ እንዲዘጋና ተማሪዎችም ግቢውን እንዲለቁ፣ ምረቃም እንደማይኖር እንዲደረግ ትእዛዝ ማስወጣታቸው ተሰማ፡፡ ደብዳቤው ተግባራዊ መሆኑ ግን አጠራጣሪ ሆኗል፡፡ ፓትርያርኩ የጻፉት ደብዳቤ ዛሬ የተሰበሰበውን ቋሚ ሲኖዶስ ያጨቃጨቀ ሲሆን በዋናነት ኮሌጅን መዝጋት የሚያበቃ ችግር አልተፈጠረም፡፡ የተፈጠረ ቢሆንም እንኳ በሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንጂ በእርስዎ ደብዳቤ ኮሌጁ ሊዘጋ አይችልም የሚል ጠንካራ ተቃውሞ ከጳጳሳት በኩል ቀርቧል፡፡ በተለይም አባ ሉቃስ ደብዳቤውን ከተቃወኑት መካከል ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም አባ ጢሞቴዎስ በአባ ሉቃስ ላይ የስድብ ውርጅብኝ ያወረዱባቸው ሲሆን “አንተ ሰዶማዊ አዋሳ ላይ ስታሳድም የኖርህ ባለፈውም ቀሚስ አሰፍተህ ፓትርያርክ እሆናለሁ ብለህ ስታሳድም አልነበርህም?” ማለታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአጸፋውም አባ ሉቃስ “አንተ መሃይም እውር መቼም ከትምህርቱ የለህበት ለዚያ ነው ኮሌጁ ይዘጋ የምትለው” ማለታቸውን ምንጮቻችን አክለዋል፡፡ ይህን ዱላ ቀረሽ መዘላለፍ ተከትሎ ፓትርያርኩ ቆመው “ኧረ ስለ ማርያም ብላችሁ ተዉ” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
“ባለቤቷን የተማመነች በግ…” እንደሚባለው ከፓትርያርክ ፓትያስ ጋር ባላቸው የጠበቀ ወዳጅነት ተመክተው ከሚገኙበት የጤንነት ሁኔታ የማየት ችግር አንጻር ጡረታ መውጣት ያለባቸው አባ ጢሞቴዎስ ኮሌጁን በርስትነት ይዘው ለዛሬዪቱም ቤተክርስቲያን ተስፋ የሆኑትንና የነገዪቱም ቤተክርስቲያን ወራሾች የሆኑትን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማባረር ኮሌጁን የሚያዘጋ ደብዳቤ ማጻፍ ለቤተክርስቲያኒቱ ትልቅ ውድቀት እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ደብዳቤውን የጻፉት ፓትርያርክም በምን መነሻነት ይህን እንዳደረጉ ግራ አጋቢ ሆኗል፡፡ ምንም ወዳጅ ቢሆኑ ወዳጅነት የሚገለጸው በሌላ በግል ጉዳይ እንጂ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቁር ጠባሳ የሚጥልና ራሳቸውንም ትዝብት ውስጥ የሚከት ይህን መሰል ደብዳቤ በመጻፍ መሆን አልነበረበትም የሚሉ አሉ፡፡
 እንደአንዳንድ ተንታኞች የቅድሰት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በፓትርያርኩ ጥርስ ውስጥ የገቡት ፓትርያርኩ ወዳጄ አባ ጢሞቴዎስ ለምን ተነኩ በሚል ብቻ ሳይሆን ለፕትርክና እጩነት እኔን ትታችሁ አባ ሳሙኤልን ደግፋችኋል በሚል ሳይሆን እንዳልቀረ ይናገራሉ፡፡ ኮሌጁንና ተማሪዎቹን የመናፍቃን መፈልፈያ ሆኗል ሲሉ ይተቹ የነበሩት የማቅ ብሎጎችም አሁን ተማሪዎቹን ደግፈውና ቀድሞ ይደግፏቸው የነበሩትን አባ ጢሞቴዎስን እየተቹ መጻፋቸው ደግሞ ምን አይተው ይሆን እያሰኘ ነው፡፡
 ለተማሪዎቹ የአካዳሚክ ነጻነት ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለጥያቄዎቹ ሌላ መልክ በመስጠት የመማር ማስተማሩን ሂደት ሲያስተጓጉሉ የቆዩት አባ ጢሞቴዎስና አስተዳደራቸው ኮሌጁን በመዝጋትና ተማሪዎቹን በማባረር መፍትሄ የሚያመጡ መስሏቸው ከሆነ እጅግ ተሳስተዋል የሚሉት ምንጮች ችግሩን ከስር አጣርቶ ተገቢው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በወዳጅነት ምክንያት በጭፍን ደብዳቤ ጽፎ ኮሌጅን ያህል ነገር መዝጋት ከበድ ያለ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ይላሉ፡፡ የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎች አሉብን የሚሏቸውን ችግሮች ማዳመጥና ተገቢውን መፍትሄ መስጠት ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡
 የአንድን ጳጳስ አንባገነናዊ አስተዳደር እድሜ ለማራዘም በሚል በግብታዊነት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ግን የኮሌጁን ተማሪዎች ልብ በእጅጉ የሚያሻክርና ያስተማረቻቸውን ቤተክርስቲያን እንዲጠሉና ከዚህ ቀደም ብዙዎቹ ደቀመዛሙርት እንዳደረጉት ወደሌሎች መንግስታዊና የግል ተቋማት እንዲፈልሱ ያደርጋል፡፡ ቤተክርስቲያንንም ለፍቶ መና ያስቀራታል፡፡ ስለዚህ ለደቀመዛሙርቱ ከኮሌጅ ጀምሮ በአገልግሎት ላይ እስኪሰማሩ ድረስ ተገቢውን ጥበቃና የኑሮና የአገልግሎት ዋስትና መስጠት ይገባል፡፡ ፓትርያርኩ በቅርቡ በተናገሩት መሰረት ቤተክርስቲያን ትልቁን በጀት መበጀት ያለባት ለስብከተ ወንጌል ከሆነ በዋናነት የኮሌጅ ምሩቃንን ደመወዝ ከጊዜው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ማሳደግና ወደሌላ እንዳይሄዱ በሚያደርግ መንገድ ማደላደል ያስፈልጋል፡፡
aba selama

የህወሀት ስትራቴጂ በአማራውን ህዝብ ቁጥር ቅነሳ



የተከበሩ የምክር ቤት የተቃዋሚ ተወካይ አቶ ግርማ ሠይፉ ምክር ቤቱ በቀኝ ክንፍ ሲያጠቃ ዋለ ሲሉ ያስነበቡን ፁሁፍ እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር እንዳክልበት አስገደደኝ። ለፌዴሬሽን ጉዳዬች ሚኒስቴር የቀረበ ጥያቄ በዋዛ የሚታይ አልነበረም ጥያቄዉም በብዙ የምክር ቤቱ አባል ለመጥቀስ ፈራ ተባ ሲሉ አንደኛዉ የምክር ቤቱ አባል ግን ደፍረዉ የአማራ ክልል ህዝብ በተለየ ሁኔታ በኤድስ ሞቷል መባሉ ትክክል ስላልሆነ ይቅርታ መጠየቅ ሲከፉም በሀላፊነት መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑ ሞግተዋል ብለዉ አቶ ግርማ ሠይፉ በፁሁፋቸዉ አስነቡበዉናል።
ይህ በእዉነቱ የምክር ቤቱ ተወካይ በአጋጣሚ አምልጧቸዉ ወይም ደግሞ እዉነታዉን ስለሚያውቁት እንጂ ይህ ለአማራዉ ህዝብ ህወሀት ኢትዬዽያን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ በፕሮግራም የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ በረጅም እቅዳቸዉ ላይ የተቀመጠ ነዉ። ይህንን ልል የቻልኩት እንደ ኢትዬዽያ ዘመን አቆጣጠር በ2002 ዓ፤ም በአለም ጤና ድርጅት እገዛነት በጤና ተቋማት ላይ የሚደረገውን ምዝገባ ወይም  ግምገማ  በአማራው ክልል ላይ ለመስራት እድሉን አግኝቼ በምሰራበት ወቅት ያየሁትን እይታዬ ለማጋራት ያህል ነው። ይህም ምዝገባ ወይም  ግምገማ  የሚያካትተው በኢትዬዽያ ዉስጥ ያሉት የጤና  ተቋማት ምን ያህል ባለሙያ፥ ታካሚ፥ የወሊድ አገልግሎት፥ የቲቢ እና ኤድስ አገልግሎት፥ የላብራቶሪ አገልግሎት ፥ የህፃናት ህክምና እና ክትትል እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎችን እና መድሀኒቶች ከመቼ ጀምሮ እጥረት እንደነበረ እና በተለይ የኤድስ በሽታ እድሜ ማራዘሚያው መድሀኒት እና የቅድመ ምርመራ መሣሪያ ቆጠራ ወይም ምዝገባ ይደረጋል። ነገር ግን የህወሀት መንግስት የተሰበሰበውን መረጃ እንደ ኢኮኖሚው ሁሉ በመቀየር ለፖለቲካ ፍጆታ እና ገንዘብ ማግኛ ዘዴ ሆኖታል። እውነታው ግን ህብረተሰብ በተጏዳኝ በሽታዎች፥ በህክምና መሳሪያዎችና መድሀኒቶች እጥረት እንደሚሰቃይ እና እንደሚማት የአደባባይ ሚስጥር ነው።
የወያኔ መንግስት የአማራውን ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ በኤድስና በተጏዳኝ በሽታዎች ዙሪያ ፩ኛ የህብረተሰቡ ጤና አጠባበቅ በተመለከተ ምንም አይነት ግንዛቤ እንዳይኖረዉ በማድረግ ፪ኛ  በኤድስ በሽታ ህብረተሰቡ መያዝ አለመያዙ የመመርመሪያ መሳሪያ በክልሉ ሆነ ተብሎ እጥረት እንዲኖርና ምንም አይነት የቅድመ ምርመራ ግንዛቤ እንዳይኖራቸዉ መደረጉ ፫ኛ በኤድስ በሽታ የተጠቁ ሰዎች የእድሜ ማራዘሚያ በአግባቡ እንደማይሰጣቸዉና የመድሀኒቱም ተጠቃሚዎች እንደማይቆጧጠሯቸዉ ከጤና ጣቢያም ሆነ ከሆስፒታል ምንም አይነት ክትትል እንደማይደረግላቸዉ እና ከዚህም በተጨማሪ ይህ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒትና ሌሎችም ተጏዳኝ በሽታ መድሀኒቶች ከአማራዉ ህዝብ ቁጥር አንጻር ተመጣጣኝ ስርጭት እንደሌለው ፬ኛ ደግሞ የመድሀኒቶቹ የመገልገያው ጊዜ (expired date) በጣም የቀረበ በተለይ ለነዚህ ለሁለቱ ክልሎች እንደሚላክ በጤና ጥበቃ ስር የሚገኘዉ የመድሀኒት ፈንድ ኤጀንሲ መስሪያ ቤት በምሰራበት ወቅት ይህ ከላይ የዘረዘርኳቸውን ለማስተዋል ችያለው ።
ይህንን እና በጤና ጥበቃ ስር ኢ-ፍህታዊ የሆነ የመድሀኒት ስርጭት እና ክፍፍል ዙሪያ ላይ ለተመረጡ ክልልሎች በተለይም ለአማራው እና ለኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ለመቀነስ ሆነ ተብሎ የህወሀት መንግስት እንዴት እንደሚጠቀምበት በቅርቡ በመረጃ በማስደገፍ በሰፊው እመለስበታለው።

በቦንድ ሽያጭ ያልተሳካው የገንዘብ ዘረፋ በኮንደሚኒየም ሰበብ መሳካት የለበትም!!!

ወያኔ በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በከተሞች አካባቢ ምንም አይነት ሕዝባዊ ተቀባይነት ኖሮት አያውቅም። ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት ከተሞች በጠላትነት በተፈረጀው አማራና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች የተሞሉ ስለሆነ ነው ይላል… ዋና ከተማችን አዲስ አበባ በዚህ ውንጀላ ዋጋ ከከፈሉት ከተሞች ግንባር ቀደሟ ናት። በተለይ በመጀመሪያው የወያኔ 10 (አሥር) የሥልጣን አመታት የከተማዋን የነዋሪዎች አሰፋፈር ስብጥር ሆን ብሎ ለመቀየር ከመሞከር ጀምሮ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋሞችን አቅም ለማዳከም በርካታ አሳዛኝ እርምጃዎች ተወስደዋል።
ታሪክን ወደኋላ መለስ ብለን እንቃኝ። የፋሺስት ጣልያን ጦር በእንግሊዝ ጦር ትብብር በኢትዮጵያ አርበኞች ከተደመሰሰ በኋላ በአሸናፊነው ወደከተሞች የገባው የእንግሊዝ ጦር ያገኘውን ንብረት በወቅቱ የቅኝ ግዛቶቹ ወደ ነበሩት ኬንያና ሱማሌ አሽሽቷል።
ከብዙ ዓስርተ ዓመታት በኋላ ወያኔ ይህንኑ እኩይ ተግባር ደገመው። ወያኔ በያዛቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘኛቸውን ውድ ዋጋና ትላልቅ ጥቅሞች የሚሰጡ በርካታ ንብረቶችን ከተለያዩ መንግሥታዊና ወታደራዊ ተቋሞች፤ ዩኒቨርስቲዎች፤ ሆስፒታሎች፤ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጫዎች ዘርፎ እስከዛሬ ትክክለኛ አደራሻው ለሕዝብ ይፋ ወደ አልተደረገ የሰሜን አካባቢ አይናችን እያየ በረጃጅም የጭነት መኪናዎች አጓጉዞአል። በቀድሞ መንግሥት ዘመን ምንም ዕጥረት እንዳልነበረው የሚታወቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የ24 ሰዓት መብራት አገልግሎትን እንኳ ሳይቀር በማስተጓጎል የከተማውን ሕዝብ ተበቅሎአል።
ወያኔ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ጥላቻ በጥቂቱም ቢሆን ረገብ ያደረገ የሚያስመስል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጀመረው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት በቃኝ የማያውቁት የቀድሞ ተጋዳላዮች የአገሪቱን አንጡራ ሃብት እንዲበዘብዙ በተመቻቸላቸው እድል ዘርፈው የያዙትን ገንዘብ ከውልደታቸው ጀምሮ ከሚታወቁበት አካባቢ ሕዝብ እይታ አርቀው “ለደም ካሳ” በዋና ከተማችን እምብርት በነፃ በታደላቸው የከተማ ቦታዎች ላይ ህንጻዎችን በመገንባት ንብረት እንዲይዙ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በርካታ የአለም አቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቶች መቀመጫ በሆነቺው አዲስ አበባ ምርጫ 97ን ተከትሎ ገጥሞት የነበረው ሽንፈት ባስከተለው መዘዝ የተበላሸ ገጽታውን በህንጻና መንገዶች ግንባታ ስም ለማሳመር መጣር ናቸው።
የአዲስ አበባ ኮንደሚኒዬም ቤቶቾ ግንባታ ከምርጫ 97 ቦኋላ በመኖሪያ ቤቶች እጥረት የሚሰቃየውን ሕዝብ ልብ ለማማለልና የፖለቲካ ድጋፍ ለመግዛት ያስችላል ተብሎ የታሰበ ብቻ ሳይሆን የሚከተሉት ድብቅ ዓላማዎችም አሉት።
  1. በዘረፋ የከበሩ የቀድሞ ተጋዳላዮችና የጥቅም ተካፋዮቻቸው አይናቸው ያረፈባቸውን ቁልፍ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎች ሁሉ ለዘመናት በባለይዞታነት ይዘው የኖሩትን በልማትና በእንቨስትመንት ሥም በማፈናቀል ወደ ግላቸው ላማዞር ያስችላቸዋል፤
  2. በተለያዩ ሥም የተቋቋሙ የህንጻ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶቻቸው በግንባታው ሥራ በመሳተፍ መጠነ ሰፊ የሆነ ትርፍ ለማግበስበስ ያመቻቸዋል፤
  3. የሥርዓቱን ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ከሌላ ቦታ አምጥቶ በማስፈር በጠላትነት የተፈረጀውን የኅብረተሰብ ክፍል ተጽዕኖ ለማምከን ይረዳል፤
  4. በሀብት ዘረፋው ለመሳተፍ እድል የሌላቸው የበታች ካድሬዎችና ታማኝ አገልጋዮችን ተጠቃሚ በማድረግ በአለቆቻቸው ዘረፋ ተማረው ልባቸው እንዳይሸፍት ይከላከላል ፤
  5. ከተወለዱበትና ካደጉበት የግልና የቀበሌ ቤቶች ያለውደታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የኮኖዶሚኒየሙን ሂሳብ መክፈል እስከቻሉ ድረስ “ከቤታችን ተፈናቅለን ሜዳ ላይ ተጣልን” የሚል እሮሮ በማሰማት መንግስት ላይ አመጽ እንዳያስነሱ ስጋት ለመቀነስ ይረዳል፤
  6. ከሰሞኑ 40 ከመቶ ተብሎ በወጣው ፖሊሲ እንደታዘብነው ደግሞ ዜጎችን በማጓጓት ተቸግረው ያጠራቀሙትን ገንዘብ ዝግ የባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲከቱ በማድረግ የገንዘብ እጥረት አንገቱ ድረስ የዘለቀውን አገዛዝ ለመታደግ ያስችላል (በ16 የሥራ ቀናት ብቻ ከተመዘገበው 750, 000 የኮንዶሚንዬም ቤት አመልካች 750 000 000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ብር መሰብሰቡን ልብ ይሏል)
ከዚህም በተጨማሪ የኮንደሚኒዬም ቤቶች ግንባታ በቂ ጥናትና ዝግጅት ያልተደረገበት የይድረስ ይድረስ ሥራ መሆኑን የቤቶቹ ርክክብ በተፈጸመ ማግሥት ስለ ህንጻው መሬት ውስጥ መስጠምና መጣመም መጀመር እየወጥ ያሉ ዜገባዎች ዋቤ ምስክር ናቸው።
የወያኔ መሪዎችና ታማኝ አገልጋዮቻቸው ከኮንደሚኒዬም ግንባታ በተጨማሪ ከምርጫ 97 ወዲህ ከፍተኛ ገንዘብ እያግበሰበሱ ያሉት የከተማ ቦታዎችን በውድ ዋጋ የልጅ ልጆቻቸው እንኳ ሊደርሱበት ለማይችል የግዜ ገደብ በሊዝ በመቸብቸብ ነው። በዚህ የመሬት ቅሪሚያ አንዳንድ ስግብግቦች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” እንዲሉ “ወያኔዎች መሬታችንን እየተቀራመቱ ስለሆነ ተሻምተን ማስቆም አለብን” በሚል ብልጣ ብልጥነት ከሚኖሩበት የስደት አገር እየተጓዙ የወያኔን ገቢያ በማድራት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በትዝብት ተመልክቶአል። አገርን ዘርፎ ለዘራፊ እየሰጠ ያለ መንግሥት ሴራ ተባባሪ መሆን በሞራልም ሆነ በህሊና ዳኝነት የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑ ሳያንስ እነዚህ በስግብግብነት የተጠመዱ ወገኖች ለንብረታቸው ደህንነት ሲባል ወያኔ ዓይናቸው እያየ ጆሮአቸው እየሰማ በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽማቸውን ሰቆቃዎች እንኳ ለመቃወም ድፍረት በማጣት ሌላ ትዝብት ውስጥ ሲወድቁ ተስተውለዋል:: ለመሆኑ እነዚህ ወገኖች ለፍተው ባገኙት ገንዘብ የገዙት ባርነትን ነው ወይስ የንብረት ባለቤትነትን ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይኖራቸዋል?
የዜጎች መብት በተከበረበት አገር ከዜግነት መብቶች አንዱ የግል ሀብት ባለቤት ለመሆን ገደብ የሌለው ነፃነትና እድል መኖሩ ነው::
ወያኔ በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያችን ግን የንብረት ባለቤት ለመሆን የሥርዓቱ ባለሟል መሆን አለያም ከፖለቲካ ባላንጣነት መራቅ ዋና መስፈርት ናቸው። በዚህ መስፈርት ከወያኔ ጋር ተሻምተው ወይም ተሻርከው የንብረት ባለቤት ለመሆን እየተሽቀዳደሙ ያሉ ወገኖች ሊያውቁት የሚገባው ሃቅ ቢኖር አድሎአዊነት በሰፈነበት መንገድ የተገኘ ማንኛውም አይነት ሀብት ወይም ንብረት ወደፊት በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ በሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ህገዊ ጥበቃ የሚኖረው አለመሆኑን ነው። ብሄራው የአገር ጥቅም ላይ ክህደት ከፈጸመ ፤ ዜጎችን በማፈን ሰቆቃ ካደረሰ ፤ የአገሪቷን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል መሬታቸውን ቀምቶ ለሌሎች አሳልፎ ከሰጠ ፤ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ዘርፎ ለዘራፍ ከሰጠ ወንጀለኛ መንግሥት ጉያ ውስጥ ተወሽቆ እስከ ወዲያኛው የህግ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችል ንብረት ባለቤት መሆን ማሰብ እጅግ ይቸግራል። ዜጎች በራሳቸው ወዝ ለፍተው ያገኙትን ንብረት ሳይቀር በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት ብቻ በሽብርተኝነት እየፈርጀ የሚነጥቅ ሥርዓት ዕድሜ እንደምንጠብቀው ረዥም ሊሆን እንደማይችል ማሰብ ብልህነት ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ አገዛዝ በውጭው ዓለም በስደት ከሚኖረው ወገናችን በአባይ ግድብ የቦንድ ሺያጭ ሥም ለመሰብሰብ ሞክሮ ያልተሳካለትን ገንዘብ በመሬት ሺያጭ እና በኮንደሚኒዬም ቤት ግዥ ሥም እንዲያገኝ ሊፈቀድለት አይገባም ብሎ ያምናል:: ስለዚህም እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ከዚህ ከኮንደሚኒዬም ቤቶች በስተጀርባ ያለውን ድብቅ አጀንዳ በማጋለጥ ጥረቱን በማምከን የሕዝባዊ እምብተኝነት ትግል አካል እንዲሆን ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያስተላልፋል።

በቦንድ ሽያጭ ያልተሳካው የገንዘብ ዘረፋ በኮንደሚኒየም ሰበብ መሳካት የለበትም!!!


ወያኔ በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በከተሞች አካባቢ ምንም አይነት ሕዝባዊ ተቀባይነት ኖሮት አያውቅም። ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት ከተሞች በጠላትነት በተፈረጀው አማራና የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች የተሞሉ ስለሆነ ነው ይላል… ዋና ከተማችን አዲስ አበባ በዚህ ውንጀላ ዋጋ ከከፈሉት ከተሞች ግንባር ቀደሟ ናት። በተለይ በመጀመሪያው የወያኔ 10 (አሥር) የሥልጣን አመታት የከተማዋን የነዋሪዎች አሰፋፈር ስብጥር ሆን ብሎ ለመቀየር ከመሞከር ጀምሮ የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋሞችን አቅም ለማዳከም በርካታ አሳዛኝ እርምጃዎች ተወስደዋል።
ታሪክን ወደኋላ መለስ ብለን እንቃኝ። የፋሺስት ጣልያን ጦር በእንግሊዝ ጦር ትብብር በኢትዮጵያ አርበኞች ከተደመሰሰ በኋላ በአሸናፊነው ወደከተሞች የገባው የእንግሊዝ ጦር ያገኘውን ንብረት በወቅቱ የቅኝ ግዛቶቹ ወደ ነበሩት ኬንያና ሱማሌ አሽሽቷል።
ከብዙ ዓስርተ ዓመታት በኋላ ወያኔ ይህንኑ እኩይ ተግባር ደገመው። ወያኔ በያዛቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘኛቸውን ውድ ዋጋና ትላልቅ ጥቅሞች የሚሰጡ በርካታ ንብረቶችን ከተለያዩ መንግሥታዊና ወታደራዊ ተቋሞች፤ ዩኒቨርስቲዎች፤ ሆስፒታሎች፤ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጫዎች ዘርፎ እስከዛሬ ትክክለኛ አደራሻው ለሕዝብ ይፋ ወደ አልተደረገ የሰሜን አካባቢ አይናችን እያየ በረጃጅም የጭነት መኪናዎች አጓጉዞአል። በቀድሞ መንግሥት ዘመን ምንም ዕጥረት እንዳልነበረው የሚታወቀውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የ24 ሰዓት መብራት አገልግሎትን እንኳ ሳይቀር በማስተጓጎል የከተማውን ሕዝብ ተበቅሎአል።
ወያኔ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ጥላቻ በጥቂቱም ቢሆን ረገብ ያደረገ የሚያስመስል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የጀመረው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው። አንደኛው ምክንያት በቃኝ የማያውቁት የቀድሞ ተጋዳላዮች የአገሪቱን አንጡራ ሃብት እንዲበዘብዙ በተመቻቸላቸው እድል ዘርፈው የያዙትን ገንዘብ ከውልደታቸው ጀምሮ ከሚታወቁበት አካባቢ ሕዝብ እይታ አርቀው “ለደም ካሳ” በዋና ከተማችን እምብርት በነፃ በታደላቸው የከተማ ቦታዎች ላይ ህንጻዎችን በመገንባት ንብረት እንዲይዙ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በርካታ የአለም አቀፍ ድርጅቶችና ዲፕሎማቶች መቀመጫ በሆነቺው አዲስ አበባ ምርጫ 97ን ተከትሎ ገጥሞት የነበረው ሽንፈት ባስከተለው መዘዝ የተበላሸ ገጽታውን በህንጻና መንገዶች ግንባታ ስም ለማሳመር መጣር ናቸው።
የአዲስ አበባ ኮንደሚኒዬም ቤቶቾ ግንባታ ከምርጫ 97 ቦኋላ በመኖሪያ ቤቶች እጥረት የሚሰቃየውን ሕዝብ ልብ ለማማለልና የፖለቲካ ድጋፍ ለመግዛት ያስችላል ተብሎ የታሰበ ብቻ ሳይሆን የሚከተሉት ድብቅ ዓላማዎችም አሉት።
  1. በዘረፋ የከበሩ የቀድሞ ተጋዳላዮችና የጥቅም ተካፋዮቻቸው አይናቸው ያረፈባቸውን ቁልፍ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎች ሁሉ ለዘመናት በባለይዞታነት ይዘው የኖሩትን በልማትና በእንቨስትመንት ሥም በማፈናቀል ወደ ግላቸው ላማዞር ያስችላቸዋል፤
  2. በተለያዩ ሥም የተቋቋሙ የህንጻ ሥራ ተቋራጭ ድርጅቶቻቸው በግንባታው ሥራ በመሳተፍ መጠነ ሰፊ የሆነ ትርፍ ለማግበስበስ ያመቻቸዋል፤
  3. የሥርዓቱን ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ከሌላ ቦታ አምጥቶ በማስፈር በጠላትነት የተፈረጀውን የኅብረተሰብ ክፍል ተጽዕኖ ለማምከን ይረዳል፤
  4. በሀብት ዘረፋው ለመሳተፍ እድል የሌላቸው የበታች ካድሬዎችና ታማኝ አገልጋዮችን ተጠቃሚ በማድረግ በአለቆቻቸው ዘረፋ ተማረው ልባቸው እንዳይሸፍት ይከላከላል ፤
  5. ከተወለዱበትና ካደጉበት የግልና የቀበሌ ቤቶች ያለውደታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የኮኖዶሚኒየሙን ሂሳብ መክፈል እስከቻሉ ድረስ “ከቤታችን ተፈናቅለን ሜዳ ላይ ተጣልን” የሚል እሮሮ በማሰማት መንግስት ላይ አመጽ እንዳያስነሱ ስጋት ለመቀነስ ይረዳል፤
  6. ከሰሞኑ 40 ከመቶ ተብሎ በወጣው ፖሊሲ እንደታዘብነው ደግሞ ዜጎችን በማጓጓት ተቸግረው ያጠራቀሙትን ገንዘብ ዝግ የባንክ ሂሳብ ውስጥ እንዲከቱ በማድረግ የገንዘብ እጥረት አንገቱ ድረስ የዘለቀውን አገዛዝ ለመታደግ ያስችላል (በ16 የሥራ ቀናት ብቻ ከተመዘገበው 750, 000 የኮንዶሚንዬም ቤት አመልካች 750 000 000 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን) ብር መሰብሰቡን ልብ ይሏል)
ከዚህም በተጨማሪ የኮንደሚኒዬም ቤቶች ግንባታ በቂ ጥናትና ዝግጅት ያልተደረገበት የይድረስ ይድረስ ሥራ መሆኑን የቤቶቹ ርክክብ በተፈጸመ ማግሥት ስለ ህንጻው መሬት ውስጥ መስጠምና መጣመም መጀመር እየወጥ ያሉ ዜገባዎች ዋቤ ምስክር ናቸው።
የወያኔ መሪዎችና ታማኝ አገልጋዮቻቸው ከኮንደሚኒዬም ግንባታ በተጨማሪ ከምርጫ 97 ወዲህ ከፍተኛ ገንዘብ እያግበሰበሱ ያሉት የከተማ ቦታዎችን በውድ ዋጋ የልጅ ልጆቻቸው እንኳ ሊደርሱበት ለማይችል የግዜ ገደብ በሊዝ በመቸብቸብ ነው። በዚህ የመሬት ቅሪሚያ አንዳንድ ስግብግቦች “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ” እንዲሉ “ወያኔዎች መሬታችንን እየተቀራመቱ ስለሆነ ተሻምተን ማስቆም አለብን” በሚል ብልጣ ብልጥነት ከሚኖሩበት የስደት አገር እየተጓዙ የወያኔን ገቢያ በማድራት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በትዝብት ተመልክቶአል። አገርን ዘርፎ ለዘራፊ እየሰጠ ያለ መንግሥት ሴራ ተባባሪ መሆን በሞራልም ሆነ በህሊና ዳኝነት የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑ ሳያንስ እነዚህ በስግብግብነት የተጠመዱ ወገኖች ለንብረታቸው ደህንነት ሲባል ወያኔ ዓይናቸው እያየ ጆሮአቸው እየሰማ በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ የሚፈጽማቸውን ሰቆቃዎች እንኳ ለመቃወም ድፍረት በማጣት ሌላ ትዝብት ውስጥ ሲወድቁ ተስተውለዋል:: ለመሆኑ እነዚህ ወገኖች ለፍተው ባገኙት ገንዘብ የገዙት ባርነትን ነው ወይስ የንብረት ባለቤትነትን ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይኖራቸዋል?
የዜጎች መብት በተከበረበት አገር ከዜግነት መብቶች አንዱ የግል ሀብት ባለቤት ለመሆን ገደብ የሌለው ነፃነትና እድል መኖሩ ነው::
ወያኔ በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያችን ግን የንብረት ባለቤት ለመሆን የሥርዓቱ ባለሟል መሆን አለያም ከፖለቲካ ባላንጣነት መራቅ ዋና መስፈርት ናቸው። በዚህ መስፈርት ከወያኔ ጋር ተሻምተው ወይም ተሻርከው የንብረት ባለቤት ለመሆን እየተሽቀዳደሙ ያሉ ወገኖች ሊያውቁት የሚገባው ሃቅ ቢኖር አድሎአዊነት በሰፈነበት መንገድ የተገኘ ማንኛውም አይነት ሀብት ወይም ንብረት ወደፊት በወያኔ ከርሰ መቃብር ላይ በሚመሰረተው ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ህገዊ ጥበቃ የሚኖረው አለመሆኑን ነው። ብሄራው የአገር ጥቅም ላይ ክህደት ከፈጸመ ፤ ዜጎችን በማፈን ሰቆቃ ካደረሰ ፤ የአገሪቷን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል መሬታቸውን ቀምቶ ለሌሎች አሳልፎ ከሰጠ ፤ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ዘርፎ ለዘራፍ ከሰጠ ወንጀለኛ መንግሥት ጉያ ውስጥ ተወሽቆ እስከ ወዲያኛው የህግ ጥበቃ ሊደረግለት የሚችል ንብረት ባለቤት መሆን ማሰብ እጅግ ይቸግራል። ዜጎች በራሳቸው ወዝ ለፍተው ያገኙትን ንብረት ሳይቀር በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት ብቻ በሽብርተኝነት እየፈርጀ የሚነጥቅ ሥርዓት ዕድሜ እንደምንጠብቀው ረዥም ሊሆን እንደማይችል ማሰብ ብልህነት ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ አገዛዝ በውጭው ዓለም በስደት ከሚኖረው ወገናችን በአባይ ግድብ የቦንድ ሺያጭ ሥም ለመሰብሰብ ሞክሮ ያልተሳካለትን ገንዘብ በመሬት ሺያጭ እና በኮንደሚኒዬም ቤት ግዥ ሥም እንዲያገኝ ሊፈቀድለት አይገባም ብሎ ያምናል:: ስለዚህም እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ከዚህ ከኮንደሚኒዬም ቤቶች በስተጀርባ ያለውን ድብቅ አጀንዳ በማጋለጥ ጥረቱን በማምከን የሕዝባዊ እምብተኝነት ትግል አካል እንዲሆን ግንቦት 7 የትግል ጥሪውን ያስተላልፋል።

Saturday 6 July 2013

ብዙ ያልተነገረለት የኢህአዴግ ራዕይ – የአፍሪካ አውራ ፓርቲ መሆን!

መቼም የፖለቲካ ኮሜዲው ደራሲያንና ተዋንያን ማን እንደሆኑ አይጠፏችሁም ብዬ አስባለሁ፡፡ ፖለቲከኞቹ ናቸዋ! ተደራስያኑ ደግም ምስኪኑ ህዝብ! (“ልማታዊ ህዝብ” ይባላል እንዴ?) ለነገሩ “የበይ ተመልካች” ወይም ታዛቢ ብንባልም አይከፋንም (ሃቅ ነዋ!) እናላችሁ —- ፖለቲከኞቹ ይበላሉ፤ እኛ ኩራዝ እንይዛለን፡፡ ፖለቲከኞቹ ይወስናሉ፤ እኛ እንሰማለን፡፡ ምን ይደረግ … እጣ ፈንታችን እኮ ነው፡፡ (ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም!) ለነገሩ ተሰጥኦ ከሌለን ቀሽም ኮሜዲ ነው የምንሰራው (አያስቅ አያስለቅስ!) አያችሁ የፖለቲካ
ኮሜዲ ችሎታ ይጠይቃል – ልዩ ተሰጥኦ!
እኔ መቼም የፖለቲካ ኮሜዲ ዘመን መሆኑ በጣም ነው ደስ ያለኝ (ምርጫ የለኝማ!) ግን እኮ በምናብ ባቡር (እውነተኛው ባቡር እስኪጀመር–) ወደ ኋላ ሸተት ብላችሁ የ60ዎቹን የፖለቲካ ተውኔቶች ብትመረምሩ የአሁኑን የፖለቲካ ኮሜዲ “ተመስገን!” ማለታችሁ አይቀርም፡፡ መቼም ከፖለቲካ ትራጄዲ የፖለቲካ ኮሜዲ ይሻላል፡፡ እኔ በበኩሌ ከምናዝን ቢቀለድብን እመርጣለሁ (Choosing the lesser evil እንደሚባለው!)
አንዳንዶች የቀድም ጠ/ሚኒስትር “ግልባጭ” የሚሏቸው (እሳቸውም የእሱ “ግርፍ” ነኝ ብለዋል እኮ) የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ ከኢቴቪ ጋር የመጀመርያውን ቃለምልልስ ሲያደርጉ፤ አገራችን ከባለ ሁለት ዲጂት የኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር፣ በመንገድ ግንባታና ማስፋፊያ ሥራዎችም ከአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌላት ቀዳሚዋ አገር መሆኗን ሲገልፁ፤ (ሲያበስሩ በሚል ይተካልኝ!) ነፍሴ እንዴት በደስታ ጮቤ እንደረገጠች አልነግራችሁም፡፡ ከምሬ እኮ ነው! (ካልማልኩ አታምኑኝም?) ወዲያው ግን … አንድ “ነገረኛ ጥያቄ” ከአዕምሮዬ ጥግ ብቅ አለና ደስታዬን ነጠቀኝ። በቃ በጣፋጭ ህልም ከተሞላ የጥጋብ እንቅልፍ ላይ የተቀሰቀስኩ ነው የመሰለኝ፡፡ “በመንገድ ግንባታና ማስፋፊያስ ቀዳሚ ሆንን … በዲሞክራሲ ግንባታስ? በመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ምስረታስ? በነፃና ፍትሃዊ ምርጫስ? በፕሬስ ነፃነትስ? የህዝቦችን ሰብአዊ መብት በማክበርስ?–” ደህና የነበርኩት ሰውዬ የነፃነት ታጋይ ሆኜላችሁ ቁጭ አልኩ፡፡ አይገርማችሁም? ያለ ዕቅድና ያለ ፍላጐቴ እኮ ነው በእነዚህ ሁሉ የጥያቄዎች ጐርፍ የተጥለቀለቅሁት፡፡ ታዲያ ምን እንደቆጨኝ ታውቃላችሁ? ያንን ጠ/ሚኒስትሩን ኢንተርቪው ያደረገ የኢቴቪ ጋዜጠኛ ባገኝ ኖሮ “ጠይቅልኝ” ብዬ እማፀነው ነበር (ለእኛ እስኪገኙ ልማታዊ ጋዜጠኛ ልጠቀም ብዬ እኮ ነው!)
በነገራችሁ ላይ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ቶፕ 10 ውስጥ መግባቷን ሰምታችኋል አይደል? (ሪፖርቱ ኢህአዴግ አይልም – ኢትዮጵያ እንጂ!)
ከዓለም ጋዜጠኞችን በብዛት በማሰር ቁጥር አንድ አገር ማን መሰለቻችሁ? ቱርክ ናት ይላል- ሪፖርቱ። 49 ጋዜጠኞቿ ቤታቸው ወህኒ ሆኗል፡፡ ኢራን 45 ጋዜጠኞችን አስራ በሁለተኛነት ትከተላለች፡፡ ቻይንዬ ደግሞ 32ቱን የፕሬስ ሰዎች ሸብ አድርጋ ሶስተኛ ደረጃ ይዛለች፡፡ አራተኛዋ አገር ዘመዳችን ኤርትራ ስትሆን 28 ጋዜጠኞችን ዘብጥያ አውርዳለች፡፡ ኢትዮጵያ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች – ጋዜጠኞቿን በማሰር፡፡ በነገራችሁ ላይ መንግስታት ምን እንደነካቸው አይታወቅም ጋዜጠኞችን እንደጦር መፍራት ጀምረዋል፡፡ እናም ዘንድሮ ከ1990 ዓ.ም ወዲህ በመላው ዓለም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ነው ሪፖርቱ ይፋ ያደረገው – በጠቅላላው በ27 አገራት ውስጥ 232 ሪፖርተሮች፣ የፎቶ ጋዜጠኞችና ኤዲተሮች ለእስር ተዳርገዋል (ስልጣን ሳይሆን መረጃ ጠይቀው!)
እኔ የምላችሁ ግን … ኢቴቪ የሚዲያ ዳሰሳ የሚለው ፕሮግራሙ ላይ የስያሜ ለውጥ አደረገ እንዴ? የሚዲያ ዳሰሳው ቀርቶ የኒዮሊበራል አቀንቃኝ አገራት የተራራቁበትን “ልማታዊ መፃህፍት” እያስኮመኮመን እኮ ነው፡፡ እኔ ግን አንድ ሃሳብ አለኝ – ስለ ፕሮግራሙ፡፡ ሃሳቤ በይዘቱ ወይም በአቀራረቡ ላይ አይደለም፡፡ በፕሮግራሙ ርዕስ ወይም ስያሜ ላይ ብቻ ነው! እንደኔ እንደኔ የሚዲያ ዳሰሳም ሆነ የመፃህፍት ዳሰሳ የሚለው ስያሜ ፈፅሞ ፕሮግራሙን አይመጥንም፡፡ እውነቴን እኮ ነው … ጋዜጠኞቹ የሚያቀርቡልን እኮ ዳሰሳ ሳይሆን የስብከትና የፕሮፓጋንዳ ቅይጥ ነገር ነው (ሚስቶ እንደሚሉት) ስለዚህ ለምን በኢቴቪ የፕሮፓጋንዳና የቅስቀሳ ዲፓርትመንት ሥር “የልማታዊ አስተሳሰብ ማስፋፊያ ፕሮግራም” አይባልም? የሚል ሃሳብ አለኝ (ዲፓርትመንቱ ከሌለ ይቋቋማ!) ልብ አድርጉ! እንዲህ ያሻኝን የምናገረው ኢቴቪ የእኛ የሰፊው ህዝብ ሃብትና ንብረት ነው ብዬ ነው (ለግል ባለሃብት ተሸጠ እንዳትሉኝ?)
አንዳንዴ ተቃዋሚዎች፤ “ኢህአዴግ ሚዲያውን በሞኖፖል ተቆጣጥሮታል” ሲሉ እሰማና እኛ ሳናውቅ ንብረታችን ተሸጠ? ብዬ እደነግጣለሁ (ኢህአዴግ ገዝቶት እንዳይሆን ብዬ እኮ ነው!) አለዚያማ ማን የማንን ንብረት ይቆጣጠራል? ወይም ደግሞ እንደ መሬት “የህዝብና የመንግስት” ነው ይበሉንና አርፈን እንቀመጥ፡፡ እኔ የምለው ግን —- የፖለቲካ ምህዳር የማን ንብረት ነው? “የህዝብና የመንግስት” ነው እንዳትሉኝና እንዳታስቁኝ (የዘመኑ ፖለቲካ ኮሜዲ ነው አልተባባልንም?) ኢህአዴግ ግን አንዳንዴ ያበዛዋል፡፡ ምናለ እቺን እንኳ ለተቃዋሚዎች ቢለቅላቸው (የፖለቲካ ምህዳር መሬት መሰለው እንዴ?)
በነገራችሁ ላይ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ምስጉን ሠራተኞች ሰሞኑን መሸለማቸውን ስሰማ እንዴት ደስ እንዳለኝ አታውቁም፡፡ የህዝብ ሽልማት ቢቀርባቸው የድርጅቱን እንኳን ያግኙ እንጂ! (ከሁለት ያጣ ሆኑ እኮ) ይሄን ደስታዬን ለአንዱ “ሟርተኛ” ወዳጄ ሳጋራው ምን እንዳለኝ ታውቃላችሁ? (“ደርግም እኮ “ኮከብ ሠራተኞች” እያለ ይሸልም ነበር!”) ምኑ ጨለምተኛ ነው ባካችሁ?
እናንተ— ሰሞኑን የሰማኋት አንዲት ዜና እንዴት ያለች የፖለቲካ ኮሜዲ መሰለቻችሁ! የዜናዋን ፍሬ ነገር ልንገራችኋ — ባለፈው ሳምንት ወደ ሩዋንዳ የተጓዙት ጠ/ሚኒስትራችን፤ ከሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ጋር መወያየታቸውን የዘገበው ኢቴቪ፤ ፓርቲያቸው ኢህአዴግ ከሩዋንዳዉ ገዢ ፓርቲና ከሌሎች ተራማጅ አስተሳሰብ ያላቸው የአፍሪካ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁሟል (ዘይገርም ነገር!) የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን የህይወት ታሪክ በሚተርከው “የነጋሶ መንገድ” የተሰኘ መፅሃፍ ላይ ያነበብኩትን አንድ መረጃ ካልነገርኳችሁ የዚህን ዜና አንደምታ ልታገኙት አትችሉም፡፡ ኢህአዴግ ገና ድሮ በትግል ላይ ሳለ (ከስልጣን ጋር ሳይተዋወቅ ማለት ነው) ስለነበረው ራዕይ ነጋሶ ሲናገሩ፤ “ኢህአዴግ በአፍሪካ ግዙፍና ተፅዕኖ ፈጣሪ ገናና ፓርቲ የመሆን ራዕይ” እንደነበረው ገልፀዋል፡፡ አሁን ትንሽ ተገለጠላችሁ? እኔ ሳስበው ኢህአዴግ ሩዋንዳ ድረስ ሄዶ ከባዕድ ፓርቲ ጋር ተስማምቶ የተመለሰው እቺን የጥንት ራዕይ ለማሳካት ይመስለኛል፡፡ አንዳንዶች “እዚህ መዲናዋ እምብርት ላይ 34 ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደራደር እያሉ ሲማጠኑት ሩዋንዳ ተሻግሮ መደራደር ምን ዓይነት ንቀት ነው?” ሊሉት ይችላሉ (ሲሰማቸው አይደል!)
አያችሁ — ኢህአዴግ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መስራትን በተመለከተ ሁለት ራዕዮች እንዳሉት የደረስኩበት ሰሞኑን ነው – አገራዊና አህጉራዊ ይባላል። ቅድም እንደነገርኳችሁ አህጉራዊ ራዕዩ በአፍሪካ ገናና ፓርቲ መሆን ነው – ተፅዕኖ ፈጣሪ ግዙፍ ፓርቲ! አገራዊ ራዕዩስ? እንግዲህ ራዕይ ይሁን አይሁን አላውቅሁም እንጂ ከ2002 ምርጫ በኋላ “አዲስ ራዕይ” በተሰኘው የራሱ ልሳን ላይ እንዳሰፈረው ተቃዋሚዎች እንዳያንሰራሩ ለማድረግ በርትቶ እንደሚታትር ጠቁሟል (ጨለምተኛ ራዕይ ይሏል ይኼ ነው!)
አህጉራዊ ራዕዩን በተመለከተ ትንሽ የሚያሰጋኝ ምን መሰላችሁ? ኢህአዴግ ከአፍሪካ ልማታዊ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት ወይም ግንባር ከመሰረተ በኋላ እዚህ አገር እንዳደረገው “ገናና ፓርቲ ነኝ” ብሎ ሸብ ለማድረግ እንዳይሞክር ነው (እነሱስ በእጃቸው ሙቅ ይዘዋል እንዴ?) ለነገሩ ኢህአዴግም ቢሆን አብዛኞቹ የአፍሪካ ገዢ ፓርቲዎች እንደሱው የነፃነት ታጋዮች እንደነበሩ የሚዘነጋው አይመስለኝም (ሁሉም በልቡ ገናና ነኝ ባይ እኮ ነው!) ምናልባት ዘንግቶት ችግር ላይ ከወደቀም የሚያዝንለት የለም፡፡ “የአገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጡር ነው” እየተባለ መሳለቂያ ነው የሚሆነው፡፡
እኔ የምለው ግን— ከአገሩ አልፎ በአህጉር ደረጃ ገናና የመሆን ህልም ያለው ፓርቲ እንዴት የኮሙኒኬሽን አቅምና ብቃት አይኖረውም? ኢህአዴግ እኮ በኮሙኒኬሽን “Poor” ነው (ድክም ያለ!) አንዴም እንኳ የመግባባት ብልሃቱን ሳያሳየን ይኸው 21 ዓመት ሞላው። እንኳንስ “ጠላቴ” ብሎ ከፈረጃቸው ተቃዋሚዎች ጋር ቀርቶ ከእኛ ከህዝቦቹ ጋር እንኳ ሁሌ አይደል የሚላተመው? (ደግነቱ አጥፍቻለሁ ማለት ይወዳል!) እውነቴን ነው የምላችሁ —- ኢህአዴግ ከአገር በቀሎቹ ፓርቲዎች ጋር እንዲህ ዓይንና ናጫ ሆኖ አህጉራዊ ራዕዩን ለማሳካት ቢነሳ ፈፅሞ አይሳካለትም፡፡ ለማንኛውም ግን ያስብበት ለማለት ያህል ነው
source : andinetethiopia

Amnesty International in Canada launched petition campaign to the release of Eskinder Nega

July 6, 2013

Eskinder Nega: Journalist unjustly jailed in Ethiopia

Amnesty International for the release of Eskinder Nega

Please add your name toAmnesty International’s petition to the Ethiopian authorities to release Eskinder Nega immediately.

Eskinder’s story

Eskinder Nega is an Ethiopian journalist and human rights activist.
Eskinder has been subjected to outrageous injustices. He was sentenced to 18 years in jail for writing articles calling for freedom of expression and an end to torture in Ethiopia.
Sadly, this is not the first time that Eskinder has been jailed for his activism. Eskinder and his wife, Serkalem, a newspaper publisher, were previously jailed for speaking out against the government in 2005 and released in 2007 after continued campaigning by Amnesty International.
His previous arrest came after the Ethiopian government ordered a violent crackdown on post-election protests in 2005. Security forces reportedly killed nearly two hundred people. Eskinder and Serkalem wrote and published articles criticizing the government’s actions. For this, they were both arrested and put in prison.Their son, Nafkot, was born in that prison.
For Eskinder, this was one more brutal act of oppression in a life spent being hounded by his government for defending human rights. Few families have sacrificed more for their people.
In recent years, the Ethiopian government has clamped down alarmingly on its citizens for speaking out. According to Serkalem, “freedom of expression and press freedoms are at their lowest point.” Now the regime has enacted a “terrorism” law that they use to silence anybody critical of them.
They used these laws to threaten Eskinder. To ban him from writing. To force Serkalem to stop publishing. To terrorize their family and threaten Eskinder with the death penalty.
And now – to arrest Eskinder alongside many other prominent journalists.
Amnesty International believes Eskinder Nega is a prisoner of conscience detailed solely for his peaceful and legitimate activities as a journalist. Join our call for his immediate release.

Human Rights in Ethiopia

In Ethiopia, the authorities routinely use criminal charges and accusations of terrorism to silence dissenters. Repression of freedom of expression has increased alarmingly in recent years. The Ethiopian government has systematically taken steps to crush dissent in the country by jailing opposition members and journalists, firing on unarmed protesters, and using state resources to undermine political opposition. More than a hundred other Ethiopians, including nine journalists, were charged under the antiterrorism law. About 150 Ethiopian journalists live in exile — more than from any other country in the world.
Use this form to add your name to Amnesty’s call for the Ethiopian government to immediately and unconditionally release Eskinder Nega from prison.

What else you can do

Write a letter
Write a polite letter in your words directly to Ethiopia urging the release of Eskinder. In your letter you can address some of the following points:
  • Release Eskinder Nega immediately and unconditionally on the grounds that he is a prisoner of conscience
  • Reunite his family and allow him to return to his work as a journalist
  • Until he is free he must be protected from torture and other ill-treatment
  • He should also have regular access to his lawyer, family, and to any medical care he may require
Address your letter to:
Prime Minister, Hailemariam Desalegn
P.O. Box 1031 Addis Ababa Ethiopia
Minister of Justice, Berhan Hailu
P.O. Box 1370 Addis Ababa Ethiopia

በግብፅ ያየነው ህዝባዊ ትዕይንት በኢትዮጵያም እንደምናየው ጥርጥር የለንም!

ECADF_Ethiopian_News
July 6, 2013
ስምንቶቹ
ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም
በአለማችን እጅግ አስከፊ አምባገነናዊ ስርዓቶች ታይተው አልፈዋል:: በቅርቡ ካየናቸው አምባገነኖች መካከል የግብፁ ሙባረክ፣ የቱኒዚያው ቤን አሊ፣ የሊቢያው ጋዳፊ፣ እንዲሁም የኛው መለስ ዜናዊ ይጠቀሳሉ። ለአምባገነናዊ ሥርዓት መፈጠር በዋናነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ ከጥቂት ግለሰቦች ከልክ ያለፈ የበላይነትን የማፍቀር አስቀያሚ ባህሪ የመነጨ በመሆኑ፤ እንደነዚህ ያሉ ሰይጣን ግለሰቦች አሁንም ድረስ በሰው ልጅ መሃል መብቀላቸው አይቀሬ ነው። በተለይ በአፍሪካ የሚገኙ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራት ውስጥ አምባገነን ሲገረሰስ ሌላ አምባገነን ሊወጣ እንደሚችል አስቀድሞ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። አምባገነኖች የግለኝነት ባህሪያቸውን በሚገርም መልኩ መቆጣጠር ባለመቻላቸው ምክንያት በሚችሉት አቅምና በሚያገኙት ቀዳዳ ሁሉ የግል ፍላጎታቸውን እውን ለማድረግ መሞከራቸው አይቀሬ ነው። ለዚህም በቅርቡ በግብፅ አምባገነኑ ሙባረክን ለማስወገድ በአንድነት የወጣው ህዝብ የእግር ኮቴ ሳይደርቅ ዳግም አምባገነን ለመሆን ሲሞክሩ የተወገዱት ፕሬዚዳንት ሙርሲን እንደ አብነት ማስታወሱ በቂ ይመስለናል:: የኚህ ሰው ታሪክ በራሱ አምባገነንን ለመጣል በሚደረግ ትግል ውስጥ ሌላ አምባገነናዊ ሥርዓት ዳግም እንዳይመጣ ለማረጋረጥ ሊወሰዱ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች ስለመኖራቸው ጠቋሚ ነው። በዚህ ዙሪያም በቅርቡ ሃሳባችንን በስፋት ለማካፈልና ለመወያየት እንሞክራለን።
የሁሉም አምባገነናዊ ሥርዓቶችና በጭቆናቸው ቀንበር ስር ወድቀው የሚሰቃዩ ህዝቦች ብሶቶች ተመሳሳይነት በፅሁፋችን ርዕስ ባነሳነው ሃሳብ ዙሪያ መወያየቱ አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራሉ። በተጨማሪም አበው “ነገር በምሳሌ …” እንዳሉት፤ በቅርቡ “የአረብ ስፕሪንግ” ተብሎ የሚጠራው በመካከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍሪካ የተካሄደውን የህዝብ አመፅ እንደ አብነት ማንሳቱ ጠቃሚ ይመስለናል::
ቱኒዚያ የአረብ ስፕሪንግ ጀማሪዋ ሃገር መሆኗ ይታወቃል:: የህዝብ አመፁ በቱኒዚያ በተሳካ ሁኔታ ከተጠናቀቀና ቤንአሊም ከተባረረ በኋላ ይህ የህዝብ አመፅ ወደ ግብፅ ሊሄድ ይችል ይሆን? በሚለው ጥያቄአዊ ሃሳብ ላይ የፖለቲካ ጠበብቶች ብዙ ብለው ነበር:: በተለይ ቱኒዚያ ግብፅ አይደለችም ስለዚህ የህዝብ አመፁ እንደ ቱኒዚያ ሁሉ በግብፅ ሊከሰት አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ ደግፈው ምክንያታቸውን ሲደረድሩ የነበሩ ብዙ ናቸው::
ይህንን ቱኒዚያ ግብፅ አይደለችም የሚል ሃሳባቸውን ለማስረዳት ሲጠቅሷቸው ከነበሩት ምክንያቶች መካከል በቱኒዚያ ህዝብ መካከል ያለው የሙስሊሙና የክርስትናው ሃይማኖቶች ውጥረት ግብፅ ካለው እጅግ በጣም ያነሰ ስለሆነ በግብፅ ህዝብ አንድ ሆኖ ሊታገል አይችልም፣ ቤንአሊ እንደ ሙባራክ ጨካኝ አይደለም፣ ሙባራክ ጠንካራ የጦር ሰራዊት አለው ስለዚህ በቀላሉ ከህዝብ መካከል ጥቂቶችን ገድሎ ሊቀጨው ይችላል፣ ቱኒዚያዎች ከግብፆች የበለጠ የተማሩ ናቸው፣ የፌስቡክና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎችንም ቱኒዚያዎች በስፋት ተጠቃሚዎች ስለሆኑ ግብፅ ውስጥ እንደ ቱኒዚያ ያለ አመፅ ሊከሰት አይችልም፣ ሌላም ሌላም… እያሉ ትንታኔዎችን ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወቃል:: ይታዩአቸው የነበሩት ምክንያቶች ግብፆች በሙባረክ አምባገነናዊ አገዛዝ ለአመታት ብዙ ተረግጠዋል፣ ተጎድተዋል፣ ተበዝብዘዋል፣ እነርሱ በድህነት እየማቅቁ ሳሉ ጥቂት ግለሰቦች በሃብት ሲትረፈረፉ ምንም አላደረጉም የሚሉት ብቻ ነበሩ:: ነገር ግን ፍፃሜው ላይ የታየው እውነታ፤ ግብፆች እጅግ ማራኪ የሆነ የህዝብ ትብብርና ሰላማዊ ተጋድሎን በአደባባይ ለአለም ህዝብ በሚገባ ማሳየታቸውና፤ አስፈሪና ጨካኝ እየተባለ ሲነገርለት የነበረውን የሙባረክ ስርዓት ከትከሻቸው ላይ አሽቀንጥረው መጣል መቻላቸው ነው:: በዚህ ዙሪያ ምሁሮቹና ፖለቲከኞቹ ያለማስተዋል ችላ ብለውት የነበረው ዋናው ቁምነገር የህዝብ እምቅ ሃይል በአምባገነኖች አስፈሪነት ሊሟሽሽ ፈፅሞ እንደማይችል ነበር::
የወያኔ/ኢህአዴግ ቡድን ስልጣን ከተቆናጠጠበት ሰአት ጀምሮ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እጅግ ስር የሰደዱ ችግሮችንና በደሎችን ሲፈፅም ኖሯል:: የኢትዮጵያ ህዝብ የተጫነበት ህመም ከግብፅና ከቱኒዚያ እጅግ የከፋ ነው:: በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ 11ኛው ሰአት ላይ እንደሚገኝ ለሁላችንም ግልፅ ነው:: ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደ ግብፆቹ ሁሉ፤ የወያኔ/ኢህአዴግ ጦር ሰራዊት መብዛት፣ ፍቅር እያለው በዘር በሃይማኖት ሳይወድ መከፋፈሉ፣ ጥቂቶች ሲበለፅጉ እርሱ ግን በድህነት መማቀቁ፣ በተቃውሞ ሰልፍ ብሶቱን ለማሰማት በወጣ ቁጥር በአጋዚው የወያኔ ሃይል በተደጋጋሚ በግፍ መጨፍጨፉ፣ መታሰሩና፣ ስቃይን መቀበሉ የህዝብን እምቅ ሃይል በበለጠ ያጎለብትለት እንጂ ሊያዳክመው ፈፅሞ አይቻለውም::
ነገር ግን በግብፅ የተደረገው የተሳካ አመፅ ዝም ብሎ በመላ የመጣ አይደለም:: የአመፁ አስተባባሪዎችና አንቀሳቃሾች እጅግ በጣም በሳል ስራዎችን ስለሰሩ፣ የህዝብን የልብ ትርታ እጅግ አድርገው በመረዳታቸው፣ ቁስሉ ስለተሰማቸው፣ የሙባረክ ስርዓት ሃገርንና ህዝብን እንደሚያጠፋ በመረዳት እውነታውን ለህዝብ ስላመላከቱት፣ ብሎም ህዝብ ወዶና በቃኝ ብሎ ትግሉን እንዲቀላቀል ስላስቻሉት ነው:: የኛም ፖለቲከኞችና የድርጅት መሪዎች ፍፁም የሆነ የአመለካከትና የአካሄድ መሰረታዊ ለውጥ በማድረግ፤ የህዝብ ቁስል ሊያማቸው፣ እውነታውንም ሊነግሩትና፣ ወደ ህዝብ ገብተው ከዚህ ስቃይና መከራ ሊታደጉት ይገባል:: ስለሆነም እጅግ ብዙ ስራዎች እንደሚጠብቃቸው መረዳት ያለባቸው ይመስለናል:: ከግብፆቹ ተምረው እራሳቸውን ካስተካከሉ የምንመኛትን፣ ለሁሉም እኩል የሆነችና፣ የህዝብ የበላይነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን በቅርቡ እንደምናያት ጥርጥር የለንም::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት? በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ?

በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ?

workneh and bereket


ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የአዲስ የሚኒስትሮችና የ”ከፍተኛ” ባለሥልጣናት ሹመት ተከትሎ ከውስጥም ከውጭም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ሪፖርተር “ምንጮቼ ነገሩኝ” በማለት አቶ በረከት ስምዖንን የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር የሚያደርጋቸው አዲስ ሹመት እንደሚሰጣቸው ዘግቦ ነበር። ይህንኑ ዜና ተከትሎ “ኢትዮጵያ በኦፊሴል በኤርትራ መመራት ጀመረች” በማለት ቅድመ አስተያየት የሰነዘሩ ጥቂት አልነበሩም።

ሚዲያውን መዳፋቸው ስር አኑረው የቆዩት አቶ በረከት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነታቸው ተነስተው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም የፖሊሲና ጥናት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው “በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ከመለስ ህልፈት በኋላ ኢህአዴግ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያሳዩት አቶ በረከት ከድርጅታቸው ይሁንታ ውጪ “አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስትር ይሆናሉ። የሚቀረው የስርዓት ማሟላት ጉዳይ ነው” ማለታቸው  የህወሃትና የኦህዴድ ሰዎችን ክፉኛ አበሳጭቶ እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች “አቶ በረከት አማካሪ ሆነው ወደ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ መዛወራቸው ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር የመገፋት ወይም ስራ አልባ የማድረግና ከቀጥተኛ ተሳታፊነት የመታቀብ ያህል ነው” ባይ ናቸው።
“በዜግነታቸው ብቻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የመሳተፍ መብት የሌላቸው አቶ በረከት ሲፈነጩበት ከነበረው የኢህአዴግ ሚዲያ bereketመሰናበታቸው በራሱ በርካታ ጉዳዮችን የሚያመላክት ነው” የሚሉት ምንጮች “የፖሊሲና የጥናት ጉዳዮች ከፍተኛ የቀለም እውቀትና ልምድ የሚጠይቅ ሃላፊነት ነው። አቶ በረከትም ሆነ አቶ ኩማ ለዚህ አይመጥኑም። ውሳኔው ማቀዝቀዣ ውስጥ የማስገባት ያህል ነው” ሲሉ አቶ በረከት ያላቸው የአደባባይ ሚና ማክተሙን ያወሳሉ።
በሌላ በኩል የተለየ አስተያየት የሚሰነዝሩ ክፍሎች እንደሚሉት “አቶ በረከት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ እለት እለት ሥርስራቸው ሆነው እንዲሰሩ የተሰጣቸው ስልጣን ነው። ይህ የሚያሳየው እሳቸው አሁንም ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቀጠላቸውን ነው” በማለት የሃሳብ ልዩነታቸውን ያስቀምጣሉ።
አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የቀረበ ግንኙነት እንደነበራቸው፣ አቶ መለስ በህይወት እያሉም ቢሆን ሶስቱ እንደማይለያዩ ያመለከቱት ክፍሎች፣ የህወሃት የበላይ አመራርና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር መሪ የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስትር ውስጥ የሚሰይሙት ሚኒስትር፤ ሪፖርትር እንዳለው አቶ በረከት ካልሆኑና የህወሃት ሰው ከተሾመ “በትክክልም አቶ በረከት ወደ ማቀዝቀዣ ክፍል ገብተዋል ማለት ነው” ሲሉ ሁለት ጫፍ ያለው አስተያየት ሰንዝረዋል።
አቶ ኩማ አሁን ባለው ኦህዴድ ውስጥ አንጋፋና ታማኝ፣ በቅጣት ከሶስት ዓመት ማዕቀብ በኋላ ወደ መንግስት ሃላፊነት የተመለሱ፣ kumaኦህዴድን ማጥራት ሲፈለግ በትር የሚጨብጡ፣ በመሆናቸው ከንቲባነቱን ሲለቁ እንዳያፈገፍጉ አዲሱ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው አብዛኞች ይስማማሉ። አቶ ኩማ ካላቸው ልምድና ዕውቀት አንጻር አቶ ሃይለማርያምን በፖሊሲ ጉዳዮችና በጥናት ረገድ ለማማከር የሚችሉ ሰው እንዳልሆኑ ስምምነት መኖሩን የሚጠቁሙ ጥቂት አይደሉም። ከዚህ አንጻር በዓለምቀፋዊ ዋና ከተማነት ከምትታወቀው አዲስአበባ ከንቲባነት ወደ አማካሪነት ኩማ ደመቅሳ “ሲሾሙ” እንደ ሥልጣን ሽረት ከተቆጠረ፤ የበረከት ስምዖን በተመሳሳይ መልኩ መታየት የማይችልበት ምክንያት ሊኖር እንደማይችል የሚከራከሩ አሉ፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሥልጣን በምክትል ጠ/ሚ/ርነት ሲያድግና ኢህአዴግ በምርጫ የመሸነፍ ቅንጣት ችግር ሳይኖረው ኩማን ከከንቲባነት ሥልጣን ማንሳቱ የብቃት ማነስና አለመፈለግ እንደሆነ ተጨማሪ አስተያየቶች አሉ፡፡
ለሶስትና አራት ዓመት ህጻን “ከክልላችን ስለተባረርክ የትምህርት ገበታህ ላይ መቀመጥ አትችልም” የሚል ደብዳቤ የሚጽፉና በሙስና በከፍተኛ ደረጃ የሚታሙት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ትምህርት ሚኒስትርነት የተሻገሩት አቶ ሃይለማርያም ደቡብ ክልል ላይ ያለውን ሰንሰለት ለመበጣጠስ እንዲያመቻቸው እንደሆነ ይገመታል። ሃዋሳ ነዋሪ የሆኑ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ሽፈራው የዘረጉት ድር መበጣጠስ እንዳለበት የታመነው አሁን አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠር የክልል በጀት እንደፈለጉ ከሚያስኬዱበትና ያለገደብ ሥልጣናቸውን ከሚያከናውኑበት የክልል ፕሬዚዳንትነት ወደ ሚኒስትርነት “መሾም”፤ የሥልጣን ሽረት ተብሎ ከመጠራት ውጪ ምንም ሊባል እንደማይችል በሽፈራው ሽጉጤ አመራር የተማረሩ ብቻ ሳይሆኑ ደጋፊዎቻቸውም ያመኑበት ጉዳይ ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስቴርን መምራት ያቃታቸው አቶ ደመቀ በስራ ብዛት ሰበብ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸውን ወንበር ብቻ እንዲይዙshiferaw መደረጉን ያመለከቱት ክፍሎች “አቶ ሽፈራው በሹመቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ ከሚቀርቧቸው ሰምተናል። ሃዋሳ በክልሉ መስተዳድር ውስጥ እሳቸው የሰገሰጓቸውም ስጋት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሃይለማርያም “ታማኛቸውን” በመሾም (“በማስመረጥ”) እውነተኛ የደኢህዴን ሊቀመንበርነታቸውን እንደሚያረጋግጡም ይጠበቃል፡፡
ደመቀ መኮንን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸው ብቻ እንዲቀጥሉ የተደረጉት ምን አልባትም አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስቴር ውስጥ በአማራ ክልል ከነበራቸው “ልምድ” አኳያ ለኮታ ማሟያ ታስበው ነው በሚል ካድሬው በስፋት እንደሚያወራ እየተሰማ ነው። አቶ ደመቀ በአማራ ክልል የደህንነቱ መሪ እንደነበሩና በዚሁ በተግባራቸው “የተመሰገኑ ታማኝ” ለመሆን መብቃታቸውን የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።
ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ልጆቻቸውን በትምህርት ቤት እየሰደቧቸው በመቸገራቸው እንደነበር የሚያስታውሱት እኒህ ክፍሎች “አቶ ደመቀ የአማራው ክልል መሬት ተላልፎ ሲሰጥ አቶ አያሌው ጎበዜ አልፈርምም ሲሉ፣ እሳቸው መፈረማቸው ይፋ ከሆነ በኋላ DemekeM‘ከሃዲ’ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ህጻናት ልጆቻቸውም ትምህርት ቤት መማር ያልቻሉት ለአባታቸው በተሰጠ ስም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቻቸው ስለሚያበሽቋቸው ነው” በማለት አቶ ደመቀ ቀደም ሲል ጀምሮ ከደህንነቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት ታማኝ እንዳሰኛቸው አስታውቀዋል። ከዚሁ ውለታቸውና ልምዳቸው አንጻር በደህንነት መ/ቤት ውስጥ ይካተታሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሰኔ 27 ቀን ለተሰየመው ፓርላማ በቀረበው ሹመት መነጋገሪያ ከሆኑት መካካል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ችግር እንደተጣባው የተመሰከረለትን የትምህርት ሚኒስቴርን እንዲመሩ መመደባቸው፣ አንዲሁም የአቶ ደመቀ በ”ስልጣን በዛባቸው” ሰበብ የሚኒስትርነት ቦታቸውን መነጠቃቸው በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው።

የወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ሹመት

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው ከሚቀርቡት ምክንያቶች መካከል ቀደም ሲል ለረዥም ዓመታት ከደህንነቱና ከሽብር መከላለከል ግብረ ሃይል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ከፍተኛ መሆኑ በግንባር ቀደም ይገለጻል። ለጎልጉልአስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ኢህአዴግ የትራንስፖርቱን ዘርፍ በቅርብ መቆጣጠር ይፈልጋል።
በምርጫ 97 ወቅት ለታየው ህዝባዊ መነቃቃት የትራንስፖርቱ ዘርፍ፣ በተለይም የታክሲና የግል ማመላለሻዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ያስታውሳሉ። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እስከወዲያኛው እንዳይታሰቡ ለማድረግ ዘርፉን ከደህንነቱ ጋር በቅርብ ማጠላለፍ፣ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ እየገነባሁ ነው የሚላቸውን መንገዶች፣ የስልክና የብሮድ ባንድ መስመሮች፣ የባቡር ትራንስፖርት በቅርብ ለመቆጣጠርና የቁጥጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ለማስገባት አቶ ወርቅነህ ሁነኛ ሰው ሆነው መገኘታቸውን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።
አዲሱ ቴሌን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን ከደህንነቱ መዋቅር ጋር በቀላሉ ለማያያዝ ልምዳቸውና የመረቡ አባል ሆነው Workineh-Gebeyehu-መቆየታቸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ያደረጋቸው አቶ ወርቅነህ፣ የጄኔራልነት ማዕረጋቸው ከሳቸው ጋር ይቆይ ወይም ይነሳ የተገለጸ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች አቶ ወርቅነህን በታማኝነት መድበው የተቀበሏቸው ሰው ስለመሆናቸው ጥርጥር የላቸውም።
አቶ ወርቅነህ ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በዚሁ ታማኝነታቸው ስልጣናቸውን ሳይጠቀሙ በፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርነት ለረዥም ጊዜ መቆታቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አቶ ወርቅነህ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሰባት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ተውጣጥቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የ”ደህንነት ኮር” ውስጥ አባል እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህንን ኮር በአዲስ እየተዋቀረ ስለሆነ አቶ ወርቅነህ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት የተዛወሩት ከደህንነቱ የኮር መዋቅር ውስጥ እንዲወጡ ስለተፈለገ መሆኑን ይገልጻሉ።
ዝርዝር ጉዳዩን ለማብራራት እንደሚቸገሩ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ እንዲዋቀር አዋጅ የታወጀለት የደህንነት መ/ቤት ሚኒስትርና የበላይ ሃላፊዎች ይፋ ሲሆኑ ነገሮች ይበልጥ እንደሚጠሩ ተናግረዋል። በኢህአዴግ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረውና አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዳልጠራ የሚነገርለትን ልዩነት ተከትሎ የተሸናፊውን ወገኖች የማጥራት ስራ በተለያዩ ስልቶች እንደሚሰሩ የጠቆሙት እነዚህ ክፍሎች፣ የደህንነት ሚኒስትር ሲቋቋም የሚሾሙት ባለስልጣን ከቀድሞዎቹ መካከል እንደማይሆን ምልክት ማየታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን የአዲስ ሹመትና ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሃሙስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በአንድ ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።በዚህም መሰረት
አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ – የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው አስፋው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ – በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ – የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ በከር ሻሌ ዱሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ – የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር
አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
ሆነው የተሾሙ ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።

Thursday 4 July 2013

የኩማ አስተዳደር የመጨረሻውን የስንብት ጉባዔ ሊያደርግ ነው

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባን ለ5 አመታት ሲመራ የነበረው የኩማ አስተዳደር  ሐሙስ ሰኔ 27 ጀምሮ  ለአዲሱ ኢህአዴግ መራሽ ካቢኔ ሥልጣኑን እንደሚያስረክብ ተጠቆመ፡፡
በመልካም አስተዳደር ችግር፣ በሙስናና ብልሹ አሰራር የሚተቸው የኩማ አስተዳደር የምርጫ 97 ቀውስን ተከትሎ ከተመሰረተው የባለአደራ አስተዳደር ስልጣኑን በግንቦት ወር 2000 ዓ.ም በምርጫ ስም የተረከበ ሲሆን ባለፉት አምስት ዓመታት የከተማዋን ሕዝብ የሚያረካ ሥራ ሳያከናውን ለመሰናበት መብቃቱን ለአስተዳደሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
የኩማ አስተዳደር ስራ እንደጀመረ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚል የኢህአዴግ አባላትና
ደጋፊ ለሆኑ በሺ የሚቆጠሩ ጀማሪ ምሩቃን ተማሪዎችን በመቅጠርና ያለልምድ በከፍተኛ ኃላፊነቶች ጭምር ማሰቀመጡ ነባሩን ሠራተኞች ከማስከፋቱም በተጨማሪ አብዛኛዎቹ ወጣቶች በሙስናና ብልሹ አሰራር ውስጥ በመጠለፋቸው ዕቅዱ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
የአስተዳደሩ ምክር ቤት ከሰኔ 27 እስከ 29 ድረስ ምክር ቤቱ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ የአስተዳደሩን የአምስት አፈፃጸምና የ2006 በጀት ጨምሮ በስምንት አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል ። በጉባዔው ማጠቃለያ ሰኔ 29 ነባሮቹን የምክር ቤት አባላት የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥነሥርዓት ከተከናወነ በሃላ አዲሱ ምክር ቤት ስልጣን እንዲረከብ ይደረጋል ።
አዲሱ ምክርቤትም  ከንቲባውንና ምክትል ከንቲባውን ይመርጣል። አዲሱ ከንቲባም ካቢኔያቸውን በመሰየም ስራቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በመምረጥ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአ/አ አስተዳደር ውስጥ ከፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ሹማምንት መካከል   የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽነር ወርቅነህ ገበየሁ ፣  የትራንስፖርት ሚኒስትር ድሪባ ኩማ  ፣ የከተማ ልማት ፣ኮንስትራክሽንና ቤቶች
ሚኒስትር አቶ መኩሪያ ኃይሌ   ፣ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ባለቤትና የፓርላማ አባል  ወ/ሮ አዜብ መስፍን  እንደሚገኙበትታውቋል፡፡
በሌላ ዜና ደግሞ ፓርላማው በዛሬ፣ በነገ እና አርብ ውሎው የ2006 በጀት ላይ ተወያይቶ ጠ/ሚ ሃ/ማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ያጸድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በተጨማሪም ወደ አዲስአበባ በምርጫ ስም እንዲዛወሩ በተደረጉት ሹማምንት ምትክ  እንዲሁም ለአዲሶቹ መ/ቤቶች ማለትም ለመረጃና ደህንነት መስሪያቤት ፣ ለፍትህ ሚኒስቴር እና ለአካባቢና ደን ሚኒስቴር አዳዲስ ሚኒስትሮችን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተጨማሪ የስልጣን ሽግሽግ ሊኖር እንደሚችልም ይጠበቃል።
በመተካካት ስም የኦህዴድ ፓርቲ ስልጣናቸውን ያጡት አቶ ኩማ ደመቅሳ በአቶ ሃ/ማርያም ካቢኔ ውስጥ የሚኒስትርነት ቦታ ያገኛሉ የሚሉ ግምቶች አሉ።
ፎርቹን ጋዜጣ በእሁድ  ዘገባው እንደገለጸው በአለቃ ጸጋየ በርሄ ተይዞ የነበረውን በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊነቱን ስልጣን አቶ በረከት ስምኦን ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል። አቶ በረከት ስልጣኑን ከተረከቡ ቦታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከህወሀት ውጭ ባለ ሰው ይያዛል። የደህንነት ሹሙ ስልጣናቸውን አስረክበው ከህወሀት ውች ባለ ሰው ከተተኩ፣ እነ አቶ በረከት ሀይላቸውን ቀስ በቀስ እያጠናከሩ ነው በሚል ለሚሰጠው አስተያየት ትክክለኛነት ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል በማለት አስተያየታቸውን የሚሰጡ ወገኖች እንዳሉ የአዲስ አበባው ዘጋቢ ከላከልን መረጃ ለመረዳት ይቻላል።

በግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ በህዝብ እና በወታደራዊ ግፊት ስልጣናቸውን ካጡ በሁዋላ አገሪቱ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ እየተነገረ ነው

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :- ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ፍትሀዊ እና ግልጽ በሆነ ምርጫ ተመርጠው ለአንድ አመት ያክል በስልጣን ላይ ከቆዩ በሁዋላ በህዝብ ተቃውሞና በወታደራዊ ግፊት ከስልጣን እንዲወርዱ ተደርጓል።
ፕሬዚዳንቱ በአንድ አመት የስልጣን ጊዜያቸው ፣ እርሳቸውን ለስልጣን ያበቃውን የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባላትን ከመጥቀም ባለፈ የፈየዱት ነገር የለም በሚል ተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲቀርብባቸው ቆይቷል። በአገሪቱ ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን ስራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት እና የጸጥታ ችግር ተከትሎ በርካታ የግብጽ አብዮታዊ ወጣቶች ” ለዚህ ነበር የታገልነው” በማለት ቅሬታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።
ፕሬዚዳንቱ አንደኛ አመት የስልጣን ጊዜያቸውን ለማክበር ሽር ጉድ በሚሉበት ጊዜ “ታማሮድ” ወይም አመጸኞች በማለት ራሳቸውን ሰየሙ የግብጽ ወጣቶች ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲነሱ የሚጠይቁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፊርማዎችን ከመላው አገሪቱ አሰባሰቡ። ከፊርማ ባለፈ ተቃውሞአቸውን በአደባባይ ማሰማት ጀመሩ። ሺዎች ወደ አደባባይ ጎረፉ። የህዝቡን ስሜት የተረዱ የሚመስሉት ወታደራዊው አዛዥ ጄኔራል አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ፕሬዚዳንቱ የተቃዋሚዎችን ድምጽ እንዲሰሙ ጠየቁ። ፕሬዚዳንቱ በመጀመሪያ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቱን እንዳልወደዱት ቢገልጹም፣ በሁዋላ ሁኔታው እየገፋ መሄዱ ስላሰጋቸው ጥምር መንግስት የማቋቋም ሀሳብ አቀረቡ። ተቃዋሚዎች ግን የሚቀበሉት ሆኖ አልተገኘም።
ጄኔራል ሲሲም ለውጥረቱ ማስተንፈሻ የሚሆን አዲስ አቅጣጫ መቀየሳቸውን አስታወቁ። በዚህ መሰረት የአገሪቱ ህገመንግስት ፈረሰ ፕሬዚዳንት ሙርሲም ከስልጣን ተነሱ።
የፕሬዚዳንት ሙርሲ ከስልጣን መነሳት የአለምን ህዝብ እያወዛገበ ነው። አንዳንድ ወገኖች በዲሞከራሲያዊ ምርጫ የተመረጠ መሪ ከስልጣን መውረድ የሚገባው በህዝብ ተቃውሞና በወታደራዊ መንገድ ሳይሆን በምርጫ ብቻ ነው በማለት ድርጊቱን ከመፈንቅለ መንግስት ጋር ሲያይዙት ፣ ሌሎች ወገኖች ደግሞ ወታደሩ ስልጣኑን ለፍትህ ሚኒሰትሩ አል ማንሱር በጊዜያዊነት በማስረከቡ መፈንቅለ መንግስት ነው ተብሎ ሊታይ አይገባውም በማለት ይሞግታሉ።
ምእረባዊያን አገራት እርምጃውን መፈንቅለ መንግስት በማለት አለመጥራታቸውን ተከትሎ በሙርሲ ከስልጣን መነሳት የተደሰቱ ይመስላሉ የሚሉ አስተያየቶች በብዛት እየቀረቡ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም 2ኛውን አብዮት “መፈንቅለ መንግስት” ብሎ ከመፈረጅ  ተቆጥቧል።
አብዛኞቹ የአረብ አገራት ድርጊቱን ሲደግፉት ፣ በውስጥ ችግሩ እየታመሰ የሚገነው የሶሪያ መንግስት አስተያየት ግን ያልተጠበቀ ሆኗል። ፕሬዚዳንት በሽር የግብጽን ወጣቶች አወድሰው፣ እስልምናን ለፖለቲካ ስልጣን መያዢያ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሀይሎች እንደማያስካላቸው ያመላከተ ነው በማለት እርምጃውን ደግፈዋል።
ብዙዎች ” ሙርሲን ከስልጣን ማውረድ ፣ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን ከስልጣን እንደማውረድ ቀላል ላይሆን ይችላል” ይላሉ። የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች እርምጃውን አንቀበልንም በማለት ትግላቸውን ከቀጠሉ በሶሪያ የሚታየው አይነት ደም መፋሰስ ሊከተል እንደሚችል እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ። እርምጃው የአብዛኛውን ህዝብ ድጋፍ ያገኘ በመሆኑ እና ምርጫ በፍጥነት ሊካሄድ የሚችልበት እድል ሰፊ በመሆኑ የተፈራው ችግር አይከሰትም በማለት የሚናገሩም አሉ።