“እያንጓለለ” የአዜብ ኮሜዲ
ከቴድሮስ ሐይሌ (TADYHA@GMAIL.COM)
“መለስ ወደዚህ ዓለም ጭንቅላቱን ይዞ ለዝህች አገር ለዚህች ምድር የሚጠቅም ሃሰብ አመነጨ ለግሌ ለቤተሰቦቼ ሳይል አንድ ቀን ለራሱ ሳይሆን መንግስት በሚሰጠው ደመወዝ በፔሮል የሚከፈል መሪ በዓለም ላይ መለስ ብቻ ነው።” አዜብ መስፍን
የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ዝናው ገኖ የነበረው የቀድሞው መንግስት ተራ ወታደር የነበረው ታምራት ገለታ የተባለ አባይ ጠንቋይ ሴት ወንዱን መሃይም ምሁሩን ብቻ ከተራው ዜጋ እስከዘመኑ ባለስልጣናት ሲያሰግድ ለቃልቻ ጣዖቱ ግብር ሲያስገባ የበረታ መንፈሳዊ ሃይል የተቀዳጀ እንደሆነ በአንድ ግዜ በተለያየ ቦታ እንደሚገለጽ ለተማጠነው ሃብት ጤና ትዳር እንደሚሰጥ በመስበክ ብዙ የዋሃንን አሳምኖ እስከ መመለክ ደርሶ የእግሩን እጣቢ እነደ ጠበል ሲያስጠጣ የነሆለሉለትን ሃብታሞች መድሃኒት በማጠጣት ገድሎ ሃብታቸውን የወረሰበትን የዩንቨርስቲ ምሩቃንን ሳየቀር ሳር እያስጎዘጎዘ ቡና እያስወቀጠ ይካደም የነበረበትን ሞራል አልባ የእውነት ድራማ በፍርድ መቋጫ እስካገኘበት ድረስ ያለውን የግለሰቡን የአጭበርባሪ ጥንቆላ ተውኔት ያንድ ወቅት መነጋገሪ ሆኖ የድርጊቱ ሰለባዎችና ራሱ ወንጀል ፈጻሚው ጭምር ለፖሊስ ይሰጡ የነበረውን መረጃ በየፌስቡኩና በዩትዩብ ተለቆ ጉድ ሲባል ነበር። ይህ አባይ ጠንቋይ ታዲያ በማጭበርበር ባካበተው ሃብቱ የገነባቸውን የቢዝነስ ተቋማት የላቡ ውጤት መሆኑንና ህብረተሰቡን በመርዳት ያበረከተው በጎ አስተዋጾ የማይገባ ስም እንደተሰጠው ለመከራከር ያቀረበው እፍረት አልባ ሙግት ተገቢ በሆነ ቅጣት መደምደሙን አስተውለናል።
ይህ አባይ ጠንቋይ ቢታሰርም አምሳያዎቹ የፖለቲካ ሟርትና የሙት ራዕይ አስፈጻሚ ተንበርካኪ የወያኔ ሎሌዎች መለስ የተባለ ጣዖት አቁመው ሲበሉም ሲጠጡም ስሙን ካለነሱት የማይሆንላቸው እንደ ሃይለማርያም ደሳለኝ ያለ ነሆለል ወንጌላዊ ነኝ የሚል ወንጀለኛ ከጠንቋዩ ካዳሚዎች በባሰ አገላለጽ መንገድና እውነት መለስ ነው ሲል የሬሳ አምልኮውን የገለጠበት አጋጣሚ የዘርና መንደር ደዌ አይነልቦናቸውን የጋረዳቸው ካህን ነን ባይ ባለጥምጥሞች ሳይቀር ቃላት ያረከሱበትን ቅጥፈታዊ ሙገሳዎችንና የተጋነኑ በተረት የተሞሉ ከንቱ ውዳሴያቸውን እንደ ቃልቻው ታሪክ በመገረም ስንከታተለው የከረምንው ቴያትር ገና ትዝታው ሳይጠፋ ወይዘሮ አዜብ ሰሞኑን ባህርዳር ላይ የዘላበደችው የሃገሬ ሰው የአቡዬን መገበሪያ የበላ ያስለፈልፈዋል እንዲሉ ሳትጠየቅ ባሏ በድህነት ኖሮ በድህነት ማለፉን ቅንድቧ ሰበር እንኳ ሳይል ተጨፈኑ ላሞኛችሁ መሐይማዊ ትንተናዋ ብዕሬን እንዳነሳና ከነባለቤቷ ሲፈጽሙ የቆዩትን ወንጀል ለማስታወስ እንድገደድ አድርጎኛል ታዲያም እንዲሁ በደረቁ እንዳይሆን ያ ህዝብ አዳም ያሸረግድለት የነበረ ቃልቻ ሴራው ከሽፎ ዘብጥያ ከወረደ በኋላ ኮሜድያኑ አዝናኝና አስተማሪ
የሆነውን እያንጓለለ በሚል የተሰራው ክሊፕ ከቁመቱ በላይና በሌለው ራዕይ በወያኔዎች ዘንድ ተመላኪ ከሆነው መለስ ዜናዊ ጋር በአጭበርባሪነት ይሁን በጣዖትነት ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳላቸው ይህ በኩምክና የታጀበች ሙዚቃ እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ
ልባዊ ወዳጄ የሆነው የቀድሞው የሕወሃት ታጋይ የዛሬው የዲሞክራሲ አክቲቪስት አቶ መኮንን ዘለለው የዛሬዋን ስም የለሽ ንግስት አንዳንዶች የዘረፋ ሴትወይዘሮ ሲሉ የሚጠሯት የሰው በላውና የዘረኛው መለዝ ዜናዊ ባለቤት አዜብ ጎላ (አዜብ መስፍን) ወልቃይት ከሚገኝ አንድ መሸታ ቤት መልምሎ ለትግል ሲያሰልፋት ያቺ የገጠር ኮረዳ ዛሬ በሚለዮኖች ህልውና የምትቀልድ መከራ የማይመክራን ልበ ድፍን ትሆናለች ብሎ የገመተም ሆነ ያሰበ አልነበረም። ምግብ አጥተው ለሞት ከሚዳረጉ ህጻናት አፍ በበሽታ ከሚማቅቀው ደሃ ወገናችን ላይ በባሏ አመራር ከነጭፍሮቿ ያለ ይልኙታ ሲዘርፉ የኖሩት የህዝብ ሃብት የውጭ ሃገራትን ባንኮች ማጨናነቁን ሪፖርቶች ይፋ በሚያደርጉበት ወቅት ላይ 11 ቢለዮነ ዶላር መዘረፉንና በህገወጥ መንገድ ከሃገር መውጣቱ በአስተማማኝ መረጃ ይፋ በተደረገበት ሁኔታ ላይ ባሌ በችግር ነው የኖረው መንግስት ከሚከፍለው ውጪ ቤሳ ቤስቲን የሌለው ሃቀኞች ነን ስትል ጆሮ አልሰማ አይል ሰማናት
ባለፉት ሃያሁለት አመታት ከስሙኒ ማራገቢያ ሻጭነት ተነስተው ዛሬ ቢጠሯቸው የማይሰሙ ሚሊየነሮች በሆኑበት ታጋይ ከበርቴዎች ልማታዊ ዘራፊዎች ከራሳአቸው አልፈው ተርፈው ለቅምጦቻቸው ሳይቀር የቅንጦት መኪና ስጦታ የሚያበረክቱበት የወታደራዊ አዛዠነት ከቁመታቸው በላይ የታደላቸው የትግሬው ነጻ አውጪ አባሎች የሚሰሩት ቪላ ኢንቨስት የሚያደርጉት ገንዘብ ከደደቢት ይዘው የመጡት ነው ካልተባለ በስተቀር አለም የሚያውቃቸው አዲስ አበባ ሲገቡ ከራሳቸው ተባይ ከገላቸው እድፍና ከእግራቸው ንቃቃት ውጪ የረባ ኩባያ እንኳ ያልነበራቸው ወያኔዎች የዛሬዎቹ ሻኛ ቁርሱ ወርቅ ትራሱ ለመሆን የበቁት ከደሃው ኢትዮጽያዊ አፍ ነጥቀው ለመሆኑ ማስረጃ ለመደርደር መሞከሩ ለቀባሪው ማርዳት ነው።እነዚህ የወያኔ ጉዶች ቁርበት ላይ ተወልደው ቁረበት ላይ እንዳላደጉ ዘርፈው ከሚያካብቱት ሃብት በተጨማሪ በቀል ባጫጨው አይምሮአቸው ለሚቀመጡበት የቢሮ ወንበርና ጠረጤዛ ሳየቀር በውድ ዋጋ በውጭ ምንዛሪ እንዲገዛ በማድረግ የሚያወድሙት ሃብት ስፍር ቁጥር የለውም። በችግር የሚለበለበው መላው ህዝባችን የ21 አመት የወያኔ ጉዞ የት እንዳደረሰው አርቲስቶቹ በሙዚቃ በተቀናበረ ኮሜዲ ያቀረቡት የፈጠራ ስራ ሁኔታውን በሚገባ ይገልጸዋል ብዬ ስለገመትኩ ሌላም የኮሜዲ ሙዚቃ ተጋበዙ።
የአዜብና የባሏ ጭፍራዎች እንዲህ በቅንጦት ካበዱ ዋናዎቹ ምን ሊኖራቸው እንደሚችል ለመገመት ጠንቋይ መሆንን አይጠይቅም። በአጭሩ የሌቦች አውራና የዘራፊዎች አዛዠ በግፍ የሰበሰበውን ሳይበላ የተጠራው መለስ ከምድራዊ ፍርድ ባያመልጥም በጥይት ያስፈጃቸው ብቻ ሳይሆን በረሃብ ከጠወለገች እናታቸው ደረቅ ጡት እየማጉ በሞት የተነጠቁት ጨቅላ ህጻናት ሳይቀር በአረመኔነቱ ለፍርድ ከጌታ ዘንድ እንደሚያቀርቡት እሙን ነው። የትላንቷ ኮማሪት የዛሬዎ ኤፈርት የተባለው የኢትዮጽያውያንን ደም የሚመጥ ሃገር ገዳይ ሞኖፖሊስት የቢዝነስ ተቋም ሃገሪቷ የሌላትን የገንዘብ አቅም ያካበተ ተጠያቂነቱ ማንና ለምን እንደሆነ የማይታወቅ ብድር ወስዶ የማይመልስ ሂሳቡን እንኳ ኦዲት የማያስደርግ በባልና ሚስት አመራር ይዘወር የነበረው ይህ ተቋም የማን ሆነና ነው መለስ የፔሮል ደመወዝ ተከፋይና የገንዘብ ደሃ የሚሆነው አዜብ መስፍን ለማያቅሽ ታጠኝ ዘራፊነታችሁን አለም ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ለመሆኑ ትንሿ ማስረጃ ልጃችሁ እንግሊዝ ሃገር የምትማርበት ክፍያ ከዛች ከባሎ ደመወዝ ላይ ተቆርጦ ነው! ወይስ ልጆቻችሁ እንደ ጓድ መንግስቱ ሃይለማርያም ልጆች በሃገር ቤት እንደ ሌላው ዜጋ የመንግስት ትምህርት ቤት ነው የሚማሩት እሜዬቴ በካድሬነቶ ዘመን ትንሽ እንኳ ሂሳብ አልተማሩም እንዴ ቀጣፊ።
ወይዘሮ አዜብ ሌላው በዚህ ቅብጥርጥሯ ካነሳችሁ ውስጥ የመለስ ሃብት ጭንቅላቱ ነው ለዚህች ምድር ታላቅ ሃሳብ ያመጠቀ ፈላስፋ አድርገዋለች ለመሆኑ መለስ ለጥቅስ እንኳ የሚበቃ እውቀት ትቷል ወይ በየትኛው መጽሃፉ ነው ችሎታው የታየው በየትኛውስ ነጻ መድረክ ላይ ተገኝቶ ተከራክሮ ችሎታውነ ያስመሰከረው መቼመ ሴትየዋ ከዛ ከከብት በረት ካልተሻለው ፓርላማ ላይ ያለከልካይ ይቀባጥር የነበረውን ባዶ የቃላት ጋጋት በሚያቀርበው ዲስኩር እጁ እስኪግል እንዲያጨበጭብ መመሪያ የሚሰጠው ካድሬ ሁካታ ካልጠቀሰች በስተቀር ሌላ ብትጠየቅ የምትሰጠው መልስ አይኖርም። መለስ በዘመኑ ከጻፋቸው ውስጥ ህዝብ ዘንደ የደረሰው የሃገር ልዑዓላዊነትን አሳልፎ የሰጠበት የሻብያ መወድስ የተባለለት ኤርትራ
ከየት ወዴት ብሎ የደረሰው ቀሽም የክህደት ዶሴ ቀለሙ ሳይደርቅ ተሰብስቦ መቃጠሉ ይታወቃል ከዛ በተረፈ ይህ ነው የሚባል በሎጂክና በዲያሌቲክስ የዳበረ የራሱ ፈጠራ ውጤት ሳያኖር ያለፈ ቢሆንም ምንአልባት በብልጣብልጥነትና ውሸትን አጣፍጦ በማቅረብ በመልቲነቱ በመሪነት ደረጃ በዓለም ውስጥ የሚወዳደረው የሌለ የክብረ ወሰን ባለቤት ያደርገዋል።
ለሃገሩ ቀን ከሌት ሲደክም የኖረ እንደነበርም ደስኩራለች፤ ለመሆኑ መለስ የትኛውን በጎ ነገር ነው ለሃገር ያበረከተው፤ ዲሞክራሲን መልካም አስተዳደርን ፤እኩልነትን፤ ልማትን መለስ ለሃገራችን አበርክቷልን መልሱ በተቃራኒው ነው እድሜ ለመለሰ አመራር አንድነታችን ተዳክሞ ቁርሾ በህዘቦች ዘንድ እንዲኖር ተደርጓል፤ ህዝባችን በሃገር የመኖር የመስራት የመማርና ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብት ተነፍጎ ሃገር ጥሎ በመሰደድ የዓለም ክብረወሰን ጨብጧል፤ መለስ በዋሾነቱ በጫት ቃሚነቱና በትንባሆ አጫሽነቱ ጭምር ለትውልዱ መልካም አርዓያ በመሆን ፋንታ የጥፋት ተምሳሌት ሆኖ ያለፈ ምግባረ ብልሹ ነበር። ሌላው መለስ በአገዛዘ ዘመኑ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም ጭምር ኢትዮጽያን በማድማት ትግራይን ለማበልጸግ እቅድ ነድፎ ዘረኝነት ለትውልድ እንዲተላለፍ ጭምር ያደረ እኩይ ግለሰብ ነበር።

ውሃን ድንጋይ ያናግረዋል እንዲሉ ሴትየዋ እንደ አለት ጠጥሮ ከተጣባት ሃሰተኝነት አልላቀቅ ብላ በሞተው ሰውዬ ላይ እርግማን እንድናበዛ አደረገችን እዚህ ላይ ሴትዮይቱም ሆነ ሌላው ወገን ሊያውቀው የሚገባ በደርግ ዘመን ጠቅላይ ሚንስትር የነበረው በመልከ መልካምነቱ የሚወሳው ፍቅረስላሴ ወግደረስ በግዜው አበላል እንደ ደርግ አባል አለባበስ እንደወግደረስ ተብሎ ይነገርለት የነበረው ይህ ከፍተኛ ባለስልጣን ወያኔ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ከዚህ ግለሰብ ካዝና የተገኘው ገንዘብ በጣም ትንሽ በመሆኑ ለራሳአቸው ለወያኔዎቹ አስደንግጦዓቸው እንደነበር በግዜው ከተለያዩ ጽሁፎች አንብቤያለሁ ፤ አዎን በደረጉ ግዜ የነበረ ባለስልጣን ግፋ ቢል ከጮማና ከውስኪ የማያልፍ በዘረፋ ያልተጠመደ በአብዛኛው በደመወዙ የሚተዳደር እንደነበር ከማንም በላይ ያረጋገጡት ራሳቸው ወያኔዎች ቢሆኑም ከላይ እንደተባለው የወያኔው ባለማሎች የሚያነቀሳቅሱተ የገንዘበ መጠን ለቁጥር የሚታክት ቢሆንም እንዲህ ጥቂቶች በቅንጦት በሚቀብጡባት ሃገር የእለት ጉርስ የአመት ልብስ አጥቶ በየበረንዳው ፍግም ብሎ ከሚያድረው አውታታ ጀምሮ ዛሬ ዛሬ ቤተሰብ ልጆቹን መመገብ ተስኖት ህጻናት በየትምህርት ቤታቸው ጠኔ ሲጥላቸው መስማት የተለመደበት ቁራሽ እንጀራ ማግኘት የከበደበት የመከራ ዘመን ለመድረሳችን አንዱና ዋናው ምክንያት መለስና ቡድኑ ያለቅጥ በዘረፋ መጠመዳቸውና ዘረኛና አድሏዊ በሆነው የልማትና የዕድገት ፖሊሲያቸው ከትግራይ ክልል በስተቀር መላዋ ኢትዮጽያ የሰቆቃ ቀጠና እንድትሆን በማደረጋቸው ነው። አዜብ መስፍን የባሏን ፍሬ አልባ ተረት ትቀባጥር በነበረበት የባሕርዳር ከተማ በትንሽ ኪሎሜትር እርቀት ላይ በዘራቸው ምክንያት ውጡልን ተብለው ለዘመናት ከኖሩበት ቅያቸው ሃብት ንብረታቸው ተቀምተው የወገን ያለህ የሚሉበት ሁኔታ መለስ ዘርቶት የሄደው አረም ሃገር ሊያጠፋ ዳርዳር ያለበት ሁኔት ተፋፍሞ በሚገኝበት ሁኔታ ላይ እንኳ አለመንቃቷ የሴትዮይቱን ለከት የለሽ እብሪት ከማሳየት ባሻገር ገና ሃገሪቱ በዚሁ ሙት መንፈስ ብዙ አበሳ እንደሚመጣባት ጠቋሚ ሆኖ ይታየኛል።
ኢትዮጽያን እግዚያብሄር ይባርክ አሜን !
ትንሳዔዋን ያሰየን!!
አሜን!!!

No comments:
Post a Comment