የካቲት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ” በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የአማራ ተዋላጆች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ መታዘዙ፣ ችግሩን በእጅጉ ውስብስብ አድርጎታል።
በደቡብ ክልል በጉርዳ ፈርዳ ወረዳ የተጀመረው መፈናቀል ሳይቆም፣ በባሌ፣ በአፋርና በሶማሊ ክልሎች ተመሳሳይ መመሪያዎች እየተላለፉ መሆኑን የገለጡት ምክትል ሊቀመንበሩ ፣ ተፈናቃዮች ለሞት መዳረጋቸውን ገልጸዋል
አቶ ወንድማገኝ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የህወሀት የቆየ የዘር ፖሊሲ መሆኑን ገልዋል
” መኢአድ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ ችግሩን ለማስቆም ምን የሚወስደው እርምጃ አለ ተብለው የተጠየቁት አቶ ወንድማገኝ፣ ችግሩ የሚቆመው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሲተባበርና ድርጅቶችም በጋራ ሲቆሙ መሆኑን ገልጸው፣ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማካሄድ እቅድ መኖሩንም ተናግረዋል
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በአማራ ክለል ዋና ከተማ ባህርዳር የደረሱ የአማራ ተወላጆች የክልሉ ባለስልጣናት መፍትሄ እንዲሰጡዋቸው ቢጠይቁም ፣ ባለስልጣናቱ ጉዳዩ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉዳይ በመሆኑ እንደማያገባቸው መግለጻቸውን ተፈናቃዮች ለኢሳት መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment