Wednesday 24 April 2013

በወልድያ ከተማ በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በመላው አገሪቱ ከሚካሄደው የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በወልድያ ከተማ 10 ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአለፈው አርብ ጀምሮ መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በዛሬው እለትም እንዲሁ አንድ የሁለተኛ ደረጃ እንግሊዝኛ መምህር የሆኑት አቶ አብደላ እና የመደርሳ ትምህርት ቤት የእቃ ግምጃ ቤት ሀላፊ የሆኑ ግለሰቦች ተይዘው ታስረዋል።
መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለማፈን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቃውሞው አስተባባሪዎች ናቸው የሚላቸውን ሰዎች እየያዘ በማሰር ላይ ይገኛል። የተያዙት ተማሪዎች በአሁኑ ጊዜ በወልድያ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የዞኑን የፖሊስ አዛዥ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ፖሊሶቹ አሁንም ተጨማሪ ወጣቶችን ለማሰር እየተንቀሳቀሱ ነው

No comments:

Post a Comment