Thursday 4 April 2013

ከ120-150 ሺህ ኢትዮጵያውያንን የማፈናቀሉ ሃሳብ አደጋ ገጠመው::ብኣዲኖች እያጉረመረሙ ነው::

Untitledበወያኔ መንግስት ፖሊሲ መሰረት ከተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ዘርን መሰረት አድርጎ ለአገዛዝ እድሜ ማስረዘሚያ እና ለሙስና በሚያመቸው መንገድ እያፈናቀለ የሚገኘው ዘረኛው ጁንት በውስጡ ከማፈናቀል ሂደቱ ጋር በተያያዘ አደጋ እንደገጠመው አንድ የብኣዴን ሰው ለምንሊክ ሳልሳዊ ትላንት ምሽቱን በስልክ አረጋግጠውለታል::
እኚሁ የብኣዴን ሰው እንዳሉት የማፈናቀሉን ሂደት ተከትሎ ከተለያዩ አካላት እየጎረፈ ያለውን የተቃውሞ ጋጋታ መቋቋም ያቃተው ብኣዴን በግል ተገናኝቶ እና ተደዋወሎ ከማውራት በስተቀር አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ድፍረቱን አግኝቶ የተናገረ አባል እንዳሌለ ሲገልጹ አቶ አያሌው ጎበዜ በግል ብቻ ይህ ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው ለፌዴራሉ መንግስት ሪፖርት ማድረጋቸውን ተናግረዋል::
ላለፉት 150 አመታት እና ከዛ በላይ በኢትዮጵያ እየተዘዋወረ አገር ያቀናውን ህዝብ ከቀየው ከሃገሩ ማፈናቀሉ እና የመኖር ዋስትና እንዲያጣ መደረጉ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት እኚሁ በኢሚግሬሽን ባለስልጣን ተመድበው የሚሰሩ የብኣዴን ምንጫችን የኢሕኣዴግን በህይወት የመቆየት ሃሳብ እሳት የጫረበት አደጋ ነው ብለዋል::አያይዘውም ህገመንግስታችን እና የመልካም አስተዳደራችን እያልን እየተጨነቅን የምንናገረውን በተግባል ለመተርጎም የደከምን ሲሉ አምርረው ውድቀታቸውን ሲያሳብቁ ድርጅታችንን ከውድቀት እናንሳ ያልነው ታዲያ ምኑ ላይ ነው ብለዋል::
የወጣትነት ጊዜያችንን በትግል ያሳለፍነው ለህዝቦች ነጻነት እና እኩልነት እንጂ ለእንደዚህ አይነት አደጋዎች አይደለም:: ገና ቀሪ የሚፈናቀሉ ወገኖች ከደቡብ ከምስራቅ እንዲሁም ከምእራብ ኢትዮጵያ የተደገሰላቸው ሲሆን አላስፈላጊ የዘረኝነት መርዝ በመርጨት አስደንጋጭ ፍርሃት የሚሰዱ ንግግሮችን በመናገር እና ከመካከላቸው አንዱን በመግደል….የሚሉ መጥፎ መመሪያዎች በመስጠት መሬቶችን ለውጪ ባለሃብቶች በሊስ የማከራየት እቅድ ተይዟል::
ይህንን እቅድ ተከትሎ ወደ 150 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንን ከየአከባቢው የማፈናቀል እቅድ ሲኖር ይህ እቅድ ደርግ በሰፈራ ፕሮግራም ያሰፈራቸውን ዜጎች ሳይቀር ያካተተ መሆኑን  እና በየከተማውም የህ አይነት እርምጃ እንዲወሰድ ክልሎች ተግተው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል:: ይህን ጉዳይ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው የብኣዴን በጉዳዩ ዙሪያ አለመነጋገሩ ግን አሳሳቢ እና ከፊታችን የተጋረጠ ትልቅ የመበታተን አደጋ አለ ሲሉ ገልጸዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ::
ማንኛችንም ብንሆን ዛሬ ስለእነዚህ ኢትዮጵያውያን ዝም ብንል ነገ ታሪክ ይፋረደናል።

No comments:

Post a Comment