Sunday, 17 March 2013

ውድ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች ሁሉ


ውድ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች ሁሉ

ይህ አልባሌ የቅስቀሳ ወረቀት ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ መልዕክት ስለሆነ በጥሞና አንብባችሁ ተረዱ።

በሕዝብ ሃብትና ጉልበት የቆመችው ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ለኢትዮጵያ መንግሥት (ኢህአዲግ) ለማስረከብ የተወሰኑ ካህናት ከኤምባሲ ጋር ድርድር እያደረጉ ነው።
አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው የእግዚአብሔር ቤት የሆነውንና ሕዝብ በሃብቱና በጉልበት ገዝቶ ያቆመውን ቤተ ክርስቲያን በአብይ ጾም ሕዝብ እንዳይጸልይበት ከ11/03/2013
London Ethiopian Orthodox Church
ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን
ጃምሮ ከዘጉ በኋላ ለንደን ወደሚገኘው የኢትዮጵያ (የኢህአዲግ) ኤምባሲ በስውር በመሄድ በኤምባሲው አደራዳሪነት ቤተ ክርስቲያኑን የኢትዮጵያ (ኢህአዲግ) መንግሥት እንዲረከበው ለማድረግ ድርድር መጀመራቸውን በተጨባጭ ማረጋገጥ ተችሏል።
አባ ግርማ ከበደ፤ መሪ ጌታ አለማየሁ ደስታና ድቁናውን ያፈረሰው የቀድሞ ሊቀ ዲያቆን ዳዊት ገ/ዮሐንስ በመሆን ከአሁን በፊት የማርያም ቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በመዝረፉ፤ ከዛም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1998 ዓ/ም ቤተ ክርስቲያኗን ለኢህአዲግ አሳልፎ ለመስጠት ሲል አገልግሎቷን አቋርጣ እንድትዘጋ አድርጎ የነበረውና ከዚህም ሁሉ በላይ ደግሞ የኦርቶዶክስ እምነቱን ክዶ ጴንጤ በመሆን ጴጤ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ የኦርቶዶክስ እምነት የበሰበሰና የገማ ነው በማለት ምሥክርነት መሥጠቱ የሚታወቀው ሙሉጌታ አሥራትን በኤምባሲ ውስጥ በማግኘት ለተንኮል ሥራቸው እንዲተባበራቸው ማድረጋቸው ታውቋል።
ከሃገሩ ኢትዮጵያ ተሰድዶ በUK የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ባደረገው 40 ዓመታትን ያስቆጠር ድካምና ጥረት በእግዚአብሔር ተራዳኢነት ሃብትና ጉልበቱን አስተባብሮ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን በመግዛት ሁለተኛ ኢትዮጵያ የምትሆነውን ቤተ ክርስቲያን ካቆመ ብዙም ሳይቆይ ቤተ ክርስቲያኑን ከእጁ ነጥቀው አሳልፈው በመሥጠት መሾሚያና መሸለሚያ ለማድረግ የሚጥሩ አባ ግርማ ከበደን የመሰሉ ባላንጣዎች ተነሱበት።
ሕዝብ ሃብትና ጉልበቱን አስተባብሮ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን መግዛት ብቻ አይደለም የካህናቱን ደምወዝና አበልም ሆነ የቤተ ክርስቲያኑን ጥገናና እድሳት ጨምሮ እያንዳንዱን የቤተ ክርስቲያኑን የዕለት ተዕለት ወጪ ከኪሱ እያወጣ በሚሰጠው ገንዘብ ሸፍኖ የሚያኖረው ይኸው ሕዝብ ሆኖ ሳለ አባ ግርማ ከበደ በመጀመሪያ የምእመኑ ተወካይ የሆኑትን 4 የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በተጽዕኖ ሥራቸውን እንዲለቁ አደረጉ። ቀጥሎም የምእመኑ ተወካዮች በሌሉበት ተከታዮቻቸው የሆኑትን ከህናት በመያዝ ሕዝብ አንዳችም ነገር ሳያውቅና ምንም ዓይነት ፍንጭ ለሕዝብ ሳያሳዩ 15 ሕዝብ የመረጣቸውን የኮሚቴ አባላትና ቤተ ክርስቲያንን ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ የቤተ ክርስቲያን አባላትን ቅጥር ግቢው ውስጥ እንዳይደርሱ ብለው በደብዳቤ አባረሩ። ይህንን በመሰለ ሁኔታ ከቤተ ክርስቲያን ምንም አይነት ጥቅም ሳይፈልጉ የሚያገለግሉና ለእውነት የቆሙ የምእመናኑን ተወካዮች ካስወገዱ በኋላ እነሆ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው ብቻ የቤተ ክርስቲያኑ ሃብትና ንብረትም ሆነ የወደፊት እጣ ፋንታዋ ወሳኞቹና ፈላጭ ቆራጮቹ እኛ ነን ብለው በመቅረብ ቤተ ክርስቲያኗን ከነ ንብረቷ ለኢህአዲግ መንግሥት በማስረከብ በምትኩ ሹመትና ሽልማት ይሰጠን በማለት ከኤምባሲ ጋር በመደራደር ላይ ይገኛሉ።
ይህ ለማመን የሚያዳግት ሕዝብንም ሆነ እግዚአብሔርን የተዳፈረ ተግባር በሕዝብ ላይ ሲፈጸም የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤትና ባለንብረት የሆነው ሕዝብም ሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዝም ብሎ ስለማያይ አጠቃላይ ሕዝቡ በአንድነት ተንቀሳቅሶ ሕዝብን ከነ ቤተ ክርስቲያኑ ለመሸጥ በማስማማት ላይ የሚገኙትን የአባ ግርማ ከበደና የተከታዮቻቸውን ደባ በማስቆም የጥፋት ዓላማቸውን ሊያከሽፍባቸው ይገባል።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ሕዝብ በፈራ ተባና በመዘናጋት ለአባ ግርማና ተከታዮቻቸው ጊዜ ከሰጣቸው “ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆሞ ማውረድ ያቅታል” ነውና ዓይናችን እያየና ጆሮአችን እየሰማ ቤተ ክርስቲያን ከሕዝብ እጅ ወጥታ የማትሄድበት ምክንያት ስለሌለ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ከምንግዜውም በበለጠ በመነሳት ቤተ ክርስቲያንህን ለመከላከልና ለማዳን ከአስተባባሪ ኮሚቴው በሚሰጥህ መረጃና መመሪያ መሠረት በአስፈላጊው ቦታ ሁሉ በመገኘት የሚጠበቅብህን ሁሉ እንድታደርግ በማርያም ስም ጥሪአችንን እናስተላልፋለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አስተባባሪ ኮሚቴው

No comments:

Post a Comment