አዲስ ቤተመንግስት ሊገነባ ነው ተባለ
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል ግቢ ውስጥ አዲስ ቤተመንግሥት ሊገነባ መሆኑን ምንጮችን በመጥቀስ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል።
የስብሰባ ማዕከል ያለበት ቦታ ለቤተመንግሥቱ ግንባታ የተመረጠው፣ ቦታው ከመሐል ከተማ ወጣ በማለቱ፣ ዙሪያ ገባው ለደህንነት ምቹ ስለሆነ፣ መንግሥት ከምኒሊክ ቤተመንግሥት ወጥቶ የራሱን አዲስ ታሪክ ለመስራት በመፈለጉ ነው ተብሎአል።
በስብሰባ ማዕከል ዙሪያ የሚገኙ የድሃ መኖሪያ ቤቶችና ተቋማት በቅርቡ በልማት ሥም እንደሚነሱ እንዲሁም ህንፃ ለመስራት በዝግጅት ላይ የነበሩ ሰዎችም ህንጻ እንዳይሰሩ መከልከላቸው ታውቋል፡፡
ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በምኒሊክ ቤተመንግሥት ውስጥ ልዩ የመኖሪያ ቤት በከፍተኛ ገንዘብ በማስገንባት ላይ እንደነበሩ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment