Wednesday 9 April 2014

አስደንጋጭ ዜና! ተጠንቀቁ! (ሹክሹክታ)


ወሬውን በዜና መልክ ለማቅረብ ተጨማሪ መረጃ ባለማግኘታችን፤ “ሹክሹክታ” ብለነዋል – ርዕሱ ላይ። አንዳንዴ በሹክሹክታ መልክ የምንሰማቸው ወሬዎች እውነት ሆነው ይገኛሉ፤ አንዳንዴም ሹክሹክታው ህዝብ ጆሮ ከመድረሱ በፊት ቶሎ እርምት ይደረግለታል። ዛሬም  በሹክሹክታ መልክ የተሰራጨውን ወሬ ወደናንታ እንደወረደ ከዚህ ቀጥሎ አቅርበነዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በኤች. አይ.ቪ በሽታ ህዝብን በመጨረስ እርዳታ ለማሰባሰብ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ኤች. አይ.ቪን ለመከላከል ተብሎ ለኢትዮጵያ መንግስት ከምእራባውያን የሚሰጠውን እርዳት በመቆሙ አዲስ አበባ የሚገኙ ከጤና ጣቢያ እስከ ሆስፒታል በተለይም ዘውዲቱ ሆስፒታል ኤች አይቪ መመርመሪያ ኪት በማጣታቸው ኤች. አይ.ቪ ያለባቸው እናቶች ፖዘቲቭ የሆነ ህጻን እየወለዱ ይገኛሉ፡፡ እርዳታው የሚቆምበት ምክንያት ኢትዮጵያ ኤች. አይ.ቪን በመከላከሉ ረገድ የተሳካላት በመሆኑ እና ምንም ታማሚ ስለሌለ እርዳታ ሰጪ ሀገራት ፊታቸውን ወደ ሌላ ሀገር በማዞራቸው እና በተለያዩ ጊዜ ለኢትዮጵያ የተሰጠው ገንዘብ በባለስልጣናት በመዘረፉ እንዲሁም ሂሳባቸውን በወቅቱ ማወራረድ ባለመቻላቸው እንደሆን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው እርዳታ ለጸረ ኤች. አይ.ቪ መድሃኒት መግዣ ብቻ ሲሆን ይህንንም በአግባቡ ገንዘቡን ባለመጠቀማቸው ምእራባውያን ርዳታውን ለማቆም ቢፈልጉም ከሰብዓዊነት አንጻር ብለው እንደሆነ የሚረዱት ተብላል፡፡ ባለፉት ዓመታት በርካታ ረጂ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የአፈጻጸም ስምምነት ለመፈራረም ቢመጡም አንዳንድ ባለስልጣናት ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ አቃቂር እያወጡ ተቋማቱን በማጉላላት አንፈራረምም በማለታቸው ምክንያት ረጂ ተቋማቱ ፊታቸውን ወደ ሌላ ሀገር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የሆኖ ሆኖ በኤች አይቪ ምክንያት የሚሞትና ስርጭቱ ቀንሷል በሚል ርዳታ ያጣው መንግስት የኤች አይቪ መመርመሪያ ኪቶችን በመደበቅ ለጤና ተቋማቱ ባለመስጠት ኤች. አይ.ቪ ሆን ተብሎ እንዲሰራጭ እና ትኩረት በማግኘት የኤች. አይ.ቪ ብር ለመብላት በሚል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት የኤች .አይ.ቪ መሳሪያዎች በጤና ተቋማቱ አይገኝም፡፡

No comments:

Post a Comment