Thursday 21 March 2013

የወያኔ ካድሬዎች ሳውዲ አረቢያ ላይ ለሁለተኛ ግዜ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድል ተደረጉ !!

የወያኔ ካድሬዎች ሳውዲ አረቢያ ላይ ለሁለተኛ ግዜ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድል ተደረጉ !!

በአባይ ግድብ ሸፋን ወያኔንን ማጠናከሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ለማስፈጸም ትላንት ጅዳ ላይ በአባሳደር ዘነበ ከበደ የተጠራው የዐማራ ልማት ማህበር ስብሰባ በተሰብሳቢው ተቃውሞ በውርደት ተበተነ ።
የጅዳው አምባሳደራችን አቶ ዘነበ ከበደ በለመዱት የመከፋፈል ዘይቤያቸው በዛሬው ምሽት የአማራ ክልል ተወላጆችን ሰብስበው ነበር::ይህ ጽሁፍ መዘጋጀት ከመጀመሩ የተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀው ስብሰባ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ባልተለየ መልኩ አምባሳደሩ የልማት ዲስኩራቸውን ሊያስተጋቡበት የታቀደ ነው::ስብሰባውን የጠሩበት ምክንያት ለትውውቅ እንደሆነ ከጠቆሙ በኋላ ከሰሞኑ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ዜጎቻችን በተመለከተ እየሆነ ያለው እንዳሳዘናቸው ሀገራችን ድሀ ባትሆን እንደዚህ ባልተዋረድን ብለው የአዞ እንባ አንብተዋል::ከሀገራችን ድህነት በላይ የኢህአዴግ ስልጣን ላይ መቀመጥ ችግራችን መሆኑን ዘንግተውት አይመስለንም::
ሰውየው ርቱዕ በሆነ አንደበታቸው ተሰብሳቢውን ባሰመሩለት ቀለበት እንዳጠመዱት ከገመቱ በኋላ ቤቱ ሀሳብ እንዲሰጥ እድሉን ሰጡ::የመጀመሪያውን የመናገር እድል ያገኘው ወጣት የሀይማኖት ሰው የአምባሳደሩን ድፎ ሊጥ አደረገባቸው::”….ክቡር አምባሳደር በርግጥ እርስዎ እንዳሉት ሀገር በልማት መበልጸጓ አስፈላጊነቱ አነጋጋሪ አይደለም::የልማቱም ሁኔታም እንዲሁ ነገር ግን ሰላማዊ ወገኖቻችን የእምነት ነፃነታቸው ተገፎ በግፍ እያሰቃየ ከሚገኘው ኢህአዴግ ጋር እንዴት ስለልማት ማሰብና ማውራት ይቻላል?እንዴት አድርገን ነው ወንድሞቻችን በየእስር ቤቱ እየማቀቁ እኛ ስለሀገር ብልጽግና ልንወያይ የምንደፍረው?…” ብሎ ሲናገር አምባሳደሩ አቋረጡት”…ይህ ነጥብ ከመወያያ አጀንዳችን ውጭ ነው::ስለዚህ ጉዳይ አንድ ራሱን የቻለ ስብሰባ ጠርተን ከተመረጡ የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች ግለሰቦች ለመወያየት እቅድ ተይዞለታል::”አቶ ዘነበ ማጠቃለላቸውን አይቶ ወጣቱ ቀጠለ”…በመሰረቱ እኔ ከአጀንዳው አልወጣሁም፥የምንወያየው ስለልማት እንደመሆኑ ልማት ከመወሳቱ መቅደም ስላለበት ሰላም ነው እያወራሁ ያለሁት፥አሁንም ማለት የምፈልገው ከልማት ቅድሚያ የሰላም መሰረት የሆነው የሙስሊሙ መብት ይከበር::”
ሌላ ተናጋሪ ተከተሉ”…አምባሳደራችን ስለልማት ያነሱትን በጥሞና አድምጠኖታል::ጥሩ ነው::ነገር ግን ከልማትም ከብልጽግናም ከሀገርም በፊት ኢስላም ይቀድማል!”ብለው መጨረሻውን ነገሯቸው::”…ኢነ ሰላቲ ወኑሱኪ ወመህያያ ወመማቲ ሊላሂ ረበል አለሚን!” አስከተሉ ጀግናው”…እኛ ሙስሊሞች የምንኖረው ለኢስላም ነው!ሁሉን እንቀበላለን ሁሉን እንሸከማለን፥በዲናችን የመጣብንን ግን በፍጹም አንታገስም!የሰኡዲ አረቢያ ነዋሪዎች በልማቱም በጦርነቱም ስንተባበር ኖረናል፥አሁን መንግስት በአይናችን በዲናችን መጥቷል::መሸነጋገል አያስፈልግም::ከሁሉ በፊት መብታችን ይከበር!”ብለው ተቀመጡ::
አዳራሹ ውስጥ ተበታትነው ከተቀመጡ ሆድ አደር ካድሬዎች ሁለቱ የተለየ የውይይት ሀሳብ አቅርበው አጀንዳ በማስቀየር አምባሳደሩ ትንፋሽ የሚሰበስቡበት ፋታ እንዲያገኙ ረዷቸው::ይህም አላዋጣ ሌላ ወንድም ተነስቶ እቅዳቸውን አኮላሸ!”…እኛ ሀገራችን በልጽጋ ልጆቻችን ወደ ሀገር ልከን እንዲኖሩልን እንፈልጋለን::ነገር ግን እንኳን ልጆቻችን ልንልክ መልእታችን ሊያደርሱ የወከልናቸው የሰላም አምባሳደሮቻችን አስራችሁብናል::በዚህ አይነት እንዴት ስለልማት ማውራት አይገባም::በቅድሚያ ሀገር ሰላም ስጡ!ልማቱ ከዚያ ወዲያ የምንነጋገርበት ይሆናል::”ብል ተቀመጠ::
“የተለየ ሀሳብ ከሌለ ይህን አጀንዳ አላስተናግድም”ብለው ላኮረፉት አምባሳደር አንድ ወንድም “የተለየ ጥያቄ አለኝ”አላቸው::”ጠይቅ”አሉት “ልማት የሚለማው ለማን ነው?”አላቸው ለአምባሳደሩ ፊታቸውን አጥቁረው ዝም አሉት”ለህዝብ ነው አይደል?!”ራሱ ቀጠለ”ታዲያ ለህዝብ ከልማት መቅደም ያለበት ሰላም እኮ ነው!”ድንቅ አባባል!
ለጉድ የላካቸው አምባሳደር ግራ ቀኙን በተማጽኖ እየቃኙ”…ቅድም እንዳስቀመጥኩላችሁ በዚህ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት በናንተው የተወከሉ የተወሰኑ የሀይማኖት አባቶችና ግለሰቦች የሚሳተፉበት ውይይት ይኖረናል::በዚሁ ወቅት ሀገር ስላለው ሁኔታ(የሙስሊሙ የመብት ጥያቄ ማለት አልደፈሩም) እንወያያለን::” በማለት ስብሰባውን አጠቃለው የሽንፈት ባርኔጣቸውን በማጥለቅ ከመድረኩ ተስፈንጥረው ወርደዋል!
ኢስላማዊ መብታችን ተከብሮ በሀገራችን እንደሙሉ ዜጋ እስከምንኖርባት የመጨረሻዋ ሰከንድ ሰላማዊ የመብት ትግላችን በአላህ እርዳታ ተጠናክሮ ይቀጥላል!ኢንሻ አላህ!

No comments:

Post a Comment