Saturday, 21 December 2013

Amnesty International: Will you help free her husband?

Eskinder Nega has been sentenced to 18 years in prison for telling the truth. Will you help us to secure his release and return him to his family?
By making a donation today you will support our campaign to get Eskinder home to his family and his vital work as a journalist. Click here
In this video, Eskinder’ wife Serkalem, talks about the pain both her and their son are going through being separated from Eskinder.
When the Ethiopian government used anti-terror laws to silence its critics, Eskinder spoke out in protest. As a result he was arrested for the eighth time and sentenced to 18 years in prison.
Despite the lies and the pain of separation from his wife and son, Eskinder’s hope for the future of Ethiopia and its people is as strong as ever. In a letter smuggled out of prison he said:
‘Freedom is partial to no race. Freedom has no religion. Freedom favours no ethnicity. Freedom discriminates not between rich and poor countries. Inevitably, freedom will overwhelm Ethiopia.’
What we are doing
To help free Eskinder we are mobilising our worldwide network to take action in support of his release. Over 20,000 people in the UK have already joined the campaign by writing letters, sending cards or signing the global petition.Eskinder' wife Serkalem, talks about the pain both her and their son
We are also lobbying Prime Minister Hailemarian Desalegn directly, and focusing media attention on Eskinder’s case and the worsening crackdown on free speech and freedom of expression in Ethiopia.
This is the same kind of campaigning that in 2010 helped secure the release of Eskinder’s friend, Birtukan Mideksa
She was serving a life sentence when the Ethiopian government set her free thanks to pressure from Amnesty International.
We know we can get Eskinder home. Help us do it!

ከ35 ሚ.ብር በላይ በሙስና አከማችቷል የተባለ የጉምሩክ ኃላፊ ተከሰሰ

የአዳማ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የህግ ማስከበር ሃላፊ የነበረው አቶ ተመስገን ጉላን በራሱና በወንድሙ ስም ከገቢው ጋር የማይመጣጠን ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና ንብረት ይዞ በመገኘቱ ክስ የቀረበበት ሲሆን በፖሊስ ክትትል ስር የነበረው ወንድሙም ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት ቀርቦ ክሱ ተነቦለታል፡፡ ቀደም ሲል ተከሳሹ ሁለት ዶዘሮችን በ15ሚ.ብር መግዛቱን ደርሼበታለሁሲል አቃቤህግ መግለጫ መስጠቱ ይታወሣል፡፡ 
የ33 ዓመቱ የህግ ማስከበር ሃላፊ አቶ ተመስጌን ጉላን ዓለሙ፣ በሌላ ስሙ ተመስገን ስዩም አሰፋ፤ ሁለት ክሶች የቀረቡበት ሲሆን በግብረአበርነት በተያዙት የወልደሚካኤል ሃለፎም አጠቃላይ አስመጪና የፈሣሽ ትራንስፖርት ድርጅት ባለቤት አቶ ወ/ሚካአል ሃለፎም፣ የታደለ ብርሃኑ አስመጪና ላኪ ድርጅት ባለቤት አቶ ታደለ ብርሃኑ፣ ስራው ያልተገለፀውና እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋለው አቶ ብርሃኑ ዝናቡ ሹመይ እንዲሁም የ24 አመቱ የ1ኛ ተከሣሽ ወንድም አቶ ካህሣይ ጉላን ዓለሙ ደግሞ በአንድ መዝገብ ተከሰዋል፡፡ 
በአቶ ተመስጌን ጉላን ላይ በተናጠል የቀረበው 1ኛው ክስ፤ ተከሣሹ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በተለያየ ሃላፊነት ላይ ተመድቦ ከ1999 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ለስድስት ዓመታት ሲሠራ፣ አስቀድሞ በነበረበት የመንግስት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ሲያገኘው ከነበረው ህጋዊ ገቢ ጋር የማይመጣጠን፣ በወንድሙ በካህሣይ ጉላን ስም በዳሽን ባንክ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ፤ በራሱ ስም ደግሞ በወጋገን ባንክ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በማስቀመጥ እና በማንቀሳቀሱ በአጠቃላይ በራሱና በወንድሙ ስም ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ አስቀምጦ በመገኘቱ ተከሷል፡፡ 
ተከሣሹ በጓደኛው ብርሃኑ ዝናቡ ስም ስድስት ቦቴ መኪናዎችን ከነተሳቢያቸው፣ በአቶ ወ/ሚካኤል እና ታደለ ብርሃኑ አማካኝነት ከባንክ 10.5 ሚሊዮን ብር በመበደር ከራሱ 10.5 ሚሊየን ብር በመጨመር በድምሩ በ21 ሚሊዮን ብር ከሰኢድ ያሲን ኃላ.የተ.የግል ማህበር ገዝቶ መኪኖቹን በ2005 ዓ.ም ለተለያዩ ግለሰቦች በመሸጥ፣ በወንድሙ ስም ከቢዩ ኃ/የተ/የግ/ማህ ሁለት ዶዘሮችን በብር 15 ማሊዮን ብር መግዛቱ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በወንድሙ ስም በቦሌ ክ/ከተማ 325 ሜ.ካ ቦታ ላይ የተሠራ መኖሪያ ቤት በማፍራቱ እና በ2.8 ሚሊየን ብር በመሸጡም ተከሷል፡፡ 
ቀሪዎቹ ተከሣሾች ደግሞ፣ አቶ ተመስገን ሙስና ፈፅሞ ያገኘው ገንዘብ እና ንብረት መሆኑን እያወቁ መኪኖቹ የሚገዙበትን ሁኔታ ሃሣብ በማፍለቅና በመርዳት፣ የባንክ ብድር እንዲገኝ በማመቻቸት እና በመበደር እንዲሁም በራሱ አስመጪና የትራንስፖርት ድርጅት ስር መኪኖቹ ተጠቃለው እንዲሠሩ በማድረግ አቶ ወ/ሚካኤል ሃለፎም ተጠያቂ ሲሆን አቶ ታደለ ደግሞ በሙስና ወንጀል የተገኘው ገንዘብና ንብረት እንዳይታወቅ ለማድረግ አቶ ብርሃኑ ዝናቡ እና ካህሣይ ጉባል የቀበሌ መታወቂያ እንዲያወጡ በማመቻቸት እና በቀበሌው መታወቂያ መነሻነት የተጠቀሡትን ወንጀሎች እንዲፈፅሙ በማድረጉ  በወንጀሉ በመሣተፉ መከሠሡ ተመልክቷል፡፡ በቁጥጥር ስር ያልዋለው አቶ ብርሃኑ ዝናቡ፤ መኪኖቹ በስሙ እንዲገዙ፣ የባንክ ብድርም በስሙ እንዲበደር በማድረጉ ክስ የቀረበበት ሲሆን ወጣት ካህሣይ ደግሞ ለወንድሙ ውክልና ሠጥቶ በስሙ ገንዘብ እንዲያስቀምጥና እንዲያንቀሣቅስ እንዲሁም መኖሪያ ቤት እንዲገዛ በማድረጉ ተከሷል፡፡ 
ቀደም ብሎ በነበሩት ሁለት ቀጠሮዎች አቶ ተመስገን፣ አቶ ወ/ሚካኤል እና አቶ ታደሰ፤ ክሡ ተነቦላቸው መቃወሚያቸውን አቅርበው፣ አቃቤ ህግም ለመቃወሚያው መልስ የሠጠ ሲሆን ካህሣይ ጉላል ለመጀመሪያ ጊዜ ከትናንት በስቲያ ቀርቦ ክሡ ከተነበበለት በኋላ፣ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ከሌሎች ተከሳሾች ጋር አብሮ እያየው ነው፡፡ 
አቃቤ ህግ በተከሣሾቹ ላይ 14 የሠውና 14 የሠነድ ማስረጃዎችን ከክሡ ጋር አያይዞ አቅርቧል፡፡ 
ከትናንት በስቲያ የዋለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 15ኛው ችሎት፤ በመዝገቡ ላይ የተለያዩ ትዕዛዞችን ያስተላለፈ ሲሆን በእለቱ የቀረበው 5ኛ ተከሣሽ፤ የዋስትና መብቱ ተከልክሎ በቀጣይ ቀጠሮ ከጠበቃ ጋር እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት፣ መዝገቡን ለጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡ -

አድርባይነት (ለጥቅም ሕሊናን መሸጥ)

ከማርቆስ ዐብይ
ኢትዮዽያ ሀገሬ ሞኘ ነሸ ተላላ፣
የሞተልሸ ቀርቶ የገደለሸ በላ፣
The Ethiopian government spokesman Shimeles Kemal
እኚ ሰው የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ሚንስትር ዴእታ አቶ ሽመልሰ ከማል ይባላሉ…
አድርባይነት ቀለል ባለ አገላለጽ ማስመስል ወይም ለጥቅም ሲባል ሕሊናን መሸጥ እንደማለት ነው፣፣ ይህ እኩይ ባሕሪ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቀላል የማይባል እድሜ አስቆጥሯል የሩቁን ትተን የቅርቡን ከጣሊያን ወረራ ቦኋላ ያለውን አሁን እስካለንበት ጊዜ ያለውን ለማየት ብንሞክር እንኳ በጣም ብዙ ነገሮችን መታዘብ እንችላለን።
ጣሊያን ኢትዮጵያን በግፍ በወረረበት ወቅት የክርስቶስን ወንጌል ይሰብኩ ከነበሩ የሐይማኖት አባቶች መካከል በጥቅማ ጥቅም የተደለሉ ጥቂት የሐይማኖት አባቶች በየአውደ ምሕረቱ ለምዕመናን ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ኤሳው ለምስር ወጥ ሲል ብኩርናውን አሳልፎ ለወንድሙ ለያዕቆብ መሸጡን በመጥፎ ተምሳሌትነት እንዳላስተማሩ ሁሉ ራሳቸው ለቁራሽ እንጀራ ሲሉ ሕሊናቸውን በመሸጥ ከወራሪው ከጣሊያን ጎን በመሰለፍ ለምዕመናኑ በሃሰት በእግዚአብሔር ሃምሳል ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጣ ነው በማለት ሕዝቡ ወራሪው ጣሊያንን አሜን ብሎ እንዲቀበል ያግባቡ ነበር።
በዚህ የወረራ ዘመን የንጉሠ ነገሥቱ የቅርብ ባልሙዋል ከነበሩ መኩዋንንቶች እና መሳፍንቶች መካከል ሳይቀር ለጣሊያን ያደሩ ነበሩ፣፣ እነዚህ ሹማምንቶች ህዝቡ ተቃውሞውን በማቆም ይዘውለት የመጡትን እውቀት እና ስልጣኔ በመቅሰም ሀገሩን ያለማ ዘንድ ሰዎቹን በትዕግሰት እንዲጠብቃቸወ በሀሰት ይሸነግሉት ነበር።
ታዋቂው ደራሲ አቤ ጎበኛ የረገፉ አበቦች በሚል ርዕሰ ያሳተሟት ልብ ወለድ መፅሃፍ ውስጥ ስለነዚህ ከዳተኞች የአድርባይነት መጠን ማሳያ የሚሆን አንድ ታሪከ ያሰነብቡናል፣ ይህውም በዚያ ዘመን የነበሩ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ትልቅ ስም ያላቸው አንድ ሰው ነበሩ እኚ ሰው ባለቤታቸው ሲወልዱ ትልቅ ግብዣ አዘጋጅተው ብዙ ሰው ይጋብዛሉ ከተጋባዡቹ መካከል የጣሊያን ወታደሮች የክብር ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል በግብዣው ሰፍራ ላይ ተገኝተዋል አሳላፊዎች ሰውን ለማስደሰት ከወዲህ ወዲይ ይራወጣሉ በዚህ መሀል ከክብር እንግዶች አጠገብ ተጎልተው የነበሩት ጋባዠ በእጅ ምልክት ሰውን ፀጥ እንዲል በማድረግ የልጃቸውን ሰም በታዳሚው ፊት ለማውጣት እንደሚፈልጉ ገለፁ በማሰከተልም ልጄን ሮማ (ROMA) ብያታለሁ አሉ አድናቆትና ጭብጨባ የክብር እንግዶች ካሉበት አካባቢ ብቻ ቀረበ የተቀረው ተጋባዠ እነሱን ተከትሎ አጨበጨበ እንጂ ሰለሰሙ የሚያውቀው ነገር ስለሌለ ነገሩ እሰከሚገለፅለት ድረሰ አላወቀም ነበር፣ በመቀጠልም ሮማ አሉ በአሰመሳይነት ኩራት የጌቶቻችን ሀገር ዋና ከተማ ነች ብለው ተቀመጡ፣ ሰው ሕሊናውን ሲሸጥ መቼም እራሱንብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም ለመሰዋትነት ያቀርባል።
መቼም እንዳያልፈው የለምና ያ የመከራ ጊዜ አለፈና በአርበኞች ፅናትና ተጋድሎ ዘመቻው በድል ተጠናቀቀ ፣ ወራሪው ጣሊያን በኩራት የተመላለሰባቸው እነዛ ጎዳናዎች በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ የሞተው ሞቶ የተረፈው በደመነፍሰ ተራወጠባቸው በግፍ የወረራትን ሃገር በሃፍረት ጥሉዋት ፈረጠጠ ፣ እነዛ ወራሪውን አዝለው ህዝቡን ሲያሰጨንቁት የነበሩት ሆዳደሮች ግን ያዘሉትን ያህል እንኩዋን ሊያዝላቸው ቀርቶ እጃቸውን ይዞ የሸሸበት ያህል እንኩዋን ይዟቸው ሊሄድ አልወደደም እንደ ፓሰታ መቀቀያው ዕቃ የትም ጥሏቸው ሄደ እንጂ፣ እነዚ ከመጣው ጋር እንደ ሴተኛ አዳሪ ወዳጅ መሰለው መቅረብ እንደ መልካም በሐሪ የተጣባቸው ግለሰቦች አርበኞች ወደ ከተማ ሲገቡ ፀጉራቸውን አሳድገው ተቀላቀሉዋቸው እኛ ልጃቸውን ሮማ ብለው የሰየሙ ግለሰብም የልጃቸው ሰም ላይ ’ን’ በመጨመር ሮማን በማለት አይናቸውን በጨው አጥበው ከአርበኞች ጋር ላይ ታች ሲሉ ያያቸው የሀገሬው ሰው በትዝብት እጁን አፉ ላይ ጭኖ በመገረም ነበር የሚያያቸው ይሉናል አቤ ጎበኛ።
እሰካሁን ለመቃኝት የሞከርነው ህሊናቸውን ሸጠው ታሪክ አበላሸተው ወደማይቀረው ሞት ሰለነጎዱ ሰዎች ነው፣ አሁን ደግሞ በህይወት ያሉ ነገር ግን ህብረተሰቡ አፈር ካለበሳቸውና ሃውልታቸው ላይ ሆዳደር ብሎ ካተመባቸው ግለሰቦች መካከል ለናሙና አንዱን በመውሰድ እናወጋለን ከዛ አሰቀድመን ግን እንደመሸጋገሪያ ይሆነን ዘንድ ከጥቂት አመታት በፊት ጠቅላይ ምኒሰትር መለሰ ዜናዊ የሀገር ሸማግሌዎችን ሰብሰበው ሲያወያዩ አንድ የሃይማኖት አባት የተናገሩትን አሰገራሚ ንግግር እናሰቀድም እንዲህ ነበር ያሉት “በአባቶቻችን እሰከ አሁን ድረስ ሲነገር የቆየው ከወደ ሰሜን በመነሳት ኢትዮዽያን በጠነከረ አንድነት የሚያሰተዳድራት ንጉስ ይመጠል የተባለው ትንቢት ተፈፀመ ይህውም አንተ ነህ ብለው ጣታቸውን ወደሰብሳቢው ጠቆሙ” እሳቸውም በትዝብት ፈገግ ብለው ምላሸ ሰጡ፣ እኝህ አሰተያየት ሰጪግለሰብ ሀገሪቱ ቋንቋን መሰረት ባደረገ ክልል ተሸንሸና እንደባቢሎን ሰዎች እርስ በእርሰ መግባባት እንዳልተቻለ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም ይህን ባሉበት ወቅት ሰዎች በዘመቻ መልክ ክልላችሁ አይደለም እየተባሉ የዘሩትን ሳይሰሰቡ ከየቦታው የሚፈናቀሉበት ውቅትም ነበር ይህንንም አሳምረው ያውቃሉ ነገር ግን እሳቸው እያሰሉ ያሉት ይህን መናገራቸው እንደውለታ ተቆጥሮላቸው ወደ ቅያቸው ሲመለሱ ስለሚደረግላቸው ከንቱ ውዳሴ ወይም ስልጣን ብቻ ነው፣ ይህን እዚህ ላይ ቋጭተን እሰኪ በአዲሰ መስመር ላይ እላይ ወደጀመርነው አንድ አስገራሚ ሰው እንመለስ።
እኚ ሰው የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ሚንስትር ዴእታ አቶ ሽመልሰ ከማል ይባላሉ፣ አቶ ሽመልሰ በመጀመሪያ ኒሻን የምትባል የግል ጋዜጣ በማቋቋም የመንግስትን ስህተት እየነቀሱ በጣም ጠንከር ባለ አገላለፅ ይተቹ ነበር ከዚህ ጎን ለጎን ሌላው የሚታወቁበት ደግሞ መንግስት በውሃ ቀጠነ የሀሰት ክሰ ጋዜጠኞችን ፍርድ ቤት ሲያቆማቸው እሳቸው ባላቸው የህግ እውቀት በነፃ ፍርድ ቤት በመቆም ለንፁሃን ጋዜጠኞች ሸንጣቸውን ገትረው በመከራከራከረቸው ነበር ፣ እኚህ ስው ታዲያ ትንሽ ጠፋ ብለው ከራርመና ሲመለሱ ባንዴ ጎፈር ሆነው ሲያወግዙት የነበረው መንግስት ባለስልጣን በመሆነ ከኔ በላይ ታማኝ የለም ብለው ቁጭ አሉ፣ ያኔ በደጉ ጊዜ ከህሊናቸው ጋር በነበሩ ሰአት ሲሟገቱላቸው የነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸውን ንፁሃን ጋዜጠኞችን መሰረተ ልማት ለማውደምና የመንግሰት ባለስልጣናት ለመግደል ከአሸባሪዎች ጋር ሲያሴሩ እጅ ከፍንጅ ያዝናቸው ብለው በአደባባይ ህጉን እያወቁት ከፍርድ ቤት ቀደመው ፍርድ አስተላለፉ፣ እነዚያ ንፁሃን ጋዜጠኞችም ያለጥፋታቸው የእድሜአቸውን እኩሌታ ዘብጥያ እንዲያሳልፉ የፖለቲካ ውሳኔ ተወሰነባቸው እናቃሊቲ ተወረወሩ፣ እኚህ ግለሰብ መንግስት እራሱን አሻሸሎ ነው የተቀላቀሉት እንኩዋን እንዳይባል እርሳቸው ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት የነበረው የጋዜጠኞች የመሰራት ነፃነት አሁን ካለው ዘጠና በመቶ ይሻል ነበር ታዲያ ምን ነካቸው ከተባለ መልሱ ለጥቅም ሲባል ሕሊናቸውን ሸጡ ይሆናል።
ሰው ሕሊናውን በጥቅም ከተያዘ ዕውቀትና ስልጣን መጠሪያው ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም ፣ በጣም የሚገርመው እኚህ ሰው መንግስትን በመወከል በተደጋጋሚ የተናገሩዋቸውን ንግግሮች አለቆቻቸው ውድቅ በማድረግ ሸመልስ ያለው ውሸት ነው በማለት በአደባባይ ሲያዋርዱአቸው በፊት ለሎች ሲከራከሩ የነበሩ ሰው እንዳልነበሩ ሁሉ በጥቅም ስንሰለት እግር ተወርቸ ታሰረው እራሳቸውን እንኩዋን መከላከል አቅቷቸው ሲወራጩ በመታዘብ አይተናል።
ባጠቀላይ ህሊና ትንሹ እግዚአብሔር ነው ይባላል መልካም ስንሰራ የሚያበረታታን መጥፎ ሰንሰራ ደገሞ እንድንፀፀተና ዳግም እንዳንሰራ እረፍት የሚነሳን ታድያ ሰው ይህንን ትልቅ ነገር አጥቶ ሀብትና ዝናን ቢሰበሰብ እንዴት የዓይምሮ ሰላም ሊያገኝ ይችላል?
“ሰው እግዚአብሔርን አጥቶ አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ምን ይጠቅመዋል” እንዳለው መፀሃፍ ቅዱስ፣
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅ!

Wednesday, 18 December 2013

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ



ታህሳስ 7  2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ  አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት  በጭንቅና  በአሳር  ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ  ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ የአሳርና የውርደት ህይወት ይበልጥ እየሰፋ፣ የሚፈጸምበት ግፍ ይበልጥ እየገዘፈ መሄዱን አይተነዋል። በሃገርና በህዝብ ላይ እየወረደ ያለውን ወያኔ ወለድ የስቃይና የፍዳ ናዳ በቅጡ ላጤነው  ሃገሪቱና ህዝቧ የአዳዲስ የስቆቃና የመከራ አይነቶች መፈተኛ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር አይኖረውም። ለሚራበው ለሚረገጠው በግፍ ለታጎረው፣ በኑሮ ውድነት ለሚጠበሰው፣ ለተሰደደው ለተፈናቀለው ኢትዮጵያዊ እንድ አመት በሲኦል የቀናትና የወራት መቁጠሪያ እንደሚለካ ዘመን እጅግ የረዘመ የስቃይ ግዜ ነው።
Ginbot 7 Popular Force logoየዋልድባ መነኩሳት ገዳማችን  አትድፈሩ አታፍረሱ በማለታቸው እየተገረፉ ለዘመናት ፈጣሪያቸውን ከሚማጸኑበት ለሃገርና  ለህዝብ ምልጃ ከቆሙበት ገዳም በዘር መመዘኛ እየተለዩ  እንደቆ ሻሻ ተጠርገው የተባረሩበት ፣ እምነታችን አትንኩ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችና  መሪዎቻቸው በሃሰት ክስ ተመስርቶባቸው  ወህኒ መውረዳቸው አንሶ  ወንድሞቻችን ይፈቱ በማለት  ሰላማዊ  ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖቻቸን በወያኔ ነፍሰ- ገዳዮች  በአረመኔያዊ ጭካኔ የተጨፈጨፉት በዚሁ አመት ነው። ወያኔ በህዝብ መሃከል በዘራው የዘር መርዝ የተነሳ በሽዎች የሚቆጠሩ አማሮች ከጉራ ፈርዳና ከቤንሻንጉል፣ ኦሮሞዎች ለዘመናት ከኖሩበት ምስራቅ ሃረርጌ  አካባቢ  እንዲፈናቀሉና በገዛ ሃገራቸው መድረሻ ቢሶች  እንዲሆኑ የተደረገው በዚህ አንድ አመት ውስጥ ነው። ጋምቤላዎች ሙርሲዎች አፋሮችና ሌሎችም ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች የተጨፈጨፉበት፣በልማት ስም ለመጡ የውጭ ወራሪዎችና ወያኔ ለፈጠራቸው ቱጃሮች ቦታ እንዲለቁ ተደርጎ ቀደምቶቻቸው ለዘመናት ከኖሩባቸው ቀየዎች እንዲነቀሉ ተደርገው እንደ አልባሌ ነገር የትም እንዲበተኑ የማድረጉ ሂደት ከመቼውም በላይ ተጠናክሮ የቀጠለው በዚሁ አመት ነው። በዚሁ አንድ አመት በወያኔ የሃገሪቱ ገዥዎች በህዝብ ላይ የተፈጸመው  ጭካኔና ወንጀል ተዘርዝሮ  የሚያልቅ አይደለም።
ይህ ወያኔ  ሰራሽ ሃገር በቀል የውርደትና  የስቃይ ህይወት አልበቃ  ብሎ ወያኔ ከሳውዲ የጨለማ ዘመን ገዥዎች ጋር በመተባበር ወንድሞቻችን በሳውዲ አውራ ጎዳናዎች ላይ እንዲታረዱ እህቶቻችን በቡድን በተደራጁ የሳውዲ ጎረምሳዎች  እንዲደፈሩ ሁኔታዎችን አመቻችቶ  ለኢትዮጵያውያን ያለውን እጅግ የከረረ ጥላቻ በአደባባይ ያሳየበት አመት ነው። እንዲህ አይነቱ የጅምላ ግፍና  ውርደት ከመከሰቱ በፊት ህዝባዊ ሃይሉ በአረብ ሃገር በባርነትና  በስደት የሚገኙ እህትቶቻችንን ወንድሞችችን ስቃይ  ስቃዩ አድርጎ በመውሰድ “ላንቺ ነው” በሚለው ድርጅታዊ መዝሙሩ “በባለጌ  አረቦች መዳፍ ውድ ክብራቸው ለጎደፈው እህቶቻችን፣ በአረቦች የባርነት ቀንበር ጀርባቸው ለጎበጠው  ወገኖቻችን እንደርስላችኋለን፣ የተሰባሰብነው  ደማችን የሚፈሰው የመከራ ቀናችሁን ለማሳጠር ነው” የሚል ቃል ኪዳኑ ሰጥቶ  ነበር። የድርጅታችንን ምስረታ አንደኛ  አመት ስናከብር ልባችንን ደስታ ሳይሆን ሃዘን እንዲሞላ የሚያደርገው ይህ ቃል ኪዳናችን ለማክበር የጀመርነው ጉዞ ከድርጅት ምስረታና ከድርጅታዊ ዝግጅት አልፎ   በኢትዮጵያ ህዝብ ጥላቻና ንቀት  የተነፋውን የወያኔን እብሪት በማስተንፈስ የወሰዳቸው ተጨባጭ የአለኝታነት እርምጃዎች ባለመኖራቸው ነው።
ምንም እንኳን ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል እራሱን እንደ ድርጅት አቁሞ  ኢትዮጵያውያንን አሰባስቦ  መራራው ትግል የሚጠይቀውን የፖለቲካ  የወታደራዊ ስልጠናና ትጥቅ አስታጥቆ  በወያኔ  ላይ ለመዝመት የጀመረውን ጉዞ የሚያስቆመው ምድራዊ ሃይል እንደሌለ ብናውቅም የህዝብ ስቃይ ለግዜው መቀጠሉ የህባዊ ሃይሉን አባላት ማሰቃየቱ አልቀረም። በወያኔ  ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው ወገናችን ህዝባዊ ሃይሉ የወያኔን አገዛዝ እድሜ  የሚያሳጥሩ ፈጣን እርምጃዎችን እንዲወስድ በከፍተኛ  ጉጉት እየተጠባበቀ እንደሆነ  እናውቃለን። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የሃገሪቱ ዜጎች በተጠንቀቅ እንደቆሙ እናውቃለን። እነዚህ ዜጎች ከሁሉም የእምነት የቋንቋ  የጾታ የእድሜ  የኑሮና  የማህበረሰብ ስብጥር የሚያካተቱ  እንደሆኑ እናውቃለን። በሃገሪቱ ታሪክ ተሰምቶና  ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ  የወታደር ልብሱን  እየጣፈ እንዲለብስ፣  የወታደር ጫማውን መቀየሪያ አጥቶ  ሸበጥ እንዲያደርግ የተገደደውን፣  የወያኔ ጀነራሎች በስልጣንና  በዘረፋ ሲያብጡ በድህነት እንዲሟሽሽ የተፈረደበት የሃገሪቱ ሰራዊት በዘር በእምነት ሳይለያይ ከህዝባዊ ሃይሉ ጎን ለመቆም አሰፍስፎ  የቆመ  እንደሆነ  እናውቃለን። ይህ ሃገራዊ እውነታ ለህዝብ የገባነውን ቃልኪዳን የለምንም ጥርጣሬ  ማስከበር እንደምንችል በሙሉ ድፍረት እንድናውጅ የሚያስችለን ሃቅ ነው።
የወያኔ ጀንበር እየጠለቀች የኢትዮጵያ  ህዝብ ጀንበር እየፈካች የመሄዱ ጉዳይ እንደማይታጠፈው  የመንጋትና  የመምሸት የተፈጥሮ ህግ ነቅነቅ የማይል እንደሆነ ግንቦት7 ጠንቅቆ ያውቃል።  እውቀታችን ልዩ ጥበብ የሚጠይቅ ኣይደለም። ግፍ ፍትህን አሸንፎ፣ እውነት በሃሰት ተደፍቃ፣ ጥላቻ ፍቅርን፣ አድሎ እኩልነትን፣ ሃገራዊ ክህደት ሃገር መውደድን፣ ባንዳነት አርበኛናትን ለዘላላሙ ቀብረው የሄዱበት የሃገራችንና  የሰው ልጆች ታሪክ የለምና የወያኔን አይቀሬ ሞት ለመተንበይ  ልዩ ጥበብ አያሻንም። ይህን እኛ ብቻ ሳንሆን በዘረፋና በጥላቻ  የደነዘዘ ህሊና ያዳበሩት የወያኔ  ባለስልጣናትም ያውቁታል። ያለእኔ  ጀግና የለም፣ ያለእኔ  አልሞ  ተኳሽ የለም በሚል እብሪት በመጻደቅ የሚታወቁት ወያኔዎች በመቶ ሽዎች በሚቆጠሩ ወታደሮች ተከበው፣  በታንክ በአይሮፕላን በሚሳይል ታጅበው ከሚኖሩበት ቤተመንግስትና ቪላዎች ውስጥ ብርክ እንዲይዛቸው ያደረገው ለመሆኑ፣  ሳር ቅጠሉ ግንቦት ሰባት እየመሰላቸው ሲበረግጉ እንደሚያመሹ፣  የግንቦት ሰባት አባላት እያሉ ከድርጅታችን ጋር አንዳችም ግንኙነት የሌላቸውን ዜጎች እያሰሩ ሲያሰቃዩ ፣  ከምላሳቸው ላይ ግንቦት 7  የሚል ስም ተፈናጦባቸው  እንደሚውሉ በራሳቸው ሚድያ  ወያኔዎች ራሳቸው እያሳዩን እያስደመጡን ነው። ከዚህም አልፎ በዚህ አንድ አመት ውስጥ  የህዝባዊ ሃይሉን መሪዎች በመግደል ድርጅቱን ለማኮላሸት ይቻላል በሚል ወያኔ የላካቸው ነፍሰ ገዳዮችና ድርጅቱን ከውስጥ ለመቦርቦር ያሰማራቸው ሰርጎገቦች ተራ በተራ ተልእኳቸው እየከሸፈ በህዝባዊ ሃይሉ እጅ እየወደቁ ወይም ተልእኳቸው እንደማይሳካ ሲረዱ እየፈረጠጡ ወደ ወያኔ ሲመለሱ አይተናል።
ያለፈው አንድ አመት ተመክሯችን ስለወያኔ  ብቻ ሳይሆን ስለራሳችንም ጥንካሬና  ድክመት ብዙ ነገሮች ያስተማረን ኣመት ነው። የቀደምቶቻችን የጀግንነት የአርበኛነት ቅርስ በመላ ህዋሳቸው የተሸከሙ  ለኢትዮጵያ እና  ለህዝቧ ሲሉ ደማቸው ለማፍሰስ ውድ ህይወታቸውን ለመሰዋት ወደኋላ የማይሉ ቆራጥ ብቻ ሳይሆኑ አርቀው የሚያዩ  በርካታ ልጆች  ሃጋሪቷ ያሏት መሆኑን ያረጋገጥንበት አመት  ነው።  በሌላ በኩል ደግሞ  ድርጅታችን የኢትዮጵያን ህዝብ ብቸኛው የመንግስት ስልጣን ባላቤት የማድረጉን ታሪካዊ ራእዩን ለመሳካት የሚያደረገው ትግል ከወያኔ ጋር ብቻ ሳይሆን ከራሳችንም ጋር የሚደረግ እንደሆነ  በሚገባ  የተረዳነው  በዚሁ የአንድ አመት የድርጅታችን እድሜ  ነው። ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል ወያኔ በማህበረሰባችን ውስጥ ከዘራቸውና የሃገሪቱን ዜጎች እንዲበክሉ ካደረጋቸው የዘረኛነት የአድሎ  ከህዝብና  ከሃገር ጥቅም በፊት የራስን ጥቅም ማስቀደም፣ የሱሰኛነትና የሙስናና ሌሎችም አደገኛ ባህሎች ጋር ነው።
ህዝባዊ ሃይሉ ደግሞ  ደጋግሞ  እንደገለጸው ትግላችን አንድ መንግስታዊ ስርአት ወድቆ ሌላው የመንግስት ስርአት በመጣ ቁጥር የህዝብ ተስፋ እየጨለመ  “አዲስ ከመጣው ስርአት ያላፈው ያረጀ ስርአት በግፈኛነቱ በዘራፊነቱ ያነሰ ነበር” የሚል የግፈኛና የዘራፊ ስርአቶች ንጽጽር ላይ የቆመ አሳዛኝ የህዝብ ህይወት እንዲያበቃ ነው። ደርግን ያየ የአጼውን ስርአት እንከኖች ረስቶ ንጉሱ ይሻሉን ነበር ያለበት፣ ወያኔን ያየ የደርግን አስከፊ ዘመን ረስቶ መንጌ በስንት ጣሙ ያለበት አሳዛኝ ሁኔታ ከወያኔ መውደቅ በኋላ በሃገራችን እንዳይደገም ነው ትግላችን። የኢትዮጵያ ህዝብ የውድ ልጆቹን ህይወት ገብሮ ወያኔን በማስወገድ የሚያመጣው ስርአት ከወያኔ ብሶ ህዝብ ወያኔ ማረኝ የሚልበትን ቅስም ሰባሪና አዋራጅ የታሪክ ቅጥልጥሎሽ  እንዳይቀጥል ማድረግ ህዝባዊ ሃይሉ የተመሰረተበት፣ አባላቱ መከራ ለመቀበልና መስዋእትነት ለመክፈል በረሃ የገቡበት ዋናውና ብቸናው ምክንያት ነው። ትግላችንን መራራ የሚያደርገው ከበሰበሰውና የአንድ ጀምበር የህዝብ ቁጣ ከታሪክ ቆሻሻ የመጠያ ስፍራ ከሚከምረው  የወያኔ ስርአት ጋር ብቻ ሳይሆን በወያኔ ቦታ የሚተካውን ስርአት ከአድሎና ከዘረኛነት ከዘረፋና ሃገራዊ ክህደት የጸዳ፣ ዳግም ለኢትዮጵያውያን ውርደትና እንግልት ምክንያት እንዳይሆን ለማድረግ ከራሳችን ጋር ሳይቀር የማያቋርጥ ትግልን ማድረግ የግድ ስለሚል ነው። ህዝባዊ ሃይሉ የአመጽ ትግል የሚያደርግ፣ የመሳሪያው ብዛትና  የሰራዊቱ ቁጥር እያደገ  የሚሄድ ሃይል መሆኑን ስለምንረዳ  ይህን ሃይል ገና ከጅምሩ ከብዙ እንከኖች እያጸዱ ማደራጀት ካልተቻለ  በሃገርና በህዝብ ላይ የሚመጣውን አደጋ  የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ጠንቅቀው የተረዱት ሃቅ ነው። ይህ ግንዛቤ የሰራዊቱን አባላት በጥንቃቄ መመልመልን፣ ማሰልጠንንና መገንባትን የግድ የሚል ነው።
ይህ ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል እጅግ መራራ ነው። ታሪካዊ ስህተቶችን ላለመድገም የሚደረግ ትግል ነው። ይህ ትግል የአካልና የመንፈስ ጽናትን፣ ሃቀኛነትን፣ ታማኝነትን፣ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትግል ነው። የወያኔ ስርአት ከሃገር ግድያው በተጨማሪ ትውልድን ለመግደል ሆን ብሎ ያስፋፋቸው እኩይና ጎጂ ባህሎችና ልምዶች ምን ያህል ማህበረሰባችንን እንደጎዱት ህዝባዊ ሃይሉ ባላፈው አንድ አመት እድሜው በሚገባ የተረዳው ጉዳይ ሆኗል። ህዝባዊ ሃይሉ የሚመኘውን የኢትዮጵያ ትንሳኤና ተሃድሶ እውን ለማድረግ እነኝህ  ወያኔ ሆን ብሎ  ያስፋፋቸውን የባህልና የሞራል ብክለት ማጽዳት የግድ እንደሆነ የተረዳ አካል ሆኗል።
ትግላችን መደፍረስን መጥራትን፣ መንተክተክን መስከንን የትግሉ ሂደት አካል አድርጎ  የሚጓዝ ነው።   ትግሉ የሚልመጠመጠውን እንደቀስት ቀጥ ብሎ ከሚራመደው፣ በካፊያው የሚንቀጠ ቀጠውን ለዶፉ ደንታ ከሌለው፣ ዝናር በቅፌን ከምሩ ተኳሽ  የሚለይ መራራ ትግል ነው። ያለፈው አንድ አመት ይህን አስተምሮናል። ህዝባዊ ሃይሉ ትግሉ ቀላል ነው የሚል ከእውነታ ጋር ያልተያያዘ ቃል ለህዝብም ሆነ ህዝባዊ ሃይሉን ሊቀላቀሉት ለተዘጋጁት ወገኖቹ አይናገርም። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል ለተሰለፉ በሽዎች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን ትግሉ የሚጠየቅውን የሞራል የስብእና ጥብቅነት፣ከፍተኛ  የሃገርና የወገን ፍቅር፣ ጥልቅ የሆነ የመስዋእትነት ፈቃደኛነት የሚጠይቅ መሆኑን ከማስረዳት አንቦዝንም። ህዝባዊ ሃይሉ ለህዝብ ቃል እንደገባው ከወያኔ  ጋር የምናደርገው ትግል በጥበብ በእውቀት በጥናት በጥንቃቄ የምናደርገደው ነው። ነጻነት ያለመስዋእትነት እንደማይሳካ ብናውቅም ለተራ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስንል በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት የሃገሪቱን ውድ ልጆች በከንቱ የሚማግድ ጀብደኛ እንቅስቃሴ  አናደርግም። የውሸት ተስፋ  ህዝብን አንመግብም።  አይናችንን ከዋናው የኢትዮጵያና  የህዝቧ  ጠላት ከሆነው ከወያኔ ላይ አንስተን በሌሎች  ወያኔን እቃወማለሁ በሚሉ ሃይሎች ላይ አንተክልም። ከወያኔ ሌላ ወደ ጎን የምንዋጋው፣ የምንጨቃጨው አታካራ የምንገጥመው ምንም ሃይል አይኖርም። ወያኔን ለመምታት ህዝባዊ ሃይሉ የጨበጠው  ቡጢ ወገኖቻችን በፍቅር ለመጨበጥ የሚዘረጉ ጣቶች  እንዳሉት በጸረ ወያኔ ዴሞክራሲያዊ ትግሉ  ከልባቸው ለመተባበር ለሚፈልጉ ሃይሎች ሁሉ ግልጽ እናደርጋለን።
ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ የድርጅት ምስረታ  መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ  ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ነው። በዚህ ረገድ የተሰራው ስራ አጥጋቢ ውጤት አስገኝቷል። ስልጠናው፣ ድርጅት ማጠናከሩና  ማጥራቱ ወደፊትም የሚቀጥል ነው። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሃይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባላፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የሃገራችንን ግፉአን ህዝቦች መታደግ የሚችልበትን እርምጃዎች መውሰድ የሚችልበት አመት መሆኑ ነው። በዚህ የህዝባዊ ሃይላችን የአንደኛ አመት ምስረታ  ክብረ በአል ወቅት ወገንም ጠላትም በግልጽ እንዲያውቀው የምንፈልገው ይህን ሃቅ ብቻ ነው።
ውድመት ለዋናውና  ለብቸኛው የኢትዮጵያ ህዝብና  የኢትዮጵያችን ጠላት ለሆነው የወያኔ ገዥ ጉጅሌ!
ድል በወያኔ ግፈኛ ስርአት አበሳውን ለሚያየው የመላው የኢትዮጵያ  ህዝብ!


የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል
Ginbot 7 Popular Force
www.ginbot7pf.org
Tel: +44 208 123 0056
email: pr@ginbot7pf.org

Monday, 16 December 2013

አንድ ወጣት የመንግስት ሰራተኛ መንግስትን በመቃወም ራሱን አጠፋ

 (ስድስት)ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :-በሲዳማ ዞን በአለታ ጩኮ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤ ባለሙያ የሆነው  ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ በሙያው ለአመታት ህብረተሰቡን ሲያገለግል ቢቆይም የመንግስትን አሰራር በተደጋጋሚ በመተቸቱ፣ ከመስርያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ግዜያት ግጭት ውስጥ ከመግባቱም በላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሳይቀር ደርሶት ነበር።
ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ መንግስትን በግልፅ በመቃወም፤ መስተካከል ያለበትን ጉዳይ በግልፅ መናገር ልዩ ባህሪው እንደነበር የሚናገሩት ጓደኞቹ፣ በዚህ ባህሪው በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጎም ነበር። “መቼ ነው ነፃ የምንወጣው?’ በማለት በተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ እንደነበር የሚናገሩት ባልደረገቦቹ፣ ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓም አዋሳ አውሮፕላን ማረፍያ ሜዳ ላይ 20 ገፅ ያለው መንግስትን የሚቃወም ደብዳቤ ፅፎ የትምህርት ዶክመንቶቹን እንደታቀፈ እራሱን አጥፍቶ ተገኝቷል።
በሰዓቱ ደርሰው ደብዳቤውን ያነበቡ ሰዎች እንደተናሩት ደብዳቤው
‹‹ እስከዛሬ ነፃ እወጣ ይሆን ብዬ ጠብቄ ነበር ግን ነፃ የምወጣበት መንገዱ እየጠበበ ነፃነቴ እየራቀኝ መጣ፣ ታዲያ ነፃ እንዲያወጣኝ በማን ተስፋ ላድርግ? ‘በማንም … ‘ለካ ነፃ መውጣት ይቻላል፣   እኔ ግን በቀላሉ እራሴን ነፃ ማውጣት እንደምችል ተረድቻው ፣ ስለዚህ እራሴን ከመራር ግፍ አላቅቄ በነፃነት ነፃነቴን አውጃለሁ፤ ስለዚህም ሞቴ ነፃነቴ ነው፡፡ ሳልገድል ፣ በሞቴ እራሴን ነፃ አወጣለው ››.. የሚል ይዘት አለው።
በግል ማስታወሻው ላይ ደግሞ ‹‹ በዚህች ሀገር ላይ ሶስተኛ አራተኛ አምስተኛ ዜጋ ሆኜ መኖሬ የሚያበቃው መቼ ነው ›› ኢትዮጵያ ነፃ መውጣት ባትችል እኔ ግን እራሴን በሞቴ ነፃ አወጣለሁ የሚል መልዕት” ሰፍሯል።
ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ የፃፈው 20 ገፅ የተቃውሞ ደብዳቤ በአሁን ሰዓት በአዋሳ ፖሊስ እጅ የሚገኝ ሲሆን ለቤተሰብ እና ለጓደኞቹ ደብዳቤውን ለመስጠት ፖሊስ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ወጣቱ በ30 ዓመቱ ይህችን አለም የተሰናበተ ሲሆን ስርዓተ ቀብሩ በጌደኦ ዞን ዲላ ከተማ ዲላ ኢየሱስ ቤ/ክ ታህሳስ 5 ቀን 2006  ዓ.ም ተፈፅሟል፡፡  
ወጣት ነጋልኝ  በጉራጌ ዞን ልዩ ስሙ ሜልኮ ተብሎ ከሚጠራው መንደር በ1976 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን ትምህርቱን በዲላ ከተማ እና በሀዋሳ ከተማ የተማረ መሆኑንም ከቤተሰቦቹ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ወጣቱ በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ1998ዓ.ም በማዕረግ ተመራቂ ስለመሆኑም የኮሌጁ ቆይታው ያሳያል።
ወጣት ነጋልኝ በሲዳማ ዞን በሎካ አባያ ወረዳ ለሁለት ዓመታት ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም ሲሰራ ከቆዬ በኋላ  ወደ አለታ ጩኮ ወረዳ የተዛወረ ሲሆን፣ ህይወቱ እስካለፈበት ዕለት ድረስ በስራ ላይ እንደነበረ  ከስራው ጎን ለጎንም  በ agricultural business management ከያርድስቲክ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የመጀመርያ ዲግሪውን ይዟል፡፡
ለሰዎች መብት ዘወትር የሚታገል በሃፊዎቹ ዘንዳ ጥያቄ በመጠየቅ እና ያላመነበትን ነገር በመከራከር ሃላፊዎቹን መልስ በማሳጣት የሚታወቅ እንደነበር የስራ ባልደረቦቹ ገልጸዋል።
ወጣት ነጋልኝ ፡ አልንና ዝም አልን በሚል ርእስ በጻፈው አጭር ግጥም እንዲህ ይላል

በጅጅጋ የተካሄደው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ማለፉ በክልሉ ሰላም አለመኖሩን ያመለክታል ሲሉ አንድ ታዛቢ ተናገሩ

 (ስድስት)ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :-በመንግስት የሀላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ አንድ ስማቸው እንዳይገለጸት የፈለጉ ሰው ለኢሳት እንደተናገሩት በክልሉ በቆዩባቸው ቀናት የታዘቡት ነገር ቢኖር በክልሉ የሰላም እጦት ዋናው ችግር መሆኑን ነው።
ምንም እንኳ መንግስት ያለምንም ችግር በአሉ መጠናቀቁን ቢገልጽም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ እንደነበር ሃላፊው ይናገራሉ። በከተማዋ ዳርቻዎች ታንኮች፣ ከባድ መሳሪያ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ፣ ልዩ ኮማንዶችና እና እስካፍንጫቸው የታጠቁ እግረኛ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት የ24 ሰአታት ጥበቃ ሲያደርጉ ፣ ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ደግሞ የአየር ላይ ቅኝት ያደርጉ ነበር። ጥበቃው እስከ አዋሳኝ ወረዳዎች ዘልቆ እንደነበር የገለጹት ሀላፊው፣ መኪኖች በበአሉ ዝግጅት ወቅት እንዳይንቀሳቀሱ ታግተው እንደነበር ገልጸዋል።  የበአሉ አከባበር በስታዲየሙ ውስጥ ብቻ ይካሄድ እንደነበር የገለጹት እኝሁ ሀላፊ፣ ሌላው የጅጅጋ ክፍል የሞት ከተማ ይመስል ነበር ሲሉ አክለዋል። በጦርነት ቀጠና ውስጥ እንኳ ቢሆን፣ በዚህ አይነት ወታደራዊ ጥበቃ ማንኛውንም አይነት በአል ማክበር እንደሚቻል የገለጹት ባለስልጣኑ፣ አካባቢውን የጎበኙ የውጭ አገር ዜጎችና ሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው   ሰላም በኢህአዴግ እይታ ምን ማለት እንደሆነ በቂ ግንዛቤ ወስደዋል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በበአሉ ላይ ለመሳተፍ እንግድነት ተጠርተው ከሄዱት እንግዶች መካከል የኬንያውና የሩዋንዳው አፈ-ጉባኤዎች ተቀባይ አጥተው ሲቸገሩ እንደነበር እኝሁ ሀላፊ ተናግረዋል። የኬንያው አፈጉባኤ የተጋበዙት በአባ ዱላ ገመዳ ሲሆን፣ የሩዋንዳው ደግሞ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉበኤ ካሳ ተክለብርሀን ነበር። ይሁን እንጅ ሁለቱ ልኡካን ጅጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቶ አባ ዱላም ሆኑ አቶ ካሳ ተክለብርሀን አልተቀበሉዋቸውም፣ እነሱን የሚቀበል ሌላ ሰውም አላዘጋጁም። ልኡካኑ ግራ ተጋብተው በጅጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከቆዩ በሁዋላ፣ የጅጅጋ ፖሊስ በአንድ አሮጌ ፒክ አፕ የፖሊስ መኪና አሳፍሮ ጅጅጋ ሆቴል እንዲያርፉ አድርጓል። ልኡካኑ እንዲያርፉ የተደረገበት ሆቴል ደረጃውን የማይመጥን ነበር ሲሉ ባለስልጣኑ ገልጸዋል። የልኡካን ቡድኑ በመጡበት ወቅት አባ ዱላና አቶ ካሳ ተክለብርሀን በተዘጋጀላቸው የእንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ በመዝናናት ላይ ነበሩ።
ልኡካኑ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሄደው ባለመቀበላቸው ማዘናቸው ሳያንስ በተያዘላቸው ሆቴል እጅግ ተበሳጭተው ነበር።  የሶማሊ ክልል አስተዳደር የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ለውጭ አገር እንግዶች ተገቢውን ክብር ባለመስጠታቸው ማዘኑን መግለጹም ታውቋል።

ለጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ ህክምና የሚውል የእራት ግብዣ ተዘጋጀ

 (ስድስት)ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :-በቀረረበባቸው የፕሬስ ክስ ወደ አዋሳ በተጉዋዙበት ወቅት በድንገት በተከሰተ የተሸከርካሪ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ  አዘጋጅ ለሆነው ለወጣት ኤፍሬም በየነ የሕክምና ወጪ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት ሰኞና ማክሰኞ በአዲስአበባ እንደሚካሄድ ከዕርዳታ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ለሪፖርተራችን ገልጿል፡፡
በዚህ የእራት ምሽት ላይ 500 ብር ዋጋ ያላቸው ትኬቶች ተዘጋጅተው በመሸጥ ላይ ሲሆኑ በተለይ ጋዜጠኞች ትኬቱን በመሸጥና በግዥ በመሳተፍ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸው ታውቆአል፡፡
በአዲስአበባ በአትላስ ሆቴል አካባቢ የሚገኘው ካናዳ ካፌ፣ባር እና ሬስቶራንት የእራት ፕሮግራሙን ስፖንሰር ያደረገ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ከዚህ ዝግጅት ከ80ሺ ብር በላይ ገቢ ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የ27 ዓመቱ ጋዜጠኛ ኤፍሬም በደረሰበት ጉዳት በማጅራቱ አካባቢ የአከርካሪ አጥንቱ የተጎዳ ሲሆን በሳምባው ላይ የተከሰተው ሕመም እያገገመ መሆኑን ባለፈው ቅዳሜ  ከወጣው ከአዲስአድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ አስታውቆአል፡፡
ጋዜጠኛ ኤፍሬም ለጊዜው በኮርያ ሆስፒታል እየተረዳ ቢሆንም በዘላቂነት ለማገገም የውጪ አገር ከፍተኛ ሕክምና እንደሚስፈልገው በሕክምና ባለሙያዎች እንደታመነበት አስተባባሪው አስታውሶአል፡፡