Tuesday, 23 April 2013

ESAT Daily News - Amsterdam April 23 2013 Ethiopia


ከእሁድ እስከ እሁድ


(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)


sidamaበሲዳማ ህዝብ እያመጸ ነው
ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓ ም ኢህአዴግ ብቻውን ሊያካሂደው የነበረውን ምርጫ አንቀበልም በማለት ከተለያዩ ወረዳ በትስስር የተቃወሙ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት መታሰራቸውን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በአካባቢው ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከምርጫው ራሱን ማግለሉ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳገኘም አመልክተዋል።
በቀበሌ የመሰብሰቢያ አዳራሾች የታጎሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብሔረሰቡ አባላት እንዲፈቱ በሚጠይቁና በታጣቂ ሃይሎች መላከል የተካረረ ግጭት ይነሳል የሚል ፍርሃቻ እንደነበር ያመለከቱት ምንጮች የሲዳማ ተወላጆች የታጠቁ ስለሆነ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ አንጋቾችን ማሰማራቱን አመልክተዋል።
ለምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው እጩዎቼ፣ ታዛቢዎቼና አባላቶቼ በእስር፣ በድብደባና ከሥራ በመባረር እየተንገላቱ ነው በማለት ራሱን ከምርጫው ያገለለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፤ ከምርጫው በኋላም እስሩና እንግልቱ መቀጠሉን ማስታወቃቸውን፣ በአንድ ሳምንት 26 አባላቱ እስር እንደተፈረደባቸው፣ በሲዳማ ዞን በየወረዳው ጊዜያዊ ፍርድ ቤቶችና ሸንጎዎች እየተቋቋሙ የፓርቲው እጩዎች፣ ታዛቢዎችና አባላት ከ400 ብር በላይ የገንዘብ ቅጣትና ከ3ወር እስከ አንድ ዓመት ከስድስት ወር የሚደርስ እስራት እየተፈረደባቸውና ፍርደኞቹ ወህኒ መውረዳቸውን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የደርጅቱ ጉዳይ ሃላፊ ዶ/ር አየለ አሊቶ በመጥቀስ ኢሳት ዘግቧል። የኢህአዴግ አመራሮች ከሳሽም ፈራጅም በሆኑበት ሁኔታ ዜጎቻችን እየተንገላቱ ነው፤ ከምርጫው ብንወጣም ትግላችን ይቀጥላል ማለታቸውን የኢሳት ዘገባ ያስረዳል። (ፎቶ: worancha blogpost)
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታስረው ተፈቱ
semayawiበቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ለማጣራት ወደ መተከል ዞን አቅንተው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳና የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በቃሉ አዳነ በቡለን ወረዳ ታስረው ተፈቱ። ኢሳት ሚያዚያ 12 ቀን 2005 ዓም እንደዘገበው አመራሮቹ የታሰሩት ከፌደራል፣ ከክልል መንግስትና ከዞን ባለስልጣናት ወደ ወረዳው ገብተው ሰዎችን ለማነጋገር የሚያስችል የፈቃድ ወረቀት ይዛችሁ አልመጣችሁም በሚል ነው። “ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ያለፈቃድ ሄዶ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ለመነጋገር አይቻልም፣ በዚያ ላይ እናንተ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ናችሁ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ኢ/ር ይልቃል፣ እንዲህ አይነት ስራ ለመስራት በቅድሚያ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ፣ ይህን አለማድረግ ደግሞ የብሄረሰቦችን የራስን በራስ የማስተዳደር መብት መናቅ ተደርጎ እንደሚታይ እንደተነገራቸው ኢ/ር ይልቃል ከእስር ተለቀው እየተመለሱ እያሉ ለኢሳት መናገራቸውን ዘገባው ያስረዳል።
በስፍራው ተገኝተው አንዳንድ ሰዎችን በማናገር ያዘጋጁት ቪዲዮ በወረዳው ባለስልጣናት ትዕዛዝ እንዲደመሰስ መደረጉን ኢንጂነሩ ተናግረው፣ ይሁን እንጅ በአይናቸው ያዩት፣ በጆሮዋቸው የሰሙት በቂ መረጃ እንደሰጣቸው ኢሳት በዘገባው አመልክቷል።
ታሪካዊ የሪፖርተር አንደበት
“ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የመክፈቻ ንግግራቸውን አድርገው ሲያበቁ፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የተዘጋጀ የሟቹ ጠቅላይ azebሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሕይወት ዘመን ትውስታ ከሕፃንነት እስከ ግባተ መሬት ድረስ የነበረውን ዘጋቢ ፊልም ሲታይ በታዳሚዎች ላይ የተደበላለቀ ስሜት ሲፈጠር ተስተውሏል፡፡ በተለይ በዘጋቢ ፊልሙ የአቶ መለስ አስከሬን ከቤልጂየም ብራሰልስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስና ቤተሰቦቻቸው ከአውሮፕላኑ ሲወርዱ፣ አስከሬኑ ከቦሌ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ቤተ መንግሥት ሲጓዝ፣ የቀብራቸው ዕለት በመስቀል አደባባይ አስከሬናቸውን የያዘው ሳጥን ሲቀመጥና ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ አስከሬኑ በሰረገላ ሆኖ ወደ ቅድሥት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሲያመራ የሚያሳየውን ፊልም የተመለከቱ በአፍሪካ ኅብረት የታደሙ ሰዎች፣ ከንፈራቸውን ከመምጠጥ እስከ እንባ ማፍሰስ ድረስ በሐዘን ስሜት ውስጥ ገብተው ተስተውሏል፡፡ ሌላው አዳራሹን ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሐዘን ድባብ ውስጥ የከተተ ክስተትም ተፈጥሮ ነበር፡፡ ዘጋቢ ፊልሙን ከሚመለከቱ ታዳሚዎች መካከል የነበሩት የአቶ መለስ እህቶች ድምፅ አውጥተው ለቅሶ በመጀመራቸው፣ ከሰባት ወራት በፊት የነበረውን የሐዘን ሁኔታ ያስታወሰና የሁሉንም ታዳሚዎች ቀልብ የሳበ ሆኖ ነበር፡፡”
ምንጭ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ታምሩ ጽጌ “ከለቅሶ ቤት” እንደዘገበው (10 April 2013)
አርበኞች ግንባር ማርኬ ገደልኩ አለ
የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ስፍራ  በሁለት ተከታታይ ቀናት ከአገዛዙ  የፈጥኖ ደራሽ ሃይል ጋር ባካሄደው  የፊት ለፊት ውጊያ ወታደራዊ የበላይነትን ስለመቀዳጀቱ ለጎልጉል በላከው መግለጫ አስታወቀ።
eppfግንባሩ ሚያዚያ 8 ቀን 2005 ዓ ም በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ሃያ አንድ የአገዛዙ ወታደሮችን ግዳይ ማድረጉን፣ ሃያ አምስት ማቁሰሉን፣ በቀጣይ ቀን በዋልድባ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ በተከፈተ ውጊያ  ሃያ አምስት የአገዛዙ ወታደሮችን መግደሉንና ሰላሳ ዘጠኝ በማቁሰል ከፍተኛ ድል እንዳገኘ በመግለጫው አመልክቷል።
ግንባሩ ካደረሰው ሰብአዊ ጥቃት በተጨማሪ  የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አገኘሁ ስላለው ድልና ተቀዳጀሁት በሚል በይፋ የገለጸውን ዜና አስመልክቶ ከመንግስት በኩል እስካሁን በይፋ የተሰጠ መልስ የለም። ግንባሩም ቢሆን ሪፖርቱን በምስል አላስደገፈም።
የአውሮፓ ህብረት አቋም አልጠራም
የሰብአዊ መብት ማስከበር የህልውናችን ጉዳይ ነው
ከሰብአዊ መብት፣ ከፕሬስ ነጻነት፣ ዜጎች አመለካከታቸውን በነጻ የማራመድና የተፈጥሮ መብታቸው መገፈፉንና አጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ የሰፈነው አምባገነንነት አስጊ ደረጃ መድረሱን አስመልክቶ የአውሮፓ ህብረት የጠራ አቋም አለመያዙ ታውቋል። አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ በአውሮፓ የቀድሞውን ወዳጅነት አጥብቀው እንደሚቀጥሉበት ለማረጋገጥ አውሮፓን  የዞሩትን  የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ  ጉብኝትን አስመልክቶ የጀርመን ሬዲዮ እንደዘገበው የአውሮፓ ህብረት ኢህአዴግን ከማድነቅ አልፎ የ30 ሚሊዮን ዶላር ርዳታeu መስጠቱን አመልክቷል። በሶማሊያ ስለተፈጠረው መረጋጋት፣ በደቡብ ሱዳን ጉዳይና በምስራቅ አፍሪቃ አጠቃላይ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን ያወሳው ሬዲዮው፣ የህብረቱ ሊቀመንበር ማሳሰቢያ ቢጤ ማስተላለፋቸውን አመልክቷል።
በኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ያደነቁት የህብረቱ ሊቀመንበር፣ “ይህ ዕድገት ቀጣይነቱ ሊረጋገጥ የሚችለው ፣ የአገሪቱ ሕዝብ መሠረታዊ መብቶች፣ የመናገርና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነቶች ሲከበሩ ብቻ ነው” ብለዋል። በጋራ በተዘጋጀው መግለጫ አቶ ሃይለማርያም “የሰብአዊ መብቶች መከበር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው”  አያይዘውም “የመሬት ወረራ ብሎ ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም፤ አንድም ጋዜጠኛ ሃሳቡን በመግለጹ አልታሰረም “ሲሉ የተለመደውን የመለስን ዓይነት መልስ በመመለስ ሸምጥጠዋል።

“ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”


“በቤኒሻንጉል የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ እርሻ አላቸው”


በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ2000 ሺህ በላይ ትግሬዎች ባለይዞታ መሆናቸውንና ማንም ሳይነካቸው በሰላም እንደሚኖሩ፣ በቶጎ ወረዳ ከስልሳ በላይ ነባር የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ የእርሻ መሬት ወስደው በባለሃብት ደረጃ እንደሚገኙ የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አስታወቁ። ከሌሎች ብሔረሰቦች ተለይቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ያለውን የአማራ ብሔረሰብ በድጋሚ ለማስወጣት መታቀዱንም በመረጃ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።
በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን መረጃ እንደሰበሰቡ ለአሜሪካ ሬዲዮ የገለጹት የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ በክልሉ ከሚኖሩት የተለያዩ ብሔረሰቦች ተለይቶ የአማራ ብሔረሰብ እንዲፈናቀልና እንዲሰቃይ የሚደረገው በማዕከላዊ መንግስት ትዕዛዝ እንደሆነም አመልክተዋል።
Justice Gavelመኢአድ ያሰራጨውን መግለጫ ተከትሎ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ ድርጊቱ በበታች የቀበሌና ወረዳ አመራር አካላት ተፈጽሟል መባሉን ተቃውመዋል።”ሰዎቹ እንዲወጡ ሲታዘዝ ያ ሁሉ ወታደር ከየት መጣ?” በማለት የጠየቁት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ በርካታ የወያኔ ሰዎች በቦታው እያሉ አማራው ተለይቶ እንዲፈናቀል የበታች ባለስልጣናት በራሳቸው ውሳኔ ይህን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ተናግረዋል። በማያያዝም በርካታ ተጨባጭ ማስረጃ ስለተሰባሰበ ጉዳዩን ወደ ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል።
ባላቸው የተለያየ መስመር ፍርድ ቤቱ የሚቀበላቸውን ማስረጃዎች በማጣራት አስፈላጊ መረጃዎችን እንዳሰባሰቡ የገለጹት ኢንጂነር ሃይሉ ሻወል፣ “የሰውና የቪዲዮ መረጃ አለን። የመንግስት ወታደሮች ህዝብ ሲደበድቡ፣ መኪና ተገልብጦ ሰዎች ሜዳ ላይ ሲሰቃዩ፣ በግድ ሲፈናቀሉ … የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ አሰባስበናል። ወደ ክስ እናመራለን” በማለት መናገራቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ (ቪኦኤ) አመልክቷል።
የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ አባል በበኩላቸው የመንግስት ባለስልጣኖችና ካድሬዎች በኩምሩክ ሕዝብ በመሰብሰብ ማነጋገራቸውን ይጠቅሳሉ። እሳቸው እንዳሉት ህዝቡ “ለምን በዘራችን ሳቢያ ይህ ሁሉ ስቃይ ይደርስንባል?” በማለት ጠይቆ ነበር። የሰበሰቧቸው ባለስልጣናት “ክልሉ የናንተ አይደለም ውጡ” ሲሉ  እንደመለሱላቸው የጠቀሱት የስራ አስፈጻሚ አባል፣ በሌላ በኩል የተፈጸመው ህገ ወጥ የዘር ማጥፋት ተግባር የመንግስት እጅ ያለበት እንዳይመስል ለክልሉ ነዋሪዎች “አማራን አታስጠጉ፣ ከአማራ ጋር አትብሉ፣ ከአማራ ጋር አትጠጡ፣ ቤት አታከራዩ፣ ይህን ማድረግ ወንጀል ነው” በማለት መንገራቸውንና በዚሁ መነሻ ህዝቡ በክልሉ ያሉ አማሮች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጥያቄ እንዲያቀርቡ መመሪያ መሰጠቱን አመልክተዋል። ይህ የሚሆነውም ጥያቄው ከህዝብ የመጣ እንደሆነ ለማሳየት እንደሆነም አስታውቀዋል።
ahmed
የቤኒሻንጉል ፕሬዚዳንት አህመድ ናስር
በዘር፣ በሐይማኖትና በአመለካከት አንድን ማህበረሰብ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት መሞከር፣ ማሸማቀቅ፣ ሴቶችን መድፈር በዘር ማጥፋት እንደሚያስጠይቅ ያመለከቱት የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ አባል፣ “ይህ ሁሉ ተፈጽሟል” በማለት ድርጅታቸው በዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ከድምዳሜ መድረሱን ገልጸዋል።
የቤኒሻንጉል ክልል ፕሬዚዳንት ለሪፖርተር በሰጡት መግለጫ ስህተት መሰራቱን ማመናቸውና ድርጊቱን የፈጸሙት ኪራይ ሰብሳቢ የወረዳና የበታች አመራሮች እንደሆኑ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። በተመሳሳይ ለስራ ፈረንሳይ አገር በነበሩበት ወቅት ለጀርመን ሬዲዮ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ፕሬዚዳንቱ ተፈጸመ ስላሉት ስህተት “የማውቀው ነገር የለም። አልሰማሁም። እኔ የማውቀው ደን ጨፍጭፈው በሃይል መሬት የያዙ መፈናቀላቸውን ነው” ብለዋል። ዶ/ር ያዕቆብ ሃይለማርያም ቀደም ባሉት ሳምንታት ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉትን ዜጎች አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ወንጀሉ የዘር ማጥፋት ስለሆነ ክስ መመስረት እንደሚቻል አመልክተው ነበር።
መኢአድ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ አረካ ቀደም ሲል የተፈጸሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አያይዞ ለክስ እንደሚጠቀምበት አመልክቷል። በጥያቄና መልሱ ወቅት ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል “የተፈናቀሉት ተመልሰዋል። ለምን አትተውትም” በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ጋዜጠኞች እንደነበሩ የቪኦኤው የአዲስ አበባ ዘጋቢ ጠቆም አድርጎ አልፏል።

Wednesday, 17 April 2013

በሰሞኑ ምርጫ ከፍተኛ ዘለፋዎችን ያስተናገዱት ወ/ሮ አዜብና ባለራእዩ ባለቤታቸው ናቸው


በሰሞኑ ምርጫ ከፍተኛ ዘለፋዎችን ያስተናገዱት ወ/ሮ አዜብና ባለራእዩ ባለቤታቸው ናቸው

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም በጨርቆስ ክፍለከተማ በተካሄደው ምርጫ ከፍተኛውን ዘለፋና ትችት ያስተናገዱት ወ/ሮ አዜብ መስፍን እና ባለራእዩ ባለቤታቸው እንደነበሩ በቆጠራው የተሳተፉ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
ኢሳት በ8 የአዲስ አበባ የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ የተሳተፉ ታዛቢዎችን በመጠየቅ ባሰባሰበው መረጃ ከ30 በመቶ ያላነሰ መራጭ ድምጹን የሰጠ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ባዶ ወረቀት ሲያስገቡ፣ አብዛኞቹ ደግሞ ከዘለፋ ጀምሮ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ጽፈው አስገብተዋል። እንደ ታዛቢዎች መረጃ አብዛኞቹ ስድቦች በወ/ሮ አዜብ መስፍንና በባለቤታቸው ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን፣ ስድቦቹም በአብዛኛው ወ/ሮ አዜብን በሙስና የሚከሱ ናቸው።
የአዲስ አበባ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ እንደቀበራቸው እና ከፍተኛ የህዝብ ፍቅር እንዳላቸው በመንግስት መገናኛ ብዙሀን የተነገርላቸው አቶ መለስ ዜናዊም ትችቱ አልቀረላቸውም። በእሳቸው ላይ የተሰነዘረው ዘለፋና ትችት ባለራእይነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
መራጮች በጻፉዋቸው መልክቶች የተደናገጡት የምርጫ ቦርድ እና የቀበሌ ባለስልጣናት በ ወረቀቶቹ ላይ ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ ተጋብተዋል።
በ ምርጫው መላው ኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ቃል ኢህአዴግን እንደማይደገፍ ግልጽ ማድረጉን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።
ኢሳት ከወራት በፊት ለምርጫው የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር ከተጠበቀው በታች መሆኑን መዘገቡ ይታወሳል።

የህወሓት መንግስት የአመስት መቶ ብር ኖት ላይ የመለስ ዜናዊ ምስል ሊያትም ነው


የህወሓት መንግስት የአመስት መቶ ብር ኖት ላይ የመለስ ዜናዊ ምስል ሊያትም ነው

አንዳንዴ ወሬ በባዶ ሜዳ ይናፈሳል። ብዙ ጊዜ ትንሽ ጫፍ ይዞ ይናፈሳል። የህወሓት መንግስትን በተመለከተ አያደርጉም የምለው ነገር ስለሌለ ለመጠራጠሬ ገደብ አብጂቸ ነው የምጠራጠረው። ብዙ ጊዜ ግን ስለነሱ የሚወራውን አልጠራጠርም። ያደርጉታል።
ሰሞኑንን (ምናልባት ሌሎቻችሁ ከሰማችሁ ቆይታችሁ ይሆናል!) የህወሓት መንግስት የአመስት መቶ ብር ኖት የማዘጋጀት ሃሳብ እንዳለው እና በገንዘቡ ላይ የ “ባለ ራዕዮ መሪ” ምስል እንደሚያርፍበት ሰማሁ። የታላላቅ መሪዎችን ምስል በምንዛሬ ላይ ማስቀመጥ አዲስ ነገር አይደለም። ጥያቄው ግን ታላቅ ማነው? ታላቅነቱ እንዴት ነው? በየትኛውም ማህበረሰብ የበቀሉ የፖለቲካ መሪዎች የራሳቸው የሆኑ ተቃዋሚዎች እንደሚኖራቸው እሙን ነው። ነገር ግን ከሚከተሉት ፖሊሲ በመነሳት ዜግነታቸው ጭምር ጥያቄ ውስጥ የገባ እና በእኛ ሃገር ዘይቤ በባንዳነት ሂሳብ የተያዙ የሌሎች ሃገር መሪዎች ያሉ አይመስለኝም። ያውም ምስላቸው ምንዛሬ ላይ የሚወጣ?! ፈጽሞ አይመስለኝም። የቻይናው ማኦ የጠባብ ብሔርተኛ የፖለቲካ መሪ አልነበረም። የዘር ትምክህት አባዜ አልነበረውም። የኢንዶኔዢያው ሱካርኖ እንደዚያው። የፓኪስታኑ መሃመድ አሊ ጂና እንደዚያው። ብዙ የ”ሶስተኛውን ዓለም” ሃገሮች መሪዎች ለአብነት ማንሳት ይቻላል።
የመለስ ዜናዊ ታሪክ ሌላ ነው( ለማን ይተረካል እንጂ!)። የመራውን የፖለቲካ ቡድን ለይስሙላም ቢሆን ሃገራዊ መልክ ሳይሰጠው የህወሓት ሊቀመንበር እንደሆነ ነው የሞተው። ከዚያ በላይ ግን የመለስ ዜናዊን የጎሰኛነት ጠባይ ትግራይም አዲሳባም ላይ ሆኖ የተናገራቸው የተለያዮ ንግግሮች የሚመሰክሩት አንድ ነገር ነው፡- የመለስ ዜናዊን ከልክ ያለፈ ጎጠኛነት። ምንም ጥያቄ የለውም ህወሃት ውስጥ አብረውት ብዙ ዓመት የፖለቲካ ስራ ለሰሩ፣ታገልን ለሚሉ ጓደኞቹ መለስ ዜናዊ ሌላ ሰው ነበር-ምንም እንኳን አንዳንዶች ጉደኞቹ ከጊዜ በኋላ ቢቀየሙትም (ወይንም የተቀየሙት ቢመስሉም)። እነዚህ የሚወዱት ጓደኞቹ ከፈለጉ የወርቅ ሃውልትም ሊያቆሙለት ይችላሉ ( ለባለ “ራዕዮ” መሪያቸው ያልሆነ ግዳይ ምን ይፈይዳል ታዲያ!)
ነገር ግን ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ እንደው በህወሃትኛ ቋንቋ እንኳን መለስ ዜናዊ ለጉራጌው ምኑ ነው?? በአማራው ምኑ ነው? ለኦሮሞው ምኑ ነው? ለወላይታው ምኑ ነው? እያለ እያለ ይቀጥል እና አጥብቆ ጠያቂ ከመጣ ደሞ “እንኳን ለሌላው ለተምቤኑ ምኑ ነው?” ጥያቂ ሊነሳም ይችላል።
መለስ ዜናዊ ትልቁን ከሃዲ እና ጎጠኛ ነበር የሚለውን ነጥብ ትተን በትንሹ አወዛጋቢ የሚባል የፖለቲካ ሰው ነበር። ህወሓት ይሄን አላውቅም ካለ ፓለቲካ አያውቅም ሊያስብለው ይችላል። እውነቱ ይሄ ሆኖ እያለ ህወሓት የመንግስት ስልጣን ስለያዘ ብቻ እንደፈለኩ ገንዘብ ላይ የመለስ ዜናዊ ምስል አትማለሁ ቢል የህወሓትን የአክራሪነት ስሜት ከሚጠቁም በስተቀር ትርፍ ያለው ነገር አይመስለኝም። ከህወሓት ጋር አብሮ የሚሞት የገንዘብ ኖት ነው የሚያዘጋጀው ማለት ነው። ምናለበት ህወሓት ለጎጠኝነቱ ለከት ቢያበጂለት?! ህወሓት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ምንድን ነው የሚፈልገው?? ሌልቹስ “እህት” ነን የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ይሄን ጉዳይ በቸልታ ይመለከታሉ?!
የመለስ ዜናዊ ምስል በምንዛሬ ላይ የመውጣቱ ነገር በትክክል ሊደረግ ታስቦ ከሆነ ክህወሓት በላይ ተጠያቂ የሚሆኑት ክህወሓት ጋር እየሰሩ ያሉ ድርጂቶች ናቸው!
source: Borkena.com

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በኑሮ ውድነቱ መማረሩን ቀጥሎአል


አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በኑሮ ውድነቱ መማረሩን ቀጥሎአል

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኑሮ ውድነቱ ቅናሽ ያሳይ ይሆን በማለት ኢትዮጵያውያን ከአመት አመት ተስፋ ቢያደርጉም ተስፋቸው ግን ከተስፋነት እንዳልዘለለ በተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአምስት ክልሎች የሚኖሩ ዘጋቢዎቻችን አጠናቅረው የላኩት ዘገባ እንደሚያመለክተው በሁሉም ክልሎች የኑሮ ውድነቱ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በመላ እየጠበሰ ነው።
በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል  የኑሮ ውድነቱ ተባብሶ በመቀጠሉ ህዝቡ ኑሮውን በአግባቡ መምራት እየተሳነው ነው። በድሬዳዋ፣ ሀርር እና ሌሎችም አካባቢዎች አንድ ኩንታል ጤፍ እሰከ 2 ሺ ብር በመሸጥ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
በኦሮሚያ ክልልም እንዲሁ የኑሮ ውደነቱ መባባሱ ህዝቡን ተስፋ እያስቆረጠ መምጣቱን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ሰዎች ይገልጻሉ።
በደቡብ ክልል በሚገኙ አብዛኛቹ ክልሎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች እና በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የኑሮ ውድነቱ በሞት እና በህይወት መካከል የጣላቸው መሆኑን ለኢሳት የደቡብ ክልል ዘጋቢ ገልጸዋል። ስኳር እና ዘይት ከገበያ መጥፋታቸውን ፣ በተለይም የእንዱስትሪ ምርቶች ዋጋቸው እየናረ መምጣቱን ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ። ከማዳበሪያ ጋር በተያያዘም አርሶ አደሩ በእዳ እየተሰቃየ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በአማራ ክልልም እንዲሁ አብዛኞቹ የመንግስት ሰራተኞች የሚያገኙት ወርሀዊ ገቢ ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር እንዳላስቻለቸው ገልጸዋል።
የማእከላዊ ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት ባወጣው የመጋቢት ወር ሪፖርት የ2005 ዓም የ12 ወራት ተንከባላይ አማካኝ አገራዊ የዋጋ ግሽበት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር በ18 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በመጋቢት ወር 2005 ዓም አገራዊ የ12 ወራት ተንከባላይ አማካኝ የምግብ ዋጋ ግሽበት በ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። የ12 ወራት ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች የዋጋ ግሽበትም በ17 በመቶ ጨምሯል።
በመጋቢት ወር የታየው አጣቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው የካቲት ወር 2005 ዓም ጋር ሲነጻጸር ከአንድ በመቶ ያላነሰ ጭማሪ አሳይቷል።
መንግስት በየጊዜው የሚንረውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር እንደተሳነው አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ። መንግስት የኑሮ ውድነቱ በከፊል የሚጨምረው  የህዝቡ ኑሮ እየተሻሻለ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የህዝቡ ፍጆታ በመጨመሩ ነው ይላል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን በማነጋገር ተጨማሪ ዘገባ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

! ….. ህወሓት ማስጠንቀቅያ ተሰጠው …….!


! ….. ህወሓት ማስጠንቀቅያ ተሰጠው …….!

መንግሥትና ዘመናዊ የሌብነት ስልቶቻቸው
ባለፈው እሁድ በተካሄደው ያከባቢና ከተሞች ‘ምርጫ’ (ይቅርታ አማራጭ የሌለው ምርጫ ምርጫ ኣይባልም ግን ሌላ ስም ለግዜው አላገኘሁም) የትግራይ ህዝብ ባልጠበኩት ሁኔታ (ህወሓት የትግራይ ህዝብ ድጋፍ እንደሌለው ባውቅም) ለህወሓቶች ኣስደንጋጭ ማስጠንቀቅያ መስጠቱ መረጃ ደሶኛል። በብዙ አከባቢዎች ህዝቡ ለመምረጥ ፍቃደኛ ኣልነበረም። አንዳንድ ካድሬዎች ህዝብን እያስገደዱ ወደ ምርጫ ጣብያ እንዲሄድ ቢያድርጉም ዉጤቱ እንደጠብቁት ኣልነበረም።
በትግራይ ተወዳዳሪ ተቃዋሚ ፓርቲ ኣልነበረም (በኣላማጣ ኣንድ ነበር ኣሉ)። በምርጫው ዋዜማ ሁሉም የመንግስት አካላት ህዝብ በምርጫው እንዲሳተፍ ቅስቀሳ ያደርጉ ነበር (‘ይሄው በህዝብ ተመርጠናል’ ለማለት ያህል)። ነገር ግን በኣክሱም፣ ሸረ፣ ሸራሮ፣ ዓዲግራት፣ ዉቅሮ፣ ሓውዜን፣ አላማጣ፣ ዓብዪዓዲ፣ መቐለ ብዙ ችግሮች ነበሩ። ለምሳሌ ያህል በመቐለ ከተማ ባንዳንድ ምርጫ ጣብያዎች ያጋጠመ ነገር ላካፍላቹ።
መቐለ 05 ቀበሌ በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣቢያ 1140 መራጮች ተመዝግበው ነበር። ከነዚህ ተመዝጋቢዎች በምርጫው የተሳተፉ 619 ብቻ ነበሩ። ከተሳተፉት 370 ደግሞ የምርጫ ምልክት ሳያስቀምጡ በስድብ የታጀቡ ኣስተያየቶች ብቻ የፃፉ ናቸው (ምርጫ ጣብያ ተገደው ቢሄዱም ኣልመረጡም)።
ማይ ሊሓም በሚገኝ አንድ ምርጫ ጣብያ ደግሞ 1201 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን 910 መርጠዋል (ከነዚህ መራጮች ግን 521 የስድብ ኣስተያየት የሰጡ ናቸው)።
አቶ ኣባይ ወልዱ (የህወሓት ሊቀመንበር) የተሳተፉበት በዓዲ ሹምድሑን አከባቢ በሚገኝ አንድ የምርጫ ጣቢያ 1446 የተመዘገቡ መራጮች የነበሩ ሲሆን 945 ሰዎች በምርጫው ተሳትፈዋል። ከነዚህ ተሳታፊዎች 415 ስድብ ብቻ ፅፈው ያስገቡ ሲሆን 202 ደግሞ ነፃ ወረቀት ብቻውን (ምንም ምልክት ወይ ፅሑፍ ሳያስቀምቱ) ወደ ኮረጆው ከተው ተመልሰዋል። 330 ብቻ ድምፃቸው በኣግባቡ ሰጥተዋል።
ባጠቃላይ በመቐሌ (እንዲሁም በትግራይ ክልል ማለት ይቻላል) ተመሳሳይ ነው። በተለይ በመቐለ (በዓይደር፣ 06፣ ዓዲሓ፣ ሓዲ ሓቂ) ጭራሽ ሰው አልመረጠም ማለት ይቻላል። የሚገርመው ነገር የህወሓት አባላት ራሳቸው አለመምረጣቸው ነው። ብዙዎቹ የህወሓት አባላት (ከቀበሌ ሰራተኞች በቀር) በምርጫው ለመሳተፍ ዝግጁ አልነበሩም። ሙሁራንና ነጋዴዎች ወደ ምርጫ ጣብያ ላለመሄድ ተደብቀው የዋሉ ሲሆን አንዳንድ ካድሬዎች የምርጫ ካርዳቸው እየሰበሰቡ ራሳቸው ይመርጡላቸው እንደነበር ተሰምተዋል። በትክክል የመረጡ ጥቂት ሴቶች (የህወሓት አባላት) ብቻ ናቸው።
በምርጫው ቀን ብዙ ህዝብ ባለመሳተፉ የተናደዱ አንዳንድ ባለስልጣናት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ (እስከ አስር ተኩል) ቤትለቤት እየዞሩ ሰዎች ለምርጫ እንዲወጡ ያስገድዱ ነበር። በኋላ ግን በምርጫ ወረቀቱ (ድምፁ ሲቆጠር) የተፃፉ ስድቦችና አስተያየቶች ካድሬዎቹን እጅግ አስደንግጧል። በኣንድ ምርጫ ጣብያ ኣስመራጮቹ (ታዛቢዎችና ፖሊሶች) ደንግጠው ለኣለቆቻቸው ደውለው ሁኔታው ኣስረድተዋል። እንደዉጤቱም ሦስት ከፍተኛ ባለስልጣናት (የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት) ከምሽቱ አራት ሰዓት በምርጫ ጣብያው የተገኙ ሲሆን በሁኔታው ደንግጠው በሁሉም የምርጫ ጣብያዎች ያለ የድምፅ ቆጠራ ሂደት እንዲቆም አዘዋል። ግን ኣልተሳካም፤ ምክንያቱም ኣብዛኞቹ ቆጥረው ጨርሰው ነበር።
ባለስልጣናቱ ካስደነገጡ የህዝብ ኣስተያየቶች መካከል “ ህወሓት ሌላ፣ ምርጫ አታጭበርብሩ፣ ፍትሕ አጣን፣ ከሌሎች ህዝቦች አታጣሉን፣ በሃይማኖት ጣልቃ ኣትግቡ፣ ድምፃችን ዓፍናቹ ድምፅ እንድንሰጣቹ ትፈልጋላቹ?፣ ሙስና ይቁም፣ በእኩል ዓይን እዩን …” ወዘተ።
ከዚህ በተያያዘ የዉቅሮ ህዝብ ከሌላ አከባቢ ተሽሞ የመጣው የወረዳው ኣስተዳድሪ እንዲቀየር ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰማ ይገኛል። የወረዳው ህዝብ የዉቅሮ ተወላጅ ኣስተዳዳሪ ይፈልጋል። ህወሓቶች ግን (በኣብዛኞቹ ሌሎች የትግራይ ወረዳዎች እንደሚያደርጉት ሁሉ) የህዝቡን የተቃውሞ ድምፅ ማዳመጥ ኣልፈለጉም። በኣፅቢ ወንበርታ ወረዳም ተመሳሳይ ችግር ኣለ።
በርግጠኝነት መናገር የምችለው ተቃዋሚዎች በምርጫ ቢሳተፉ ኑሮ በትግራይና አዲስ አበባ ያለ ጥርጥር ያሸንፉ ነበር። ግን ያሸነፉበት ድምፅ በገዢው ፓርቲ ይሰረቅ ነበር።
አዎ! ‘ድምፃችን ዓፍናቹ ድምፅ እንድንሰጣቹ አትጠብቁ’።