Wednesday 23 October 2013

በቅርቡ ከቴሌ ጋር ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ውል የተፈራራመው የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ንብረት ሊወረስ ነው

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ኩባንያው ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ እቃዎችን ታክስ ሳይከፍል በቴሌ ስም ሲያስገባ በመገኘቱ ንብረቱ እንዲወረስ እንደሚደረግ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል።
ቴሌ ለኩባንያው እቃዎችን እንዲያስገባ ፈቃድ አለመስጠቱን በመግለጹ ችግሩ ይፋ መውጣቱን ጋዜጣው ዘግቧል።
ሁዋዌ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በአይነት ከ235 በላይ እቃዎችን አስገብቷል፤
ይኸው ኩባንያ ከሶስት ወር በፊት የማስፋፋት ስራ ለመስራት በሚል የ800 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከቴሌ ጋር መፈራረሙ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment