Monday 18 March 2013

ድሮ የምናውቀው ኢህዴግ አሁን አለ የሚለኝ ካለ ተሳስቷል


ስጋት የገደለው የህወአት ሰራዊት አሁንም መሳሳቱን ይቀጥላል
TPLFይሄ ሌላ ነው፡፡ የዛሬው ሰልፍ መከልከል እንደተለመደው ከኢህአዴግ አምባገነናዊ እና አፋኝ አስተሳሰብ ጋር ብቻ ማዛመድ ይበቃል ብዪ አላስብም፡፡፡ድሮ የሚናውቀው ኢህዴግ አሁን አለ የሚለኝ ካለ ተሳስቷል፡፡ የድሮ ነገሩን እየመነዘረ የሚበላ ምንመጣ ምን ይከሰት ይሆን ብሎ ሌትተቀን በጥቃቕን ኮሽታ ሰላሙን ያጣ ድርጅት ሆኗል፡፡ የዛሬውም ክልከላ የዛ ውጤት ነው፡፡ትናንት አንድ የኢህዴግ ጽህፈት ቤት ሰብሳቢ ነኝ ከሚል ሰው ድርጅታችንን በአሁኑ ወቅት ሶስት በገሮች እንደሚያሰጉት ግልጽነው፡ 1 የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ፣፡2፣በኑሮ ውድነት ያኮረፉ ወገኖች፡ 3፣በሀይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች፡ የሚል ነበር፡፡ ትናንት እንደገለጽኩት፡ በዘንድሮ ምርጫ ከኢህዴግ ጋር የሚፎካከሩት ፓርቲዎች አቅም የላቸውም ብቻ ማለት በቂ አይደለም በተከፈተ ቀዳዳ ሁሉ እየገቡ በሳላምና በእድገታችን ላይ ችግር የሚፈጥሩ አይጠፉም ብሎን ነበር፡፡ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም በየትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ተሰባስበው በቀልድ ወይም ለጫወታ ብለው ቢጯጯሁ ሀላፊዎች መውጫ መግቢያ ነው የሚያጡት፡፡ ጮክክ ብላችሁ ለምን ሳቃችሁ ግቢውን ለምን ትረብሻላችሁ እየተባሉ ብዙ ተማሪዎች የተጠየቁበት ጊዜ አስታውሳለሁ፡፡ አንዳንዴ በኳስ ጫወታ ወቅት በተፈጠሩ የቲፎዞዎች ጩኀት እንኳን ሳይቀር ምንያህል መደናገጥ እነዳለ አስተውያለሁ፡፡ስለዚህ የዛረው ሰልፍ ለምን ተከለከለ የሚለው ነገር የሚነሳው እንደዚህ ካለው የኢህዴግ ቀልበቢስነት ጋር ተያይዞ ይመስለኛል፡፡ ኢህዴግ በአሁኑ ሰአት ትንሽኮስታም አይፈልግም፡፡በየቤቱ በረሀብና በሀዘን ተኮራምቶ ያለ ብሶተኛ ሁሉ ተንጋግቶብን ቢመጣስ ብሎ ያስባል፡፡ይፈራል፡፡ ግራዚያነኒን መቃወም ለኢህዴግ ህልውናዬ ብሎ ከሚያስበው ስልጣን አይበልጥም፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ በፍጹም ከስልጣኑ አይበልጥበትም፡፡ ለኢህአዴግ ማንም ምንም ከስልታን የሚበልጥ የለም፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ፈቀደ እንዲህ ገብተ እንዲ ወጣ የሚባል ምንም አይነት ሙገሳ ሌትተቀን እንቅልፍ አጥቶና እንቅል አሳጥቶ ካለለት ስልጣን አይበልጥም፡፡በአሁኑ ሰኣት ተነቃንቆ ያለ መንግስት ነው ትንሽ ነፋስ ከገባበት ወዴት እንደሚናድ ስለሚያውቀው እንኳን ሌላ ይቅርና ጠንከር ያለ ነፋስም ቢመጣ የሚያንቀጠቅጠው ይመስለኛል፡፡ ወቅቱ የፍረሀትና በጣም የስጋት ወቅት ነው ለኢህዴግ ፡፡ስለዚህ የዛሬው ሰልፍ በጣም በራስ አለመተማመን ምክንት የተፈጠረ፤ የድርጅቱ ውስጥዊ ማንነት አጉልቶ የሚያሳይ በመደናገጥና ዙሪያ ገባውን ማን ምን መጣብኝ፣እያለ ቀልብና ልብ ባጣ መንፈስና ሁኔታ ይለይለት ብሎ የወሰነው ውሳኔ ነው፡፡ እኔን በአሁኑ ሰኣት በጣም እያነደደኝ ያለው እንዲህ አይነቱን የኢህአዴግ ድክመትና ክፍተት መጠቀም የሚችለ፤ አቅም ያለው ተቃዋሚ መጥፋቱ ነው፡፡ ለሰማያዊ ፓርቲ ግን አሁንም አክብሮቴ ትልቅ ነው፡፡መሳምንት ውስጥ ሁለቱ ኢህዴግ እርቃኑ ያለ መሆኑን ማየት ለሚችል ሁሉ አሳይቷልና፡፡

No comments:

Post a Comment