! … በህወሓት መሪዎች ምርጫ የትግራይ ህዝብ ኣሳዘነ …!
ኣንድበቅድመ ጉባኤ ስብሰባቸው፣ ሁለቱም ቡድኖች ልዩነታቸውን ለማጥበብ ‘የመተካካት መርህ’ እንደሚተገብሩ ቃል ገብተው ነበር። ከሁለቱም ቡድኖች የተወሰኑ እንደሚቀነሱ (የቀሩ ደግሞ ስልጣን እንደ ሚከፋፈሉ) ስምምነት ነበር። ሸምጋዮቹ ኣዲሱ ለገሰ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝና ቴድሮስ ኣድሓኖም (በረከት ስምዖንም እጅ ነበረው) የነ ኣባይ ወልዱ ኣደረጃጀት ስለተረዱ በነ ኣርከበ ቡድን ጫና ፈጥረዋል።
የሸምጋዮቹ ኣቋም ‘ህወሓት መከፋፈል የለበትም፤ ህወሓት ከተዳከመ ኢህኣዴግ ኣቅሙ ይዳከማል፣ ስለዚ compromise ማድረግ ኣለባቹ’ የሚል ነበር። ግዝያዊ ሽምግልናው ሰራና ወደ ጉባኤ ተገባ።
ሁለት
የነ ኣባይ ወልዱ ቡድን ራሱ የመለመላቸው ጉባኤተኞች (በራስ ኣለመተማመን ይመስላል) በስብሰባው 1ለ5 ኣደረጃጀት (የድርጅት ስራ) ተግባራዊ በማድረግ እነሆ የነ ኣርከበ ቡድን መምታት ችለዋል። ዕቅዱ የነ ኣርከበ ቡድን ሙሉ በሙሉ ከስራ ኣስፈፃሚነት ማስወገድ ነበር።
በጉባኤው ‘የመለስ ታሪክና ራእይ’ የኣንድ ቀን ሙሉ ኣጀንዳ ነበር። ‘የመለስ ራእይ’ ተብለው የሚነገሩ ፖሊሲና ስትራተጂዎች በቡድኖቹ ልዩነት ፈጥረው ሲያከራክሩ ውለዋል። ኣንዱ ቡድን ‘የመለስ ራእይ ሳይከለስ ሳይበረዝ መተግበር ኣለበት’ ሲል (እነ ኣባይና ኣዜብ) ሌላኛው ደግሞ ‘መለስ የራሱ ሚና ተጫውተዋል፣ ሁሉም የህወሓት ታሪክ ለመለስ መስጠት ግን የሰማእታት ሚና ማራከስ ይሆንብናል’ ተብሏል (የነ ኣርከበ ቡድን)።
ኣርከበ ‘መለስን ኣታካብዱት የራሳችሁን ታሪክ ስሩ’ (ቃል በቃል ኣይደለም) የሚል ሓሳብ ሲያንፀባርቅ፣ ስዩም መስፍን ደግሞ ‘መለስ ጥሩ ነገር ሰርተዋል ግን በዲፕሎማሲ እሱ የሰራውን ካለ ‘እስቲ የሰራቸውን ነገሮች ዘርዝሩልኝ’ ዓይነት ኣንድምታ ያለው ሓሳብ ሲሰጥ የመለስን ሚና ኣታጋንኑት ለማለት ነበር። ነገር ግን የስዩምን ሓሳብ በኢቲቪና ሬድዮ ፋና ሲቀርብ መለስን ያሞካሸበት ሓሳብ ኣስመስለው እንዳቀረቡት ስምቻለሁ።
ባጠቃላይ ልዩነታቸው ግልፅ ነበር። የነ ኣርከበ ቡድን በነ ኣባይ ወልዱ የተደራጀ 1ለ5 ታክቲክ ተረድተውታል። እንደሚሸነፉ ገብቷቸዋል። ተመካከሩ። በምርጫ ተሸንፈዋል ከሚባሉ ራሳቸው እንድያገሉ (እንዲቀነሱ) ተገደዱ። ጥሩ ማምለጫ ኣገኙ፤ ‘ተገንጥለው ወጡ’ ወይ ምርጫ ተሸነፉ ከሚባሉ ‘በፍቃደኝነት ተሰናበቱ’ ቢባሉ ይሻላል።
ከተቀነሱ ዘጠኝ ሰዎች ሰባቱ የነ ኣርከበ ናቸው። ኣንዱ የነ ኣባይ ወልዱ ሲሆን ኣንድ ደግሞ ከመሃል ሰፋሪዎች ነው። ጸጋይ በርሀ እንዲቀነስ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ንጉሰ ገበረ ተቀነሰ። ከተመረጡት 45 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ዘጠኙ ሲቪል እንደሆኑ ከመንግስት ሚድያ ሰምተናል። ዘጠኝ ከኣርባ ኣምስት ትንሽ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ እነዚህ ሲቪሎች የኣለቆቻቸው ታማኝ ኣገልጋዮች የነበሩ ናቸው። በራሳቸው መቆም የሚችሉ ኣይደልም።
በስራ ኣስፈፃሚ ኮሚቴ ኣባልነት ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ እነ ኣባይ ወልዱ ኣሸናፊ ናቸው። ስምንት ለ ኣንድ (ቴድሮስ መሃል ሰፋሪ ቢሆንም) በሆነ ውጤት ኣሸንፈዋል። የነ ኣርከበ ቡድን ኣንድ ነጥብ (ዶ/ር ደብረፅዮን ብቻ) ኣለው። የነ ኣባይ ቡድን ኣባዲ ዘሞና ፀጋይ በርሀ (ሁለቱም የነ ኣርከበ ቡድን ነበሩ) ከስራ ኣስፈፃሚነት በማባረር ኣለም ገብረዋህድ (የኣባይ ወልዱ የቅርብ ወዳጅ)ና ገብረመስቀል ታረቀ ኣስገብተዋል። መለስ ዜናዊ ደግሞ በትርፉ ኪዳነማርያም (የኣባይ ወልዱ ሚስት የነበረች ወይ የሆነች) ተይዘዋል።
የትርፉ ኪዳነማርያም ፖሊትብሮ ኣባል መሆን የነ ኣባይ ወልዱ ቡድን ማሸነፉ ማረጋገጫ ነው የሚሉ ኣስተያየት ሰጪዎች ኣሉ። ‘ትርፉ የፖሊት ቢሮ ኣባል ሆነች’ ሲባል ማን ትዝ እንዳለኝ ታውቃላቹ??? ተወልደ ወልደማርያም። ይህንን ሲሰማ ብፃይ ተወልደ ምን ብሎ ይሆን (ኣጠገቡ በነበርኩ!)?
ሦስት
ባሰባሰብኩት የህዝብ ኣስተያየት መሰረት በህወሓት ጉባኤና ወጤቱ የትግራይ ህዝብ (ኣብዛኛው የፓርቲው ኣባል ጨምሮ) በጣም ኣዝነዋል። በተመረጡ ሰዎች ተስፋ የለውም። ህዝቡ ኣዳዲስ የህወሓት ኣመራሮች በመጠባበቅ ላይ ነበር። የፓርቲው ሊቀመንበርነቱን ይዞ የቀጠለው ኣባይ ወልዱና ምክትሉ እንደሆነ የሚቆየው ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ይቀየራሉ (በሌሎች ወጣት ሙሁራን ይተካሉ ብሎ) ሲጠባበቅ ነበር።
የትርፉ ኪዳነማርያም ፖሊት ቢሮ ኣባል መሆን ብዙ ሰው ኣስገርሟል። ኣባይ ወልዱና ኣዜብ መስፍንም ኣልተጠበቁም። ቴድሮስ ሓጎስ ስልጣኑ ይለቃል የሚል ግምት ነበር። ኣባይ ፀሃየና ኣርከበ ዕቁባይ ለፓርቲው ሊቀመንበርነት ታስበው ነበር (በህዝቡ)። ባጠቃላይ የፖሊት ቢሮ ኣባላት ማንነት ኣስጨናቂ ሁነዋል። ‘እነዚህ ሰዎች መርተው የት ያደርሱናል?’ በሚል የፓርቲው ኣባላት ግራ ተጋብተዋል። በጉባኤው የተሳተፉ ኣባላት ጭምር በድራማው ተገርመዋል።
ህዝቡን በጣም ተስፋ ያስቆረጠው ጉዳይ ‘መተካካት’ ነው። ‘የመተካካት ዕቅድ’ በህወሓቶች ከሽፈዋል ማለት ይቻላል። የመተካካት መንፈስ ፈፅሞ ኣልታየም። ከጉባኤው በፊት በነበረ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ስብሰባ የተስማሙበት ነጥብ ዋነኛው ‘መተካካት’ እንደሚኖር ነበር። ኣሁን የታየው ግን ‘መተካካት’ ሳይሆን የተወሰኑ ሰዎች የመቀያየር ሁኔታ ብቻ ነው።
እነዚህ የተቀያየሩ ሰዎች በምን መስፈርት ነው? በዕድሜ? በስልጣን ሰኔሪቲ? በብቃት? NO. በሁሉም ኣይደለም። በፖለቲካ ልዩነትና በዝምድና ነው። ይሄን የሚያሳየን ህወሓት ተተኪ ወጣቶች ማበራታታት ኣይፈልግም። የመሪዎቻችን ዓላማ በስልጣን መቆየት መሆኑ ግልፅ ሁነዋል። በህወሓት ውስጥ ጥሩ ሓሳብ የያዘ ወጣት ተቀባይነት ኣይኖረውም። በህወሓት ውስጥ ሁነው ለለውጥ መታገል ውጤት ሊያመጣ ኣይችልም።
ደግሞ የትእምት ሃብት ለማን ትተው ስልጣን ሊለቁ??? መተካካት፣ ስልጣን መልቀቅ ኣይታሰብም። በፓርቲው ኣባላት ጥያቄ (በጉባኤ) ቀርቶ በህዝብ ጥያቄም (በምርጫ) ከስልጣን ለመውረድ ፍቃደኞች ኣይሆኑም። የሚያስገደድ ሁኔታ ካላጋጠማቸው በቀር። ዋናው መፍትሔ የሚሆነው የህዝቡ የፖለቲካ ንቃተ-ህልና ከፍ እንዲል ማድረግ ነው።
It is so!!!
No comments:
Post a Comment